የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
Ir al canal en Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
Mostrar más4 374
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
4 374
💚ይኸውም ምሳሌነቱ በመተርጉማን እንደተተነተነው ካህኑ መልከ ጼዴቅ በስንዴና በወይን ያስታኩት እንደነበር ሊቀ ካህናት ጌታም ሥጋውን ደሙን በስንዴና በወይን ሰጥቶናልና (ዘፍ ፲፬፥፲፰፤ ማቴ ፳፮፥፳፮-፳፯)፡፡
✥መልከ ጼዴቅ ሹመቱን ከእግዚአብሔር ተሾሞታል እንጂ ከእገሌ ተሾመው እንዳይባል፤ ሊቀ ካህናት ጌታም ሥልጣኑ የባሕርዩ ነው እንጂ ከሌላ የተሰጠው አይደለምና፡፡
✥መልከ ጼዴቅ አባትና እናት ቢኖሩትም ቅሉ በሌሎች መጻሕፍት እንጂ በሌዋውያን መጽሐፍ የአባቱና የእናቱ ነገር እንዳልተጻፈ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በእውነት ለቀዳማዊ ልደቱ እናት፤ ለደኀራዊ ልደቱ አባት የለውምና፡፡
✥መልከ ጼዴቅ ምንም መነሻና መድረሻ ቢኖረውም ቅሉ ለዘመኑ ጥንት ለአነዋወሩ ፍጻሜ አለው ብሎ የጻፈለት የሌዋውያን መጽሐፍ እንደሌለ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን አማን በአማን ለዘመኑ ጥንት ለአነዋወሩ ፍጻሜ የሌለው፤ ቅድመ ዓለም የነበረ፤ አኹንም ያለ፤ ዓለምንም አሳልፎ የሚኖር ነውና፡፡
✥አብርሃም ለመልከ ጼዴቅ ከዐሥር አንድ እንደሰጠው፤ ምእመናንም ዘወትር ዐሥራተ ጾም ዐሥራተ ጸሎታቸውን ለጌታ ይሰጣሉና፡፡
✥መልከ ጼዴቅ የስሙ ትርጓሜ “የእውነት ንጉሥ” እንደኾነ፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ለመንግሥቱ ፍጻሜ የሌለው ንጉሠ ነገሥት ነውና፡፡
✥ዳግመኛም ይኽ መልከ ጼዴቅ “የሰላም ንጉሥ” ተብሎ እንደተጠራ፤ ጌታም በከበረ ደሙ ፈሳሽነት ለኹሉም ሰላምን ያደለ “ወሀቤ ሰላም፣ ንጉሠ ሰላም” ነውና ተመስሎበታል (ኤፌ ፪፥፲፬-፲፯፤ ዮሐ ፲፬፥፳፯)፡፡
✥ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የመልከ ጼዴቅን ምሳሌነት ስለዚኽ ነገር አምልቶ አስፍቶ ሲያስረዳ፡-
☞ “ናሁኬ አብጽሐ ዘይንእስ ኀበ ዘየዐብዮ ወዘይቴሐት ኀበ ዘይትሌዐሎ መሥዋዕተ መልከ ጼዴቅ…” (እነሆ የሚያንሰው ወደሚበልጠው ዝቅ ዝቅ የሚለውም የመልከ ጼዴቅ መሥዋዕት አደረሰ፤ የመልከ ጼዴቅስ መሥዋዕት የመለኮት ኀይል በላዩ አላደረም፤ የርሱን ሥጋና ደም ብሎ ይጠራው ዘንድ ያን ጊዜ ክርስቶስ ሰው አልኾነምና፤ ዳሩ ግን ለምእመናን እንደሚሰጥ የተጸለየበት ኅብስትና የተባረከ ጽዋ ክብር ነበረው (ዘፍ ፲፬፥፲፰) የመልከ ጼዴቅም ክህነት እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ክህነት ፍጹም አልኾነም፤ አብ ከሰማይ “የምወድደው ልጄ ይኽ ነው፤ ርሱን ስሙት” ብሎ አልመሰከረለትምና፤ መልከ ጼዴቅ አምላክ አይደለምና፨
✢መልከ ጼዴቅ አብርሃምን እንደባረከው (ዘፍ ፲፬፥፳) ክርስቶስም ደቀ መዛሙርቱን ባረካቸው (ሉቃ ፳፬፥፶)፤
✢መልከ ጼዴቅ ከአብርሃም ከዐሥር አንድ እንደተቀበለ ክርስቶስም ከሰብአ ሰገል እጅ መንሻ ተቀበለ (ማቴ ፪፥፲፩)፤
✢መልከ ጼዴቅ በኦሪት መጽሐፍ የእግዚአብሔር ካህን ተብሎ እንደተጠራ (ዘፍ ፲፬፥፲፰፤ መዝ ፻፱፥፬) ክርስቶስም በጳውሎስ አንደበት ሊቀ ካህናት ተባለ (ዕብ ፭፥፱-፲)፤
✢መልከ ጼዴቅ የሳሌም ንጉሥ እንደተባለ ክርስቶስም የእስራኤል ንጉሥ ተብሎ ተጠራ፤ ሚክያስ የኤፍራታ ምድር የኾንሽ አንቺ ቤተልሔም ከይሁዳ መሳፍንት አታንሺም፤ ወገኖቼ እስራኤልን የሚጠብቃቸው ንጉሥ ከአንቺ ይወጣልና ብሎ ተናግሯልና (ሚክ ፭፥፪)) ይላል፨
💚ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፦
“ሰላም ለመልከ ጼዴቅ ዐቢይ ካህን አምሳሊሁ ለወልደ እግዚአብሔር ዘእእመረ ምስጢሮ ኅቡአ ዘሀሎ ይትገበር” (ሊከናወን (ሊፈጸም) ዘንድ ያለውን ስዉር (ድብቅ) ምስጢሩን ያወቀ፤ ለእግዚአብሔር ልጅ ምሳሌው ለኾነ ለታላቁ ካህን ለመልከ ጼዴቅ ሰላምታ ይገባል) ብሎ ሰላምታ አቅርቦለታል፨
💚ኢትዮጵያዊው ሊቅ ዐርከ ሥሉስም በዐርኬው ላይ፦
"ሰላም ለመልከ ጼዴቅ አምሳሉ ወሱታፉ ለዘመጽአ ቃል በደመና ድንግል ዐፅፉ ጠቢባን ግብሮ በከመ ጸሐፉ ለሥጋ አቡነ አዳም ኀበ ተሐንጸ ምዕራፉ ዝንቱ ካህን ይነብር ለዝሉፉ" (በደመና የተመሰለች የድንግልን ሥጋ ተጎናፅፎ (ተዋሕዶ) ለመጣው ሥግው ቃል ምሳሌው ለኾነ ለመልከ ጼዴቅ ሰላምታ ይገባል፤ ጠቢባን ሥራውን እንደጻፉ የአባታችን አዳም የሥጋው ማረፊያ በታነጸበት ይኽ ካህን ለዘወትር ይቀመጣል) በማለት ድንቅ ውዳሴን ያቀርብለታል፨
💚ታላላቅ ሊቃውንት ሕገ ኦሪት ሳይሠራ ገና በሕገ ልቡና አበ ብዙኃን አብርሃምን የባረከው የወልደ እግዚአብሔር ምሳሌ የኾነው መልከ ጼዴቅ ከነገደ ሴም ሳይኾን ከነገደ ካም በመኾኑ የርሱም ርስት አህገራችን አፍሪካና ምስርን ኖባን አንድ አድርጋ የገዛች ኢትዮጵያ ናትና ታላቋ ሀገራችን ኢትዮጵያ ገና ሕገ ኦሪት ለእስራኤል ሳይሠራ በሕገ ልቡና አምላኳ እግዚአብሔርን በመልከ ጼዴቅ በኩል ስታመልክ የኖረች ናት ይላሉ፨
💚ካም የነበረበት ከአምላካችን ከክርስቶስ ልደት በፊት 3244 ዓመት ሲኾን በዚኽ ላይ የሐዲስ ኪዳንን የ2011 ዓመተ ምሕረትን ስንጨምርበት 5255 ዓመታት ሳታቋርጥ በሦስቱ ኪዳናት በሕገ ልቡና፣ በሕገ ኦሪት፣ በሕገ ወንጌል አምላኳ ፈጣሪዋ ልዑል እግዚአብሔርን ስታመልክ ኖራለች፤ እስከ ዕለተ ምጽአትም ንጹሕ ምስጋናዋን ለፈጣሪዋ ለክርስቶስ ታቀርባለች፨
💚"ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የሚማልዱኝ የተበተኑት ሴቶች ልጆቼ ቍርባኔን ያመጡልኛል።" (ትንቢተ ሶፎንያስ 3፥10)
"የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር" (ትንቢተ አሞጽ 9፥7)
✍በመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ
🙏✞የመልከ ጼዴቅ በረከት ይደርብን✞🙏
✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
https://t.me/EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
🌾⛪️ #ታላቁ_ካህን_መልከ_ጼዴቅ ⛪️🌾
ጳጉሜ ፫
💚ይኽ መልከ ጼዴቅ ዐፅመ አዳምን እንደ ታቦት አድርጎ በኅብስት በወይን መሥዋዕት ያቀርብ የነበረ ደገኛ ካህን ነበር (ዘፍ ፲፬፥፲፰)፡፡ ይኸውም ሊቃውንት እንደጻፉልን ኖኅ ከጥፋት ውሃ በኋላ ከመርከብ ሲወጣ ከዚኽ ኹሉ ላዳነኝ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባዋል ሲል፤ ዐፅመ አዳምን እንደታቦት አድርጎ መሥዋዕት ሠዋ፡፡
💚ከዚኽም በኋላ ሴምን ጠርቶ “ዐጽመ አዳምን ወስደኽ እግዚአብሔር ወዳዘዘኽ ቦታ አኑር” ብሎታል፡፡ ሴምም ከካም ወገን የተወለደው መልከ ጼዴቅን ከናት ካባቱ አሰናብቶ ዐጽሙን አሸክሞ ይዞት ኼደ፤ መላእክት እየመሩ መስቀል ከሚተከልበት ቀራንዮ አደረሱት እዛም ሲደርስ ምድር ተከፈተችለት፤ ዐፅመ አዳምንም አግብቶ አኖረ መልከ ጼዴቅም ዐፅመ አዳምን እንደታቦት አድርጎ ዐሥራ ኹለት ደንጊያዎችን በመትከል መሥዋዕት ጸሎት ያቀርብ ነበር፡፡
💚የሶርያ ሰዎች በነገር ተከራክረው ወደ ርሱ ሲኼዱ እውነት ይፈርድላቸው ስለነበር “ንጉሠ ጽድቅ” ሲሉት፤ ቢጣሉ ስለሚያስታርቃቸው “ንጉሠ ሰላም” ብለው ጠርተውታል፡፡
💚ክህነቱም ከሌዊ የሚበልጥ ደገኛ ክህነት ነበርና በስንዴና በወይን ሲያስታኩት ኖሯል፡፡ ምግቡንም መላእክት ያመጡለት ነበር፤ ልብሱም ዳባ ነበር፡፡
💚የትውልዱንም ነገር ዮሐንስ መደብር ባራተኛው ክፍል ላይ:-
“መልከ ጼዴቅ ውእቱ ዘወፅአ እምነገደ ሴዱ ወልደ ንጉሠ ምስር ወኖባ፤ ወውእቱ ሴዱ ዘነግሠ ከነዓን፣ ወውእቱ አምነገደ ጽኑዓን፤ ወውእቱ ተጻብኦሙ ወተቀንዩ ሎቱ፤ ወሶበ አስተፍሥሕዎ ነበረ ውስቴታ ወሐነጸ ሀገረ ወሰመያ በስመ ዚኣሁ ሳይዳ፤ ወእስከ ዮም ትሰመይ ሳይዳ ወአቡሁ ለመልከ ጼዴቅ ወቦአ እምነ ሳይዳ” (የኖብና የምስር ንጉሥ ልጅ ከሚኾን ከሴዱ ነገድ የወጣ (የተወለደ) መልከ ጼዴቅ ነው፡፡ ያውም ሴዱ በከነዓን የነገሠ ነው፤ ርሱም ከጠንካሮቹ ነገድ ነው፤ ርሱም ተዋጋቸውና ተገዙለት፤ በስደቱም ጊዜ በውስጧ ተቀመጠ፤ ከተማንም ሠርቶ በርሱ ስም ሳይዳ ብሎ ጠራት፣ እስከ ዛሬም ሳይዳ በመባል ትታወቀለች፤ የመልከ ጼዴቅ አባትም ከሳይዳ ወጣ) ይለዋል፡፡
💚በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ ፲፬ ላይ እንደምናነበው ዐምስቱ ነገሥተ ሰዶም ወገሞራ ለአራቱ ነገሥተ ኮሎዶጎሞር ፲፪ ዓመት ገብረው በ፲፫ኛው ዓመት አንገብርም በማለታቸው፤ በዐዘቅተ ኤሌቅ በተዋጉት ውጊያ፤ አራቱ ነገሥተ ኮሎዶጎሞር ድል አድርገው ሎጥን ከዚያ አግኝተው ማርከውታል፤ አብርሃምም ይኽነን ሰምቶ ከቤተሰቦቹ ፫፻፲፰ት ሰዎች ይዞ ኼዶ ነገሥተ ኮሎዶጎምርን ድል ነሥቶ የተማረከ ወንድሙ ሎጥን መልሶታል፡፡
💚ይኽም ምሳሌ ነው አብርሃም የጌታ፤ ሎጥ የሃይማኖት፤ ፫፻፲፰ቱ የ፫፻፲፰ ሊቃውንት፤ አራቱ ነገሥተ ኮሎዶጎሞር የመናፍቃን፤ ዐምስቱ ነገሥተ ሰዶም የምእመናን ምሳሌ፤ አብርሃም ፫፻፲፰ ሰው ይዞ አሕዛብን ድል ነሥቶ ሎጥን እንደመለሰ ጌታም በ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ዐድሮ ሃይማኖትን የመመለሱ ምሳሌ እንደኾነ መርተርጒማነ ብሉይ ያስተምራሉ፡፡
💚ከዚኽ በኋላ አብርሃም ደስ ብሎት ለአዳምና ለልጆቹ የድኅነት ተስፋን የሰጠ አምላክን በዐይነ ሥጋ ለማየት ተመኝቶ “በመዋዕልየኑ ትፌኑ ወልደከ ወሚመ ታርእየኒ ኪያሃ ዕለተ” (ልጅኽን በዘመኔ ትልከዋለኽ? ወይንስ ዕለቷን ታሳየኛለኽ) አለው፤ ጌታም “አኮ ዘአርእየከ ኪያሃ አላ አምሳሊሃ ዕድዎ ለዮርዳኖስ ወትረክቦ ለመልከ ጼዴቅ” (ያችንስ ዕለት የማሳይኽ አይደለም፤ ምሳሌዋን እንጂ፤ ዮርዳኖስን ተሻገር መልከ ጼዴቅን ታገኘዋለኽ) ብሎ ምሳሌውን ጠቆመው።
💚አብርሃምም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ሲኼድ ታላቅ ግርማ የነበረውን መልከ ጼዴቅን አይቶ ደነገጠ፤ መልከ ጼዴቅም አብርሃምን “አትፍራ፤ አንተን ወደ ዮርዳኖስ እንድትሻገር ያዘዘኽ እግዚአብሔር እኔን ኅብስተ አኰቴት ጽዋዐ በረከት ይዤ ወደ ዮርዳኖስ እንድመጣ ለአንተ እንድሰጥኽ አዝዞኝ” ነው፤ በማለት ከያዘው ኅብስትና ወይን ለአብርሃም ሰጥቶ ባርኮታል፤ አብርሃምም ከያዘው ኹሉ ዐሥራትን ሰጠው፡፡
💚ይኽ አብርሃምም በኋላ ዘመን አካላዊ ቃል ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሥጋውን ደሙን በኅብስት በወይን የሚሰጥ መኾኑን በማወቁ እጅጉን ተደስቷል፤ ጌታም ይኽቺን ታላቅ ሰዓት አብርሃም ለማየት እንደተመኘ ለአይሁድ “አባታችኍ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት ዐደረገ፤ አየም ደስም አለው” በማለት ነግሯቸዋል (ዮሐ ፰፥፶፮)፡፡
💚ሊቁ አባ ጊዮርጊስም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ለመጣ ለአብርሃም መልከ ጼዴቅ በመሶብ ከያዘው ከስንዴው ኅብስት በጽዋው ከያዘው ከወይኑ እንደሰጠው ኹሉ፤ ዘመኑ ሲፈጸም አካላዊ ቃል ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ተወልዶ፤ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማሕፀነ ዮርዳኖስ ለተወለድነው ክርስቲያኖች፤ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በስንዴና በወይን አምሳል የሰጠን መኾኑን በእንዚራ ስብሐት መጽሐፉ ላይ፡-
"መካነ ሞጻሕቱ አንቲ ለመልከ ጼዴቅ በኅብስተ ሥርናይ ወወይን ዘከሠተ ምሥጢረ ጽድቅ" (በወይንና በስንዴ የእውነትን ምስጢር የገለጠ የመልከ ጼዴቅ የመሠዊያ ቦታ አንቺ ነሽ) በማለት ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ተወልዶ ቅዱስ ሥጋውን በአምሳለ ኅብስት የሰጠ ምግበ ርኁባን፤ ክቡር ደሙን በአርአያ ወይን የሰጠ ስቴ ጽሙኣን፤ አማናዊ ካህን ኢየሱስ ክርስቶስን ያገኘንባት መኾኗን መስክሯል።
💚በተመሳሳይ መልኩ ሊቁ በነገረ ማርያም ላይ፦ "ወአጸደ ወይን ዘጽድቅ ዘሐንበበቶ ለአስካለ መለኮት ዘርእየ አምሳሊሁ መልከ ጼዴቅ አመ አውጽሐ በኅብስተ ሥርናይ ወበደመ ወይን" (መልከ ጼዴቅ በስንዴ ኅብስትና በወይን ደም ባስታኮተ ጊዜ፤ ምሳሌውን ያየው የመለኮት ፍሬን ያፈራቺው እውነተኛ የወይን ቦታ ርሷ ናት) በማለት ያመሰጥራል።
💚ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ጌታን ከመልከ ጼዴቅ ጋር አነጻጽሮ ቢጠቅስም መልከ ጼዴቅ ግን ምሳሌ ብቻ እንደኾነ ሳይጠቅስ አላለፈም፤ ይኸውም በዕብራውያን ክታቡ ምዕ ፯፥፩-፫ ላይ፦
“የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን የኾነ ይኽ መልከ ጼዴቅ አብርሃም ነገሥታትን ገድሎ ሲመለስ ከርሱ ጋር ተገናኝቶ ባረከው፤ ለርሱም ደግሞ አብርሃም ከኹሉ ዐሥራትን አካፈለው የስሙም ትርጓሜ በመዠመሪያ የጽድቅ ንጉሥ ነው፥ ኋላም ደግሞ የሳሌም ንጉሥ ማለት የሰላም ንጉሥ ነው፤ አባትና እናት የትውልድም ቍጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት ለሕይወቱም ፍጻሜ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ኾኖ ይኖራል” ይለዋል፡፡
✢✥❖ #ይቀጥላል ❖✥✢
4 374
4 374
4 374
4 374
🌾✞ #ጳጉሜ ✞🌾
☞✞ ጳጉሜ ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ዮሐንስ ጳጉሜ ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ / Thirty months of sunshine / በመባል ትታወቃች፡፡ ጳጉሜ በዘመነ ዮሐንስ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት / የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡
☞✞በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዋኑ ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፡2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋ በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡
☞✞ ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት። ዮዲ 8፡2፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡ ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡
☞✞ የጳጉሜ ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው፡፡ ይህም ጳጉሜ የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነው፡፡
☞✞ ክርስቲያኖች ሁሉ በየዓመቱ በጳጉሜ ወር ሁሉም ተሰብስበው ከሌሊት ጀምረው በቤተክርስቲያን ተገኝተው ጸበል ይጠመቃሉ፡፡ ይህንን የምናደገውም እግዚአብሔር የተባረከ ዓመት እንዲሰጠን፣ ባሳለፍነው ዓመት የሰራነውን ኃጢአት ይቅር እንዲለን ነው፡፡ የምንጠመቀውም ንስሐ ገብተን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ስም የተቀደሰው ጸበል ደግሞ ከበሽታችን ያድነናል፣ የተቀደስንም ያደርገናል፣ መጪውንም ህይወታችን የተባረከ ያደርግልናል፡፡
❀✿ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✿❀
መልካም የአዲስ ዓመት ዋዜማ (ጷጉሜ) ይሁንልን፡፡
✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው✞
╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮
@EOTC2921
╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯
4 374
⛺️✝ በኢትዮጵያ የተሰወሩ ፒራሚዶች ያሉበት ቦታ ታወቀ !
📌 እነዚህ ፒራሚዶች እና ቤተ መቅደሶች የሚገለጡበት ዘመን ታወቀ
📌 እውነት በኢትዮጵያ መሬት በሰማያዊ ሀይል ተቀብረው የሚገኙ ፒራሚዶች እና ቤተ መቅደሶች አሉ ? እንዴትስ ተሰሩ ?
📌 ስለ እነዚህ ፒራሚዶችና ቤተመቅደሶች አስገራሚ ምስጢሮች
📌 በቅዱሳን አባቶቻችን ስለተሰወረው ድንቅ መፅሐፍ
እነዚህን እና ሌሎች ሚስጢራትን ስለ ኢትዮጵያ ስውር ቤተ መቅደሶች እንዲሁም ፒራሚዶች ማወቅ ከፈለጉ በ Youtube ቻናላችን ሙሉ ትምህርቱን ማግኘት ትችላላቹ ከስር ያለውን Open የሚለውን ተጭነው ! እንዲሁም ሌሎች ድንቅ ፕሮግራሞችንም ማግኘት ይችላሉ በዛውም የ Youtube ቻናላችንንም Subscribe ያርጉ !
👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇👇 👇
ይህን ይጫኑት ... ይህን ይጫኑት
.
❎█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN ▒▓█❎