cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ሥርዓተ ቤተክርስቲያን Tube

https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw #subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
35 051
Suscriptores
+13924 horas
+9457 días
+2 03030 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

በዚህ የtiktok ገጽ ላይ የሁሉንም አገልግሎቶች በድምጽ ታገኛላችሁ! like follow እና shear እንዳይረሳ!🥰
Mostrar todo...
🔔✝ ከመምህራን የማንን ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇 ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ምሕረተአብ አሰፋ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ዘበነ ለማ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ሄኖክ ኃይሌ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ዮርዳኖስ አበበ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 አባ ገብረ ኪዳን ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ያረጋል አበጋዝ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር እዮብ ይመኑ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔መምህር ገብረ እግዚአብሔር ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔መምህር አባ ገብረ ኪዳን ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ 🔗የሁሉንም መምህራን ትምህርት ለማግኘት🔔 🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
Mostrar todo...
ትምህርቶችን ለማዳመጥ
🌹ዐርብ በዘጠኝ ሰዓት🌹 አቡን ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ሶበ ሰቀልዎ(፫) ለእግዚእነ ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ ዬ ዬ ዬ አድለቅለቀት ምድር ወተከሥቱ መቃብራት። "ለከ ሃይል"ን በል ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ምንባብ ይነበባል። ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል በዜማ እየተሰገደ ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ : ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ : ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ። ዲያቆኑ ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ከ ግብረ ሕማማት በውርድ ንባብ ይበል። ሶስት ካህናትና አንድ ዲያቆን ጥቁር ልብሰ ተክህኖ ለብሰው በስዕለ ስቅለት ፊት ይቀመጡ : ከአንዲት መብራት በቀር ሌላውን ያጥፉና አንድ ግምጃ በራሳቸውና ገፃቸው ላይ ያድርጉ (ምዕመናን ደግሞ በነጠላቸው ይሸፈኑ) : አንገታቸውን ዝቅ አድርገው በዕዝል ዜማ በታላቅ ድምጽ በሀዘንና በፍርሃት በለቅሶና በዕንባ ጭምር ካህኑና ሕዝቡ በመቀባበል "አምንስቲቲ"ንና "ተዘከረነ እግዚኦ"ን እያንዳንዱን ሦስት ሦስት ጊዜ ይዝለቁ : እስከ አራት ዙር (አጠቃላይ ቊጥሩ ፸፪ እስኪሞላ ድረስ) ይበሉ : እንደገናም "አምንስቲቲ"ንና "ተዘከረነ እግዚኦ"ን እያንዳንዱን አንድ አንድ ጊዜ በመቀባበል በሁለት ዙር (አጠቃላይ ቊጥሩ ፲፪ እስኪሞላ ድረስ) ይበሉ : ዲያቆኑም በየክፍሉ በሐዘን ዜማ (በውርድ ንባብ) እያስገባ ያንብብ። ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል አምንስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ አምንስቲቲ ሙዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ : ተዘከረነ እግዚኦ ኦ ሊቅነ : ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ። ይ.ሕ በከመ ተዘከርኮ ለፈያታዊ ዘየማን እንዘ ሀሎከ ዲበ ዕፀ መስቀል ቅዱስ። ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፷፰ : ፳፮ ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ ወአስተዩኒ ብሒዐ ለጽምዕየ ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ : ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በኅብረት ይበሉ። ማቴ: ፳፯ : ፵፮ - ፶ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት : ጸርሐ ኢየሱስ በቃሉ ወይቤ ኤሎሄ ኤሎሄ ማር: ፲፭ :፴፬ - ፴፯ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት : ገዓረ ኢየሱስ በቃሉ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ። ሉቃ: ፳፫ : ፵፭ - ፵፯ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት : ከልሐ ኢየሱስ በቃሉ ወአማኅጸነ ነፍሶ ሶቤሃ። ዮሐ: ፲፱ : ፳፰ - ፴ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት : አጽነነ ርእሶ ኢየሱስ ወይቤ ተፈጸመ ኲሉ። ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ አዘጋጅ ✍#ዲያቆን ፍቅረ አብ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!! https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw #subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆 ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ 💛 @seratebtkrstian 💚 💛 @seratebtkrstian 💚 💛 @seratebtkrstian 💚 💙💙💙💙💙💙💙💙💙 🙏join👍
Mostrar todo...
🌹ዐርብ በአስራ አንድ ሰዓት🌹 አቡን ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ንዜኑ (፫) ዘአምላክነ ኂሩተ ትሕትና ወየውሃተ ዘእንበለ ዐቅም ዬ ዬ ዬ እንዘ ይጼዕልዎ ኢጸዐሎሙ እንዘ ያሐምምዎ ኢተቀየሙ። በዚህ ሰዓት "ለከ ሃይል ፣ ኪርያላይሶንና መልክዐ ሕማማት" የለም። የሰዓቱን ምንባባትም በቅዳሜ ሌሊት ማንበብ ይቻላል። 🌹ሥርዓተ እግዚኦታ🌹 ካህናቱ ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው ሥርዓተ ግንዘትን ይስሩ : ሦስት ካህናትም ሥርዓተ ግንዘቱን በእጃቸው አቅፈው ይያዙት : አንድ ካህን መስቀልና ጽንሐሕ ይዞ በኋላቸው ይከተል : አንድ ዲያቆን ደግሞ መስቀልና መብራት በመያዝ ፊት ለፊት ይምራ : በምዕራብ በኩል ፊታቸውን ወደ ምሥራቅ አዙረው ይቁሙ : ከዚህ በኋላ በአራቱም ማዕዘናት እየዞሩ እግዚኦታ ያድርሱ አደራረሱም ካህናቱና ሕዝቡ በግራና በቀኝ በአራቱም አቅጣጫ በአራት ተመድበው በመቆም:- በዐቢይ ዜማ አምስት አምስት ጊዜ : በንዑስ ዜማ ባለአምስቱን ዘጠኝ ዘጠኝ ጊዜ : እንደገና በዐቢይ ዜማ አምስት አምስት ጊዜ : በንዑስ ዜማ በእንተ ማርያም ዘጠኝ ዘጠኝ ጊዜ። ምሕላው ከተፈጸመ በኋላ ካህኑ "አቡነ ዘበሰማያት" ይስጥ : እስከ ትንሣኤ ድረስ የኑዛዜ ጸሎት ስለሌለ ካህኑ ፵፩ ጊዜ ኪርያላይሶን ይበል : ሕዝቡም እንደርሱ ይበሉ። #ከዚህ_በኋላ_በቅኔ_ማኅሌት_ሁሉም_ይሰብሰቡ_መቋሚያ_ይዘው_በመካከላቸው_ጧፍ_አብርተው_ይያዙ_የዳዊትንና_የነቢያትን_ጸሎት_እየተቀባበሉ_ያንብቡ_አንብበው_ሲጨርሱ_በመካከላቸው_ያለውን_መብራት_በያዙት_መቋሚያ_ያጥፉት_የዲያቢሎስ_ገዢነት_መደምሰስ_ምሳሌ_ነው_ከዚያም_መዘምራን_ንሴብሖን_ይዘምሩ_ካህናትም_ሕዝቡን_በወይራ_ቅጠል_እየጠበጠቡ_እና_ስግደት_እያዘዙ_ወደ_ቤታቸው_ይሸኟቸው። አዘጋጅ ✍#ዲያቆን ፍቅረ አብ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!! https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw #subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆 ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ 💛 @seratebtkrstian 💚 💛 @seratebtkrstian 💚 💛 @seratebtkrstian 💚 💙💙💙💙💙💙💙💙💙 🙏join👍
Mostrar todo...
ዐርብ ጠዋት በ፫ ሰዓት አቡን ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) አርዑተ መስቀል ፆረ (፪) ይስቅልዎ ሖረ ዬ ዬ ዬ ከመ ኪያነ ይቤዙ እግዚእ ኮነ ገብረ። "ለከ ሃይል"ን በል ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል። ዲያቆኑ መዝሙር ፴፬ትን ፫ ቦታ ከፍሎ በውርድ ንባብ ይበል። ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል እየተሰገደ:- ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ ጽብኦሙ እግዚኦ ለእለ ይጸብኡኒ ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ ይ.ዲ ምስባክ:- መዝ: ፳፩ : ፲፮ ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን ወአኃዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን። ማቴ: ፳፯ : ፲፭ - ፲፯ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ፫ቱ ሰዓት : አኃዝዎ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ። ማር: ፲፭ : ፮ - ፲፭ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ፫ቱ ሰዓት : አሕየወ ሎሙ በርባንሃ ወወሀበ ሎሙ ኢየሱስሃ ይስቅሉ። ሉቃ: ፳፫ : ፲፫ - ፳፭ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ፫ቱ ሰዓት : ወሰድዎ ለኢየሱስ ውስተ ዓውደ ምኲናን። ዮሐ: ፲፱ : ፩ - ፲፪ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ፫ቱ ሰዓት : ቀሠፎ ጲላጦስ ለኢየሱስ ወመጠዎሙ ይስቅልዎ። ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚህ በኋላ የሰዓቱን መልክዓ ሕማማት ያድርሱ። አዘጋጅ ✍#ዲያቆን ፍቅረ አብ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!! https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw #subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆 ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ 💛 @seratebtkrstian 💚 💛 @seratebtkrstian 💚 💛 @seratebtkrstian 💚 💙💙💙💙💙💙💙💙💙 🙏join👍
Mostrar todo...
🌹ዐርብ በስድስት ሰዓት🌹 አቡን ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ተሰቅለ (፫) ወሐመ ቤዛ ኲሉ ኮነ ዬ ዬ ዬ በመስቀሉ ቤዘወነ እሞት ባልሐነ። "ለከ ሃይል"ን በል ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል። ዲያቆኑ ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ከገላትያ በውርድ ንባብ ይበል። ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል በዜማ እየተሰገደ:- ለመስቀልከ ንሰግድ ኦ ሊቅነ : ወለትንሣኤከ ቅድስት ንሴብሕ ኲልነ : ይእዜኒ ወዘልፈኒ። ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፳፩ : ፲፮ ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ ወኆለቊ ኲሎሙ አዕፅምትየ ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ : ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በኅብረት ይበሉ። ማቴ: ፳፯ : ፳፯ - ፵፭ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ፮ቱ ሰዓት : አልበስዎ አልባሲሁ ለኢየሱስ ወወሰድዎ። ማር: ፲፭ : ፲፮ - ፴፫ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ፮ቱ ሰዓት : ዐበጥዎ ለስምኦን ከመ ይፁር መስቀሉ። ሉቃ: ፳፫ : ፳፯ - ፵፬ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ፮ቱ ሰዓት : ሰቀልዎ ለኢየሱስ በቀራንዮ መካን። ዮሐ: ፲፱ : ፲፫ - ፳፯ ከተነበበ በኋላ ጊዜ ፮ቱ ሰዓት : ቀትር ሶቤሃ ሊቃነ ካህናት ሰቀልዎ ለኢየሱስ ማዕከለ ፪ኤ ፈያት። ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚህ በኋላ የሰዓቱን መልክዐ ሕማማት ያድርሱ። አዘጋጅ ✍#ዲያቆን ፍቅረ አብ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!! https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw #subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆 ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ 💛 @seratebtkrstian 💚 💛 @seratebtkrstian 💚 💛 @seratebtkrstian 💚 💙💙💙💙💙💙💙💙💙 🙏join👍
Mostrar todo...
#ሥርዓተ_ጸሎት_ወስግደት_ዘዓርብ_ስቅለት ዐርብ ጠዋት በ፲፪ ሰዓት አቡን ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ነአምን ሕማሞ ለዘኢየሐምም ርግዘተ ገቦሁ ነአምን ወቅንዋተ እደዊሁ ነአምን ዬ ዬ ዬ ነአምን ሞቶ ወትንሣኤሁ። "ለከ ሃይል"ን በል ከኦሪት ምንባብ እስከ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል። ምስባክ መዝ: ፳፮ ፣ ፲፪ እስመ ቆሙ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ ወሐሰት ርዕሰ ዐመፃ እስመ ቆሙ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በዜማ በኅብረት ይበሉ:- ማቴ: ፳፯ : ፩ - ፲፬ ከተነበበ በኋላ ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት : ይስቅልዎ ለኢየሱስ ዲበ ዕፀ መስቀል። ማር: ፲፭ : ፩ - ፭ ከተነበበ በኋላ ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት : አውጽእዎ አፍአ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ። ሉቃ: ፳፪ : ፷፮ - ፸፩ ከተነበበ በኋላ ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት : አውጽዕዎ ለኢየሱስ ወመጠውዎ ለጲላጦስ። ዮሐ: ፲፰ : ፳፰ - ፵ ከተነበበ በኋላ ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት : አውጽዕዎ ለኢየሱስ ወነበረ ዐውደ ሶቤሃ። ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚህ በኋላ የሰዓቱን "መልክዐ ሕማማት" ያድርሱ። የ12 ሰአቱ ስግደት ተፈጸመ የ3 ሰአት ይቀጥላል...... አዘጋጅ ✍#ዲያቆን ፍቅረ አብ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ቻናል!! https://www.youtube.com/channel/UCyyw8be1uLS-PdwVLd-zyKw #subscribe ያርጉ ይቀላቀሉ እና ይማሩ👆👆👆 ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ 💛 @seratebtkrstian 💚 💛 @seratebtkrstian 💚 💛 @seratebtkrstian 💚 💙💙💙💙💙💙💙💙💙 🙏join👍
Mostrar todo...
🔔✝ ከመምህራን የማንን ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇 ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ምሕረተአብ አሰፋ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ዘበነ ለማ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ሄኖክ ኃይሌ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ዮርዳኖስ አበበ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 አባ ገብረ ኪዳን ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር ያረጋል አበጋዝ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔 መምህር እዮብ ይመኑ ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔መምህር ገብረ እግዚአብሔር ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ ┏━━━━━━━━━━━━━━┓ 🔔መምህር አባ ገብረ ኪዳን ┗━━━━━━━━━━━━━━┛ 🔗የሁሉንም መምህራን ትምህርት ለማግኘት🔔 🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
Mostrar todo...
ትምህርቶችን ለማዳመጥ
Mostrar todo...
መንግስት
ሠርግ
ሕዳር
ምሕረት
ሀጢአት
ትምሕርት