cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

@ነቅዐጥበብ

ነቅዕ ንጹሕ ዘእምአንቅዕተ ሕግ

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
6 266
Suscriptores
-224 horas
-117 días
+4630 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#ከኦስሎ #አዲስአበባ በሰላም ገባሁ ኖርዌይ ለሁለተኛ ጊዜ በአገልግሎት የጎበኘኋት ሀገር ናት የአሁኑ አገልግሎቴ በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ትሮንደሄም ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ አብያተ ክርስቲያናት ሰበካ ጉባኤ ጋባዥነት የተከናወነ  ነው በኖርዌይ ሀገር የምትገኘዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዋናነት ሦስት ነገሮችን አስተምራኛለች 👇 1. ትውልድ ላይ መሥራትን በተግባር 2. ቸር አገልጋይነትን በተግባር 3. መንፈሳዊ ራእይን በተስተካከለ አቅጣጫ (ዘመኑን ያሰላ ፤ የወደፊቱን የገመተ)  አስተውያለሁ እነዚህ ከላይ የገለጽኳቸው ነገሮች በሀሳብ ደረጃ በሁሉም ያሉ ቢሆንም በጥቂት ቦታዎች ብቻ በተግባር ይገለጣሉ 1.ትውልድ ላይ መሥራት 👉በውጪ ሀገራት ያሉ አብያተ ክርስቲያናት አሁናዊ ወሳኝና መሠረታዊ ጥያቄ 👇 • ቤተ ክርስቲያንን የሚከፍት ወንዶች ልጆችን ለዲቁና ፤ ሴቶችን ለዝማሬ አገልግሎት ወላጆችን ለንስሐና ለቁርባን የሚያበቃ አባት ማግኘት ነው ። ትውልድ ላይ መሥራት መንፈሳዊ ትውልድን ማፍራት ማለት ይህ ነው ...ይህንንም ደግሞ በተግባር በየአብያተ ክርስቲያናቱ እዚሁ ሀገር ተወልደው ተምረው ለዲቁና በቅተው የሚቀድሱ ዲያቆናትን ማየት የሚዘምሩ ወጣቶችን መመልከት እጅግ በሚያስገርምና በሚያስደስት መልኩ ውጤታማ እየሆነ ነው ይህም ማለት በሌላ አገላለጽ ከ ሆይ ሆይታ ሰብከት ወጥተው  መሠረታዊ ወደ ሆነው የቤተ ክርስቲያን ትምህርትና አገልግሎት ተሸጋግረዋል ማለት ነው 2.አገልጋይነት • ዓለማዊ ሥራ እየሠሩ ቤተ ክርስቲያንን ግን በነጻ የሚያገለግሉ ለክህነት ለገቡት ቃል የታመኑ አገልጋዮችን በብዙ ቦታ ተመልክቻለሁ • ለትምህርትና ለሥራ አገሪቱ ላይ የመኖር እድል ያገኙ መምህራን ቀሳውስትና ዲያቆናት ደሞዝ ሳይኖራቸው ልክ እንደባለደሞዝ አገልጋይ  ሲያገለግሉ አይቻለሁ በእርግጥ በደሞዝ ማገልገል ነውር  ባይሆንም ደሞዝ እየተቀበልን አገልግሎቱ ላይ ለምንቀልድ አገልጋዮች ግን ሊያስደነግጠን የሚገባ ትምህርት ነው !!! 3. መንፈሳዊ ራእይ መኖር ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የወደፊት ራእይ አላቸው ትውልዱ ላይ መሥራት ብቻ ሳይሆን የተሠራው ትውልድ የሚቀድስበትና የሚያስቀድስበት የሚቆርብበት የራሳቸው ቦታ እና ሕንጻ ቤተ መቅደስ እስከ መግዛት ድረስ ራእይ አላቸው ከሚጠራቀመው ገንዘብ ሽራፊ ሳንቲም ሳይነካ በታወቀ የሂሳብ አሠራር ቁጥጥር  ቦታ ለመግዛት ዓቅም እስሚሆን ድረስ ይቀመጣል...ይህ እጅግ የሚያስደንቅ ራእይ ነው ! ይህ ብቻ ሳይሆን በሀገረ ኖርዌይ ጠቅላላ የሚገኙ  ከ 13 ዓመት ጀምሮ ያሉ ልጆችና ወጣቶችን (ኢትዮጵያውያን ፣ ኤርትራውያን፣ኖሽኮች ወይም የሀገሩ ዜጎች) በመሰብሰብ  መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርት እንዲማሩ ከአሜሪካ ዲያቆን ጎርጎርዮስ ደጀኔ ተጋብዞ በእንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲያስተምራቸውና ጥያቄዎቻቸውን  እንዲመልስላቸው መደረጉ ሌላ የመንፈሳዊ ራእይ በር ማሳየት የሚችል አስደሳች ጅምር ነው ይህንኑ ጉባኤ እኔም ተገኝቼ በመካፈሌና  ለጥያቄዎቻቸውም መልስ በመስጠት በመሳተፌ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል! ይህ ትልቅ ተስፋ ትልቅ መንፈሳዊ ራእይም ነው!!! አማኝና አመስጋኝ ትውልድ እንዲቀጥል እነዚህን መሠረታውያን ነገሮች መያዝ አለብን👇 1. ትውልድ ላይ መሥራትን 2. አገልጋይነትን በተግባር ማሳየትን 3. መንፈሳዊ ራእይ ያለው ሰው መሆንን ...መያዝ አለብን! ይህንን አይቼ እንድመሰክር እድል የሰጠኝ ፤ በመንገዴ የማይለየኝ ፈጣሪዬ አምላኬ እግዚአብሔር ይመስገን!!! በመስተንግዶና ሀገሩን ከተማውን በማስጎብኘት በመንከባከብ ያከበራችሁኝን ሁሉ እግዚአብሔር ያክብርልኝ!!!! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው የቦሌ ገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሰባኬ ወንጌል አዲስ አበባ ግንቦት 19 /2016 ዓ.ም
Mostrar todo...
👍 53 37🙏 9
#ጌታችን_ከትንሣኤው_በኋላ_ለምን_በላ? (ሉቃ 24፡36-46) የቴሌግራም ቻናሌ👇 https://t.me/QH7OEcjEvXswNDc8 1. ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ 2. ሥጋውንም ነፍሱንም ተዋሕዶ እንደተነሣ ለማጠየቅ 3. ቀጠሮ ስለነበረው ጌታችን ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ በኅብረት ሳሉ 3 ጊዜ እንደተገለጠላቸው የታወቀ ነው ፤ በኅብረታቸው ውስጥ የተገለጠው 3 ጊዜ ይሁን እንጂ በ40ው ቀናት ውስጥ ለእያንዳዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት ሆነውም ሳይገለጥላቸው የዋለበት ያደረበት ጊዜ እንደሌለ መተርጉማነ ሐዲስ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ በተገለጠላቸው ጊዜም አስገራሚና አስደናቂ ያልተለመዱ ነገሮችን በማሳየት ነበር፡፡ በተዘጋ ደጅ መግባቱ አስደንግጧቸዋል፤ እሱ መሆኑን በአካለ ሥጋ እየተመለከቱ ቢሆንም ምናልባት ምትሐት ቢሆንስ? መንፈስ እሱን መስሎ አስመስሎ ተገልጦልን ቢሆንስ? የሚል ከባድ ጥያቄ በኅሊናቸው ይወጣ ይወርድ ነበር፡፡ ረስተዉት ነው እንጂ በባህር ላይ ሲራመድ አይተዉት ነበር፤ ባህሩን ሲገሥጸው ማዕበሉን ጸጥ ሲያደርገው ነፋሱን ሲያዘው ተመልክተው ነበር ዘንግተዉት እንጂ የአራት ቀን ሬሳ ሲቀሰቅስ የዕለት ሬሳ ከእንቅልፍ እንደማንቃት ሲያስነሣ በዓይናቸው አይተው ነበር ግን ሌሎችን ከሞት ያስነሣውን አምላክ የእሱን ከሞት መነሣት ለማመን ተቸገሩ! በዚህ ምክንያት "በምትሐትነት" ጠረጠሩት! ጌታም  በተዘጋው ደጅ ብቻ ሳይሆን በተዘጋው ልባቸውም ውስጥ ገብቶ ሀሳባቸውን እየመረመረው ነበርና  "ለምንት የዐርግ ኅሊና እኩይ ውስተ ልብክሙ፤ ክፉ ሀሳብ በልባችሁ ለምን ይመላለሳል?" እኔ ራሴ እንደሆንኩ እጆቼንና እግሮቼን እዩ ...መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ግን ዳስሳችሁ አረጋግጡ አላቸው፡፡ ይህንም ብሏቸው ግን አላመኑም ነበር ቅዱስ ሉቃስ እንደጻፈው "ወእንዘ ዓዲ ኢአምኑ እምድንጋፄ.." ከድንጋጤም ከደስታም የተነሣ ገና አለማመናቸውን ተመልክቶ ♥በዚህ አንዳች የሚበላ አላችሁን?♥ በማለት ጠየቃቸው አነሱም የተጠበሰ ዓሣና የማር ወለላ ሰጡት፤ ተቀብሎም በፊታቸው በላ፡፡ ለልማዱ ጌታችን ሲመገብ 6ቱ ይቆማሉ ስድስቱ ይቀመጡ ነበር በዚህ ጊዜ ግን ሁሉም ቆመው ዓይን ዓይኑን እያዩት በፊታቸው በላ፡፡ በፊታቸው የበላበት ምክንያት፦ 1. ምትሐት እንዳልሆነ ለማረጋገጥ ፦ ✝ጌታችን ፍጹም ሰው መሆኑን ለማረጋገጥ ያከናወናቸው ብዙ ነገሮች አሉ ፤ መራብ መጠማት መብላት መጠጣት፤መተኛት መነሣት፤ ራሱን ከምእመናን ጋር መቁጠር፤ መፍራት መጸለይ ...ሁሉ ለአጽድቆተ ትስብእቱ (ሰው የመሆኑ ትክክለኛነት) ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ሐዋርያት ምትሐት እንዳልሆነ ያምኑ ዘንድ ቀድሞ ሲበላ እንዳዩት ሁሉ ዛሬም እያዩት በፊታቸው መመገቡ ምትሐት ላለመሆኑ ማረጋገጫ ነበር፡፡ 2. ሥጋውንና ነፍሱን ተዋሕዶት እንደተነሣ ለማጠየቅ፦ ✝ ብዙ መናፍቃን ከጥንት ጀምሮ ይሰናከሉ ከነበረበት ትልቅ ጉዳይ አንዱ የጌታችንን ትንሣኤያዊ ማንንነት የተመለከተ ነው ፤ መለኮቱና ሥጋው በመስቀል በሞት የተለያዩ የሚመስላቸው ፤ ያም ባይሆን ሥጋን በመቃብር ትቶት የተነሣ የሚመስላቸው ፤ ወይም በሌላ የተለየ አዲስ ሥጋ የተነሣ የመሰላቸው ብዙዎች አሉ፡፡ ጌታችን እዩት እጄን እዩት እግሬን እዩት ጎኔን ብሎ የቀኖትና የጦር ምልክቱን ያሳያቸው ያንኑ የተገረፈውን የተሰቀለውን ሥጋ ተዋሕዶት የማይፈርስ የማይበሰብስ አድርጎ እንዳስነሣው ለማጠየቅ ነው፤ ቶማስም በተወጋው ጎኑ ቀዳዳ እጁን እንዲያስገባ የፈቀደለት ከሌላ የክህደት ቀዳዳ ለመታደግ ነው ፡፡ መብላት መጠጣት የነፍስና የሥጋ ተዋሕዶ ምልክት ነው፤ ጌታም ይህንን ተዋሕዶ ለማረጋገጥ እንጂ ርቦት ወይም ከትንሣኤ ወዲያ መራብ መጠማት መብላትና መጠጣት ያለ ሆኖ አይደለም፡፡ The Orthodox Study Bible ላይ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ኅዳግ (Foot note) ላይ እናገኛለን " Christ eats not because He in His resurrected body needs food, but to prove to the disciples that He is truly risen in the flesh" ክርስቶስ የተመገበው በተነሣበት አካል ምግብ የሚያስፈልገው ሆኖ ሳይሆን በእውነት በሥጋ መነሣቱን ለደቀመዛሙርቱ ለማረጋገጥ ነው እንጂ" ይላል፡፡ ትርጓሜ ወንጌልም "ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ" ካለ በኋላ "ትንሣኤውን እንዲረዱ እንዲያምኑ" በፊታቸው በላ በማለት ግልጽ አድርጎታል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅም "አኮ ፈቂዶ ለመብልዕ አላ በልዐ ወሰትየ ከመ ይእመኑ ከመ ውእቱ ተንሥአ እምውታን፤ ምግብ የሚያስፈልገው ሆኖ እይደለም፤ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን ያምኑ ዘንድ በላ ጠጣ እንጂ" ብሏል፤ ሃይ.አበ 66፡8፡፡ 3. ቀጠሮ ስለነበራቸው፦ ዕለተ ሐሙስ ማታ ላይ "ኢይሰቲ እምዝንቱ አጺረ ፍሬ ወይን እስከ አመ እሰትዮ ምስሌክሙ ሐዲሰ በመንግሥተ አቡየ ዘበሰማያት፤ በአባቴ ሥልጣን ታድሼ እስከምነሣ ድረስ ከዚህ የወይን ጭማቂ አልጠጣም" ብሏቸው ነበር ፡፡ ይህ አነጋገር ብዙ ምሥጢራት ያሉት ቢሆንም በዋናነት የሚያመለክተው ግን ትንሣኤን ነው፦ "በአባቴ ሥልጣን.." የሚለው የማይራብ የማይጠማ የማይደክም አይሁድ ለመከራ የማይፈልጉት፤ ከእንግዲህ ወዲህ የመስቀል ሞት የሌለበት ሆኖ መነሣቱን የሚያመለክት ሲሆን የወይኑን ጭማቂ ጽዋ አለመጠጣቱ ግን እሱ የሚጠጣው የመስቀል ጽዋ ስለነበረው ነው ...ይኸውም ሊታወቅ "ይህቺ ጽዋ ከእኔ ትለፍ" እያለ መላልሶ ይጸልይ እንደ ነበር ተገልጧል፤ ያን ጽዋ እሱ ካልጠጣልን እኛ የወይኑን/የደሙን ጽዋ መጠጣት አንችልምና፡፡ ያንን ሁሉ አጠናቆ በሐዋርያት ፊት የማር ወለላ ቀረበለት እሱንም በፊታቸው በመብላትና በመጠጣት የዕለተ ሐሙሱን ንግግሩን አስታወሳቸው፡፡ ይህንንም ግእዝ በግእዝ ትርጓሜ ወንጌል "በበሊዖቱ አዖቀ ጽድቀ ትንሣኤሁ ወሰትዮቱኒ ያሌቡ እንበይነ ቃሉ ዘይቤ "ኢይሰቲ እምዝንቱ አጺረ ፍሬ ወይን"" በማለት ገልጦታል፡፡ ✝ማስታወሻ፦ የቀድሞው የፋሲካ በግ ሥጋው ተጠብሶ መራራ ቅጠል ይጨመርበት ነበር፤ አሁን ግን አዲሱ ፋሲካ ክርስቶስ ስለታረደ መራራ ቅጠል ሳይሆን እርሱ ባወቀ የማር ወለላ ቀረበለት! ✝ሌላው በጣም የምንገረምበት ጉዳይ ደግሞ "ወነሥአ ዘተርፈ ወወሀቦሙ፤ የተረፈውን አንሥቶ ሰጣቸው" የሚለው ነው፡፡ ☞ለምን ሁሉንም አልበላውም? ☞ለምን ቀምሶ አልተወውም? ☞ለምን አስተረፈ? ☞ካስተረፈስ ለምን የተረፈውን ለነሱ ሰጣቸው? የሚሉትን ጥያቄዎች በመገረም መጠየቅ እንችላለን!!! የተጠበሰው ዓሣና የማር ወለላው፦ ➊የትንቢተ ነቢያት ምሳሌ ነው ➋የዘመን ምሳሌ ነው ➌የሥራ ምሳሌ ነው ➍የትምህርተ ወንጌል ምሳሌ ነው ➎የተአምራት ምሳሌ ነው ጌታ የበላውን በልቶ የተረፈውን ለሐዋርያት መስጠቱ፦ ✝፩. በእሱ የተፈጸመውንና ወደፊትም በእነርሱ የሚፈጸመውን ትንቢት ለትውልድ፡እንዲገልጡ የተረፈውን ሰጥቷቸዋል፡፡ ✝፪. ዘመነ ነቢያትንና የእርሱን ዘመን (33 ዓመት ከ 3 ወር) አሳልፎ የተረፈውን ዘመን ሰጥቷቸዋል (ዘመነ ሐዋርያት) ✝፫. እሱ ሠራዬ ኃጢአት ሊቀ ካህናት ከባቴ አበሳ እንደሆነው ሁሉ እነሱም እንዲያጠምቁ እንዲያቆርቡ እንዲያስሩ እንዲፈቱ ሥልጣነ ክህነትን ሰጥቷቸዋል ✝፬. እሱ 3 ዓመት ከ 3 ወር እንዳስተማረ እነሱንም "ሑሩ ወስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት" ብሏቸዋል
Mostrar todo...
@ነቅዐጥበብ

ነቅዕ ንጹሕ ዘእምአንቅዕተ ሕግ

20👍 10🙏 1
✝፭. እሱ ብዙ ተአምራትን እንዳደረገ እነሱንም ♥እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል♥ ብሏቸዋል፤ ዮሐ 14 ፡12፡፡ ከዚህ በኋላ የተረፈውን ምግብ እንደሰጣቸው ሁሉ ከ3 ዓመት ከ3 ወሩ የተረፈውን ትምህርት አስተማራቸው.... የነገርኳችሁ ሁሉ ቃሌ ይህ ነው ብሎ አእምሯቸውን እንደተዳመጠ ብራና ንጹሕና ቀለም ለመቀበል የተዘጋጀ አደረገላቸው፡፡ ...... ....ሐዋርያትም ማስተዋል ጀመሩ...!!! እንድናስተውል ይርዳን!!! አሜን! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው (በድጋሚ የተለጠፈ) ከኖርዌይ ኦስሎ
Mostrar todo...
65👍 14👏 5🙏 4
#ከትንሣኤ_እስከ_ዕርገት የቴሌግራም ቻናሌ👇 https://t.me/QH7OEcjEvXswNDc8 የጌታችን መዋዕለ ሥጋዌ በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፦ 1. ቅድመ መስቀል፦ ቅድመ መስቀል የምንለው 33 ዓመት ከ 3ወሩን ነው፤ ይህ ጊዜ ኃጢአት ያልሆነ ማንኛውም ነገር በክርስቶስ የተከናወነበት ልዩ ጊዜ ነው፡፡ 2. ጊዜ መስቀል፦ በመስቀል/በጽኑ ስቃይ የቆየበት ሰዓት 3. ድኅረ መስቀል፦ ድኅረ መስቀል የምንለው ደግሞ በአካለ ሥጋ ከመስቀል ወደ መቃብር ፤ በአካለ ነፍስ ወደሲኦል ከሄደበት ቅጽበት ወዲህ ያለውንና 40ዎቹን ቀናት ወይም 1 ወር ከ10 ቀናትን ነው፡፡ *(ከዕርገት እስከ ጰራቅሊጦስ ያሉትን 10 ቀናት ለብቻ እናያቸዋለን)* ✝ጌታችን ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኀላ 40 ቀን በዚህ ምድር ቆይቷል ፡፡ በነዚህ ቀናት ውስጥም በዋናነት 2 ዋና ዋና ሥራዎችን እንደሠራ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ 1. ለሐዋርያት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እና መጽሐፈ ኪዳንን ማስተማር፦ ለቅዱሳን ሐዋርያት በጉባኤ የተገለጠላቸው 3 ቀናት ቢሆንም ለእያንዳንዳቸው ለየብቻም 2 ወይም 3 ሆነው ግን ሳይገለጥላቸው የዋለበት ያደረበት ጊዜ አልነበረም፡፡ "ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው" እንዲል ሉቃስ ፤ሐዋ 1 : 3፡፡ በተገለጠላቸውም ጊዜ ቤተ ክርስቲያን እንዴትና በምን በማን መተዳደር እንዳለባት አስተምሯቸዋል፡፡ ለምሳሌ ፦ " እርሱም። መረቡን በታንኳይቱ በስተ ቀኝ ጣሉት ታገኙማላችሁ አላቸው። ስለዚህ ጣሉት፤ በዚህም ጊዜ ከዓሣው ብዛት የተነሣ ሊጐትቱት አቃታቸው" ፤ ዮሐ 21 :6 ፤ በማለት ቅዱስ ዮሐንስ እንደጻፈው መረቡ በቀኝ እንዲጣል ማዘዙ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሁሉ በቀኝ በክብርና በፍቅር እንደሚፈጸም ያሳያል፡፡ ሐዋርያት "እንደቃልህ እናደርጋለን" ብለው እንደ ቃሉ መሠረት ማድረጋቸው ደግሞ ቤተ ክርስቲያን የምትፈጽመው ሥርዓት ሁሉ መሠረቱ የጌታ ቃል እንደሆነ ይህም በማመን የሚፈጸም መሆኑን ያመለክታል፡፡ ዓሣዎቹም በየጊዜው የሚያምኑ የሚጠመቁ ምእመናን ምሳሌዎች ናቸው፤ ቀጥሎ በተዘጋጀው ማእድ በአንድነት መመገባቸውም የሁላችን ማእድ የሚሆነውን ከመላእክት ጋር የምናመሰግነውን የምስጋናችንን አንድነት ያመለክታል፦ " ወደ ምድርም በወጡ ጊዜ ፍምና ዓሣ በላዩ ተቀምጦ እንጀራም አዩ"፤እንዲል ዮሐ 21 : 9፡፡ ይህንም ማእድ መላእክት እንዳዘጋጁት መተርጉማነ ሐዲስ ገልጸዋል፦ ትርጉሙ ኅብረተ መላእክት ወሰብእ ነው፡፡ "ወኅብስተ መላእክቲሁ በልዑ እጓለ እመ ሕያው"( ሰዎች የመላእክትን ምግብ በሉ) የሚለው ትንቢተ ዳዊት የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜው በዚህ ፍጻሜውን አግኝቷል፤ መዝ 77፡25፡፡ በዓለም መጨረሻም የሚሆነው ይኸው ነው፤ ከመላእክት ጋር ለዘለዓለም ማመስገን!!! ከዚህም ቀጥሎ ደግሞ ለጴጥሮስ በጎቹን የመጠበቅ ኃላፊነቱን (ክህነትን) አጠንክሮ አደራ ይለዋል፡፡ ስለዚህ ይህ ሁሉ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ነበር፡፡ ለዚህም መጠበቂያ መመሪያ የሚሆን ጸሎት 7ቱን ኪዳናት አስተምሯቸዋል፡፡ 2. ለነፍሳት አህጉራተ ገነትን ማካፈልና ምሥጢረ መንግሥተ ሰማያትን ማሳየት/ማስተማር፦ ገነት በ15 አህጉራት እኩል የተከፈለች መሆኗን አበው አስተምረውናል (መጽሐፈ ቀሌምንጦስ)፤ ዓለማችን በሰው ሰራሽ አከፋፈል መሠረት 7 አህጉራት አሏት፤ ገነት ግን የአንዱ አህጉር መጠን ባይታወቅም ቅሉ በ15 አህጉራት የተከፋፈለች ሰፊ መሆኗን ያሳያል፤ ይህች ዓለም የቅጣት ቦታችን ናት (ምድረ ፋይድ/ምድረ ፍዳ) ገነት ግን ጥንተ ርስታችን ናት፡፡ ጌታ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ካወጣ በኀላ ወደ ገነት አሳልፏቸዋል፤ እርሱ ባወቀም ነፍሳት መኖር በሚገባቸው እያመሰገኑ እንዲኖሩ ቦታ ቦታቸውን አስይዟቸዋል፤ ፍጡር ሆኖ ያለ ቦታ መኖር አይቻልምና፡፡ "በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው" እንዲል ቅ.ጴጥሮስ፤ 1ኛ ጴጥ 3 : 19፡፡ ✝ገነት ከገቡ በኀላም ገነት የዘለዓለም መኖሪያቸው እንዳልሆነችና ለዘለዓለም የሚያወርሳቸውን የማታልፈውን የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር አስተምሯቸዋል፡፡ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር በዓይነ ሥጋ ማየት፤ በእዝነ ሥጋ መስማት፤ በአእምሮ ጠባዕይ ማወቅ አይቻልም፤ የሚታወቀው በአእምሮ መንፈሳዊ በዓለመ ነፍስ ነውና ለነፍሳት አስተማራቸው፤ ይህም መዓርግ ወይም ደረጃ ነው፤ ምሥጢራትን የምናውቅበት ደረጃ አለ በዓለመ ነፍስ የምንረዳውን በዓለመ ሥጋ አንረዳውም ፦ "ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ፤ እንዳለ ቅ.ጳውሎስ፡፡ 1ኛ ቆሮ13 : 12፡፡ ዳግመኛም፦ "ነገር ግን ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን"፤ ብሏል፡፡ 1ኛ ቆሮ 2 : 9፡፡ እኛም በዚህ በዓለ ሃምሳ ስለ ምሥጢረ ትንሣኤና ስለ ዘለዓለማዊው ሕይወት አብዝተን የምንማርበትና የምንመረምርበት ሊሆን ይገባል፡፡ 40ዎቹ ቀናት፦ • አዳም ከተፈጠረ በኋላ ገነት ከመግባቱ በፊት 40 ቀን በምድር ቆይቷል፦ ሁለተኛው አዳም ክርስቶስም ከዕርገቱ በፊት 40 ቀናትን በዚህ ምድር ቆይቷል፡፡ • የሰው ተስእሎተ መልክዕ በማኅፀን የሚፈጸምለት በ 40 ቀንናት ውስጥ ነው፤ ቤተ ክርስቲያንም የሥርዐቷ ተስእሎተ መልክዕ ተቀርጾ የተጠናቀቀው በ40 ቀናት ነው፡፡ • ሰገኖ እንቁላል ከጣለች በኋላ 40 ቀን ዓይኗን ከአንቁላሉ አትነቅልም፤ ትታው ብትሄድ እንደ ድንጋይ ይደርቅባታል! ጌታችንም ለ40 ቀናት ከቤተክርስቲያን ሐዋርያትን ዓይኑን ሳይነቅል ትክ ብሎ ሲመለከታት ነበር፤ ተለይቷቸው ቢሆን ሐዋርያት በቀቢጸ ተስፋ በደረቁ ነበረና፡፡ (ዛሬም አልተለያትም!) ወነበረ አርብዓ መዋዕለ እንዘ ይሜሕሮሙ ምሥጢረ መንግሥተ ሰማያት" እንዲል መቅድመ ወንጌል፡፡ “ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው።” እንዲል ሉቃስ — ሐዋርያት 1፥3 ጌታችን 40 ቀናት መቆየቱ እነዚህን ምሥጢራት ያመለክታል፡፡ አምላካችን ምሥጢሩንና ጥበቡን ሁሉ ይግለጥልን!!! ከዕለት እኪት፣ ከዘመን መቅሰፍት ይሠውረን!!! አሜን! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው ዘቦሌ ገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን YouTube chanal 👇 https://youtu.be/ajtQIZSCUs4 ከ ኖሮዌይ ትሮንዳሄም
Mostrar todo...
@ነቅዐጥበብ

ነቅዕ ንጹሕ ዘእምአንቅዕተ ሕግ

51👍 19🙏 9🥰 3👎 2
ይህንን የመሰለ ሕንፃ ቤተ መቅደስ 👇 • መቅደስ ቢኖረውም ይጎበኛል እንጂ አይቀደስበትም • አሁን ምዩዚዬም ነው • ሁሉ ተሟልቶ የተሠራለት ቢሆንም አምልኮ አይፈጸምበትም • መጠመቂያ ቢኖረውም የሚጠመቅበት የለም ምክንያቱም የሀገሩ ሰዎች ሃይማኖታቸውን ትተዋል ሃይማኖት አልባ ሆነዋል ....ከሃይማኖት ባዶ መሆናቸውን በኩራት ያስጎበኛሉ...የካቴድራሉን ሕንጻ ከአገልግሎት ባዶ መሆኑን በኩራት ይናገራሉ!!!! እኛም ይህንን አይተን ጎብኝተን ስለ ራሳችን • ሀገር • ሃይማኖት • ቤተ ክርስቲያን • ባህል ...ተነጋግረን ከመቅደሱ ወጣን እኔም ይህንን ቃል አስቤ አዘንኩ 👇 ማቴዎስ 23 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁸ እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል። ³⁹ እላችኋለሁና፥ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም።" 👉እንደ አማኝና አገልጋይ ሁሌም የሚሰማኝ ይህ ነው ! ወደፊት የሚመጣው ትውልድ ቤተክርስቲያኗን ከነሥርዓቷ በምን ያህል መጠን ይረከባታል? እኛ ስለ ዘርና ስለ ብሔር ስለ ሥልጣንና ሢመት ስለ ገንዘብና ኑሮ ስናስብ ትውልዱን ከእጃችን እየተቀማን ቤተ ክርስቲያንን ዝቅ አድርገን የኛን ልዕልና ብቻ ለማሳየት እየተጋን የት እንደርስ ይሆን?.... የቤተ ክርስቲያን አምላክ ትውልዳችንን በሃይማኖት ያጽናልን ይጠብቅልን ተረካቢ አያሳጣን!!!! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው ከ ኖርዌይ ትሮንዳሂም ግንቦት 5 /2016 ዓ.ም
Mostrar todo...
55😭 28👍 12🙏 7🔥 6😱 2
#እንኳን_ለዳግማይ_ትንሣኤ_አደረሳችሁ! #አግብኦተ_ግብር ፤ #ዳግማይ_ትንሣኤ የቴሌግራም ቻናሌ 👇 https://t.me/QH7OEcjEvXswNDc8 "ጊዜው ደረሰ" ዮሐ 17÷1 ✝ዳግማይ ትንሣኤ እና አግብኦተ ግብር፡- ለሐዋርያት በጉባኤ ለሁለተኛ ጊዜ ቶማስ ባለበት የተገለጠበት ቀን ስለሆነ ዳግማይ ይባላል እንጂ ትንሣኤው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ✝ ዳግማይ ትንሣኤ ከመባሉ በተጨማሪ በሊቃውንት ምሥጢራዊ አጠራር "አግብኦተ ግብር" ይባላል፤ ቀጥታ ትርጉሙ "ሥራን መመለስ" ማለት ነው፤ ምሥጢሩ ግን "ግብረ ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ" ብሎ እንዲያመጣው እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነበትን ሥጋ የለበሰበትን ዓላማ በመስቀል የሚያጠናቅቅበት ጊዜው መድረሱን የሚያሳይ ነው፤መስቀሉ ላይ "ተፈጸመ ኩሉ" ብሎ መጮኹም የዚሁ የመጨረሻ ክፍል ነው፡፡ ✝በዳግማይ ትንሣኤ ዕለት ጠዋት ከቅዳሴ በኋላ የዮሐንሰ ወንጌል 17÷1-ፍጻሜ ድረስ ሙሉው ይነበባል፡፡ በዓሉ የጸሎተ ሐሙስ ሲሆን በዕለቱ ብዙ የተደራረቡ በዓላት በመኖራቸው ምክንያት "አግብኦተ ግብሩ" ከዳግማይ ትንሣኤ ተደርቦ ይታሰባል፡፡ ✝የዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ 17 ሙሉው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸሎት ነው፡፡ ✝ይህም ጸሎቱ እንደ ብሉዩ ሊቀ ካህናት የኃጢአት መሥዋዕትን ተክቶ የቀረበ ጸሎት ነው፤ የብሉይ ኪዳኑ የካህናት አለቃ ለሕዝቡ የኃጢአት ሥርዬት የሚሆነውን መሥዋዕት ከማቅረቡ አስቀድሞ እሱ ራሱ ኃጢአተኛ ነውና ፤ ስለኃጢአቱ ስለ ጥንተ አብሶው ለራሱ መሥዋዕት ያቀርባል፤ ከዚያ በኋላ ስለ ሕዝቡ ሥርዬተ ኃጢአት የሚሆነውን መሥዋዕት አርዶ አወራርዶ ፤ደሙን ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባል፤ስለ ሕዝቡ ኃጢአትም ይለምናል፡፡ ✝ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ምንም እንኳን ኃጢአት ባይኖርበትም ነገር ግን ሕግን ለመፈጸም ነውና የመጣው እንደ ብሉዩ ሥርዓት ኃጢአት ሳይኖርበት ወይም ኃጢአተኛ ሳይሆን የኃጢአት መሥዋዕት ያቀርባል ፤ ይህም ያለ ኃጢአት የሚቀርበው ጸሎቱና መሥዋዕቱ የሁሉ ነገር መዝጊያና ማብቂያ ነው፤ የአዳምና የልጆቹ የነቢያት እንባቸው ፤ኀዘናቸውና ትካዜያቸው ማብቂያ የሚያገኘው በጌታ እንባ፤ኀዘንና ትካዜ ነው፤ጸሎታቸው የሚታተመው በጌታ እንባ ጸሎት ነው፤የካህናቱ መሥዋዕታቸውና አገልግሎታቸው የሚታተመው በጌታ አገልግሎትና መሥዋዕት ነው፤ በአጠቃላይም የብሉይ ኪዳኑ አስተምሕሮ የሚጠናቀቀው በጌታ አስተምሕሮ ነው፡፡ የነቢያት አስተምሕሮ "በዘመንየኑ ትፌኑ ወልደከ…."፤ "አንሥእ ኃይለከ ፤ፈኑ እዴከ፤ኢትዝክር ለነ አበሳነ ዘትካት፤ወነዓ አድኅነነ፣ ፍጡነ ይርከበ ሣህልከ እግዚኦ፤እስመ ተመንደብነ ፈድፋደ፤አድኅነነ ወባልሐነ……" (መዝ 78÷8) እያሉ ነበር፡፡ ✝ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን "ጊዜው ደርሷል" ብሎ ነው የሚጀምረው ይኸውም የመዳን ዘመን ምሕረት የተደረገበት ዓመት መሆኑን ለማጠየቅ ነው “ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤” — ገላትያ 4፥4 አምላካችን ለሁላችንም ምሕረቱን ቸርነቱን አያጉድልብን መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው የቦሌ ገርጂ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሰባኬ ወንጌል ከ ኖርዌይ ኦስሎ
Mostrar todo...
@ነቅዐጥበብ

ነቅዕ ንጹሕ ዘእምአንቅዕተ ሕግ

43👍 22🙏 11
Photo unavailableShow in Telegram
ዛሬም የሴቶች ቀን ይከበራል! የቴሌግራም ቻናሌ👇 https://t.me/QH7OEcjEvXswNDc8 የዛሬው ዕለት #ቅዱሳት_አንስት ወይም #አንስት_አንከራ ተብሎ ይጠራል 👉"አንስት አንከራ ትንሣኤሁ ነገራ" እንዲል ቅዱስ ያሬድ ፤ ሴቶች አደነቁ ትንሣኤውን ተናገሩ ማለት ነው ለጊዜው የጌታን ትንሣኤ ያበሠሩ ሴቶች መታሰቢያ ቢሆንም ፍጻሜው ግን ለክርስቲያን ሴቶች ሁሉ መታሰቢያ ቀን ነው። ዛሬም ብሥራተ ትንሣኤውን በዝማሬ በምስጋና በማስቀደስ በመቁረብ በሚዲያ በቃል በተግባር በማብላት በማጠጣት በማስተናገድ በጸሎት....በልዩ ልዩ አገልግሎት የሚፋጠኑ የሚመሰክሩ ሴቶች "ቅዱሳት አንስት" ይባላሉ (የተለዩ የተመረጡ የጸኑ ማለት ነው)። እግዚአብሔር እናቶችንና እህቶችን ይጠብቅልን! ሠናይ ቅዳሜ🙏 መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው ከ ኖርዌይ ኦስሎ
Mostrar todo...
👍 49 33🙏 8🥰 6
#የትንሣኤው_ሦስተኛ_ቀን_ቶማስ_ይባላል የቴሌግራም ቻናሌ👇 https://t.me/QH7OEcjEvXswNDc8 የትንሣኤ ሦስተኛው ዕለት ቶማስ ይባላል፡፡ ቶማስ ማለት ፀሐይ ማለት ሲሆን ፣ዲዲሞስ ማለት ደሞ መንታ ማለት ነው፡፡ ማመኑ በፀሐይ ፤መጠራጠሩ በመንታነት ይመሰላል፡፡ ቶማስ ሰዱቃዊ ነው ሰዱቃውያን ትንሣኤ ሙታን የለም ብለው ያምናሉ ቶማስም ሰዱቃዊ ስለሆነ ትንሣኤ ሙታንን የማይቀበል የማያምን ሰው ነበር፤ የጌታን ትንሣኤ ለመቀበል የተቸገረው አእምሮውን ገድሎት የነበረው ሰዱቃዊው ሀሳብ ስላልተለየው ነበር፡፡ ይሄ ብቻ ሳይሆን ጌታ አልዓዛርን ለማስነሣት ሐዋርያትን እንሂድ ሲላቸው "ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት። ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ አለ" ይላል ዮሐ 11፡16፡፡ የጌታችንን ከሞት መነሣት እርግጥ ሆኖ ሲያገኘው ግን የሞተው አእምሮው/ሀሳቡ ተነሥቷል ፤ "ጌታዬ አምላኬ" ብሎ ጠርቶ ሕያውነትን ተቀላቅሏል፡፡ "አንሥአኒ በትንሣኤከ፤ በትንሣኤህ አንሣኝ" እንዲል ቅዱስ ያሬድ ቶማስን በትንሣኤው አንሥቶታል፤ ስለዚህ የትንሣኤው 3ኛው ቀን ለቶማስ መታሰቢያ ሆኗል፡፡ ቶማስም ከ 3 ዓመት ትምህርት በኋላ ከጥርጥር ሞቱ ተነሥቷልና። ቶማስ ጠያቂ ነው፤ ያልገባውን ይጠይቃል፤ ማየት የፈለገውን ልየው ይላል፡፡ በዚህም ፍጥረታዊ ወይም ሳይንሳዊ ሰውን ይመስላል፤ ፍጥረታዊ ሰው ተነግሮት አያምንም፤ካልጨበጠ ካልዳሰሰ እውነትነቱን አይቀበልም ፦ " ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም።" እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ 1ኛ ቆሮ 2 : 14፡፡ ቶማስ የጌታችንን ድርጊቶች በጥርጣሬ ይመለከት የነበረ ሐዋርያ ነበር ፡፡ ለምሳሌ ጌታችን አልዓዛርን ለማስነሣት ሲሄድ ደስተኛ አለመሆኑን በሞት ስጋት ገልጾ ነበር፦ "ስለዚህ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ለባልንጀሮቹ ለደቀ መዛሙርት። ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ አለ" በማለት እንደተጻፈ፡፡ ዮሐ 11 : 16፡፡ በሌላ ጊዜም ቶማስ መንገዱን የጠየቀው ለዚህ ነበር፤ ያ መንገድ ወዴትና የት የሚወስድ ነው? የሚል ጥያቄ በውስጡ ይመላለስ ስለ ነበረ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ እንደጻፈው፦ "ቶማስም። ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን? አለው" ዮሐ 14 : 5፡፡ በዚህ ሁሉ ጥያቄውና ጥርጥሩ ግን ጌታችን አንድም ቀን ሰልችቶት ተቆጥቶት ወይም በጥርጣሬ አትከተለኝ ብሎት አያውቅም ፤ ድካማችንን የሚያውቅ የሚሸከምልን አምላክ ነውና፤ ዛሬም ምንም ያህል ኃጢአት ብንሠራ ተጸጽተን በንስሐ ከተከተልነው አትከተሉኝ አይለንም፤ ከየትኛውም ክህደት ከየትኛውም ሃይማኖት ብንመለስ ወደ እውነተኛው ሃይማኖት ከገባን በኀላ አልፈልጋችሁም፡ውጡልኝ አይልም፤ "ወደኔ የመጣውን ወደ ውጪ አላወጣውም "ብሎናልና፤ ዮሐ 13፡32፡፡ ጌታችን ከሞት ከተነሣ በኀላ ለሁሉም ሲገለጥ ለቶማስ ግን አንድ ሳምንት ሙሉ አልተገለጠለትም ነበር፤ ቶማስም ጌታን በአካል ያዩት ሐዋርያት ሲነግሩት፦ • የችንካሩን ምልክት በእጆቹ ካላየሁ • ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ካላገባሁ • እጄንም በጎኑ ካላገባሁ አላምንም" ይላቸው ነበር። ዮሐ 20 : 25፡፡ ጌታችን ይህንን ያደረገበት ምክንያትም፦ 1. ቶማስ በውስጡ መንፈሳዊ ቅናት እንዲያድርበት፤ ሁሉም ስለ ትንሣኤው ሲናገር እየሰማ እንዲጓጓ ነው፤ ይህ መጎምጀት ወደ ፍጹም መንፈሳዊነት ይመራልና፤ እኛም ዛሬ ለመንፈሳዊ ነገር ስንጓጓና ስንቸኩል እግዚአብሔርን እናገኘዋለን፤ በውስጣቸው የሚቀጣጠለው ፍቅረ እግዚአብሔር እርሱን ራሱን ይጠራዋል፤ ቀድሞም ለሞት ያደረሰው ፍቅር ነውና፡፡ 2. ጌታችን የአንዲት ነፍስ ጉዳይ ጉዳዩ እንደሆነ ያጠይቃል፡፡ የተገለጠው ለቶማስ ሲል ነበር ለሱም ሲባልም አስቀድሞ በሌለበት የተገለጠበት ፦ • ዕለት • ሰዓት • ቦታ • በተዘጋ ደጅ መግባቱ • ሰላምታው (ሰላም ለሁላችሁ ይሁን) • ሁኔታው /መልኩ አልተቀየረም፡፡ ቶማስ ባለበት የተገለጠበትና ሳይኖር የተገለጠበት ልዩነት ቢኖረው በመጀመሪያ ቀንና በስምንተኛ ቀን መሆኑ ብቻ ነበር፡፡ ይህም የሚያሳየው ፦ • ለሰው ሁሉ ያለውን ክብር/ፍቅር/ግድ • ትንሣኤው እርግጥ መሆኑን • ፍጹም ቸርነቱን • መጀመሪያ ያዩትም መጨረሻ የሚያዩትም በአንድነት እንደሚወርሱት ያጠይቃል፡፡ የቶማስ የመጨረሻ እምነት፦ "ጌታዬ አምላኬም" ፤ዮሐ 20፡28፡፡ ይህ ቃል የመጨረሻው የእምነት ጥግ ቃል ነው፤ የምናምነው ይህን ነው ፤ የምንናገረው ይህን ነው፤ የምንሰብከው ይህንን ነው፤ ከዓለም የምንለየውም በዚህ ቃል ነው፡፡ ቶማስ ብዙ ቢጠይቅም፤ ቢጠራጠርም በመጨረሻ ግን "አምላኬ" ብሎ አመነ፤ ዛሬ "ኢየሱስን አምላክ " ብለው መጥራት የሚከብዳቸው ብዙዎች ናቸው፤ እኛ እንኳን የቶማስን ቃል የወንጌሉን ፍጥጥ ያለ እውነት ስንናገር ይጠሉናል፡፡ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድላቸው!!! ቶማስ ጌትነቱን አምላክነቱን ያመነው በመዳሰስና በማየት ከሆነ እኛስ ሳናይ እንዴት እናምናለን እንዳንል ጌታችን " ኢየሱስም። ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው" በማለት ወሳኝ መልእክት አስቀምጦልናል፡፡ ዮሐ20 : 29፡፡ ወንጌላዊውም ታሪኩን ሲጠቀልለው፦ " ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል" በማለት ይህን አንብበን፤ ሰምተን ብቻ እንድናምን አስገንዝቦናል፡፡ ዮሐ 20 : 31፡፡ እኛም የቶማስን እጅ እጅ አድርገን ዳሰነዋል የሐዋርያትን ዓይን ዓይን አድርገን አይተነዋል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም "ክብሩን አየን.." እንዳለ አባ ሕርያቆስም " ከእርሱ ጋር በላን ጠጣን.." እንዳለ እኛም እንደ ቶማስ " ጌታችን አምላካችን" እንላለን!!!!! በዚህም እኛ "ብፁዓን ነን"!!! እንድናምነው የረዳን አምላካችን ይመስገን!!!! በበጎ ሥራም ደስ እንድናሰኘው ይርዳን!!! በረከተ ሐዋርያት ይደርብን!!! አሜን!!! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው የቦሌ ገርጂ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ሰባኬ ወንጌል
Mostrar todo...
@ነቅዐጥበብ

ነቅዕ ንጹሕ ዘእምአንቅዕተ ሕግ

39👍 26🙏 12
Photo unavailableShow in Telegram
ትክክለኛው ይህ ነው! በልዩ ሁኔታ የ ነቅዐጥበብ ቴሌግራም ግሩፕ አባላት እንኳን አደረሳችሁ!!! መልካም በዓል ይሁንላችሁ የትንሣው ብርሃን በልባችን ይብራ በአእምሯችን ይገለጥልን!!!!
Mostrar todo...
87👍 15🙏 11
Photo unavailableShow in Telegram
#እንኳን_ለብርሃነ_ትንሣኤው_አደረሳችሁ -ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን -በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን -አሰሮ ለሰይጣን -አግዐዞ ለአዳም -ሰላም -እምይእዜሰ -ኮነ -ፍሥሓ ወሰላም ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ሰይጣንን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው ከዛሬ ጀምሮ ደስታና ሰላም ሆነ ። “አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።” — 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥20 በዓሉን የደስታ የሰላም የጤና የበረከት ያድርግልን ለሁላችሁም መልካም በዓል🙏 መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
Mostrar todo...
59👍 15🥰 4🙏 4👏 3🤔 2