cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ኢትዮ ቀልድና ቁምነገር

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
359
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የኢትዮጵያ ኮኮብ ምንድነው የሚሉ ጥያቄዎች በውስጥ እና በፌስፑክ ስላየሁ እንድታውቁት ያክል የኢትዮጲያ ኮኮብ አኳሪየስ ነው
Mostrar todo...
❤️💛ኮኮቦች በፍቅር ሚወድቁለት ነገር❤️🖤 1. "ኤሪስ" »» ራስ ወዳድ ያልሆኑ፣ አብሮ መስራትን ሚወዱ፣ ምስኪን ፀባይ ያላቸውን እንዲሁም ደጋግ ሰዎችን ይወዳሉ። ♈️ 2. "ቶረስ" »» ቤተሰባዊነት፣ ታማኝነት፣ ጠንካራና እንዲሁም ፈታ ብሎ ያለፈ ሚስጥራቸውን ሚነግራቸውን ሰው ♉️ 3. "ጄሚኒ" »» በዝርዝር ( የሚያንፀባርቅ አይን፣ እውነተኛ ፈገግታና ትሪት) እንዲሁም ሚስጥሮችን ሚያጋራቸው ሰው ♊️ 4. "ካንሰር" »» ምቾት፣ ሰማያዊ መልክ፣ ወርቃ የሆነ ልብ ያላቸው ሰዎች እና ቅኔአዊ ቀልዶችን ♋️ 5. "ሊዮ" »» ፈጣን፣ ማራኪ ፈገግታ፣ ረጋ ያለ ንክኪ፣ ዝርክርክ ያለ ፀጉርና ኮንፊደንስ ያላቸውን ♌️ 6. "ቪርጎ" »» ከግዜ፣ ከሱፍና ከረባት፣ በስራኣቱ ከተስተካከለ ፀጉር፣ መግነጢሳዊ ውበት እንዲሁም ፅድት ካለ ነገር ጋ በፍቅር ይወድቃሉ ♍️ 7. "ሊብራ" »» ተጫዋች፣ ቃሉን ሚጠብቅ፣ ጥሩ ቀረቤታ፣ ሚስጥርን መጋራትና የአለኝታናት ቃላት ልውውጥ ማድረግ በሊብራ ነጥብ ያስገኛል ♎️ 8. "ስኮርፒዮ" »» አስቂኝ ቀልዶች፣ ትርጉም አዘል ንግግሮች፣ እንዲሁም አንፀባራቂ አይታዎች ♏️ 9. "ሳጁታሪየስ"»» ነፃነት፣ late night conversation ፣ ምርጥ ፈገግታ፣ አሪፍ ስታይል እንዲሁም የሚያምር ከንፈር ♐️ 10. "ካብሪኮርን" »» ጣፋጭ የሆኑ፣ የደስ ደስ ፣ ቆንጆ ፀጉርና ተነሳሽነት ያላቸው እንዲሁም ደግና ለስራ ተነሳሽ የሆኑ ሰዎችን ♑️ 11. "አኳሪየስ" »» ጥልቅ የሆነ የአምሮ ግንኙነት፣ አሪፍ ጓደኝነትና ግሩም ስሜት ሚሰጡ ቀልዶችን ♒️ 12. "ፓይሰስ" »» መሳጭ፣ ሞቅ ያለ፣ የጋለ ሽሙጦችና አስቂኝ ታሪኮች ባለቸው ሰዎች ይመሰጣሉ።
Mostrar todo...
ለምን አሪፍ ጓደኛ ሆኗቹ ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። » ኤሪስ፦ ያነቃቁሃል፣ ምርጥ አድርገው ይሰሩሃል/ሻል » ቶረስ፦ ታማኝ ይሆኑልሃል/ሻል ፣ ምንም ቢፈጠር » ጄሚኒ፦ ምርጥ ምክር ይመክሩሃል/ሻል » ካንሰር፦ ብዙ እቅፍ ይሰጡሃል/ሻል » ሊዮ፦ ማንኛውንም ዋጋ ይከፍሉልሃል/ሻል » ቪርጎ፦ እርዳታቸው ካስፈለጋቹ ሁሌም አሉ » ሊብራ፦ ካስቀየምካቸው ይቅርታን ያደርጉልህል ። » ስኮርፒዮ፦ ያስቀየመህን/ሽን ሰው አሳደው አይለቁትም » ሳጁታሪየስ፦ ለልደትሽ/ህ ምርጥ የሆነ አቀራረብ ያዘጋጃልሃል/ሻል » ካብሪኮርን፦ ሁሉንም የቤት ስራሽን/ህን ይሰሩልሃል/ሻል » አኳሪየስ፦ ፈገግ እንድትይ/ትል ያደርጉሃል » ፓይሰስ፦ ይወዱሃል/ሻል፣ አንተን\ቺን መውደድ ባይኖርባቸውም እንኳን .
Mostrar todo...
በመጀመሪያ እይታ ኮኮቦችን ስንቃኝ፣ ምን ይመስላሉ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ »» ኤሪስ ፦ እንደተገናኟቻቸው ምቾት ሚሳጥ ባህሪና ግልፅ ስለሆኑ፣ እናንተም ማንነታቹን የመለወጥ አዝማሚያ አታሳዩም። ተነሳሽነትና ትልቅ ሀይል ስላላቸው ለማንም ብርታት ይሆናሉ። »» ቶረስ ፦ ለማውራት ቅልል ያሉ እንደሆኑ ትረዳላቹ፣ የፈላጋቹትን አይነት ጥሩም ይሁን መጥፎ ታሪካቹን ብትነግሯቸው ምንም አይመስላቹም፣ ምክንያቱም ቶራሶች ሚሰማቹን ይሁን ምታስቡትን ስሜት ይረዷቸዋልና። »» ጄሚኒ ፦ ለምንም ነገር ዝግጁ ናቸው፣ ሁሉም ጄሚኒዎች የሆነ ቦታ መሄድ ይፈልጋሉ፣ አንድ አንዴ የት እንደሆነ ላያዎቁትም ይችላሉ፣ ብቻ ደስታና ለየት ያለ ልምድ ሚገኝበት ቦታ ቀልባቸውን ይስበዋል። የፈለጋቹት ቦታ ለመሄድ ጄሞዎች ቀዳሚ አጋሮቻቹ ናቸው። »» ካንሰር ፦ ካንሰሮች ልስልስ የሆነ ልብ ሲኖራቸው፣ ሁሉም ሰው ደስተኛ ማድረግ ቢችሉ ደስታቸው ነው፣ ምርጥ አዛኝ ልብ አላቸው። »» ሊዮ ፦ ትልቅ ተነሳሽነት አላቸው፣ ለሁሉም ነገር ዝግጁ ነው ሚመስሉት፣ ሊዮዎች ስለሆነ እቅድ ወይም ፕላን ሲናገሩ፣ እንዴት በራስ መተማመናቸው ጉልህ እንደሆነ ታስተውላላቹ ። »» ቪርጎ ፦ በጎ እንደሆኑ በግዜ ሂደት ማንም ሰው ይረዳቸዋል፣ የተሻለ ቀናቶችን እንድታሳልፉ ያግዟቸዋል፣ እውነተኛ ጓደኛ ናቸው፣ የናንተም እውነተኛ ፍላጎት ሲታከል። »» ሊብራ ፦ የሰውን ስሜት እንደራስ ማየት ይችላሉ፣ አይኑን ብቻ በማየት ምን እንደሚሰማው፣ ምን እንደፈለገና ማን እንደሆነ መረዳት ይችላሉ። »» ስኮርፒዮ ፦ ስኮርፒዮች ፀጥ ያሉና ብዙ የተለየ ነገር ማይነበብባቸው ሲሆኑ፣ ወደ ህይወታቸው ሰው ቶሎ አያስገቡም፣ የገባ ግን በብዙ የታደለ ነው ሚሆነው ። »» ሳጁታሪየስ ፦ ደግ መሆናቸውን ለመረደት ምንም ግዜ አይፈጅባቹም፣ ለሀገሩ እንግዳ እንዲሁም ከዚ በፊት አይተውት ማያቁትን ሰው ቢያዩ እንኳን ከመርዳት መቼም ወደ ዋላ አይሉም። »» ካፕሪኮርን ፦ የህይወት ቅመም ናቸው፣ ከካፔዎች ጋ ተገናኝታቹ ወደ ላይ ለመውጣትና ለማደግ ያላቸውን ፍላጎት አለማክበር ይከብዳል፣ ያደርጉታልም። »» አኳሪየስ ፦ አዕምሯቹን ያነበቡት ይመስል፣ ለመናገር ያሰባቹትን እንዳለ ያውቃሉ፣ እነሱም ቢሆኑ ሚሰማቸውን ከመናገር ወደ ዋላ አይሉም። »» ፓይሰስ ፦ ስሜታዊ ናቸው ለአንተ/ቺ፣ ለአከባቢያቸውና ለሚወዷቸው እንዳለ ንፁ መልካምነት ይሰጧቸዋል። Share
Mostrar todo...
>>>➪ ከጥንት ጀምሮ የነበሩ የሰው ልጆች ዋና ጥያቄዎች ሆነው የቆዩ ቢሆንም አሁን ባለንበት ዘመንም በዘመናዊ የሳይንሳዊ ምርምር መስኮች ውስጥ ትልቅ ትኩረት ከሚሰጣቸው ዘርፎች ውስጥ ስነ-ህዋ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዋነኞቹ ናቸው። ስለ እልፍ አዕላፍ ስነ-ከዋክብት፤ አፈጣጠራቸው ከሰው ልጅ ውጭ ሌላ አለማት/ ስልጣኔዎች ስለመኖራቸውና ስላለመኖራቸው ወዘተ… የተለያዩ ሳይንሳዊ መላ ምቶችን መሰረት አድርገው የመስኩ ሊቃውንት በትኩረት እያጠኑ ይገኛሉ። >>>➪ ይህ አዲስ ቢመስለንም ወይም አዲስ ነገር ፍለጋ ወደ እነዚህ ዘመናዊና የሳይንሳዊ ምርምር ውጤቶች ብናዘነብልም የቀደሙ የሃገራችን ጥንታዊ አባቶች ስለ ሰማያትና የተለያዩ አለማት በተሰጣቸው መገለጥ (እምነት) መሰረት ብዙ ጽፈውልን ያለፉ ነገሮች አሉን። >>>➪ ከዘመናዊ ሳይንሱ (Horoscope or Astrology) ጎን ለጎን እነዚህን ሃገር በቀል ምንጮችንም ቃኘት ማድረጉ አይከፋምና ስለ ሰማያት፣ህዋና ክዋክብት አለማት ተጽፈው ከተገኙት ውስጥ የግዕዝና ቅኔ ሊቅ በሆኑት በመሪ-ራስ አማን በላይ አማካኝነት ከግዕዝ ተተርጉሞ ከታተመ 'መጽሐፈ ብሩክ..ዣንሸዋ ቀዳማዊ' ከተሰኘው መጽሃፋቸው ውስጥ በመውሰድ ለየትኛውም አንባቢ እንዲመች አድርገን በመቅዳት ጥቂቱን ልናካፍላችሁ ወደድን። >>>➪ ቀጥሎ የሚገለፁት በክዋክብቱ ግዛት ውስጥ የሚኖሩ፣ የሚመሩ ፍጡረ-ረቂቃን ሲሆኑ ባህሪያቸውንና መንደራቸውን እንዲሁም የአስተዳደራቸውን ሁኔታ የምናይበት ነው። #ሐመል♈️ ይህ የምድር ሠራዊት እንሆን ዘንድ እኛ የተፈጠርንበት ዓለም ነው። ጠባቂውና እንዲሰለጥንበት አምላክ የፈቀደለት ፍጡር ነው። የመጀመርያው ሰው ነገድ ሁሉ ከእርሱ አብራክ ወጥቶአል። #ሠውር♉️ በዓለም ሰውር ውስጥ የሚኖሩ ፍጥረቶች የበግና የፍየል መልክ የመሰለ ገፅ ሲኖራቸው የተሰጣቸው አእምሮ ከሰው ልጆች የላቀ የራቀውን የሚያውቁ የረቀቀውን የአምላክ ፍጥረትን ማየት የሚችሉ ናቸው። ከነርሱም ሌላ በረሐም ዓለም ውስጥ የተለያዩ ገጽ ያላቸው ቁጥራቸው ትእልፈተ-ትእልፊታት ፍጥረታቶች አሉ። #ገውዝ♊️ ገውዛውያን መልካቸው እንደ ሰው ልጆች መልክ ሁኖ ቀንድና ጅራት አላቸው። መልካቸው የዝንጆሮና የጉሬዛ መልክ የሚመስሉም አሉ። ግዙፋንና እረቂቃን የሆኑ በራሪዎች ይኖሩባቸዋል። እርስ በእርሳቸው አይነካኩም። #ሸርጣን♋️ በሸርጣን ዓለም የሚኖሩ ፍጥረቶች እንደ ዳሞትራ ስምንት እግሮች ያላቸው የአንበጣ ገጽ ያላቸው ምግባቸው እርስ በእርስ በመበላላት አንዳንዶችም እንደ እባብ የሚያሸቱበት አፍንጫ ባይኖራቸውም በምላሳቸው መካከል ባለ ቀዳዳ ያሸታሉ፣ በምላሳቸው ይነድፋሉ፣ ያያሉም። በየጊዜው ተፈጥረው የሚሞቱ ፍጥረቶች ናቸው። #አሰድ♌️ አሰዳውያን ወደዚህ ዓለምና ወደ ሌላው ዓለም ለመንጠቅ እድል ተሰጥቷቸዋል። በሄዱበት ምድር ያለውን እፅዋት ያደርቃሉ፤ እሳተ ገሞራ ይፈጥራሉ፤ ተንቀሳቃሹን ሁሉ በነፋስ ያደርቁታል፤ ምግባቸው የሚያቃጠል ዲንና ባሩድ የመሰለ ነው። #ሰንቡላ♍️ በሰንቡላውያን ዓለም ትእልፊተ-ትእልፊታት የሚሆኑ በአየር የሚንሳፈፉና የሚበሩ በምድር የሚሽከረከሩ አእዋፋትና እንስሳት አራዊትም አሉ። እንደነዚህ ምድር ዓለም እርስ በእርሱ ይጣላል፤ ይበላላልም። ነገር ግን የማይበላሉ አሉ እነርሱም እድሜያቸው በእነሱ አቆጣጠር ከመቶ እስከ አራት መቶ ይደርሳል። ነገር ግን የእኛ ዘመንና የሰንበላውያን ዘመን የተለየ ነው። #ሚዛን♎️ መልካቸው የእንስሳና የአውሬ መልክ ይምሰል እንጂ የተፈጥሮ ባህሪያቸው ቅዱስ ነው። አምላክን በክብር ያመሰግናሉ ይዘምራሉም። ከኤሮርያ ሰማይ ክልል ውስጥ ከሜምሮስ ዓለም ክበብ ውስጥ የሚኖሩትን ሮሃንያን ይመስላሉ (ረውሃንያ) የተለያዩ የዜማ ድምፅ መሥሪያዎች አሏቸው። አንዳንድ ጊዜ ወደ እኛ ዓለም ምድር ይመጣሉ፤ የሚከለክላቸው የዓየር ጠባይ የለም፤ ግዙፋንም እረቂቃንም አሉአቸው። በባሕር ቢሄዱ አይሰጡም በእሳተ ገሞራ ቢገቡ አይቃጠሉም አለቱን ሰንጥቀው ቢገቡ የሚያግዳቸው የለም። የአምላክን ፍጥረት ያከብራሉ የሰው ልጆችን ይወዳሉ። #አቅራብ♏️ በዓለም አቅራብ ውስጥ የሚኖሩት ፍጥረታት በባሕር ውስጥ ይኖራሉ። ገጽ የዝሆንና የጊንጥ ቅርፅ አላቸው። የተለያዩ የፍጥረት ነገዶች አሉ ሁሉም በበሐር ውስጥ እንጂ ወደሌላ የአፈርና የእሳት ጠባይ ወደአላቸው አይሄዱም አይኖሩምም። #ቀውስ♐️ በቀውስ መሬት የሚኖሩ ከእሳት ተፈጥረው ከእሳት ፈሳሽ ውስጥ ስለሚኖሩ ብዛታቸው እንደሌሎች ዓለም ፍጥረት አይበዙም ቀውሳውያን የአገኙትን ይመገባሉ ያቃጥላሉ የእሳት ሕይወት ነው ያላቸው። #ጀዲ♑️ በጀዲ ወይም በዠዲ ዓለም የሚኖሩ ፍጥረታት ከዚህች ምድር ዓለም የተፈጠሩትን እንስሳትና አራዊት አእዋፋትንም ይመስላሉ። በመልክ በገጽ እርስ በእርሳቸው የተለያዩም ቢሆን በልሳን ቋንቋ አንድ ናቸው በተለያየ የድምፅ መሳሪያ ይጠቀማሉ። ከሰው ልጆች የላቀ አእምሮ ስላላቸው የተጠበቡ መርማሪዎች ናቸው። በሰሩት የጥበብ መንኮራኵር ብዙ ዓለማትን ጎብኝተዋል ነገር ግን ከተፈጠሩበት ከጀዲ ዓለም ተለይተው ስለማይኖሩ ወደ መጡበት ተመልሰው ይከትማሉ። ምግባቸውን እንደ ሰው ልጅ አብስለው የሚበሉና በመአዛው ብቻ የሚረኩ ነገዶች አሉአቸው አምላክን በጣም ያመሰግናሉ። #ደለዊ♒️ ይህ ደለዊ ዓለም የክበቡ ጥልቀት በጣም የጠቆረ ጨለማ ከመሆኑ የተነሳ እንደበርባሮስ የሚያስፈራ ነው። ነገር ግን በውስጡ የሚኖሩ እልፍ አእላፋትና ትእልፊተ አእላፋት የሚሆኑ ፍጥረታት በትናጋቸውና በምላሳቸው በማሽተት የሚፈልጉትን መርጠው ይበላሉ:: በጆሮአቸው በዓይናቸው ፈንታ በምላሳቸው እንዲያዩና እንዲሰሙ አምላክ ስለፈጠራቸው ጨለማንና ብርሃንን ለይተው አያውቁም። #ሁት♓️ በሁት ዓለም የሚኖሩ ፍጥረቶች እንደንብ መንጋ በአንድ ላይ የሚሰፈሩ እንደተራራም የሚከመሩ ናቸው፤ ከመካከላቸው እንደንብ አንዲት እናት አላቸው። እናቲቱ እድሜዋ አልቆ ከሞተች ሁሉም በነው ያልቃሉ አፈር ይሆናሉ፤ በሕይወታቸው ለእንስቲቱ ብቻ ሲሉ ይቆያሉ። በዚያ ከነሱ ሌላ ሕይወት ያለው ፍጥረት የለም። .
Mostrar todo...
ሌላ እንዲሰራልዎት የሚፈልጉት ካለ ኮመንት ላይ አሳዉቁን
Mostrar todo...
የእናንተ ተስማሚ የስራ መስክ ??? ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ――――  "ሊዮ"―――― Follow the Leo, The star »» ሊዮዎች መስራት የሚፈልጉትን ነገር መስራት ይችላሉ፣ ብዙ ነገር ውስጥም ተሳትፎ ያደርጋሉ፣ ይሳካላቸዋልም። ግርማ ሞገሳም፣ አስተዋይ፣ ደፋር፣ እብድ፣ ፖዘቲፍ ኢነርጂና በመሪነትም ማንንም ማስገረም ይችላሉ፣ እስከሁን አለም ላይ ብዙዎቹ ፕሬስዳንቶችና መሪዎች ሊዮ ናቸው። በሀገራችንም እነ ዶ/ር አብይ አህመድና ኦቦ ለማ መገርሳን መየት እንችላለን። »» የሚሰሩትንም ስራ በአግባቡና አድሏዊ ባልሆነ መንገድ መስራት ነው የሚፈልጉት፣ ብዙ እቃዎችን ኦርደር በማድረግ፣ ፓርቲዎችን በመውደድና ዘና ማለትን ይወዳሉ፣ በተፈጥሯቸውም ሰው እንዲከተላቸው ማድረግ ይችላሉ፣ የሚሰሩትንም ስራ ያለምንም ተፅኖና ፍራቻ፣ በጥልቅ ተነሳሽነትና ወገንታዊነት ይሰራሉ፣ ሰማይ እንዳሉ ኮኮቦችም የሚፈልጉት ነገር ብዙ ነው፣ በሰሩት ስራም ምስጋናና ክብር እንዲሰጣቸው ይፈልጋሉ። ደፋር ቢሆኑም ውስጥ ውስጡን ፈራ ይላሉ። »» ተራ ሰራተኛ ወይም ከመጋረጃ ጀርባ የሚሰሩ ሰዎች አይደሉም፣ አይወዱምም፣ ካልሆነም ስራውን ለቀው ይሄዳሉ። ጭምቱም ሆነ ግልፁ ሊዮ፣ ቶሎ እንዲታወቁና እንዲደነቁ ይፈልጋሉ፣ ሁሉም ሊዮዎች የማዕረግ ስም ይወዳሉ፣ አመራር የመስጠት ፍለጎት በልባቸው ስር የሰደደ ነው ። √√ ጥሩ እሴቶች »» ኮንፊደንሳም፣ ተስፈኛ፣ ኢንተርፕሬነር፣ ደግና ሀይለኛ ናቸው፣ መስራት የሚፈልጉትም ስራ የእነሱን የተለያየ ብቃት የሚያሳይ ቢሆን ይመረጣል። እንዲሁም አስተዋፅዖ ማድረግ የሚችሉበትን። √√ ስኬታማ የስራ መስክ »» ኢንተርፕሬነር፣ ፕሬዝዳንት፣ ኢንተርቴይመንት፣ ፖለቲካ፣ ህዝብ ግንኙነት፣ ሴናተር ፣ ሙዚቀኛ፣ CEO ፣ አስተማሪ፣ አስጎብኚ፣ የሪልስቴት ባለቤት፣ ፋሽን ዲዛይነር፣ ሽያጭ፣ ሶሻል ሚዲያና የመሳሰሉት ላይ ምርጥ ናቸው። √√ ተስማሚ ያልሆኑ መስኮች »» ማንኛውም አይነት ስራ ይሁን፣ ጎልተው መውጣት የማያስችላቸው ከሆነ አይመቻቸውም።
Mostrar todo...
ምን አይነት ተማሪ ኖት???? ―――― ሊዮ―――― ( ከሀምሌ 17 እስከ ነሀሴ 17 የተወለዱ) »» ሊዮ ተማሪዎች ሁሌም ክን'ፍ እንዳሉ ነው፣ ህይወትና ትምህርትን ቀለልና ሳያካብዱ ሚኖሩ አስደሳች ተማሪዎች ናቸው። ክፍል ውስጥም ያለምንም የፆታ ልዩነት ከማንም ጋ መኖር ሚችሉ ተግባቢ ናቸው። የመሬት ኮኮብ ተፅኖ  ካልጎላባቸው በስተቀር ከግቢም ሆነ ከግቢ ውጪ ምንም አይነት ፓርቲ ከለ አይቀሩም። እዛው ፓርቲ ላይም የሆነ የክላስ ልጅ ተዋውቀው፣ የረሱትን የቤት ስራ አስታዎሶ ሚሰራላቸው ወዳጅም ያገኙ ይሆናል፣ ጥሩ እድል አላቹ። »» የሊዮ ገዥ ፀሀይ ማንንም ማስተዳደር ትችላለች፣ ሊዮዎችም ማንኛውንም አይነት ስራ ይስሩ ማንንም መሳብ ይችላሉ፣ አንድ አንዴ ትምህርት ላይ ሊዘናጉ ይችላሉ፣ ነገር ግን እንደተዘናጉ ካወቁ ቶሎ ወደ ቀድሞ ብቃታቸው ለመመለስ ይሞክራሉ። ነገሮችን ቶሎ መረዳት ይችላሉ፣ ጥሩ ተማሪ ብቻ ሳይሆን ጥሩ አስተማሪም መሆን ይችላሉ። »» ብዙ ተማሪዎች በሚስጥር የሊዮ አድናቂ ናቸው። ክፍል ውስጥም በሚፈጠረው ነገር ግድም አይሰጣቸውም፣ ነገር ግን አስተማሪ ወይ ተማሪ ብቻ ሰው በሚበዛበት ቦታ ላይ ከተሳደቧቸው፣ ከተቆጧቸውና ካመናጨቋቸው በጣም ነው ሚናደዱት፣ ሊጣሏቸውም ይፈልጋሉ።
Mostrar todo...
#ሊዮዎች ለምን ይከፋሉ  ------------------------------------- »» ማንም ዞዳይክ እንደ ሊዮዎች ሀዘናቸውን ተውኔታዊ ሚያደርግ የለም፣ እስከመጨረሻው ሽርፍራፊ ተስፋ ወይም ጥልቅ የሀዘን ስሜት እስኪሰማቸውና አስኪፈነዳ ድረስ ይይዙታል። ለምን እንደዛ እንደሆነና እንዴት እንደተፈጠረ አጥብቀው ያስባሉ፣ በቶሎም ለመቀበል ይቸገራሉ፣ ከባዶ የመጣ ሀዘን፣ ምክንያት የለሽ ሀዘንም ሚሆንበት አጋጣሚ አለ። ሊዮዎች ሀዘን ውስጥ እንኳን ሆነው ያላቸው ተነሳሽነት ትልቅ ነው። »» ሀዘን ውስጥ በሚሆኑበት ግዜ፣ ለስሜታቸው ከለላ ሚሰጡላቸው ታማኝና ቅርብ ጓደኞቻቸው አብረዏቸው ቢሆኑ ተመራጭ ነው። ሊዮዎች ሁሌም ቢሆን ለተሻለ እቅድ ሚሰሩ ሰዎች ናቸው፣ ምንም ይፈጠር ምን ለራሳቸው ይቅርታ ማድረግና ምንም ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ማሰብ ይኖርባቸዋል፣ በቶሎም ካሉበት እንዲላቀቁ ያግዛቸዋል። ማንኛውም ነገር ይሁን ሊዮዎች ሚፈልጉትን ነገር ካላገኙ ይናደዳሉ። እነሱ ላይ ትኩረት እንደበዛ ካሳቡ የበለጠ እየጠነከሩ ይመጣሉ፣ በሚኖሩትም ሆነ በሚያደርጉት ሁኔታም ሆነ ውሳኔ እርግጠኛ ስለሆኑ፣ የመከፋትም ሆነ የማዘን ሁኔታ አያጋጥማቸውም፣ ቢያጋጥማቸውም ምንም እንዳልተፈጠረ ያልፉታል። »» ሰዎች ካሉበት አከባቢ ሊያነሷቸው፣ ሊያሳንሷቸው ካሳቡ ይናደዳሉ፣ አይደለም በሌሎች ኔጌቲቭ አስተሳሰብና በራሳቸው ኔጌቲቭ አስተሳሰብ ሁላ ሚናደዱ ሰዎች ናቸው፣ ቅን ናቸው። በተቻላቸው መጠንም ከኔጌቲቭ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ራሳቸውን ቢያርቁ ተመራጭ ነው። ሊዮዎች በሚከፉበት ግዜ ከሰዎች ጋ ብዙ አይገናኙም፣ ለራሳቸውም ያላቸው አመለካከት ይወርዳል። ቅርብ ጓደኞቻቸው ወደ ሆነ ዝግጅት በመጋበዝ ወደ ቀድሞ በራስ መተማመናቸው በቶሎ እነሱን ለመመለስ ቀላሉ መንገድ ነው። »» የህይወታቹን የስኬት ከፍታ ማንም ሰው ሊቀማቹ አይችልም፣ ስለዚህ ስላለፈው ስኬታቹ ማሰብ ትታቹ አሁን ላይ ስለሚጠብቃቹ ፈተናና ስራ ለናንተ ወሳኝነት አለው፣ በተለይ ለወደፊት ደስታቹ። ሊዮዎች ያላቸውን ማንነት ማንም ሰው ሊንድባቸው መሞከርም ሆነ ማሰብ የለበትም፣ አይቻልም፣ እነሱም አይፈልጉም፣ ደስታም ያሳጣቸዋል። እነሱን ለማሳነስ መሞከር ትልቅ ጥፋት ያመጣል፣ የተከፋ ሊዮ ስሜቱ ቅርብ፣ ንዴታቸውም ቅስበታዊ ስለሆነ፣ በዚ ግዜ ማንንም አይሰሙም።
Mostrar todo...
ከሐምሌ 17 እስከ ነሐሴ 17 ለተወለዳቹ በሙሉ ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። »» ዞዳይካቹ ሊዮ ይባላል »» ትምክታቸው ያስደነግጣል፣ ፈገግታቸው ደግሞ ያስደምማል። ለሊዮ ሰዎች ትእቢት የሞላበት ጉራ እና ፀሐይ ሞቅ ያለን ተጫዋችነት በአንዴ ይዞ መገኘት የተለመደ ነው። »» ሊዮን ለማግኘት ከፈለክ በከተማው ውስጥ ብሩህና አንፀባራቂ ከሆኑ ቦታዎች አፈላልገው፣ ሊዮ ሰው ጨለማና ድባት ነገር አይወድም፣ ገዥ ብላኔቱ ፀሀይ ነች »» በቀላሉ የሚያፍር ሊዮ ማግኘት ይከብዳል፣ ፊቱ ከድካም እና ከጭፈራ ብዛት የተነሳ ቲማቲም ሊመስል ይችል ይሆናል እንጂ ወፍ። »» ራሳቸውን በፍፁም ዝቅ አድርገው አይመለከቱም፣ ሆድ ይፍጀው የሚለው ነገርም የላቸውም፣ ዝምተኛ መስለው የሚታዩ ሊዮዋች አሉ ፣ በውስጣቸው ግን ጠንካሮችና ክብራቸውን የሚጠብቁ ናቸው። »» ሴቷ ሊዮ ቀልጣፋ እና ደንጋጣ መስላ ትታያለች ፣ እንቅስቃሴዋ ግን በግርማ ሞገስ የተሞላ ነው። በሊዮ ገፅታ ላይ የአዛዥነትና የበላይነት መንፈስ ሁሌም እንደሰፈነ ነው፣ ንግግሩም የታሰበበትና በእርጋታ የተሞላ ነው። »» ሊዮዎች ምክርን በነፃ መስጠት ያስደስታችዋል፣ ያፈቁሩታልም፣ ይህን ሲያደርጉ ካንተ በላይ አውቃለው በሚል መንፈስ ነው። »» የሊዎዋች የበላይነት መንፈስ በቅንነት የተሞላ ነው። በብዙ ችሎታው ወደር የሌለው ነው ፣ የእኔነት ኩራቱ ግን ለጉዳት የተጋለጠ ነው። »» አፍቅሬ ውዳሴም ናቸው፣ እጅግም ሲበዛም ብልጥ ናቸው። ፍቅር ምግባቸው ነው ፣ ፍቅርን ይወዳሉ፣ በሌሎች ትከሻ ላይ መደገፍን በፍፁም አይወዱም። »» ሊዮዎች አባ ዝራው ናቸው ፣ ስስትና ቁጠባ ሊዮዎች በዞረበት አይዞሩም፣ ማእረግና ቅንጦትን ይፈልጋሉ፣ አንዲት ሊዮ ምን ቆጣቢ ብትሆንም በጣም ውድ የሆኑ ልብሶችን መግዛትዋ አይቀርም። »» ሊዮ ታማኝ ጓደኛ፣ ኅይለኛም ወዳጅም ነው። ጠላትም ሲሆን እንደዛው ነው። »» ስላክብርና ስላዝናቸውም ይጨነቃሉ ግን ደግ እና ሩህሩህ ናቸው። .
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.