cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ቤተ_ዜማ

Publicaciones publicitarias
199
Suscriptores
Sin datos24 horas
-27 días
-1030 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የታህሳስ ፫ በአታ ለማርያም ዋዜማ ወማህሌት፦ በ፪፡ ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ፤ ርስዒ ሕዝበኪ ወቤተ አቡኪ ፤ እስመ ፈተወ ንጉሥ ስነኪ፤ ቀደሰ ማህደሮ ልዑል፤ወይቤ፤ ዝየ አኃድር እስመ ኃረይክዋ ምልጣን፦ እስመ ፈተወ ንጉሥ ስነኪ፤ ቀደሰ ማህደሮ ልዑል፤ወይቤ ዝየ አኃድር እስመ ኃረይክዋ፤ ወይቤ ዝየ አኃድር እስመ ኃረይክዋ አመላለስ፦ ወይቤ ዝየ አኃድር እስመ ኃረይክዋ ወይቤ ዝየ አኃድር ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ፦ ሰአሊ ለነ ማርያም እንተ እግዚእ ኃረያ ሰአሊ ለነ ማርያም እግዚአብሔር ነግሠ፦ በከመ ይቤ ኢሣይያስ ነቢይ ናሁ ይወርድ እግዚአብሔር ውስተ ምድረ ግብፅ ተፅዒኖ ዲበ ደመና ቀሊል ደመናሰ ዘይቤ ይእቲኬ ድንግል ዘሀዘለቶ ለአማኑኤል ፫ት፦ ማርያምሰ እሙኒ ዐመቱኒ በትረ አሮን እንተ ሠረጸት እንበለ ተክል ይትባረክ፦ እግዝእትየ እብለኪ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ ቃል ቅዱስ ኃደረ ላዕሌኪ ሰላም፦ ወኵሉ ነገራ በሰላም ፡ወኵሉ ነገራ በሰላም ሰላማዊት ይብልዋ ቅድስተ ቅዱሳን ፣ ወኵሉ ነገራ በሰላም ወኵሉ ነገራ በሰላም ጥዕምት በቃላ ወሰናይት በምግባራ ፡ ወኵሉ ነገራ በሰላም ወኵሉ ነገራ በሰላም ንፅህት ይእቲ በድንግልና አልባቲ ሙስና ዕራቁ ደመና፤ ወኵሉ ነገራ በሰላም ወኵሉ ነገራ በሰላም ማርያም ታዕካ በምድር ወታዕካ በሰማይ ሥርዓተ ማኅሌት ዘታኅሣሥ በዓታ ለማርያም መልክአ ሥላሴ ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣህል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል። ዚቅ ለማርያም ዘምሩ፤ ለማርያም ዘምሩ፤ መስቀሎ ለወልዳ እንዘ ትጸውሩ። መልክአ ሚካኤል ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል፤ ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል፤ ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል፤ አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል፤ እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል። ዚቅ ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል፤ ወብሥራት ለገብርኤል፤ ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል። መልክዐ ኪዳነ ምሕረት ሰላም ለእራኅኪ ተመጣዌ ኅብስት ወማይ፤ ሶበ ያመጽኡ ለኪ መላእክት ሰማይ ፤ እንዘ ሀሎኪ ማርያም ወመቅደሰ ኦሪት ዐባይ፤ ይትወከፍ ሊተ ኪዳንኪ ከመ መሥዋዕት ሠርክ ኅሩይ፤ ለእመ ኅፍነማይ አስተይኩ ለጽሙዕ ነዳይ። ዚቅ አንቲ ዉእቱ ንጽሕት እምንጹሐን፤ ዘነበርኪ ዉስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦር፤ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ፤ ስቴኬኒ ስቴ ሕይወት ዉእቱ፤ ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ። ዘጣዕሙ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ። ዚቅ ወመሠረቱ ወመሠረቱ ለዓለም አንቲ፤ ዕጓለ አንበሳ ዕጓለ አንበሳ በከርስኪ ፆርኪ፤ እምአንስት ቡርክት አንቲ ነግሥ መቅደሰ ኦሪት ዘቦዕኪ ማርያም እምነ፤ ወእሙ ለእግዚእነ፤ በሕፅነ ሐና ተማኅፀነ፤ ፈንዊዮ ለፋኑኤል ይዕቀብ ኪያነ፤ በረምሃ መስቀል ረጊዞ ሰይጣነ። ዚቅ ፈንዊ ለነ እግዝእትነ፤ ፋኑኤልሃ መልአክኪ ሄረ፤ በሃይለ ጸሎቱ ይዕቀበነ ወትረ። መልክአ ማርያም ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤ እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤ ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትእዛዝ፤ ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤ ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ። ዚቅ ይዌድስዋ ኲሎሙ በበነገዶሙ፤ ወበበማኅበሮሙ ለቅዱሳን፤ ወይብልዋ በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ። ወረብ "ይዌድስዋ ኲሎሙ"/፪/ በበነገዶሙ/፪/ ወይብልዋ በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ/፪/ መልክአ ማርያም ሰላም ለልሳንኪ ሙኀዘ ኃሊብ ወመዓር፤ ዘተነብዮ ወፍቅር፤ ማርያም ድንግል ወለተ ድኁኃን አድባር፤ ኅብእኒ እምዓይነ ፀር ወአንጽሕኒ እምነውር፤ እስመ ተስፋየ አንቲ በሰማይ ወምድር። ዚቅ ፀቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍርኪ፤ ኃሊብ ወመዓር እምታሕተ ልሳንኪ፤ ወይቤላ ንዒ ንሑር ኀበ ደብረ ከርቤ፤ ውስተ አውግረ ስኂን። መልክአ ማርያም ሰላም ለእመታትኪ እለ ፀንዓ ይፍትላ፤ ሜላተ ወወርቀ በናዝሬት ወበገሊላ፤ ማርያም ድንግል ለዮዲት ጥበበ ቃላ፤ ብጽሂ በሠረገላ ንትመኃል መኃላ፤ ከመ ታኅድርኒ በብሔር ዘተድላ። ዚቅ ገብርኤል መልአክ መጽአ፤ ወዜነዋ ጥዩቀ፤ በዕንቊ ባሕርይ እንዘ ትፈትል ወርቀ። ወረብ ገብርኤል መልአክ መጽአ "ወዜነዋ"/፫/ ጥዩቀ/፪/ "በዕንቊ ባሕርይ"/፫/ እንዘ ትፈትል ወርቀ/፪/ መልክአ ማርያም ሰላም ለአብራክኪ በስብሐተ ልዑል ዘአስተብረካ፤ እምአመ ወሀቡኪ ብፅአ ውስተ ኦሪታዊት ታዕካ፤ ማርያም ድንግል መንበር ዘእብነ ፔካ፤ ጊዜ ስደቶሙ ለኃጥአን እምዓጸደ ዓባይ ፍሲካ፤ ጼውውኒ መንገሌኪ እኩንኪ ምህርካ። ዚቅ እንዘ ዘልፈ ትነብር ውስተ ቤተ እግዚአብሔር፤ አስተርዓያ መልአክ፤ ዘኢኮነ ከመ ቀዲሙ፤ ግሩም ርእየቱ፤ ኢያውአያ እሳተ መለኮት። ወረብ እንዘ ዘልፈ ትነብር ውስተ ቤተ እግዚአብሔር/፪/ አስተርአያ መልአክ ዘኢኮነ ዘኢኮነ ከመ ቀዲሙ ኢኮነ/፪/ መልክአ ማርያም በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ፤ ለዘይስዕለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ፤ ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ፤ ማርያም ዕንቊየ ክርስቲሎቤ ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ፤ ዘጸገየ ማኅጸንኪ አፈወ ነባቤ። ዚቅ ናሁ ተግህደ ልዕልናሃ ለወለተ ሀና፤ህብስተ ህይወት ተጸውረ በማኅጸና፤ጽዋዐ መድኃኒት፤ ዘአልቦ ነውር ወኢሙስና፤ እፎ አግመረቶ ንስቲት ደመና፤ ኢያውአያ በነበልባሉ፤ወኢያደንገጻ በቃሉ፤ አላ ባሕቱ ትብራህ፤ረሰያ ዘበጸዳሉ ፤ይዜኑ ብሥራተ፤ መልአኮ ፈነወ፤ ዮም ተሠርገወ በከመ ተዜነወ። ማኅሌተ ጽጌ የኃዝነኒ ማርያም ዘረከበኪ ድክትምና፤ አመ ቤተ መቅደስ ቦዕኪ እንዘ ትጠብዊ ኃሊበ ሀና፤ ወያስተፌሥሐኒ ካዕበ ትእምርተ ልኅቀትኪ በቅድስና፤ ምስለ አብያጺሁ ከመ አብ እንዘ ይሴስየኪ መና፤ ፋኑኤል ጽጌ ነድ ዘይከይድ ደመና። ዚቅ ንጽሕተ ንጹሐን ከዊና፤ ከመ ታቦተ ዶር ዘሲና፤ ውስተ ቤተ መቅደስ ነበረት በቅድስና፤ ሲሳያ ህብስተ መና፤ ወስቴሃኒ ስቴ ጽሙና። ምልጣን ጽርሕ ንጽሕት ማርያም፤ ተፈሥሂ ሀገረ እግዚአብሔር፤ ቃል ቅዱስ ይወጽእ እምኔኪ፤ አእላፍ መላእክት ይትለአኩኪ። እስመ ለዓለም በጽሐ ሠናይ ወአልጸቀ ዘመን፤ ወበዓላ ለቅድስት ማርያም፤ እንተ በላዕሌሀ ተመርዓወ ቃል፤ አንጺሆ ሥጋሃ ኃደረ ላዕሌሃ፤ ተፈሥሂ ፍሥሕት ቡርክት አንቲ እምአንስት፤ አንጺሆ ሥጋሃ ኃደረ ላዕሌሃ፤ ይመጽእ ላዕሌኪ መንፈስ ቅዱስ፤ ወሃይለ ልዑል ይጼልለኪ፤ አንጺሆ ሥጋሃ ኃደረ ላዕሌሃ፤ ዘኒ ይትወለድ እምኔኪ ቅዱስ ውእቱ፤ ወይሰመይ ወልደ እግዚአብሔር፤ አንጺሆ ሥጋሃ ኃደረ ላዕሌሃ፤ ኢሳይያስኒ ይቤላ ቅንት ሐቌኪ፤ ወልበሲ ትርሢተ መንግሥትኪ፤ አንጺሆ ሥጋሃ ኃደረ ላዕሌሃ፤ ዳዊትኒ ይቤላ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤ አንጺሆ ሥጋሃ ኃደረ ላዕሌሃ፤ ይሰግዱ ለኪ ኲሎሙ ነገሥታተ ምድር፤ ወይልሕሱ ጸበለ እግርኪ፤ አንጺሆ ሥጋሃ ኃደረ ላዕሌሃ፤ ወተወልደ እምኔሃ፤ ወይቤላ ንዒ ርግብየ ሠናይት፤ ንባብኪ አዳም። ወረብ በጽሐ ሠናይ ወአልጸቀ ዘመን/፪/ ወበዓላ ለቅድስት ማርያም/፪/ እንተ በላዕሌሃ ተመርዓወ ቃል አንጺሆ ሥጋሃ ኃደረ ላዕሌሃ/፪/
Mostrar todo...
ኅዳር 24 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ሃያ አራት በዚች ቀን የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የበዓላቸው መታሰቢያ ነው፣ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥሉስ ቅዱስን መንበር ያጠኑበት ነው፣ የአቡነ ዜና ማርቆስ ልደታቸው ነው። ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ኅዳር ሃያ አራት በዚህች ቀን በእግዚአብሔር ዙፋን ዙሪያ የሚኖሩ የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የበዓላቸው መታሰቢያ ነው። እሊህም ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን የእውነት ካህናት የሆኑ ከቅዱሳን ሁሉ በላይ የሆኑና ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ ከፍ ከፍ ያሉ ናቸው እነርሱም ለእግዚአብሔር ቀራቢዎች በመሆን ለሰው ወገን የሚማልዱ ከእጃቸው ውስጥ ካለ ማዕጠንት ጋርነ እንደ ዕጣን የቅዱሳንን ጸሎት የሚያቀርቡ ናቸው ያለእነርሱም አቅራቢነት ጽድቅና ምጽዋት ወደ እግዙአብሔር አይቀርብም። ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ እንዲህ ብሎ እንደተናገረ። በዙፋኑ ዙሪያ ሃያ አራት መንበሮች አሉ በእነዚያ መንበሮች ላይም ሃያ አራት አለቆች ተቀምጠዋል ነጭ ልብስ ለብሰዋል በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል አለ። ሁለተኛም እንዲህ አለ ሌላም መልአክ መጥቶ በመሠዊያው ፊት ቆሞ የወርቅ ጽንሐሕ ይዟል በመንበሩ ፊት ባለ በወርቁ መሠዊያ ላይም የቅዱሳንን ሁሉ ጸሎት ያሳርግ ዘንድ ብዙ ዕጣንን ሰጡት ። የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳኑ ጸሎት ጋር በዚያ መልአክ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት ዐረገ። የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም ። እሊህም እንስሶቹ ለዘላለሙ ሕያው ለሚሆን በዙፋን ላይ ለተቀመጠ ለሱ እንዲህ እያሉ ክብር ምስጋና አቀረቡ። እሊህ ሃያ አራቱ አለቆች አክሊላቸውን በዙፋኑ ፊት አውርደው ለዘላለሙ ሕያው ለሚሆኑ በዙፋን ላይ ለተቀመጠ ለእሱ ሰገዱለት ። አክሊላቸውንም ወደ ዙፋኑ ፊት ወስደው አቤቱ ፈጣሪያችን ኃይልና ምስጋና ክብር ላንተ ይገባል ይሉታል አንተ ሁሉን ፈጥረሃል የተፈጠረውም ሁሉ በአንተ ፈቃድ ይኖራልና ። እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ መሆናቸውንና ስለሁላችን የአዳም ልጆች ስለሚለምኑና ስለሚማልዱ ከብሉይና ከሐዲስ የከበሩ መጻሕፍት ምስክር ሁነዋል ስለዚህም የበዓላቸውን መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ። ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥሉስ ቅዱስን መንበር እንዳጠኑ፡- አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መጥተው በሐይቁ ዳር ቆመው ሳለ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦላቸው ነው በእግሩ በውኃው ላይ እየሄደ እያሳያቸው ተከትለውት እንዲሄዱ የነገራቸው። አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትም መልአኩን ተከትለው ሐይቁን በእግራቸው ተራምደው ተሻግረው አቡነ ኢየሱስ ሞዐን አገኟቸው፡፡ እርሳቸውም አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ እርሳቸው እየመጡ እንደሆነ በመንፈስ ዐውቀው ነበርና ሲያገኟቸው በጣም ተደስተው ከተቀበሏቸው በኋላ አመነኩሰዋቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን በዚያው በሐይቅ በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ አክፍሎትንም በየሳምንቱ ያከፍላሉ፣ ከእሁድና ከቅዳሜ በቀር ምንም አይቀምሱም ነበር፡፡ በእነዚህም ዕለት የአጃ ቂጣ ወይም የዱር ቅጠል ይመጉ ነበር፡፡ ወዛቸው እንደ ውኃ ፈስሶ ምድሪቷን እስኪያርሳት ድረስ እስከ 70 ሺህ ስግደትንም በመስገድ ራሳቸውን እጅግ አደከሙ፡፡ በእነደዚህ ዓይነቱ ተጋድሎ ላይ ሳሉ ነው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ድንገት ነጥቆ ወስዶ ከሥሉስ ቅዱስ ዙፋን ፊት ያቆማቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ስለሆነው ነገር ራሳቸው አባታችን ተክለ ሃይማኖት ሲናገሩ ‹‹…ከዚህ በኋላ መልአኩ ወደ ሰማይ አውጥቶ ከመጋረጃው ውስጥ አስገብቶ ከሥላሴ ዙፋን ፊት አቆመኝና ሰገድኩለት፡፡ ከዚያ አስቀድሞ በማላውቀው በሌላ ምስጋና አመሰገንኩት፡፡ ‹ተክለ ሃይማኖት ክፍልህ ከ24ቱ ካህናቶቼ ጋር ይሁን› የሚል ቃል ከዙፋኑ ውስጥ ወጣ፡፡ የወርቅ ጽና አምጥተው ሰጡኝና ከእነርሱ ጋር አንድነት አጠንሁ፡፡ ምስጋናዬ ከምስጋናቸው ጋር ልብሴም እንደልብሳቸው ሆነ፡፡ ፈጣሪዬንም በሦስትነቱ ተገልጦ አየሁት፡፡ በጸሎትህ የሚታመን ሰው ሁሉ ስለአንተ ይድናል አለኝ…..›› (ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገጽ 216-223) ይህንን ታላቅ በዓል ነው ዛሬ የምናከብረው፡፡ አቡነ ተክለሃይማኖት እንኳን አንደበታቸው የለበሱትም ልብሳቸውም ጭምር እግዚአብሔርን በሰው አንደበት እንደሚያመሰግን በቅዱስ ገድላቸው ላይ ተጽፏል።
Mostrar todo...
👍 1
እንኳን ለጽዮን "ማርያም ማሕደረ አምላክ" እና ለቅዱሳኑ "ጐርጐርዮስ ወዮሐንስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ "ጽዮን ማርያም" "ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው:: አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም: ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል:: እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በሁዋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር: ሞገስ: አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል:: (ዘጸ. 31:18) ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች:: ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ: በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች:: እነሆ በሃገራችን የ3ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው:: ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ መስቀሉንና ታቦተ ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን:: ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን:: ግን አንጨነቅም:: ምክንያቱም የመጣችውም: የምትጠበቀውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም:: በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም:: ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም:: ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን: ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች:: "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው:: "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው:: "ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው:: ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል:: ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው:: በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን:: (2ቆሮ. 6:16, ራዕይ. 11:19) #በመጨረሻም_ኅዳር_21 ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች እንመለከታለን:: በዚህች ቀን:- 1. ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን:: ይሕ ሲሆንም ቅዱስ ሙሴ 40 መዓልት: 40 ሌሊት ጾሞ እንደ ተቀበለ ሳንዘነጋ ማለት ነው:: (ዘጸ. 31:18, ዘዳ. 9:19) 2. በዘመነ ኤሊ ሊቀ ካህናት ታቦተ ጽዮን በታሪኩዋ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካለች:: ግን ደግሞ ዳጐንን ቀጥቅጣዋለች:: (1ሳሙ. 5:1) 3. በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና: ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ: አገለገለ:: ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ ተቀኘላት:: በዚህም ሜልኮል ንቃው ማሕጸኗ ተዘግቷል:: (1ዜና. 15:25) ሊቃውንትም "ድንግል እመቤታችን ማርያም በትንቢት መነጽር ተመልክቷል" ብለውናል:: "ሰላም ለኪ ማርያም እምነ:: ዘሰመይናኪ ጸወነ:: ሶበ እምርሑቅ ርእየ ዘጽላሎትኪ ስነ:: ለቢሶ ዳዊት ልብሰ ክብር ዘየኀይድ ዓይነ:: ቅድመ ታቦተ ሕግ ኀለየ ወዓዲ ዘፈነ::" እንዲል:: (አርኬ ዘኅዳር 21) 4. በዘመነ ንጉሥ ሰሎሞን (መፍቀሬ ጥበብ) ግሩም የሆነ ቤተ መቅደስ ተሰርቶላት ስትገባ ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: እግዚአብሔርም በደመና ወርዶ ንጉሡን አነጋግሯል:: (2ዜና. 5:1, 1ነገ. 8:1) 5. በዚያው ዘመንም በፈጣሪ ፈቃድ ንጉሥ ምኒልክ ቀዳማዊ (ዕብነ ሐኪም) ታቦተ ጽዮንን ይዞ ወደ ኢትዮዽያ ገብቷል:: 6. በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች:: በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታል:: 7. በ4ኛው መቶ ክ/ዘመንም ነገሥት ጻድቃን አብርሐ ወአጽብሐ 12 መቅደሶች ያሏትን ግሩም ቤተ ክርስቲያን ለእመ ብርሃን ሠርተው በዚሁ ቀን በጌታችን ተቀድሷል:: 8. በተጨማሪም በየጊዜው: ማለትም በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ ወደ ዝዋይ ትሰደድ ነበር:: ተመልሳ ስትታነጽም ቅዳሴ ቤቷ የሚከበረው ኅዳር 21 ቀን ነው:: በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ይህ በዓል ልዩ ነው:: " አማናዊት ጽዮን እመ ብርሃን ድንግል ማርያምን እንዲህ እንላታለን " "ቅድስት" የሚለው ቃል ለሁሉም ቅዱሳት እናቶች ቢሰጥም ቅሉ ለድንግል ማርያም ሲሰጥ ግን ትርጉሙ ይለያል:: እርሷ "ቅድስተ ቅዱሳን: ንጽሕተ ንጹሐን: ቡርክት እምቡሩካን: ኅሪት እምኅሩያን" ናትና:: ከሰው ልጆችም ሁሉ ትበልጣለች:: ይቅርና የሰው ልጅን ንጹሐን መላእክትንም በንጽሕናና በቅድስና ትበልጣቸዋለች:: እርሷ እመ ብርሃን: የአምላክ እናቱ: የሰውነታችን መመኪያ ናትና:: #እመቤታችንን "ቅድስት" ስንል "ጽንዕት: ንጽሕት: ክብርት: ልዩ" ማለታችን ነው:: 1. "ንጽሕት" ትባላለች:: ሌሎች ቅዱሳን ቢነጹ ከገቢር: ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም:: እርሷ ግን ከነቢብ: ከገቢር: ከኃልዮ ንጽሕት ናት:: "ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና: ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ-ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው: ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል:: (ተአምረ ማርያም) 2. "ጽንዕት" እንላታለን:: ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በሁዋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ: ጊዜ ጸኒስ: ድኅረ ጸኒስ: ቅድመ ወሊድ: ጊዜ ወሊድ: ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና:: ¤ "ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት:: (ቅዱስ ያሬድ) ¤ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም "ወትረ ድንግል ማርያም-ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ) 3. ድንግልን "ክብርት" እንላታለን:: ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን: ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው:: እመቤታችንን ግን የምናከብራት "ወላዲተ አምላክ-የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና:: 4. እመቤታችንን "ልዩ" እንላታለን:: ከእርሷ በቀር እናት ሁና ድንግል: እመቤት ሁና አገልጋይ የሆነች: በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና::
Mostrar todo...
 🕊  ጾመ ነቢያት   🕊     የጾመ ነብያት ምስጢር ምንድነው ?      ጾመ ነቢያት [ የገና ጾም ] ከልደት አስቀድሞ የሚጾም ጾም ነው፡፡ ከህዳር ፲፭ [ 15 ] ጀምሮ ለ ፵፫ [43] ቀናት የሚጾም ሲሆን ፋሲካው [ ፍቺው ] በልደት በዓል ነው፡፡ ይህም ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ቅዱሳንና ምዕመናን ጾመውታል፡፡ ጾመ ነብያት ስያሜውን ያገኘው ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ስለተፈጸመበት ነው፡፡ በየዘመናቱ የተነሡ ነቢያት እግዚአብሔር ወደፊት ሊያደርግ ያሰበውን በእምነት ዓይን እያዩ ምስጢር ተገልጦላቸው የራቀው ቀርቦ ፣ የረቀቀው ገዝፎ ጎልቶ እየተመለከቱ ትንቢት ተናገሩ ፤ ያዩትም መልካም ነገር እንዲደርስላቸው ጾሙ ጸለዩ፡፡ ነቢያት ከእመቤታችን ስለ መወለዱ ፥ ወደ ግብፅ ስለ መሰደዱ ፥ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ ፥ ብርሃን በሆነው ትምህርተ ወንጌል ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ ፥ ለሰው ልጆች ድኅነት ጸዋትወ መከራ ስለመቀበሉና ስለ መሰቀሉ ፥ ስለ ትንሣኤው ፥ ስለ ዕርገቱና ስለ ዳግም ምጽአቱ ትንቢት ተናግረው አላቆሙም፡፡ ለአዳም የተሠጠው ተስፋ ተገልጦላቸው ለተናገሩት ትንቢት ፍፃሜ እንዲያደርሳቸው ፈጣሪያቸውን ተማፀኑትም እንጂ፡፡ በየዘመናቸው ፦ "አንሥእ ኃይልከ ፣ ፈኑ እዴከ" እያሉ ጮኹ፡፡ በጾምና በጸሎት ተወስነውም እግዚአብሔር ሰው የሚሆንበትን ጊዜ በቀናት ፣ በሳምንታት ፣ በወራትና በዓመታት ቆጠሩ፡፡ ለምሳሌ ነቢዩ ኤርምያስ ስለ ሥጋዌው ትንቢት በተናገረ በ፬፵፮ ዓመት ጌታችን ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኗል፡፡ ነቢያት ተስፋው በዘመናቸው ተፈጽሞ በዓይነ ሥጋ ለማየት ባይችሉም እግዚአብሔር ፦ "አያደርገውን አይናገር የተናገረውን አያስቀር" ብለው አምነው ከወዲሁ ተደሰቱ፡፡ ለዘመነ ሥጋዌ ቅርብ የነበሩ እነ ነቢዩ ኢሳይያስ ጾሙ እንዴት መፈጸም እንዳለበት ተናግረዋልም፡፡ [ኢሳ.፶፰፥፩]፡፡ በመሆኑም በጌታ ልደት ትንቢተ ነቢያት ስለተፈጸመበት ይህ ጾም "የነቢያት ጾም" ይባላል፡፡ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት ስለሆነም "ጾመ ስብከት" ይባላል፡፡ ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል፤ በዚህም ምክንያት የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት፡፡ እነርሱም፦ † ፩. [    ጾመ አዳም   ] ፦ አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከገነት ከተባረረ በኋላ በፈጸመው በደል አዝኖ ፥ ተክዞ ፤ አለቀሰ [እንባ ቢያልቅበት እዥ እስከሚያፈስ ፤ እዥ ቢያልቅበት ደም በዓይኑ እስከሚፈስና ዓይኑ ይቡስ ወይም ደረቅ እስከሚሆን ድረስ አለቀሰ] ፥ ጾመ፣ ጸለየ፡፡ ከልብ የሆነ ጸጸቱን፣ ዕንባውን፣ በራሱ መፍረዱንም እግዚአብሔር አይቶ ተስፋ ድኅነት ሰጠው፡፡ "ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ፣ በደጅህ ድኼ ፣ በዕፀ መስቀል ተሰቅዬ፣ ሞቼ አድንሃለሁ፡፡" የሚል ነው፡፡ [ገላ. ፬፥፬፣ መጽ.ቀሌምንጦስ] ስለዚህ ጾሙ የተሰጠው ተስፋ ፥ የተቆጠረው ሱባኤ ስለተፈጸመበት "ጾመ አዳም" ይባላል፡፡ † ፪. [   ጾመ ነቢያት   ] ፦ ነቢያትም የምሥጢረ ሥጋዌ ነገር ተገለጦ ስለታያቸው ፣ ክርስቶስ ለሰው ልጅ የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ በትንቢት ተመልክተው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል፡፡ ይህ ጾም ከአባታችን አዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የተነሱ አበውና እናቶች : ድኅነትንና ረድኤትን ሲሹ የጾሙት ጾም ነው:: በተለይ አባታችን አዳም : ቅዱስ ሙሴ : ቅዱስ ኤልያስ ፣ ቅዱስ ዳንኤልና ቅዱስ ዳዊት በጾማቸው የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው:: [ዘዳ.፱፥፲፱ ፣ ነገ.፲፱፥፰ ፣ ዳን.፱፥፫ መዝ.፷፰፥፲ ፻፰፥፳፬] ቅዱሳን ነቢያት በጭንቅ በመከራ ሆነው የጾሙት ጾም ወደ መንበረ ጸባኦት ደርሶ: ወልድን ከዙፋኑ ስቦታል:: ለሞትም አብቅቶታል:: † ፫.  [   ጾመ ሐዋርያት  ] ፦ ሐዋርያት "ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብራለን ፣ ልደትን ምን ሥራ ሠርተን እናከብረዋለን?" ብለው ከልደተ ክርስቶስ በፊት ያሉትን ፵፫ ዕለታት ጾመዋልና፡፡ † ፬.  [   ጾመ ማርያም   ] ፦ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ቅድስናዋን አይቶ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ አምላክን ያለ ሰስሎተ ድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ ጸንሳ እንደምትወልደው ቢነግራትም የትሕትና እናት ናትና "ምን ሠርቼ የሰማይና ምድርን ፈጣሪ እችለዋለሁ?" ብላ ጌታን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማለችና "ጾመ ማርያም" ይባላል፡፡ † ፭.  [   ጾመ ፊልጶስ   ] ፦ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ እያስተማረ ሳለ በሰማዕትነት ሲሞት ፤ አስክሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ ፤ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስክሬን እንዲገለጽላቸው ከኅዳር ፲፮ ጀምረው ጾመው በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስክሬን ተመልሶላቸዋል፤ ነገር ግን አስከሬኑ ቢመለስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል፡፡ † ፮.  [   ጾመ ስብከት  ] ፦ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት ፥ የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት ፥ የምስራች የተነገረበት ስለሆነ ጾመ ስብከትም ይባላል፡፡ † ፯.  [   ጾመ ልደት   ] ፦ የጾሙ መጨረሻ [ መፍቻ ] በዓለ ልደት ስለሆነ "ጾመ ልደት" ይባላል፡፡ በጾማችን በጸሎታችን - ስለ ቤተክርስቲያን ፥ ስለ ሀገር እና ስለ ሕዝብ በማሰብ በእንባ እራሳችንን ዝቅ በማድረግ እንጾም ዘንድ ይገባል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡ ወለወላዲቱ ድንግል ፡ ወለመስቀሉ ክቡር፡፡
Mostrar todo...
🄱🄾🄱 𝒎𝒂𝒓𝒍𝒆𝒚

Weleam

​​#ሕዳር_ሚካኤል ! #እንኳን_ለመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ሚካኤል #በዓለ_ሲመት_በሠላም_አደረሰን ! በዓለ ሲመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል (ሕዳር 12) (አንብባችሁ ስትጨርሱ ለሌሎችም ታሪኩን እንዲያዉቁ #SHARE ብታደርጉ ብዙ አተረፋችሁ፡፡) ቤተ ክርስቲያን ልጆቹዋ የመላእክትን ተራዳኢነት አውቀው እንዲጠቀሙና የመንግሥቱ ወራሾች ለመሆን እንዲበቁ ስትል ለቅዱሳን መላእክት የመታሰቢያ ቀን በመስጠት በእነርሱ የምናገኛቸውን እርዳታዎች እንዲታወሱ ታደርጋለች፡፡ በዚህም መሠረት በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡ እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል። ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በተሰኘው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው ፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት “… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘ ሰው በፊቱ ቆመ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” (ኢያ.5፡13) ይለናል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ሹመቱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይም በመሆኑ ስለ እነርሱ ዲያብሎስ ይዋጋው፣ በጸሎትም ይራዳቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ኃጢአት ሠርተው ሲያገኛቸው ለእግዚአብሔር አድልቶ ኃጢአተኞችን ስለሚቀጣ እግዚአብሔር ሕዝቡን “በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት” (ዘጸ.23፡21) ብሎ አስጠንቅቋቸው ነበር፡፡ ይህም ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙን ያስረዳናል፡፡ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱት ጥቅሶች ሕዝበ እስራኤልን ይራዳቸው የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ አያረጋግጥም የሚል ካለ “መልአክ” የተባለው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ነቢዩ ዳንኤል በተላከ ጊዜ ገልጦልን እናገኛለን፡- ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ቅዱስ ሚካኤል ስለመሾሙ ሲመሰክር “በእውነት በመጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ ማንም የለም”(ዳን.10፡21) ብሎአል፡፡ ስለዚህም ለኢያሱ የተገለጠውና እስራኤላውያንንም የመራው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን እንረዳለን፡፡ የቅዱስ ሚካኤል አለቅነት በሐዲስ ኪዳንም አንደሚቀጥል ይህ ነቢይ በትንቢቱ “በዚያ ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ ሚካኤል ይነሣል..” (ዳን.12፡1) በማለት ተናግሮለታል ፡፡ ስለዚህም ቅዱስ ሚካኤል እኛን ከሰይጣን አሽክላና ወጥመድ ይጠብቀንና በጸሎቱ በእግዚአብሔር ፊት ይቆምልን ዘንድ በእኛም ላይ ሹም ነው። ምክንያቱም እኛ የእግዚአብሔር ሕዝቦችና የርስቱ ወራሾች ነንና፡፡ እግዚአብሔር ነቢዩ ሙሴን የሕዝቡ መሪ አድርጎ መሾሙ እጅግ ትሑትና ስለመንጎቹ ነፍሱን እንኳ አሳልፎ እስከመስጠት ደርሶ ስለሚወዳቸው ነበር፡፡ (ዘኁል.12፡3፤ዘጸአ.32፡32)በሕዝቡም ላይ እርሱን መሾሙ እንዲሠለጥንባቸው ወይም እንዲገዛቸው ሳይሆን በትምህርቱና በጸሎቱ እነርሱን እንዲያግዛቸው ነው፡፡ እንዲህም ስለሆነ ቅዱስ እስጢፋኖስ ስለሙሴ ሲመሰክር “እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው”አለ፡፡ (የሐዋ.7፡35) እንዲሁ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እጅግ ትሑትና ለሠራዊቱ ተቆርቋሪ የሆነ መልአክ በመሆኑ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ተሾመ፡፡ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙ ልክ እንደ ሙሴ በእነርሱ ላይ ሊሠለጥንባቸው ወይም ሊገዛቸው ሳይሆን መላእክትን ሊመራ ፣ እኛን ደግሞ ከሰይጣን ጥቃት ሊጠብቀንና በጸሎቱ ሊራዳን ነው (ይሁዳ.12) ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን መላእክት እኛን እንደሚጠብቁና እንደሚራዱ እንዲሁም ስለእኛ በፊቱ አንደሚቆሙ ሲያስተምረን “ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ስንኳ እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ሁል ጊዜ በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁ” (ማቴ.18፡10) ብሎናል፡፡ እኛን ይጠብቁ ዘንድ የተሰጡን ቅዱሳን መላእክት ስለእኛ እንዲህ የሚቆረቆሩና ስለመዳናችን የሚተጉ ከሆነ በቅድስናው ልቆ የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመው ቅዱስ ሚካኤል እንዴት ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ይበልጥ አይቆም? (ሉቃ.13፡6-9) እንዴትስ በተሰጠው ሥልጣንና ኃይል አይረዳን? (መዝ.33፡7) እርሱ “ስለሕዝብህ ልጆች የሚቆመው” መባሉም እኛን በጸሎቱና በተራዳኢነቱ የጽድቅ ሕይወታችንን በሚገባ እንድናከናውን እንደሚራዳን የሚያሳይ ኃይለ ቃል ነው፡፡ የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ጸሎቱና በረከቱ በእኛ ላይ ለዘለዓለሙ ይደርብን አሜን፡፡
Mostrar todo...

ስርአተ  ማህሌተ ሚካኤል ህዳር ፲፪ https://t.me/bete_zemas የየትኛውም ማህሌት መጀመርያ                                         ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። መልክአ ሥላሴ ሰላም ለጒርዔክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ፤ ብዑላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ፤ እመትትኃየዩኒሰ ኢትኅድጉኒ ጽኑሰ፤ ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ስጋየ ጌሠ፤ ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ። ዚቅ አመ ይፈጥራ እግዚአብሔር ለምድር፤ ኢዜነዎ ለሰማይ፤ ወኢተማከረ ምስለ መላእክቲሁ፤ ወተከለ ፫ተ ዕፀ ህይወት በዲበ ምድር። ነግሥ ጎሣዐ ልብየ ጥበበ ወልቡና፤ ለውዳሴከ ጥዑመ ዜና፤ ቅዱስ ሚካኤል ልማድከ ግብረ ትኅትና፤ አንተኑ ዘመራኅኮሙ ፍና፤ ወአንተኑ ለ፳ኤል ዘአውረድከ መና። ወረብ አንተኑ ሚካኤል መና መና ዘአውረድከ/፪/ ወአንተኑ ለ፳ኤል መና ዘአውረድከ/፪/ ዚቅ አዝነመ ሎሙ መና ይብልዑ፤ ፀዓዳ ከመ በረድ፤ ወርእየቱ ከመ ተቅጻ፤ ኅብስተ እምሰማይ ወሀቦሙ፤ አውኃዘ ሎሙ ማየ ህይወት፤ ዘትረ ኮክሕ ፈልፈለ ነቅዕ ዘኢይነጽፍ፤ ኅብስተ እምሰማይ ወሀቦሙ። መልክአ ሚካኤል ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ፤ ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ጸሐፈ፤ ሶበ እጼውዕ ስመከ ከሢትየ አፈ፤ ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ፤ ለረዲኦትየ ነዓ ሰፊሐከ ክንፈ። ወረብ ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል ረዳኤ ምንዱባን/፪/ በከመ ከመ ታለምድ ዘልፈ/፪/ ዚቅ ውእቱ ሚካኤል መልአከ ሃይል፤ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር፤ ይስአል ለነ፤ ረዳኤ ይኲነነ አመ ምንዳቤነ፤ ሠፊሆ ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ ወረብ፦ ውእቱ ሚካኤል መልአከ ሃይል ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር/፪/ ይስአል ለነ አመ ምንዳቤነ ይስአል ሰፊሆ ክነፊሁ/፪/ መልክአ ሚካኤል ሰላም ለልሳንከ በነቢበ ጽርፈት ዘኢተኃበለ፤ በእንተ ሥጋሁ ለሙሴ አመ ምስለ ሰይጣን ተበኃለ፤ ሚካኤል ክብርከ እምክብረ መላእክት ተልዕለ፤ ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ፤ በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ። ወረብ ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ/፪/ "በብሂለ ኦሆ"/፪/ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ/፪/ ዚቅ ረሰዮ እግዚኦ ለውእቱ ሚካኤል፤ እምኲሎሙ መላእክት ይትለዓል መንበሩ፤ ስዩም በኀበ እግዚኡ ምእመን። ወረብ እግዚኦ ረሰዮ ለውእቱ ሚካኤል/፪/ እምኲሎሙ መላእክት መላእክት ይትለዓል መንበሩ/፪/ መልክአ ሚካኤል ሰላም ለሕንብርትከ ሕንብርተ መንፈስ ረቂቅ፤ ዘቱሣሔሁ መብረቅ፤ ነግኃ ነግኅ አንተ በአዝንሞ መና ምውቅ፤ በገዳም ዘሴሰይኮሙ ለነገደ ኅሬ ደቂቅ፤ ሴስየኒ ሚካኤል ሕገከ በጽድቅ። ወረብ "በገዳም"/፫/ ዘሴሰይኮሙ/፪/ ለነገደ ለነገደ ኅሬ ደቂቅ/፪/ ዚቅ ባሕረ ግርምተ ገብረ ዓረፍተ፤ ወበውስቴታ አርዓየ ፍኖተ፤ በእደ መልአኩ ዓቀቦሙ በገዳም ለሕዝቡ አርባዐ ዓመተ፤ ወሴሰዮሙ መና ኅብስተ፤ ኪነ ጥበቡ ዘአልቦ መስፈርተ። ወረብ ባሕረ ግርምተ ዓረፍተ ገብር አርአየ ፍኖተ እግዚአብሔር/፪/ በእደ መልአኩ ዓቀቦሙ ለ፳ኤል አርብዐ ዓመተ ለሕዝቡ በገዳም/፪/ መልክአ ሚካኤል አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክእከ ኲሉ፤ ለለ፩ ፩ ዘበበክፍሉ፤ ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ፤ ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኀ ሰማያት ዘላዕሉ፤ ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ። ዚቅ ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኀ ሰማይ፤ ወስዕለተነ ከመ መዓዛ ሠናይ፤ ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኀ ሰማይ። ወረብ ተወከፍ ጸሎተነ ጸሎተነ ውስተ ኑኀ ሰማይ/፪/ ወስዕለተነ ከመ መዓዛ ሠናይ ሊቀ መላእክት/፪/ ምልጣን ውእቱ ሚካኤል መልአከ ሃይል፤ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር፤ ይስአል ለነ፤ ረዳኤ ይኲነነ አመ ምንዳቤነ፤ ሰፊሆ ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ አመላለስ፦ ሰፊሆ ክነፊሁ/2/ ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ/4/ እስመ ለዓለም ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ አስተምህር ለነ ሰአልናከ በ፲ ወ፬ ትንብልናከ፤ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ዓይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ ሐመልማለ ወርቅ፤ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ይሰግድ በብረኪሁ እስከ ይመጽእ ሥርየት ለኃጥአን፤ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ መኑ ከማከ ክቡር ሰላም መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዐቢይ።     # Join & share       መልካም በዓል !
Mostrar todo...
👍 2
ስርአተ ዋዜማ ዘህዳር ሚካኤል https://t.me/bete_zemas መርሆሙ መዓልት በደመና፤ ወኩሉ ሌሊት በብርዐነ እሳት ፤ ወአውጽኦሙ በትፍስዕት፤ ፈነወ መልዐኮ ፣ ወአድዐኖሙ፤ማ፦ እንዘ ሚካኤል የሐውር፤ ቅድመ ትይንቶሙ ለእስራኤል። አመላለስ፦ እንዘ ሚካኤል የሐውር/2/ ቅድመ ትይንቶሙ ለእስራኤል እንዘ ሚካኤል የሐውር/2/ ለእግዚአብሔር ምድር፦ በዕደ መልዐኩ ይቀበነ ወይከሠት አዕይንተ አልባቢነ በዕደ መልዐኩ ይቀበነ እግዚአብሔር ነግሰ፦ ሚካኤል መልአክ ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ ወበእንተ ነፍሰ ኩልነ መልአኪየ ይቤሎ መልአክት ሠምሮ መልአከ ኪዳኑ ለክርስቶስ አኮኑ ይት፦ ነዋ ሚካኤል መልአክክሙ ይስዕል ለክሙ ኃበ እግዚአብሔር ልዑል ዘይሰርር ለመድሀኒተ ኩሉ ዓለም በክልዔ ክንፍ ሰላም፦ በ፪ ዳንኤልኒ ይቤ ነዋ ሚካኤል አሐዱ እመላእክት፤ እምቅዱሳን ቀደምት መጽአ ይርድአኒ፤ አጽንዓኒ ወይቤለኒ፤ ኢትፍራህ ብእሲ ፍትወት አንተ፤ ሰላም ለከ ጽናዕ ወተአገሥ፤ ወእንዘ ይትናገረኒ ጸናዕኩ ወይቤሎ፤ ንግረኒ እስመ አጽናዕከኒ፤ ወይቤለኒ ሶበ ተአምር ዳዕሙ፤ ሚካኤል መልአክክሙ። አመላለስ፦ ንግረኒ እስመ አጽናዕከኒ ወይቤለኒ፤[፪] ወይቤለኒ ሶበ ተአምር ዳዕሙ ሚካኤል መልአክክሙ[፬]     # Join & share #
Mostrar todo...

+በዚች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ እንዲሁም ከዮሴፍ እና ሰሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ 6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ ሀገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው። ታድያ ጌታችን በእመቤታችን ጀርባ ላይ ሆኖ በእነዛ የምህረት ጣቶቹ ወደ #ኢትዮጵያ ይጠቁም ነበር እመቤታችንም ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን ምታመለክተው ስትለው ""ያቺ የተባረከች ሀገር ናት"" እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ናት!!ያንቺ ዘመዶች ሰቅለው ይገሉኛል በዚች አገር ያሉ ግን ሳያዩ ያምኑኛል አስራት በኩራት ትሁንሽ ብሎ ሰቷታል በቅዱስ እግራቸውም ጣና ሀይቅን ዋልድባንና ሌሎችንም ዞረው እንደባረኩም ድርሳነ ኡራኤልና ታምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል። እመቤታችንን ከሐና መሀፀን ፈጥሮ ከፍጥረት አለም ለይቶ ከሁሉ አልቆ የእናት አማላጅ ትሁናችሁ ብሎ የሰጠን ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን ! የእመቤታችን ቁስቋም ማርያም ምልጃዋና በረከቷ አይለየን !! ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን !! ኀዳር 6 ቀን ወደ ግብጽ አገር ተሰዳ ስትመለስ ቁስቋም በምትባል አገር ገብታ ያረፈችበት በዓል ነው፡፡ ከገነት የተሰደደውን አዳም ወደ ገነት ለመመለስ ሲል ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ከአረጋዊው ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡ ጌታችን ከ3 ዓመት ከ6 ወር የግብጽ ስደት በኋላ ወደ እስራኤል እንደሚመለስ አስቀድሞ ነቢየ ልኡል ሆሴዕ በትንቢት መነጽርነት ተመልክቶ “ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት ” ብሎ ተናግሯል ሆሴ 11÷1 ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር - እነሆ የተወደደው ማኅሌተ ጽጌ ተፈጸመ! «ተመየጢ ተመየጢ ሱላማጢስ ...ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ ተመለሽ » መኃ ፯፥፩ የተዋህዶ ልጆች እንኳን እመቤታችን ከስደት ተመልሳ ቁስቋም የገባችበት በዓል ቀን በሰላም አደረሳችሁ!
Mostrar todo...
ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር🌹፤ እነሆ የተወደደች ማኅሌተ ጽጌ ተፈጸመ! ሥርዓተ ማኅሌት ዘዘመነ ጽጌ "በዓለ ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ፣ ወኢዮብ ጻድቅ፣ ወአቤል" "፮ኛ ሳምንት" "ተፈጸመ" የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ) ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። መልክአ ሥላሴ ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል። ዚቅ ሃሌ ሉያ፤ ለክርስቶስ ይደሉ ስብሐት፤ ለዘአብጽሐነ እስከ ዛቲ ሰዓት፤ እግዚአ ለሰንበት፤ አኮቴተ ነዓርግ ለመንግሥትከ፤ ምድረ በጽጌ አሠርጎከ። ማኅሌተ ጽጌ ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስዕልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ፤ ዘኢየኃልቅ ስብሐተ እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ፤ ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ፤ ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ፤ ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ። ወረብ ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስዕልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ/፪/ ዘኢየኃልቅ "ስብሐተ"/፪/ እንዘ እሴብሐኪ/፪/ ዚቅ እለ ትነብሩ ተንሥኡ፤ ወእለ ታረምሙ አውሥኡ፤ ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውኡ፤ ቁሙ ወአጽምዑ ተአምረ ድንግል ከመ ትስምዑ፤ ጸልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል፤ መርዓተ አብ ወእመ በግዑ። ማኅሌተ ጽጌ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ። ወረብ እንዘ ተሐቅፊዮ "ለሕፃንኪ"/፪/ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/ ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ሚካኤል/፪/ ዚቅ ንዒ ርግብየ ሰላማዊት፤ ንባብኪ አዳም፤ ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍሪሃ፤ እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላዕክት፤ አልቦ ዘይመስል ዘከማኪ ክብረ፤ እግዚአ ለሰንበት በማኅፀንኪ ተጸውረ። ዓዲ (ወይም) ዚቅ ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ኲሎሙ መላእክት፤ ከመ ታዕርጊ ጸሎተነ ጊዜ መንፈቀ ሌሊት። ማኅሌተ ጽጌ ሰዊተ ሥርናዩ ለታዴዎስ ወለበርተሎሜዎስ ወይኑ፤ እንተ ጸገይኪ አስካለ በዕለተ ተከልኪ እደ የማኑ፤ ማርያም ለጴጥሮስ ጽላሎቱ ወለጳውሎስ ሰበኑ፤ ብኪ ምውታን ሕያዋነ ኮኑ፤ ወሐዋርያት መላእክተ በሰማይ ኮነኑ። ወረብ ማርያም ለጴጥሮስ "ጽላሎቱ"/፪/ ወለጳውሎስ ሰበኑ/፪/ ወሐዋርያት "መላእክተ"/፪/ በሰማይ ኮነኑ/፪/ ዚቅ ኦ መድኃኒት ለነገሥት፤ ማኅበረ ቅዱሳን የዓውዱኪ፤ ነቢያት የዓኲቱኪ፤ ወሐዋርያት ይሴብሑኪ፤ እስመ ኪያኪ ኀቤ ለታዕካሁ ከመ ትኲኒዮሙ ማኅደረ፤ መላእክት ይኬልሉኪ፤ ጻድቃን ይባርኩኪ፤ አበው ይገንዩ ለኪ፤ እስመ ኪያኪ ኀቤ ለታዕካሁ ከመ ትኲኒዮሙ ማኅደረ። ማኅሌተ ጽጌ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቌ ባሕርይ ዘየኀቱ፤ ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤ አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ። ወረብ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየኀቱ እምዕንቊ ባሕርይ/፪/ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግስቱ ለጊዮርጊስ መንግስቱ ለሕዝበ ክርስቲያን/፪/ ዚቅ ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት፤ ወስብሕት በሐዋርያት፤ አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ፤ ወትምክሕተ ቤቱ ለ፳ኤል። ማኅሌተ ጽጌ ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ አርአያ ኮስኮስ ዘብሩር፤ ተአምርኪ ንፁሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤ ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፤ ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር። ወረብ ናሁ "ተፈጸመ"/፪/ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ/፪/ "አስምኪ ቦቱ"/፪/ ንግሥተ ሰማያት /፪/ ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ፤ ጥቀ አዳም መላትኅኪ ከመ ማዕነቅ፤ ይግበሩ ለኪ ኮስኮሰ ወርቅ። ሰቆቃወ ድንግል ተመየጢ እግዝእትየ ሀገረኪ ናዝሬተ፤ ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፤ በላዕሌኪ አልቦ እንተ ያመጽእ ሁከተ፤ ለወልድኪ ዘየኃሥሦ ይእዜሰ ሞተ፤ በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ። ወረብ "ተመየጢ"/፪/ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ/፪/ ወኢትጎንድዪ "በግብጽ"/፪/ ከመ ዘአልብኪ ቤተ/፪/ ዚቅ ሃሌ ሉያ፤ ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት፤ ወንርዓይ ብኪ ሰላመ፤ ምንተኑ ትኔጽሩ በእንተ ሰላመ ሰጣዊት፤ እንተ ትሔውጽ እምርኁቅ፤ ከመ መድብለ ማኅበር ሑረታቲሀ ዘበስን ለወለተ አሚናዳብ። መዝሙር በ፮: ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበተ፤ ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበት፤ ወጸገወነ ዕረፍተ ከመ ንትፈሣሕ ኅቡረ፤ አዕጻዳተ ወይን ጸገዩ፤ ቀንሞስ ፈረየ፤ ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ ከመ ፩ እምእሉ። ዓራራይ በሰንበት እውራነ መርሐ፤ በሰንበት አጋንንተ አውጽአ፤ እለ ለምጽ አንጽሐ፤ ቃለ ማዕነቅ ተሰምዓ በምድርነ፤ ሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት። ዕዝል መንክር ግብሩ ለ፩ እግዚአብሔር አብ ዘላዕለ ኲሉ፤ መንክር ግብሩ ለዘሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት፤ መንክር ግብሩ ለዘአሠርገዋ ለምድር በጽጌያት፤ መንክር ግብሩ ለዘገብረ ብርሃናተ ዓበይተ ባሕቲቱ። ሰላም ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ፤ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሐረገ ወይን፤ እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ ሐረገ ወይን፤ እንተ በሥሉስ ትትገመድ፤ ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከት ሐረገ ወይን፤ ሲሳዮሙ ለቅዱሳን ሐረገ ወይን፤ ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ፤ ወጸገወ ሰላመ ለኵሉ። መልካም በዓል!!
Mostrar todo...
26. በእናት ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ዋናኛ ችግር አባባሽና አጋፋሪ በመሆን በሐሰት አስመሳይ ደጋፊ በመሆን እያፋፉሙ ያሉ አጽራረ ቤተ ክርስቲያንን ማጋለጥ፣ በሕግ መፋረድ፣ እንዲታወቁ ዘመቻ ማድረግ ለዚህም ከሕግ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በጥብቅ ሥራ እንዲሠራ ጉባኤው በጥንቅ ያሳስባል፤ 27. አንዳችን ለአንዳችን በአንድነት ድምጽ መሆን በአንዱ ሀገረ ሰብከት ችግር ሲፈጠር ሌላውን እኩል መጮኽ፣ ሁሉም ለሁሉም ድምጽ መሆን ለሚመለከተው አካል ያለማቋረጥ መጮኽ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ በሀገር ውስጥ ሳንወሰን፣ ችግራችንን ለመላው ዓለም መስረዳት መቻል፤ ጠላቶቻችን መቼም ዝም አይሉምና፣ ዘዴና አካሔድ ይቀይራሉ አንጅ ጥቃታቸውን አያቆሙምና ለዚህ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሠራ ጉባኤው ይጠይቃል፤ 28. በዋናው ማእከል፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሚሰጡ መመሪያዎች፣ ደንቦች ውሳኔዎች እና ል ልዩ ትእዛዞች እስከ ታች ድረስ በማውረድ ለማስፈጸም ሁላችንም ቃል በመግባት ይኽ የተናበብና የተሰናሰለ አሠራር እንዲኖር የበኩላችንን ለመወጣት ቃል እንገባለን፤ 29. ብፁዕ አቡነ ሙሴ የምዕራብ አውስትራልያ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ሲኖዶስ አባል በሚመሩት ሀገረ ሰብከት ፓለቲከኞች እና የጎሣ ሐሳብ አራማጆች፣ ከክርስያን በማይጠበቅ የከፋ የጥላቸ ስበከት ቤተ ክርስቲያንን የብጥብጥና የክፍፍል ማእከል አድርገው እንደከፈሏት፣ ቦርድ በማቋቋም እየበጠበጧትን እንሆነ በሪፖርታቸው አጠንክረው ገልፀዋል፤ በዚህም ጉባኤው ብፁዕነታቸውን ያመሰግናል፤ በሌሎችም ክፍላተ ዓለም ይኽው የመከፋፈል ምንፈስ እነዳለ ይተመናል ስለዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ጉዳይ ላይ አሐቲ ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈልና የፒለቲካ መድረክ ለማድረግ በቤተ ክርስቲያን ስም ለሚንቀሳቀሱት ሀይሎች ላይ ይሰጥበት ዘንድ በጥብቅ እንጠይቃለን፡፡ 30. በራያ አካባቢ የቤተ ክህነት ወረዳዎች በታሪክ፣ በቀኖና፣ በአስተዳደርና በትውፊት የማይታወቅ “መንበረ ሰላማ” የሚል ማደናገሪያ ፈጥረው በቡድን ተደራጅተው ምእመናን ሲያዉኩ የነበሩ አካላት በፈተሩት ችግር ካህናትና ምእመናንን የቤተ ክርስያንን አንድነት ለማስጠበቅ ያደረጉትን ጥረት እያደነቅን ጉዳዩ በቅዱስ ሲኖዶስ ተጨማሪ ድጋፍ እንዲያገኙ እናሳስባለን፡፡ 31. ጠባብ ብሔርተኝነትና ጎሠኝነትን በተግባር በመቃወም፣ ድክመትን ማረም፣ አብሮ የመሥራት ልምድን ማዳበር፣ ለሰላምን ለአንድነት ትኩረት ሰጥቶ መሥራት፣ ጥላቻን በማራቅና የቤተ ክርስቲያንን ክብርና ልዕልና ለመጠበቅ የሚገባንን ሁሉ ለመወጣት ቃል በመግባት፡፡ 32. የሕገ ተፈጥሮና የሕግ ሁሉ ፍጻሜ በሆነው በቅዱስ መጽሐፍ አጥቆ የተከለከውና ከጥንት ጀምሮ በዓለም ላይ ለፍጥረታት ጥፋት ምክንያት የሆነው ርዕሰ ኃጣውእ ግብረ ሰዶማዊነት ኃጢአት ከወሬ መጽሐፍና ከድምጸ ዜና አልፎ በዓለማችንና በሀገራችን በከፍተኛ ደረጃ ያለከልካይ በየአደባባዩ ገሀድ ሆኖ ትውልድል የማጥፋ ሴራ በስፋት፣ እየተሠራበት እንደሆነ ማንኛውም ኢትዮያዊ፣ የሚውቀው ሐቅ ስለሆነ ይኽንን ዐቢይ ጉዳይ አጥብቆ ያወግዛል፤ ጉዳዩ በቅዱስ ሲኖዶስም ጠንካራ ውሳኔ እንዲያስተልለፍበት ጉባኤው በጥብቅ እናወግዛለን፣ ቅዱስ ሶኖዶስም ውሳኔ እንዲያሳርፍበት፤ 33. ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ጀምሮ፣ ከተሰሙት ሪፖርቶች፣ በውይይት ከተገኘው ሐሳብ እንደተገነዘብነው በአሁኑ ጊዜ ለተፈጠሩ ችግሮች ሁሉም የድራሽውን መውድ እንዳለበት፣ ወደራሳችንና ወደልባችን ተመለስን በፈጣሪያችን ታዘን ያልፈጸምነው እንደሚበዛ፣ ከሠራነው ያላሠራነው እንደሚበልጥ፣ ለድክመታችን ተጠያቂዎቹ ራሳችን መሆናችንን እና ኃላፊነት መወሰድ እንደሚገባን አምነንበታል፤ ይሁን እንጅ ከውድቀት ለመነሣት፣ ካጠፋነው ጥፋት ለመዳን፣ ያልሠራነው ለመሥራት ሁነኛው መፍትሔ ንሥሓ በመሆኑ ሁላችንም በአባቶቻችን ትእዛዝና መመሪያ ንሥሓ ገብተን ተልእኮአችንን ለመፈጸም ቃል እንገባለን፡፡ ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና (ማቴ 18፡20) ብሎ ለቅዱሳን ሐዋርያት የሰጠውን ቃል ኪዳን ለእኛም አቆይቶ በመካከላችን የተገኘ ሞገስነ፣ ወክብርነ፣ ቀርነ መድኀኒትነ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ከባህርይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ከባህርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ የተመሰገነ ይሁን! ልዑል እግዚአብሄር አምላካችን የአባቶቻችን አምላክ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን፣ ቅዱስ አባታችንን፣ ብፁዓን አባቶቻችንን፣ አገላጋይ ካህናትና ምእመናንን ሁሉ ይጠበቅልን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ፣ የቅዱሳን መላእክት፣ የቅዱሳን ሰማእታት፣ ቅዱሳን አበው፣ የቅዱሳት አንስት፣ የነቢያትና ሐዋርያት ጸሎትና ቃልኪዳን፣ የአበው በረከትና ጸሎት አይለየን፡፡ ጥቅምት 10ቀን 2016 ዓ/ም አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጰያ https://t.me/bete_zemas https://t.me/bete_zemas https://t.me/bete_zemas
Mostrar todo...