cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

🇪🇹 Ethio Students Text Book And News grade 1 - 12 University 🎓

📚ከ 1_12 ክፍል የተማሪና የአስተማሪ መጽሀፍትን PDF ያገኛሉ አዳዲስ የትምህርት መረጃንም እንዲሁ እናጋራችሁሀለን። YOU TUBE :- https://www.youtube.com/channel/UCZuIXbtTfzfV10GsiwFo1vQ?sub_confirmation=1 በዚህ ቻናል ላይ ያጣችሁት መጽሀፍ ካለ በ @Ethio_student_ASTYAYTE በመቀላቀል አስተያየትና መጽሀፍት ማግኘት ይችላሉ።

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
9 041
Suscriptores
-824 horas
-567 días
-15130 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
#remediyal_result Is there any one ? If you are not see your result i can send your result privately send me your registered numbers 👍
Mostrar todo...
👍 1😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
የ2016 ሀገር አቀፉ የሬሜዲያል ፈተና ይፋ ተደርጎ ተማሪዎች በኦንላይን ውጤታቸውን በመመልከት ላይ ይገኛሉ። ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ነው እየተመለከቱ ያሉት። ድረገጹ በተመሳሳይ ጊዜ ብዙ ተማሪዎች እየሞከሩት ስለሆነ ከፍተኛ መጨናነቅ አለ።
Mostrar todo...
👍 2
#Update የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ውጤት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልኳል። የተማሪዎቹ ውጤት ዛሬ ለተቋማቱ መላኩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አረጋግጧል። በዚህም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ውጤት ከዛሬ ጀምሮ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። የዘንድሮው የመውጫ ፈተና ለ57 የመንግሥት እና ለ124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በ244 የቅድመ ምረቃ መርሐግብሮች መሰጠቱ ይታወቃል።
Mostrar todo...
👍 1
የ2016ዓ.ም የፋርማሲ የመዉጫ ፈተና (Exit Exam) ለተፈተናችሁ ተማሪዎች በሙሉ ……………………………………………. ከሰኔ 14 እስከ 19 ቀን 2016 ዓ. ም በ 244 ፕሮግራሞች በ57 የመንግስትና በ124 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለነበሩ ተማሪዎች የመዉጫ ፈተና ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ለስድስት ቀናት ያለምንም እንከን የተሰጠው ፈተና ያለምንም እንከን የተጠናቀቀ ሲሆን ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የተሰጠዉ የፋርማሲ ፈተና ብቻ የቴክኒክ ችግር አጋጥሞታል። ስለሆነው ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎቹ ፈተናውን በድጋሜ እንዲወስዱ አመቻችቷል። በዚሁ መሰረት ፈተናው በድጋሜ ቅዳሜ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት ከ 3:00 ሰአት ጀምሮ እና ከሰአት ከ 8:00 ሰአት ጀምሮ ስለሚሰጥ ለፈተናው ተቀምጣችሁ የነበራችሁ የፋርማሲ ተማሪዎች በተፈተናችሁበት የፈተና ጣቢያ በሰዓቱ በመገኘት በድጋሜ የሚሰጠውን ፈተና እንድትወስዱ እናሳስባለን፡፡
Mostrar todo...
#Update የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና እና የሪሚዲያል ማጠቃለያ ፈተና ውጤቶች መቼ ይፋ ይደረጋሉ? የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተናቸውን ሰኔ 11/2016 ዓ.ም ማጠናቀቃቸው ይታወቃል፡፡ በተመሳሳይ የ2016 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ትናንት ሰኔ 19/2016 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡ የፈተናዎቹ ውጤት መቼ ይፋ እንደሚደረግ አንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራርን ጠይቀናል፡፡ የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ውጤት ከሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት ይፋ እንደሚደረግ ኃላፊው ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል። በጣም ከዘገየ እስከ ሰኞ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ይፋ ይሆናል ብለዋል፡፡ የመውጫ ፈተና ውጤት በቀጣይ ቀናት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ማስመረቅ ከመጀመራቸው በፊት ይፋ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡ source tikva https://t.me/Ethio_Student_Textbook_And_News https://t.me/Ethio_Student_Textbook_And_News
Mostrar todo...
#ETQRA የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ለ2017 የትምህርት ዘመን በከተማዋ ምዝገባ ማከናወን የተፈቀደላቸው አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል። በአዲስ አበባ ለ2017 የትምህርት ዘመን የተቀመጡ መስፈርቶችን አሟልተው ምዝገባ ማከናወን የተፈቀደላቸው 125 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መሆናቸውን ባለስልጣኑ ገልጿል።
Mostrar todo...
👍 4
ላልጀመራቹ ትንሽ ሳምንታት ነው የቀረው ኮምቦ በመሰብሰብና ፕሮፊት ፐር ሀወር በማሳደግ መስራት ትችላላችሁ😊👍 😁 NOT coin ያየ ጥቅሙ ይገባዋል ለመጀመር ለመጀመር ሊንኩን በመጫን ወደ ቦቱ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/hamster_koMbat_bot/start?startapp=kentId1160061225
Mostrar todo...
Hamster Kombat

Just for you, we have developed an unrealistically cool application in the clicker genre, and no hamster was harmed! Perform simple tasks that take very little time and get the opportunity to earn money!

#ይነበብ ❗️ለተመራቂ ተማሪዎች❗️ ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመራቸው ስራዎች አንዱ የሆነ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከዛሬ ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ/ም ይጀምራል። ለመሆኑ በዚህ ፈተና ወቅት ከተማሪዎች እንዲሁም ከፈታኞች ምን ይጠበቃል ? [ ከተፈታኞች የሚጠበቅ ] - ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍል ሲመጡ ማንኛውም አይነት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት ፣ ላፕቶፕና ... ወዘተ ተመሳሳይ ኤክትሮኒክ ቁሳቁስ መያዝ በፍፁም የተከለከለ ነው።  (ይዞ የተገኘ ፈተናው /ውጤቱ ተሰርዞበት በቀጣይ ጊዜ እንዲቀመጥ ይደርጋል) - ፈተና ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት መፈተኛ ክፍል መገኘት አለባቸው ይህም ማለት ከጥዋቱ 2፡00 በፊት ፤ ከሰዓት ደግሞ ከ8፡00 በፊት ተፈታኞች መገኘት አለባቸው። - ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ID መያዝ ያለባቸው ሲሆን User Name እና Password lower-case and upper-case ፊደላትን ለይተው በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው። - ተፈታኞች ፈተና ከተጀመረ በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ከፈተናው ክፍል መውጣት የለባቸውም። - ተፈታኞች ፤ ፈተናውን የሚያስፈትኑ መምህራን በሚያሳዩት ቦታ ብቻ መቀመጥ አለባቸው። - ሁሉም ተፈታኝ እንዲቀመጥ የተመደበበት የራሱ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተቀምጦ መክፈትና መጠቀም አለበት። - በፈተና ክፍል ውስጥ መነጋገር እና ከቦታ ቦታ መዘዋወር በፍፁም የተከለከለ ነው። እንዲሁም ማንኛውም ተፈታኝ ከጎኑ ያለውን ተማሪ ኮምፒውተር በፍፁም ማየት የለበትም። - ምንም ዓይነት ወረቀት ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መምጣት አይቻልም። - ተፈታኞች በምንም ሁኔታ መኮርጅም ሆነ ማስኮርጅ ተግባር ላይ ቢሳተፉ እርምጃ ይወሰድባቸዋል። - ሁሉም ተፈታኞሽ ለፈታኝ መምህራንና ለአስተባባሪዎች  መታዘዝ ያለባቸው ሲሆን የፈተናው ደንብ እና ስርዓት ተገዢ መሆን ይጠበቅባቸዋል። NB. ሁሉም ተፈታኞች ወደ መፈኛ ክፍል ተፈትሸው እንዲገቡ የሚደረግ ሲሆን ማንኛውም ተፈታኝ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በፍተሻ ወቅት ይሁን ሥርዓት ለማስያዝ በሚደረግ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኖ ከተገኘ ከመፈተኛ አከባቢ እንዲገለል ተደርጎ በቀጣዩ የመውጫ ፈተና መስጫ ወቅት እንዲቀመጥ ይፈቀድለታል። [ ከፈታኝ መምህራን የሚጠበቅ ] - የተፈታኝ ተማሪዎችን ID በአግባቡ በማረጋገጥ ወደ ክፍል እንዲገቡ ማደረግ ይጠበቅባቸዋል። - ተፈታኝ ተማሪዎችን በሥም ዝርዝራቸው መሠረት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል። - ፈታኝ መምራህን የተማሪዎችን አቴንዳንሰ ይወስዳሉ ፤ ተማሪዎችን ፊርማ ያስፈርማሉ። - በፈተና ክፍል ውስጥ ደምጽ እንዳይሰማ፣ ተማሪዎች ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው። - የፈተናው አጠቃለይ ሂደት በትኩረት መከታተል አለባቸው። - በህመም ምክንያት ተማሪዎች ከክፍል መውጣት ቢፈልጉ ከሱፐርቨዘር ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እርዳታ ያደርጋሉ። - ተማሪዎች በጎናቸው ያለውን ሌላ ኮምፒውተር እንዳይመለከቱ መቆጣጠር አለባቸው። - ተማሪዎች ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በፊት እንዳይወጡ መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል። - ሲኮርጂ ወይንም ሲያስኮርጅ የተገኘ ተማሪ ከመፈተኛ ክፍል እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። - ፈተናው ከጀመረ 15 ደቂቃ በኃላ የሚመጣ ተማሪ እንዲገባ ማድረግ የላባቸውም። - የፈተና አፈጻጸም ሪፖርት ለሱፐርቨዘር ማቅረብ 🔲ፈተናውን እናልፋለን አብረንም እንመረቃለን! 🔲ለተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ መልካም ፈተና እንዲሆንልን እንመኛለን! ASTU https://t.me/Ethio_Student_Textbook_And_News https://t.me/Ethio_Student_Textbook_And_News
Mostrar todo...
04:12
Video unavailableShow in Telegram
❗️የመውጫ ፈተና (Exit Exam)  የተመለከተ አጭር ተንቀሳቃሽ ምስል የይለፍ ቃል (Password) እንዴት እንቀይራለን የሚለውን ጨምሮ በፈተና ወቅት መከተል ያሉብንን መሰረታዊ ነጥቦች ይዳስሳል። ❗️ከቀየርን የምንቀይረው የይለፍ ቃል (Password) ልናስታውሰው የሚገባ መሆን አለበት
Mostrar todo...
video_2024-06-19_11-52-50.mp48.88 MB
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በዛሬው እለት በተለያዩ የፈተና ጣቢያዎች መሰጠት ጀመረ፡፡ (ሰኔ 12/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ  ከምክትል ቢሮ ኃላፊዎቹ አቶ አሊ ከማል ፣ ወይዘሮ ታጋይቱ አባቡ እና ከአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከአቶ ደሳለኝ ደበሌ ጋር በመሆን በኒው ኤራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚገኘው የፈተና ጣቢያ  ፈተናውን በማስጀመር ተማሪዎችን አበረታተዋል። በከተማ አስተዳደሩ የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በ183 ጣቢያዎች እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በፈተናው ማስጀመሪያ ገልጸው ፈተናው ያለምንም እንከን  እንዲጠናቀቅ በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች የፈተና አስፈጻሚዎችን ጨምሮ በቂ የጸጥታ አካላት መመደባቸውን አስታውቀዋል። ዶክተር ዘላለም አክለውም ተማሪዎች ለፈተናው ብቁ እንዲሆኑ የማጠናከሪያ ትምህርት ከመሰጠቱ ባሻገር ለትምህርት ደረጃው የሚመጥን ሞዴል ፈተና መሰጠቱን ጠቁመው ፈተናው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በየደረጃው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ ለሚገኙ የፈተና አስፈጻሚዎችና  የጸጥታ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
Mostrar todo...
👍 2😁 1
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.