cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Sena Fashion

4 እና ከዛ በላይ ላዘዙን ያሉበት ድረስ እናቀርባለን. Address. 906418283

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
434
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

4.22 KB
Join join join
Mostrar todo...
b621
Mostrar todo...
Mostrar todo...

Learn how the Biden-Harris Administration is tackling our nation’s challenges and building our country back better from this crisis.

8.01 KB
Watch "HIndake Daniel" on YouTube https://youtu.be/EBJRgVAZeYE
Mostrar todo...

┈┈••◉❖◉●••┈ ፍቅር ያሸንፋል🌺 ❣️ :¨·....................:¨·.❣️ 💢ክፍል 3❣️እውነትኛ የፍቅር ታሪክ አባዬ ገብቶ ሁኔታዬን ሲያይ በጣም ነበር የደነገጠው እንባዬን አይቶ አይኖቹ እምባ ሲያቀሩ ተመለከትኩ ከዛ መቶ ያባትነቱን እያቀፈኝ ወረቀቱን ተቀበለኝና ወደ ጠረጴዛ ላይ ወርወር አርጎት ልጄ ምን ሆነሽ ነው ውጤት ተበላሽቶብሽ ነው? ሲል ጠየቀኝ እኔም ይበልጥ ሆድ እየባሰኝ ምንም ሳልመልስለት ለቅሶዬን ቀጠልኩ አባቴ ቢማር ኖሮ ደብዳቤውን በማንበብ ለምን እንደማለቅስ ያውቅ ነበር ግን እሱ ሳይማር እኔን እያስተማረ ነው፡፡ እኔ ደግሞ የማላገኘውን ሰው አፍቅሬ መንገዴ ሊበላሽ ነው እኔ መሆን የምፈልገው ቤተሰቦቼ እንድሆን የሚፈልጉትን ነው ግን መሀል ላይ ምርጫ የሌለው የተፈጥሮ ግዴታ ላይ ወደኩ፡፡ አባቴ ምክንያቴን ሳያውቅ አባብሎኝ ብቻ ያ ቀን ነጋ ትምህርት ቤት መሄድ ግድ ነውና ጠዋት ቦርሳዬን አንግቤ ወደ ትምህርት ቤት መንገድ ጀመርኩ ይሄኔ ነበር ወደትምህርት ቤታችን መታጠፍያ ጋር ስደርስ ድንገት ካሌብን አገኘሁት እየጠበቀኝ እንደነበር ያስታውቃል እኔ ግን ሳየው ልቤ ለሁለት ስንጥቅ ነበር ያለው ያስሚ አለኝ ቆም አልኩኝ የኔ ቆንጆ ናፍቀሽኝ ነው በጥዋት የመጣሁት አለኝ ዝም አልኩ አላስጨንቅሽም እሺ ፍቅር የጋራ ስሜት ነው ስለዚህ ሲል አቋርጬው ትቼው መንገድ ጀመርኩ በትክክል ማሰብ አልቻልኩም ግራ ተጋባሁ ይሄኔ ካሌብ ካንደበትሽ መስማት አያስፈልገኝም የኔ ቆንጆ ፍቅሬን ባትቀበይም አንቺን ማፍቀሬን ግን እቀጥላለሁ አለና አልፎኝ ወደ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ገባ፡፡ ክፍል ገብቼ መማር አቃታኝ ግን እንደምንም እረፍት ደረሰ ተደብቄ ላየው ወደ ኳስ ሜዳ ሄድኩ ግን ብቅ እንኳ ሳይል እረፍት አለቀ ምሳ ሰአትም ጠበኩት ግን የሚወደው መረብ ኳስ እንኳ አስጠልቶታል ነበር ፡፡ 2 ቀን በተደጋጋሚ ሳንገናኝና ካሌብን ሳላየው አደርኩ ከዛ በላይ ግን ሳላየው መቆየት አልቻልኩም ክፍላቸው ሄጄ ካጣሁት እቤታቸው ልሄድ ወሰንኩ ከዛም ልክ እረፍት ስንለቀቅ ክፍላቸው ሄድኩ ያኔ ይበልጥ የምሩን እንዳፈቀረኝ አረጋገጥኩ ፡፡ ካሌብዬ ብቻውን ተቀምጦ ትክዝ ብሎ የነበረ ልክ ስንተያይ ሁለታችንም ደነገጥን ከዛ ማንም ማንንም ሳያናግር ተቃቀፍን እኔ እምባዬን መቆጣጠር አቃተኝ ጥቂት ተቃቅፈን ከቆየን ቡሃላ ካሌብዬ አልኩት ወዬ አለኝ አይኖቼን ለማየት ከደረቱ ቀና እያረገኝ እወድሃለው አልኩት ይሄኔ በደስታ የሚያደርገው ጠፋው እኔና ካሌብዬ በዚ መልኩ ፍቅር ጀመርን ሁሌም በድብቅ ቢሆንም እንገናኛለን ሰፈሬ ድረስ ይሸኘኛል ግን የኔና የሱን ፍቅር ያወቀችው የቃላብ እህት ሜሮን ብቻ ነች እሷም ሁሌም ከጎናችን ሆና ትረዳናለች ይህ በንዲህ እንዳለ እኔ 9ኛ ክፍል ስደርስ እሱ ደግሞ 12ን ተፈትኖ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ደረሰው ይሄኔ ሁለታችንም በጣም አዘንን የምናደርገው ግራ ገባን ትምርቱ ይቅርብኝ እንጂ ትቼሽ አልሄድም አለ እኔ ደግሞ የለፋበት እንዲቋረጥ አልፈልግም አልኩትና ተለያየን ይህ በንዲህ እንዳለ አንድ ቀን ምሽት ላይ ካሌብዬ በሜሮን አስጠራኝ እኔም በጣም ናፍቆኝ ስለነበር እነ አባዬ ሳያዩኝ ወጣሁ ልክ ሳየው እሩጬ ተጠመጠምኩበት ሁሌም ሳገኘው ሁሉን ነገር እረሳለው ተጠምጥሜበት አንድ ቁጥር መስለን ያለወትሮዬ አለማችንን እየቀጨን እያለ ፍርቅራችንን አጣጥመን እንኳ ሳንጨርስ ፈተና ገጠመን በምሽት ስወጣ የተጠራጠረው አባዬ ተከትሎኝ ኖሯል ለካ ያስሚን ያስሚን ብሎ የሚጣራ ድምፅ ስሰማ የአባዬ ድምስ መሆኑን ተጠራጥሬ ዞር ስል አባዬን ሳየው የደነገጥኩት ድንጋጤ እና የተሠማኝ ፍርሀት ሽንቴን ልለቀው ደረስኩ ወንድ ቀና ብዬ እንዳላይ አድርጓ ሲያስጠነቅቀኝ አሳድጓኝ ኖሮ ዛሬ ይህን ሲያይ ምን ሊያረግ ሊሆን እንደሚችል መገመት ተሳነኝ ሁለታችንም ደርቀን ባለንበት ቀረን....... ✎ ክፍል አራት ከ300 View♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ share♥️ ማድረግ አይርሱ። ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»✽̶┉┉┄┄
Mostrar todo...
Cᴏᴜᴘʟᴇ quotes ♥️︎

Join for daily couple vibes, love quote and all that good stuff 😍 For comment 👉 @couple_vibesbot ☢️ friendly channel ↪️ @Likeemood

┈┈••◉❖◉●••┈ ፍቅር ያሸንፋል🌺 ❣️ :¨·....................:¨·.❣️ 💢ክፍል 2❣️እውነትኛ የፍቅር ታሪክ ካሌብ ከትምህርት የቀረው አሞት እንደነበር ለማወቅ ብዙ ደቂቃ አሎሰደብኝም ነበር አይኑን ካየሁት በኋላ ከዚ በላይ መቆየት ስለሌለብኝ ደግሞም እቤት ብዙ ከቆየው ስለምቆጣ ወጥቼ ወደቤት መሄዴን ቀጠልኩ፡፡ በየመንገዱ ግን የማስበው ስለሱ ነበር ሜሪዬ ቆንጂዬ ጓደኛ አለሽ ያላትን ሳስታውስ ደስታዬ እጥፍ ይሆናል እቤት እንደገባው ፊቴን አስሬ በመስታወት እያየው ግንኮእውነትም ቆንጆ ነኝ! እላለው፡፡ ከዛ ቀን ቡሃላ ካሌብዬ አወቀኝ እኔም ፍቅሬ ጨመረ ይባስ ብሎ አንድ ቀን እሱን ለማየት እንደለመድኩት ሜዳ ሄድኩ ይሄኔ እየተጫወቱ ነበር እኔም ከሩቅ ተመስጬ ማየቴን ቀጠልኩ ይሄኔ ካሌብ የመረብ ኳሱን የመጀመሪያ ውጤት አስመዘገበ የእውነት ማንም ባያየኝም ከልቤ ነበር የተደሰትኩት፡፡ በዚ ሰአት በቅፅፈት አንዲት ቆንጂዬ ሴት እሩጣ ተጠመጠመችበት በጣም ደንግጬ ይሁን ተናድጄ ሳይታወቀኝ ከተቀመጥኩበት ብድግ አልኩ አይኔ እምባ አቀረረ ቀናሁ መሰለኛ ከዛ ወደነሱ ሄድኩ ለምን እንደሄድኩ ግን እኔም አልታወቀኝም ልክ ሲያየኝ ያስሚንዬ የኔ ልእልት ብሎ ጉንጬን ሳመኝና እዚ ምን ትሰርያለሽ ሲል ጠየቀኝ ይሄኔ መልስ ስላልነበረኝ ድንገት ከአፌ መቶልኝ መረብ ኳስ እወዳለው ለዛ ነው አልኩት ኦ አንድ አይነት ስሜት አለን ታዲያ እሷ ቤቲ ትባላለች ጓደኛዬ ናት ብሎኝ ካስተዋወቀኝ በኋላ እና መረብ ኳስ ደግሞ መልመድ ከፈልግሽ አስለምድሻለው እሺ አለኝ በጣም ከመደሰቴ የተነሳ መቼ ነው አልኩት ከፈለግሽ ከትምህርት ቡሃላ ከፈለግሽ ብሎ ገና ሳይጨርሰው በረፍትም አልኩት እሱም በዕረፍት ሰዓት ሊያለማምደኝ እሺ አለኝ፡፡ ጓደኛዬ ናት ስላላት ልጅ ሳስብ ስናደድ ኳስ አስለምድሻለው ያለኝን ሳስብ ስደሰት የዋልኩበት ያን ቀን መሽቶ ነጋ በኳስ ስበብ አብሬው መቆየቴ ለኔ ትልቅ ደስታ ስለነበር እረፍት ደርሶ እስክወጣ ቸኮልኩ ከዛ ለሜሮን አሁንም የምሄድበትን ሳልነግራት ሄድኩ ስደርስ አሁንም ያቺ ቤቲ የምትባል ሴት አለች ከሩቅ አይቻቸው ስመለስ ካሌብ አይቶኝ ስለነበር ወደኔ እየሮጠ መጥቶ ያስሚ ብሎ ሲጠራኝ ሄጄ መቅናቴን ለመሸሸግ እየሞከርኩ ፈገግ ብዬ ሰላም አልኩት ያን ቀን እንደኔ ደስተኛ ያለ አልመስልሽ አለኝ ምክንያቱም ስለ ቤቲ ያወኩበት ቀን ነበር የሆነውም ደግሞ እየተናደድኩኝ እና ውስጤ እየተቃጠለ እኔ የምልክ ካሌብ ቆንጆ እና ተጫዋች ፍቅረኛ አለችክ ስለው አረ 10qw ሲለኝ ፊቴ መለዋወጥ ሲጀምር አረ ስቀልደሽ ነው ብሎኝ ቤቲ ፍቅረኛው ሳቶን ጓደኛው እንደሆነች ነገረኝ፡፡.…ካሌብ በጣም ጎበዝ ተማሪ ስለነበር ከሜሮን ጋር አብሬ ላስጠናቹ ሲለኝ ደስተኛ ሆኜ ነበር እሺታዬን የገለፅኩት በዚ መልኩ ማፍቀሬ እንዳይታወቅ እየተጠነቀኩ ቀናቶች እሩጫቸውን ቀጠሉ፡፡ ታድያ አንድ ቀን እነ ካሌብ ቤት እንደተለመደው ለማጥናት ስሄድ እንደድንገት ሆኖ ሜሮን አልነበረችም ነበር እናም እኔና ካሌብ ስለነበርን ካሌብ እኔን ያስጠናኝ ጀመር፡፡ እናታቸው ደግሞ በጣም ስለምትወደኝ አልፈራትም ነበር እዛ ቤት ስሄድ እንደቤቴ ነበር የምቆጥረው ከዛ እሱ እያስረዳኝ እኔ ግን ሀሳቤ ግን ጥናቱጋር ሳይሆን አይን አይኑን እያየውት ተመስጬ ምናለ ሀይማኖታችን አንድ ሆኖ ፈጣሪ እሱን ለኔ ቢፈቅድልኝ እጣ ፈንታዬ ባረገው አልኩ በውስጤ ብዬ ልስመው ፈለጉና ወደሱ ጠጋ ስል እሱም ገብቶታል መሰልኝ ወደ እኔ ጠጋ ሲል ሲታወቀኝ ጊዜ ሰውነቴ የሆነ ስሜት ሲሰማኝ ከተቀመጥኩበት ስነሳ ካሌብን እንደመደንገጥ ብሎ ይቅርታ አስቤው አይደለም ሲለኝ its ok ብዬው እሱግ ድንጋጤው ስላልለቀቀው ወሬ ማስቀየስ ፈለኩና በላ አሁን ምን ትጠብቃለክ አስተናኝ እንጂ ቢዬው ከዛን ወደጥናታችን ተመልሰን ከዛ ልክ ስንጨርስ ወደቤት ሄድኩ ቤት ገብቼምመኝታ ክፍሌ ውስጥ የቤት ስራ ልሰራ የሂሳብ ደብተሬን ስገልጠው አንድ ሁለት ቦታ የታጠፈ ወረቀት አገኘሁ ልቤ ድንግጥ አለና ገለጥኩት የቃልዬ ፅሁፍ ነው፡፡ "ቅድም በተፈጠረው ነገር ያስሚኒዬ ይቅርታ አርጊልኝ እኔ ለአንቺ እንደወንድምሽ ሊሆን ይችላል የምታይኝ እኔ ግን አንቺን በቃ አፍቅሬሻለው መልስሽ ምንም ይሁን ምን አፈቅርሻለሁ "ይላል በድንጋጤ ከተቀመጥኩበት ተነሳው ወረቀቱን አተኩሬ ተመለከትኩት ቤተሰቤን አሰብኩ ፍቅሬንም አሰብኩ ሳላስበው ትኩስ እምባ በጉንጮቼ ይወርድ ጀመር ይሄኔ አባዬ በሩን ከፍቶ ገባ ወረቀቱን በጄ እንደያዝኩ ደርቄ ቀረሁ...… ✎ ክፍል ሶስት ከ300 View በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ share ማድረግ አይርሱ።❤️ ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»✽̶┉┉┄┄
Mostrar todo...
Cᴏᴜᴘʟᴇ quotes ♥️︎

Join for daily couple vibes, love quote and all that good stuff 😍 For comment 👉 @couple_vibesbot ☢️ friendly channel ↪️ @Likeemood

┈┈••◉❖◉●••┈ ፍቅር ያሸንፋል🌺 ❣️ :¨·....................:¨·.❣️ 💢ክፍል 1 ❣️እውነትኛ የፍቅር ታሪክ ውድ ጓደኞቼ ጥሩ ያልኩትን አስተማሪ የፍቅር ታሪክ መርጬ ለናንተ በሚመች መልኩ ማቅረብ ጀምሬአለው እንደምትወዱት አልጠራጠርም እንድታነቡልኝ እጋብዛለሁ፡፡🌺 ያስሚን ሙሐመድ እባላለው የተወለድኩት አማራ ክልል ወሎ ክፍለ ሀገር ደሴ የምትባል ከተማ ላይ ነው ታድያ ደሴ እናትና አባቴ ጋር ስኖር ደስተኛ ነበርኩ ቤተሰቦቼ ሀብታም ባይባሉም ሌላ ልጅ ስለሌላቸው እኔን በደምብ ይንከባከቡኛል ትምህርትም በግዜ ነበር የገባሁት ፡፡ የልጅነት ህይወቴ ብዙም የተለየ ነገር ስለሌለው ወደ የፍቅር ህይወቴ ልግባላቹ ልክ በ16 አመቴ የ9ኛ ክፍል ተማሪ ሆንኩ ይሄኔ ነበር የኔም የሰውነት ቅርፅ ለውጥ ያሳየው ከዛም ባለፈ እኔ በባህሪዬ ዝምተኛ ስሆን ከሰውነት ቅርፄ ጀምሮ የብዙሃን ሠው ቀልብ የምስብና በሠዎች አስተያየት ውብ የምባል አይነት ሴት ነበርኩ ፡፡ እኔ የእስልምና ሀይማኖት ተከታይ ነኝ ሆኖም ብዙ የክርስትና እምነት ተከታይ ጓደኞች አሉኝ፡፡ እናም ከነሱጋ ነበር አብዛኛውን ጊዜዬን የማሳልፈው የነበረው አንድ ዓመቱን እንዲ ሆኘ ነበር ያሳለፍኩት አዲሱን ዓመት ተቀብለን ክላስ ጀምረን መማር ጀመርኩ። ከዕታት ባንዱ ቀን ክፍላችን ውስጥ እንግዳ ፊት አየሁ ለኔ ለየት ያለብኝ ደግሞ ልክ ሳየው መደንገጤ ነበር ሁሌም በምናቤ የምስለው አይነት ወንድ ከለሩ ቸኮሌት ቁመቱ እረዘም ያለ ፀጉሩ የሚያምር ፍሪዝ አስተያየቱ ልብ የሚሰርቅ ባጠቃላይ ውብ ቃሉ የሚያንስበት ልጅ ነው በርግጥ የኔ የተገናኘን ቀን እድሜዬ 17 አካባቢ ነበር እሱ ደግሞ በግምት 19 አካባቢ ይሆነል እኛ ክፍል የገባው ደግሞ ለምን እንደሆነ ለማጣራት ወደ ክፍል ገብቼ ሳይ ለታናሽ እህቱ እቃ ለመስጠትነበር የመጣው የነበረው፡፡ ስሙ ካሌብ ይባላል የግቢያችን የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነው ያን ቀን ልቤን እንደወሰደ እስካሁን አልመለሰልኝም እሱን ካየሁበት ቅፅበት ጀምሮ መሉ ሀሳቤ እሱ ነው፡፡ እናም እሱን ለማግኘት ስል መጀመርያ ማድረግ ያለብኝ እህቱን ሜሮንን ተዋወኳት ከሜሪ ጋር በጣም ተግባባን ግን ወንድሟን ማፍቀሬን ፈፅሞ አልነገርኳትም ሁሌም ስናወራ በጣም የማፈቅረው ወንድ እንዳለ ስነግራት ሁኔታዬን አይታ ታድሎ ያስሚኔ ትለኛለች፡፡ ካሌብ መረብ ኳስ መጫወት ይወዳል ለዛም እሱን ለማየት ከሜሪ ተደብቄ ኳስ ሜዳ እሄድና አየዋለሁ ሁሌም እሱ የሚገኝበት ቦታ እሄዳለው ሳየው ደስስ ይለኛል ካላየሁት ግን እናቷን እንዳጣች ጥጃ ያረገኛል እነጫነጫለሁ፡፡ ግን አንድ ነገር አውቃለው ከካሌብ ጋር የሀይማኖት ልዩነት አለን ቤተሰቦቼ ደግሞ በሀይማኖት ድርድር አያውቁም ያም ማለት ካሌብን ማፍቀር እንጂ የኔ ማድረግ አልተፈቀደልኝም፡፡ ይህ በንዲህ እንዳለ በተከታታይ 3ቀን ካሌብዬ ትምህርት ቤት ቀረ እሱን ሳላይ ስቀር 3ቱ ቀን አመታት ሆነብኝ ያለኝ ምርጫ ስበብ ፈልጌ ሜሮን ቤታቸው እንድትወስደኝ ዘዴ ማፈላለግ ነበር እናም ተሳክቶልኝ መፅሀፍ ፈልጌ በሚል ሰበብ ከሜር ጋር ቤታቸው ሄድኩ ቤታቸው ያምራል የግቢው በር ተከፍቶ ስንገባ የኔ ካሌብዬ በረንዳው ላይ ቁጭ ብሏል ልክ ሳየው ደርቄ ቀረው ሜሪም ግራ ገብቷት ችግር አለ ያስሚኔ አለችኝ ይሄኔ ነበር ማፍጠጤ የታወቀኝ ካሌብም የታላቅነት ስሜቱ እያንፀባረቀበት ኦኦኦኦኦ ሜሪዬዬ ቆኝጂዬ ጓደኛ አለችሽ አላት እንደሱ ሲላት ይበልጥኑ የደስታ ሲቃ ተናነቀኝ በሱ ደግሞም በምወደው ሰው በካሌብ አፍ ቆንጆ መባሌን ማመን አቃተኝ....... ✎ ክፍል ሁለት ከ50 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
Mostrar todo...
Cᴏᴜᴘʟᴇ quotes ♥️︎

Join for daily couple vibes, love quote and all that good stuff 😍 For comment 👉 @couple_vibesbot ☢️ friendly channel ↪️ @Likeemood

Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.