es
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Ir al canal en Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Mostrar más
4 374
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
https://t.me/EOTC2921 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻 🌼🌼 🌻 🌼🌼 🌼🌼🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌻 🌼🌼 🌼🌼🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻 🌼🌼🌼🌼🌼🌻 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼🌼🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼 🌻 🌼🌼 🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 🌺 🌸🌸 🌺 🌸🌸 🌸🌸 🌸🌸 🌺 🌸🌸 🌺 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 🌸 🌻🌻🌻🌻 🌸 🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌸 🌻🌻 🌸 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻እንቁጣጣሽ🌻🌻🌻 🌻መልካም አዲስ አመት🌻 🌻🌻🌻@EOTC2921🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

🌻✞🕊 #ስርዓተ_በዓል_ወጾም_ዘኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ቤተ_ክርስቲያን 🕊✞🌻 🌻🌼✞ https://t.me/EOTC2921 ✞🌼🌻 ❀✞ #ዓመተ_ምህረት፥ ፪፻፲፫(2013 ዓ.ም) ❀✞ #ወንጌላዊ፥ ማቴዎስ ❀✞ #የዘመን_መለወጫ_ቀን፥ ዐርብ ❀✞ #አበቅቴ፥ ፲፯(17) ❀✞ #መጥቅዕ፥ ፲፫(13) ❀✞ #ጾመ_ነነዌ፥ የካቲት ፲፭(15) ❀✞ #ዐብይ_ጾም፥ የካቲት ፳፱(29) ❀✞ #ደብረ_ዘይት፥ መጋቢት ፳፮(26) ❀✞ #ሆሳዕና፥ ሚያዝያ ፲፯(17) ❀✞ #ስቅለት፥ ሚያዝያ ፳፪(22) ❀✞ #ትንሣኤ፥ ሚያዝያ ፳፬(24) ❀✞ #ርክበ_ካህናት፥ ግንቦት ፲፰(18) ❀✞ #ዕርገት፥ ሰኔ ፫(3) ❀✞ #ጰራቅሊጦስ፥ ሰኔ ፲፫(13) ❀✞ #ጾመ_ሐዋርያት፥ ሰኔ ፲፬(14) ❀✞ #ጾመ_ድኅነት፥ ሰኔ ፲፮(16) 🌻🌼✞ #እንኳን_አደረሳችሁ ✞🌼🌻 🌻🌼✞ #እንኳን_አደረሰን❗ ✞🌼🌻 🌻🌻 #በእግዚአብሔር_ፈቃድ 🌻🌻 🌾መጪው_2013 ዓ.ም፦ 🌻የተከፋ፣ የአዘነና የአለቀሰ፤ የሚደሰትበት። 🌻የተራበና የተጠማ፤ የሚጠግብበት። 🌻የተሰደደ፤ በሰላም ተመልሶ የሚኖርበት። 🌻ፍቅር፣ ዕምነትና ትዕግሥት፤ የምንጎናጸፍበት። 🌻ዕውቀቱን፣ ጥበብና ማስተዋሉን፤ የምናገኝበት። 🌻ከችግርና ከመከራ፤ ተላቀን በሐይማኖት በምግባር የምንጸናበት ዘመን ይሁንልን። ✞አሜን✞ 🙏✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ልዑል ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✞🙏 ✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

🌼 መልካም አዲስ ዓመት 🌼    2013   አብረን እንጓዝ ! ብለን ተነስተናል በመንፈሳዊ ስራዎቻችን ውስጥ መልካም የሚባል አሻራ ለማሳረፍ እርምጃ ጀምረናል ይቀላቀሉን ይህ አጥንትን የሚያጠነክሩ መንፈስን የሚያለመልሙ ከተዋህዶ መፅሀፍት መዝገብ ስነጽሁፋዊ መፍለቂያ የሆነው የተዋህዶ Tube ነው       ይህ የተዋህዶ ቲዩብ ማዕዳችን ነው ! 🌻 መንፈሳዊ መፅሀፍቶችን እየዳሰስን እምንማማርበት 🌻 ጥንካሬን ያድለን ዘንድ የቅዱሳናትን ታሪክ 🌻 የደጋግ አባቶች ተግሳፃትን የምናወሳበት 🌻 ዝማሬዎች 🌻 ስብከቶች የምናቀርብበት የ Youtube ቻናል ነው ።  © የተዋህዶ ቲዩብ ያወቅነውን ልናሳውቅ ዘንድ ለወዳጆ መልካም ሕሊናን እንፍጠር በ Youtube መተናል  ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው Subscribe ያርጉ ! 🔻 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://www.youtube.com/channel/UCPPV0Jj4491QFJIHxs9WyJQ?subconfirmation=yes 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

🌻 ልጄ ሆይ በክርስትናህ መጎልመስ ከፈለክ ከቅዱሳት መፅሀፍት ጋር ራስህን አዛምድ                          .......................................                    🌼  ቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ  🌼   አብረን እንጓዝ ! ብለን ተነስተናል በመንፈሳዊ ስራዎቻችን ውስጥ መልካም የሚባል አሻራ ለማሳረፍ እርምጃ ጀምረናል ይቀላቀሉን ይህ አጥንትን የሚያጠነክሩ መንፈስን የሚያለመልሙ ከተዋህዶ መፅሀፍት መዝገብ ስነጽሁፋዊ መፍለቂያ የሆነው የተዋህዶ Tube ነው       ይህ የተዋህዶ ቲዩብ ማዕዳችን ነው 🌻 መንፈሳዊ መፅሀፍቶችን እየዳሰስን እምንማማርበት 🌻 ጥንካሬን ያድለን ዘንድ የቅዱሳናትን ታሪክ 🌻 የደጋግ አባቶች ተግሳፃትን የምናወሳበት 🌻 ዝማሬዎች 🌻 ስብከቶች የምናቀርብበት የ Youtube ቻናል ነው ።  © የተዋህዶ ቲዩብ ያወቅነውን ልናሳውቅ ዘንድ ለወዳጆ መልካም ሕሊናን እንፍጠር በ Youtube መተናል  ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው Subscribe ያርጉ ! 🔻 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://www.youtube.com/channel/UCPPV0Jj4491QFJIHxs9WyJQ?subconfirmation=yes 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ሴጋ (Masterbation) ➾ በእምነት ላይ ➾ በትዳር ላይ ➾ በወጣትነት ➾ አጠቃላይ በወደፊት እጣ ፋንታችን ላይ ሚያመጣው ችግር ምንድነው?? እንዴት መላቀቅ ይቻላል ? 👆👆በዚህ ዙሪያ ማወቅ ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ቻናላችንን ይቀላቀላሉ👇👇 👉 https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng ▰▰▰ በዩቲዩብ ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናላችንን Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ!! 👇 👉 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA 👉 https://youtu.be/SY-D-qGgT0U ▰▰▰▰▰ 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

🌾⛪️ #ቅዱስ_ሩፋኤል ⛪️🌾 💚ቅዱስ ሩፋኤል ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲኾን፤ ሩፋ ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፤ ሄኖክም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥3)። 💚ይኽ መልአክ በራማ ሰማይ ያሉ ነገደ መናብርትን የሚመራቸው ነው፡፡ ነገደ መናብርት ያላቸው ቅዱስ ሩፋኤል የሚመራቸው በራማ ሰማይ የሚኖሩ ነገደ መላእክት ናቸው፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ “ወለዳግም ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ መናብርት ወሊቆሙ ሩፋኤል እሉ እሙንቱ እለ ይቀልል ሩጸቶሙ እምነፋስ ወእለ ይጸውሩ ወላትወ መብረቅ ወኲናተ እሳት ዘይነድድ ወአንበሮሙ በዳግሚት ሰማይ” ይላል በራማ ሰማይ የሚገኘውን ኹለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፤ እነዚኽም ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ በራማ በኹለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ከሚመራው ከዚኽ ነገድ 24ቱ ካህናተ ሰማይ ወጥተዋል፡፡ 💚አባ ጊዮርጊስም በሰዓታቱ ላይ፡- “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጽርሐ አርያም ማኅፈዱ መካነ ትጉሃን ዐጸዱ ካህናተ ሰማይ ቅዉማን በዐውዱ አክሊላቲሆሙ ያወርዱ ቅድመ መንበሩ እንዘ ይሰግዱ ይርዕዱ ወኢይዝብጦሙ ሶበ ይበርቅ ነዱ” (ጽርሐ አርያም አዳራሹ፤ የትጉሃን መኖሪያ ቦታው የሚኾን እግዚአብሔር ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ተብሎ በአንድነት በሦስትነት ይመሰገናል፤ ካህናተ ሰማይ በዙሪያው ይቆማሉ፤ በዙፋኑ ፊት እየሰገዱ አክሊሎቻቸውን ያወርዳሉ፤ እሳትነቱ (ባሕርዩ) በሚበርቅ፣ ወገግ በሚል ጊዜ እንዳይመታቸው ይንቀጠቀጣሉ) ይላል 💚ሊቁ እንደጠቀሰው በዕለተ እሑድ ሥሉስ ቅዱስ ሰባቱን ሰማያት ፈጥረዋል፤ ከዚያም ልዑል እግዚአብሔር በዕለተ እሑድ ሰባቱን ሰማያት ከፈጠረ በኋላ ሊቁ በአክሲማሮስ እንደገለጸው ከቅዱሳን መላእክት መኻከል፡- “ወእምዝ ነሥአ እግዚአብሔር እምሰራዊተ ሩፋኤል ፳ወ፬ተ ሊቃናተ ወአቀሞሙ ዐውደ መንበሩ፤ ወሰመዮሙ ለእሙንቱ ካህናተ ሰማይ ወወሀቦሙ ማዕጠንታተ ዘእምወርቀ እሳት ወአክሊላተ ብርሃን ዘእምጳዝዮን ወአብትረ ዘከተማሆን መስቀል ወአልበሶሙ አልባሰ ክህነት” ይላል ከሰራዊተ ሩፋኤል ፳፬ት ሊቃናትን መርጦ በመንበረ ስብሐት በመጋረጃዋ ውስጥ ዙሪያዋን ክንፍ ለክንፍ ገጥሞ አቁሟቸዋል (ሕዝ ፩፥፲፩-፲፪)፤ ቊጥራቸውን ኻያ አራት ማድረጉ በኻያ አራቱ ጊዜያት ጸልየው ሌላውንም ራሳቸውንም ጠብቀው ዋጋቸውን ተቀብለው የሚኖሩ በመኾናቸው ሲኾን እነዚኽንም መላእክት “ካህናተ ሰማይ” ሲላቸው የእሳት የወርቅ ጽና ሲያሲዛቸው የብርሃን አክሊል ጳዝዮን የሚባል የብርሃን ዘውድ ደፍቶላቸዋል፤ የብርሃን ዘንግ ማኅተሙ መስቀል የኾነ ሲያሲዛቸው የብርሃን ካባ ላንቃ ሕብሩ መብረቅ የመሰለ አልብሷቸዋል ( ራእ ፬፥፬-፭፤፲-፲፩)። 💚እነዚኽ ሰማያውያን ካህናት በአንድ ላይ ባጠኑ ጊዜ ዛሬ በክረምት ጊዜ ጉም ተራራውን እንደሚሸፍነው ከማዕጠንታቸው የሚወጣው ጢስ መልኩ መብረቅ፣ ድምፁ ነጐድጓድ፣ መዐዛው መልካም የኾነና ጽርሐ አርያም፣ መንበረ መንግሥት የተባሉትን የብርሃን ሰማያት የሚሸፍንና የሚጋርድና ከጢሱ ጋር የቅዱሳን ጸሎት ዐብሮ ወደ እግዚአብሔር ፊት ይወጣል፤ “ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሠዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሠዊያ ላይ ለቅዱሳን ኹሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ” እንዳለ ዮሐንስ በራእዩ (ራእ ፰፥፫-፭)፡፡ 💚ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በአክሲማሮስ ላይ፦ “ወቦ ኪሩቤል ይቀውሙ በየማን በአምሳለ ቀሳውስት ወሱራፌል ይቀውሙ በአምሳለ ዲያቆናት ወድኅሬሆሙ ካህናተ ሰማይ ወቦ እልፍ አእላፋት ወትእልፊተ አእላፋት መብረቅ ወነጐድጓድ ወሠረገላሆሙኒ ምሉኣነ አዕይንት” እንዳለ ኪሩቤል በቀኝ ሱራፌል በግራ ከፍ ብለው ካህናተ ሰማይ ክንፍ ለክንፍ ገጥመው በስተኋላቸው ሲታዩ በሰማይ ውዱድ ዙሪያ እልፍ አእላፋት መብረቅ፣ ነጐድጓድ፣ ሠረገላ፣ እንደ መስታየት ብሩህ የኾነ ሲኖርበት እነዚኽ ቅዱሳን መላእክትም ሳያቋርጡ “ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር” እያሉ ፈጣሪያቸውን በአንድነቱ በሦስትነቱ ያመሰግኑታል (ራእ ፬፥፰)፡፡ 💚ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስም ስለነዚኽ ቅዱሳን መላእክት ሲገልጽ “ወኲሎሙ ሰራዊተ መላእክት እለ ይቀውሙ ቅድሜሁ ይጸርሑ ወይባርክዎ ለእግዚአብሔር…” (በፊቱ የሚቆሙ የመላእክት ሰራዊትም ኹሉ ጩኸው ያመሰግኑታል፤ የመላእክት አለቆችም ለማይታይ ለባለዚኽ ስም ዘንበል ብለው ይሰግዳሉ፤ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑና የሚዘምሩ ዙፋኑን የሚሸከሙ አርባዕቱ እንስሳ ጩኸው ያመሰግኑታል፤ ዕጣንን የተመሉ የወርቅ ማዕጠንት በእጆቻቸው ያለ ኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ይኸውም የቅዱሳን ጸሎት ነው እስከ ዘላለሙ ሕያው በኾነው ፊት የሚቀበለው መሥዋዕት አድርገው ወደ ላይ ያሳርጋሉ) በማለት የቅዱሳንን ጸሎት ቅድመ እግዚአብሔር በማዕጠንታቸው ለማሳረግ የተመረጡት መላእክት ኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይ መኾናቸውን አስተምሯል፡፡ 💚ይኽ መልአክ ጦቢትን የተራዳ መልአክ ነው፤ ይኽ ጦቢት ዐሥሩ ነገድ በ፯፻፳ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ሲማረኩ ዐብሮ የተማረከ ጻድቅ ሰው ነው፤ ይኽ ሰውን በመርዳት በደግነቱ የታወቀው ጦቢት ከመንገድ ወድቆ የተገኘ በድን ቀብሮ፤ በዚያው ሌሊት ከቅጥሩ አጠገብ ፊቱን ተገልጦ ተኝቶ ሳለ አዕዋፍ ትኩስ ፋንድያ ዐይኑ ላይ ጥለውበት እንደ ብልዝ ያለ ወጥቶበት ዐይኑ ጠፋ፤ ሚስቱም ባለማስተዋል “አይቴ ውእቱ ምጽዋትከ ወጽድቅከ” (በጐነትኽ ምጽዋትኽ ያዳነኽ ወዴት ነው?) በማለት በተናገረችው ጊዜ ዐዝኖ ሞትን ተመኘ (ጦቢ ፪፥፲፬)፡፡ 💚ያን ጊዜ መልአኩ ሩፋኤል ርሱንና ባሎቿ ስለሞቱባት ቤተሰቦቿ ያንቋሽሿት የነበረችውን የራጉኤል ልጅ ሳራን ለማዳን ተልኮ በመምጣት አስቀድሞ በርሷ ላይ ዐድሮ ባሎቿን ይገድልባት የነበረውን ጋኔን አስወጥቶ የጦቢት ልጅ ጦብያ እንዲያገባት አድርጓል፤ በዚኽም “ፈታሔ ማሕፀን” ተብሏል፡፡ በኋላም ወደ ጦቢት በመኼድ ረዥም ዘመን የታወረ ዐይኑን አብርቶለት “አነ ውእቱ ሩፋኤል መልአክ አሐዱ እምነ ሰብዐቱ ቅዱሳን መላእክት” (ከሰብዐቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሩፋኤል እኔ ነኝ) ብሏቸው ተሰውሯል (ጦቢ ፲፪፥፲፭)፡፡ ✍በመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ 🙏✞ የቅዱስ ሩፋኤል ረድኤት በረከት ይደርብን ✞🙏 ✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

💚ይኸውም ምሳሌነቱ በመተርጉማን እንደተተነተነው ካህኑ መልከ ጼዴቅ በስንዴና በወይን ያስታኩት እንደነበር ሊቀ ካህናት ጌታም ሥጋውን ደሙን በስንዴና በወይን ሰጥቶናልና (ዘፍ ፲፬፥፲፰፤ ማቴ ፳፮፥፳፮-፳፯)፡፡ ✥መልከ ጼዴቅ ሹመቱን ከእግዚአብሔር ተሾሞታል እንጂ ከእገሌ ተሾመው እንዳይባል፤ ሊቀ ካህናት ጌታም ሥልጣኑ የባሕርዩ ነው እንጂ ከሌላ የተሰጠው አይደለምና፡፡ ✥መልከ ጼዴቅ አባትና እናት ቢኖሩትም ቅሉ በሌሎች መጻሕፍት እንጂ በሌዋውያን መጽሐፍ የአባቱና የእናቱ ነገር እንዳልተጻፈ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በእውነት ለቀዳማዊ ልደቱ እናት፤ ለደኀራዊ ልደቱ አባት የለውምና፡፡ ✥መልከ ጼዴቅ ምንም መነሻና መድረሻ ቢኖረውም ቅሉ ለዘመኑ ጥንት ለአነዋወሩ ፍጻሜ አለው ብሎ የጻፈለት የሌዋውያን መጽሐፍ እንደሌለ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን አማን በአማን ለዘመኑ ጥንት ለአነዋወሩ ፍጻሜ የሌለው፤ ቅድመ ዓለም የነበረ፤ አኹንም ያለ፤ ዓለምንም አሳልፎ የሚኖር ነውና፡፡ ✥አብርሃም ለመልከ ጼዴቅ ከዐሥር አንድ እንደሰጠው፤ ምእመናንም ዘወትር ዐሥራተ ጾም ዐሥራተ ጸሎታቸውን ለጌታ ይሰጣሉና፡፡ ✥መልከ ጼዴቅ የስሙ ትርጓሜ “የእውነት ንጉሥ” እንደኾነ፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ለመንግሥቱ ፍጻሜ የሌለው ንጉሠ ነገሥት ነውና፡፡ ✥ዳግመኛም ይኽ መልከ ጼዴቅ “የሰላም ንጉሥ” ተብሎ እንደተጠራ፤ ጌታም በከበረ ደሙ ፈሳሽነት ለኹሉም ሰላምን ያደለ “ወሀቤ ሰላም፣ ንጉሠ ሰላም” ነውና ተመስሎበታል (ኤፌ ፪፥፲፬-፲፯፤ ዮሐ ፲፬፥፳፯)፡፡ ✥ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የመልከ ጼዴቅን ምሳሌነት ስለዚኽ ነገር አምልቶ አስፍቶ ሲያስረዳ፡- ☞ “ናሁኬ አብጽሐ ዘይንእስ ኀበ ዘየዐብዮ ወዘይቴሐት ኀበ ዘይትሌዐሎ መሥዋዕተ መልከ ጼዴቅ…” (እነሆ የሚያንሰው ወደሚበልጠው ዝቅ ዝቅ የሚለውም የመልከ ጼዴቅ መሥዋዕት አደረሰ፤ የመልከ ጼዴቅስ መሥዋዕት የመለኮት ኀይል በላዩ አላደረም፤ የርሱን ሥጋና ደም ብሎ ይጠራው ዘንድ ያን ጊዜ ክርስቶስ ሰው አልኾነምና፤ ዳሩ ግን ለምእመናን እንደሚሰጥ የተጸለየበት ኅብስትና የተባረከ ጽዋ ክብር ነበረው (ዘፍ ፲፬፥፲፰) የመልከ ጼዴቅም ክህነት እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ክህነት ፍጹም አልኾነም፤ አብ ከሰማይ “የምወድደው ልጄ ይኽ ነው፤ ርሱን ስሙት” ብሎ አልመሰከረለትምና፤ መልከ ጼዴቅ አምላክ አይደለምና፨ ✢መልከ ጼዴቅ አብርሃምን እንደባረከው (ዘፍ ፲፬፥፳) ክርስቶስም ደቀ መዛሙርቱን ባረካቸው (ሉቃ ፳፬፥፶)፤ ✢መልከ ጼዴቅ ከአብርሃም ከዐሥር አንድ እንደተቀበለ ክርስቶስም ከሰብአ ሰገል እጅ መንሻ ተቀበለ (ማቴ ፪፥፲፩)፤ ✢መልከ ጼዴቅ በኦሪት መጽሐፍ የእግዚአብሔር ካህን ተብሎ እንደተጠራ (ዘፍ ፲፬፥፲፰፤ መዝ ፻፱፥፬) ክርስቶስም በጳውሎስ አንደበት ሊቀ ካህናት ተባለ (ዕብ ፭፥፱-፲)፤ ✢መልከ ጼዴቅ የሳሌም ንጉሥ እንደተባለ ክርስቶስም የእስራኤል ንጉሥ ተብሎ ተጠራ፤ ሚክያስ የኤፍራታ ምድር የኾንሽ አንቺ ቤተልሔም ከይሁዳ መሳፍንት አታንሺም፤ ወገኖቼ እስራኤልን የሚጠብቃቸው ንጉሥ ከአንቺ ይወጣልና ብሎ ተናግሯልና (ሚክ ፭፥፪)) ይላል፨ 💚ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፦ “ሰላም ለመልከ ጼዴቅ ዐቢይ ካህን አምሳሊሁ ለወልደ እግዚአብሔር ዘእእመረ ምስጢሮ ኅቡአ ዘሀሎ ይትገበር” (ሊከናወን (ሊፈጸም) ዘንድ ያለውን ስዉር (ድብቅ) ምስጢሩን ያወቀ፤ ለእግዚአብሔር ልጅ ምሳሌው ለኾነ ለታላቁ ካህን ለመልከ ጼዴቅ ሰላምታ ይገባል) ብሎ ሰላምታ አቅርቦለታል፨ 💚ኢትዮጵያዊው ሊቅ ዐርከ ሥሉስም በዐርኬው ላይ፦ "ሰላም ለመልከ ጼዴቅ አምሳሉ ወሱታፉ ለዘመጽአ ቃል በደመና ድንግል ዐፅፉ ጠቢባን ግብሮ በከመ ጸሐፉ ለሥጋ አቡነ አዳም ኀበ ተሐንጸ ምዕራፉ ዝንቱ ካህን ይነብር ለዝሉፉ" (በደመና የተመሰለች የድንግልን ሥጋ ተጎናፅፎ (ተዋሕዶ) ለመጣው ሥግው ቃል ምሳሌው ለኾነ ለመልከ ጼዴቅ ሰላምታ ይገባል፤ ጠቢባን ሥራውን እንደጻፉ የአባታችን አዳም የሥጋው ማረፊያ በታነጸበት ይኽ ካህን ለዘወትር ይቀመጣል) በማለት ድንቅ ውዳሴን ያቀርብለታል፨ 💚ታላላቅ ሊቃውንት ሕገ ኦሪት ሳይሠራ ገና በሕገ ልቡና አበ ብዙኃን አብርሃምን የባረከው የወልደ እግዚአብሔር ምሳሌ የኾነው መልከ ጼዴቅ ከነገደ ሴም ሳይኾን ከነገደ ካም በመኾኑ የርሱም ርስት አህገራችን አፍሪካና ምስርን ኖባን አንድ አድርጋ የገዛች ኢትዮጵያ ናትና ታላቋ ሀገራችን ኢትዮጵያ ገና ሕገ ኦሪት ለእስራኤል ሳይሠራ በሕገ ልቡና አምላኳ እግዚአብሔርን በመልከ ጼዴቅ በኩል ስታመልክ የኖረች ናት ይላሉ፨ 💚ካም የነበረበት ከአምላካችን ከክርስቶስ ልደት በፊት 3244 ዓመት ሲኾን በዚኽ ላይ የሐዲስ ኪዳንን የ2011 ዓመተ ምሕረትን ስንጨምርበት 5255 ዓመታት ሳታቋርጥ በሦስቱ ኪዳናት በሕገ ልቡና፣ በሕገ ኦሪት፣ በሕገ ወንጌል አምላኳ ፈጣሪዋ ልዑል እግዚአብሔርን ስታመልክ ኖራለች፤ እስከ ዕለተ ምጽአትም ንጹሕ ምስጋናዋን ለፈጣሪዋ ለክርስቶስ ታቀርባለች፨ 💚"ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የሚማልዱኝ የተበተኑት ሴቶች ልጆቼ ቍርባኔን ያመጡልኛል።" (ትንቢተ ሶፎንያስ 3፥10) "የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር" (ትንቢተ አሞጽ 9፥7) ✍በመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ 🙏✞የመልከ ጼዴቅ በረከት ይደርብን✞🙏 ✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

🌾⛪️ #ታላቁ_ካህን_መልከ_ጼዴቅ ⛪️🌾 ጳጉሜ ፫ 💚ይኽ መልከ ጼዴቅ ዐፅመ አዳምን እንደ ታቦት አድርጎ በኅብስት በወይን መሥዋዕት ያቀርብ የነበረ ደገኛ ካህን ነበር (ዘፍ ፲፬፥፲፰)፡፡ ይኸውም ሊቃውንት እንደጻፉልን ኖኅ ከጥፋት ውሃ በኋላ ከመርከብ ሲወጣ ከዚኽ ኹሉ ላዳነኝ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባዋል ሲል፤ ዐፅመ አዳምን እንደታቦት አድርጎ መሥዋዕት ሠዋ፡፡ 💚ከዚኽም በኋላ ሴምን ጠርቶ “ዐጽመ አዳምን ወስደኽ እግዚአብሔር ወዳዘዘኽ ቦታ አኑር” ብሎታል፡፡ ሴምም ከካም ወገን የተወለደው መልከ ጼዴቅን ከናት ካባቱ አሰናብቶ ዐጽሙን አሸክሞ ይዞት ኼደ፤ መላእክት እየመሩ መስቀል ከሚተከልበት ቀራንዮ አደረሱት እዛም ሲደርስ ምድር ተከፈተችለት፤ ዐፅመ አዳምንም አግብቶ አኖረ መልከ ጼዴቅም ዐፅመ አዳምን እንደታቦት አድርጎ ዐሥራ ኹለት ደንጊያዎችን በመትከል መሥዋዕት ጸሎት ያቀርብ ነበር፡፡ 💚የሶርያ ሰዎች በነገር ተከራክረው ወደ ርሱ ሲኼዱ እውነት ይፈርድላቸው ስለነበር “ንጉሠ ጽድቅ” ሲሉት፤ ቢጣሉ ስለሚያስታርቃቸው “ንጉሠ ሰላም” ብለው ጠርተውታል፡፡ 💚ክህነቱም ከሌዊ የሚበልጥ ደገኛ ክህነት ነበርና በስንዴና በወይን ሲያስታኩት ኖሯል፡፡ ምግቡንም መላእክት ያመጡለት ነበር፤ ልብሱም ዳባ ነበር፡፡ 💚የትውልዱንም ነገር ዮሐንስ መደብር ባራተኛው ክፍል ላይ:- “መልከ ጼዴቅ ውእቱ ዘወፅአ እምነገደ ሴዱ ወልደ ንጉሠ ምስር ወኖባ፤ ወውእቱ ሴዱ ዘነግሠ ከነዓን፣ ወውእቱ አምነገደ ጽኑዓን፤ ወውእቱ ተጻብኦሙ ወተቀንዩ ሎቱ፤ ወሶበ አስተፍሥሕዎ ነበረ ውስቴታ ወሐነጸ ሀገረ ወሰመያ በስመ ዚኣሁ ሳይዳ፤ ወእስከ ዮም ትሰመይ ሳይዳ ወአቡሁ ለመልከ ጼዴቅ ወቦአ እምነ ሳይዳ” (የኖብና የምስር ንጉሥ ልጅ ከሚኾን ከሴዱ ነገድ የወጣ (የተወለደ) መልከ ጼዴቅ ነው፡፡ ያውም ሴዱ በከነዓን የነገሠ ነው፤ ርሱም ከጠንካሮቹ ነገድ ነው፤ ርሱም ተዋጋቸውና ተገዙለት፤ በስደቱም ጊዜ በውስጧ ተቀመጠ፤ ከተማንም ሠርቶ በርሱ ስም ሳይዳ ብሎ ጠራት፣ እስከ ዛሬም ሳይዳ በመባል ትታወቀለች፤ የመልከ ጼዴቅ አባትም ከሳይዳ ወጣ) ይለዋል፡፡ 💚በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ ፲፬ ላይ እንደምናነበው ዐምስቱ ነገሥተ ሰዶም ወገሞራ ለአራቱ ነገሥተ ኮሎዶጎሞር ፲፪ ዓመት ገብረው በ፲፫ኛው ዓመት አንገብርም በማለታቸው፤ በዐዘቅተ ኤሌቅ በተዋጉት ውጊያ፤ አራቱ ነገሥተ ኮሎዶጎሞር ድል አድርገው ሎጥን ከዚያ አግኝተው ማርከውታል፤ አብርሃምም ይኽነን ሰምቶ ከቤተሰቦቹ ፫፻፲፰ት ሰዎች ይዞ ኼዶ ነገሥተ ኮሎዶጎምርን ድል ነሥቶ የተማረከ ወንድሙ ሎጥን መልሶታል፡፡ 💚ይኽም ምሳሌ ነው አብርሃም የጌታ፤ ሎጥ የሃይማኖት፤ ፫፻፲፰ቱ የ፫፻፲፰ ሊቃውንት፤ አራቱ ነገሥተ ኮሎዶጎሞር የመናፍቃን፤ ዐምስቱ ነገሥተ ሰዶም የምእመናን ምሳሌ፤ አብርሃም ፫፻፲፰ ሰው ይዞ አሕዛብን ድል ነሥቶ ሎጥን እንደመለሰ ጌታም በ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ዐድሮ ሃይማኖትን የመመለሱ ምሳሌ እንደኾነ መርተርጒማነ ብሉይ ያስተምራሉ፡፡ 💚ከዚኽ በኋላ አብርሃም ደስ ብሎት ለአዳምና ለልጆቹ የድኅነት ተስፋን የሰጠ አምላክን በዐይነ ሥጋ ለማየት ተመኝቶ “በመዋዕልየኑ ትፌኑ ወልደከ ወሚመ ታርእየኒ ኪያሃ ዕለተ” (ልጅኽን በዘመኔ ትልከዋለኽ? ወይንስ ዕለቷን ታሳየኛለኽ) አለው፤ ጌታም “አኮ ዘአርእየከ ኪያሃ አላ አምሳሊሃ ዕድዎ ለዮርዳኖስ ወትረክቦ ለመልከ ጼዴቅ” (ያችንስ ዕለት የማሳይኽ አይደለም፤ ምሳሌዋን እንጂ፤ ዮርዳኖስን ተሻገር መልከ ጼዴቅን ታገኘዋለኽ) ብሎ ምሳሌውን ጠቆመው። 💚አብርሃምም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ሲኼድ ታላቅ ግርማ የነበረውን መልከ ጼዴቅን አይቶ ደነገጠ፤ መልከ ጼዴቅም አብርሃምን “አትፍራ፤ አንተን ወደ ዮርዳኖስ እንድትሻገር ያዘዘኽ እግዚአብሔር እኔን ኅብስተ አኰቴት ጽዋዐ በረከት ይዤ ወደ ዮርዳኖስ እንድመጣ ለአንተ እንድሰጥኽ አዝዞኝ” ነው፤ በማለት ከያዘው ኅብስትና ወይን ለአብርሃም ሰጥቶ ባርኮታል፤ አብርሃምም ከያዘው ኹሉ ዐሥራትን ሰጠው፡፡ 💚ይኽ አብርሃምም በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሥጋውን ደሙን በኅብስት በወይን የሚሰጥ መኾኑን በማወቁ እጅጉን ተደስቷል፤ ጌታም ይኽቺን ታላቅ ሰዓት አብርሃም ለማየት እንደተመኘ ለአይሁድ “አባታችኍ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት ዐደረገ፤ አየም ደስም አለው” በማለት ነግሯቸዋል (ዮሐ ፰፥፶፮)፡፡ 💚ሊቁ አባ ጊዮርጊስም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ለመጣ ለአብርሃም መልከ ጼዴቅ በመሶብ ከያዘው ከስንዴው ኅብስት በጽዋው ከያዘው ከወይኑ እንደሰጠው ኹሉ፤ ዘመኑ ሲፈጸም አካላዊ ቃል ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ተወልዶ፤ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማሕፀነ ዮርዳኖስ ለተወለድነው ክርስቲያኖች፤ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በስንዴና በወይን አምሳል የሰጠን መኾኑን በእንዚራ ስብሐት መጽሐፉ ላይ፡- "መካነ ሞጻሕቱ አንቲ ለመልከ ጼዴቅ በኅብስተ ሥርናይ ወወይን ዘከሠተ ምሥጢረ ጽድቅ" (በወይንና በስንዴ የእውነትን ምስጢር የገለጠ የመልከ ጼዴቅ የመሠዊያ ቦታ አንቺ ነሽ) በማለት ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ተወልዶ ቅዱስ ሥጋውን በአምሳለ ኅብስት የሰጠ ምግበ ርኁባን፤ ክቡር ደሙን በአርአያ ወይን የሰጠ ስቴ ጽሙኣን፤ አማናዊ ካህን ኢየሱስ ክርስቶስን ያገኘንባት መኾኗን መስክሯል። 💚በተመሳሳይ መልኩ ሊቁ በነገረ ማርያም ላይ፦ "ወአጸደ ወይን ዘጽድቅ ዘሐንበበቶ ለአስካለ መለኮት ዘርእየ አምሳሊሁ መልከ ጼዴቅ አመ አውጽሐ በኅብስተ ሥርናይ ወበደመ ወይን" (መልከ ጼዴቅ በስንዴ ኅብስትና በወይን ደም ባስታኮተ ጊዜ፤ ምሳሌውን ያየው የመለኮት ፍሬን ያፈራቺው እውነተኛ የወይን ቦታ ርሷ ናት) በማለት ያመሰጥራል። 💚ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ጌታን ከመልከ ጼዴቅ ጋር አነጻጽሮ ቢጠቅስም መልከ ጼዴቅ ግን ምሳሌ ብቻ እንደኾነ ሳይጠቅስ አላለፈም፤ ይኸውም በዕብራውያን ክታቡ ምዕ ፯፥፩-፫ ላይ፦ “የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን የኾነ ይኽ መልከ ጼዴቅ አብርሃም ነገሥታትን ገድሎ ሲመለስ ከርሱ ጋር ተገናኝቶ ባረከው፤ ለርሱም ደግሞ አብርሃም ከኹሉ ዐሥራትን አካፈለው የስሙም ትርጓሜ በመዠመሪያ የጽድቅ ንጉሥ ነው፥ ኋላም ደግሞ የሳሌም ንጉሥ ማለት የሰላም ንጉሥ ነው፤ አባትና እናት የትውልድም ቍጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት ለሕይወቱም ፍጻሜ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ኾኖ ይኖራል” ይለዋል፡፡ ✢✥❖ #ይቀጥላል ❖✥✢

#በደላችንን_ይቅር_በለን https://telegram.me/EOTC2921 1. እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን እንደሚወድ አምላካችን ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ባይወድ ኖሮ ይቅርታን እንድንጠይቅ አይነግረንም ነበር፡፡ አዎ እኛ ከተመለስን ምንም ያህል በደለኛ ብንሆን ይቅር ሊለን፤ ምንም ያህል ብንቆሽሸ ሊያድነን ዝግጁ ነው፡፡ እንዲህ እያለ ይጠራናል፤ «እናንተ ሸክማችሁ የከበዳችሁ፤ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ»፡፡ ስለዚህ በዚሀ ጸሎትም ላይ «በደላችንን ይቅር በለን» ብለን እንድንጠይቀው አስተማረን፤ ይቅር ይለን ዘንድ፡፡ 2. ይቅር ለመባል ምን ማድረግ እንዳለብን፤ ይቅር ሊለን ስለወደደም ይቅርታን ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለብን በዚሁ ቃል ነግሮናል፤ ማድረግ ያለብን ምንድን ነው? - ኀጢአታችንን ማወቅ፣ ማመን፣ ማስታወስ - የበደሉንን ይቅር ማለት - ይቅርታን መለመን #ኅጢአታችንን_ማወቅ /ማመን/ ጌታ «በደላችንን ይቅር በለን» ብለን እንድንጸልይ ሲነግረን በመጀመሪያ ደረጃ በደለኛ እንደሆንን እያስታወስን /እንድናስታውስ እያደረገን/ ነው፡፡ ሁልጊዜም በማሰብ፣ በመናገርና በማድረግ የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ የሆነውን ልባችንን /ኅሊናችንን/ እና ሰውነታችንን እናቆሽሻለን፤ መድኃኔዓለም ክርስቶሰ የሞተለትን ማንነታችንን እናጎድፋለን፡፡ ይህም የሰው ልጆች በቅድስና እርሱን መስለን እንድንኖር በኋላም የተዘጋጀልንን የዘለዓለም መንግሥት እንድወርስ ብቻ ፈቃዱ የሆነውን እግዚአብሔርን ያሳዝናል፤ በአርአያውና በአምሳሉ ለክብር የፈጠረው ሰውነታችን መጉደፍ ያስቆጣዋል፤ ንጹሐ ባሕርይ የሆነ እርሱ ኀጢአት አይስማማውምና፡፡ እንግዲህ ይቅር ለመባል በመጀመሪያ እንዲህ ኀጢአት እየሰራን መሆኑን ማወቅና ማመን ያስፈልገናል፡፡ ወደዚህ ዕውቀት ለመድረስም የቅዱሳት መጻሕፍትን ቃል መማር የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ስህተት የሚታወቀው ያለውን ሁኔታ /ድርጊታችንን ንግግራችንን፣ ሀሳባችንን.. / መሆን ከነበረበት /ከትክክለኛው/ ጋር በማነጻጸር በሚዛን ላይ በማስቀመጥ ነው፡፡ የማነጻጻሪያ ሚዛኖቻችን ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈ ሕግጋትና ትዕዛዛት ናቸው፡፡ እነዚህን ስናውቅ ጉድለቶቻችን፣ ድካሞቻችን ፍንተው ብሎ ይታዩናል፡፡ አሊያ ግን እየበደለን ያልበደልን ሊመስለን ይችላል፡፡ https://telegram.me/EOTC2921 #የበደሉንን_ይቅር_ማለት ጌታ በዚህ ጸሎት ይቅርታ እንድንጠይቀው በማስተማር ይቅር ሊለን እንደሚወድ ዝግጁም እንደሆነ ቢነግረንም ይቅር ለመባል ግን እኛ የበደሉንን ይቅር ማለታችን የግድ እንደሆነ በግልጽ አስቀምጦልናል፤ «በደላችንን ይቅር በለን» ከማለታችን በፊት «እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል» እንድንል ያዘዘን እኛ ይቅርታ የምናገኘው ሌሎችን ይቅር ስንል ብቻ መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡ ጌታችን ይህንን ጉዳይ በሌሎች የተለያዩ ቦታዎችም በተደጋጋሚ አስተምሮናል፤ በዚሁ በተራራው ስብከት ይኸው ጉዳይ ሁለት ጊዜ በጌታችን ትምህርት ተሰጥቶበታል፡፡ «እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል፡፡ » /ማቴ.7-2/ በሌላ ቦታም እንዲህ ሲል ይህንኑ ጉዳይ በምሳሌ አስተምሯል፤ መንግስተ ሰማያት ባሮቹን ለመቆጣጠር የወደደን ንጉሥ ትመስላለች መቆጣጠርም በጀመረ ጊዜ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፡፡ ባለ እዳው ሰው የሚከፍለው ስላጣ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ንጉሡ አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ ባርያው ወድቆ ሰገደለትና ጌታ ሆይ ታገሰኝ፤ ሁሉንም እከፍልሃለሁ አለው፡፡ የዚያም ባርያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው፡፡ ይህ ባርያ ግን ወጥቶ ከባልጀሮቹ /እንደርሱ ባርያ ከሆኑት/ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን አንዱን አገኘና ዕዳህን ክፈለኝ ብሎ ያዘና አነቀው፡፡ ባልንጀራው ባርያም ወድቆ ታገሰኝ፤ ሁሉንም እከፍልሃለሁ፤ ብሎ ለመነው፡፡ እርሱ ግን ሊተወው አልወደደም፡፡ ዕዳውን እስኪከፍልም በወኀኒ አኖረው፡፡ ይህንን ያዩ ሰዎችም አዘኑ፤ ሄደውም የሆነውን ሁሉ ለንጉሡ ተናገሩ፡፡ «ከዚህ ወዲያ ንጉሡ ጠርቶ፣ አንተ ክፉ ባርያ ስለለመንከኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህን የሆነውን ባርያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን አለው፡፡ ጌታውም ተቆጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚያሰቃዩት አሳልፎ ሰጠው፡፡» ጌታ ይህንን ምሳሌ ከተናገረ በኋላ የምሳሌውን ትርጉም እንዲህ ሲል ገልጦታል፤ ብሏል፤ «ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርገባችኋል»/ማቴ.18. 23- 35/ በአጠቃላይ ይቅር ለመባል ይቅር ማለት የግድ ነው፡፡ በእኛ ላይ የሚፈረድብን ፍርድ በእኛው እጅ ላይ ነው፡፡ ጌታችን በእነዚህ ትምህርቶች እንዲህ እያለን ነው «እኔ እናንተ ላይ የምፈርደው እናንተ በራሳችሁ ላይ በፈረዳችሁበት መንገድ /መልኩ ነው/»፡፡ #ይቅርታ_መጠየቅ ኀጢአታችንን ካወቀንና ካመንን፣ የበደሉንንም ከልብ ይቅር ካልን በኋላ ይቅር እንድንባል መጠየቅ /መለመን/ አለብን ፡፡ «ይቅር በለን» ብላችሁ ጸልዩ ብሎ በማስተማሩ ይህንን እንረዳለን፡፡ ወደ ንስሐ አባት መሄድና ኀጢአትን ተናዞ ቀኖና መቀበለ የሚገባወሙ መጀመሪያ በዚህ መልኩ ስለ ኀጢአት ካለቀሱ በኋላ ነው፡፡ ከዚያም ቀኖና ተቀብለን ስንፈጽምም ሆነ ከዚያ በኋላ ይኸው ስለ ኀጢአት ይቅርታ መጠየቁ ይቀጥላል፡፡ በእርግጥም ይቅርታ የምንጠይቀው አዳዲስ ስለሰራናቸውና ንስሐ ገና ስላልገባንባቸው ኀጢአቶቻችን ብቻ ሳይሆን ንስሐ ስለገባንባቸው ስለ ቀደሙት በደሎቻችንም ጭምር ነው፡፡ እንደ ቅዱስ ዳዊት «የቀደመ በደላችንን አታስብብን ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን» /መዝ.78-8/ እያልን ሰለ ቀድሙ በደሎቻችንንም እያሰብን በሕይወታችን ዘመን ሁሉ መጠየቅ አለብን፡፡ ይቅርታ የምንጠይቀው ስለምናውቃቸው /ስለምናስተውላቸው/ ኀጢአቶቻችን ብቻ ሳይሆን ስለማናስተውላቸውም መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ «ይቅር በለን» ስንል እኛ ካስተዋልናቸው መንገዶች ውጪ በብዙ መልኩ እርሱን እንደምንበድል አስበን ተማጽኗችን ስለነዚህም መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ ለጸሎት ከመቆማችንና የጌታን ጸሎት ከመጸለያችን በፊት የበደሉንን ይቅር እንዳልን እርግጠኛ መሆን አለብን እኛ የበደሉንን ይቅር እንዳልን ልንል ነውና፡፡ «እኛንም በደላችንን ይቅር በለን» ስንልም ከላይ ያየናቸውን ነገሮች ሁሉ እያሰብን፤ ይቅር ሊለን የወደደ አምላካችንንም እያመሰገንን መሆን አለበት፡፡ በእውነት ይህንን ጸሎት የምንጸልየው በዚህ መልኩ ነውን? ካልሆነ ልምምዱን ዛሬውኑ እንጀምረው ፡፡ ይህንን ማድረግ እንችል ዘንደ የእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ አሜን፡፡ https://telegram.me/EOTC2921 ወስብሐት ለእግዚአብሔር

✝  የ Youtube ቻናላች ተከፈተ !         ሐይማኖትና መልካም ሕሊና ይኑርህ                          1ኛ ጢሞ 1፥19    💌 📣 ኑ እምነታችንን እንጠብቅ መልካም ሕሊና ኖሮን ኦርቶዶክሳዊ ጉዞን በሕብረት እንጓዝ  << እነሆ እርሱ ከእኛ ጋር ነው በምንሄድባትም መንገድ ሁሉ ይጠብቀናል ወደዚህችም ምድር ይመልሰናል >>  ዘፍ 28፥15       ይህ የተዋህዶ የ Youtube ማዕዳችን ነው ! 🎯መንፈሳዊ መፅሀፍቶችን እየዳሰስን እምንማማርበት 🎯የደጋግ አባቶች ተግሳፃትን የምናወሳበት ቻናል ነው   🎯ጥንካሬን ያድለን ዘንድ የቅዱሳናትን ታሪክ   🎯ዝማሬዎች         🎯ስብከቶች የተዋህዶ ቲዩቦች ያወቅነውን ልናሳውቅ ዘንድ በ Youtube ቻናል መተናል አሁኑኑ የ Youtube ቻናላችንን  SUBSCRIBE ያርጉት ! ከታች ያለውን Link ተጭነው  ! 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://www.youtube.com/channel/UCPPV0Jj4491QFJIHxs9WyJQ?subconfirmation=yes 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

#ሽሽታችኹ_በክረምት_ወይም_በሰንበት_እንዳይኾን_ጸልዩ ✞🙏 አባቶቻችን ሲያስተምሩ የረቀቀውን አጉልተው ነውና፤ ይህን ሀይለ ቃል ሲያመሠጥሩ፤ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ እንደነገራቸው፤ ሐዋርያትም ❝ጌታ ሆይ ንገረን የአንተ መምጣትና የአለም መጨረሻው ምልክቱስ ምንድን ነው?❞ ብለው በጠየቁት ጊዜ እርሱም በብዙ ምሳሌ እየመሰለ አስተምሮናል። ከቃሎቹም ውስጥ፦ #ሽሽታችሁ_በክረምት_እንዳይሆን_ጸልዩ ማለቱ እንዴት ነው ቢሉ፤ በመዠመሪያ ክረምት የምንለው የአመቱን መጨረሻ ወሮችና የአመቱ መዠመሪያ ወር ማለትም (እስከ መስከረም ፳፭) ያለውን ያጠቃልላል። ምሳሌውስ ምንድነው ቢሉ፤ የአመቱ መጨረሻ በአረጋውያን (እድሜያቸው በገፋ ሰዎች) ይመሰላል። ትርጉሙስ ያሉ እንደሁ፤ በእድሜ የገፉ ሰዎች በክረምት ወራት ዳጡ አለ ዝናቡ ይበዛልና በዚያችም ወቅት ለማምለጥ ይቸገራሉና። የአመቱ መዠመሪያ ክረምትም በህፃናት ይመሰላል፤ ይህም ለአልበረቱ ልጆች ከባድ ይሆንባቸዋልና። #ሽሽታችሁ_በሰንበት_እንዳይሆን_ጸልዩ ማለቱስ ያሉ እንደሁ፤ ሰንበት ክቡር ናትና በዕለቷስ እግርህና እጅህን አታንሳ ተብላልና። በሌላም በሰንበት ቀን ወንዝ ተሻግሮ መሄድም አይቻልምና፤ በዚህች ክቡር ቀን መከራ የመጣ እንደሆን ህጉን ላለመሻር ወዴት ተሸሽቶ ይኬዳል። በሌላም ክረምት ስለሚሆን ወንዞች ቢሞሉ በየት ይሻገራሉ በዚያው ባሉበት እልቂት ይሆናል እንጂ፤ አንድም ዕለተ ሰንበት የመጨረሻው የምጽአት ዘመን የሚሆንበት ቀን ነው ተብሎ ተጽፏልና ነው። #ለርጒዞችና_ለሚያጠቡ_ወዮላቸው ማለቱም በቀጥታ ትርጉሙ ሁለቱም በመከራ ወቅት ብዙ ተጓዙ ቢባሉ ይከብዳቸዋል፤ ደግሞም አይሮጡም እራብንም አይችሉም። በሌላኛው ትርጉሙ ለርጉዞች ማለት ኃጢአትን ላረገዙ፤ ወልደው ለሚያጠቡ ማለቱም እራሳቸው ኃጢአትን ሰርተው ለሚያሰሩ በዚያች ወቅት ንጹሃንን ለሚያሰቃዩ ወዮላቸው የሞትን ሞት በእነሱ ዘንድ ፍርዱ ግልጽ ነውና። እናም ይህ ሁሉ እንዳይሆን ተግታችሁ ጸልዩ ነው የተባልንና፤ እግዚአብሔር ዕድሜ ለንስሐ ሰጥቶን በዚያች የምታስፈራ የፍርድ ቀን ከነ ኀጢአታችን እንዳንቀርብ በዕየለቱ መልካም በሆነው ነገር ሁሉ ልንጓዝ ይገባል። ሙሉውን የርሳችን ሀሳብ እነሆ አንብቡ፤ 🌾✞ #የማቴዎስ_ወንጌል_ምዕራፍ_፳፬ ✞🌾 ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ኼደ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ። እርሱ ግን መልሶ፦ ይህን ዅሉ ታያላችኹን፤ እውነት እላችዃለኹ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው። ርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው፦ ንገረን፥ ይህ መቼ ይኾናል፤ የመምጣትኽና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው፤ አሉት። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችኹ ተጠንቀቁ። ብዙዎች፦ እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ። ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችኹ፤ ይህ ሊኾን ግድ ነውና፥ ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው። ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይኾናል፤ እነዚህም ዅሉ የምጥ ጣር መዠመሪያ ናቸው። በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችዃል ይገድሏችኹማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ዅሉ የተጠላችኹ ትኾናላችኹ። በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ ርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ፥ ርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤ ብዙ ሐሰተኛዎች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ ከዐመፃምብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን ርሱ ይድናል። ለአሕዛብም ዅሉ ምስክር እንዲኾን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ዅሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል። እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኵሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉት ወደ ተራራዎች ይሽሹ፥ በሰገነትም ያለ በቤቱ ያለውን ሊወስድ አይውረድ፥ በዕርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ዃላው አይመለስ። በዚያችም ወራት ለርጕዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው። ነገር ግን፥ #ሽሽታችኹ_በክረምት_ወይም_በሰንበት_እንዳይኾን_ጸልዩ፤ በዚያን ጊዜ ከዓለም መዠመሪያ ዠምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልኾነ እንግዲህም ከቶ የማይኾን ታላቅ መከራ ይኾናል። እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ዅሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን፥ እነዚያ ቀኖች ስለተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ። በዚያንጊዜ ማንም፦ እንሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም፦ ከዚያ አለ ቢላችኹ አትመኑ፤ ሐሰተኛዎች ክርስቶሶችና ሐሰተኛዎች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ። እንሆ፥ አስቀድሜ ነገርዃችኹ። እንግዲህ፦ እንሆ፥ በበረሓ ነው ቢሏችኹ፥ አትውጡ፤ እንሆ፥ በዕልፍኝ ነው ቢሏችኹ፥ አትመኑ፤ መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይኾናልና፤ በድን ወዳለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ። ከዚያች ወራትም መከራ በዃላ ወዲያው ፀሓይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥ የሰማያትም ኀይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ዅሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፥ የሰው ልጅንም በኀይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤ መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋራ ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ። ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፏ ሲለሰልስ ቅጠሏም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችኹ፤ እንዲሁ እናንተ ደግሞ ይህን ዅሉ ስታዩ በደጅ እንደ ቀረበ ዕወቁ። እውነት እላችዃለኹ፥ ይህ ዅሉ እስኪኾን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም። ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም። ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢኾኑ ልጅም ቢኾን የሚያውቅ የለም። የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይኾናልና። በዚያች ወራት ከጥፋት ውሃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥ የጥፋት ውሃም መጥቶ ዅሉን እስከወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይኾናል። በዚያን ጊዜ ኹለት ሰዎች በዕርሻ ይኾናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል አንዱም ይቀራል፤ ኹለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች አንዲቱም ትቀራለች። ጌታችኹ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ። ያን ግን ዕወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር። ስለዚህ፥ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችኹ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና። እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎች ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው፤ ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው፤ እውነት እላችዃለኹ፥ ባለው ዅሉ ላይ ይሾመዋል። ያ ክፉ ባሪያ ግን፦ ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል ብሎ በልቡ ቢያስብ፥ ባልንጀራዎቹን ባሪያዎች ሊመታ ቢዠምር፥ ከሰካሮችም ጋራ ቢበላና ቢጠጣ፥ የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፥ ከኹለትም ይሰነጥቀዋል፥ ዕድሉንም ከግብዞች ጋራ ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይኾናል። ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯