cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

infoኢንፎ

ከኛጋ ሲሆኑ የሚያገኞቸው # Free Scholarship opportunity # የኳስ HIGHLIGHT # የስራ ማስተዋወቂያዎች # ኢንስፓየረሺን ይፈጥራሉ የምንላችሀወን ወደናንተ ለበለጠ በ @jahhman1 የይቱብ ቻናላችንን ተቀላቀሉንhttps://www.youtube.com/channel/UCVopZwmmmnMYyuzi-d7puIg?sub_confirmation=1 https://www.instagram.com/info

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
198
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የበለጸገች ሀገር ለመገንባት የሚደረገው ጉዞ በራሱ ፈታኝ ነው። ነገር ግን፣ በታላቁ አበበ ቢቂላ በተግባር እንዳየነው፣ ምቹ የሚባለው መንገድ እንኳ ባዶ እግርን ያቆስላል። የጉዞውን ስኬታማነት ራዕይን አጥርቶ በማየት እና በ“ባዶ እግር”ም ቢሆን ጎዳናውን ሳይለቅቁ በመገስገስ ይወሰናል። The road to a new prosperous nation is bound to have its own rough patches. But just as the great Abebe Bekila demonstrated, even the smoothest of roads will give blisters to the barefoot, what matters is the clarity of vision and “barefooted” determination to stay on the course.
Mostrar todo...
ኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ እንዲሳተፍ ፈቃድ የሰጠችው ተቋም ከፍተኛ መጠን ያለው መዋዕለ ነዋይ ወደ አገሪቱ እንደሚያስገባና በርካታ የሥራ ዕድሎችን እንደሚፈጥር ተነገረ። ግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ የተባለውና የስድስት ኩባንያዎች ጥምረት የሆነው ተቋም አገሪቱ ለጨረታ አቅርባቸው ከነበሩት ሁለት የቴሌኮም ፈቃዶች ውስጥ አንዱን በማሸነፍ በዘርፉ እንዲሰማራ መመረጡን የገንዘብ ሚኒስቴርና የኮምዩኒኬሽን ባለሥልጣን ይፋ አድርገዋል። የኬንያው ሳፋሪኮም፣ የዩናይትድ ኪንግደም ቮዳፎን እና ሲዲሲ ግሩፕ፣ የደቡብ አፍሪካ ቮዳኮም፣ የጃፓኑ ሱሚቶሞ እንዲሁም ዲኤፍሲ ናቸው በአገሪቱ በኢትዮ ቴሌኮም ከ120 ዓመታት በላይ በብቸኝነት ተይዞ ወደነበረው ዘርፍ ለመግባት ፈቃድ ያገኙት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በበኩላቸው የተሰጠውን ፈቃድ "ታሪካዊ ውሳኔ" ብለውታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመረጠው ተቋም ከፍተኛ የፈቃድ ክፍያ ዋጋ እና አስተማማኝ የመዋዕለ ነዋይ ፍሰት ዕቅድ እንዳቀረበ ጠቅሰው ይህም "እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ከተደረጉት የውጪ ቀጥተኛ የዋዕለ ነዋይ ፍሰቶች ብልጫ እንዳለው" በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። በዚህም መሠረት የተለያዩ ኩባንያዎች ጥምረት የሆነው ግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ የተባለው ተቋም ከፍተኛውን 850 ሚሊዮን ዶላር በማቅረብ በጨረታው ተመራጭ ሆኗል። ሁለተኛው የቴሌኮም ዘርፍ አዲስ ፈቃድ ሳይሰጥ ቢቀርም በቀጣይ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ ለጨረታ እንደሚቀርብ የገንዘብ ሚኒስትሩ አማካሪ ዶ/ር ብሩክ ለብሉምበርግ ገልጸዋል። (ቢቢሲ)
Mostrar todo...
" ከውድድሩ መጀመር ቀደም ብሎ በዚህ ጉዳይ ላይ ስናወራ ታርጌት ያደረገው ቁጥር #30 ጎል ነበር. . . '' - #አሰልጣኝ_ውበቱ_አባተ አቡበከር ናስር ከዓመቱ የመጨረሻ ጨዋታ በፊት #29 ጎል ላይ ደርሷል።
Mostrar todo...
የታደልነውን ጸጋ እና ዘርፈ ብዙ ባህላችንን ከማየት አልፈን በመተባበር ልንጠቀምበት ያስፈልጋል። በፍቅር፣ በይቅርታ፣ በመተባበር፣ በመደመር መንፈስ አንድ ሆነን ኢትዮጵያን አበልጽገን ለአፍሪካ ተምሳሌት እንሁን።
Mostrar todo...
እንደአባቶቻችን ከተባበርን ማንም አይደፍረንም! - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ #Ethiopia | በአንድነት ፓርክ እየተካሄደ ባለው የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) የአማራ ባህል ማዕከል ግንባታ ማስጀመሪያ ዝግጅት ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያስደንቁ የማዕድን ክምችቶች ቢኖሩም ከመተያየት ባለፈ ጥቅም ላይ ማዋል እንዳልተቻለ ገልጸዋል። በወንድማማች ፓርክ እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ ሳምንት የሚያስደንቅ ባህልና ምግብ መቅረቡንም ተናግረው፤ የትብብር፣ የመጎራረስ፣ አብሮ የመቆም፣ የመደጋገፍ ሁኔታ ላይ ካልተሰራ በስተቀር አሁን ባለው ሁኔታ እንዲሁ በመተያየትና በማዘን ከመኖር ያለፈ ለውጥ ሊመጣ እንደማይችል አስገንዝበዋል። “ይህ እንዳይሆን በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭም በብዙ የሚሰሩብን ሃይሎች አሉ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያን የሃብታም ልጅ በጀርባዋ በተሸከመች ደሃ እናት መስለዋታል። “ከኢትዮጵያ ጋር መስራት እንፈልጋለን የሚሉ ብዙዎች እንዲሁ ትልቅ እያልናችሁ ኑሩ እንጂ ትልቅ መሆን እምብዛም አያስፈልጋችሁም ይላሉ” ሲሉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ “የእነሱን ልጆች አዝለን ማሳደግ ግዴታችን እንደሆነ ስለሚያምኑ ነው” ብለዋል።ኢትዮጵያ ጥያቄዋ በህብረት መልማትና መበልጸግ እንደሆነ ገልጸው፤ “የሃብታም ልጆችን እያዘልን ማሳደግ ሳይሆን እርስ በርስ ተጎራርሰን ተደጋግፈን በህብረት ማደግ፣ መለወጥና ሲተርፈን ሳናዝል መደገፍ የምንችልበት ቁመናን ኢትዮጵያናኢትዮጵያውያን ሊፈጥሩ ይችላሉ የሚል እምነት ስላለን ነው” ሲሉ አስገንዝበዋል። “የኢትዮጵያ ህዝብ ብልጽግና ይገባዋል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ብልጽግና መጓጓት፣ መሻትና መፈለግ በመሆኑ ጉዞው ፈታኝ መሆኑን ጠቁመው፤ ለዚህም መተባበር ወሳኝ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
Mostrar todo...
Mostrar todo...
ፍሲል ከነማ የኢትዮጲያ ፕሪሜሊግ ሻምፒዮን 2013 Ethiopian Bitking Prieam leage Champion 2021

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታሪካዊ ውሳኔን ወስኗል። ከፍተኛ የፈቃድ ክፍያ ዋጋ እና አስተማማኝ የሙዓለ ነዋይ ፍሰት ዕቅድ ላቀረበው ለግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን አዲስ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም ፈቃድ እንዲሰጥ በአንድ ድምፅ አጽድቋል። በአጠቃላዩ ከ8 ቢሊዮን ዶላር በሚበልጥ የሙዓለ ነዋይ ፍሰት፣ እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ከተደረጉት የውጪ ቀጥተኛ የሙዓለ ነዋይ ፍሰቶች ብልጫ እንዲኖረው ያደርገዋል። ኢትዮጵያን ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል አገልግሎት የማስገባት ዕቅዳችን ፈር ይዟል። ይህንን ግልጽነት እና ውጤታማነት የሞላበት ሂደት ላሳካችሁ ሁሉ ምስጋናዬ ይድረስ። The Council of Ministers has unanimously made a historic decision today allowing Ethiopian Communications Authority to grant a new nationwide telecom license to the Global Partnership for Ethiopia which offered the highest licensing fee and a very solid investment case. With over USD 8 billion total investment, this will be the single largest FDI into Ethiopia to date. Our desire to take Ethiopia fully digital is on track. I would like to thank all that have taken part in this and for pulling off a very transparent and effective process!
Mostrar todo...
ሰበር መረጃ‼️ #Ethiopia : 6ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ለሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲካሄድ መወሰኑን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። በዛሬው ዕለት በሆቴል ዲሊኦፖል እየተሰጠ በሚገኘው መግለጫ ላይ የቦርዱ ኮሚኒኬሽን ኃላፊ ሶሊያና ሽመልስ ተናግረዋል ። የመራጮች ምዝገባ ላይ ቅሬታ ያለባቸው ቦታዎች ላይ ግን ሰኔ 14 ቀን እንደማይካሄድ ገልፀዋል ።
Mostrar todo...