የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
Ir al canal en Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
Mostrar más4 374
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
4 374
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
#የአምላክ_እናት_ከማን_ጋር_ላነጻጽርሽ_በቅዱስ_አትናቴዎስና_በቅዱስ_ኤፍሬም
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
✍በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
🎤ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ እንዲኽ አላት፦🎤
☞ “አንቺ የተከበርሽ የተደነቅሽ ድንግል ሆይ ከየትኛውም ታላቅነት በላይ ታላቅ
ነሽ፤ ከፍጡራን ወገን እንዳንቺ ያለ ታላቅነት ያለው ርሱ ማን ነው? አንቺ
የእግዚአብሔር ወልድ ማደሪያ ድንግል ሆይ ከፍጥረታት መኻከል ከማን ጋር
ላወዳድርሽ? ከኹሉም በላይ ታላቅ ነሽና።
👉የዐዲስ ኪዳን ታቦት ሆይ ወርቅን ሳይኾን ንጽሕናን የተጐናጸፍሽ!
እውነተኛው መና በውስጧ ያኖረችው መሶበ ወርቅ የተቀመጠባት ታቦት ነሽ
እኮን! ይኸውም ሥጋን የተዋሐደው መለኮት ነው።
👉ከለመለመችው ምድርና ከፍሬዋ ጋር ላነጻጽርሽን? ግን አንቺ ኹሉንም
ትበልጫቸዋለሽ ምክንያቱም “ምድር የእግሬ መረገጫ ናት” ተብሎ ተጽፏልና
(ኢሳ ፷፮፥፩) ነገር ግን አንቺ ፍጹም የኾነውን የባሕርይ አምላክ እግር፣ ራስ እና መላ አካል (ኲለንታ ትስብእት) ይዘሻልና።
👉ሰማይ ታላቅ የኾነ ቢኾንም ግን ያንቺ አቻ አይኾንም “ሰማይ ዙፋኔ ነው”
ተብሎ ተጽፏልና (ኢሳ ፷፮፥፩)፤ አንቺ ደግሞ የአምላክ ማደሪያ ነሽ።
👉መላእክት እና የመላእክት አለቆች ታላቅ ናቸው ብልም አንቺ ከኹሉም
ታላቅነት በላይ ነሽ፤ ይኸውም መላእክት እና ሊቃነ መላእክት ባንቺ ማሕፀን
ላደረው ለርሱ በረአድ የሚያገለግሉ በመኾናቸው በፊቱ መናገር የማይችሉትን
አንቺ በነጻነት ታናግሪዋለሽ፡፡
👉ኪሩቤልን ታላላቅ ናቸው ብንልም አንቺ ከነርሱ ታላቅነት በላይ ነሽ፤ ኪሩቤል
የእግዚአብሔርን ዙፋን ይሸከማሉ ፤ አንቺ ግን እግዚአብሔርን በእጅሽ ያዝሽው።
👉ሱራፌልንም ታላቅ ናቸው ብልም አንቺ ከነርሱ ታላቅነት በላይ ታላቅ ነሽ፤
ሱራፌል በክንፎቻቸው ፊታቸውን ይሸፍናሉ (ኢሳ ፮፥፪)፤ ፍጹም የኾነውን
ጌትነቱን ማየት አይችሉም አንቺ ግን ፊቱን እያየሽ እና እየዳሰስሽው ጡትን
በክቡር አፉ ውስጥ አጥብተሻልና ከነርሱ ትልቂያለሽ" (St. Athanasius,
Homily of the Papyrus of Turin)
🎤ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ እንዲኽ አላት፦🎤
☞ ‘O Virgin full of wonder who bore for us the Son of
God…’ (የእግዚአብሔርን ልጅ ለእኛ የወለደሽልን በድንቅ የተመላሽው ድንግል
ሆይ፣ የእኔ ደካማ ከንፈሮች የአንቺን ንጽሕና ለመናገር በቂ አይደሉም።
ባለአራት ፊቶች ኪሩቤል የአንቺን ያኽል ክቡር አይደሉም፤ ባለስድስት
ክንፎች ሱራፌልም ከአንቺ ውበት የበለጠ ሞገስ የላቸውም፡፡ ባንቺ ማሕፀን
ያለውን ልጅ ዙፋን የሚሸከሙ በላይ በሰማይ ያሉ የነገደ መላእክት ጭፍሮች
በንጽሕናቸው አንችን አይልቁም፡፡
የእሳት ሠረገላው በፍርሃት ኾነው ርሱን ተሸክመውታል፤ የእመቤታችን
ጒልበቶች ግን ሳይቃጠሉ ተሸክመውታል፤ የነበልባል መንኰራኲሮች በመደነቅ
አጓጉዘውታል፤ ቢኾንም ግን በዳዊት ብላቴና በድንግል ጭን ርሱ በፍቅር ታቀፈ።
👉ኪሩቤል በፍርሃት ተሸክመውት ይንቀጠቀጣሉ፤ ሱራፌልም “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ” ብለው እየጮኹም ወደ ኋላ ያፈገፍጋሉ (ኢሳ ፮፥፫)፤ እመቤታችን
ማርያም ግን በጡቶቿ ውስጥ ዐቅፋዋለች፡፡
👉ታማኝዋ ድንግል ማርያም ከሴቶች ተለይታ የተባረክች ናት፤ ድንግልም
ብትኾን እንኳን ከጡቶቿ ወተትን ታጠባዋለች፡፡ ይኽ እንዴት ድንቅ ነው! እንዴት እንደተካኼደ ማን የመናገር ብቃት አለው?) (T.j. Lamy, Sancti Ephream
Syri Hymni et Sermones, II)
[በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ተዘጋጅተው ከታተሙት ከ19 መጻሕፍት ውስጥ
ነገረ ማርያም በሊቃውንት ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ]
🙏ምሳሌ ያጣንልሽ የፈጣሪያችን እናት ሆይ ቅዱስ አትናቴዎስንና ቅዱስ
ኤፍሬምን እንደባረክሻቸው እኛ ልጆችሽን ባርኪን፨🙏
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
ዓለመ፡፡
✍ቸር እረኛ እስራኤልን የሚጠብቃቸው
ታዛዥ የሆነ ክርስቶስ ለአሕዛብ የመጣ፡፡ እሺ ብሎ ታዛዥ ሆኖ ዓለምን ይቤዥና ያድን ዘንድ ከሰማይ ወረደ፤
መጣ፡፡›› (ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ ገጽ)፡፡ በማለት ሁሉን
የሚገዛ አምላክ ዓለሙን ሊቤዥና ሊያድን እሺ ብሎ በፈቃዱ መምጣቱን መሰከረ፡፡
ሁሉን የሚመግብ፣ የሕይወት እንጀራንና የሕይወት መጠጥን የሚሰጥ ጌታ ወደ ሰርግ ተጠራ፡፡ ለፍጥረቱ ማዕድን የሚያዘጋጅ ጌታ በፈሪሳዊው ስምዖን ቤት
ለግብዣ ተጠራ፡፡ ዮሐ 2፤2፣ ሉቃ ፤36-37፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም በፈሪሳዊው ማዕድ ላይ የቀረበው የጌታ ማዕድ በሚለው ስብከቱ ‹‹ ንስሓ ስለምትገባው ስለዚያች ኃጢአተኛ ሴት ሲል ከግብዣው ቤት ተገኘ፤ ጌታ ርሀቡ ሥጋዊው ምግብ ሳይሆን የዚያች ኃጢአተኛ እንባ እንጂ… ወደ ፈሪሳዊው ስምዖን ቤት የሄደው በምግብና በመጠጥ ለመዝናናት አልነበረም ሕይወት መድኃኒት የሆነውን ትምህርቱን በማዕዱ ለማቅረብ በመሻቱ ነበር እንጂ፡፡ … ክፉ የተባለው ሰይጣን በመብል ምክንያት አዳምና ሔዋንን ሞትን የሚያመጣ ምክርን እንደመከራቸው እንዲሁ ቸሩ ጌታችን ደግሞ በማዕድ ቦታ ተገኝቶ ሕይወት ሰጪ የሆነ ትምህርቱን ለአዳም ልጆች በማዕዱ አቀረበ፡፡ እርሱ ጌታችን የጠፉትን ነፍሳት ለማጥመድ አሳ አስጋሪ ነበር፡፡ ቀራጮችና አመንዝሮች ወደ ስካርና ሥርዐት አልበኝነት ሲፋጠኑ ተመለከታቸው፤ ሥጋንም ከሚያወፍር የማዕድ ቦታ እነርሱን በማስገር ነፍስን ወደሚያወፍር ጾም ሊያሻግራቸው የቃሉን መረብ በማዕዱ ውቅያኖስ ላይ ጣለው፡፡››በማለት ገለጸው፡፡"ስብከት ወተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም"
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
#JOIN #JOIN #JOIN #JOIN
🌻🌻 @EOTC2921 🌻🌻
🌻🌻 @EOTC2921 🌻🌻
🌻🌻 @EOTC2921 🌻🌻
4 374
✍☞⛪️ ነገረ ክርስቶስ ⛪️☜✍
🌼💓 @EOTC2921 💓🌼
✍ብርህት፣ ንጽህት፣ ጽድልት፣ የሆነች ቤተክርስቲያናችን
ከምታስተምራቸው ትምህርቶች አንዱና ዋነኛው ነገረ
ክርስቶስ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን ትምህርት ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል ወልድ ሲሆን
ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለ ሲሆን በኋላኛ
ዘመን ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን
ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ሰው ሆነ፡፡
እንዲህ እናምናለን፤ እንዲህም እናስተምራለን፡፡(ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ)፡፡
✍ነገረ ክርስቶስ ማለት ስለ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ የምናምነውን እምነት የምናስተምረውን
ትምህርት የሚያጠቃልል ነው፡፡ ይህ ክፍለ ትምህርት
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ስለ ጌታችን
መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ
የሚታመነው፣ የሚነገረው፣ የምንመራበት ምንድነው
የሚለውን በሚገባ ለመረዳት በቅዱሳት መጻሕፍት፣
በሊቃውንት፣ በትውፊት የተላለፈውን አስተምህሮ
የምናቀርብበት ነው፡፡
አግዚአብሔር አምላካችን የሚታየውን ዓለም
ከማስገኘቱ በፊት እስከ ዘላለም ድረስ በአንድነቱና
በሦስትነቱ፣ በመለኮቱ፣ በመንግሥቱ አለ፡፡ ከጎሕና
ከጽባሕ በፊት፣ ከመዓልትና ከሌሊት በፊት፣ መላእክት
ሳይፈጠሩ እግዚአብሔር አለ፡፡ ሰማያት ሳይዘረጉ፣
የየብስም ፊት ሳይታይ፣ ሐመልማላት ሳይበቅሉ
እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ፡፡ ከሚንቀሳቀስ እንስሳ
በፊት ከሚበሩም አዕዋፍ በፊት፣ ከባሕር አራዊት በፊት፣ እግዚአብሔር በመንግስቱ ነበረ፡፡ አዳምን በእርሱ
አምሳልና አርአያ ሳይፈጥረው፣ ትእዛዙንም ሳያፈርስ
እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ (ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ)፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው ወወልደ
ማርያም ሥግው ከአምላክ የተገኘ አምላክ፣ ከብርሃን
የተገኘ ብርሃን፣ ከባሕርይ የተገኘ ባሕርይ፣ ከሕይወት
የተገኘ አዳኝ ከመድኃኒት የተገኘ መድኅን፣ ከገዥ የተገኘ
ገዢ፣ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ህላዌ እንደሆነ
እናምናለን (መዝገበ ሃይማኖት)፡፡
ከአብ መወለዱም በዚህ ዘመን፣ በዚህ ወቅት፣ በዚህ
ሰዓት ተብሎ ዘመን አይቆጠርለትም፤ በሰውና በመላእክት
አእምሮም ሊመረመር አይችልም፡፡ ሰውንም ስለማዳን
በአባቱ ፈቃድ በእርሱም ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ
ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ ወንድ ዘር በድንግልና
ተወለደ፡፡ ከወለደችውም በኋላ ድንግልናዋ
አልተለወጠም፡፡ በሚያስደንቅ ትሕትና ሰው ሆነ፤
በሚያስደንቅ ዙፋኑ ለደቀመዛሙርቱ ሲያገለግል ባዩት
ጊዜ አገልጋዮች መላእክት ደነገጡ፡፡ ትሕትና ወዳለበት
ፍቅር የአሕዛብን እግረ ልቡና ያቀና ዘንድ ግሩም እሳት
በትሕትና መገለጡን ባዩ ጊዜ መላእክት ደነገጡ
(ሃይማኖተ አበው ዘያዕቆብ ዘስሩግ)፡፡ ፍጥረቱን ሁሉ
ሰብስቦ የያዘና ፍጥረቱን ሁሉ የሚመግብ ጌታቸው
በብብቷ (በክንዷ) ተቀምጦ ጡቷን ሲጠባ ባዩ ጊዜ
በአርያም ፈለጉና በዚህ ዓለም እንደ ቀድሞው ከአባቱና
ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አገኙት፡፡ የጌታን ትሕትና ባዩ ጊዜም
ዓይኖቻቸውን ወደ ላይ ወደ አርያም ከፍ ከፍ አደረጉ
ክንፋቸውንም ዘርግተው ለሁሉ ጌታ ለአንተ ምስጋና
ይገባሃል እያሉ ጌታቸውን አመሰገኑ፡፡ (አንቀጸ ብርሃን)
አዳምን ካልታረሰች መሬት የፈጠረው ሔዋንንም ከአዳም
ያለእናት የፈጠራት እርሱ ከንጽሕት ድንግል ያለ ወንድ
ዘር ተወለደ፡፡ ያለ እናት ሔዋን ተገኝታ ነበርና ስለዚህ
የአዳምን ብድራት ትከፍለው ዘንድ አዳም ያለ እናት
ሔዋንን ስላስገኘ እንዳይመካ ድንግል ያለ አባት
ክርስቶስን ወለደች ይህም ድንቅ በሚሆን አንድነት
የፍጥረት ሁሉ እኩልነት ይታወቅ ዘንድ ነው፡፡ (ሃይማኖተ
አበው ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)፡፡
ዳግመኛም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹‹ከአዳም አጥንት
ጎድን ሲነሳ ምንም አካል እንዳልጎደለው እንዲሁ
ከድንግል የምትናገር ነፍስን ሲነሳ ማኅተመ ድንግልናዋ
አልተለወጠም፡፡ አዳም የጎድን አጥንት ከእርሱ ከተነሳ
በኋላ አካል ሳይጎድለው ፍጹም ሆኖ እንደኖረ እንዲሁ
ድንግልም ሕጻን ክርስቶስ ከእርሷ ከተወለደ በኋላ
በድንግልና ጸንታ ኖረች›› አለ፡፡ ሕዝ 44፤1-3፣ መኃ 4፤12
ነቢያት ስለእርሱ ሰው መሆን ተነበዩ፡፡ ኢሳይያስ ‹‹እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም
አማኑኤል ይሉታል ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር
ሆነ ማለት ነው›› አለ፡፡ ዳግመኛም ‹‹ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም
በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና
በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ
የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።›› በማለት ትንቢት ተናገረ፡፡ ዳግመኛም ‹‹ሕፃኑ አባቱንና
እናቱን መጥራት ሳያውቅ የደማስቆን ሀብትና የሰማርያን
ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወስዳልና ስሙን፦ ምርኮ ፈጠነ፥ ብዝበዛ ቸኰለ ብለህ ጥራው አለኝ›› አለ፡፡ (ኢሳ
14 ፣ 9፤6፣ 8፤4)፡፡ ጌታችን በመወለዱ በዲያብሎስ የተያዙትን ማርኳል፣ ሲኦልን በዝብዟልና ስሙ ‹‹ምርኮ ፈጠነ ብዝበዛም ቸኮለ›› ተብሎ ተጠራ፡፡
የማይደፈር ግሩም ነው፤ በእኛ ዘንድ ግን ትሑት ነው፡፡ የማይደረስበት ልዑል ነው፤ በእኛ ዘንድ ግን የባርያውን
መልክ ነሳ፡፡ የማይዳሰስ እሳት ነው፡፡ እኛ ግን አየነው፣ ዳሰስነው፣ ከእርሱም ጋር በላን ጠጣንም (ቅዳሴ
ማርያም)፡፡ ሁሉ በእርሱ የተፈጠረና ሁሉን ሚመግብ
ሁሉ በእጁ የተያዘ መላእክት የሚታዘዙለትና የሚያገለግሉት፣ እኔ ግን በመካከላችሁ እንደሚያገለግል
ነኝ አለ (ሉቃ 22፤27)፡፡
በአዳም ምክንያት የጨለመውን ልቡናችንን ለማብራትና በእርሱ የሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር ብርሃን ሆኖ የመጣ (ዮሐ 12፤16)፡፡ ጨለማን ያስወገደ ብርሃን
የሃይማኖትና የጽድቅ ጣሪያዋ (ጠፈሯ)፣ ሃይማኖትም ወንጌልም፣ በብዙ ድካም እርሱን ደስ ያሰኙት የሚወርሱት፣ የሃይማኖት ገንዘብን ይዘው በሠርክ
የሚገቡበት መንግስተ ሰማያት እርሱ ነው (ሉቃ 17፤21፣ መልክአ ኢየሱስ)፡፡
ክብርና ምስጋና ይግባውና የእኛን ሞት ሞቶ የእርሱን ሕይወት የሰጠን፡፡ ድዳ ለነበሩት ቃል፣ ለተሰበሩት ምርጉዝ፣ ለዕውራን ብርሃን፣ለሐንካሶች መሄጃ፣
ለለምጻሞች የሚያነጻቸው ሆነ፡፡ በዴዌ የተያዙትን አዳነ፣ ደንቆሮዎችን ፈወሰ፣ ሞትን ዘለፈው ጨለማንም
አሰቃየው፡፡ ብርሃን ኅልፈት የሌለበት፣ ፀሐይ፣ የማይጠፋ
ፋኖስ፣ በቅዱሳን ላይ ዘወትር የሚያበራ ፀሐይ፣ በተወሰነ በቁርጥ ፈቃድ ለዓለም ጌጥ ሁሉን የፈጠረ፣ ሰውን
ለማዳን ለሁሉ የተገለጠ፣ ነፍሳችንን የመለሳት እርሱ ነው
(ኪዳን ዘነግህ)፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹‹ምንስ እላለሁ ምንስ እናገራለሁ ከዘመን በፊት የነበረ እርሱ ትንሽ ሕጻን ሆኗልና ፈጽሜ አደንቃለሁ፡፡ ከሰማየ ሰማያት በላይ
የሚሆን በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ›› በማለት የጌታን ትሕትና አደነቀ፡፡ ነፋሳት
የሚታዘዙለት፣ መላእክት የሚላላኩት እርሱ ለእናቱና ለዘመዶቹ እየታዘዘ አደገ፡፡ ሁሉን አዋቂ ሲሆን አልአዓዛርን የት ቀበራችሁት ብሎ ጠየቀ፤ እርሱ የሕይወት ውሃ ሲሆን ከሳምራዊት ሴት ውሃ ለመነ፡፡ ምራቅ ከጭቃ ጋር ለውሶ እውር ያበራ እርሱን አይሁድ ምራቅ ተፉበት፡፡ ጠባቂ አጥተው ለባዘኑት መልካም እረኛ ሆኖ መጣ ስለበጎቹም ነፍሱን ሰጠ፡፡ (ዮሐ 1፤11) ቅዱስ ያሬድ ‹‹ኖላዊ ኄር ኖላዊሆሙ ለእስራኤል ዘመጽአ ውስተ ዓለም ተአዛዚ ከዊኖ ክርስቶስ ለአሕዛብ፡፡ ኦሆ ብሂሎ ተአዛዚ ከዊኖ ወረደ ወመጽአ ለአድኅኖ… ከመ ይቤዙ ወያድኅን
4 374
#መድኃኔዓለም_አዳነን
መድኃኔዓለም አዳነን በማይሻር ቃሉ /2/
ደስ ይበለን /2/ እልል በሉ /2/
አዳነን በማይሻር ቃሉ /2/
4 374
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
#ልብ_ብለህ_አስተውል
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
#አትመኝ፦ እንደ አዳም የዲያብሎስ ባሪያ ትሆናለህ፡፡ ዘፍጥ 3÷1-8
#አትቅና፦ እንደ ቃየል ወንድምህን ትገላለህ፡፡ ዘፍጥ 4÷1-
#አትስከር፦ አዕምሮ አሳጥቶ የማይገባ ሥራ ትሠራለህ፡፡ ዘፍጥ 19÷30-38
#ዓለምን አትመልከት፦ እንደ ሎጥ ሚስት የጨው ዐምድ ሆነህ ትቀራለህ፡፡ ዘፍጥ 19÷22-23
#በአባትህ አትሳቅ፦ እንደ ካም ትረገማለህ፡፡ ዘፍጥ 9÷20
#እልከኛ አትሁን፦ እንደ ፈርዖን ትሰጥማለህ፡፡ ዘፀ 14÷28
#በሐሰት አትመስክር፦ እንደ ሐማ ባዘጋጀኸው ጉድጓድ ትገባለህ፡፡ መጽ.አስቴ 7÷1
#ትዕቢተኛ አትሁን፦ እንደ ሰናክሬም ትወድቃለህ፡፡ 2ነገ:19÷35
#ክፉ ባልንጀራን አትያዝ፦ እንደ ሶምሶን በጠላት እጅ ትወድቃለህ፡፡ መጽ.መሳ 16÷15
#አትዘሙት፦ እንደ ሰሎሞን አምላክህን አስረስቶ ጣዖትን እንድታመልክ ያደርግሃል፡፡ 1ነገ 11÷1-8
#ሥልጣንን አትውደድ፦ እንደ አቤሴሎም #በአባትህ ላይ ትነሣለህ፡፡ 2ነገ ሳሙ 15÷13-17
#ገንዘብን አትውደድ፦ እንደ ይሁዳ ጌታህን ያስክድሃል፡፡ ማቴ:26÷14-16
☞☞☞✞ @EOTC2921 ✞☜☜☜
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!
4 374
☞= "ፍፁም ፍቅር" =
ባልንጀራውን የሚወድ በባልንጀራው ላይ ክፉ ሥራ
አይሠራም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው።[ ሮሜ 13፥10]
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
☞"ይቅር ባይነት"
በምትጸልዩበትም ጊዜ በሰማያት ያለው አባታችሁ በደላችሁን ይቅር እንዲላችሁ በወንድማችሁ ያለውን በደል ይቅር በሉ።
እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም በደላችሁን
ይቅር አይላችሁም።" (ማር. 11፥25-26)
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
☞"በጎነት (ቸርነት)"
ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚበድሉአችሁና ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ። ||ማቴ 5፥44||
ክፉ ላደረገባችሁ ክፉ አትመልሱ፤ የሰደባችሁንም አትስደቡ፤ጠላታችሁንም መርቁ፤ በረከትን ትወርሱ ዘንድ ለዚህ
ተጠርታችኃልና።[ 1ኛ ጴጥ.3፥9]
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
☞"ትህትና"
ለትዕቢተኞች ጥፋት ፈውስ የላትም፤ ክፉ ተክል በውስጣቸው ሥር ሰድዶአልና። (መ.ሲራክ 3፥26)
ራሱን ከሁሉ ዝቅ የምያደርግ እርሱ ታላቅ ይሆናል።{ሉቃስ 9፥48}
እግዚአብሔርን በመፍራት ለባልንጀራችሁ ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ።// ኤፌሶን 5፥21//
ትህትናን በያዘ ልቡና ከራሳችሁ ይልቅ ባልንጀራችሁን አክብሩእንጅ አትታበዩ።
ትዕቢትን የሚያደርግ በቤቴ መካከል አይኖርም፤ ዐመፃን የሚናገር በፊቴ አይጸናም። መዝ 100 ፥ 7
ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ኦሪትም ነቢያትም የሚያዝዙት ይህ ነውና። [[ማቴ7፥12]]
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
"ለራስህ የምትጠላውን ለማንም አታድርግ።" (መ.ጦቢት 4፥15)
አቤቱ አባታችን ሆይ! ማስተዋሉን አድለን፤ እኛ ደካሞች ነንና አንተ አጋዥ ሁነን። ከሁሉ አስቀድመን እንለምንሃለንና ሁሉን
እንወድ ዘንድ ንፁህ ልብን ስጠንን፤ የይቅርታ ልብንም ስጠን፤
ነፍሳችን ትህትናን ትላበስ ፤ በጎ ምግባርን ይዘን 30,60,100
ያማረ የሕይወት ፍሬ አፍርተን የመንግሥትህ ወራሾች እንድንሆን
ፍቀድልን ሁሉ ይቻልሃልና። ክብር ምስጋና ለስምህ ይሁን አሜን።
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
#ፍቅር
ከእግዚአብሔር ቤት መራቅ ስትጀምር ፍቅር ካንተ ትርቃለች። ከምታየው ነገር ጋር ሁሉ ትጣላለህ። የምትጣላውም ከሰዎች ጋ ብቻ አይደለም። ካገኘከው ነገር ጋ እና ከራስህም ጋ ጭምር እንጂ። ከራስህ ጋ ተከራክረህ እራስህን መርታት ከማትችልበት ጭንቀት ውስጥ ትወድቃለህና የምትሞትበትን ጊዜ ታመቻቻለህ። እንደ ይሁዳ ታንቆ ለመሞት አልያም እንደ ሌሎቹ በሌላ ምክንያት እራስህን እስከማጥፋት ድረስ ማንነትህን ትጥላለህ። እራስህን እንደ ሰው መቁጠር ከማትችልበት ከባድ ሙግት ውስጥ ትወድቃለህ። በዚህም ከአምላክህ ጋ እና ከሰዎች በፍቅርና በሰላም መኖር አልችል ትላለህ። ሁልጊዜ ከሰዎች ጋ ክርክርና ጥላቻ ይሆንብሀል። ጠላትን የምታጠፋበት ትልቁ መሳሪያ ፍቅር ብቻ መሆኑን ትዘነጋለህ። ይህን የከበሩ እንቁዎች የማይተካከሉትን ልዩ ፀጋ ማጣት ማለት ሰው ሁኖ ተፈጥሮ ሰው ሁኖ አለመገኘት ነው። የሰውነት መመዘኛው ትልቁ ሚዛን ፍቅር ነው።
ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮህ ንሀስ ወይንም እንደሚንሿሿ ፅናፅል ሁኛለሁ። ትንቢትም ቢኖረኝ፣ ሚስጥርንም ሁሉና፣ እውቀትንም ሁሉ ባውቅ፣ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፣ ስጋዬን ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።
ፍቅር ይታገሳል፣ ቸርነትንም ያደርጋል፣ ፍቅር አይቀናም፣ ፍቅር አይመካም፣ አይታበይም፣ የማይገባውን አያደርግም፣ የራሱንም አይፈልግም፣ አይበሳጭም፣ በደልን አይቆጥርም፣ ከእውነት ጋ ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም።
ሁሉን ይታገሳል፣ ሁሉን ያምናል፣ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል በሁሉ ይፀናል።
ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም። እንዲህም ከሆነ እምነት፣ ተስፋ፣ ፍቅር እነዚህ ሶስቱ ፀንተው ይኖራሉ። ከነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።
1ኛ ቆሮ 13፥1-13
ፍቅር በሰዎችና በመላእክት ልሳን ከመናገር በላይ ነው። ድሆችንም ከመመገብና ስጋችንም ለእሳት አሳልፈን ከመስጠት የላቀ ነው። እውነተኛ ፈቅር የሚታገስ፣ ሁሉን የሚያምን፣ ከእውነት ጋ ደስ የሚለው፣ የማይቀና፣ ቸርነት የሚያደርግ የማይመካ፣ በደልን የማይቆጥር፣ ሁሉን ተስፋ የሚያደርግ ነው። ይህንን ፍቅር የምናገኘው ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋ በመሆን ብቻ ነው። ምክንያቱ ፍቅር ከእግዚአብሔር ነው እራሱ እግዚአብሔርም ደግሞ ፍቅር ነውና።
ሐዋርያው ዮሃንስ በመልእክቱ እንዲህ ይላል:-ወዳጆቼ ሆይ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ የሚወደው ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለተወለደ እግዚአብሔርም ስለሚያውቅ እርስ በራሳችን እንዋደድ።1ኛ ዮ 4፥7
ለዚህም ነው ፍቅር የሆነውን እግዚአብሔርን ስትርቅ ፍቅር ደግሞ ከአንተ የምትርቀው። ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍፃሜ በመሆኗ ትልቁ ገንዘብ ናት። ፍቅርን የምንገልፀው ሰውን እግዚአብሔርን እንዲሁም ሀገርን በመውደድ ነው።
እኛም እንደታማኙ አገልጋይ ጌታ የሰጠንን መክሊት ልናተርፍበት ይገባል። በመክሊታችን ትርፋማ ለመሆን ደግም ፍቅር ትልቁን ሚና ይጫወታል። ስለዚህ ፍቅርን ለብሰን ትህትናን ተጫምተን በማስተዋል መጓዝ አለብን።
የፍቅር አምላክ ፍቅርን ያድለን!
የአብ_ፀጋ_የወልድ_ፍቅር_የመንፈስ_ቅዱስ_አንድነት አይለየን አሜን።
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንንበየቀኑ አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
#የልዳው_አንበሳ
የቤሩቱ ኮከብ የልዳው አንበሳ
ሦስት ጊዜ ሞቶ ጊዮርጊስ ተነሳ/2/
#አዝ........
በተጋድሎ ጸና........ቅዱስ ጊዮርጊስ
በእውነት መሰከረ...ቅዱስ ጊዮርጊስ
ኃያሉ ጊዮርጊስ......ቅዱስ ጊዮርጊስ
በሰይፍ ተመተረ.....ቅዱስ ጊዮርጊስ
የልዳው አንበሳ......ቅዱስ ጊዮርጊስ
ጠላት አይገዛህ......ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሰይጣንን ተዋጋው..ቅዱስ ጊዮርጊስ
ጎልማሳው ሥጋህ...ቅዱስ ጊዮርጊስ
#አዝ..........
ዲድያኖስ ተቆጣ....ቅዱስ ጊዮርጊስ
ጽናትህን አይቶ.......ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሊቀጣ ተነሳ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ
በትዕቢት ተሞልቶ...ቅዱስ ጊዮርጊስ
ባንተላይ ወገኑ......ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሰባ ነገሥታት........ቅዱስ ጊዮርጊስ
ከምድረ ገፅ አንተን....ቅዱስ ጊዮርጊስ
ፍፁም ለማጥፋት.....ቅዱስ ጊዮርጊስ
#አዝ.........
በመበለቷ ቤት ..........ቅዱስ ጊዮርጊስ
ጊዮርጊስ ተአምር ሰራ....ቅዱስ ጊዮርጊስ
ምሶሶ አለምልሞ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ
እውራን አበራ................ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሰባት አክሊላትን ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ
ጊዮርጊስ ተቀበለ...........ቅዱስ ጊዮርጊስ
ስለ ጌታ ፍቅር ..............ቅዱስ ጊዮርጊስ
ባደባባይ ዋለ................ቅዱስ ጊዮርጊስ
#አዝ..........
ዝክርህን ዘክሮ......ቅዱስ ጊዮርጊስ
ስምህን የጠራ......ቅዱስ ጊዮርጊስ
በነፍስም በሥጋ....ቅዱስ ጊዮርጊስ
የለበት መከራ.......ቅዱስ ጊዮርጊስ
ደራጎንን አጥፋ.....ቅዱስ ጊዮርጊስ
አርቅልን ከኛ........ቅዱስ ጊዮርጊስ
በዝሙት በኃጢአት....ቅዱስ ጊዮርጊስ
ደርሶብናልና..............ቅዱስ ጊዮርጊስ
4 374
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
#የቅዱስ_ጊዮርጊስ_ተጋድሎ_በኢትዮጵያ_ሊቃውንት
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
❖ የዚኽም ቅዱስ አባቱ በቀጶዶቅያ መስፍኑ አንስጣስዮስ ሲኾን እናቱ
ቴዎብስታ ትባላለች፤ የተወለደውም በልዳ በሶርያ ፍልስጥኤም በ፪፻፹ ዓ.ም.
ነው፤ ታናሽ ኾኖ ሳለ አባቱ ዐርፏል፤ ቅዱሳት መጻሕፍትን ፈረስ ግልቢያን ተምሮ
ኻያ ዓመት በኾነው ጊዜ ቢሩት ሀገር በመኼድ በዚያ ሀገር ይመለክ የነበረውን
መንፈሰ ሰይጣን ያደረበትን የመኰንኑን ልጅ እንዲበላት የተሰጠውን ዘንዶ
በክርስቶስ ስም ከገደለው በኋላ እጅ መንሻ ይዞ ወደ ንጉሠ ፋርስ ኼደ፡፡
❖ በዚያ ሀገር ግን ነገሥታቱ ጣዖታትን በማምለክ ክርስቲያኖችን
ሲያሳድዷቸው አይቶ ዐዘነ፤ ልቡም በክርስቶስ ፍቅር ነድዶ ወደ ሀገሬ
አልመለስም ስለ ክርስቶስ ስም እሞታለኊ አለና “ክርስቲያናዊ አነ ወአአምን
በእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ” (እኔ የክርስቲያን ወገን ነኝ እምነቴም በጌታችን
በኢየሱስ ክርስቶስ ነው) በማለት መሰከረ፡፡
❖ ከዚያም ንጉሡ ልብሱን ገፍፈው በዕንጨት ላይ እንዲሰቅሉት፤ ዳግመኛ
የዘንባባ እሾኽ የመሳሰሉ ፸ የብረት ችንካሮች ሠርተው በነዚያ እንዲቸነክሩትና
ዐጥንቱን ኹሉ እንዲቀጠቅጡት አዘዘ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን በትዕግሥት
በመኾን “እፎ ኢይኄሊ ከመ አምላኪየ ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ
መስቀል” (ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል እንደተሰቀለ እንዴት አላስብም)
አለ፡፡
❖ ዳግመኛም በውስጡ ረዣዥም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማን
ባጫሙት ጊዜ “ሠጠቅዎ ወመተርዎ ዐሥራዊሁ እስከ ውኅዘ ደሙ ዲበ ምድር
ከመ ማይ ወሶበ ስዕነ ሠጊረ ድቡተ ሖረ” ይላል ችንካሮቹ ደሙ እንደ ውሃ
በምድር ላይ እስኪፈስስ ድረስ እግሩን ዘልቀው ሥሩን በጣጠሱት፤ መኼድም
ባልቻለ ጊዜ አጐንብሶ ኼዷል፤ ከዚያም የፈላ የብረት ጋን ውስጥ ከትተው
ሰውነቱ በደም እስኪጥለቀለቅ ድረስ ራሱን በመዶሻ ሲመቱት ወደ ጌታችን ጸለየ፤
ያን ጊዜ “ጊዮርጊስ ሆይ ከአንተ ጋር ነኝና ጽና” የሚል ቃል ከሰማይ መጣለት፤
ቅዱስ ሚካኤልም ተገልጾ ከሕመሙ ፈውሶታል፡፡ ይኽነንም ባዩ ጊዜ ብዙዎች
በጌታችን አመኑ፡፡
❖ ንጉሡም ይኽነን ባየ ጊዜ እጅግ የሚያስጨንቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀን
አሠርቶ ለቅዱስ ጊዮርጊስ “እመሰ ትሠውዕ ለአጵሎን ትነሥእ ጌራ መንግሥት
ወእመሰ ኊልቊ አንተ ከመ ትትልዎ ለክርስቶስ ነጽር ዘንተ መንኰራኲረ
ዘግበርኩ ለከ ከመ እግድፍ በውስቴታ ታማስን ሥጋከ” (ለአጵሎን ብትሠዋ
የመንግሥትን ዘውድ ትቀዳጃለኽ፤ ግን ክርስቶስን ለማገልገል የቈረጥኽ
ብትኾን ሥጋኽን ትፈጭ ዘንድ በውስጧ ልትጣልባት ያዘጋጀኋትን መንኰራኲር
ተመልከት) አለው፤ ይኽ ሲኾን ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጣሪው ክርስቶስን አመሰገነ፡፡
❖ እነርሱም ወደ መንኰራኲሩ በመወርወር ፵ ሰዎች ያዞሩት ዠመር
ከዚያም ሰውነቱ ለዐሥር ክፍል ተከፋፈለ፤ እነርሱም ሥጋውን በጒድጓድ ውስጥ
ቀበሩት፤ ክብር ይግባውና ጌታችን መላእክትን አስከትሎ በመምጣት እንደገና
ከሞት አስነሣውና ባረከው፡፡
❖ ርሱም ከሞት ተነሥቶ እንደገና ወደ ከተማ ገብቶ ስለ ክርስቶስ
አምላክነት መሰከረ፤ እነርሱም እጅግ ለመስማት የሚከብዱ መከራዎችን
አደረጉበትና ሰውነቱን ጨምቀው አንጀቱን ዘረገፉት፤ ከዚያም ሥጋውን አቃጥለው
በዕንጨት ቀፎ በማድረግ ይድራስ ወደተባለ ተራራ ወስደው ዐመዱን በትነውት
ተመለሱ፤ ክብር ይግባውና ጌታችን መላእክትን አስከትሎ በመውረድ አራቱን
ነፋሳተ ምድር የተበተኑትን የቅዱስ ጊዮርጊስን ሥጋዎች እንዲሰበስቡ አዝዞ
እንደገና ከሞት አስነሥቶታል፤ ይኽነንም ባዩ ጊዜ ብዙዎች በክርስቶስ አምነው
የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጅተዋል፡፡
❖ በመጨረሻም ብዙ ተጋድሎዎችን ለሰባት ዓመታት ከፈጸመ በኋላ ንጉሡ
የቅዱስ ጊዮርጊስ ራስ በሰይፍ እንዲቈረጥ አዝዞ ወደ መሰየፊያው ቦታ ሲኼድ
እሳት ከሰማይ ወርዶ ፸ውን ነገሥታት ያቃጥላቸው ዘንድ መከራውም
ከክርስቲያኖች ጸጥ ይል ዘንድ ጸለየ፤ ወዲያውኑም እሳት ከሰማይ ወርዶ ፸ውን
ነገሥታት አቃጥሏቸዋል፤ ከዚያም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ለቅዱስ ጊዮርጊስ ብዙ ቃል ኪዳንን ከሰጠው በኋላ በክብር ወደ ሰማይ ወጣ፤
ከዚያም ፊቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ ራሱን ዘንበል አድርጎ ሚያዝያ ፳፫ በሰይፍ
ቈርጠውት የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጅቷል፡፡
❖ ከአገልጋዮቹ የቀሩት ሥጋውን ወስደው በንጹሕ ልብስ ጠቅልለው ወደ
ሀገሩ ልዳ በመውሰድ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው በውስጡ አኖሩት፤ ከርሱም
ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች ድንቆች ተአምራት ተገልጠዋል፡፡
❖ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አባ ጽጌ ብርሃን በማሕሌተ ጽጌ ድርሰታቸው ላይ፦
“ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየሐቱ
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ
አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ”
(የስሙና የሞቱ መታሰቢያ ባንቺ የተጻፈብሽ የሚያበራ ከኾነ ዕንቈ ባሕርይ ይልቅ
የጠራ ወርቅ ክበብ ያለው የራስ ቊር የተባለ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ የራስ
ልብስ ጌጥ ሽልማት የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ አንቺ ለርሱ ኹሉን
ታሰግጅለታለሽ (ታንበረክኪለታለሽ) ርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል) ይሉታል፨
❖ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቁ አርከ ሥሉስም የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ
ጊዮርጊስን ተጋድሎ፡-
“ሰላም ለከ ሰርዌ ሰማዕታት አእላፍ
ዘሞገሰ ስምከ በጽሐ መንገለ ኲሉ አጽናፍ
በቅድመ ፀሓይ ብሩህ ዘኢየዐርብ ለዘልፍ
ሕማምየ ዝሩ ነሢአከ ወጸዊረከ እስትንፋሰ አፍ
ጊዮርጊስ ቀሊለ ክንፍ ከራድዮን ዖፍ”
(ዘወትር በማይጠልቅ በብሩህ ፀሓይ ፊት በምድር ዳርቻዎች ኹሉ የስምኽ
ባለሟልነት የደረሰ የአእላፍ ሰማዕታት አለቃቸው ሰላምታ ለአንተ ይገባል፤ ክንፈ
ፈጣን ከራድዮን ዖፍ የተባልኽ ጊዮርጊስ ሆይ የአፍ እስትንፋስን ተቀብለኽና
ተሸክመኽ ሕማሜን በትን) እያለ ተማፅኖታል፡፡
❖ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፦
“ሰላም ለጊዮርጊስ ሰማዕት ዘፀሓየ ጽድቅ
ዘተአምሪሁ ከመ ኆጻ ባሕር
ዘኢይትኌለቊ ኮከበ ክብር
ዘማእከለ ሰማይ ወምድር
ዘአርአየ ኀይለ በዲበ ሰሌዳ መንበር
ብእሲ አዛል ወመስተጋድል
ኀያል ዝሕዙሐ ገድል”፡፡
(ገድሉ የበዛ የተትረፈረፈ ኀያል፤ ተጋዳይ ጐልማሳ (ብርቱ) ሰው፤ በተዘረጋ ዙፋን
ላይ ኀይልን ያሳየ፤ በሰማይና በምድር መኻከል ያለ የማይቈጠር የክብር ኮከብ፤
ተአምሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ የኾነ፤ የፀሓየ ጽድቅ የኢየሱስ ክርስቶስ ሰማዕት
ለኾነ ለጊዮርጊስ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፨
❖ የስብሐተ ፍቁር ዘጊዮርጊስ ደራሲ ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ፦
"እምብሩር ወወርቅ ይትበደር ሞገሱ
ለጊዮርጊስ ቅዱስ በዲበ ጸዐዳ ፈረሱ
ለረዲኦትነ ይምጻእ ወያንሶሱ"
(ከወርቅና ከብር ይልቅ ሞገሱ የሚበልጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረሱ እኛን
ለመርዳት ይምጣ፤ ይመላለስም) ይለዋል፨
👇👇👇👇👇👇👇
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
ማቸዋል፡፡
♥️ ❖ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ጽዮንን የሚጠሉ ኹሉ ስለሚደርስባቸው ዘላለማዊ ምክነት በመዝ 128፥5-8 ላይ፦ "ጽዮንን የሚጠሉ ኹሉ ይፈሩ፤ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ፤ በሰገነት ላይ እንደበቀለ ሣር ሳይነቀል እንደሚደርቅ ለሚያጭደው እጁን፤ ነዶዎቹን ለሚሰበስብ ዕቅፉን እንደማይመላ ይኹኑ፤ በመንገድም የሚያልፉ የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይኹን በእግዚአብሔር ስም እንመርቃችኋለን አይሉም" በማለት እንደተናገረ ጽዮን የተባለች የድንግል ማርያም አማላጅነት የሚቀዋወሙ የዲያብሎስ የግብር ልጆች መናፍቃን እንደ ሜልኮል ከእግዚአብሔር ጸጋ የራቁ ናቸው፡፡
♥️❖ ከሊቃውንትም አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው:-
"እስከ መነነቶ ሜልኮል ቅድመ ታቦት ሕግ ከመ ዘፈነ
ንጉሠ እስራኤል ኪያኪ ዘጸገየ ሥነ
ቅድመ ገጸ ሥዕልኪ ድንግል እዘፍን አነ
ዘይሜንን ተአምረኪ ወስብሐተኪ ቊርባነ
በአፈ መላእክት ወሰብእ ለይኩን ምኑነ"
✍️ (አንቺን ያስገኘ የእስራኤል ንጉሥ ዳዊት ሜልኮል እስከናቀችው ድረስ በእግዚአብሔር የሕግ ታቦት ፊት እንዳመሰገነ፤ ድንግል ሆይ እኔም በሥዕልሽ ፊት እዘምራለኍ፤ ድንቅ ታምርሽንና የቀረበ መንፈሳዊ ምስጋናሽን የሚንቅ በመላእክትና በሰው አንደበት የተረገመ ይኹን) በማለት አስተምረዋል፡፡
🙏የአማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም በረከት ይደርብን፡፡🙏
✍️ ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
