ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
Ir al canal en Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
Mostrar más603
Suscriptores
-324 horas
-87 días
-1730 días
Archivo de publicaciones
የበዓታ ማርያም በዓለ ንግሥ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በአድኣ ወረዳ ቤተ ክህነት የጥንታዊቷ ኤረር ደብረ ገነት በዓታ ለማርያም ገዳም በደማቅ ሥርዓት ተከበረ።
ታህሳስ 03/2016 ዓ.ም
የባዕታ ለማርያም በዓል ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም እና ደብረ መንክራት ሥዕል ቤት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን በደማቅ ሥርዓት ተከበረ።
ታህሳስ 03/2016 ዓ.ም
የባዕታ ለማርያም በዓል በባቴ ደብረ ማዕቶት ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል በደማቅ ሥርዓት ተከበረ።
ታህሳስ 03/2016 ዓ.ም
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓታ እና የአባታችን አብነ ዜና ማርቆስ በዓለ ንግሥ በሀዋሳ ደብረ ምጥማቅ መድኅኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከበረ የአባታችን ዜና ማርቆስም ታቦት ለመጀመርያ ጊዜ ነግሷል።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት በዓል በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።
ታኅሣሥ 3 ቀን 2016 ዓ.ም
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በአድኣ ወረዳ ቤተ ክህነት የጥንታዊቷ ኤረር ደብረ ገነት በዓታ ለማርያም ገዳም :-
ገዳሟን ተሳልመን በረከት ለመካፈል ያብቃን
በመልዕክታቸው መጨረሻ ላይም ይህ የአዲስ አበባ ማእከል ሕንጻ የዚህ ስኬት አካል ስለሆነ ሁላችንም የድርሻችንን ብንወጣ በአንድ ዓመት ውስጥ መጨረስ እንችላለን በማለት ተናግረዋል።
የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም በበኩላቸው ይህ ዛሬ በአዲስ አበባ ማእከል እየተገነባ ያለው የወጣቶች ማእከል በአጠቃላይ ወጣቱ ትውልድ ስለ አገሩና ስለቤተ ክርስቲያኑ የሚመራመርበት፣ ዘመኑ ከሚያመጣቸው ፈተናዎች ተጠብቆ ለበጎ ነገር የሚነሳሳበት መሆኑን ተገንዝበን ምዕመናን ሁሉ ተረባርበን በአጭር ጊዜ ልናጠናቅቀው ይገባል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ሰብሳቢው አክለውም ማኅበሩ ባለፉት 32 ዓመታት በሀገር ውስጥ እና በውጪ፣ በገጠርና በከተማ ውጤታማ ተግባራትን ማሳካት የቻለው በአባቶች ቡራኬ፣ በአባላቱ ጠንካራ ሥራ እና በምዕመናን ድጋፍ በመሆኑ ይህ ፕሮጀክት እንዲሳካ የሁሉም አካላት ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በዕለቱ በገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሩ ላይ ከተገኙት ታዳሚዎች 7,500,000.00 (ሰባት ሚሊዮን አምስት መቶ ሽህ ብር) ቃል የተገባ ሲሆን ለዚህ በጎ ዓላማ ምዕመናን ሁሉ እንዲሳተፉ የሕንጻ ግንባታ ኮሚቴው ጥሪውን አቅርቧል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ባከናወነው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ከ7.5 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ለሚያስገነባው ባለ ዐስራ ሁለት ወለል ሕንጻ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም በግራንድ ኤልያና ሆቴል አካሂዷል። በመርሐ ግብሩ ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ(ዶ/ር)፣ የጅጅጋ ሱማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ሙሉጌታ ስዩም(ዶ/ር)፣ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ እና የአዲስ አበባ ማእከል ሰብሳቢ ዲ/ን ኃ/ማርያም መድኅን እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የሚገነባው አዲሱ ሕንጻ ማእከሉ ወጣት የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን በሙሉ አቅሙ በማስተማር የቤተ ክርስቲያን እና የሀገር ተረካቢ እንዲሆኑ ለማስቻል የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ እና በማእከሉ ለሚከናወኑ ልዩ ልዩ የሐዋርያዊ አገልግሎት፣ የሙያ አገልግሎት፣የሚዲያ ተደራሽነት እና ለቅዱሳት መካናት ተግባራት አቅም የሚፈጥር መሆኑ በዕለቱ ተገልጿል።
በመርሐ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ለሁሉ ነገር መሠረት እና ለምንፈልገው ለውጥ የምርምር እና የትምህርት ተቋማት ያስፈልገናል ብለዋል፡፡ ብፁዕነታቸው አክለውም የትምህርት፣ የጤና እና ሌሎች ትልልቅ ተቋማትን ለማቋቋም የማንንም ርዳታ ሳንጠብቅ ዐሥር ሚልዮን የምንሆን ኦርቶዶክሳውያን በዓመት ውስጥ ባሉን የፆም ወቅቶች ብቻ ለቁርስ ወጪ የምናደርገውን ብናዋጣ ዓላማችንን ማሳካት እንችላለን ብለዋል፡፡
እመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት በጎንደር ደብረ ኃይል ወደብረ ጥበብ በዓታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
ታኅሣሥ 3 ቀን 2016 ዓ.ም (ጎንደር)
በመናኔ መንግሥት ተክለ ሃይማኖት በ1763 ዓ.ም ተመስርታ በ1765 ዓ.ም ቅዳሴ ቤቷ የተከበረው የሀገራችን የታች ቤት አቋቋም ጉባኤ ቤት ምስክር መስጫ የሆነችው ጥንታዊቷ የጎንደር ደብረ ኃይል ወደብረ ጥበብ በዓታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን በጎንደር እና አውራጃዋ እንዲሁም በተለያየ ቦታ የሚገኙ ከዚህ የምስክር ጉባኤ ቤት ተመርቀው የወጡ በርካታ የአቋቋም መምህራን በተገኙበት የዕለቱን ምስጋና በልዩ ያሬዳዊ ዜማ በማኅሌት ያደረ ሲሆን የንግሡም በዓል የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በተገኙበት በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
ከሀገራችን በልዩ ውበት በማኅሌታዊ ሥርዓት በታላቅ ድምቀት ከሚከበርባቸው ቦታዎች መካከል በከፍተኛ ደረጃ በዚህች ታላቅ የአቋቋም ምስክር ጉባኤ ቤት መቀመጫ በሆነችው በዓታ ለማርያም መገኘት ታላቅ መንፈሳዊ ደስታ ይሰጣል።ሊቃውንቱ እና ምእመናንም ማኅሌቱን ናፍቀው ፤ ከተለያየ ቦታ ሊቃውንቱ የዓመቱን ቀለም ለመስማት ተሰባስበው በዚያውም ከቀድሞ መምህራን ወንድሞቻቸው እና አባቶቻቸው ጋር ተገናኝተው ቃለ እግዚአብሔርን የሚያፈሱበት ልዩ በዓል ነው።
ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ያሳትፈን ።
ዘጋቢ :- ዲ/ን አንዳርጋቸው ከጎንደር
እመቤታችን ድንግል ማርያምም ከዚህ በኋላ ከቤተ መቅደስ ወጥታ ከጻድቁ ዮሴፍ ጋር ኖረች፡፡ እርሱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ፀንሳ ስትወልድ፣ በስዳቷ ወቅትም ወደ ግብጽና ኢትዮጵያ ስትጓዝ እንዲሁም መከራ ስትቀበል ሁሉ ከጎና ሳይለይ የጠበቃት ነው፡፡ ይህን ሁሉ ግን አምላካችን እግዚአብሔር በቸርነቱ ለእኛ ድኅነት ሲል ያደረገው በመሆኑ በእመቤታችን በኩል የተፈጸመውን የክርስቶስ የማዳን ሥራ በእምነት በመቀበል አማላጀነቷንና ተራዳኢነቷን ተስፋ በማድረግ ልንኖር ይገባል፡፡
በዓሉን የምሕረት፣ የበረከትና የረድኤት ያድርግልን፤ አሜን!
ምንጭ፡- “ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን” በመጋቤ ሐዲስ መምህር ሮዳስ ታደሰ
ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐናም የእግዚአብሔርን ስእለት ለመፈጸም ዘመዶቻቸውንና ባልንጀሮቻቸውን በመጥራት ልጃቸውን ልዩና ንጹሕ ልብስን አልብሰው በመንፈሳዊ ዝማሬ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ፣ መብራትን በእጆቻቸው ይዘው እያበሩ ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደስ ወሰዷት፤ በዚያን ጊዜም ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ከካህናቱ ጋር በመሆን እነርሱን ለመገናኘት ከመቅደስ ወጣ፡፡
በቤተ መቅደሱ ባሉት የሊቀ ካህናቱ መግቢያ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ የሚያስወጡ ፲፭ ደረጃዎች ነበሩ፤ በእነዚያም በእያንዳንዱ ደረጃዎች መዝሙረ ዳዊት ተደጋግሞ የሚደረስባቸው ናቸው፤ ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐናም ልጃቸው እመቤታችን ማርያምን ከአንደኛው ደረጃ ላይ ቢያኖሯት መንፈሳዊ ኀይልን ተመልታ ያለምንም ረዳት ብቻዋን ደረጃዎቹን በመውጣት ወደ ሊቀ ካህናቱ ወዳለበት ስፍራ ሄደች፤ እርሱም በእጅጉ ተደንቆ ባረካት፤ በዚያን ጊዜም ለሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ መንፈስ ቅዱስ ምሥጢርን ገለጠለት፤ ነቢያት ትንቢት የተናገሩላት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እንደምትወልድ አስገነዘበው፤ መኖሪያዋም በዚሁ ቤተ መቅደስ እንዲሆን የአምላክ ፈቃድ መሆኑን አወቀ፡፡
እርሱም ይህንን የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራን በማድነቅ ‹‹ይህቺን የመሰለች ልጅ ምን እናደርጋታለን? ምን እናበላታለን? ምንስ እናጠጣታለን? ምን እናነጥፍላታለን?›› ብሎ ሲጨነቅ ቸርነቱ የማያልቅ ልዑል እግዚአብሔር መልአኩ ፋኑኤልን ላከላት፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤልም ኅብስት ሰማያዊን በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወትን ይዞ ረብቦ ታየ፤ ካህኑ ዘካርያስም ለእርሱ የመጣ ኅብስተ መና እንደሆነ አስቦ ታጥቆና እጅ ነሥቶ ቢቆም ወደ ላይ ራቀበት፡፡ የተሰበሰበው ሕዝብ በተራ በተራ ቢሞክሩም በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ ላይ ራቀባቸው፡፡ ሐና እና ኢያቄምም ለእነርሱ የመጣ እንደሆነ ለማወቅ ቢቀርቡም ወደ ላይ ከፍ አለባቸው፤ ከዚህ በኋላ ካህኑ ዘካርያስ ሐናን ‹‹እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምና ልጅቷን ትተሸ ወደዚህ ነይ›› አላት፡፡ በዚህ ጊዜም መልአኩ በመውረድ አንድ ክንፉን አንጽፎ፣ አንዱን ክንፉን አጐናጽፎ ከመሬት የሰው ቁመት ያህል ከፍ አድርጓት ኅብስቱን መገባት፤ ጽዋውን አጠጣት፤ በኋላም ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡ ሊቀ ካህናቱም ‹‹የምግቧ ነገር ከተያዘልን ቦታዋ ከቤተ መቅደስ ይሁን›› ብለው ምንጣፉን አንጥፈው፣ መክዳውን ግራና ቀኝ፣ መጋረጃውን አድርገው ወደ ቤተ መቅደስ አስገቧት፤ ይህም ታኅሣሥ ፫ ቀን ነበር፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ሰማያዊ ኅብስት እየተመገበች፣ ስቴ ሕይወት እየጠጣችና ከመላእክት ጋር እየተጫወተች ፲፪ ዓመት በቤተ መቅደስ ኖረች፡፡ ሆኖም ግን በቤተ መቅደስ ሳለች አይሁድ ተሰብስበው ክፉ ምክርን መከሩባት፤ “ሰማይንና ምድርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለችና እርሷም እንደ ባሪያ ልትገዛን ነው” በሚል ለማስገደል ሰዎችን ላኩ፡፡ እነዚያም አይሁድ የላኳቸው ሰዎች ሊገድሏት ሲሄዱ ቤተ መቅደሱ አራት ማዕዘን እሳት ሆኖ፣ መላእክትም ሰይፋቸውን መዘው፣ ረበው ታዩአቸው፡፡ ይህን ሲመለከቱ እመቤታችን በእሳት እንደ ተቃጠለች አስበው በመደሰት ወደ መጡበት ተመልሱ፤ በማግስቱ ግን በቤተ መቅዱስ በደኅና አገኟት፡፡
አይሁድ በዚህን ጊዜ እንዲገድሏት ወዳዘዙአቸው ሰዎች በመሄድ ለምን እንዳልገደሉአት ጠየቁአቸው፤ እነርሱም የሆነውን ባለ መረዳት በድጋሜ ሊገድሉአት ሄዱ፤ ዳግመኛም መንገዳቸው ዱር፣ ገደልና ባሕር ሆነባቸው፡፡ ይህን ጊዜ በአስማት እንዲህ የምታደርጋቸው እንደሆነ በማሰብ የእርሷን አስማት የሚበልጥ ለመፈለግ ተስማምተው መጥቁል የሚባል መተተኛ ጋር ሄዱ፡፡ እርሱም ‹‹ዋጋዬን ከሰጣችሁኝ እሺ፤ እርሷንስ አጠፋላችኋለሁ›› አላቸው፡፡ እነርሱም ብዙ ወርቅ፣ ፈረስ፣ በግ፣ ፍየል፣ ጊደርና አልባሳት ሰጡት፡፡ ነገር ግን ይህን ሁሉ ሀብት ለማግኘት መለስ ቢል ብሩ፣ ወርቁና ሁሉ ነገር ዝጎና አፈር በልቶት አገኘው፡፡ ይህን ጊዜ ‹‹የኢያቄምና የሐና ልጅ ሳልቀድማት ቀደመችኝ›› ብሎ እጅን ጸፋ፡፡ ከዚያም ለእነርሱ ሲያሳያቸው ‹‹እኛማ ቀድመን አላልንህምን? አንተ ነህ እንጂ ሁሉን ማድረግ ይቻለኛል ያልከው›› አሉት፡፡ ገንዘባቸውንም እንዲመልስላቸው አስጨንቀው ያዙት፤ መጥቁልም ‹‹ቆዩኝ፥ የእርሷንስ ነገር አሁን በመንፈቀ ሌሊት አሳያችኋለሁ›› ብሎ ከእነርሱ መካከል ጎበዝ ጎበዙን መርጠው ፫፻፸ ሰው እንዲሰዱለት በጠየቃቸው መሠረት ሰጡት፤ ከእነርሱም መካከል ወንዝ ወርዶ አንዱን አርዶ ፫፻፸ አጋንንት ስቦ ካወጣ በኋላ እንዲረዱት ጠየቃቸው፤ በጠየቃቸው ነገር ደስ በመሰኘትም አጋንንቱ ከፊት፣ መጥቁል በመካከል አይሁድ በኋላ ሆነው ነጋሪት እየተመታ፣ እምቢልታ እየተነፋ፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ለመግደል ቤተ መቅደስ ሊደርሱ ሁለት ምንዳፈ ሐጽ ሲቀራቸው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከዚያ ድረስ ያልተደረገ መብረቅና ነጎድጓድ ወርዶ አጋንንትን፣ መጥቁልንና አይሁድን ቀጥቅጦ አጠፋቸው፡፡
እመቤታችን ድንግል ማርያምም በማግስቱ ይህን አይታ ‹‹መጥቁል ሆይ፥ እኔን አጠፋ ብለህ መጥተህ አንተ እንዲህ ሆንክ? ከአንተ መከራና መዓት ያወጣኝ አምላክ ይክበር ይመስገን›› ብላ አመሰገነች፡፡ ‹‹ዮሰሜር፣ አድሜሽ፣ ድቸር፣ አዶናዊስ፣ ሰራሰቅሰሬል›› ብላ የጌታን ኅቡእ ስሙን ብትጸልይበትም መሬት ተከፍቶ ከእነ ሥጋቸው ዋጣቸው፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከዚህ በኋላ ተፈራች፤ ለመልካም ሰው ወዳጅ ለክፉ ሰዎችም ጭምር አማላጅ የሆነችው እናታችን ለጠንቋይና ለአስጠንቋይ ግን በሕይወተ ሥጋ እስካሉ ድረስ ንስሓ ካልገቡ በስተቀር እንደማታማልዳቸው ከዚህ ታሪክ እንረዳለን፡፡
እናታችን፣ አማላጃችንና ተራዳኢያችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጠላት የተነሡባት በዚህ ጊዜ ብቻ አይደለም፡፡ ፲፭ ዓመት ሲሞላትም ‹‹ለአቅመ ሔዋን በመድረሷ ከቤተ መቅደስ መውጣት አለባት›› በሚልም አይሁድ በጠላትነት ተነሥተውባት ነበር፡፡ ካህኑ ዘካርያስም ይህን ሰምቶ እመቤታችንን እንዲህ ብሎ ጠየቃት፤ «ኦ ወለተ እስራኤል እፎ ትፈቅዲ ትንበሪ፤ ልጄ እንደምን ሆነሽ ልትኖሪ ትወጂያለሽ?» አላት፡፡ እርሷም «ከእግዚአብሔር በታች ያለኸኝ አባት አንተ ነህ፤ በዚያውም ላይ እናትና አባቴ አደራ ያሉህ አንተን ነው፤ ወደ እግዚአብሔር አመልክትልኝ» አለችው፡፡ ዘካርያስም ጸለየ፤ አምላካችን እግዚአብሔርም ለካህኑ ዘካርያስ ከነገደ ይሁዳ መካከል ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን ሰዎች በመምረጥ በትራቸውን ሰብስቦ በቀዳማይ ሰዓተ ሌሊት ከቤተ መቅደስ አግብቶ ሲጸልይ እንዲያድር እንዲሁም በቀዳማይ ሰዓተ መዓልት አውጥቶ ምልክቱን እንዲመለከት ነገረው፡፡ እርሱም እንደታዘዘው አድርጎ በማግስቱ ካህናቱን ሰብስበው በትሮቹን አውጥተው ቢያዩ የዮሴፍ በትር አብባና አፍርታ ተገኘች፡፡ ከበትሩ ጫፍ ላይም «ኦ ዮሴፍ ወልደ ዳዊት ዕቀባ ለማርያም ፍኅርትከ፤ ዮሴፍ ሆይ እጮኛህ ማርያምን ጠብቃት» የሚል ጽሑፍ በመገኘቱ ርግብም መጥታ በራሱ ላይ አርፋ ነበርና ለእርሱ ተጠሰች፡፡
‹‹ትነብር ውስተ ቤተ መቅደስ፤ በቤተ መቅደስ ውስጥ ትኖር ነበር›› ቅዱስ ያሬድ
ዓለም ሁሉ ተሰብስቦ ቢመዘን አንድ የራሷን ፀጉር የማያህል ደግ ፍጥረት፣ ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች፣ ንጽሕናዋንም ይሁን ቅድስናዋን ፍጥረት በአንደበቱ ተናግሮም ሆነ ጽፎ የማይጨርሰው፣ የአምላክ ማደሪያ፣ እመ አምላክ፣ እመ ብዙኃን፣ ሰዓሊተ ምሕረት፣ አቁራሪተ መዓት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት የከበረ በዓል ነው፡፡
ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ‹‹ትነብር ውስተ ቤተ መቅደስ፤ በቤተ መቅደስ ውስጥ ትኖር ነበር›› በማለት ስለ እርሷ የቅድስናና የንጽሕና ሕይወት ገልጿል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በፈቃደ እግዚአብሔር ከአባቷ ቅዱስ ኢያቄምና ከእናቷ ቅድስት ሐና በስእለት የተገኘች መሆኗ ታሪኳ የተመዘገበበት የነገረ ማርያም መጽሐፍ ይገልጻል፡፡
ቅድስት እናታችን ድንግል ማርያም በተለወደች በስድስት ወሯ ከእናቷ እቅፍ ወርዳ በመቆምና ሰባት እርምጃን ተራምዳ ዳግም ወደ እናቷ እቅፍ ውስጥ በመግባት ሐናን አስደንቃታለች፡፡ አንድ ዓመት ሲሆናትም አባቷ ኢያቄም ታላቅ ድግስ አዘጋጅቶ ካህናቱንና ሕዝብን ጠርቶ ጋበዘ፡፡
ከዚህም በኋላ እመቤታችን ሦስት ዓመት በሆናት ጊዜ እናቷ ሐና የልጇን ስእለት አስታውሳ ለቤተ መቅደስ አገልጋይ እንድትሆን መስጠት እንዳለባቸው ለባሏ ለኢያቄም እንዲህ ብላ አወሳችው፤ ‹‹ይህቺ ብላቴና የስእለት ገንዘብ እንደሆነች ታውቃለህ፤ ወስደን ለቤተ እግዚአብሔር እንስጣት፤›› እርሱም ‹‹ፍቅርሽ ይለቅልሽ ብዬ ነው እንጂ እኔማ ፈቃዴ ነው›› አለ፤ ኢያቄም ይህን ማለቱ ሐና እመቤታችንን በመካንነት ኖራ ያገኘቻት አንዲት ልጇ ናትና ከፍቅሯ ጽናት የተነሣ ተለይታት አታውቅም ነበርና ነው፡፡
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ታኅሣሥ ፫ (3) ቀን።
✝ እንኳን #አምላክን_ለወለደች_ለእናታች_ለእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም_በሦስት_ዓመቷ_ወደ_ቤተ_መቅደስ_ለገባችበት (ለበዓታ ለማርያም) በዓል፣ ለሊቀ መላእክት #ለቅዱስ_ፋኑኤል_እመቤታችንን_ሰማያዊ_መናና_መጠጥን_ለመገበበትና_ላጠጣበት ዓመታዊ ክብረ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ።
✝ ✝ ✝
✝ #የእመቤታችን_ወደ_ቤተ_መቅደስ_መግባት፦ እናቷ ቅድስት ሐና ልጅ የሌላት ስለሆነች በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ ከሴቶች ተለይታ ርቃ ትኖር ነበር ሽማግሌ ከሆነ ከኢያቄም ከባሏ ጋርም እጅግ የምታዝ ሆነች። እግዚአብሔርም ኀዘናቸውን ሰማ ቅድስት ሐናም እንዲህ ብላ ለእግዚአብሔር ተሳለች "የሰጠህኝን ፍሬ ለእግዚአብሔር አገልጋይ አደርገዋለሁ"።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ታኅሣሥ ፪ (2) ቀን።
✝ እንኳን #ለሠለስቱ_ደቂቅ_ለአናንያ_ለአዛርያና_ለሚሳኤል #እግዚአብሔር_ኃይል_ላደረገላቸው ለመታሰቢያ በዓላቸው፣ #ለቅዱስ_አውክያኖስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ከላይኛው ግብጽ ከሚኖሩ ሰዎች ወገን ለሆነ #ለቅዱስ_አባት_ለአባ_ሖር ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ፋሲለደስ አገልጋዮቹና ዘመዶቹ ከሆኑ #ከሰባት_ሺህ_ሠላሳ_ሦስት_ከሆኑ_ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው፣ #ከአብላፍታን፣ ከዐረብ ወገን ከሆነ #ከሰማዕት_አንበስና_ከመነኰስ_ናትናኤል ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #ሠለስቱ_ደቂቅ፦ በዚች ቀን ናቡከደነፆር ከአባታቸው ጋር ለማረካቸው ሦስቱ ለሆኑ ለይሁዳ ንጉሥ ለኢዮአቄም ልጆች እግዚአብሔር ኃልን አደረገላቸው። እሊህም አናንያ አዛርያ ሚሳኤል ናቸው በቤቱም ውስጥ አሳድጎ በባቢሎን አገሮች ውስጥ ሾማቸው።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
በወቅታወ ጉዳይ ዙሪያ ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል፦
በስመአብ፣ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ፤ አሜን፡፡
በወቅታዊ ጉዳዮች ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
“ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን” ሮሜ 8፡35-36
ቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ ጸዋትወ መከራን፣ ሞትንና ስደትን፣ የመቀበል ታሪኳ ዛሬ የተጀመረ ባይሆንም በአሁኑ ጊዜ የሰው ልጅ ይኽንና መሰል መተኪያ የሌለው ሕይወት የሚያጠፋና ሥጋት ላይ የሚጥሉ ተፈጥሮአዊ፣ ሰብዓዊ ክብሩን የሚያራክስ ተግባራት እንዳይደገሙ ለማድረግ በሚጥርበት ዓለም ችግሩ በተለይም በሀገራችን እየተባባሰ መቀጠሉ እጅግ ያሳስበናል፡፡
በአርሲ ዞን በሹርካ ወረዳ ሶሌ ሚካኤል፣ በዲገሎ ማርያም፣ በሮቤ እንደቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም አብያተ ክርስቲያናት ላይ በተለያዩ ጊዜያት ሠላሳ ስድስት፣ እንዲሁም በሶሌዲገሉና ጢጆለቡ በተባሉ ቀበሌዎች ሃያ ስምንት ኦርቶዶክሳዊያን ከየቤታቸው ተለቅመው ሰማዕትነትን ሲቀበሉ ከእነዚህም ሰባቱ ሴቶችና ሃያ አንዱ ወንዶች ናቸው፡፡ በዚህ ጥቃት የሰባ ዓመት አዛውንትና የሃያ ስምንት ቀን ጨቅላ ሕጻናት ይገኛሉ፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊትም በዲገሉ ማርያም ቤተክርስቲያን አምስት ምእመናን ሰማዕት ሲሆኑ የሦስት ምእመናን ቤት ተቃጥሏል። በሮቤ አንዲቶ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም አጥቢያ በዓለ ድንግል ማርያምን አክብረው በመመለስ ላይ የነበሩ ሦስት ኦርቶዶክሳዊያን ጨለማን ተገን ባደረጉ ገዳዮች ሰማዕትነት የተቀበሉ መሆኑን ከሀገረ ስብከቱ ሪፖርት ደርሶን ከሐዘናችን ገና ሳንጽናና ይባስ ብሎ በማዕከላዊ ጐንደር ሀገረ ስብከት የጐንደር ዓቢየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት የአቋቋም መምህር የሆኑት መምህር ፍሥሐ አለምነው ባልታወቀ ግለሰብ በድንጋይ ተወግረው መገደላቸው እና ኅዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ከሌሊቱ 11፡00 ላይ የማዕከላዊ ጐንደር ዞን ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት በኲረትጉሃን ዘርዓዳዊት ኃይሉ ባልታወቁ ግለሰቦች በጥይት ተመተው መገደላቸው በእጅጉ ከማዘናችንም በላይ የጉዳዩን አሳሳቢነት የሚያረጋግጥ አድራጐት ሆኗል፡፡
በዚህ መግለጫ በቅርብ የተፈጸመውን ለማቅረብ ተሞከረ እንጅ ተመሳሳይ ግድያና፣ ስደት፣ የንብረት ውድመትና መፈናቀል የየዕለት ዜናችን ከሆነ ሰንብቷል፡፡ ለአብነትም ያህል በወለጋ፣ በጐንደር፣ በጐጃም፣ በወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በመሳሰሉት እየተፈጸመ ያለው ድርጊት መንግሥትና ሕገ መንግሥት ባለበት ሀገር፣ የውጭ ወራሪና ድንበር ተሻጋሪ ጠላት ሳይኖርብን፣ እርስ በርሳችን በምናደርገው መጠፋፋት፣ ሃይማኖት ተኮር ጥላቻዎች፣ የንፁሐን ሕይወት መቀጠፉና የሀገርን ሀብት መውደሙ እኛንም ሆነ በመላው ዓለም መፍቀሬ ሰብእ የሆኑ የሰብዓዊ ክብር አስጠባቂ ተቋማትን ሳይቀር ማሳዘኑ ቀጥሏል፡፡
ይህ ሁኔታ በታሪክ ከመመዝገቡ በላይ የዜጎች በሕይወት የመኖር፣ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የመሥራት፣ የአካልና የንብረት ደኅንነታቸው መጠበቅ፣ የሃይማኖትና የእምነት ነፃነት መከበር፤ የዜጎች ሁለንተናዊ ደኅንነት የመጠበቅና የማስጠበቅ ግዴታ ያለባቸውን አካላት በሙሉ በምድርም ሆነ በሰማይ ተጠያቂ የሚያደርግ ጉዳይ ነው፡፡ እየተፈጠረ ባለው አስከፊ መከራ፣ በጭካኔ የተሞላ ድርጊት፣ ኃላፊነትና ተጠያቂነት ማጣት የዜጎችን ሕይወት፣ አካልና ንብረት፣ የእምነት ተቋማትን፣ መተኪያ የሌላቸው የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ቅርሶችና መስሕቦችን ሲያወድም፣ በሀገር ሁለንተናዊ ደኅንነትና በሕዝቦች ትሥሥር ላይ የፈጠረው አለመተማመን በቀላሉ የማይመለስ አደጋ ነው፡፡
ይኽ እንደተጠበቀ ሆኖ ከተከሰተው ረሀብ፣ ድርቅ፣ የኑሮ ውድነትና ሥራ አጥነት በተጨማሪ በየቦታው በተፈጠሩ አለመረጋጋቶችና ግጭቶች ምክንያት በርካቶች ቀያቸውን ለቀው፣ መነኰሳት ገዳማትን ትተው ተሰደዋል፤ ወላድ እናቶች፣ ሕሙማንና አረጋውያን በሕክምና እጦት እያለቁ ነው፣ ሕፃናትና ወጣቶች ከጤናማ እድገትና ከትምህርት ገበታ ተደናቅፈዋል፣
በመሆኑም
፩. ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ከግጭትና ከጦርነት፣ ከርስ በርስ መገዳደል ወጥተው በውይይትና በምክክር፣ በኃላፊነትና በተጠያቂነት ስሜት የታላቋን ሀገር መልካም ስምና ክብር እንዲሁም የዜጎቿን ሁለንተናዊ ደኅንነት የመጠበቅና የማስጠበቅ ተግባር ቅድሚያ እንዲሰጡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
፪. በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ንፁሐን ምእመናንና ተቋማት ላይ ያተኮሩ ጥቃቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ፣ መንግሥትና የሚመለከታችሁ ሁሉ ዋስትና እንድትሰጡ፣ ወንጀል ፈጻሚዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ ድርጊቱንም መላው ዓለም እንዲያወግዘው ቋሚ ሲኖዶስ በአጽንዖት ይጠይቃል፡፡
፫. ከቤተ ክርስቲያን አልፎ የሀገርና የዓለም ሀብት የሆኑ ቅዱሳን መካናት፣ እንደ ዝቋላ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም፣ አሰቦት ደብረ ወገግ አቡነ ሳሙኤል ገዳም እና አካባቢው፣ ደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ገዳምና አካባቢው የመሳሰሉ ሁሉ ታላላቅ አድባራትና ገዳማት አደጋ የተጋረጠባቸው በመሆኑ ልዩ ጥበቃ እንዲደረግላቸው እናሳስባለን።
፬. በመጨረሻም በየቦታው የሚያጋጥሙ ተመሳሳይ ጥቃቶችን ለማስቀረት ይቻል ዘንድ የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት ለቅድመ ወንጀል መከላከል ሥራ ቅድሚያ በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እያሳሰብን ለቅድመ ወንጀል መከላከል ሥራው መሳካትም በየደረጃው ያላችሁ አህጉረ ስብከት የስጋት መረጃዎችን ለሚመለከተው ሁሉ በማሳወቅ ግዴታችሁን እንድትወጡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
ልዑል እግዚአብሔር አምላካችን ለሞቱት የተዋሕዶ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን አስበ ሰማእትታን እንዲከፍልልን፣ ለወገኖቻቸው ሁሉ መጽናናት እንዲሰጥልን፣ ስለስሙና ስለሰብዓዊ ማንነታቸው በመከራና ሥጋት ወስጥ ለሚገኙ ወገኖቻችን ሁሉ ጽናቱንና ብርታቱን እንዲሰጥልን፣ አጥፊዎችን እንዲገስጽልን፣ ስደትና አለመረጋጋትን እንዲያርቅልን፤ የሀገራችንን አንድነትና ሰላም፣ የቅድስት ቤተክርስቲያንን ሕልውና እንዲጠብቅልን የአምላካችን የልዑል እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
ታኅሣሥ 1 ቀን 2016 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስበከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ለተፈናቀሉ ሕዝቦች ድጋፍ አደረጉ።
ታህሳስ 1 /2016 ዓ.ም
ብፁዕነታቸው ዕርዳታውን የሰጡት ትናንት እሑድ ኅዳር 30/2016 ዓ.ም ለሐዋርያዊ ጉዞ ወደ ገጠሪቱ የደቡብ ኦሞ አካባቢ በዳሰነች ወረዳ ቡቡአ ቀበሌ በሔዱበት ወቅት ነው።
በብፁዕነታቸው የተመራው ይህ ሐዋርያዊ ጉዞ ዕርዳታውን ከ850 በላይ ለሆኑ በኦሞ ወንዝ መሙላት ለተፈናቀሉት ማኅበረሰቦች ከሰጠ በኋላ በአደጋው ከመኖሪያ አካባቢ ርቀው በችግር ላይ ለሚገኙት ወገኖች ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የማጽናኛ ትምህርትና ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋል።
ይህ የብፁዕነታቸው ሐዋርያዊ ጉዞ የቀጠለ ሲሆን በዛሬው ዕለት ታኅሣሥ 01/2016 ዓ.ም የአሪ ማኅበረሰቦችን በመባረክና ቃለ እግዚአብሔርን በማስተማር በጉብኝት ላይ ይገኛሉ።
ብፅዕነታቸው በሚመሩት ሀገረ ስብከት ከሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅና ሌሎች አገልጋዮች ጋር ባደረጉት ሐዋርያዊ አገልግሎት ከተለያዩ ቤተ እምነቶች የመጡ 25,041 ሕዝብ አጥምቀው ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን መመለሳቸው የሚታወስ ነው።
መረጃውን ከቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የፌስቡክ ገጽ አግኝተነዋል።
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የበኩረ ትጉኃን ዘርዓዳዊት የቀብር ሽኝት ሥነ ሥርዓት በጎንደር ከተማ ተካሄደ !
ታኅሣሥ 1 ቀን 2016 ዓ.ም
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የነበሩት የበኩረ ትጉሃን ዘርዓዳዊት የቀብር ሽኝት ሥነ ሥርዓት በጎንደር ከተማ ተካሄደ።
በሸኝት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የጎንደር ከተማ አስተዳር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ደብሬ የኃላ እንደተናገሩት በበኩረ ትጉኃን ዘርዓ ዳዊት ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሃዘን ገልፀው አባታችን በህይወት እያሉ መልከም ሥራዎችን ሰርተዋል ብለዋል።
ወንጀለኞችን ለመያዝ የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ እየተሰራ ሲሆን ሕብረተሰቡ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመቀናጅት ወንጀሎችን ለፍርድ ለማቅረብ በትብብር ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በመምህር በኩረ ትጉሃን ዘርዓዳዊት ዕረፍት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።
የቤተክርስቲያን ዐይን ነበሩ የሀገረ ስብከታችን ሥራ አስኪያጅ ያሉት ብፁዕነታቸው ሥራ ወዳድ እና ሰው አክባሪ አባት ነበሩ ብለዋል።
ብፁዕነታቸው ተጠርጣሪዎችን ሕዝቡ አጋልጦ ሊሰጥ እንደሚገባው አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ሲል የጎንደር ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው የዘገበው።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም ለሐዋርያዊ አገልግሎት እስራኤል ገቡ።
ዘጋቢ ዲ/ን ሙሉዓለም ዐሥራት
(#EOTCTV ታኅሣሥ ፩ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም ቴልአቪቭ እስራኤል)
+++++++++++++++++++++++++++++++++
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፥ የባህር ዳርና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ዻዻስ በእስራኤል ቴልአቪቭ ቤንጎርዮን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስና በገዳማቱ በሚያገለግሉ አበው መነኮሳት አቀባባል ተደርጐላቸዋል።
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ለአምስት ቀናት በሚያደርጉት ሐዋርያዊ አገልግሎት ከእስራኤል የሃይማኖት ሚንስትር፥ የቱሪዝም ሚንስትርና ከአይሁድ እምነት መሪዎች ( ራብአዮች) ጋር በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ።
በተጨማሪም በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳማት ከሚያገለግሉ መነኮሳት ጋር ገዳማቱ አንድነታቸው ተጠብቆ ሰላምና ፍቅር የነገሠበት አገልግሎት እንዲሰጡና ይህንንም ለመፈጸም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ዻዻስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ስለሚደረገው ድጋፍ ይወያያሉ።
በተጨማሪም የገዳሙ ሰላምና የማኅበረ መነኮሳቱ አንድነት ተጠብቆ አገልግሎቱ እንዲከናወን መመሪያም ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
++++++++++++++++++++++++++++++++
