ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
Ir al canal en Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
Mostrar más602
Suscriptores
-124 horas
-87 días
-1830 días
Archivo de publicaciones
🌹🌹🌹🌹✨️✨️✨️✨️🌹🌹🌹🌹
ማሕሌተ ጽጌ በግራር ደብረ ዓባይ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ጥቅምት 04/02 / 2016 ዓ.ም
ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
✨✨✨✨✨✨✨
▭▭▭ ◎⃝ ◎⃝ ⃟ ◎⃝ ◎⃝ ▭▭▭
🔎
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
የሳምንት ሰው ይበለን
✨️✨️✨️✨️🌹🌹🌹🌹✨✨✨✨
🌹🌹🌹🌹✨️✨️✨️✨️🌹🌹🌹🌹
ማሕሌተ ጽጌ በግራር ደብረ ዓባይ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ጥቅምት 3/02 / 2016 ዓ.ም
ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
✨✨✨✨✨✨✨
▭▭▭ ◎⃝ ◎⃝ ⃟ ◎⃝ ◎⃝ ▭▭▭
🔎
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
የሳምንት ሰው ይበለን
✨️✨️✨️✨️🌹🌹🌹🌹✨✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥቅምት ፬ (4) ቀን።
✝ እንኳን #ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ሃይማኖት #በኢትዮጵያ_ብሔራዊ_ሃይማኖት_እንዲሆን_ላደረጉ ለቅዱሳን ለወንድማማቾች ነገሥታት ያለፈረቃም በፍቅር አንድነት በአክሱም ተቀምጠው ለነገሡ (ለገዙ) #ለቅዱሳን_አብርሀና_አጽብሐ_ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል፣ #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ወሎ ራያ ውስጥ ያለችውን ጥንታዊቷንና ባለታሪኳን ቅዱስ ሉቃስ የሳላት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ስዕል የምትገኝበት #ደብረ_ዘመዳን_ለመሠረቱ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_በርተሎሜዎስ_ለዕረፍታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት አንዱ ለሆነው ሐዋርያው #ቅዱስ_ጳውሎስ_በደማስቆ_ላጠመቀው ለሐዋርያ #ለቅዱስ_ሐናንያ_ሰማዕትነት_ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና #ለቅዱስ_ሰርጊስ ባልንጀራ #ለቅዱስ_ባኮስ በከሀዲ ንጉሥ በአንጥያኮስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ የቅዱስ ባኮስ ሥጋ ወደ በዓታቸው ከወሰዱ ከቅዱሳን ወንድማማቾች ባሕታውያን ከባባና ከማማ ከመታሰቢያቸው፣ ከከበሩ ሮማውያን ጻድቃን ከጃንደረባው ዮሐንስና ገብረ ክርስቶስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ
(ዲ/ን ሕሊና በለጠ)
በማኅሌተ ጽጌ
"አክሊለ ጽጌ ማርያም
ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ
ክበበ ጌራ ወርቅ" እያልን እንዘምራለን። ግን ለምን እንዲህ እንላለን?
በቅድሚያ ሙሉ የማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱን ከነ ትርጉሙ ላስቀምጥ:-
"ክበበ-ጌራ-ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኀቱ፣
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፣
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፣
አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ፣
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።"
#ትርጉም:-
"ባሕርይ ከሚባል ከሚያበራ ዕንቁ ይልቅ የጠራ የወርቅ ጌጥ የኾንሽለት፣
(የጊዮርጊስ) የስሙ ምልክትና የሞቱ መታሰቢያ የተጻፈብሽ፣
ለጊዮርጊስ የመንግሥቱ ዘውድ የሆንሽ የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ፣
አንቺ ለእርሱ ኹሉን ታሰግጂለታለሽ፣
እርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል።"
ቅዱስ ጊዮርጊስ የ7 ዓመታት ተጋድሎውን የጀመረው በ20 ዓመቱ ነበር። ለሰባት ዓመታት ያክል እየሞተ እየተነሣ ተጋድሎውን ፈጽሞ በ27 ዓመቱ፣ በሚያዝያ 23፣ በ304 ዓ.ም. ዐረፈ። እስከዚያው ጌታችን ቃል እንደ ገባለት 3 ጊዜ ሞቶ 3 ጊዜ ተነሥቷል። በዐራተኛው ሞቱ ፈጽሞ ዐረፈ። ያረፈውም በዕለተ ዓርብ በ9 ሰዓት ነበር።
ቅዱስ ጊዮርጊስ 4 ጊዜ መሞቱን "ማርያም" ከሚለው ባለ 4 ፊደል ቃል ጋር ያመሣጠረው ደራሲው "ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ - የስሙ ምልክትና የሞቱ መታሰቢያ የተጻፈብሽ" ሲል እመቤታችንን በማኅሌተ ጽጌ አመሰገናት።
ቅዱስ ጊዮርጊስን ያንገላታ የነበረው ንጉሥ ዱድያኖስ ንግሥት እለስክንድርያ የምትባል ሚስት ነበረችው። መሳፍንቱና መኳንንቱ ኹሉ ለእርሷ ይሰግዱ ነበር። በሰማዕቱ ትምህርት አምና ለቅዱስ ጊዮርጊስ የፀጋ ስግደትን ሰገደችለት። በዚህም ምክንያት በሚያዝያ 15 አንገቷን በሰይፍ እንድትቆረጥ ተደርጋለች።
ያቺ ሣር ቅጠሉ ኹሉ ይሰግድላት የነበረች ንግሥት ለቅዱስ ጊዮርጊስ መስገዷን ያስተዋለው ሊቁ ግን በማኅሌተ ጽጌው "አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ - አንቺ ለእርሱ ኹሉን ታሰግጂለታለሽ" ሲል በእመቤታችንና በሰማዕቱ ምስጋና ላይ ዘከራት። ቅዱስ ጊዮርጊስ ፍጥረት ኹሉ "ብፅዕት" ለሚላት ለድንግል እንደሚሰግድም "ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ - እርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል" ሲል ገልጾአል።
"የደናግል መመኪያ፣ የሰማዕታት አክሊል፣ ..." የምትባለው እመቤታችን: ቀደም ሲል ባነሣናቸው ምክንያቶች የተነሣ: ይልቁንስ ለሊቀ ሰማዕታት ለቅዱስ ጊዮርጊስ የከበረች አክሊሉና ዘውዱ መኾኗን ሲገልጽም "ክበበ-ጌራ-ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኀቱ... አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ - ባሕርይ ከሚባል ከሚያበራ ዕንቁ ይልቅ የጠራ የወርቅ ጌጥ የኾንሽለት... ለጊዮርጊስ የመንግሥቱ ዘውድ የሆንሽ የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ" ብሏል።
እኛም እንደ አባ ጽጌ ድንግልና እንደ አባቶቻችን በማኅሌተ ጽጌ "ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ" እያልን እመቤታችንንና ሰማዕቱን እንዘክራለን።
ዘመነ ጽጌ፣ 2016 ዓ.ም.
ይቆየን......
✨✨✨✨🌹🌹🌹🌹🌹✨✨✨✨🌹🌹🌹🌹✨✨✨✨🌹🌹🌹🌹✨✨✨✨🌹🌹🌹🌹✨✨✨✨🌹🌹🌹🌹✨✨✨✨🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
✨✨✨✨✨✨✨
▭▭▭ ◎⃝ ◎⃝ ⃟ ◎⃝ ◎⃝ ▭▭▭
🔎
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ጥቅምት ፫ (3) ቀን።
✝ እንኳን #ለታላቁ_ሊቅ_ከመጽሐፈ_ሰዓታት ውጭ እጅግ ብዙ ድርሰቶችን ለደረሰ ፈላስፋም ጻድቅም ደራሲም መናኝ ባሕታዊም ለሆነ ድርሰቶቹንም ለቅዱሳን በነፋስ ጭኖ ይልክላቸው ለነበረ ለቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ ኩራት ለሆነ #ለኢትዮጵያዊው_ቄርሎስ ለአባታችን #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_ለጽንሰት በዓል በሰላም አደረሰን።
እንኳን #ለእስክንድርያ_ለአባቶች_ሊቃነ_ጳጳሳት ሃምሳ አንተኛ ለሆነ ሊቀ ጳጳሳት #ለአባ_ስምዖን ለዕረፍት በዓል፣ #ለሐዲስ_ለቅዱስ_ጊዮርጊስ ለምስክርነቱ መታሰቢያ በዓልና ለታላቁ ቴዎዶስዮስ ልጅ ለሆነ ለንጉሥ አርቃድዮስ ለወለዳት #ለቅድስት_ታኦድራ ለመታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከኒኀዋ_ከወገን_ከነገዱ_ከመቃርስና_ታኦፊላ፣ #ከአውመራና_ከአርማንያ_ሊቀ ጳጳሳት #ከአባ_ጎርጎርዮስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
ጥቅምት ፪ (2) ቀን።
እንኳን #የእመቤታችን_የቅድስት_ድንግል #ማርያም_ቅዳሴ_ለደረሰው ለብህንሳ አገር ኤጲስቆዾስ ለታላቁ አባት #ለአባ_ሕርያቆስ_ለልደትና ለዕረፍት በዓል፣ ለአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት #ለቅዱስ_አቡነ_ሳዊሮስ_ወደ_ግብጽ_አገር_ተሰዶ ለመጣ መታሰቢያ ቀን በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከሰማዕቱ_ከቅዱስ_ቴክላ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
#ሊቁ_አባ_ሕርያቆስ፦ ይህም አባት ክርስቲያን ሆኖ እመቤታችንን የሚወድ ሰው ሁሉ ይህንን አባት ያውቀዋል። አባ ሕርያቆስ ተወልዶ ያደገው በምድረ ግብጽ ሲሆን አካባቢው ብህንሳ (ንሒሳ) ይባላል። ይህቺ ቦታ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ጨምሮ በርካታ ቅዱሳንን ያፈራች ናት።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ
ቅዱሳን ማርያም ገዳም ደማቅ አቀባበል እየተደረገላቸው ነው።
ቅዱስነታቸው ከነሐሴ ፳፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ጀምሮ በሰሜን አሜሪካ ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ዛሬ ማለዳ ወደ አገራቸውና ወደ መንበረ ክብራቸው ተመልሰዋል።
ጥቅምት 1/2016 ዓ.ም
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨
የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ነገ ጥቅምት ፩ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም ከማለዳው አንድ ሰዓት ጀምሮ ቅዱስነታቸውን በአማረና በተዋበ መልኩ ለመቀበል የቅድመ ዝግጅት ሥራቸውን አጠናቀዋል። ለዚህም የገዳሟ አስተዳዳሪ፣ዋና ጸሐፊ፣ የቁጥጥር አገልግሎት ኃላፊና ሌሎች የአስተዳደር ሰሰራተኞች ቅድስት ቤተክርስቲያናችንንና ቅዱስ ፓትርያርኩን በማክበር ላደረጋችሁት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አቀባበል ኮሚቴ ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል።
"የቅዱስነታቸው በረከትና ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን"
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
#የተባረከ_የጥምት_ወር_የቀኑ_ሰዓት_ዐሥራ_አንድ ነው ከዚህም በኋላ ይቀንሳል።
ጥቅምት ፩ (1) ቀን።
✝ እንኳን #ከሮሜ_አገር ለሆነች በገድል ተጠምዳ ለኖረች #በጨካኙ_ንጉሥ_በዳኬዎስ ወታደሮች እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለች #ለቅድስት_አንስጣስያ ለዕረፍት በዓልና ለአልዓዛር እኅት #ለቅድስት_ማርያም ለመታሰቢያ በዓሏ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከኅርጣንና_ከድንግል_ቅድስት_ሶስና ከመታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #ሰማዕቷ_ቅድስት_አንስጣስያ፦ ይችም ቅድስት መስተጋድልት ከሮሜ አገር ናት ወላጆቿም ክርስቲያኖች ናቸው ጠቃሚ የሆነ ትምህርትን በማስተማር ክብር ባለው በመልካም ሥርዓት አሳደጓት።
✝ ✝ ✝
✝ "#ሰላም_ለማርያም_ለዓልአዛር_እኅቱ። እንተ አንሥኦ ክርስቶስ እምነ መቅበርቱ። በሀሊተ ብካይ ጊዜ ተቀበሎቶ ሎቱ። ሶበሰ እግዚእየ ሀሎከ በዝንቱ። እመኢትውህበ እኅየ ለሞቱ"። #ሊቀ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የጥቅምት_1።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨
ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጥቅምት ፩ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ገዳም አቀባበል እንደሚደረግላቸው ተገለጸ፡፡
----------------------------------------------
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሀገረ አሜሪካን ሲያደርጉት የሰነበቱትን ሕክምና አጠናቀው ጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ ሀገራቸው እና ወደ መንበረ ክብራቸው የሚመለሱ በመሆኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሰባት አባላት ያሉት ኮሚቴ ተቋቁሞ ለአቀባበሉ ስኬታማነት አስፈላጊውን ሥራ ሁሉ በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው።
ቅዱስነታቸው ሕክምናቸውን ጨርሰው በሰላም ወደ ሀገራቸው እና ወደ መንበረ ክብራቸው መመለሳቸውን በማስመልከት ጥቅምት 1ቀን 2016 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎች ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች ፣ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ፣ ምዕመናን በተገኙበት የአቀባበል መርሐ ግብሩ እንደሚካሔድ ተገልጿል።
ይህ የአቀባበል መርሐ ግብር የቤተክርስቲያናችንንና የቅዱስ ፓትርያርኩን ክብር በሚመጥን መልኩ በደመቀ ሁኔታ መከናወን ይቻል ዘንድ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፣ ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችና ማኅበራት ሰዓቱን በማክበር ተገኝታችሁ ለቅዱስነታቸው ያላችሁን አባታዊ ክብር እንድትገልጹና አባታዊ ቡራኬ እንድትቀበሉ የቅዱስ ፓትርያርኩ አቀባበል ኮሚቴ ጥሪውን በማክበር ያስተላልፏል ሲል የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት ገልጿል።
ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
✨✨✨✨✨✨✨
▭▭▭ ◎⃝ ◎⃝ ⃟ ◎⃝ ◎⃝ ▭▭▭
🔎
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #መስከረም ፴ (30) ቀን።
✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ አጽፋቸውን እንደጀልባ ተጠቅመው የኢያሪኮን ባሕር ለተሻገሩት ለታላቁ ጻድቅ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባሕር ደቀ መዝሙር ለሆኑ #በኤራትራና_በኢትዮጵያ_ገዳም ለመሰረቱ ለታላቁ አባት #ለአቡ_ አቡሳዲ_ለዕረፍታቸው በዓልና #ከተሰዓቱ_ቅዱሳን አንዱ ለሆኑት #ለአቡነ_ይስሐቅ_ተአምር_ሰረተው #አቡነ_ገሪማ ተብለው እንዳጠሩ ላተረጉበት ቀን መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
✝ #አቡነ 9_አብሳዲ_ዘደብረ_ማርያም (ክሳሄ)፦ እኚህ ጻድቅ አጽፋቸውን እንደጀልባ ተጠቅመው የኢያሪኮን ባሕር የተሻገሩት የታላቁ ጻድቅ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባሕር ደቀ መዝሙር ናቸው፡፡ የደብረ ክሳሄው አቡነ አብሳዲ ገድላቸውን የፈጸሙት ኤርትራ ውስጥ ነው።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በግራር ደብረ ዓባይ ቅድስት አርሴማ የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ በዓለ ንግስ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ።
መስከረም 29/ 2016 ዓ.ም
ከፎቶ ማህደር በጥቂቱ
ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
✨✨✨✨✨✨✨
▭▭▭ ◎⃝ ◎⃝ ⃟ ◎⃝ ◎⃝ ▭▭▭
🔎
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✨️✨️✨️✨️✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በግራር ደብረ ዓባይ ቅድስት አርሴማ የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ በዓለ ንግስ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ።
መስከረም 29/ 2016 ዓ.ም
ከፎቶ ማህደር በጥቂቱ
ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
✨✨✨✨✨✨✨
▭▭▭ ◎⃝ ◎⃝ ⃟ ◎⃝ ◎⃝ ▭▭▭
🔎
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✨️✨️✨️✨️✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #መስከረም ፳፱ (29) ቀን።
✝ እንኳን #ለታላቋ_ሰማዕት_ለቅድስት_አርሴማ #ለእመቤቷ_አጋታና_ለደናግል_ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል፣ ለሐዋርያው ለነባቤ መለኮት ለቅዱስ ዮሐንስ ለፈለሰበተ ሥጋው መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከጌታችንና_መድኃኒታችን_ከኢየሱስ_ክርስቶስ #ከእመቤታችን_ከቅድስት_ድንግል_ማርያም በሥጋ #ከተወለደበት_ከልደቱ_ከበዓለ ወልደ ከወራዊ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #ታላቋ_ሰማዕት_ቅድስት_አርሴማ እና #እመምኔቷ_ቅድስት_አጋታና_ደናግል፦ ይህም እንዲህ ነው በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን እርሱ መልኳ ውብ የሆነ ብላቴና ድንግል ሊአገባ ሽቶ በየሀገሩ ሁሉ ሒደው መርጠው ያመጡለት ዘንድ አሽከሮቹን አዘዘ። ይችንም የሚመስላት የሌለ ቅድስት አርሴማን በሮሜ አገር በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ አገኙዋት። ሥዕሏንም ሥለው ለንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ላኩለት ንጉሡም ሥዕሏን በአየ ጊዜ እጅግ ደስ አለውና ለሠርግ እንዲመጡ ወደ መኳንንቱ ላከ።
✝ እሊያ ደናግልም ይህን ነገር በአወቁ ጊዜ ይረዳቸው ዘንድ ድንግልናቸውንም ይጠብቅ ዘንድ አልቅሰው ወደ እግዚአብሔር ለመኑ። ከዚህም በኋላ ተነሥተው በሥውር ሸሹ የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደ ሆነ ወደ አርማንያ ሀገርም ደርሰው በአንድ ቦታ ተቀመጡ ከእርሳቸውም ጋር የተሰደዱ ቁጥራቸው ሰባ አምስት የሆነ ወንዶች፣ ሴቶችም ሠላሳ ዘጠኝ የሆኑ ከእርሳቸው ጋራ አሉ። ምግባቸውን አያገኙም ነበርና በታላቅ ችግር ውስጥ ኖሩ ከእነርሱም መብራት የምትሠራ አንዲት ሴት ነበረች ከእርሷም የእጅ ሥራ ከሚገኘው በየጥቂቱ ይመገባሉ።
✝ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም የከበረች አርሴማን በፈለጋት ጊዜ አላገኛትም ግን በአርማንያ አገር እንዳለች ስለርሷ ሰማ። ደግሞ ለአርማንያ ንጉሥ ለድርጣድስ ስለርሷ ከዲዮቅልጥያኖስ ሸሽታ እንደ መጣች የአርሴማን ሥራ ነገሩት እርሱም አንዱን የአርማንያ መኰንን ለእኔ ጠብቃት ወደ እኔም ላካት ብሎ አዘዘው።
✝ ደናግሉም ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ተሠወሩ ወደ ንጉሥም ወነጀሉአቸው ንጉሡም ቅዱስት አርሴማን በክብር አድርገው ያመጧት ዘንድ አዘዘ እርሷም ወደ እርሱ መምጣትን እምቢ በአለች ጊዜ እየጎተቱ ወስደው ወደርሱ አደረሷት። የቅድስት አርሴማንም ላህይና ደም ግባቷን በአየ ጊዜ ድንግልናዋን ሊያረክስ ሽቶ እናቷ አጋታን አባብላ እሺ ታሰኝለት ዘንድ አዘዛት አጋታም ወደርሷ ሒዳ ልቧን አስጨከነች እንዲህም አለቻት። "ዕወቂ ይህ ርኲስ አረሚ እንዳያረክስሽና ሰማያዊ ሙሽራሽን እንዳትተዪ እርሱም ክብር ይግባውና የእግዚአብሔር ልጅ ሕያው ክርስቶስ ነው"።
✝ ንጉሡም ይዞ ወደ እልፍኙ ሊአስገባት ከአደባባይ መካከል ተነሥቶ ድንግል አርሴማን ያዛት። በዚያንም ጊዜ በቅድስት አርሴማ ላይ የእግዚአብሔር ኃይል አደረባትና በምድር ላይ ጣለችው እርሱ ግን በጦርነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለ ነበር በታናሽ ሴት ብላቴና ስለተሸነፈ ያን ጊዜ አፈረ። ራሷንም በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጧት ከዚህም በኋላ ደናግሉን ሁሉ ከእናታቸው አጋታ ጋር ይገድሏቸው ዘንድ አዘዘ።
✝ አንዲት የታመመች ድንግል ነበረች በዐልጋዋ ላይም እንደተኛች ወደ ወታደሮች ጮኸች መጥተውም እንደ እኅቶቿ ራሷን ቆረጡ ሁሉም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ እነዚያንም ከሮሜ አገር አብረው የመጡ ወንዶችን ገደሏቸው ቁጥራቸውም ሰባ አምስት ናቸው ሥጋቸውም በተራራ ላይ የተጣለ ሁኖ ቀረ።
✝ ሰማዕታትም ከተገደሉ በኋላ በንጉሡ ላይ ጋኔን ተጫነበት መልኩም ተለውጦ እንደ እርያ ሆነ። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ወደርሱ መጥቶ በላዩ ጸልዮ እስከ አዳነው ድረስ ስለዚህም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ። የቅዱሳን ሰማዕታትንም ሥጋቸውን ከተጣለበት ሰብስበው በአማረ ቦታ አኖሩአቸው ያማረች ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ተሠራችላቸው። ከእነርሱም ታላላቅ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት አርሴማና በቅዱሳን ሰማዕታት ሁሉ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 29 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
✝ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ይትፌሥሐ አድባረ ጽዮን። ወትሐሠያ አዋልደ ይሁዳ። በእንተ ፍትሕከ እግዚኦ"። መዝ 47፥11-12 የሚነበበው ወንጌል ማቴ 25፥1-14 ወይም ሉቃ 21፥21-ፍ.ም።
✝ ✝ ✝
✝ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "እግዚአብሔር ይቤለኒ ወልድየ አንተ። ወአነ ዮም ወለድኩከ። ሰአል እምኔየ እሁበከ አሕዛበ ለርስትከ። መዝ 2፥7-8። የሚነበቡት መልዕክታት ገላ 4፥1-12፣ 1ኛ ዮሐ 1፥1-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 3፥1-12። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 21፥21-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የቅድስት አርሴማ የዕረፍት በዓል፣ የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ የፍልሠተ ሥጋው መታሰቢያ በዓል ሁላችንም ይሁንልን።
