es
Feedback
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏

Ir al canal en Telegram

የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921

Mostrar más
4 374
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
#መስቀሌን_በመስቀለኛ_ስፍራ_አኑር ✞ ✞ መስቀሌን በመስቀለኛ ስፍራ አኑር በተባለበት ግሼን ደብረ ከርቤ ማርያም ተገኝተው ለማየት የቻሉ ሁሉ እጅግ የታደሉ ናቸው!! ➣ግሽን በጥንት ፍጥረት በመስቀል ቅርጽ ተፈጥራ ዙሪያዋን በአራቱም አቅጣጫ በገደል የተከበበችና አንድ መግቢያ ብቻ ያላት ድንቅ የሆነች ታሪካዊ ቦታ ነች፡፡ ግሸን ደብረ ከርቤ ዳግማዊ እየሩሳሌም የተቆረቆረችው በ517 ዓ.ም በንጉስ ካሌብ ዘመነ መንግስት ሲሆን የመሰረቷትም የአፄ ካሌብ ክርስትና አባት የሆኑት አባ ፍቃደ ክርስቶስ የተባሉ መናኝ ባህታዊ መነኩሴ እንደነበሩ ታሪክ ያስረዳል፡፡ አባ ፈቃደ ክርስቶስ የእመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማሪያምንና የእግዚአብሄርአብን ጽላቶች ከሀገረ ናግራን /በዛሬው አጠራር የመን ከተባለውና በዚያን ዘመን የኢትዩጵያ ግዛት ከነበረው ቦታ ይዘው በዘመኑ አጠራር መቃድስ በአሁኑ ሞካድሾ/ሶማሊያ/ በኩል አድርገው ወደ ኢትዮጵያ በመግባት የበሸሎን ወንዝ ተሻግረው እረጅም ጉዞ በማድረግ አቀበቱን ወጥተው ወደ መስቀለኛው አምባ ጥግ ሲደርሱ በተፈጥሮ የመስቀል ቅርፅ ካለው ይህ አስደናቂ አምባ መወጣጫ ሲፈልጉ በገደሉ ላይ ንብ ሰፍሮ ማር ተጋግሮበት በማየታቸው የአካባቢውን የተፈጥሮ ፀጋ ሲያደንቁ ይህስ “አምባሰል ነው” በማለት ተናገሩ ይባላል፡፡ ✞ አባፈቃደ ክርስቶስ በእግዚአብሄር ፈቃድ የእግዚአብሄር አብንና የእምቤታችን ጥላቶች ይዘው ወደ አምባው በመግባት ሁለት ትንንሽ የሳር ጎጆዎችን አስቀልሰው በመግባት በዚያው የብህትና ኑሯቸውን በማከናወን እስከ ህይወት ፍጻሜያቸው እንደኖሩ ይነገራል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በቦታው እግዚአብሄር ሲወደስና ሲቀደስ ከኖረ በኋላ በዘመኑ ለነበሩ የኢትዮጵያ ንጉስ አፄ ዘርያቆብ “አንበር መስቀል በዲበ መስቀል” መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ” የሚል ቃል በመንፈስ እግዚአብሔር ራዕይ ተገለፀላቸው፡፡ ✞ አባታቸው አፄ ዳዊት ከግብፆች ተረክበውት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ በመንገድ ላይ በመሞታቸው ምክንያት ከመንገድ ላይ እንዲቆይ የተደረገውም ቅዱስ መስቀል እና ልዩልዩ ንዋያተ ቅዱሳትን ከግብፆች ተረክበው ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ በ1446ዓ.ም አጼ ዘርያቆብ መስቀሉን አስይዞ መስቀለኛ ቦታ ለማግኘት አያሌ የኢትዮጵያ ተራሮችን እየተዘዋወሩ ካዩ በኋላ በመጨረሻም የግሸን አምባን ስላገኙ ቅዱስ መስቀሉን አስይዘው ወደ አምባው ጥግ ከስፍራው እንደደረሱ ወደ ውስጥ ሳይገቡ ዙሪያውን ሦስት ጊዜ በመዞር ከውጭ አደሩ። ✟ በራዕያቸውም ተነስተህ በስተምስራቅ በኩል ግባ አላቸው እርሳቸውም ተናጋሪውን ሳይሆን ንግግሩን በማስተዋል እንደታዘዙት በብቸኛዋ መግቢያ ምስራቃዊ በኩል ገብተው አምባው እንብርት ወርዱና ቁመቱ አርባ ክንድ የሆነ ጉድጓድ አስቆፍረው የእየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀልን በወርቅና እንቁሳጥን ከዚያም በሸክላ ሳጥን አድርገው በመሬት ውስጥ በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ብልሀት በተዘጋጀ ቦታ በክብር አስቀምጠው ከላዩላይ የእግዚአብሔር አብን ቤተክርስቲያንን በጥሩ ሁኔታ አሳንፀው እንደፈፀሙ መስከረም 21 ቀን 1449 ዓ.ም ቅዳሴ ቤቱ በከፍተኛ ድምቀት እንዲከበር አድርገዋል፡፡ ደብሩንም ደብረ ከርቤ ሲሉ ሰየሙት ትርጉሙ ‹‹ደብር›› የተከበረ ቦታ ሲሆን ‹‹ከርቤ›› ደግሞ የተሰበረ የሚጠግን ማለት ነው፡፡ ይህ በእንድህ እያለ የንጉሱ እህት የሆኑት ንግስት እሌኒ ደግሞ የማርያም ቤተክርስቲያንን ከእግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ትንሽ ራቅ ብለው አሰሩ፡፡ ✞ በአጼ ዘርያቆብ ዘመነ መንግስት የነበሩት ሊቃነ ጳጳስ ሱባኤ ገብተው የተገለፀላቸውን መንፈሳዊ ሚስጥር ለማስረዳት እንዲህ በማለት የቦታውን ታላቅነት አረጋግጠው መስክረዋል፡፡መስቀሉ ያለበትን የግሽን ደብር የተሳለመ፤ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ያስተማረባቸውን ቀራኒዮን፤ ጎለጎታንና፤ ደብረታቦርን እንደተሳለመ ይሆንለታል በማለት ተናግረዋል፡፡ የግሽን ደብረ ከርቤ ቅዱስ ቦታ በውስጡ አምስት አብያተ ክርስትያናትን የያዘ ነው፡፡ ✞ በጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የግድግዳ ላይ ስዕሎችና ስለመስቀሉ አጠቃላይ ታሪክ የሚተርከዉ መፅሀፈ ‹‹ጤፉትም›› እዚሁ ቦታ ብቻ ይገኛል፡፡ ✞ በሌላ በኩል በዚህ ቦታ በቅዱስ ጊዮርጊስ የተፈጥሮ ዋሻ ውስጥ የቅዱሳን አባቶች አጽም ይገኛል፡፡ የግሸን በዓል ከመስከረም 17 ጀምሮ የሚከበር ትልቅ ሚስጢርና በረከት የሚገኝበት ቦታ ነው፡፡ መንግስት በአሁኑ ጊዜ የአገሪቱን በጎ ገጽታ ለሌላው አለም በማስተዋወቅ ጥረት በማድረግ የቱሪስት መስህብ በሆኑ ታሪካዊ ቦታዋች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በከፍተኛ ደረጃ እየተንቀሳቀሰ በሚገኝበት ወቅት ላይ አለም አቀፍ ቅርስ ስለሆነው የክርስቶስ መስቀል ማረፊያነት የተመረጠችው፣ በመስቀል ቅርጽ የተፈጠረችውና በራሷም ቅርስ የሆነችው ግሽን ደብረ ከርቤ ለሀገራችን በተለይም ደግሞ ለአካባቢው ህዝብ ልታስገኘው የምትችለው የቱሪስት ገቢ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ ✞ በዚህም መስከረም እና በጥር 21 ቀናት የማርያም ንግስ በዓል በሚከበርበት ወቅት ከሰሜንና ደቡብ ፤ከምዕራብና ከምስራቅ የሚሰባሰቡት ምዕመናን ቁጥር በየአመቱ እየጨመረ ይገኛል፡፡ #እንኳን_ለግሼን_ማርያም_አመታዊ_ክብር_በአል_በስላም_አደረሰን_አደረሳችሁ✞ 🙏 ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ ወላዲተ አምላክ በረከቷ ፍቅሯና አማላጅነቷ ከሁላችን ጋር ይሁን🙏 ✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

✔✞ወደ ኤፌሶን ሰዎች ምዕራፍ 2 ቁጥር 14 14-15 እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ 16 ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው። ✔✞መዠመሪያዪቱ፡የሐዋርያው፡የቅዱስ፡ጳውሎስ፡መልእክት፡ ወደቆሮንቶስ፡ሰዎች። ምዕራፍ፡1፤ 18፤የመስቀሉ፡ቃል፡ለሚጠፉት፡ሞኝነት፥ለእኛ፡ለምንድን፡ግን፡የእግዚአብሔር፡ኀይል፡ነውና።

✝ ለመስቀል በዓል ልዮ ልዮ ፕሮግራሞች ለመከታተል ከተዋህዶ የ Youtube ቻናል ጋር ቆይታ ያርጉ !   ይህ ቻናል የ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በኪነ ጥበብ ክፍል አባላት የተከፈተ የ Youtube ቻናል ነው ። በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምሮን እና ስርዓትን የጠበቁ መንፈሳዊ ስብከቶች ኦርቶዶክሳዊ ብቻ የሆኑ መንፈሳዊ ልዩ ምልከታ 📌 የ ቅድስት ቤተክርስትያን ታሪክ 📌 የ ቅዱሳን አበው እና አንስት ታሪክ               📌 መንፈሳዊ ስነ ፅሁፎች { ግጥሞች , መነባንቦች } 📌 እንዲሁም ዝማሬዎች የሚተላለፉበት ነው ስለሆነም መንፈሳዊ እህት ወንድሞች አገልግሎታችንን ለመደገፍ ቤተሰብ አንድቶኑ አንላለን ። ከታች ያለውን Link ተጭነው የ Youtube ቻናላችንን Subscribe ያርጉ  ! 🔻 👇 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://www.youtube.com/channel/UCPPV0Jj4491QFJIHxs9WyJQ?subconfirmation=yes 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆  <<የ ቤተክርስትያን ሕይወት በመስቀል ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ፈተና ይበዛባታል ስለዚህ ከ ግል ሕይወታችሁ ይልቅ የበተክርስትያናቹን አጠንክሩ >>        / ብፁእ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ / ✝ ድንግል ማርያም በ ምልጃዋ አትለየን አሜን ✝

፬. #ዘመነ_ጸደይ/በልግ/ (ከመጋቢት 25 ቀን - ሰኔ 25) ቅዱስ ያሬድ በድጓው “ይሁብ ዝናመ ተወን” የበልግ ዝናምን ይሰጣል እንዳለው የበልግ ወቅት ነው፡፡ 💚 ምልኤል፡- መጋቤ ፀደይ ነው፡፡ መ.ሄኖክ 28፥19 ኪ.ወ.ክ ገጽ 592 💚 በዚህ ወቅት መዓልቱ ከ12 ሰዓት እየረዘመ ሌሊቱ እያጠረ የሚሄድበትና ከሌሊቱ ሦስት ሰዓት ትርፍ ይገኝበታል፡፡ 💚 ከክረምት በስተቀር እያንዳንዱ ወቅት በውስጡ ዘጠና ዘጠና ቀናት ይዟል፡፡ ክረምት ግን ለብቻው 95 ቀናትን የያዘ ነው፡፡ 💚 365ቱ ቀናት ለአራቱ ክፍለ ዘመናት ሲካፈሉ ለእያንዳንዳቸው 91 ቀን ከ6 ሰዓት ይደርሳቸዋል፡፡ በአራት ዓመት አንድ ጊዜ 366ቱ ቀናት ለአራቱ ክፍለ ዘመናት ሲካፈሉ 91 ቀን ከ12 ሰዓት ይደርሳቸዋል፡፡ ሄኖክ 28÷12-34 💚 ከአራቱ ክፍለ ዘመናት በአንድ ዓመት የተገኘው ትርፍ ሦስት ሰዓተ መዓልትና ሦስት ሰዓተ ሌሊት በ4 ዓመት 24 ሰዓት ይሆናል፡፡ ይህም 60 ኬክሮስ ይሆንና 1ዕለት ሆኖ ይኸውም 6ኛዋን ጳጉሜን ይሰጠናል፡፡ 📚 ምንጭ፡- መለከት 15ኛ ዓመት ቁጥር 5 ሐምሌ 1999 ዓ.ም ገጽ 32 💛 ከድሜጥሮስ በፊት የነበረውን የጥንት ሰዎች አሰራርን ስንመለከት 💎 3 ወር ከ1ጳጉሜ ለማቴዎስ ፣ 3 ወር ከ1ጳጉሜ ለማርቆስ 💎 3 ወር ከ1ጳጉሜ ለሉቃስ ፣ 3 ወር ከ1ጳጉሜ ለዮሐንስ ይሰጡና 5ኛዋን ጳጉሜን ከጧት-ቀትር ለማቴዎስ፣ ከቀትር - ሠርክ ለማርቆስ፣ ከሠርክ-መንፈቀ ሌሊት ለሉቃስ፣ ከመንፈቀ ሌሊት-ጧት ለዮሐንስ ይሰጡና ስድስተኛዋን ጳጉሜን ለ4ቱ መገብተ ወቅት ሊቃነ ከዋክብት ማለትም፦ 🍏 ለምልክኤል- 15 ኬክሮስ ፣ 🍏 ለሕልመልመሊክ- 15 ኬክሮስ፣ 🍏 ለምልኤል- 15 ኬክሮስ፣ 🍏 ለናርኤል- 15 ኬክሮስ እያከፋፈሉ ይቆጥሩ ነበር፡፡ እነዚህ ከዋክብት የፀሐይን ዑደት እየተከተሉ ዓለምን ሲመግቡ ኖረዋል፡፡ 👑 ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን በኋላ ግን ዘመኑ በአራቱ ወንጌላውያን በማቴዎስ፣ በማርቆስ፣ በሉቃስና በዮሐንስ ይለወጣል ይፈራረቃል፡፡ መ.ሄኖክ 28፥19፣ ሄኖክ 21፥23፣40፣47ና49 ኪ.ወ.ክ ገጽ 445 💚 ዓመተ ወንጌላውያን፦ የሦስቱ ወንጌላውያን ማለትም የዮሐንስ፣ የማቴዎስና፣ የማርቆስ ዘመናት እያንዳንዳቸው ከመስከረም 1 ጀምሮ እስከ ጳጉሜን 5 ድረስ 365 ቀን ከ15 ኬክሮስ (ከስድስት ሰዓት) ነው፡፡ ዘመነ ሉቃስ ግን ከመስከረም 1 እስከ ጳጉሜን 6 ቀን በመሆኑ 366 ቀናት ይኖሩታል፡፡ 💙 #ወራት፦ በኢትዮጵያ ዘመን አቈጣጠር እያንዳንዳቸው 30 ቀናት ያሏቸው 12 ወራት፣ 5 ወይም በየአራት ዓመት 6 ቀናት የሆነች ጳጉሜን አሉ 💙 #ሳምንት፦ ሳምንት “ሰመነ” ስምንት አደረገ ከሚለው ከግዕዝ ቃል የተገኘ ነው፤ በሕገ ዑደት መሠረት ዕለት ከተነሣበት ማለትም ከእሑድ እስከ እሑድ ያለው ጊዜ ሳምንት ተብሎ ይጠራል፡፡ በዚህ ሳምንት ውስጥ ያሉት ቀናት እያንዳንዳቸው 24 ሰዓት ያላቸው ሰባት ቀናት ናቸው፡፡ ኪ.ወ.ክ.ገጽ 846 #የዕለታት_ስያሜዎች💬 ፩. #እሑድ፡- አሐደ ከሚለው ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አንድ አደረገ (የመጀመሪያ ሆነ) ማለት ነው፡፡ በዚህ ቀን ፍጥረታት መፈጠር ስለጀመሩ እሑድ ተብሏል፡፡ ፪. #ሠኑይ(ሰኞ)፡- ሠነየ ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሁለት አደረገ ማለት ነው፡፡ ለሥነ ፍጥረት ሁለተኛ ስለሆነ ሰኑይ (ሰኞ) ተብሏል፡፡ ፫. ሠሉስ(ማክሰኞ)፡- ሠለሰ ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ሦስት አደረገ ማለት ነው፡፡ ማክሰኞ የሚለው የሰኞ ማግስት ማለት ነው፡፡ ፬. #ረቡዕ፡- ረብዐ (አራት አደረገ) ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ለሥነ ፍጥረት አራተኛ ቀን ማለት ነው፡፡ ፭. #ኀሙስ፡- ኀመሰ (አምስት አደረገ) ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ለሥነ ፍጥረት አምስተኛ ቀን ማለት ነው፡፡ ፮. #ዐርብ፡- ዓረበ ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ተካተተ ማለት ነው፡፡ ፍጥረታት እሑድ መፈጠር ጀምረው ዓርብ ስለተካተቱ (ተፈጥረው ስለተፈፀሙ) ዓርብ ተብሏል፡፡ 7. #ቀዳሚት(ቅዳሜ)፡- ማለት ሰንበተ ክርስቲያን ከሆነችው ከዕለተ እሑድ ቀድማ ስለምተገኝ ቀዳሚት ሰንበት (ቅዳሜ) ተብላለች፡፡ ◀⚫✞ ይቆየን ✞⚫▶ ይ🀄️ጥላል ✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

3⃣ዳዊት፥- ቀኑ የአንተ ነው ሌሊቱም የአንተ ነው አንተ ፀሓዩንና ጨረቃውን አዘጋጀህ። መዝ. 73፥16 4⃣ሰሎሞን፡- እነሆ ክረምት አለፈ ዝናቡም አልፎ ሄደ። መኃ.2፥11-13 5⃣ኤርምያስ፡- በልባቸውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በጊዜው የሚሰጠውን ለመከርም የተመደቡትን ወራት የሚጠብቅልንን አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ አላሉም። ኤር.5፥23-24 (ስሙ የሠራዊት ጌታ የሚባል ፀሐይን በቀን የጨረቃንና የከዋክብትን ሥርዓት በሌሊት ብርሃን አድርጎ የሚሰጥ 6⃣ዘካርያስ፡- በዚያም ቀን የሕይወት ውኃ ከኢየሩሳሌም ይወጣል እኵሌታው ወደ ምሥራቁ ባሕር እኵሌታውም ወደ ምዕራቡ ባሕር ይሄዳል ይህ በበጋና በክረምት ይሆናል። ዘካ.14፥8 7⃣ጌታም፡- ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፤ ማቴ.24፥20 እናንተ ገና አራት ወር ቀርቶአል መከርም ይመጣል ትሉ የለምን? እነሆ እላችኋለሁ፡፡ ዓይናችሁን አንሡ አዝመራውም አሁን እንደ ነጣ እርሻውን ተመልከቱ። ዮሐ.4፥35፣ ማቴ.13፥3-23፣ 8⃣ሐዋርያት፡- ከዚህም ሁሉ ጋር መልካም ሥራ እየሠራ ከሰማይ ዝናብን ፍሬ የሚሆንበትንም ወራት ሲሰጠን ልባችንንም በመብልና በደስታ ሲሞላው ራሱን ያለ ምስክር አልተወም። ሐዋ.ሥ 14፥17፣ ብዙ ጊዜ በእርስዋ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የምትጠጣ መሬት ለሚያርሱአትም ደግሞ የምትጠቅምን አትክልት የምታበቅል ከእግዚአብሔር በረከትን ታገኛለችና፡፡ ዕብ.6፥7 9⃣አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፡- “ፀሐይ ጨረቃና ከዋክብት እንዲያበሩለት በመውጣታቸው በመግባታቸው የዘመኑ ቁጥር እንዲታወቅ ተፈጠሩ” አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አርጋኖን ዘሰኑይ https://t.me/EOTC2921 🛅12 በዓመት ውስጥ ያሉት የ12ቱን ወራት አመዳደብ እያንዳንዱ ወር 30 ቀናት እንዲኖረው ሆኖ የተመደበ ነው፡፡ ይህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ያለው ነው፡፡ መ.ሄኖክ 28፥17 ሀ. #ቀንን_በተመለከተ፡- “ቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ ቢኖር የዚህን ዓለም ብርሃን ያያልና አይሰናከልም… ” አላቸው፡፡ ዮሐ.11፥19 ቀኑና ሌሊቱም (24ቱ ሰዓት) አንድ ቀን ይባላል፡፡ “እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው ጨለማውንም ሌሊት አለው ማታም ሆነ ጧትም ሆነ አንድ ቀን”፡፡ ዘፍ.1፥5 ለ. #ሳምንታትን_በተመለከተ፡- ሰባት ቀናት ያሉት ነው፥“እግዚአብሔርም የሰራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፡፡… እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም…” ዘፍ.2፥2-4፣ኩፋሌ 17፥6፣ ሄኖክ 28 ፥17፣ ሄኖክ 26 ፥ 32፣ ሄኖክ 29፥18 “እርሱም ሶስት ኢዮቤልዩና አራት ሱባኤ ኖረ ይኸውም 175 ዓመት ነው፡፡” ኩፋሌ 17፥6፣ መ.ሄኖክ 28 ፥17 ሐ. #ወርን_በተመለከተ፡- አንድ ወር 30 ቀናት ያሉት ነው፡፡ መ.ሄኖክ 21፥15 “…በውኃውም ላይ ትመላለስ ነበር ውኃዎችም በምድር ላይ አምስት ወር ማለት መቶ ሃምሳ ቀን ጸንቶ ነበር፡፡” መ.ኩፋሌ 6፥32 “ዝናብም ከሰማይ ተከለከለ፣ ውኃውም ከምድር ላይ እያደር ቀለለ፣ ከመቶ ሃምሳ ቀን በኋላ ጎደለ” ዘፍ. 8፥3 💜 ይህንን ስሌት ስናሰላው 5 ወር መቶ ሃምሳ ቀን ከሆነ 1ወር ስንት ቀን ይሆናል 150 ፥ 5 = 30 ቀን ይሆናል ማለት ነው፡፡ አንድም ከአውታረ ፀሐይ ተገኝቷል፤ አውታረ ፀሐይ ስንት ነው ቢሉ? 9,900 ይህም ከምዕራብ-ምስራቅ = 6,600 እንደ ድር የተዘረጋ ሲሆን ቀሪው ፣ ከሰሜን እስከ ደቡብ = 3,300 እንደ ማግ የተዘረጋ ነው፤ ሥራውም እንደ ዓሣ መረብ እንደ አልጋ መረብረቢያ፣ እንደ ግርንግያ እንደ ቀሽመሪ ዓይነት ነው፡፡ ይህ 9,900 አውታረ ፀሐይ በሱባኤ ማለት በ70 ቢያካፍሉት 9,900፥ 70 = 141 ይደርስና ቀሪ 30 ይሆናል፤ ይህም የአንድ ወር የዕለት ብዛትን ያመለክታል፡፡ መ. ኢዮቤልዩን፡- አርባ ዘጠኝ ዓመት ሲሆን “ ሰባት ጊዜ ሰባት አድርገህ የዓመታትን ሰንበት ሰባት ቁጠር የሰባት ዓመታትን ሰንበት ዘመን አርባ ዘጠኝ ዓመት ትቆጥራለህ፡፡” ኦ.ዘሌ. 25፥8 ፣ መ.ኩፋሌ 7 ፥ 30-37፣ ዘጸ.34፥22 📖 “ኢዮቤል (ጽር፡ዮቢል፡፡ ዕብ፡ዮቤል)፤ የበግ ጠቦት ወጠጤ ተባት ቀንደ መለከት በዓለ ኀምሳ ከ፯ ሱባኤ ወይም ከ፵፱ ዓመት በኋላ ዐምሳኛው ዓመት ብዙ ጠቦት የሚሠዋበት ቀንደ መለከት የሚነፋበት ኦ.ዘሌ. 25፥1-13፡፡ ሲያበዛ ኢዮቤላት፣ ኢዮቤልዮን ኢዮቤልው፣ ኢዮቤልዎላት ይላል (ኩፋሌ)” ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገጽ 214 ♥ “የቀደሙ ሰዎች በሕይወት የሚኖሩበት ዘመኖች 19 ኢዮቤልዩ ነበሩ፡፡” ኩፋሌ 17፥6 = 19 x 49 = 931 ➣ የአዳም ዕድሜ በኢዮቤልዩ ሲሰፈር፥- አዳም በ19ኛው ኢዮቤልዩ በሰባተኛው ሱባኤ በስድስት ዓመት ሞተ፡፡ (18x19) + (6x7) + 6 = 930 ➣ አዳም ከሺህ ዓመት ሰባ አጎደሎ፡፡እንዲል ኩፋሌ 6፥2-4 🔁 በአጠቃላይ የዕለታት፣ የዓመታት የአውራኅና የዘመናት አቆጣጠር የተጀመረው በእግዚአብሔር ፍቃድ ከዓለም ፍጥረታት ጀምሮ እንጂ ሰዎች እንደፈለጉት በሥጋዌ ጥበብ፣ በግምትና በመላምት የሚወስኑት አለመሆኑን እንረዳለን፡፡ 🔶በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር (የጊዜ ቀመር) በአራት ወቅቶች የተከፈለ ነው፡፡ ፩. #ዘመነ_ክረምት (ከሰኔ 26 ቀን - መስከረም 25) ፡- ዘመኑ የአበባ ነው፡፡ ዘመነ ክረምት ማለት ዘመነ ውሃ ማለት ነውና በዚህ ዘመን ውኃ ይሰለጥናል፡፡ ውሃ አፈርን ያጥባል፣ እሳትን ያጠፋል፣ ቢሆንም በብሩህነቱ ከእሳት፣ በቀዝቃዛነቱ ከነፋስ፣ በእርጥብነቱ ከመሬት ጋር ተስማምቶ ይኖራል፡፡ ክረምት በውስጡ አራት ወራትን (ሐምሌ፣ ነሐሴ፣ ጳጉሜንና መስከረም) የያዘ ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ “ያረሁ ክረምተ በበዓመት፣ ይሰምዑ ቃሎ ደመናት፣ በየዓመቱ ክረምትን ያገባል፤ ደመናትም ቃሉን ይሰሙታል” ሲል በድጓው ገልጾታል፡፡ መ.ሄኖክ 28፥12-32፣ ዘካ.14፥8 ➣ናርኤል፡- ስመ ኮከብ፣ ዐቢይ፣ መጋቤ ክረምት ናር -እሳት፣ ብርሃን፤ ኤል አምላክ በተገናኝ ብርሃነ አምላክ ኪ.ወ.ክ. ገጽ 655 ➣ በዚህ ወቅት መዓልቱም ሌሊቱም እኩል እኩል 12 ሰዓት የሚሆኑበት ወቅት ነው፡፡ ፪. #ዘመነ_መፀው/መከር/ (ከመስከረም 26 ቀን - ታኅሣሥ 25) መፀው፡- ማለት መከር ጥቢ የፍሬ ወቅት ማለት ነው፡፡ ዘመኑ የነፋስ ነው፡፡ 💜 ምልክኤል፡- ስመ ኮከብ፣ ዐቢይ፣ መጋቤ መፀው ከአራቱ መራሕያን አንዱ እንዲል ኪ.ወ.ክ ገጽ 594 “በልባቸውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በጊዜው የሚሰጠውን ለመከርም የተመደቡትን ወራት የሚጠብቅልንን አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ አላሉም”። ኤር. 5፥24 💜 በዚህ ወቅት መዓልቱ ከ12 ሰዓት እያጠረ ሌሊቱ እየረዘመ የሚሄድበትና ከቀኑ ሦስት ሰዓት ትርፍ ይገኝበታል፡፡ “ግሩም በሆነው ኃይልህ እንመካ ዘንድ አንተ ዘመናትን ሠራህ ክረምትን ለዝናባት መፀውን ለአበቦች ሰጠህ” ቅዱስ ያሬድ ድጓ ዘጽጌ ኩፋሌ 2 ኢዮ.2÷23፣ ፫. #ዘመነ_በጋ/ሐጋይ/ (ከታኅሣሥ 26 ቀን - መጋቢት 25) “ክረምትና በጋን አንተ ሠራህ”፤ “በበጋም በክረምትም እንዲህ ይሆናል” መዝ.75፥17፣ ዘካ.14፥8፣ ዘፍ.10፥22 እንዲል ኃጋይ ማለት መገኛ መክረሚያ በጋ፣ ፀደይ፣ ደረቅ ወቅት ነው፡፡ 💜 በዚህ ወቅት መዓልቱም ሌሊቱም እኩል አስራ ሁለት (12) ሰዓት የሚሆኑበት ወቅት ነው፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 434 💜 ሕልመልሜሌክ - መጋቤ ሐጋይ 2ኛ ስሙ ፀሐይ ነው ምግብናው 91 ቀን ነው፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 445 ይ🀄️ጥላል

📖📚 #ትምህርተ_ባሕረ_ሐሳብ📚📖 💚💛❤️️ ክፍል ፱ 💚💛❤️ ✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✞ 📖 #የዘመን_አቆጣጠር_ስልት 📖 https://t.me/EOTC2921 💚 ስለ ዘመን ስንገልጽ በሦስት እንከፍለዋለን፤ (ያለፈው፣ ያለንበትና የሚመጣው) ዘመን ብለን እንናገራለን፡፡ በተጨማሪም ዓመት፣ ወር፣ ዕለት፣ ሰዓት፣ ኬክሮስ (ደቂቃ) በማለት ለአምስት ተከፍሎ ይገለጻል፡፡ አንድ ዕለት 24 ሰዓት ሲሆን ለሁለት ተከፍሎ መዓልትና ሌሊት በመባል ይታወቃል፡፡ የአቆጣጠር ልዩነት የሚጀምረው ከዕለት አቆጣጠር ሲሆን አንዳንዶቹ ፀሐይ ስትገባ ይጀምራሉ፡፡ መጨረሻውንም አንድ ጊዜ ስትገባ ያደርጋሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ከእኩለ ቀን ጀምረው በእኩለ ቀን ይጨርሳሉ፡፡ ሦስተኛው ዓይነት አቆጣጠር ያላቸው ደግሞ ፀሐይ ስትወጣ ጀምረው በመውጣቷ ይጨርሳሉ፡፡ #የወርና_የዓመት_አቆጣጠር ይህ አሰላል በሦስት ይከፈላል፦ ➣፩. ዓመቶቻቸውን በፀሐይ ☀️ ወሮቻቸውን በጨረቃ 🌙 የሚቆጥሩ ➣፪. ዓመቶቻቸውንም ወሮቻቸውንም በፀሐይ ☀️ ብቻ የሚቆጥሩ ➣፫. ዓመቶቻቸውንም ወሮቻቸውንም በጨረቃ 🌙 ብቻ የሚቆጥሩ ናቸው፡፡ #የዘመን_አቆጣጠር_ሥያሜና_መነሻ ⛪️ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስለ ዘመን አቆጣጠር የተለያዩ ስያሜዎች ተሰጥተዋል፡፡ እነዚህም ስያሜዎች የራሳቸው መነሻ ሐሳብ ያላቸው ሲሆኑ ዋናዋናዎቹ እንደሚከተሉት ተብራርተዋል፡፡ ፩. #ኀሳበ_ዘመን፡- የዘመናትን፣ የዓመታትን፣ የወራትን፣ የሣምንታትንና የዕለታትን አቆጣጠር የሚመለከት ነው፡፡ይህ አቆጣጠርበድርጊት የሚገለጽ ክንውን ሳይሆን በኀሳብ የሚቀመር ስሌት በመሆኑ ኀሳበ ዘመን ተብሎ ተሰይሟል፡፡ ፪. #ባሕረ_ሐሳብ፡- ይህ ስያሜ የስሌቱን ጥልቅነትና ስፋት በባሕር ምሳሌ ለመግለጽ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ ባሕር በተፈጥሮው ጥልቀትና ስፋት ያለው የውኃ አካል ነው፡፡ ያለ እውቀትና ስልት ቢገቡበት የሚያሰጥምና ሕይወትንም የሚያጠፋ ነው፡፡ እንዲሁም ሁሉ የዘመን አቆጣጠር ስልትም ጥልቀትና ስፋት ያለው ያለ እውቀትና ትምህርት ሊሞከርና ምስጢሩ ሊገለጽ የማይችል መሆኑን ለማጠየቅ በባሕር ምሳሌነት ተገልጾአል፡፡ ➛“ይህቺ ባሕር ታላቅና ሰፊ ናት” እንዲል መዝ.103፥25-27 ➛“ይህ ዓለም በሚዛን ተመዝኗልና ባሕርን በላዳን ሰፍሯልና ዘመኑም 8ሺህ ወስኖታልና የተሰጠው ዘመኑም እስኪፈጸም ድረስ ዝም ይላል አያልፍም” ዕዝራ ሱቱ.2፥36 ፫. #ዘመነ_ዓለም፡- የሰው ልጅ ዓለም አዳምን በሚመለከት ታሪክ የሚቀምረውን የዘመን አቆጣጠር ሲያይ የተሰጠው ስያሜ ነው፡፡ ዕዝ.ሱቱ. 13፥10-13 ፬. #አቡሻኽር፡- ይህ ስያሜ የኀሳበ ዘመን ትምህርትን ካዘጋጁ ሊቃውንት መካከል በአቤልሄረም ልጅ በዮሐንስ አቡሻክር (ጴጥሮስ መነኩሴ) በተባለ ግብጻዊ ሊቅ አማካኝነት የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ ➣አቡ ሻኽር (ዐረብ) ፤ ታላቅ፣ ስመጥር የቁጥር መጽሐፍ ብዙ ወግ ታሪክ ያለበት አበ ወርኅ፣ በዓለ ወርኅ፣ የጨረቃ ቁጥር ባለቤት መጽሐፉ የጸሐፊውን ቃል ስለያዘ በጸሐፊው ስም ይጠራል፡፡” ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገጽ 195 📚 መጽሐፈ አቡሻኽር መግቢያው ላይ እንዲህ ይላል፡- “አቡሻኽር የዘመናትን መለዋወጥ፣ የፕላኔትን አቀማመጥ፣ የፀሐይና የጨረቃን መመላለስ፣ አውታረ ፀሐይን፣ መሳክወ ፀሐይን፣ ምሕዋረ ከዋክብትን፣ የሚገልጥ እንዲሁም የዕለታትን የአውራኅን የዓመታትን የብታት መንገድ የሚያሳይ መጽሐፍ ነው፡፡ እንዲሁም የአጽዋማትን የበዓላትን መነሻና መድረሻ ማለትም ዘኢየዓርግንና ዘኢይወርድን ለይቶ የሚያሳይ መንገድ ነው፡፡ በጥንት ዘመን ግን ለሐሳበ ከዋክብት ሳይቀር መሥፈርያ መቁጠርያ መመርመሪያም ይኸው የቁጥር ትምህርት ነበር ” ፭. #የቁጥር_ትምህርት፦ በቤተ ክርስቲያን አንድን ትምህርት ከጠባዩ አንጻር ስያሜ መስጠት የተለመደ ነው፡፡ ለምሳሌ በቃል የሚጠኑና የሚዜሙ ትምህርቶች የቃል ትምህርት እንደሚባሉ ሁሉ መጻሕፍት ላይ ያተኮሩ ትምህርቶችም የመጻሕፍት ትምህርት ይባላሉ፡፡ የዘመን አቆጣጠር ትምህርትም ዘመናትን በመቁጠርና በማስላት የሚጠና በመሆኑ የቁጥር ትምህርት የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ ፮. #መርሐ_ዕውር፦ የዕውር መሪ፣ ዕውርን የሚመራ ዕውርን (ዐይነ ስውርን) እሾህ እንዳይወጋው፣ እንቅፋት እንዳይመታው፣ ባሕር ጠልቆ፣ ገደል ወድቆ እንዳይሞት መሪው ጠብቆና መርቶ ከቤት እንዲያደርሰው፣ የዘመን ቁጥርም ዐላዋቂውን ሰው (በቂ ዕውቀት የሌለውን ሰው) ሶከ ኃጢአት (የኃጢአት እሾህ) እንዳይወጋው እንቅፋተ ሥጋ እንቅፋተ ነፍስ እንዳያገኘው በባሕረ ኃጢአት ሰጥሞ በክህደት ወድቆ እንዳይሞት ጠብቆና መርቶ እንደ ነቢያት (ዳንኤልና ዕዝራ) አጽዋማት በዓላት የሚውሉበትን ወደ ማወቅ ያደርሰው ዘንድ ድሜጥሮስ ስለዘመን አቆጣጠር የደረሰው መጽሐፍ ስያሜ ነው፡፡ ⛪️ የኀሳበ ዘመን (የባሕረ ሐሳብ) አቆጣጠር በኢትዮጵያ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ700-660 ዓ.ዓ ጀምሮ እንደተለመደ በታሪክ ተዘግቧል፡፡ አቆጣጠሩም ✅ ከፋርሳውያን፣ ✅ ከይሁዳውያን (ከ፳ኤል) እና፣ ✅ ከግብጻውያን ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ይተረካል፡፡ #የኢትዮጵያ_ዘመን_አቆጣጠር_በሁለት_መሠረታዊ_ነገሮች_ላይ_ያተኮረ_ነው፡፡ ፩. #ወቅቶች:- ኢትዮጵያውያን አባቶች ወቅቶችን መሠረት አድርገው ከሰሩባቸው አንዱ ዘመን አከፋፈላቸው ነው፡፡ይህም ድርጊታቸው በቅዱሳት መጻሕፍት ጥልቅ ዕውቀት የነበራቸው መሆናቸውን ያስመሰክርላቸዋል፡፡ ነቢያተ እግዚአብሔር፣ ቅዱሳን ሐዋርያትና ጌታም ራሱ ወቅቶችን መሠረት አድርገው ብዙ ተናግረዋል፡፡ ምሳሌ:- 1⃣ሄኖክ፡- መ.ሄኖክ 28 ፥26 2⃣ሙሴ፡- በምድር ዘመን ሁሉ መዝራትና ማጨድ፥ ብርድና ሙቀት፥ በጋና ክረምት፥ ቀንና ሌሊት አያቋርጡም፡፡ ዘፍ.8፥22፣ እግዚአብሔርም ለምድርህ በወራቱ ዝናብ ይሰጥ ዘንድ፥ የእጅህንም ሥራ ሁሉ ይባርክ ዘንድ መልካሙን መዝገብ ሰማዩን ይከፍትልሃል ለብዙ አሕዝብም ታበድራለህ፥ አንተ ግን ከማንም አትበደርም። ዘዳ.28፥12-13

ገብርኤል ስለው.m4a8.76 KB

#ገብርኤል_ማን_ነው? 🌾🌾🌾🙏🙏🙏🌾🌾🌾 #ገብርኤል ማለት “ እግዚእ ወገብር” - የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው። ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው መላእክትም “ መኑ ፈጠረነ፡ ማን ፈጠረን ” ሲሉ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹ ጊዜ “ የፈጠረንን አምላካችን እስክናውቅ በያለንበት ጸንተን እንቁም ” ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ ነው። በዚህም ምክንያት ጌታ “ በእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም ” እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል። ከዚህም በኋላ ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል።ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘንድ ይወደዳል፡፡ ምክንያቱም ያዘኑትን ለማጽናናት የምሥራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካልና፡፡ #ይህ_ቅዱስ_ገብርኤል_ነው ሳጥናኤል ሥላሴን በካደ ጊዜ መላእክትን በቃሉ ያጽናናቸው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ 👉*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡* ዳንኤልን ከአናብስት ያዳነው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነቸው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ወደ ዘካርያስ የተላከ የዮሐንስን ልደት ያበሰረ 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ 👉*ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡* ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ሰብአ ሰገልን በኮከብ ምልክት የመራቸው 👉*ይህ ገብርኤል ነው፡፡* ድንግል ማርያምና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ 👉* ይህ ገብርኤል ነው፡፡* የብርሃን ራስ ወርቅ የተቀዳጀ 👉*ገብርኤል ነው፡፡* የአሸናፊና የኃይል መልአክ *ገብርኤል ነው፡፡* ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ *ገብርኤል ነው፡፡ 🙏"የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃና ረድኤት አይለየን"🙏 ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ @EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

ከመከፈቱ የብዙዎች ቀልብ የሳበው ማህሌት ቲዩብ እሆ አስተማሪ በሆኑ ቪዲዮዎች መቶልናል። በቻናሉም ◽️መንፈሳዊ ጥያቄዎች ✅ ◽️መዝሙሮች✅ ◽️ገድላት✅ ◽️ታሪኮች✅ 🔖 ሁሉንም በአንድ ላይ በ ማህሌት ቲዩብ ያገኛሉ ይቀላቀሉን። ቻናላችንንsubscribe በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ። ከትላልቅ መንፈሳዊ መፅሀፍት የተወጣጡ ጥያቄዎች የሚጠየቁበት እንዲሁም ተሳትፎ የሚደረግበት መንፈሳዊ ቻናል ለመቀላቀል ከፈለጉ።👇 ||Open Open Open|| ||Open Open Open|| ▫️በአስተማሪነቱ ተወዳጅነትን ያገኘው #መፅሐፍቅዱሳዊጥያቄዎች የተሠኘው መንፈሳዊ ቻናል እንድትቀላቀሉ በልዑል እግዚአብሔርም ስም እንጠይቃለን ። || Join Join Join Join || || Join Join Join Join || || Join Join Join Join ||

📙 ቅዱሳት መጻሕፍትን በ PDF እና መንፈሳዊ መተግበሪያዎችን እንዴት ላግኝ ወይስ ከየት ላምጣ ብለው ፈልገው ያውቃሉ 🤔🤔 በ👉 https://t.me/joinchat/AAAAAFkIxjZXhdZg59k2Nw ቻናል አዳዲስና ቆየት ያሉ PDF መጽሐፍቶችን እንዱሁም የብራና መጽፍቶችንና መተግበሪያዎችን ያቀርባል! ይቀላቀሉ👇👇 👉 https://t.me/joinchat/AAAAAFkIxjZXhdZg59k2Nw ▰▰▰ #አገልግሎቱን_ለመደገፍ ከታች ያለውን Link ተጭነው Youtube ቻናሉን Subscribe ያድርጉ ለሌሎችም Share ያድርጉ!! 👇 https://www.youtube.com/channel/UCDFE-5zWnDAIS8UxfM8RAdA https://youtu.be/SY-D-qGgT0U https://youtu.be/SY-D-qGgT0U 👆SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ! 👇የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ቻናሎች ናቸው። 👇👇 ይቀላቀሉ 👇👇

#ባሕረ_ሐሳብን_ማን_ይማረው? 💚 ባሕረ ሐሳብን ሁሉም ሰው ካህኑም፣ ክርስቲያኑም፣ መነኩሴውም ሊማረው ይገባል። ከሀገሩ ተሰዶ ተማርኮ አሕዛብ ሀገር ቢሄድ እንኳን ጾም አይገድፍም፣ በዓል አይሽርም፡፡ ምክንያቱም አጽዋማት የሚገቡበትን በዓላት የሚውሉበትን ተምሯልና፡፡ በተለይም ካህናት የመማር ግዴታ አለባቸው። እንደውም ባሕረ ሐሳብን ያልተማረና የማያውቅ ካህን በደረቅ ወንዝ፣ ሰው በሌለው መንደር እንደሚመሰል አባቶች ያስተምራሉ። ባሕረ ሐሳብን የማያውቅ ካህን በደረቅ ወንዝ እንደሚመሰል ለማሳየት፦ “ካህን ዘኢየዓምር ሐሳበ ባሕር ይመስል ከመ ፈለግ ዘአልቦ ማይ ውስቴቱ- ባሕረ ሐሳብን የማያውቅ ካህን ደረቅ ወንዝን ይመስላል” እንዲል፤ ለምን ቢሉ ደረቅ ወንዝ ነጋድያን (በእግራቸው ሄደው የሚነግዱ) ከሩቅ ሆነው ወንዝ ባዩ ጊዜ የዛፉን ፍሬ ለምለሙን መስክ አሻግረው አይተው ተደስተው “ወደ ወንዙ ሄደን፣ ጥቂት አርፈን፣ ጥሬ ቆርጥመን፣ ጠል ነስትን፣ ውሃ ተጎንጭተን እንነሳ” ብለው ይሄዳሉ፡፡ ወንዙ ጋር ደርሰው ውሃ ሲያጡበት አፍረውና ተሳቀው ይመለሳሉ። ሰው የሌለው ሀገርም እንደዚሁ እንግዶቹ መንደሩን አይተው ከዚያ አድረን እንሄዳለን ብለው ከዚያ ሲደርሱ ሰው ባጡበት ጊዜ ተሳቅቀው ይሄዳሉ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ምዕመናን ካህንን በሩቅ ሆነው ጠምጥሞ፣ አምሞ፣ መነሳነሱን ይዞ፣ ቀሚሱን አንጽቶ ሲሄድ ባዩት ጊዜ ምዕመናን ወደ እርሱ ሄደው በዓላትን አውጥቶ አጽዋማትን ለይቶ እዲነግራቸው በጠየቁት ጊዜ ሞያ ባጡበት ጊዜ አፍረውና ተሳቀው ይመለሳሉ። ስለዚህ ካህን በዓላትን አውጥቶ አጽዋማትን ለይቶ ለመናገርና ለምዕመናን ለማሰተማር ይችል ዘንድ ባሕረ ሐሳብን ሊማር ይገባዋል። 💛 ከዚህም በተጨማሪ እያንዳንዱ ቀንና ሌሊቱ የራሱ የሆነ ቁጥር አለው። ማለትም ዛሬ ቀኑ ይሄን ያህል ነው ስንል ለምሳሌ ዛሬ ነሐሴ አንድ ነው ስንል ይህ አቆጣጠር በፀሐይ ዑደት (ዙረት) የሚገኝ ነው። ነገር ግን በዚህን ቀን ያደረው ሌሊቱ ከቀኑ ጋር እኩል አይደለም፡፡ ምክንያቱም የሌሊቱ አቆጣጠር የሚገኘው በጨረቃ ዑደት ነው። ስለዚህ ሌሊቱ የሚገኘው ዕለቱ ከአበቅቴና ከሕጸጽ ጋር ተደምሮ ነው። (ይህንን ወደፊት በስፋት የምናየው ይሆናል) ስለዚህ ካህኑ ጸሎት ሲያደርግ (ሲያሠርቅ) ዕለቱን፣ ሌሊቱን እና ጨረቃውን በማንሳት ማሥረቅ ይኖርበታል፤ ለዚህ ደግሞ ባሕረ ሐሳብ ማወቅ ይኖርበታል። ❤️ እንዲሁም ምዕመናን ባሕረ ሐሳብን ሊማሩና ሊያውቁ ይገባል። ምክንያቱም ምዕመናን የሚያንሱበት ዓላውያን የሚበዙበት ዘመን ይመጣል። አልፎም በስደት ወደ ባዕድ ሀገር መሄድ ይኖራል። በዚህን ጊዜ በዓላትን አውጥቶ አጽዋምትን ለይቶ የሚነግር ካህን ማግኘት አይቻልም። በዚህን ጊዜ በዓላትን አውጥቶ ለማክበር አጽዋማትን ለይቶ ለመጾም ይቻል ዘንድ እያንዳንዱ ምዕመን ባሕረ ሀሳብን ማወቅ ይኖርበታል፤ እንዲያውቅም ይመከራል። በተጨማሪም ባሕረ ሐሳብን ስንመለከተው ከምንጠብቀው በላይ የሚያስደስትና ቤተ ክርስቲያኒቱንም ሆነ ሀገራችንን የሚያኮራ የጥበብ ትምህርት ነው። ይህንን በሂደት ከሚከተሉት ተከታታይ ጽሁፎች የምንመለከተው ይሆናል። የራሱ የሆነ ቀመር ያለው፤ እንዲሁም የአበው ሊቃውንት ስሌት በዘመናዊ የሂሳብ ስሌት እተቀየረ እና እየተሰራ አሁንም ጭምር በማደግ ላይ ነው። አንድ ነገር በሂደት ውስጥ ካለ ዘመናዊ የመሆኑ መገለጫ ነው። ስለዚህ ይህንን የቤተ ክርስቲያን ሀብት እና የሀገር ኩራት የሆነውን ትምህርት ወጣቱ ትውልድ ተምሮና አውቆ ለሌላው በማስተማር ለተተኪ ትውልድ የማስተላለፍ ኃላፊነትና ግዴታ አለበት። #የዘመን_አቆጣጠር_ትርጓሜና_ሥያሜ 💚 የዘመን አቀቆጣጠር ማለት የጊዜ መስፈሪያዎችን በማደራጀት ለረጅም ዘመናት የተዘረጋውን የጊዜ መጠን ለመቁጠር ወይም ለመለካት የተዘጋጀ ዘዴ (ደንብ) ነው፡፡ በዚህ ትርጓሜ መሠረት በርካታ የዘመን አቆጣጠር ስልቶች ያሉ ሲሆን እኩሌቶቹ ስነ ፈለካዊ ባልሆነ ረቂቅ ዘላቂና የማይቋረጥ የድግግሞሽ ክበብን መሠረት ያደረጉ ናቸው፡፡ በየትኛውም የዘመን አቆጣጠር ስልት ትንሹ የዘመን መስፈሪያ ቀን ቢሆንም ለራሱ የጊዜ መክፈያና መጠበቂያ የሚሆኑ ኬክሮስ፣ ካልዒት፣ ሣልሲት፣ ራብዒት፣ ኃምሲት፣ ሳድሲት፣ ሰከንድ፣ ደቂቃ፣ ሰዓት የሚባሉ ጓዞች ይኖሩታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቀናት እርስ በእርስ በመደመር የጊዜ መግለጫ (መለኪያ) የሚሆኑ ሳምንት፣ ወር፣ ሱባኤና ኢዮቤልዩ የሚባሉ የዕለታትና የዓመታት መስፈሪያዎች አሉ፡፡ በእነዚህ መስፈሪያዎች ዘመን የሚባለው ድርጊት (ስሌት) ይገኛል፡፡ ➛ ለምሳሌ፡- የአዳም ዕድሜ በኢዮቤልዩ ሲሰፈር፡- አዳም በ19ኛው ኢዮቤልዩ በሰባተኛው ሱባኤ በስድስት ዓመት ሞተ፡፡ (18x19) + (6x7) + 6 = 930 ➛ አዳም ከሺህ ዓመት ሰባ አጎደለ፡፡ እንዲል ኩፋሌ 6፥2-4፣ ➛ ምሳሌ 2፡- “… እርሱም (አብርሃም) ሦስት ኢዮቤልዩና አራት ሱባኤ ኖረ ይኀውም አንድ መቶ ሰባ አምስት ዓመት ነው” ኩፋሌ 17፥6፣ ዘፍ.25፥7 = (3 x 49) + (4 x 7) = 175 = 147 + 28 = 175 ይህም አብርሃም በሕይወት የቆየበት ዘመን ነው፡፡ ኩፋሌ 17፥6፣ ዘፍ.25፥7 ➣ ለዘመንና ለጓዞች መሠረት የሆኑት ደግሞ ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ናቸው፡፡ ለዚህም መጽሐፍ ቅዱስ “እግዚአብሔርም አለ፦ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ብርሃናት ይሁኑ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ። እግዚአብሔርም በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር አኖራቸው፡፡” ዘፍ. 1፥14-17 ◀⚫✞ ይቆየን ✞⚫▶ ይ🀄️ጥላል ✞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን አስተምሮና ስርዓት የጠበቁ የተለያዩ መርሃ ግብሮች በየቀኑ ወደ እርስዎ ይቀርባሉ፡፡ ለወዳጅዎ #Share በመድረግ የበረከት ተካፋይ ያድርጓቸው ✞ ╭══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╮ https://t.me/EOTC2921 ╰══•|❀:๑✞♡✞๑:❀|•══╯

📖📚 #ትምህርተ_ባሕረ_ሐሳብ📚📖 💚💛❤️ ክፍል ፰ 💚💛❤️ ✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✞ https://t.me/EOTC2921 💠 እግዚአብሔር የፈጠረውን ሰው ተናግሮ ባልፈጸመው ነበር፡፡ ነገር ግን ብዙውን አንድ ብዙውን አንድ እያሉ በየወገኑ ቢቆጥሩ ከእሁድ እስከ ዐርብ ያዘጋጀው ፍጥረት 22 ይሆናል። እስከዚህ አርዕስት ነው፡፡ ይህ ዓለም የተፈጠረበት ዕለተ እሑድ- ጥንተ ዕለት ይባላል እጽዋት አዝዕርት አትክልት የተፈጠሩበት ዕለተ ሠሉስ ጥንተ ቀመር ፀሐይ ጨረቃ ከዋክብት የተፈጠሩበት ዕለተ ረቡዕ ጥንተ ዮን ይባላል፡፡ አዳምን በፈጠረው በ40 ቀን በመንፈስ ቅዱስ አክብሮ ገነት አገባው ገነት ካገባው በኋላ ከአንዲት ዕፅ በቀር ሁሉን ብላ ሁሉን ግዛ አለው፡፡ገነት በገባ በ7 ዓመቱ ያችን ዕፅ ቢበላ ከገነት አወጣው፡፡ እርሱም ለባዊ ነውና ደንግጦ ንስሀ ገባ ቸር አምላክ ንስሀውን አይቶ ከ5 ቀን ተኩል (5500) ዘመን በኋላ ሥጋ ለብሼ አድንሀለሁ ብሎ ተስፋ ሰጠው፡፡ መ.ሲራ. 24፥6 የሰጠውንም ተስፋ ለልጆቹ ነገራቸው እኩሉ በፀሐይ፣ እኩሉ በጨረቃ፣ እኩሉ በከዋክብት መቁጠር ጀመሩ፡፡ ቁጥር መቁጠር የተጀመረበት ምክንያት ይህ ነው፡፡ 💚 ከዚህ በኋላ ዘመነ ሥጋዌ ሲደርስ ከሰማየ ሰማያት ወረደ ከድንግል ማርያም ተወለደ በዚህ ዓለም የሰውነትን ሥራ ሲሰራ እስከ 30 ዓመት ከቆየ በኋላ ወደ ገዳመ ቆሮንጦስ ገብቶ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከጾመ በኋላ ወደ ምድረ እስራኤል ገብቶ ማስተማር ሲጀምር የቃሉን ትምህርት የእጁን ተዓምራት አይተው ከ8 አህጉር የአምስት ገበያ ሕዝብ ተከተለው፡፡ እነዚህን አስከትሎ 3 ዓመት ከ3ወር ሕገ ወንጌልን ከአስተማረ በኋላ አይሁድ በመስቀል ሰቅለው ገደሉት፡፡ ከዚህ በኋላ በሞቱ ዓለምን አድኖ በ3ኛው ቀን ተነሳ በተነሳ በ40ኛው ቀን ዐረገ ፣በዐረገም በ10ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ለ120ው ቤተሰብ ላከላቸው፡፡ ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ በኢየሩሳሌም ዓመት ኖሩ ያን ጊዜ ከሕዝቡ ጋር ጾመ 40ን መጾም ትንሣኤን ማክበር ጀመሩ፡፡ 💛 ሲጾሙ ግን ጥንተ በዓሉን ጥንተ ጾሙን ለወጡ እንደምን? ቢሉ ጌታችን 40 መዓልት 40 ሌሊት ምንም ሳይቀምስ ጾሞ የነበረ ሲሆን 40 መዓልት 40 ሌሊት ሥጋ ቅቤ ወይን አንቅመስ እንጂ እየዋልን እህል ውኃ ብንቀምስ ዕዳ አይሆንብንም አሉ፡፡ ጾመ 40ም በጥር 11 ቀን ማክሰኞ ተጀምሮ የነበረ ከሰኞ አይውጣ እንጂ በየካቲት በመጋቢትም ይሁን አሉ፡፡ ተለይቶ የነበረ ከስሙነ ሕማማት ጋር ይያያዝ አሉ፡፡ ትንሣኤም በመጋቢት 29 ተጀምሮ የነበር ከእሑድ አይውጣ እንጂ በሚያዚያም ይሁን አሉ፡፡ አቆጣጠሩን ግን ለስብከተ ወንጌል ይፋጠኑ ስለነበር ለይተው አላተማሩም፡፡ ከዚህ የተነሳ ሳዊሮስ ዘእስሙናይን እንደተናገረ ከሐዋርያት ከ72ቱ አርድዕት በኋላ የተነሱ መምህራን ቁጥር ቢጠፋባቸው ጊዜ ጥንተ ጾሙን ቢሹ በዓለ ጥምቀት ፍጻሜውን ቢሹ የካቲት 20 ሆነባቸው ስለ በዓሉ ፈንታ ድራረ (ዋዜማ) ጥምቀትን ጹመው ከጥምቀት በኋላ 39 ቀን ጾሙ በመካከሉም በዓል ሳይሉ ከጾሙ አረፉ ከአረፉ በኋላ ስሙነ ሕማማትን ጹመው ጥንተ በዓሉን ቢሹ በመጋቢት 29 ቀን ትንሣኤን አከበሩ ይህም ሥርዓት ሲያያዝ እስከ ድሜጥሮስ ደረሰ፡፡ #ባሕረ_ሐሳብ_ምን_ማለት_ነው? 💜 ባሕረ ሐሳብ ማለት “ቁጥር ያለው ዘመን” ማለት ነው፡፡ ባሕሩን ዘመን ሲል “እስመ በመዳልው ደለወ ዓለመ ወበመስፈርት ሠፈራ ለባሕር” እንዲል ዓለምን በመቁጠሪያ ቆጠረ ባሕርንም በመስፊያ ሰፈራት (ለካት) እንዳለ “ይህ ዓለም በሚዛን ተመዝኗልና ባሕርን በላዳን ሰፍሯልና ዘመኑም 8ሺህ ወስኖታልና የተሰጠው ዘመኑም እስኪፈጸም ድረስ ዝም ይላል አያልፍም” ዕዝ.ሱቱ.2፥36 💙 ባሕረ ሐሳብ ከሁለት የግስ ቃል የተገኘ ሲሆን ይኸውም ባሕር እና ሓሳብ ይባላሉ። ባሕር ማለት ዘመን ማለት ሲሆን በሁለት ምክንያቶች ባሕር ዘመን ተብሏል። ባሕርን ዘመን ሲለው "በመዳልው ደለወ ዓለመ ወበመስፈርት ሰፈራ ለባሕር” ይላል። ይኸውም ባሕር ምንም ያህል ሰፊ ቢሆንም ጊዜ ይወስዳል እንጂ ልስፈረው ብሎ የተነሳ ሰው ይሰፍረዋል። እንዲሁም ሁሉ ዘመን እጅግ ብዙ እና ሰፊ ነው። ይሁን እንጂ በአዕዋዳት ይታወዳል በቀመር ይቀመራል። ስለዚህ ዘመንን ባሕር ይለዋል። ሌላው ባሕር እጅግ ሰፊና ምጡቅ የሆነ ነገር ነው ። ባሕረ ሀሳብም በውስጡ እጅግ ሰፊ የሆነና ምጡቅ የሆነ ትምህርትና እውቀት ያየዘ ነው። ስለዚህ ዘመን ባሕር ተብሏል። ስለምን ባሕርን ዘመን አለው? ቢሉ፡- ባሕር ከነቅዑ ወጥቶ ቢፈስ አያልቅም፣ ዘመንም ምጽአተ ክርስቶስ እስኪያግደው ድረስ ሰውን እያሳለፈ ሲመላለስ ይኖራል፡፡ 💚 አንድም ከባሕር ሁከት እንዳይታጣ፣ ከዘመንም ሁከተ ሥጋ ሁከተ ነፍስ አይታጣምና፡፡ አንድም ከባሕር ማዕበለ ሞገድ እንዲነሣሣ ከዘመንም ማዕበለ ኃጢአት ማዕበለ፣ ክህደት ይነሳልና፡፡ መልሕቅ ጥለው፣ ዓላማ ተከትለው የባሕር ሁከቱን ማዕበለ ሞገዱን ፀጥ እንዲያደርጉት፣ የዘመንንም ሁከተ ሥጋ ሁከተ ነፍስ ማዕበለ ኃጢአት ማዕበለ ክህደት ጹመው ጸልየው ምህላ ይዘው ፀጥ ያደርጉታልና፡፡ 💛 አንድም ባሕረ ሐሳብ ባለው መርሐ ዕውር የሚል አብነት ይገኛል፡፡ የዕውር መሪ፣ ዕውርን የሚመራ ማለት ነው፡፡ ዕውርን (ዐይነ ስውርን) እሾህ እንዳይወጋው፣ እንቅፋት እንዳይመታው፣ ባሕር ጠልቆ ገደል ወድቆ እንዳይሞት መሪው ጠብቆና መርቶ ከቤት እንዲያደርሰው፣ የዘመን ቁጥርም አላዋቂውን ሰው ሶከ ኃጢአት (የኃጢአት እሾህ) እንዳይወጋው እንቅፍተ ሥጋ እንቅፍተ ነፍስ እንዳያገኘው፣ በባሕረ ኃጢአት ሰጥሞ በክህደት ወድቆ እንዳይሞት ጠብቆና መርቶ እንደ ነቢያት (ዳንኤልና ዕዝራ) አጽዋማት በዓላት የሚውሉበትን ወደ ማወቅ ያደርሰዋልና፡፡ ❤️ ሐሳብ ማለት ደግሞ ቁጥር ማለት ነው። ሐሳብን ቁጥር ሲለው ‘’ኢትትሀሰብዎሙ ወርቆሙ ወብሩሮሙ ወለጽድቅከኒ አልቦቱ ሐሳብ- ለጽድቅህ ቁጥር የለውም’’ ማለት ነው። እንዲሁም “ብጹዓን እለ ተሓድገ ሎሙ ኃጢዓቶሙ ወእለ ኢሓሰበ ሎሙ ኩሉ ጌጋዮሙ -- ኃጢአቱ ያልተቆጠረበት ሰው ምስጉን ነው” ይላል። 💟 በአንድ ላይ ባሕረ ሐሳብ ማለት ቁጠር ያለው ዘመን ማለት ነው። ➣ አንድም ሐሳበ ዘመንም ይባላል ይኸውም የዘመን ቁጥር ማለት ነው። ➣ ባሕረ ሐሳብ ማለት ቁጥር ያለው ዘመን ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽም የሐሳብ ባሕር ማለት ነው፡፡ በዓላት እና አጽዋማትን ለማውጣት የመደመር፣ የመቀነስ፣ የማባዛት ስሌትን ብቻ ሳይሆን ሐሳበ ፀሐይን፣ ሐሳበ ወርኅን፣ ሐሳበ ከዋክብትን ፣ ሐሳበ ዐበቅቴን አጠቃሎ የያዘ እንደ ባሕር የሰፋ በመሆኑ የሐሳብ ባሕር ተብሏል፡፡ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገጽ 261 #ዘመን_አቈጣጠር፦ ማለት ስለማሕበራዊ ኑሮ ጠቄሜታና የሃይማኖት ተግባሮች ለማከናወን በሚያገለግል መልኩ ተፈጥሮአዊውን የወቅቶች ክፍፍል እርስ በርሳቸው የማመቻቸት ዘዴ ነው፡፡ ሐሳበ ዘመን የዘመን አቆጣጠር ማለት ሲሆን የሐሳበ ዘመን ትምህርት ባሕረ ሐሳብ ይባላል፡፡ ↪️ ባሕረ ሐሳብ የሚለው ቃል ሐሰበ ቆጠረ ከሚለው ግስ የወጣ ዘመድ ዘር ነው፡፡ ስለዚህ ባሕረ ሐሳብ ማለት ቁጥር ያለው ዘመን ወይም ዓመተ ዓለም ማለት ነው፡፡ ባሕረ ሐሳብ መባሉም የባሕር አዝዋሪቱ፣ መንገዱን፣ ጥልቀቱና ስፋቱ ረዥምና ሰፊ እንደሆነ የባሕረ ሐሳብ ትምህርትም መንገዱን ስፋቱ ልዩ ልዩ በሆነ የአጽዋማትና የሱባዔያት ምሥጢር የተሰናዳ ስለሆነ ነው፡፡ ዕዝ.ሱቱ. 2፥46 ይ🀄️ጥላል