የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
Ir al canal en Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
Mostrar más4 374
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
4 374
📖📻 #ፍቅር_እስከ_መቃብር 📻📖
@EOTC2921
✍ ደራሲ፦ ሀዲስ ዓለማየሁ
🎙 ተራኪ፦ ወጋየሁ ንጋቱ
✈ #የወላድ_መካኖች
ክፍል_፫_3
t.me/EOTC2921
4 374
📖📻 #ፍቅር_እስከ_መቃብር 📻📖
@EOTC2921
✍ ደራሲ፦ ሀዲስ ዓለማየሁ
🎙 ተራኪ፦ ወጋየሁ ንጋቱ
✈ #የስዕለት_ልጅ
ክፍል_፪_2
t.me/EOTC2921
4 374
🌿🌾✞ #ድንግል_ማርያም_በሉ ✞🌾🌿
ድንግል ማርያም በሉ ምዕመናን ሁላችሁ
በአማላጅነቷ ጥላ ስር ያላችሁ
እንደኔ ከፍቅሯ ፍቅርን ያገኛችሁ/፪/ //፪//
#አዝ
የሐና የኢያቄም የበረከት ፍሬ
ድንግል ስጦታዬ ክብሬ ከለላዬ
ጥላሽን ጣይብኝ ያኔ እጽናናለሁ
አረጋጊኝ ድንግል ባንቺ ታምኛለሁ
#አዝ
ድንግል እመቤቴ ድካሜን እዪና
ፍርኃት ጭኝቀቴን አርቂልኝና
የሕይወትን ፍሬ ሁሌ እንዳፈራ
ነይልኝ እናቴ ከዮሐንስ ጋራ //፪//
#አዝ
4 374
#የአዳም_ኅቱም_የታተመ_ጐኑ
#የአምላክ_እናት_ድንግል_ማርያም
ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ነገረ ማርያም በብሉይ ኪዳን ክፍል አንድ
መጽሐፌ በጥቂት የተወሰደ)
❖ ልዑል እግዚአብሔር ስሙን እንዲቀድሰው ክብሩን እንዲወርሰው
በአርአያውና በአምሳሉ ለፈጠረው ለአዳም አባታችን ረዳት እንድትኾነው፤
እናታችን ሔዋንን ከመኻል ጐኑ አንድ ዐጥንት በመንሣት፤ በእንቅልፍ ላይ
ሕመም ሳይሰማው አካል ሳይጐድለው ድንቅ በኾነ አምላካዊ ሥራ ሔዋንን
ፈጥሮለታል፤ ዐጥንት በወጣበት በአዳም ጐድንም ሥጋ መልቶበታል “ወነሥአ
እግዚአብሔር አሐደ እምዐፅመ ገቦሁ ወመልአ ሥጋ መካና” (እግዚአብሔርም
ከጐኑ ዐጥንት አንድ ዐጥንትን ነሣ ቦታውንም ሥጋ መላ) እንዳለ (ዘፍ ፩፥፳፩፤ ኩፋ ፬፥፭)፡፡
❖ አዳምም ከተኛበት ቢነቃ ረዳት ልትኾነው እግዚአብሔር ከአካሉ
ያስገኛትን ሔዋንን እርሱን መስላና አኽላ ከአጠገቡ ቢያገኛት፤ “ይኽቺ ዐጥንት
ከአጥንቴ ናት ሥጋም ከሥጋዬ ናት ርሷ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል…” (ዘፍ
፪፥፳፫)፤ በማለት ከአካሉ የተገኘች እንጂ ባዕድ አለመኾኗን መስክሯል፡፡
❖ ይኽነን የሔዋን ከኅቱም የአዳም ጐን ያለ ዘር ያለ ሩካቤ መገኘትንና፤
ከአካሉ ዐጥንት ቢነሣለት እንኳ አካሉ ያለመጉደሉን፤ በተጨማሪም ምንም
ሕመም ሳይሰማው ሔዋን ከሱ የመገኘቷን ድንቅ ምስጢር ከነገረ ሥጋዌ ልዩ ምስጢር ጋር በርካቶች የነገረ መለኮት ምሑራን በማነጻጸር ብዙ መጻሕፍትን ጽፈዋል፤ ከነዚኽም ሊቃውንት መኻከል ቅዱስ ቄርሎስ፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይገኙበታል።
❖ ይኸውም አዳም በዕለተ አርብ በካልዕ ሱባዔ ማእከለ ነቂህ ወነዊም ኹኖ ሔዋንን ከጐኑ እንዳስገኘ፤ ከድንግል ማርያምም በዕለተ ዐርብ ምውት
በሥጋ ሕያው በመለኮት ኾኖ፤ ከጐኑ ዳግሚት ሔዋን ጥምቀትን ያስገኘ ኢየሱስ ክርስቶስ ተገኝቷል (ዮሐ ፲፱፥፴፭)፡፡
❖ ዳግመኛም ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ አዳም ከጐኑ አንድ ዐጥንት ስለተነሣ አካሉ ጒድለት እንዳላገኘው ኹሉ፤ ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታን በሥጋ
በወለደችው ጊዜ ማኅተመ ድንግልናዋ ያለመለወጡን ነገር በቅዳሴው በቊ ፺፮‐
፺፯ ላይ “ወበከመ ኢሐጾ ለአዳም እምሕንፃ ሥጋሁ ዘቀዲሙ በእንተ ዘተነቅለ ዐፅመ ገቦሁ ከማሁ ኢሐጸ ማኅተመ ድንግልናሃ ለማርያም አመ ወለደቶ ለአበ አዳም በሥጋዌሁ” (አዳምም የጐኑ ዐጥንት ስለተነቀለ ከቀደመው የሥጋው ፍጥረት እንዳልጐደለበት፤ እንደዚኹ የአዳምን አባት በሥጋ በወለደችው ጊዜ
የማርያም ማኅተመ ድንግልናዋ አልጐደለም) በማለት ቅድመ ፀኒስ ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ፀኒስ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ፀኒስ ድኅረ ወሊድ ማኅተመ ድንግልናዋ ያልተለወጠ ዘላለማዊት ድንግል መኾኗን ከአዳም ጐን ምሳሌ ይዞ አስተምሯል፡፡
❖ ይኸው ሊቅ በተጨማሪም አዳም ሔዋን ከኅቱም ጐኑ ስትገኝ ምንም
ሕመም እንዳልተሰማው ኹሉ፤ ቅድስት ድንግል ማርያምም ጌታን በኅቱም
ድንግልና ስትወልደው ምንም ዐይነት ሕማመ ወሊድ ያልተሰማት መኾኑን
“ወበከመ ኢያሕመሞ ለአዳም ሶበ ተነቅለ ዐፅመ ገቦሁ ከማሁ ኢረከባ ሕማመ
ወሊድ ለእመ አምላክ ገሊላዊት” (አዳምን የጐኑ ዐጥንት በተነቀለ ጊዜ
እንዳላሳመመው፤ እንደዚኹ የገሊላ ወገን የምትኾን የአምላክን እናት ሕማመ
ወሊድ አላገኛትም) ሲል አመስጥሮታል፡፡
❖ የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም በተመሳሳይ መልኩ የአዳምን ጐንና የቅድስት ድንግል ማርያምን ማኅተመ ድንግልና እያነጻጸረ ሲያስተምር “ወበከመ አውፅአ አፅመ ገቦ እምገቦሁ ለአዳም ወኢሐጾ ለአዳም ከማሁ ዓዲ ነሥአ እምድንግል ሥጋ ዘቦቱ ነፍስ ነባቢት ወለባዊት ወኢተወለጠ ድንግልናሃ ኮነ አዳም ፍጹመ እምድኅረ ፀአተ ዐፅመ ገቦ እምኔሁ፤ ወድንግልሂ ዓዲ ነበረት እንበለ ሙስና እምድኅረ ፀአተ ሕፃን እምኔሃ” (ከአዳም ጐን የጐድን ዐጥንት እንደተነሣ አዳምንም አካል እንዳልጐደለው፤ እንዲኹ ከድንግል የምትናገር የምታውቅ ነፍስ ያለችውን ሥጋን ነሣ፤ ማኅተመ ድንግልናዋ አልተለወጠም፤ አዳም የጐድን ዐጥንት ከእርሱ ከተነሣ በኋላ አካል ሳይጐድለው ፍጹም ኾኖ ኖረ፤ ድንግልም ሕፃን ክርስቶስ ከርሷ ከተወለደ በኋላ እንዲኹ ያለመለወጥ በድንግልና ጸንታ ኖረች) በማለት የረቀቀውን የቅዱሳት መጻሕፍትን ምስጢር አጒልቶ አስተምሯል፡፡
🙏 እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ የጸናውን የእምነታችንን መታጠቂያ ሊፈታብን የሚሞክረውን ረቂቁ ጠላታችን ሰይጣን ፈጽሞ ወደ እኛ ወደ ልጆችሽ እንዳይቀርብ በምልጃሽ ጠብቂን፨🙏
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
@Orthodox2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
•••✞ #ባሰማት_ጊዜ_ቃሉን ✞•••
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ስሙ ገብርኤል የተባለ ለድንግል ነገራት መልካም ዜና
እንደምትወልደው ወልድን በድንግልና /2/
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ባሰማት ጊዜ ቃሉን ቅዱስ ገብርኤል በለዛ
ድንግል ቀረበች ወደእርሱ ፍፁም ትህትና ይዛ
#አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ •••
ትጸንሻለሽ ሲላት መላኩ ፍፁም በልቧ ሳትመካ
እንደቃልህ ይሁን አለችሁ በቃሉ ተማርካ/2/
#አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ •••
የአለም መድኃኒት ነውና ካንቺ እሚወለደው በመንፈስ ቅዱስ
ትሰይሚዋለሽ ስሙን ብለሽ ኢየሱስ/2/
#አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ •••
እፁብ ድንቅ ነው ሁልጊዜ ለድንግል ማርያም የተሰጣት ክብር
የአምላክ እናት ሆና መመረጥ ከሴቶች መካከል /2/
#አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ •••
ጸጋን የተመላሽ ድንግል ሆይ ይገባሻል ላንቺ ክብርና ምስጋና
የፍጥረታት ጌታ ሁልጊዜ ካንቺ ጋር ነውና /2/
#አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ •••
•••✞ t.me/EOTC2921 ✞•••
4 374
#አይናችን_ነሽ_ማርያም
አይናችን ነሽ ማርያም አንቺን አይንኩብን
የተዋህዶ ልጆች እንወድሻለን
ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ
በሀሴት ቆመናል ደስታን ስለወለድሽ
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
የቀደመው እባብ እጅግ ተበሳጨ
በአሸዋ ላይ ቆመ መርዙን እየረጨ
ከልጅሽ ምስክር ሊያስቀር ከዘሮችሽ
እጅጉን ይተጋል ሊለየን ከጉያሽ
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ገብተሻል ላትወጪ አንዴ ከልባችን
ጌታን ያየንብሽ ስለሆነሽ አይናችን
የራቀው ቀርቦልን የረቀቀው ጎልቶ
ያየነው ባንቺ ነው የጠፋው ተገኝቶ
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ወይኑን ያፈራሽው የወይን ሐረግ ድንግል
ምግብን የሰጠሽን በቀራንዮ መስቀል
ምልክታችን ነሽ የኛ መታወቂያ
የምንተርፍብሽ ከጥፋት ገበያ
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
የህይወት መገኛ የደስታ መፍሰሻ
ጸዋሪተ ፍሬ የሀዘናችን መርሻ
ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ
የጎደለው ሁሉ ይሞላል በምልጃሽ
#አዝ•••✞•••✞•••✞•••
ከሀገር ብንርቅ ከልፍኝ ከጓዳችን
ስንቅ ነሽ ለመንገድ ምርኩዝ ለጉዞአችን
በአደርንበት አድርሽ በሄድንበት ሂጂ
ለፃድቃን አይደለም ለኃጢያን አማልጂ
4 374
#በደላችንን_ይቅር_በለን
https://telegram.me/EOTC2921
1. እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን እንደሚወድ
አምላካችን ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ባይወድ ኖሮ ይቅርታን እንድንጠይቅ አይነግረንም ነበር፡፡ አዎ እኛ ከተመለስን ምንም ያህል በደለኛ ብንሆን ይቅር ሊለን፤ ምንም ያህል ብንቆሽሸ ሊያድነን ዝግጁ ነው፡፡ እንዲህ እያለ ይጠራናል፤ «እናንተ ሸክማችሁ የከበዳችሁ፤ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ»፡፡ ስለዚህ በዚሀ ጸሎትም ላይ «በደላችንን ይቅር በለን» ብለን እንድንጠይቀው አስተማረን፤ ይቅር ይለን ዘንድ፡፡
2. ይቅር ለመባል ምን ማድረግ እንዳለብን፤
ይቅር ሊለን ስለወደደም ይቅርታን ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለብን በዚሁ ቃል ነግሮናል፤ ማድረግ ያለብን ምንድን ነው?
- ኀጢአታችንን ማወቅ፣ ማመን፣ ማስታወስ
- የበደሉንን ይቅር ማለት
- ይቅርታን መለመን
#ኅጢአታችንን_ማወቅ /ማመን/
ጌታ «በደላችንን ይቅር በለን» ብለን እንድንጸልይ ሲነግረን በመጀመሪያ ደረጃ በደለኛ እንደሆንን እያስታወስን /እንድናስታውስ እያደረገን/ ነው፡፡
ሁልጊዜም በማሰብ፣ በመናገርና በማድረግ የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ የሆነውን ልባችንን /ኅሊናችንን/ እና ሰውነታችንን እናቆሽሻለን፤ መድኃኔዓለም ክርስቶሰ የሞተለትን ማንነታችንን እናጎድፋለን፡፡ ይህም የሰው ልጆች በቅድስና እርሱን መስለን እንድንኖር በኋላም የተዘጋጀልንን የዘለዓለም መንግሥት እንድወርስ ብቻ ፈቃዱ የሆነውን እግዚአብሔርን ያሳዝናል፤ በአርአያውና በአምሳሉ ለክብር የፈጠረው ሰውነታችን መጉደፍ ያስቆጣዋል፤ ንጹሐ ባሕርይ የሆነ እርሱ ኀጢአት አይስማማውምና፡፡
እንግዲህ ይቅር ለመባል በመጀመሪያ እንዲህ ኀጢአት እየሰራን መሆኑን ማወቅና ማመን ያስፈልገናል፡፡ ወደዚህ ዕውቀት ለመድረስም የቅዱሳት መጻሕፍትን ቃል መማር የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ስህተት የሚታወቀው ያለውን ሁኔታ /ድርጊታችንን ንግግራችንን፣ ሀሳባችንን.. / መሆን ከነበረበት /ከትክክለኛው/ ጋር በማነጻጸር በሚዛን ላይ በማስቀመጥ ነው፡፡ የማነጻጻሪያ ሚዛኖቻችን ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈ ሕግጋትና ትዕዛዛት ናቸው፡፡ እነዚህን ስናውቅ ጉድለቶቻችን፣ ድካሞቻችን ፍንተው ብሎ ይታዩናል፡፡ አሊያ ግን እየበደለን ያልበደልን ሊመስለን ይችላል፡፡
https://telegram.me/EOTC2921
#የበደሉንን_ይቅር_ማለት
ጌታ በዚህ ጸሎት ይቅርታ እንድንጠይቀው በማስተማር ይቅር ሊለን እንደሚወድ ዝግጁም እንደሆነ ቢነግረንም ይቅር ለመባል ግን እኛ የበደሉንን ይቅር ማለታችን የግድ እንደሆነ በግልጽ አስቀምጦልናል፤
«በደላችንን ይቅር በለን» ከማለታችን በፊት «እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል» እንድንል ያዘዘን እኛ ይቅርታ የምናገኘው ሌሎችን ይቅር ስንል ብቻ መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡
ጌታችን ይህንን ጉዳይ በሌሎች የተለያዩ ቦታዎችም በተደጋጋሚ አስተምሮናል፤ በዚሁ በተራራው ስብከት ይኸው ጉዳይ ሁለት ጊዜ በጌታችን ትምህርት ተሰጥቶበታል፡፡
«እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል፡፡ » /ማቴ.7-2/
በሌላ ቦታም እንዲህ ሲል ይህንኑ ጉዳይ በምሳሌ አስተምሯል፤
መንግስተ ሰማያት ባሮቹን ለመቆጣጠር የወደደን ንጉሥ ትመስላለች መቆጣጠርም በጀመረ ጊዜ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፡፡ ባለ እዳው ሰው የሚከፍለው ስላጣ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ንጉሡ አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ ባርያው ወድቆ ሰገደለትና ጌታ ሆይ ታገሰኝ፤ ሁሉንም እከፍልሃለሁ አለው፡፡ የዚያም ባርያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው፡፡ ይህ ባርያ ግን ወጥቶ ከባልጀሮቹ /እንደርሱ ባርያ ከሆኑት/ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን አንዱን አገኘና ዕዳህን ክፈለኝ ብሎ ያዘና አነቀው፡፡ ባልንጀራው ባርያም ወድቆ ታገሰኝ፤ ሁሉንም እከፍልሃለሁ፤ ብሎ ለመነው፡፡ እርሱ ግን ሊተወው አልወደደም፡፡ ዕዳውን እስኪከፍልም በወኀኒ አኖረው፡፡ ይህንን ያዩ ሰዎችም አዘኑ፤ ሄደውም የሆነውን ሁሉ ለንጉሡ ተናገሩ፡፡
«ከዚህ ወዲያ ንጉሡ ጠርቶ፣ አንተ ክፉ ባርያ ስለለመንከኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህን የሆነውን ባርያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን አለው፡፡ ጌታውም ተቆጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚያሰቃዩት አሳልፎ ሰጠው፡፡»
ጌታ ይህንን ምሳሌ ከተናገረ በኋላ የምሳሌውን ትርጉም እንዲህ ሲል ገልጦታል፤ ብሏል፤ «ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርገባችኋል»/ማቴ.18. 23- 35/
በአጠቃላይ ይቅር ለመባል ይቅር ማለት የግድ ነው፡፡ በእኛ ላይ የሚፈረድብን ፍርድ በእኛው እጅ ላይ ነው፡፡ ጌታችን በእነዚህ ትምህርቶች እንዲህ እያለን ነው «እኔ እናንተ ላይ የምፈርደው እናንተ በራሳችሁ ላይ በፈረዳችሁበት መንገድ /መልኩ ነው/»፡፡
#ይቅርታ_መጠየቅ
ኀጢአታችንን ካወቀንና ካመንን፣ የበደሉንንም ከልብ ይቅር ካልን በኋላ ይቅር እንድንባል መጠየቅ /መለመን/ አለብን ፡፡
«ይቅር በለን» ብላችሁ ጸልዩ ብሎ በማስተማሩ ይህንን እንረዳለን፡፡ ወደ ንስሐ አባት መሄድና ኀጢአትን ተናዞ ቀኖና መቀበለ የሚገባወሙ መጀመሪያ በዚህ መልኩ ስለ ኀጢአት ካለቀሱ በኋላ ነው፡፡ ከዚያም ቀኖና ተቀብለን ስንፈጽምም ሆነ ከዚያ በኋላ ይኸው ስለ ኀጢአት ይቅርታ መጠየቁ ይቀጥላል፡፡
በእርግጥም ይቅርታ የምንጠይቀው አዳዲስ ስለሰራናቸውና ንስሐ ገና ስላልገባንባቸው ኀጢአቶቻችን ብቻ ሳይሆን ንስሐ ስለገባንባቸው ስለ ቀደሙት በደሎቻችንም ጭምር ነው፡፡ እንደ ቅዱስ ዳዊት «የቀደመ በደላችንን አታስብብን ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን» /መዝ.78-8/ እያልን ሰለ ቀድሙ በደሎቻችንንም እያሰብን በሕይወታችን ዘመን ሁሉ መጠየቅ አለብን፡፡
ይቅርታ የምንጠይቀው ስለምናውቃቸው /ስለምናስተውላቸው/ ኀጢአቶቻችን ብቻ ሳይሆን ስለማናስተውላቸውም መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ «ይቅር በለን» ስንል እኛ ካስተዋልናቸው መንገዶች ውጪ በብዙ መልኩ እርሱን እንደምንበድል አስበን ተማጽኗችን ስለነዚህም መሆን አለበት፡፡
ስለዚህ ለጸሎት ከመቆማችንና የጌታን ጸሎት ከመጸለያችን በፊት የበደሉንን ይቅር እንዳልን እርግጠኛ መሆን አለብን እኛ የበደሉንን ይቅር እንዳልን ልንል ነውና፡፡
«እኛንም በደላችንን ይቅር በለን» ስንልም ከላይ ያየናቸውን ነገሮች ሁሉ እያሰብን፤ ይቅር ሊለን የወደደ አምላካችንንም እያመሰገንን መሆን አለበት፡፡ በእውነት ይህንን ጸሎት የምንጸልየው በዚህ መልኩ ነውን? ካልሆነ ልምምዱን ዛሬውኑ እንጀምረው ፡፡ ይህንን ማድረግ እንችል ዘንደ የእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ አሜን፡፡
https://telegram.me/EOTC2921
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
4 374
#ገብርኤል_ማን_ነው?
🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾
#ገብርኤል ማለት “ እግዚእ ወገብር” - የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው።
ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን
ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው መላእክትም “ መኑ ፈጠረነ፡ ማን ፈጠረን ” ሲሉ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹ ጊዜ “ የፈጠረንን
አምላካችን እስክናውቅ በያለንበት ጸንተን እንቁም ” ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ
ነው። በዚህም ምክንያት ጌታ “ በእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም ”
እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል። ከዚህም በኋላ ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል።ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡
በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘንድ ይወደዳል፡፡ ምክንያቱም ያዘኑትን ለማጽናናት የምሥራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካልና፡፡
#ይህ_ቅዱስ_ገብርኤል_ነው
ሳጥናኤል ሥላሴን በካደ ጊዜ መላእክትን በቃሉ ያጽናናቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ
👉*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡*
ዳንኤልን ከአናብስት ያዳነው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ወደ ዘካርያስ የተላከ የዮሐንስን ልደት ያበሰረ
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ
👉*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡*
ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ሰብአ ሰገልን በኮከብ ምልክት የመራቸው
👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
ድንግል ማርያምና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ
👉* ይህ ገብርኤል ነው፡፡*
የብርሃን ራስ ወርቅ የተቀዳጀ
👉*ገብርኤል ነው፡፡*
የአሸናፊና የኃይል መልአክ
*ገብርኤል ነው፡፡*
ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ
*ገብርኤል ነው፡፡
🙏"የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃና ረድኤት አይለየን"🙏
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
#የሊቀ_መላእክት_የቅዱስ_ገብርኤልና_የቅዱስ_ቂርቆስ_በዓል ✞🍇🌾
❖ሐምሌ ፲፱ ዕለት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል አምላካቸው ክርስቶስን
አንክድም በማለታቸው የፈላ ጋን ውስጥ የተወረወሩት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱን
ቅድስት ኢየሉጣ ተራድቶ ያዳነበት በዓል ነው።
❖ ይኸውም የቅድስት ኢየሉጣን ልጅ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ከሐዲው መኰንኑ
ይዞ “ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ “ነቅዕ ዘእምዐዘቅት ንጹሕ ወእማይ
ዘኢይማስን ክርስቲያን ስምየ” (ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውሃ
የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው ሞክሼ ስም ከፈለግኽ ደግሞ እናቴ የሠየመችኝ
ቂርቆስ ነው) በማለት ክርስትናው መመኪያው የኾነው ይኽ ቅዱስ ሕፃን
መለሰለት፡፡
❖ መኰንኑም ለአማልክት ከሠዋኽ ስታድግ እሾምኻለኊ ክርስቶስን ካድ ቢለው ቅዱስ ቂርቆስ ግን “የሰይጣን መልእክተኛ ለእውነትም ጠላቷ የኾንኽ ከእኔ ራቅ” አለው፡፡ መኰንኑም ይኽነን ሰምቶ በመቈጣት የቅዱስ ቂርቆስ ደሙ እንደ ውሃ እስኪፈስስ ድረስ እንዲጨምቁት እና ጨውና ሰናፍጭ በኹለቱ የአፍንጮቹ ቀዳዳዎች እንዲጨመሩ ቢያደርግበት፤ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የጠነከረው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን “ትእዛዝኽ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ኾነ ከማርና ከሥኳርም ለአፌ ጣመኝ” እያለ አምላኩ ክርስቶስን አመሰገነ፡፡
❖ መኰንኑ በዚኽ ሳያበቃ እናትና ልጇ በክፉ አሟሟት እንዲሞቱ በማሰብ
የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች
እንዲመጡ አስደርጎ ሰባቱ በእናቱ አካላት፤ ሰባቱ በሕፃኑ ሰውነት ላይ እንዲሰካ ቢያስደርግም በጌታችን ትእዛዝ ግለቱ ጠፍቶ እንደ በረዶ በመቀዝቀዝ ምንም ምን ጒዳት ሳያደርስባቸው ቀረ፡፡
❖ ከዚያም ወደ ወኅኒ ቤት እንዲገቡና እንዲዘጋባቸው አደረገ፤ ከዚያም ሕፃኑና
እናቱ የሚሠቃዩበት ታላቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀናት ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ኹለቱንም
በደራቁ ራሳቸውን ላጭተው የእሳት ፍሕምን በላያቸው ላይ ቢያደርጉም
የእግዚአብሔር መልአክ ሥቃዮቹን ኹሉ ከእነርሱ አራቀላቸው፡፡
❖ የሕፃኑ ምላስ እንዲቈረጥ አዝዞ ቢያስቈርጠውም ጌታችን ምላሱን
መልሶለታል፡፡ “ወአዘዘ ካዕበ ያፍልሑ ማየ ውስተ ጽሕርት ዐቢይ ወይደይዎሙ
ለሕፃን ቂርቆስ ወለእሙ ኢየሉጣ” ይላል በታላቅ ጋን ውሃ አፍልተው ሕፃኑንና
እናቱን እንዲጨምሯቸው ሲያዝዝ ከሚፍለቀለቀው ውሃ ድምፅ የተነሣ ለጊዜው እናቱ ፍርሀት ሥጋዊ ቢያገኛትም ልጇም ወደ ጌታችን በጸለየላት ጊዜ ፍርሃቱ ርቆላት ከልጇ ጋር ስትገባ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ውሃውን
አቀዝቅዞ ሐምሌ ፲፱ አውጥቷቸዋል፡፡
❖ በመጨረሻም የሰማዕትነትን አክሊል የሚያገኝባት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን
ተገልጾለት ስሙን ለሚጠራ ኹሉ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ ሥጋኽን በኤልያስ ሠረገላ ላይ አኖርልኻለኊ አለው፤ ይኽነን በሰማ ጊዜ በእጅጉ ተደሰተ፤ ከዚኽም በኋላ ጥር ፲፭ በሌሊቱ እኲሌታ ከእናቱ ጋር አንገቱ ተቈረጠ የሰማዕትነትን ክብር ተቀዳጅተዋል።
❖ ጥር ፲፮ ደግሞ የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበር የኾኑ ዐሥራ አንድ ሺሕ አራት
በሰማዕትነት ዐልፈዋል፡፡ ሊቁ አርከ ሥሉስም የቅዱስ ቂርቆስን ተጋድሎ በማዘከር፡-
“እግዚአብሔር ሤመ ረድኤቶ ለንእስናከ ዐቃቤ
ወስምዖ መጥበቤ
ፍትወ ምግባር ቂርቆስ ወምዑዘ ኂሩት እምከርቤ
ለዘተጽዕረ በምንዳቤ ወለዘቈስለ በጥብጣቤ
ለአባልከ ሰላም እቤ”
(እግዚአብሔር ረድኤቱን ለታናሽነትኽ ጠባቂን አስቀመጠ፤ ብልኅ የሚያደርግ
ምስክርነቱንም፤ ምግባርኽ ያማረ በጎነትኽ ከከርቤ ይልቅ የሚሸት ቂርቆስ፤
በመከራ የተቸገረ በግርፊያ የቈሰለ ለኾነ ሰውነትኽ ሰላም እላለኊ) እያለ ሕፃኑን ሰማዕት ያወድሳል፡፡
❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በመጽሐፉ፦
“ሰላም ለቂርቆስ ወሬዛ በመንፈስ
በልደት ንዑስ፤
ንጹሕ ከመ ዕጣን
ወፍሡሕ ከመ ወይን”፡፡
(በልደተ ሥጋ ታናሽ በመንፈስ ጐልማሳ፤ እንደ ዕጣን ንጹሕ እንደ ወይንም
አስደሳች ለኾነ ለቂርቆስ ሰላምታ ይገባል)
❖“ሰላም ለሰማዕታት እለ ምስሌሁ ፭፼ ወ፬፻፤ ፬፼ ወ፪፻፲ወ፬”፡፡
(ከርሱ ጋር ያሉ ፭፼ ከ፬፻፤ ፬፼ከ፪፻፲፬ ሰማዕታት ሰላምታ ይገባቸዋል) በማለት
አመስግኗል፨
✍ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
🙏✞[የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት የቅዱስ ቂርቆስ የእናቱ የኢየሉጣ፤ ስለአምላካቸው ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገታቸው በሰይፍ የተቆረጡት
የሰማዕታት በረከት ይደርብን።]✞🙏
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
@Orthodox2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
📲 #ቃለ_ስብሐት_Application 📱
@EOTC2921
✅✞ በቤተ ክርስቲያን ክህነት ማገልገልና ግብረ ዲቁና መማር ለምትፈልጉ፦
✅✞ በቅዳሴ ጸሎት ተሰጥኦ በመመለስ መሳተፍ ለሚፈልጉ፦
✅✞ በቦታ ርቀትና በተለያዩ ምክንያቶች በተለይም በትምህርት ላይ ሆናችሁ የአብነት ትምህርቱን ጎን ለጎን መማር ለምትፈልጉ በሙሉ፦ ይህ ቃለ ስብሐት የድምፅ መተግበሪያ ያግዛችሁ ዘንድ እነሆ መጣላችሁ፡፡
📲 #ቃለ_ስብሐት_በውስጡ_የያዛቸው📲
▶️ሥርዓተ ቅዳሴ [ግዕዝ ና ዕዝል]
▶️ምንባብ ዘሰዓታት ዘ፯ ዕለታት
⏩ጸልዩ፦ ዘዲያቆናት
▶️ኲሎሙ
▶️መቅድመ ተአምር
▶️መሐረነ አብ
▶️እሴብሕ ጸጋኪ
▶️ኪዳን
⏩መቅደመ ኪዳን
⏩ኪዳን [ግዕዝ፣ ዕዝልና ዓራራይ]
▶️መልክዐ ቊርባን [ግዕዝና ዕዝል]
▶️ሠራዊት [ግዕዝና ዕዝል]
▶️መሠረተ ትምህርት ዘአብነት
⏩ ጸሎት ዘዘወትር
⏩ውዳሴ ማርያም ዘ፯ ዕለታት
⏩አንቀጸ ብርሃን
⏭ምስለ ይዌድስዋ መላእክት
⏩መልክዐ ማርያም
⏩መልክዐ ኢየሱስ
#ማሳሰቢያ፦ አፑን ለማውረድ አቅማችሁ የማይፈቅድ ከዋይፋይ አሊያም ከሰው ተቀብላችሁ ወደ ስልካችሁ መጫን ትችላላችሁ።
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
