es
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Ir al canal en Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Mostrar más
4 374
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
🌾✞ ከዚህም በኋላ ጌታችን ወደ አባታችን መጥቶ ከባሕሩ ዳር በመቆም ‹‹ወዳጄ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! መላ ኢትዮጵያን ምሬልሃለሁና ተነሥ ከባሕሩ ውጣ›› አላቸው፡፡ አባታችንም አጥንታቸው እንደመርፌ ቀዳዳ ተበሳስቶ ፈጽመው ደክመው ነበርና ጌታችን በክቡራን እጆቹ ሁለንተናቸውን ቢዳስሳቸው እንደቀድሞው ደህና ሆኑ። ጌታችንም ከባረካቸው በኋላ ወደ ምድረ ከብድ እንዲሄዱ ነገራቸው፡፡ ↪️አባታችን ምድረ ከብድ እንደደረሱ እንደ ዓምድ ተተክለው ሰባት ዓመት ቆመው ጸለዩ፡፡ በዚህም ጊዜ ሰይጣን በቁራ ተመስሎ ሁለት ዐይኖቻቸውን አንቁሮ አጠፋቸው ነገር ግን አባታችን ሳያቋርጡ ሁለት ሳምንት በጸሎት ቆዩ። ከዚያም ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው በዐይኖቻቸው ላይ እፍ ብለው ብርሃናቸውን ከመለሱላቸው በኋላ አባታችንን ‹‹ከሰማይ ፍጹም ኃይል ይሰጥሃልና ጠላቶችህን ትበቀል ዘንድ ወደ ዝቋላ ሂድ›› ብለዋቸው ዐረጉ፡፡ 🌾✞ አባታችንም እንደታዘዙት ወደ ዝቋላ እየሄዱ ሳለ በመንገድ ላይ ከዛፍ ሥር ያረፉ ሦስት ሽማግሌዎችን አገኙ። ባዩአቸው ጊዜም ለመሰወር ቢያስቡም ሽማግሌዎቹ ግን ይመጡ ዘንድ ጠሯቸውና ‹‹በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጽነናል ሦስታችንንም በጀርባህ አዝለህ አንድ አንድ ምዕራፍ ሸኘን›› አሏቸው፡፡ አባታችንም ሽማግሌዎቹን በቀረቧቸው ሰዓት ሽበት የከበባቸው የደከሙ ሽማግሌዎች ሆነው አገኟቸው፡፡ ↪️ከዚህም በኋላ አባታችን አንደኛውን ሽማግሌ አዝለው ከአንድ ምዕራፍ አደረሷቸው፡፡ ያም ሽማግሌ ‹‹ከዚህ አሳርፈኝ፣ አንተ ደክመሃል የማትበላ የማትጠጣ ነህና›› አሏቸው፡፡ አባታችንም ‹‹አባ የት ያውቁኛል?› አሏቸው። ሽማግሌውም ‹‹አሁን ደግሞ ሄደህ ጓደኞቼን አምጣልኝ›› አሏቸው። አባታችንም የቀሩት ሁለቱ ሽማግሌዎች ካሉበት ደርሰው ሁለቱንም በየተራ እያዘሉ የመጀመሪያውን ካደረሱበት ቦታ አደረሷቸው፡፡ ከዚህም በኋላ እነዚያን ሽማግሌዎች ‹‹አባቶቼ ሆይ! ከየት ነው የመጣችሁት?›› አሏቸው፡፡ ሦስቱም ሰዎች ተነሥተው ቆሙና ለአባታችን በአንድነት በሦስትነት ተገለጡላቸው። አንድ ሲሆኑ ሦስት ሦስት ሲሆኑ አንድ ሆኑ፡፡ ሥሉስ ቅዱስ ለአብርሃም በመምሬ አድባር ሥር በአንድነት በሦስትነት እንደተገለጡለት ለአባታችንም ተገለጡላቸው፡፡ በጀርባቸውም አዘሏቸው፡፡ 🌾✞ የእግዚአብሔርንም ክብር ስላዩ አባታችን ፊታቸው እንደፀሐይ አበራ። ቅዱሳን መላእክት ወርደው እንደሻሽ ተነጥፈው ሲያመሰግኑ ሰማይና ምድር ተነዋውጠው ተራሮች ኮረብቶች ዓለቶች ተሰነጣጠቁ፡፡ በዚያችም ሰዓት ታላቅ ፍርሃት ሆነ፡፡ አባታችንም ዙሪያቸውን በከበባቸው በምሥጢራት ጎርፍ ተውጠው ተንቀጥቅጠው በግንባራቸው ወደቁና እንደ በድን ሆኑ፡፡ በራእይ ውስጥም ሆነው እነዚያ ሽማግሌዎች አባታችንን እስከ ሰባተኛው ሰማይ እንዳደረሷቸው ተመለከቱ፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን እንደ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደቀሰቀሳቸው አባታችንንም ቀሰቀሷቸውና ‹‹ወደ ዝቋላ ውረድ መቶ ዓመት ሙሉ አጥንትህን ሥጋህን እየነደፉ የተዋጉህን አጋንንት ታጠፋቸው ዘንድ። እነሆ እኔ እንደወሰድኩህ ባለማወቃቸው በትዕቢት ላይ ናቸውና ‹በባሕር ውስጥ አለ› ይሉሃል፡፡ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ይረዱሃል፤ መባርቅትም በፊት በኋላ ይከተሉሃል›› አላቸው፡፡ 🌾✞ ያንጊዜም አባታችን በመብረቅ ላይ ሆነው እነዚያ አጋንንት ወዳሉበት ወረዱ፡፡ አጋንንቱንም ደመናት ከበቡአቸው፣ መላእክትም በእሳት ሰይፍ መተሩአቸው፣ በመብረቅ አጨዷቸው፤ አመድ ሆነው በነፋስ በተኗቸው፡፡ የእነዚያም አጋንንት ቁጥራቸው ሰባ ሺህ እልፍ ከአንድ ሺህ ነበር፡፡ ሁሉም በአንድ ጊዜ አልቀዋልና ከእነርሱ ሸሽቶ ያመለጠም አልነበረም። ሰባቱ ሊቃነ መላእክትም ወደ ሰማይ ዐረጉ፡፡ አባታችንም አንበሶችና ነብሮች፣ ድብና ዘንዶ ወዳሉበት ምድረ ከብድ ተመለሱ፡፡ አባታችንም ወደ ምድረ ከብድ ከተመለሱ በኋላ መንፈስ ቅዱስ የጠራቸው ሦስት ቅዱሳን ሁሉም በየአንበሶቻቸው ላይ ተቀምጠው ወደ ምድረ ከብድ መጡ፡፡ እነዚህም ቅዱሳን የዋልድባው አቡነ ሳሙኤል፣ የአዘሎው አቡነ አንበስ እና ከላዕላይ ግብፅ ተነሥቶ የመጣው አቡነ ብንያም ናቸው፡፡ ነገር ግን አባታችን እነዚህን ቅዱሳን ስለተሰወሯቸው ቅዱሳኑ እስከ ሰባት ቀን ድረስ በምህላ ሰነበቱ፡፡ የአባታችን የሚያስፈሩ አንበሶች ወጥተው የቅዱሳኑን አንበሶቻቸውን ገድለው ደማቸውን አፍስሰው ሥጋቸውን በሉ፡፡ ሦስቱም ቅዱሳን በዚህ ፈጽመው ደንግጠው ሳለ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ 60 ነብሮችንና 60 አንበሶችን አስከትለው ተገለጡላቸውና ‹‹ሰላም ለእናንተ ይሁን የእግዚአብሔር ቅዱሳኑ አትፍሩ›› አሏቸው፡፡ ቅዱሳኑም ‹‹አባታችን ሆይ! ጸሎትህ ቅድስት እንደሆነች ባወቅን ጊዜ በእግዚአብሔር ፈቃድ እንባረክ ዘንድ ወደ አንተ መጣን፡፡ ነገር ግን ባላገኘንህ ጊዜ እስከ ሰባት ቀን አለቀስን›› አሏቸው፡፡ ዳግመኛም ‹‹የእርስዎም አንበሶች መጥተው አንበሶቻችንን በሉብን›› አሏቸው፡፡ አባታችንም አንበሶቻቸውን ‹‹እስከ ዕለተ ሞቴ ድረስ በእግሬ ከረገጥኩት ምድር በቀር እግዚአብሔር ያላዘዛችሁን ለምን በላችሁ? አሁንም የበላችሁትን ትፉ›› አሏቸው፡፡ እነዚያም አንበሶች አፋቸውን ከፈቱና የበሉትን የአንበሶቹን ሥጋቸውን አጥንታቸውን ከደም ጋር ተፉ፤ በሆዳቸውም የቀረ የለም፡፡ 🌾✞ አባታችንም ወደ ምሥራቅ ዞረው እግዚአብሔር ካመሰገኑ በኋላ ‹‹አቤቱ አልዓዛርን ያስነሣኸው አንተ ነህና አሁንም እነዚህን አናብስት ከሞት አስነሣቸው፤ ለባሮችህም የድካማቸውን ማረፊያ ይሆኑላቸው ዘንድ የሰጠሃቸውን አትከልክላቸው…›› እያሉ ጸለዩ፡፡ አባታችን እንዲህ ብለው ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ የአንበሶቹን ሥጋቸውን በመስቀል ምልክት ባርከው ‹‹በጌታዬ በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ተነሡ›› አሏቸው፡፡ አንበሶቹም እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥነው ተነሡና እንደቀድሞው ሆኑ፡፡ ለአባታችንም እጅ ነሥተውና ሰግደው የእግሩን ትቢያ ላሱ፡፡ አባታችንም ወደጌቶቻቸው መለሳቸው፡፡ እነዚህም ሦስቱ ቅዱሳን በአባታችን ላይ አድሮ ድንቅ ነገርን የሚሠራ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ 🌾✞ የዋልድባው አቡነ ሳሙኤልም አባታችንን ‹‹አባት ሆይ በዚህች ቀን ድንቅ ሥራን አየን፣ አርአያህ የእግዚአብሔርን መልአክ አርአያ ይመስላል፣ ቅድስናህ ፍጹም ነው፣ የጸሎትህ ኃይል ሙታንን ያስነሣል፣ የተበሉ አንበሶችን ከአንበሶች ሆድ አወጣህ›› አሏቸው፡፡ ዳግመኛም አባታችን ስለ ቅዱሳኑ ምግብ ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ በእጁ ሦስት ኅብስትና ሦስት ጽዋ ይዞ መጣ፡፡ አባታችንም ሦስቱን ቅዱሳን ‹‹እግዚአብሔር የሰጣችሁን ይህንን ኅብስትና ጽዋ ንሡ ብሉ ጠጡ›› አሏቸው፡፡ ቅዱሳኑም ሥራቸውን እያደነቁ በልተው ጠጥተው ጠገቡ፡፡ በማግሥቱም አባታችን ቅዱሳኑን ‹‹በሰላም ሂዱ›› ብለው መርቀው ሸኟቸው፤ የእግዚአብሔር ሥራ እያደነቁ ወደየበዓታቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡ 🌾✞ ከዚህም በኋላ ለአባታችን ጌታችን ተገልጦ ብዙ ምሥጢራትን ከነገራቸው በኋላ ወደ አረማውያን አገር ሄደው እንዲያስተምሩና የሚደርስባቸውንም መከራጭምር ነገራቸው፡፡ አባታችንም ክርስቶስን ፈጽመው ወደማያውቁት ዐረብ አገራት ሄዱ፡፡ የዐረብ ንጉሥም ብዙ ሠራዊቱን አስከትሎ ጣዖትን አሲዞ ሲጓዝ አገኙት፡፡ በጣዖታቱ ውስጥ አድረው የነበሩ አጋንንትም አባታችንን ባዩ ጊዜ ወጥተው ሸሹ፣ ጣዖታቱም ከምድር ላይ ወድቀው ተሰባበሩ፡፡ የዐረቡም ንጉሥ ‹‹አንተ ፀጉር ልብሱ ምንድነህ? ሰው ነህን?› አሏቸው። ይ🀄️ጥላል

🌾✞ ከዚህም በኋላ አባታችን ወደ ጫካ ገብተው ብቻቸውን የበጋውን ሐሩር የክረምቱን ቁር ታግሰው ምንም ልብስ ሳይለብሱ ራቁታቸውን ሆነው በተጋድሎ ኖሩ፡፡ ከጽኑው ተጋድሎአቸውና ከጫካው ቅዝቃዜ የተነሣ ሰውነታቸው አልቆ ከአጥንታቸው ጋር ተጣበቀ፡፡ ፍራፍሬም ሆነ ምንም ነገር አይመገቡም ውኃም ፈጽሞ አይጠጡም ነበር፡፡ አባታችን በምድረ በዳ እንደሰው ሳይሆን እንደመላእክት ኖሩ፡፡ ቅዱሳን መልእክትም ዘወትር ይጎበኟቸው ነበር፤ ስለምግባቸውም ሰማያዊ ኅብስት አምጥተው ይሰጧቸዋል፤ ነገር ግን አባታችን ያንን ኅብስት አይመገቡትም ይልቁንም ጽዋውን ባሸተቱት ጊዜ እንዲሁ ይጠግባሉ ይረካሉ፡፡ ነቢይ ክብርህን በማየቴ እጠግባለሁ እንዳለ። አባታችን በተወለዱበትም ቤት አልኖሩምና እናት አባታቸው የሥጋ ዘመዶቻቸውም አላወቋቸውም በበረሃ ብቻቸውን ኖሩ እንጂ፡፡ ነገር ግን ሰማያውያን ሁሉ ወዳጆቻቸው ሆኑ፤ እመቤታችን ወዳጄ ትላቸዋለች፡፡ ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ወገናችን ይሏቸዋል። መላእክትም ወዳጃችን እያሉ በክንፋቸው ያቅፏቸዋል። የአባታችን መዓዛቸው ጫካውን ይሞላው ነበር፡፡ በመንፈስ ቅዱስም ኃይል ወደፈለጉት ቦታ በፍጥነት እንደወፍ ይበራሉ፡፡ ስለተሰጣቸውም ጸጋ የበረሃ እንስሳት ሁሉ ያገለግሏቸዋል፡፡ 🌾✞ አባታችን ሁልጊዜ እንዲህ ይሉ ነበር፡- ‹‹የሚጣፍጥ ምግብን መውደድ ኃጢአትን ያመጣል፣ ሞትን ያስከትላል፡፡ ክንፍ ያላቸው የሰማይ ወፎች እንኳን በመብል ምክንያት ይጠመዳሉ፣ ምግብ በመሻት ከምድር ላይ ይወድቃሉ በወጥመድም ይያዛሉ፡፡ የሰው ልጅም ምግብን በመውደድ በኃጢአት ይወድቃልና እኔስ ለሰውነቴ ምግብ መጠጥን አልፈልግም፤ ልብስም አልሻም ዕራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን እንደወጣሁ እንዲሁ ዕረቁቴን ወደ መቃብር እመለሳለሁ እንጂ፡፡ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም በሞት በተለየሁ ጊዜ መብል መጠጥንና ልብስን ማን ያስከትልልኛል?›› አሉ፡፡ ዳግመኛም ‹‹ሰው ሊደርስ በማይችልበት በረሃ እኖራለሁ፣ ነጣቂ ተኩላዎችና አራዊቶች ባሉበት እነርሱ እንዲበሉኝ ሥጋዬን እጥላለሁ፤ ዳዊት በመዝሙር ‹የጻድቃን ሥጋቸው ለዱር አራዊት ነው› እንዳለ እኔ ክፉ አውሬዎች፣ ተናዳፊ እባቦችና ዘንዶዎች ወዳሉበት እገባለሁ ምግብም እሆናቸው ዘንድ እወዳለሁ›› በማለት አባታችን ራሳቸውን ለሞት አሳልፈው ይሰጡ ነበር ነገር ግን አራዊቱ ሁሉ ይገዙላቸው ከእግራቸውም በታች ይተኙ ነበር። ለጸሎትም በሚቆሙበት ጊዜ አብረዋቸው ይቆማሉ፤ ይጫወታሉም፡፡ 🌾✞ በአንደኛው ዕለት አባታችን ጸሎታቸውን እንደጨረሱ ሰማይ ተከፍቶ የእሳት ድንኳን ተገልጦ አርባእቱ እንስሳ የእግዚአብሔርን ዙፋን ተሸክመው 24ቱ ካህናተ ሰማይ ማዕጠንት ይዘው፣ ቅዱሳን መላእክትና አለቆቻቸው በየነገዳቸው በዙሪያው ቆመው ጌታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአንድነት በሦስትነት እንዳለ ተገለጠላቸው። አባታችንም ይህንን ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተውና ደግጠው መሬት ላይ ወደቁ፡፡ ጌታችንም ካጸናቸውና ካበረቻው በኋላ ‹‹ዮሐንስ ቀለምሲስ እኔን እንዳየኝ አንተም እኔን ማየት የምትችልበትን ኃይል እሰጥሃለሁ፤ ወዳጄ ሆይ ምን ትሻለህ? የምትጠይቀኝስ ነገር ምንድነው? ልይህ ብለህ በለመንከኝ ጊዜ ተገልጥኩልህ፡፡ ሰማንያ ዓመት በጫካ ኖርክ፣ በረሃዎችን ዞርክ፣ ከአንበሶችና ነብሮች ከአራዊትም ጋር መኖርን አልፈራህም ጨክነህ እስከ ሞት ድረስ ታገስህ፡፡ የመረጥኩህ ወዳጄ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ምን አደርግልህ ዘንድ ትወዳለህ?›› አላቸው፡፡ 🌾✞ አባታችንም ይህንን ቃል ከጌታችን ሲሰሙ ‹‹አምላኬ ሆይ ይህን ልታደርግልኝ አይገባኝም፡፡ በፊትህስ ሞገስን ካገኘሁ የገቦታን ሰዎች ማርልኝ እነርሱ ኃጥአን ናቸውና አንተ ንስሓን ለማይሹ ጻድቃን አልመጣህምና ኃጥአንን ወደ ንስሓ ልትመልስ ነው እንጂ›› አሉት፡፡ ዳግመኛም ‹‹አቤቱ እንደ ክረምት ውኃ እንባቸውን እያፈሰሱ ጥርሳቸውን እያፋጩ በደይን የሚኖሩትን አስባቸው ሰይጣን አስቷቸዋልና በማወቅ ባለማወቅ በሠሩት ማራቸው፣ ይቅር በላቸው›› እያሉ ለመኑት። ጌታችንም ‹‹ወዳጄ ሆይ የለመንከኝን አልከለክልህም፣ እንደቸርነቴም ስምህን የጠሩትን መታሰቢያህን ያደረጉትን ኃጥአንን ምሬልሃለሁ፤ የለመንከኝንም ሁሉ አደርግልህ ዘንድ ኪዳንን ሰጥቼሃለሁ›› አላቸው፡፡ አባታችንም እጅግ ደስ ብሏቸው በግንባራቸው መሬት ላይ ወድቀው ጌታችንን ሲያመሰግኑት ቅዱሳን መላአክትና ሰማያውያን ቅዱሳን ሁሉም አብረው ተደስተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ 🌾✞ አባታችንም ይህንን ቃልኪዳን ሲቀበሉ ዕድሜዓቸው 300 ዓመት ነበር፡፡ ጌታችንም የመላእክት አለቆችን ‹‹ስለ ወዳጄ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ምልጃ ወደ ገሃነም ሂዱና የኃጥአንን ነፍስ አውጡ፣ ከእስራታቸውም ፍቱአቸው›› አላቸውና እነርሱም የገቦታ ሰዎችን ሦስት ሺህ ነፍሳት ከደይን አውጥተው ወደ ገነት አገቧቸው፡፡ ዳግመኛም እግዚአብሔር አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ‹‹እንደ አንተ ካሉት ሰዎች በቀር በዓለም ያሉ ሰዎች እንዳያውቁህ አደርጋለሁ፤ መላእክት ይጎበኙሃል እንጂ ከካህናት ከመነኮሳት ከምእመናንም ወገን ቢሆን ምንም ያለ ፈቃድህ አያይህም፡፡ ወደጄ ሆይ እንደ ወደድህም እኔን አባቴንና መንፈስ ቅዱስን በሦስትነቴ አየኸኝ፡፡ አሁንም ወደ ኢትዮጵያ ሂድ በዚያም ከደይን የምታወጣቸው ነፍሳት አሉ›› አላቸው፡፡ አባታችንም ‹‹አምላኬ ሆይ ወደዚያች አገር ማን ያደርሰኛል?›› አሉት፡፡ እግዚአብሔርም ‹‹እኔ በሥልጣኔ አደርስሃለሁ›› ካላቸው በኋላ ከእርሳቸው ተሰወረ፡፡ አባታችንም የገቦታ ሰዎች ምሕረትን ሲያገኙ አይተው እጅግ ተደሰቱ፡፡ በሌላም ጊዜ አባታችን አራት ሺህ እልፍ እየሰገዱ፣ 300 ጊዜ የቀኝ 300 ጊዜ ደግሞ የግራ ፊታቸውን በድንጋይ እየመቱ፣ መዝሙረ ዳዊትን እየደገሙ፣ 15ቱን መኅልየ ነቢያት፣ መኅልየ ሰሎሞንንና ውዳሴ ማርያም እየጸለዩ ለኃጥአን ምሕረትን ሲለምኑ ዕንባቸው እንደ ውኃ ይፈስ ነበር፡፡ ጌታችንም ‹‹በተወለድሁባት፣ በተጠመቅሁባትና ከሞት በተነሣሁባት ዕለት እልፍ እልፍ ነፍሳትን እምርልሃለሁ›› አላቸው፡፡ 🌾✞ ከዚህም በኋላ አባታችን ስድሳ አንበሶችና ስድሳ ነብሮች እየተከተሏቸው ወደ አገራችን ኢትዮጵያ መጡ። ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤልም ከተከታዮቻቸው ጋር በነፋስ ሠረገላ ጭኖ ምድረ ከብድ አደረሳቸው፡፡ ዳግመኛም ‹‹ደብር ቅዱስ›› ወደሚባለው ወደ ዝቋላ ወሰዳቸው፡፡ አባታችንም በውኃው ዳር ቆመው ምሥራቁን፣ ምዕራቡን፣ ሰሜኑን፣ ደቡቡን በተመለከቱ ጊዜ የኢትዮጵያ ሰዎች ኃጢአታቸው በፊታቸው የተገለጠ ሆነ፡፡ ሰው ፊቱን በመሥታወት እንደሚያይ የኃጥአንም ሥራቸው በአባታችን ፊት እንዲሁ የተገለጠ ነውና፡፡ አባታችንም የኢትዮጵያን ሰዎች ኃጢአታቸውን በግልጽ በተመለከቱ ጊዜ ተወርውረው ወደ ባሕሩ በመግባት ተዘቅዝቀው መጸለይ ጀመሩ፡፡ ‹‹ከባሕር እንዳልወጣ፣ በእግሬም እንዳልቆም በሕያው ስምህ ምያለሁ›› ብለው አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ቆዩ፡፡ በ40ኛ ቀናቸው የታዘዘ መልአክ መጥቶ ‹‹ስምህን የጠራ መታሰቢያህን ያደረገውን እምርልሃለሁ ብሎሃል›› አላቸው፡፡ አባታችንም መልአኩን ‹‹መላ ኢትዮጵያን ካልማረ ከዚህ ባሕር አልወጣም›› አሉት፡፡ መልአኩም ከእሳቸው ተለይቶ ከሄደ በኋላ አባታችን በዚያ ባሕር ውስጥ መቶ ዓመት ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖሩ፡፡ አባታችንም በባሕሩ ውስጥ ተዘቅዝቀው መቶ ዓመት ሲጸልዩ ከኖሩ በኋላ ደማቸው ፈሶ አለቀና ውኃው ደም መሰለ፡፡ ሥጋቸውም አልቆ አጥንቶቻቸው እንደበረዶ ሆኑ፡፡ ሰባት ሺህ እልፍ ሦስት መቶ የሚሆኑ አጋንንትም ከአራቱም አቅጣጫ እየመጡ ሰውነታቸውን በፍላፃዎቻቸው ይወጓቸው ነበር። ይ🀄️ጥላል

✞✞✞ #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ✞✞✞ ✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✞ https://t.me/EOTC2921 🌹ጥቅምት 5🌹 🌾✞ኑሮአቸው እንደሰው ያይደለ በምድረ በዳ እንደ መላእክት የኖሩትና በዝቋላ ተራራ ባለው ባሕር ውስጥ 100 ዓመት ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ሰዎች ምሕረትን የለመኑት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታላቅ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ነው፡፡ #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ከደቡባዊ ግብፅ ከቆላው አገር ከንሒሳ የተገኙ ገዳማዊ ናቸው፡፡ አባታቸው ስምዖን ከነገደ ብንያም ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ ወላጆቻቸው በእግዚአብሔር ፊት ደጋጎች የነበሩ ቢሆኑም አቅሌስያ መካን ሆና ሆና ልጅ በማጣቷ እያለቀሰች 30 ዘመን ኖራለች፡፡ 🌾✞ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ሥዕል ካለበት ፊት ለፊት በመቆም እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣት ዘንድ አልቅሳ ስትለምን ያን ጊዜ ከሥዕሉ ቃል ወጥቶ ‹‹ሥልጣኑ ከሰማይ ከፍታ ከፍ የሚል ንጽሕናው ከሚካኤል ከገብርኤል የሚተካከል ክህነቱ እንደ መልከጼዴቅ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ እንደ ነቢይ ኤልያስ የሆነ ልጅ እንቺ ተቀበይ›› አላት፡፡ አቅሌስያም በመጋቢት 29 ቀን ፀንሳ በታኅሣሥ 29 ቀን ደም ግባቱ እጅግ የሚያምር ወንድ ልጅ እንደወለደች መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰው አምሳል መጥቶ ‹‹የዚህ ልጅሽ ስሙ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ይሁን›› አላት፡፡ ወዲያውም ሕፃኑ ተነሥቶ ከእናቱ ጭን ወርዶ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሦስት ጊዜ ሰገደ፡፡ ዳግመኛም ‹‹ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጣኸኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን›› አለ፡፡ እግዚአብሔር ነቢዩ ኤርሚያስን ‹‹በእናትህ ማኅፀን ቀደስኩህ ከማኅፀን ሳትወጣም የተመረጠ አደረግሁህ›› እንዳለው ገብረ መንፈስ ቅዱስንም ከእናቱ ማኅፀን መርጦታልና የበልአምን አህያ ያናገረ የቢታንያ ድንጋዮችንም አንደበት ሰጥቶ ስሙን እንዲያመሰግኑት ያደረገ አምላክ አሁንም ይህንን ሕፃን አንደበቱን ከፍቶለት ስሙን እንዲያመሰግን አደረገው፡፡ ኤር.1፥1፣ ዘኁ.22፥21-33፣ ሉቃ.19፥40፡፡ 🌾✞ ከዚህም በኋላ ይህ ሕፃን በተወለደ ጊዜ ለአምላኩ ሰግዶ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ካመሰገነ በኋላ እናቱ አላቀፈችውም፣ ጡቷንም አልጠባም። ከዚያ የነበሩ ሁሉ ይህንን በማየታቸው እጅግ ተደንቀው አምላካቸውን አመሰገኑ። ከ3 ዓመት በኋላም እግዚአብሔር መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን እንዲህ ብሎ አዘዘው፡ ‹‹ሕፃኑን ከእናቱ ክንድ ተቀበል፣ ብዙ ገዳማውያን ወዳሉበት ገዳም ውሰድና ከበራቸው አስቀምጠው፣ አበ ምኔቱንም ሕፃኑን ከበር አንሥተህ ካንተ ዘንድ አኑረው ስለ ልብሱ ስለ ምግቡ አታስብ ሕፃኑ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ነውና ምግቡም መንፈሳዊ ነው ይኸውም ከእግዚአብሔር የሚወጣ ቃል ነው፣ ሰው በእንጀራ ብቻ እንደማይኖር ዕወቅ በለው›› በማለት አዘዘው፡፡ 🌾✞ ብርሃናዊው መልአክ የራማው ልዑል ቅዱስ ገብርኤልም እንደታዘዘው ከሰማይ ወርዶ ሕፃኑን ከእናቱ ክንድ ወስዶ በክንፎቹ አቅፎ ስሞ እስከ ሰባቱ ሰማይ አውጥቶ በሥሉስ ቅዱስ ፊት አቅርቦት አስባረከው፡፡ እግዚአብሔርም መልአኩን ‹‹ወደ እናቴ ወደ ማርያም ውሰደውና ትባርከው›› አለውና ወስዶት እመቤታችንም ባረከችው፡፡ ዳግመኛም ከአዳም ጀምሮ ሄሮድስ በግፍ እስካስፈጃቸው ሕፃናት ያሉት ሁሉም ቅዱሳን ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ደናግልና መነኮሳት ሁሉም እንዲባርኩት አደረገው መልሶ ከእግዚአብሔር ፊት አቆመው፡፡ መድኅን ጌታም ሕፃን ገብረ መንፈስ ቅዱስን ‹‹በመንግሥቴ ከእኔ ጋር ትነግሣለህና ደስ ይበልህ፣ በርታ የሚደርስብህን ሁሉ ታገሥ ብዙ ነፍሳት በአንተ ምክንያት ይድናሉ፣ ሰላሜ ከአንተ ጋር ይሆናል›› አለው፡፡ ከዚህም በኋላ መልአኩ አባ ዘመደ ብርሃን ወዳለበት ገዳም አወረደውና ሕፃኑን ከበር ላይ አስቀምጦ እርሱ ወደ ውስጥ ገብቶ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉን ነገረው፡፡ አባ ዘመደ ብርሃንም ሕፃኑን አስገብቶ በእንክብካቤ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ እያስተማረ አሳደገው፡፡ ሕፃኑም ትምህርቱን በጨረሰ ጊዜ ዲቁና ተቀብሎ እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ሞገስን የተመላ ሆነ፡፡ ፍጹም የእግዚአብሔር ጸጋ አድሮበታልና ሥራው ሁሉ በዕውቀት የተመላና የተቃና ሆነ፡፡ አባ ዘመድ ብርሃንም በሕፃኑ ላይ ያደረበትን ጸጋ እያየ እጅግ ደስ ይለው ስለነበር እንደ ቅዱስ እንጦንስ አስኬማን ሰጠው፡፡ 🌾✞ ከዚህም በኋላ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቅስናን ተቀበሉና በጾም በጸሎት ተጠምደው በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ እንደ ሐዋርያትም የተአምራትና የፈውስ ሀብት ተሰጣቸውና ድውያንን የሚፈውሱ፣ ሙታንን የሚያነሡ፣ አጋንንትን የሚያወጡ ሆኑ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዳግመኛ ተገልጦላቸው ወደ ሰማይ አሳረጋቸውና ከእግዚአብሔር ፊት አቆማቸው፡፡ ያን ጊዜም ጌታችን ክቡራን የሆኑ እጆቹን ዘርግቶ ከባረካቸው በኋላ ‹‹በጸሎትህ ከሲኦል የምታወጣቸው ብዙ ነፍሳት አሉ፤ ድውያንንም ትፈውሳለህ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ገብተህ ከአንበሶችና ከነብሮች ጋር ኑር›› አላቸው፡፡ አባታችንም ጌታችንን ‹‹የሰጠኸኝ እነዚህ አንበሶችና ነብሮች ምን ይመገባሉ?›› አሉት፡፡ ጌታችንም ‹‹የረገጥከውን መሬት ይልሳሉ በዚያም ይጠግባሉ፡፡ ወደ እኔም እስክትመጣ ድረስ ይኸው ምግብ ይሆናቸዋል›› አላቸው፡፡ ቅዱሳን መላእክትም ይህንን በሰሙ ጊዜ ደስ አላቸው፡፡ ጌታችንም መልአኩን ወደ ቀደመ ቦታቸው ይመልሳቸው ዘንድ አዘዘው፡፡ 🌾✞ ከዚህ በኋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከራሳቸው እስከ እግራቸው ድረስ ጠጉር በቀለላቸው። የጠጉራቸውም ርዝመቱ አንድ ክንድ ከስንዝር ነው፡፡ አባታችንም በታላቅ ተጋድሎ ሲኖሩ በጸጋ ላይ ጸጋ ተጨመረላቸው፡፡ ከዕለታት በአንድዋ ቀን የፈወሳቸው ሕሙማን ብዛታቸው እልፍ ሆነ፡፡ የሀገሩ ሰዎችም ሥራቸውን ስላወቁባቸው አዘኑ፡፡ ‹‹ውዳሴ ከንቱ እንዳይሆንብኝ ተነሥቼ ሰው ወደማያውቀኝ አገር እሄዳለሁ›› ብለው ተነሥተው ሄዱ፡፡ሕዝቡም አባታችን እንደተሰወሩ ባወቁ ጊዜ በሀዘን ተላቀሱ። ይ🀄️ጥላል

በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng 👆👆👆 በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ   ! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng 👆👆👆 በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ   ! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng 👆👆👆 በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ   ! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng 👆👆👆 በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ   ! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng 👆👆👆 በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ   ! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng 👆👆👆 በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ   ! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

........... #ትዕዛዝ_ለቄሱ! .......... #እናንተ የተወደዳችሁ የቤተክርስትያን ታማኝ አገልጋይ ቀሳውስት ለእናንተ የሚመሆን "ትዕዛዝ ለቄሱ" የምትል ከግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የተገኘች ምክር እነሆ ተተርጉማ ቀርባለች እና በትዕግስት እና በማስተዋል አንብቧት! የእግዚአብሔር ፀጋ ይብዛላችሁ! ........... #ትዕዛዝ_ለቄሱ! .......... #እግዚአብሔርንና ፍጥረትን ሁሉ በፍፁም ልብህ እና በፍፁም ሀሳብህ አፍቅር! #ሰዎችን በጥሩ ምሳሌ እና በሚያፅናና ስብከት አስተምር! #የሀይማኖት መሰረት ከሆነው እና ክርስቲያኖች ከዳኑበት ከእውነተኛው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ካለ እምነት ውጪ አታፈንግጥ! #ጉባኤውን እንደ ተቀጣሪ ሳይሆን እንደ አባት ተንከባከብ! #የታማኝ መጋቢነትን ሽልማት ለማግኘት በእምነት የሆነ አገልግሎት ይኑርህ! #በስራህ ከሚጠፋውና ከሚሻግተው እንጀራህ ይልቅ የማይጠፋውን እና የዘላለም ህይወትን ለማብዛት ለሆነው አገልግሎት ትጋ! #በትህትና ፣ በቅድስና እና በፀጋ በማገልገል ለጉባኤህ ምሳሌ ሁኑ! #በፀጋ እና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሳታቋርጥ እደግ! #እራስህን የኃጢአት ሁሉ ምንጭ ከሆነው ገንዘብን ከማፍቀር አስመልጥ! #መጠጥ መጠጣት እና የስጋ ፈቃዶችን መፈፀም የህሊና ብርሃንን ያጨልምና ሰውን እንደ እንስሳ የምኞቱ ባርያ ስለሚያደርገው ከዚህ ተቆጠጥ! #ቅናት ፣ ፌዝ ፣ ጥላቻን ፣ ሁከት፣ ጠብ ፣ ክፋትን እና ኩራትን ከራስህ ላይ አስወግድ። በዚህም አገልግሎትህ ሳይባክን ዓላማውን ያሳካል! #ግብዝነት ፣ አሉባልታ፣ ወሬ ፣ ፉከራ እና ልታይ ልታይ ማለትን ፈፅመህ አስወግድ። እነዚህ የሚረብሹና ዘግናኝ ድምፆች ስለሆኑ መንፈስ ቅዱስን እና አማኞችን ያሸሻሉ! #በሁለት ገፅ እና ባለሁለት ምላስ ሆኖ በአስመሳይነት መቅረብን፤ እንዲሁም ለማሳመን የሚደረግ የሀሰት ምስክርነትን ፈፅመህ አስወግድ! #ሰዎችን የሚያስፈራና የሚያስጨንቅ አትሁን ነገር ግን ከዚያ ይልቅ ከሁሉ ጋር ተግባቢ እና ትዕግስተኛ ሁን! #እራስን በመቆጣጠር በፅድቅ፣ በምህረት ፣ በትህትና፣ በንፅህና ፣ በፍሬ፣ በመልካም ተፅእኖ፣ በትዕግስትና በፍቅር በእነዚህ በምግባርህ ቢሆን በስራህ ታላቁ መምህርህን ኢየሱስ ክርስቶስን ምሰል! #መፅሐፍ ቅዱስ ፣ የጥንት አባቶች ፅሁፎችን እንዲሁ ቤተክርስቲያን በሁሉም ዘርፍ ያላትን ቀኖናዊ ህጎች ለማጥናት ትጉ ሁን! #የእግዚአብሔርን ጉባኤ፡ በርህራሄ እና በጥበብ በመንከባከብ ወደ ክርስቶስ ደግነት ፣ ርህራሄና ብርታት እንዲያድጉ መምራት አለብህ! #በአክብሮት እና በእውነተኛ ምስክርነት የክርስትና አማኞችን በህይወታቸው ዋና ወደ ሆነው ፀጋ ወደ ፍቅር ማደግን አስተምራቸው። የትእዛዝ ፍጻሜ ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነውና። (1ጢሞ 1:5) #የቤተክርስትያን ምስጢራት ላይ ተጠንቀቁ። ቅዱስ ቁርባን (የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ የሆነ ስጋ እና ደም) እና ሌሎቹን የከበሩ ሀብቶች በገነት እንዳለች ወደ ህይወት ዛፍ እንደምትወስድ መንገድ እያቸው! (ዘፍ 3:24) #ቅዱስ ቁርባንን ንሰሃ ገብተው ለመቀበል ለተዘጋጁ ሰዎች ብቻ አቅርብ ። በልቦናው ክፋትን እንደያዘ እና ሳይገባው ወደ ጌታ ስጋና ደም መጥቶ ከቆረበ በኃጥያቱ እና በፍርዱ ከእርሱ ጋር ተካፋይ ትሆናለህ! #በመንፈሳዊ ህይወት ጥሩ ልምድ ያላቸውና በዕድሜ የገፉ የንሰሃ አባት ይኑርህ። የአንድ ቀን ልምድ እንኳ ብዙ ነውና ከእሳቸው ምክር እና መመርያዎችን ተቀበል! #አንዱ የጉባኤ አባል በኃጢአት ቢታመም ከበሽታው እንዲድን እና መንፈሳዊ ጤንነቱ እስኪመለስ መንከባከብ አለብህ! #እንደዚህ ካደረክ ከእግዚአብሔር ስለፍቅርህ እና ስለአገልግሎትህ ብዙ እጥፍ ሽልማትን ትቀበላለህ። የጌታንም አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ የሚለውን የተወደደ ድምፅ ትሰማላችሁ። (ማቲ 25:21) ❀✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞❀ ©Mahiberekidusan

ክርስቶስን መውደድ እንዴት? (በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) አንድ በጣም የምንወደው እንግዳ ወደ ቤታችን ሲመጣ እጅግ በጣም ከመደሰታችን የተነሣ የምናደርግለት ኹላ ሊጠፋብን ይችላል፡፡ እንደምንወደው፣ እንደናፈቀን እንነግሯለን፡፡ ከዚያም በላይ የሚወደውን እናቀርብለታለን፡፡ ባይኖረን እንኳን ስላላቀረብንለት እናዝናለን፡፡ ያለንን፣ ቤት ያፈራውን ግን እናቀርብለታለን፡፡ ስለምንወደውና ስለናፈቀን ርሱን የሚያስከፋ ነገር ምንም አናደርግም፡፡ ብናደርግም ወዳጃችንን ኾን ብለን ለማስከፋት ብለን የምናደርገው አይደለም፡፡ እንወዷለን የምንለው እንግዳችንን ትተን ሌላ ሥራ አንሠራም፡፡ በቃላት ብቻ እወድኻለኁ ብንለው፥ ነገር ግን በተግባር እንግዳችንን መውደዳችን ባንገልጥ ግን እንግዳችን ያዝንብናል፡፡ ከቃላችን በላይ ተግባራችንን ስለሚያይም እንደምንወደው ብንነግረውም አያምነንም፡፡ መውደድ የቃላት ጨዋታ ሳይኾን በተግባር የሚገለጥ ነውና፡፡ ልክ እንደዚኹ ፍጹም ሰው ኾኖ፣ ባሕሪያችንን ባሕርይ አድርጐ ወደ እኛ የመጣውን ክርስቶስን እንደምንወደው እየተናገርን፥ ነገር ግን በተግባር የምናሳዝነው ከኾነ መውደዳችን ትክክለኛ መውደድ አይደለም፡፡ ብንወደው ኖሮ ልክ ከላይ እንደገለጥነው እንግዳችን የሚበላ ነገርን እናቀርብለታለን፡፡ የክርስቶስ መብሉስ ምንድነው? እርሱ እራሱ እንዲኽ ሲል ነግሮናል፡- “የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው” /ዮሐ.4፡34/፡፡ ተርቦ ስናየው የሚበላ ነገርን እንስጠው፤ ተጠምቶ ስናየው የሚጠጣ ነገርን እንስጠው፤ ርሱም ይቀበለናል፡፡ የሚቀበልንም ስለሚወደን ነው፤ ከማንወደው ሰው ስጦታን አንቀበልምና፡፡ ስጦታችን ትንሽ ሊኾን ይችላል፤ ነገር ግን አፍቃሪያችን ነውና ስለ ስጦታችን ታናሽነት አልቀበላችኁም አይለንም፡፡ ስጦታችን በርሱ ዘንድ ትልቅ ነው፡፡ በስንፍና አንያዝ እንጂ ስጦታችን አምስት ሳንቲምም ልትኾን ትችላለች፤ ርሱ ግን ወዳጃችን ነውና አምስት ሳንቲም ናት ብሎ ስጦታችንን አያቃልላትም፡፡ እንደ ድልብ ስጦታ አድርጎ አምስት ሳንቲሟንም ይቀበልልናል እንጂ፡፡ ስጦታችንን የሚቀበለው ድኻ ስለኾነ አይደለም፡፡ ስጦታችንን የሚቀበልልን ስለ ስጦታችን ታላቅነት ሳይኾን ስለ ልቡናችን ኀልዮት (intention) ነው፡፡ ስለዚኽ ስንሰጥ ክርስቶስ ስለተቀበለን ትንሽዋንም ስጦታችንን ይቀበል ዘንድ በቤታችን ታዛ ስለገባ ልናመሰግነው ይገባል፡፡ እውነተኛ ሐሴት ማለትም ይኸው ነው፤ በመቀበል ሳይኾን በመስጠት የምናገኘው፡፡ ወደ ቤታችን፣ ወደ ሕይወታችን የመጣው ለእኛ ሲል ነው፡፡ ነፍሱን አሳልፎ ለሞት የሰጠው ለእኛ ሲል ነው፡፡ ፍቅሩ ግን እዚኽ ላይ አላበቃም፡፡ አኹንም እኛ ጋር እየመጣ ነው፡፡ ሐዋርያው “ስለ ክርስቶስ መልእክተኞች ነን” ብሏል /2ኛ ቆሮ.5፡20/፡፡ ስለዚህ ተርበውና ተጠምተው ወደ እኛ የሚመጡት ሰዎች የክርስቶስ መልእክተኞች ናቸው ማለት ነው፡፡ የንጉሡን መልእክተኛ፡የሚያባርር ታድያ ማን ሞኝ ነው? ነገር ግን ብዙዎቻችን ሞኞች ኾነናል፡፡ የነገሥታት ንጉሥ የክርስቶስ መልእክተኞችን እያባረርናቸው ነውና፡፡ ክርስቶስን እንወድኻለን እያልን በተግባር ግን እናባርረዋለን፡፡ ከዚኽ የበለጠ ምስኪንነት ከወዴት ይገኛል? ክርስቶስን በቃል እወድኻለኁ እያሉ በተግባር ግን ርሱን ማባረር የማይጠቅም ብቻ ሳይኾን የሚጐዳን ጭምር ነው፡፡ እንኪያስ ተወዳጆች ሆይ! ክርስቶስን በቃልም ገቢርም እንውደደው፡፡ በታላቁ እንግዳችን በክርስቶስ ደስ መሰኛታችንን በተግባር እንግለጠው፡፡ ይኽን እንድናደርግ ርስቱንና መንግሥቱንም እንደ ቸርነቱ እንዲያወርሰን እኛን በመውደዱ ወደ እኛ የመጣው ደግሞም የሚመጣው ክርስቶስ ይርዳን አሜን!!! ✞የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደናንተ ይቀርባሉ፡፡ለጓደኞቻችን #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ እናድርጋቸው✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

💙 ለምሳሌ፡- በእኛ የ2000 ዓ.ም ወንጌላዊው ዮሐንስ ነበር፤ አበቅቴው ደግሞ 23 ነበረ፡፡ ከ76 ዓመት በኋላ በ2076 ዓ.ም በተመሳሳይ መልኩ ወንጌላዊው ዮሐንስ አበቅቴውም 23 ይሆናል፡፡ “ጥንቱሰ ለቀመር ዕለተ ሰሉስ ወወንጌላዊ ማቴዎስ ወፍጻሜሁ ዕለተ ሰሉስ ወወንጌላዊሁ ዮሐንስ - የቀመር (የቁጥር) መጀመሪያ ማክሰኞ፣ የወንጌላውያን መጀመሪያ ማቴዎስ ሲሆን የቀመር መጨረሻ ሰኞ የወንጌላውያን ፍጻሜ ዮሐንስ ነው” እንዲል። 💙 አበቅቴ አስራ ስምንት የሚሆነው በየአስራ ዘጠኝ ዓመቱ ሲሆን 18 በሆነ በዓመቱ አበቅቴው ዜሮ ነው የሚሆነው። 💙 አንድ ዐውደ ማኅተም 7 ጊዜ ሲመላለስ አንድ ዐቢይ ቀመር ይሆናል፡፡ (7 × 76 = 532) 💙 ይህ ዓውደ ማኅተም ማዕከላዊ ቀመርም በመባል ይታወቃል፡፡ https://t.me/EOTC2921 ፭. #ዐቢይ_ቀመር(ዐውደ ቀመር) 532 ዓመት፡- ከ7ቱ አዕዋዳት ታላቁና የመጨረሻው ዐቢይ ቀመር እየተባለ የሚታወቀው ዐውደ ቀመር ነው፡፡ የዘመኑ ርዝመት 532 ዓመት ሲሆን ይህን ዘመን በግሪክ በርዩድ ወይም በርዮድስ ይሉታል፡፡ 💙 ሊቁ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ግን በርዮድስ - ማለት ቀመር፣ የቀመር ስም፣ የጨረቃ ቢሆን 19 የፀሐይ ቢሆን 28 ሲያበዛ በርዮድሳት ይላል፡፡ ብለው ተርጉመውታል፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 288 💙 በዚህን ጊዜ ሶስት ነገሮች በጋራ ይገናኛሉ። እነዚህም ዕለት፣ አበቅቴ እና ወንጌላዊ ናቸው። እለቱ ሰኑይ (ሰኞ) አበቅቴውና ወንጌላዊው ከላይ እንዳየነው 18 አበቅቴ እና ወንጌላዊው ዮሐንስ ይሆናሉ። 18 አበቅቴ ለአበቅቴ ፍጻሜ፣ ወንጌላዊው ዮሐንስ ለወንጌላውያን ፍጻሜ ነው ብለናል። በተጨማሪ እዚህ ጋር ሶስተኛ ሆኖ ለዐቢይ ቀመር መገኛ የሆነው ዕለት ነው። ዕለቱም ሰኞ ነው። የቀመር መጀመሪያው ማክሰኞ ከሆነ ደግሞ ፍጻሜው ሰኞ ይሆናል ማለት ነው። 💙 በሌላ አነጋገር በየ532 ዓመቱ 1 ጊዜ የአዲሱ ዓመት መግቢያ ዕለት፣ ወንጌላዊ፣ አበቅቴው ይገናኙበታል፡፡ ይህም ዕለት ሰኞ፣ ወንጌላዊው ዮሐንስ፣ አበቅቴው 18 ይሆናል፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 687 💙 ለምሳሌ፡- በእኛ የ2000 ዓ.ም የዐዲሱ ዓመት መግቢያ ዕለት ረቡዕ፣ ወንጌላዊው ዮሐንስ፣ አበቅቴው 23 ነበር፡፡ ከ532 ዓመት ዑደት በኋላ በተመሳሳይ መልኩ በ2532 ዓ.ም ላይ የዐዲሱ ዓመት መግቢያ ዕለት ረቡዕ፣ ወንጌላዊው ዮሐንስ፣ አበቅቴው 23 ይሆናል፡፡ 💙 የባሕረ ሐሳብ ሊቃውንት የቀመሩን መነሻ የሚያደርጉት ዕለቱ ሠሉስ፣ ወንጌላዊው ማቴዎስን አበቅቴውን አልቦ በሆነ ጊዜ ነው፡፡ “ጥንቱ ለቀመር ዕለተ ሠሉስ ወንጌላዊ ማቴዎስ ወፍጻሜሁ ዕለተ ሰኑይ ወንጌላዊ ዮሐንስ” ይላሉ፡፡ የዓውደ ቀመር ሌላ ስሙ ዐቢይ ዓውድ ነው፡፡ 💙 አንድ ማኅተም 4 አልቦ ነው፤ 1 ዓቢይ ቀመር በሱባዔ 76፣ በማኅተም 7፣ በአንቀጸ ወርኅ 28፣ በአንቀጸ ፀሐይ 19፣ በዓውደ ጳጉሜን በ4ቱ 133፣ በኢዮቤልዩ 10 ኢዮቤልዩ ከ6 ሱባዔ፣ በእንድቅትዮን 35 እንድቅትዮን ከ1 ሱባዔ፣ በዓውደ ሰንበት 4፣ በዓውደ ዕለት 19 እልፍ ከ4 ሺሕ ከ180 ዕለት ይሆናል፡፡ 6ኛዋን ዕለተ ጳጉሜን የጨመሩ እንደሆነ 19 እልፍ ከ4 ሺህ ከ313 ዕለት ይሆናል፡፡ ጠንቅቀህ ቁጠር ከማሁ ዘኩሎሙ ዕለታት፡፡ ፲፪. #የጠፉ(የተዘነጉ) ቀናትን ማግኘት 💙 በአንድ ወቅት አንዳንድ ተግባር ያከናወንባቸው ወይንም ለማወቅ የምንፈልገው ቀናት ለምሳሌ የተወለድንበት ቀን ለመፈለግ ወይም ባጋጣሚ ቢጠፋብን በቀላሉ ለማግኘት እንችላለን፡፡ 💙 ይህን ለመሰራት 3 ነገሮችን እንደምራለን፡- የወሩ እጥፈ + ዕለት + ጥንተ ዮን / 7 💙 ምሳሌ 1፡- ሚያዚያ 23፣ 2013 ዓ.ም ምን ቀን እንደሚውል ለማወቅ ብንፈልግ 🔶 ዕለት = የወሩ እጥፈ + ሠርቀ መዓልት + ጥንተ ዮን / 7 ሚያዚያ (8 x 2) =16 + 23 + 3 =42 / 7 = 6 ይደርስና ቀሪ 0 ይሆናል ፡፡ #አዋጅ፡- ቀሪው 1 ቢሆን እሑድ ቀሪው 2 ቢሆን ሰኞ ቀሪው 3 ቢሆን ማክሰኞ ቀሪው 4 ቢሆን ረቡዕ ቀሪው 5 ቢሆን ሐሙስ ቀሪው 6 ቢሆን ዓርብ ያለቀሪ ቢካፈል ቅዳሜ ይሆናል። 💙 ስለዚህ ቀሪው 0 ስለሆነ ሚያዚያ 23፣ 2013 ዓ.ም ቅዳሜ ዕለት ይውላል፡፡ 💙 ምሳሌ 2 ፡- የገና በዓል ታህሳስ 29፣ 2013 ዓ.ም ምን ቀን እንደሚውል ለማወቅ 💙 ዕለት = የወሩ እጥፈ + ሠርቀ መዓልት + ጥንተ ዮን / 7 (4 x 2) = 8 + 29 + 3 = 40 / 7 = 5 ይደርስና ቀሪ 5 ይሆናል ፡፡ ♠ ስለዚህ ቀሪው 5 ስለሆነ ታኅሳስ 29፣ 2013 ዓ.ም ሐሙስ ዕለት ይውላል፡፡ ፲፫. #መደብ_እና_ወንበር ፡- መደብ ማለት ወንበርን ለማግኘት የሚያስችለን ቁጥር ነው፡፡ 💙 ወንበር ማለት ደግሞ አበቅቴና መጥቅን ለማግኘት የሚያስችለን ቁጥር ነው። 💙 ወንበር ከ1-19 ድረስ በቀጥታ የሚጓዝ የዘመን መስፈርት የሆነ ቁጥር ነው፡፡ 💙 ወንበር ከ1 እስከ 19 ባሉት ቁጥሮች መካከል ሲውል ይህም በየዓመቱ አንድ ቁጥር እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ⚛️ መደብንና ወንበርን በተለያየ መንገድ መስራ ይቻላል፡፡ ሀ. መደብንና ወንበር በአበው ስሌት ማስላት፡- 💚 መደብንና ወንበርን በአበው ስሌት ለማግኘት ዓመተ ዓለምን በየቤቱ መከፋፈል 7513 ዓ.ዓ ስንከፋፍለው 7000፤ 500፤ 13 ♥ 7000/532 = 13 ይደርስና 84 ይቀራል፡፡ ♥ 84+500 = 584 ፤ 584 /76 = 7 ጊዜ ይደርስና 52 ይቀራል፡፡ ♥ 52 + 13 = 65 ፤ 65/19 = 3 ጊዜ ይደርስና 8 ይቀራል ፡፡ ➣ ስለዚህ 8 የ2013 ዓ.ም መደብ ነው፡፡ ♦ ወንበር = መደብ - 1 = 8-1 =7 ♦ የ 2013 ዓ.ም ወንበር 7 ወጣ ማለት ነው፡፡ ለ. መደብንና ወንበር በሊቃውንት ስሌት፡- ዓመተ ዓለምን ለዓቢይ ቀመር ማካፈል ሲሆን ➣ 7513 / 532 = 14 ይደርስና 65 ይቀራል፡፡ ➣ 65/19 = 3 ጊዜ ይደርስና 8 ይቀራል፡፡ 8፣ የ2013 ዓ.ም መደብ ነው፡፡ ➣ ወንበር = መደብ - 1=8-1 = 7 ➣ የ2013 ዓ.ም ወንበር 7 ነው ማለት ነው፡፡ ሐ. መደብንና ወንበር በዘመናዊ ስሌት ፡- ዓ.ዓለምን ለንዑስ ቀመር (19) ማካፈል ፣ ➣ 7513 / 19 = 395 ይደርስና 8 ይቀራል ፡፡ 8 የ2013 ዓ.ም መደብ ነው። ➣ ወንበር = መደብ - 1 = 8-1 =7 የ 2013 ዓ.ም. ወንበር 7 ነው ማለት ነው፡፡ ➣ ወንበር በሦስቱም መንገድ ቢሰራም ውጤቱ ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡ ይ🀄️ጥላል

ለ. #በዓመት_የሚቆጠሩ_አዕዋዳት፦ https://t.me/EOTC2921 ፩. #ዓውደ_ጳጉሜን፡- ዓመቱን ሁል ጊዜ በዕለት፣ በሰዓት፣ በደቂቃ፣ በዳግሚት (በሰከንድ) አስተካክሎ መክፈል ቢቻልም አይመችም፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱን ዓመት በአጠቃላይ አነጋገር 365 ዕለት አድርገው ከዕለት የተረፈውን ጊዜ (ማለትም 5 ሰዓት፣ ከ48 ደቂቃ፣ 46 ዳግሚት የሚሆነውን ጊዜ) ያከማቿል፤ የተከማቸው በየ4 ዓመቱ 23 ሰዓት፣ ከ15 ደቂቃ፣ ከ7 ዳግሚት ይወጣዋል፡፡ ይህ ለአንድ ዕለት ቅርብ ስለሆነ አንድ ዕለት ተብሎ አራተኛው ዓመት ላይ ይጨመርና አራተኛው ዓመት 366 ዕለት ይኖረዋል፡፡ ይህ የሚደረግበትን የአራቱን ዓመት ዓውድ (አራተኛውን ዓመት አይደለም፤ ለአራተኛው ዓመት ትርፍ ጊዜ የሚያዋጡትን 4ቱን ዓመቶች የሚያጠቃልለውን ዓውድ ነው) ይህን ዓውደ ጳጉሜን አሉት፡፡ #ዓውደ_ጳጉሜን፦ ዓውደ ጳጉሜን አራት ዓመት ነው፡፡ “ጳጉሜን” የግሪክ ቃል ነው፡፡ “ዓመቱ በዕለት ሲለካ የተረሳ” ማለት ነው፡፡ “የተረሳ የሰዓት፣ የደቂቃ፣ የዳግሚት (የሰከንድ) ዘመን ተረስቶ አልተረሳም፡፡ ይኸው 4 ዓመት (አንድ ዓውድ) ሙሉ ሰብስበን አንድ ዕለት አድርገነዋል፡፡” ሲሉ ነው፡፡ 👉 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በዚህ ዓውድ ውስጥ ያሉትን አራቱን ዓመታት ለወንጌላውያን መታሰቢያ አድርገዋቸዋል፡፡ የመጀመሪያው ዓመት ማቴዎስ፣ ቀጥሎ ማርቆስ፣ ቀጥሎ ያለው ሉቃስ፣ የመጨረሻው ዓመት ዮሐንስ ይባላል፡፡ ተራቸው በማቴዎስ ጀምሮ በዮሐንስ ያለቀው የወንጌላውያኑ መጻሕፍት (ወንጌሎቹ) በአንድ ሲጠረዙ የተሰጣቸውን ቅደም ተከተል ተከትሎ ነው፡፡ (ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ፣ ዮሐንስ) ፡፡ የተረሳችው (ወይም ሰዓቷና ደቂቃዋ ተጠራቅመው የፈጠሯት) ዕለት ዘመነ ሉቃስን ስለምታረዝመው የዮሐንስ ዓመት ( ዘመነ ዮሐንስ) የሚጀምረው ከሌሎቹ በአንድ ዕለት ዘግይቶ ነው፡፡ ዓመቱ በአንዲት “ሠርጎ ገባ” ዕለት ስለሚዘገይ ሠግር (በእንግሊዘኛው Leap Year) ይባላል፡፡ 💙 ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት የመሸጋገሪያ ቅጽበት በየዓመት ይለያያል ብለናል፡፡ በአበው አገማመት “ማቴዎስ ምግብናውን (ግዛቱን ማለት ነው) በሠርክ (ማታ በ12 ሰዓት ማለት ነው) ይጀምራል፤ ከሠርክ እስከ መንፈቀ ሌሊት በ6 ሰዓት፣ በ15 ኬክሮስ ይፈጽማል፤ (ከሌሊቱ 6 ሰዓት ወይም በሌላ አቆጣጠር ከሌሊቱ 15 ኬክሮስ ወስዶ ያልቃል ማለት ነው)፡፡ ማቆስ ምግብናውን በመንፈቀ ሌሊት (እኩለ ሌሊት ማለት ነው) ይጀምራል፤ ከመንፈቀ ሌሊት እስከ ነግህ (ከጧቱ በ12 ሰዓት ማት ነው) በ6 ሰዓት በ15 ኬክሮስ ይፈጽማል፡፡ ሉቃስ ምግብናውን በነግህ ይጀምራል፣ ከነግህ እስከ ቀትር (እስከ እኩለ ቀን ማለት ነው) በ6 ሰዓት በ15 ኬክሮስ ይፈጽማል፡፡ ዮሐንስ ምግብናውን በቀትር ይጀምራል፤ ከቀትር እስከ ሠርክ በ6 ሰዓት በ15 ኬክሮስ ይፈጽማል፡፡” አንድ ኬክሮስ 24 ደቂቃ ነው፡፡ በ6 ሰዓት (በ15 ኬክሮስ) የሚሉት የሠግሯን አንድ ዕለት (24 ሰዓቶች) ለ4ቱ ወንጌላውያን እኩል ለማካፈል ነው (24 ÷ 4 = 6 ሰዓት ወይም 15 ኬክሮስ)፡፡ 💚 ርዕሰ ዓውደ ዓመታችን ቅዱስ ዮሐንስ የሚባለው በወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ ሳይሆን በመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ነው፡፡ 📚 (ጌታቸው ኃይሌ (ፕ/ር) ባሕረ ሐሳብ የዘመን ቈጠራ ቅርሳችን ከታሪክ ማስታወሻጋራ ገጽ 38-39 1993) ፪. #ዐውደ_አበቅቴ(ንዑስ ቀመር) 19 ዓመት፡- 💙 በ19 ዓመት አንድ ጊዜ አልቦ አበቅቴ ወአልቦ መጥቅዕ ይፈጠራል። (በ19 ዓመት 1 ጊዜ መጥቅና አበቅቴ ዜሮ ይሆናሉ፡፡) ይህ በየአስራ ዘጠኝ ዓመቱ አንድ ጊዜ የሚመጣ ሲሆን አንድ አውደ አበቅቴ (19 ዓመት) ተፈጽሞ ሌላ አውደ አበቅቴ ሊጀምር ነው ማለት ነው። 💙 ስለዚህ በሚቀጥለው ዓመት አበቅቴው ዜሮ ይሆናል ማለት ነው። ምክንያቱም ፀሐይና ጨረቃ ተራክቦ የሚያደርጉበት ጊዜ ነው። ፀሐይና ጨረቃ ሁለቱም በዕለተ ረቡዕ በአንድ ኆኅት (መስኮት) ውስጥ የተፈጠሩ ሲሆን ከዛን ጊዜ ጀምሮ ዑደት ያደርጋሉ። ለምሳሌ ከመጀመሪያው ዓመት ጀምረን ብንሄድ ከዜሮ ይጀምርና ከዚያ 18 ይጨርሳል፡፡ 0፣ 11፣ 22፣ 3፣ 14፣ 25፣ 6፣ 17፣ 28፣ 9፣ 20፣ 1፣ 12፣ 23፣ 4፣ 15፣ 26፣ 7፣ 18፡፡ እነዚህ አበቅቴ ይባላሉ፡፡ 💙 ዓውደ አበቅቴ የሚባለው እነዚህን አበቅቴዎች የሚሰበስበው የ19 ዓመት ዓውድ ነው፡፡ 💙 በሌላ አባባል አበቅቴና መጥቅዕ ዜሮ የሚሆኑበት ዓመት ማለት ነው። በየዓመቱ ፀሐይ ሙሉ 365 ቀናት ስትዞር ጨረቃ ግን 354 ቀናት ብቻ ትዞራለች በመካከላቸው ያለው ልዩነት 11 ቀን ሲሆን ይህ ጥንተ አበቅቴ ይባላል። ሁለቱ በየዓመቱ ተለያይተው ሲዞሩ ቆይተው በአስራ ዘጠኝ ዓመት አንድ ጊዜ በተፈጠሩበት ኆኅት (መስኮት) ይገናኛሉ፤ ይኸውም ንዑስ ቀመር በመባል ይታወቃል። በዘመን አቆጣጠር ሊቃውንት ዘንድ “ሜቶኒክ ዑደት” (metonic cycle) the 19 year cycle በመባል ይታወቃል፡፡ 💙 ይህ 19ኛው ዓመት ፀሐይና ጨረቃ እንደ ጃንጥላና እንደ ሰው ከላይና ከታች ሆነው ለተወሰኑ ሰዓታት (ጊዜያት) የሚጓዙበት ወቅት ነው፡፡ 💙 ዓውደ አበቅቴን አቡሻኽር ዓውደ ቀመር ይለዋል፡፡ ቀመር ማለት በዐረብኛ ጨለቃ ማለት ስለሆነ ነው፡፡ 💙 አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመጽሐፋቸው ዐውደ አበቅቴ፡- “19 ዓመት በዚህ ጨረቃና ፀሐይ መንገዳቸውን እየፈጸሙ ተራክቦ ያደርጉበታል፡፡” ኪ.ወ.ክ ገጽ 687 ፫. #ዐውደ_ፀሐይ 28 ዓመት፡- በ28 ዓመት ዞሮ የሚመጣ ሲሆን አንዱ ወንጌላዊ 7ቱን ዕለታት ሁሉ ዞሮ ፈጽሞ በ28 ዓመቱ እንደገና በመጀመሪያው ጊዜ በገባበት ዕለት መልሶ ዐዲስ ዓመት ላይ ይገባል (4X7 = 28) ፡፡ በዚህ ጊዜ ዕለቱና ወንጌላዊው ይገናኛሉ፤ ዕለቱ - ረቡዕ፣ ወንጌላዊው - ማቴዎስ ይሆናል፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 687 💙 አንድ ዐውደ ፀሐይ 19 ጊዜ ሲመላለስ አንድ ዐቢይ ቀመር ይሆናል፡፡ (19 × 28 = 532) 💙 የዓውደ ፀሐይ ሌላ ስሙ ንዑስ ዓውድ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- 2000 ዓ.ም መስከረም አንድ ቀን አዲሱ ዓመት ዕለቱ ረቡዕ ሲሆን ወንጌላዊው ዮሐንስ ነበር፡፡ ከ28 ዓመት በኋላ በ2028 ዓ.ም ላይም በተመሳሳይ መልኩ መስከረም አንድ ዕለቱ ረቡዕ ሲሆን ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው፡፡ 💙 በዘመን አቆጣጠር ሊቃውንት ይህ ዑደት solar cycle (28-year cycle) ይባላል፡፡ ፬. #ዐውደ_ማኅተም(ማዕከላዊ ቀመር) 76 ዓመት ፡- አበቅቴውና ወንጌላዊው በ76 ዓመት ዞረው ይገናኙበታል፡፡ ዓውደ ማኅተም አራት ዓውደ አበቅቴ ነው፡፡ (4 x 19 = 76)፡፡ በየ76 ዓመቱ መስከረም አንድ ቀን፣ ወንጌላዊው ዮሐንስ፣ አበቅቴው 18 ይሆናል፡፡ (መርሐ ዕውር ገጽ 4 ተመልከት) በዚህ ጊዜ ዓውደ ዓመት፣ ዓውደ አበቅቴ፣ ዓውደ ጳጉሜን፣ ዓውደ ማኅተም እኩል አንድ ብለው ይጀምራሉ፡፡ የዓውደ ማኅተም ሌላ ስሙ ማዕከላዊ ዓውድ ነው፡፡ ማኅተም መባሉ ወንጌላዊው ለወንጌላዊ አበቅቴው ለአበቅቴ ፍጻሜ ስለሆነ ነው፡፡ ይኸውም የቀመራቸውን መነሻ አበቅቴውን 18 ወንጌላዊውን ዮሐንስ አድርገው ስለነበረ ነው፡፡ በ76 ዓመት 1 ጊዜ አበቅቴው 18 ይሆናል፤ ምክንያቱም ወንበር 0 ስለሚሆን ወይም ወንበር ከዜሮ በታች ኔጌቲቭ ስለሚሆን ነው፤ በዚህ ጊዜ ዕለቱና ወንጌላዊው ይገናኛሉ፤ ዕለቱ - ሰኞ ፣ ወንጌላዊው - ዮሐንስ ይሆናል። ኪ.ወ.ክ ገጽ 687 ይ🀄️ጥላል

📖📚 #ትምህርተ_ባሕረ_ሐሳብ📚📖 💚💛❤️ ክፍል ፲፫ 💚💛❤️ ✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✞ https://t.me/EOTC2921 🛅✝⛪️💠⛪️💠⛪️💠✝🛅 የ፳፻፲፫ ዓ.ም አጽዋማትና በዓላት ስሌት 🛅✝⛪️💠⛪️💠⛪️💠✝🛅 ፯. #ሰንበተ_ሰንበታት፡- ሰንበተ ሰንበታት የሚባለው ጸሎት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብበትና የሚያርግበት የተለየ ዕለት ነው፡፡ ሰንበተ ሰንበታት በዓመት ሦስት ጊዜ ይውላል፡፡ ከሦስቱ ሁለቱ በየ133 ዕለት ይዉላሉ፡፡ ሦስተኛው ግን በ99 ዕለት ይውላል፡፡ 💚 ዕለተ ዮሐንስ ሰኞ ቢውል ከዚያው ጀምሮ ይቆጠራል በሌላ ቀን ቢብት ግን ከሚመጣው ሰኞ ጀምሮ በመቁጠር ይገኛል፡፡ ፰. #ሰንበተ_ረቡዕ፡- ሰንበተ ረቡዕ የሚባለው ጸሎት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብበትና የሚያርግበት የተለየ ዕለት ነው፡፡ ሰንበተ ረቡዕ በዓመት አራት ጊዜ ይውላል፡፡ ይኸውም በየ 91 ቀን ልዩነት ነው፡፡ 💚 ዕለተ ዮሐንስ ሐሙስ ቢብት ከዚያው ጀምሮ ይቆጠራል፡፡ በሌላ ቀን ቢብት ግን ከሚመጣው ሐሙስ ጀምሮ ይቆጠራል፡፡ ከአለፈው ሐሙስ ጀምሮ ሊቆጠር ይችላል የሚሉም አሉ፡፡ ለምሳሌ የዘንድሮውን የ2012 ዓ.ም ሰንበተ ረቡዕ ለማግኘት ዕለተ ዮሐንስ የዋለው ሐሙስ ቀን ነው፤ ከላይ ባየነው የአቆጣጠር ስልት መሠረት 1ኛ መስከረም 1 ቀን ሐሙስ እስከ ታሕሳስ 1 ቀን ረቡዕ፣ 2ኛ ከታሕሳስ 1 ቀን እስከ መጋቢት 2 ቀን ረቡዕ፤ 3ኛ ከመጋቢት 2 ቀን እስከ ሰኔ 3 ቀን ረቡዕ፤ 4ኛ ከሰኔ 3 ቀን እስከ ጳጉሜ 4 ቀን ረቡዕ ይሆናል፡፡ 👑 #ርኀወተ_ሰማይ፡- ማለት የሰማይ መከፈት ማለት ሲሆን ርኀወተ ሰማይ የሚውልበትን ቀን ለይቶ ማወቅ ስለሚገባ መነሻው ጳጉሜን ሦስት (3) ቀን የሩፋኤል ነው፡፡ 🔶 ጥቅምት 20 ቀን 🔶 ታኅሳስ 12 ቀን 🔶 የካቲት 4 ቀን 🔶 መጋቢት 26 ቀን 🔶 ግንቦት 18 ቀን 🔶 ሐምሌ 10 ቀን ነው፡፡ ፱. #አራቱ_ሰንበታ(ሱባኤያት)፡- በአንድ ዐቢይ ቀመር አራት ሰንበታት አሉ፡፡ እነርሱም ሰንበተ ማቴዎስ፣ ሰንበተ ማርቆስ፣ ሰንበተ ሉቃስ፣ ሰንበተ ዮሐንስ ይባላሉ፡፡ መጀመሪያይቱን ሰንበት ማቴዎስ ማክሰኞ ጀምሮ በ133 ዓመተ ቀመር ቅዳሜ ይፈጽማል፡፡ ሁለተኛይቱን ሰንበት (ሱባኤ) ማርቆስ በ134 ዓመተ ቀመር እሑድ ጀምሮ በ266 ዓመተ ቀመር ሐሙስ ይፈጽማታል፡፡ ሦስተኛይቱን ሰንበት ሉቃስ በ267 ዓመተ ቀመር ዓርብ ጀምሮ በ399 ዓመተ ቀመር ማክሰኞ ይፈጽማታል፡፡ አራተኛይቱን ሰንበት ዮሐንስ በ400 ዓመተ ቀመር ሐሙስ ጀምሮ በ532 ዓመተ ቀመር ሰኞ ይፈጽማታል፡፡ (4 X 133 = 532) ይሆናል፡፡ 💚 አንዱ ሰንበት 133 ዓመት ነው፡፡ ለእነርሱም 7 አናቅጸ አበቅቴ አሉት ይኸውም 7 X 19 = 133 ይገኛል፡፡እንዲሁም በ4 ሰንበታት (4 X 7 = 28) = 28 X 19 = 532 ይሆናል፡፡ እንዲሁም የዓለምን ፍጻሜ ቀመር ሱባኤ ሰንበታት 60 X 133 = 7980 ስምንተኛውን ሺህ ዓመት የሚያመለክትና ከቀመረ ዳንኤል ጋር የሚመሳሰል በመሆኑ ወደፊት እንመለከተዋለን፡፡ ፲. #ዓውደ_ፀሐይ፡- 28 ዓመት ነው፡፡ አንድ ዓውደ ፀሐይ 19 ጊዜ ሲመላለስ አንድ ዐቢይ ቀመር ይሆናል፡፡ (19 X 28=532) 💙 ዓውደ ፀሐይን ለማግኘት ዓውደ ፀሐይ = ዓመተ ምህረት ÷ 28 2013/28 = 71 ይደርስና ቀሪ 25 ይሆናል። በ4 ዓመት አንድ ጊዜ ጳጉሜ 6 ከሆነች በ25 ዐመት ስንት ጊዜ 6 ትሆናለች? 24/4 = 6 ስለዚህ ጳጉሜ 6 ጊዜ በ25 ዓመት ውስጥ ስድስት ትሆናለች ማለት ነው። ከዚህ በኋላ ቀሪውንና ከላይ ያገኘነን ውጤት መደመር ነው። 25+6=31 ይህን ለ7 ማካፍል 31/7 = 4 ቀሪ 3 ይሆናል። 3 የሚያመለክተው መስከረም 1 የዋለበትን ዕለት ነው። ስለዚህ ቀሪው 3 ስለሆነ መስከረም አንድ ቀን 2013 ዓ.ም ዓርብ ዕለት ነው የሚውለው፡፡ #አዋጅ፡- ቀሪው 1 ቢሆን ረቡዕ ቀሪው 2 ቢሆን ሐሙስ ቀሪው 3 ቢሆን ዓርብ ቀሪው 4 ቢሆን ቅዳሜ ቀሪው 5 ቢሆን እሑድ ቀሪው 6 ቢሆን ሰኞ ያለቀሪ ቢካፈል ማክሰኞ ይሆናል። 🛅 #ሰባቱ_አዕዋዳት ️🛅 ፲፩. #አዕዋዳት ⚛️ አዕዋድ ማለት ኦደ ከሚል ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ዞሮ መምጣት፣ መዞር ማለት ነው፡፡ ይህም ከሳምንት እስከ ሳምንት፣ ከወር እስከ ወር፣ ከዓመት እስከ ዓመት ተመልሶ የሚምጣ ማለት ነው፤ በተጨማሪም ዓመተ ዓለም የሚታወጅባቸው (የሚቆጠርባቸው) ማለት ነው፡፡ 💚 አዕዋድ (ዐውዶች) ይፈጸማሉ እንጂ ማለቂያ የላቸውም፤ አንድ ዐውድ ሲፈጸም እሱን ጥሎ እሱን የሚመስል ሌላ ዓውድ ይተካበታል፡፡ አንድ ቀን ሲፈጸም ሌላ ቀን ይተካበታል፤ አንድ ሳምንት ሲፈጸም ሌላ ሳምንት ይተካበታል፤ አንድ ዓመት ሲፈጸም ሌላ ዓመት ይተካበታል፡፡ 💚 አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ይህን ሲተረጉሙ ዐዊድ፣ ዶት (ዖደ፣ የዐውድ፣ ይዑድ፡፡ በዕብራይስጡ ዒዌድ ሲሆን በዐረብኛው ዓደ ይለዋል ትርጉሙም መዞር፣ መሽከርከር፣ መገላበጥ፣ ለራሱ ማወድ፣ በዙሪያ መሄድ፣ መመላለስ፣ ማጠር፣ መክበብ፣ ዙሮ መግጠም፣ ብለው ተርጉመውታል፡፡ 💚 ዐዋዲ፣ ዐዋዲት፣ ዐዋዲያን፣ ዐዋዲያት ማለት ደግሞ የሚዞር፣ ዘዋሩ፣ ለፋፊ፣ አዋጅ ነጋሪ ማለት ነው፡፡ 💚 ዐውድ፡- ዙሪያ፣ ክበብ፣ ከበር እስከ በር፣ ከዓመት እስከ ዓመት፣ ያለ ለታጠረ ለተወሰነ ክበብ ላለው ነገር ሁሉ ይነገራል፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 687 👉 የባሕረ ሐሳብ መምሕራን በአብዛሀኛው የሚያስተምሩት ዋና ዋናዎቹ የዘመን ዓውዶች ሰባት ሲሆኑ አንዳንድ መምሕራን ደግሞ ዓውደ ጳጉሜን ጨምረው በመቁጠር ስምንት ብለው ያስተምራሉ፡፡ ስምንቱንም ዓዕዋዳት በዝርዝር እንደሚከተለው እናያቸዋለን፡፡ ♻️ ሁለት ዓይነት አዕዋዳት አሉ ♻️ ሀ. #በዕለት_የሚቆጠሩ_አዕዋዳት ፡- ፩. ዐውደ ዕለት፡- ከእሑድ እስከ ቅዳሜ ድረስ ዞረው የሚመጡ (የሚመላለሱ) ሰባቱ ዕለታት ናቸው፡፡ እነዚህ ዐውደ ወርኅን ወይም ወሮችን ለማስገኘት በሰባት በሰባት ሲመላለሱ ይኖራሉ፡፡ አንድ ሱባኤ ሰባት ዕለት ነው፡፡ ሄኖክ 26÷32፣ ኪ.ወ.ክ ገጽ 687 ፪. #ዐውደ_ወርኅ፡- በፀሐይ 30 ቀን ሲሆን በጨረቃ ደግሞ አንድ ጊዜ 29 አንድ ጊዜ ደግሞ 30 ይሆናል፡፡ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ይህን ዐውደ ወርኅን ሲተረጉሙት 30 ቀን ከልደታ መባቻ እስከ መባቻ፡፡ የጨረቃ ዐውደ ዓመት 354 ቀን፤ ብለው ተርጉመውታል፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 687 💙 አበቅቴ ወርኅ ማለት ተረፈ ጨረቃ ማለት ነው፡፡ ሄኖክ 22÷8 ፫. #ዐውደ_ዓመት፡- በፀሐይ 365 ዕለታት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልዒት በዘመናዊው አነጋገር 365 ዕለታት ከ6 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ24 ሰከንድ ሲሆን በጨረቃ ደግሞ 354 ዕለታት ከ22 ኬክሮስ ከ1 ካልዒት፣ ከ37 ሣልሲት፣ ከ52 ራቢዒት፣ ከ48 ኀምሲት ይሆናል፡፡ በዘመናዊው አነጋገር 354 ዕለታት ከ8 ሰዓት ከ48 ደቂቃ ከ39 ሰከንድ ይሆናል፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 687 💙 ይኽም ማለት ስድስት ወራት ሃያ ዘጠኝ፣ ስድስት ወራት ሰላሳ ቀናት ይሆናል። (6 × 29 = 174) ፤ (6 × 30) = 180 ሁለቱ ሲደመሩ 174 + 180 = 354 ቀናት ይሆናል። ይ🀄️ጥላል

#ስምህ_በሁሉ_ተመሰገነ ስምህ በሁሉ ተመሰገነ፣ ከክብር በላይ ክብርህ ገነነ፣ አንተን ማወደስ ያስደስተናል፣ ስምህን ማክበር ግብራችን ሆኗል።  •••✞ t.me/EOTC2921 ✞••• አምላክ ተመስገን በሰማያት፣ ስምህ ይወደስ በፍጥረታት፣ ከሕፃናት አፍ ምስጋና ይውጣ፣ አንተን ማመስገን ይሁን የእኛ እጣ፡፡ /2/  #አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ •••  •••✞ t.me/EOTC2921 ✞••• በምግብ እጦት ብንሰቃይም፣ ማኅሌትህን አናቋርጥም፣ የመከራ ዶፍ ቢወርድብንም፣ እንዘምራለን ለአምላኝችን ስም። /2/ #አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ •••  •••✞ t.me/EOTC2921 ✞••• ሰማዩ ዝናብ ደመና ሲያጣ፣ ፍቅርህ በእኛ ውስጥ አላቋረጠም፣ ቸርነትህን እንጠብቃለን፣ ከአንተ ደጅ አምላክ የት እንሄዳለን፣ ቸርነትህን እንጠብቃለን፣ ከአንተ ደጅ ጌታ የት እንሄዳለን። /2/ #አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ •••  •••✞ t.me/EOTC2921 ✞••• አምላክ ተመስገን በሰማያት፣ ስምህ ይወደስ በፍጥረታት፣ ከሕፃናት አፍ ምስጋና ይውጣ፣ አንተን ማመስገን ይሁን የእኛ እጣ፡፡ /2/  #አዝ ••• ✞ ••• ✞ ••• ✞ •••  •••✞ t.me/EOTC2921 ✞•••

🌾🕊✞ #እውነተኛው_ሰላም ✞🕊🌾 እውነተኛው ሰላም ያለው ከቤትህ ነው(2) አርዳኝ አልናወፅ እለምንሃለሁ(2) •••✞ t.me/EOTC2921 ✞••• ሀጢያቴን ሳስበው ልቤ ይጨነቃል፣ ካንተ መለየቴ ነፍሴን አድክሟታል፣ ወዳንተ መልሰኝ እኔ እመለሳለሁ፣ እውነተኛው ሰላም ያለው ከቤትህ ነው። #አዝ•••✞•••✞•••✞••• ለቅዳሴው ጸሎት ዘውትር እንዳልተጋሁ፣ ባደባባይ ቆሜ ስምህን እንዳልጠራሁ፣ ተሰነካክዬ ወድቄያለሁና፣ እርዳኝ አማኑኤል በሐይማኖት ልፅና። #አዝ•••✞•••✞•••✞••• አይኔ እንባን ያፍስ ላልቅስ ስለሀጥያቴ፣ የንስሃ ትሁን ቁሪዋ ህይወቴ፣ በመዳኔ ሰዓት በዛሬዋ ዕለት፣ ፍቅርህን አስቤ መጣሁ ካንተ ፊት። #አዝ•••✞•••✞•••✞••• ጌታ ሆይ ፀፀቴን እንባዬን ተቀበል፣ አባትሽ ነኝ በለኝ እኔም ልጅ ነኝ ልበል፣ ዘይት ሳላዘጋጅ ድንገት መተህብኝ፣ በርህን በመዝጋት ከደጅ አታስቀረኝ። #አዝ•••✞•••✞•••✞•••

በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng 👆👆👆 በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ   ! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng 👆👆👆 በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ   ! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng 👆👆👆 በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ   ! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

በየቀኑ አዳዲስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማ እና ቀኖና የጠበቁ ፅሁፎችን ፣ Pdf መጽሐፍት መንፈሳዊ መተግበሪያ APP ፣ እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቀላቀሉን ንፅህት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ። JOIN 👉https://t.me/joinchat/AAAAAEcoMBp6zzcIYdK6ng 👆👆👆 በ YOUTUBE ለመከታተል ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን ያገኙታል Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ   ! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇