cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

መዝሙር ዘተዋሕዶ

✞ ማርያም ስምኪ ጥዑም (2X) ❤ ✞ ማርያም ስምሽ ይጣፍጣል ❤ በዚህ ቻናል የኦርቶዶክስ ዝማሬዎች ይገኛሉ ኑ አብረን እናመስግን 🙏🙏🙏✞✞✞🙏🙏🙏 ይቀላቀሉን .https://t.me/joinchat/g80kykCL0883MTI0 መዝሙር መጋበዝ ለምትፈልጉ @yitbar

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
3 547
Suscriptores
Sin datos24 horas
-147 días
-8030 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Mostrar todo...
Adones Zema አዶኒስ ዜማ is going live!

"አ…ት…ማ…ረ…ኝ" #ጸሎትሰ ይእቲ ተናግሮተ ሰብእ ኀበ እግዚአብሔር ልዑል። (ጸሎትማ ይኽች ናት ሰው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገርባት) ‘ሚጸልይ ሰው ጸሎቱ ወደ እግዚአብሔር የሚሳብበት ይሁን አፍ ንባብ ይነዳ ልብ ጓዝ ያሰናዳ እንደሚለው ዓይነት እንዳይሆን! (ወአንብቦቱኒ ትኩን ዘባቲ ይከውን መንፈስ ዘያንሠሐሰሐ መንገለ ፈጣሪ) በሕሊናችን የምንጸልይ ብንሆን በጎ! በአንደበታችን የምናነበንበው ቢሆን ደግሞ ለልቡናችን እንንገረው በአንደበታችን የምንናገረውን ሕሊናችን ይተርጉመው! [እመኒ በሕሊና ባሕቲቱ፤ ወእመኒ በልሳን፤ ከመ ይተርጕም ለሕሊና] ......ዛሬ አትማረኝ ዋሻ ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ ሲደርሱ አንድ አባት ዋሻው ውስጥ “አትማረኝ - አትማረኝ- አትማረኝ” እያሉ ሲጸልዩ ያገኟቸዋል......(የአፍ ቃሉ አትማረኝ በሕሊና መሻት የልብ ትርጉሙ ግን ማረኝ) አቡነ ያሳይ ከሰባቱ የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደቀመዛሙርት መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ወደ ጣና ደሴት ከአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ጋር በመሆን በጸሎት ይተጉ እንደነበር ገድላቸው ይናገራል፡፡ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸውም ጸጋ በጣና ሐይቅ ላይ እንደ ጀልባ የሚጓዙበት አንድ ጠፍጣፋ ድንጋይ /ዛሬም ድረስ በገዳማቸው ውስጥ ይገኛል፡፡/ በጣና ደሴት ላይ ለአገልግሎት በመፋጠን ላይ እያሉ ዛሬ አትማረኝ ዋሻ ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ ሲደርሱ አንድ አባት ዋሻው ውስጥ “አትማረኝ - አትማረኝ- አትማረኝ” እያሉ ሲጸልዩ ያገኟቸዋል፡፡ አቡነ ያሳይ በሰውዬው ጸሎት በመገረም ቀርበዋቸው “አባቴ ምን ዓይነት ጸሎት ነው የሚጸልዩት?” አሏቸው፡፡ “አባቴ እንደ እርስዎ ያሉ አባት መጥተው “አትማረኝ” እያልክ ጸልይ ብሎኝ ነው በማለት መለሱላቸው፡፡ “እንዲህ ዓይነት ምክር የሚመክር ጠላት ዲያብሎስ ነው፡፡ ከዛሬ ጀምረው “ማረኝ” እያሉ ይጸልዩ በማለት አቡነ ዘበሰማያትን አሰተምረዋቸው ይሄዳሉ፡፡ አትማረኝ እያሉ ይጸልዩ የነበሩት አባትም “ማረኝ” እያሉ መጸለያቸውን ቢቀጥሉም ብዙ መግፋት ሳይችሉ ጸሎቱ ይጠፋባቸዋል፡፡ ጸሎቱን ያስጠኗቸው አባት አቡነ ያሳይ ርቀው ሳይሄዱባቸውም በውኃ ላይ እየተራመዱ በመከተል ይደርሱባቸዋል፡፡ “አባታችን ያስጠኑኝ ጸሎት ጠፋብኝ፡፡ እባክዎ ያስተምሩኝ” ይሏቸዋል፡፡ አቡነ ያሳይ የእኚህ አባት መብቃት ተመልከተው “አባቴ እግዚአብሔር የልብ ነውና የሚመለከተው እንዳስለመዱት ይጸልዩ የእርስዎ ይበልጣል” ብለዋቸው ይሔዳሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ቦታው አትማረኝ ዋሻ ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ዛሬስ የበዛው #በአፉ_ማር  #በልቡ_አትማር ባይ ነውና ኃጢኣት በአፋችን እየረገምን በልባችን ግን አጥብቀን የምንመኛት ድኩማን ነንና የልቡናችንን እግሮች ወደሰላም መንገድ ያቅናልን! ያኔ የልቡናን መሻት ዐይቶ እንደቸርነቱ ሁሉን ይማር !
Mostrar todo...
Mostrar todo...
#shorts #ቅዱስ_ሲኖዶስ #shorts #shortsvideo #shortsfeed #shortsyoutube #shortsviral #shortsbeta #shors_

#shorts #shortsvideo #shortsfeed #shortsyoutube #shortsviral #shortsbeta #shorts_video #shortsindia #shorts_ #shorts #short #shortsvideo #orthodox #orthodox_...

የእግዚአብሔር ልጅ የአብ የመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ስምህን ሲክዱ በእጃቸው ለሰሩት ጣዖት ሲሰግዱ ባየና በሰማ ጊዜ ከአንተ በቀር ሌላ ረዳት ሳይሻ በሰ፸ው ነገስት ፊት የቆመውን ይህንን ሰማዕት አመሰግነው ዘንድ ልቤን አብራልኝ አፌንም ክፈትልኝ ያንጊዜ በነገስታቱ ፊት ህግህን እናገራለሁ አላፍርም ያለውን የዳዊትን ቃል ፈጸመ። ይህ ቅዱስ ሕፃን ሲሆን የግሩማን ነገስታትን ፊት አልፈራም። ቃልህ ሕፃናትን ዐዋቂ ያደርጋልተብሎ እንደተነገረ ፯ት ዓመት በአሰቃዩት ጊዜ አልተበሳጨም ቸል አላለም የማይታየውን መንግስተ ሰማያት ተስፋ አድርጓልና። ብዙ መከራ በመቀበል በመድከም በመሰንጠቂያ በብረት ምጣድ በመገረፍ በመራቆት በረኃብ በጽም በመስቀል በመቸንከር በእሳት በሰይፍ መከራ ተቀበለ። የዚህ ሰማዕት ስቃዩ ብዙ ነው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተቀበለው ህማም አንዲቱም ብትሆን ለሞት የምታደርስ ናት። መዋቲው በሕያውነቱ ይለወጥ ዘንድ በርሱ ላይ ሌላ ልንለብስ ነው እንጂ ከርሱ ልንለይ አንወድም ያለውን ዳግመኛም የኋላየን እተዋለሁ ያለውን ወደ ፊቴም እገሠግሣለሁ ያንንም እከተላለሁ ያለውን ሐዋርያውን ጳውሎስን መሰለው።በዚህም ሁሉ መከራ ፯ት ዓመት ጨረሰ። ገድለ ጊዮርጊስ ም፲ ከቁ (2___3) የተወሰደ። የቅዱስ ጊዮርጊስ በረከት አይለየን።አሜን!
Mostrar todo...
ስለ ጌታ እናት ስለ ድንግል ማርያም ሲፃፍና ሲነበብ ሲዘመርና ሲሰበክ የሚከፋቸውና የሚቆጫቸው እንዳሉ ሁሉ የሚደሰቱትም ብዙ ናቸው።ምክነያቱም የጌታ እናት መሆኗ ብቻ ሳይሆን ከፍጥረት በላይ የገነነች ለፍጥረት ሁሉ የድህነት ምክነያት ቤዛ ሆና ከፍጥረት ተመርጣ ለፍጥረት ከፈጣሪ የተሰጠች ንፁህ ዘር እንደሆነች ስለአመኑ ነው። ት ኢሳ(1÷9) ማንም እግዚአብሔርን እወደዋለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሀሰተኛ ነው ይላል።1ኛ ዮሐ(4÷20) ዘወትር ከኃጢአትና ከበደል መለየት ያልቻለው ወንድማችንን እንድንወድ ከታዘዝን በንፅህና በቅድስና ሆና ጌታን የወለደች የጌታን እናት ድንግል ማርያምን ለመውደድ እንዴት አቅም አጣን? በሌላም ስፍራ ኢየሱስ ክርስቶስ ጠላቶቻችሁን ውደዱ በማለት አስተምሯል።ማቴ(5÷45)ታዲያ ይሄንን ቃል አምነን ከተቀበልንና ጠላቶቻችንን የሚወድ ልብ ካለን ድንግል ማርያምን የሚወድ ልብ የሚያመሰግን አንደበት እንዴት ላይኖረን ቻለ? አብርሐም እግዚአብሔርን በመታዘዙ የሚባርኩኸን እባርካለሁ የሚረግሙህንም እረግማለሁ የሚል ቃል ኪዳን እግዚአብሔር ከገባለት ዘፍ(12÷1)አብርሃምን የረገሙት ሰዎች ከተረገሙ የባረኩት ደግሞ ከተባረኩ እናት ሆና በጀርባዋ አዝላ በመከራ የተንገላታች ድንግል ማርያምን የረገመ እንደሚረገም የባረካት እንደሚባረክ የናቃት እንደሚናቅ ያከበራት እንደሚከበር እንዴት ማወቅ አቃተን? ብርሃን የሆነ ልጇን አምኖ ብረሃነኝ ካለ ሕይወት የሆነ ልጇን አምኖ ሕይወት አለኝ ካለ ብርሃንን ወልዳ እመብርሃን የተባለች ድንግል ማርያምን መናቅና ማጣጣል ከበርሃንም ሆነ ከሕይወት ተርታ መውጣት ከትውልድ ሀረግም መሰረዝ ነው። እኛግን ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል ብላ የተናገረችውን ቃል ከልባችን ተቀብለን ብፅዕት በማለት ትውልድ መሆናችንን እናረጋግጣለን።
Mostrar todo...
🚹 ከማንም ምስጋና ሳትጠብቅ የምታገለግለው አገልግሎት እንቅፋት ቢበዛው እንኳ እንቅፋቱን እርሱ ያነሳልና ከማገልገል ችላ አትበል። 🚹 መንፈሳዊ አገልግሎት ሰማያዊ ክብር የምትጎናፀፍበት እንጅ ሥጋዊ ክብር የምትሸለምበትና የምትሾምበት ሥጋዊ መድረክ አለመሆኑን አውቀህ የምታገለግል ከሆነ አንተ ልክነህና በጊዜውም ይሁን ያለጊዜው ፅና። 🚹 ከማንም ሰው ፊት የመሆን እድል ከገጠመህ ከጀርባህ ለሚከተሉህ ሁሉ የመልካም ነገር አስተማሪ እንጅ እንቅፋት አትሁን።ከፊት መሆን የተሳነህ ከማንም ኋላ ያለህ ሰው ብትሆንም ከፊትህ ለአሉት ሁሉ ድጋፋ እንጅ ወደ ኋላ የምትጎትት ሰነፍ ከመሆን ራስህን ጠበቅ። 🚹 ማንም ስለታገለህ አትወድቅም አንተ የምትወድቀው በራስህ ሥራ ነው።ሥራህ የአንተን ክብርም ሆነ ውርደት ይናገራልና ሥራህን ገምግም። 🚹 የቆምክበትን ምክነያትና ያቆመህን ማወቅ እንጅ ስለወደቁ የሰዎች ውድቀት ማውራት መቆምህን አያረጋግጥም።
Mostrar todo...
Mostrar todo...
ዘማሪ_#በረከት_ይልማ #ከጠላት_#የቀደመ_#አዲስ_የቅዱስ_ገብርኤል_ዝማሬ

ዘማሪ_#በረከት_ይልማ #ከጠላት_#የቀደመ_#አዲስ_የገብርኤል_ዝማሬ

በሥርዓት ይሁን። ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን።1ኛቆሮ14:40 እንደተባለ ያለ ሥርዓትና ያለአግባብ የሆነ ነገር ሊኖር አይገባም።ሁሉም ነገር ሥርዓት አለው።በሥርዓት ያልሆነ ነገር ጉዳቱ እጅግ የበዛ ነው።ስለዚህ ማንኛውም ሰው በሥርዓት ማድረግ በሥርዓት መኖር ግድ ይለዋል። ማንኛውም ሰው በሥርዓት እንዲኖር ሥርዓትና የሥርዓት አስፈፃሚዎች ሊኖሩ ይገባል።ሥርዓት እያለ አስፈፃሚ ከሌለ ሰው ሥርዓት አልባ ይሆናል።ይህ ደግሞ መጥፎ ነው።ሰው ሥርዓትን የሚማረው ከሁለት መንገድ አንደኛው ሃይማኖታዊ ሥርዓት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ዓለማዊ ሥርዓት ነው።ስለዚህ ሰው ሁለቱን ሥርአት እየፈፀመ እያስፈፀመ መኖር ይኖርበታል። " ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ፤ ለንጉሥም ቢሆን፥ ከሁሉ በላይ ነውና።(1ኛጴጥ 2:13) ይህ ቃል የሚያሳየን መንፈሳዊ ማለትም ሃይማኖታዊ ሥርዓትንም ሆነ ዓለማዊ ማለትም መንግስታዊ ሥርዓትን መፈፀም እንዳለብን የሚያሳይ ነው።በሥርዓት መኖራችን ሁሉ ነገር መልካምና ኑሮን የሚያቀል ነው።" በዚህም ሥርዓት በሚመላለሱ ሁሉ ላይ በእግዚአብሔር እስራኤልም ላይ ሰላምና ምሕረት ይሁን። ገላ(6:16) ያለ ሥርዓት መሄድ ሰላምንም ሆነ ምህረትን ያሳጣል።አሁን እኮ ሁሉ ነገር ከሥርዓት ስለወጣ ነው ሁሉ ነገር ምስቅልቅል ያለው።ሃይማኖተኛ ነኝ የሚለው ከሃይማኖት ሥርዓት ሲወጣ ዓለማዊውም ሰው ከመንግስት ሥርዓት ሲወጣ።ሁሉም ሥርዓት አልባ ሲሆን ይሄው ስድና ብትን ሊሰበሰብ የማይችል ጋጥ ወጥነት እየበዛ መጣ። " እኛን ልትመስሉ እንዴት እንደሚገባችሁ ራሳችሁ ታውቃላችሁና፤ በእናንተ ዘንድ ያለ ሥርዓት አልሄድንምና፤" (2ኛተሰ 3:7) ወደ ቀደመ ኑሮአችን እንመለስ ዘንድ የቀደም ት አባቶቻችን የሄዱበትን ሥርዓታዊ ጉዞ እንጓዝ።
Mostrar todo...
ሰው ሁለት ዓይነት ገፅታ አለው።ውስጣዊ እና ውጫዊ።ውጫዊው ለማንኛውም ሰው የሚታይ የማይደበቅና የማይሸሸግ ሲሆን ውስጣዊ ግን የተደበቀነ የተሰወረ ለእግዚአብሔር ካልሆነ ማንም ለማንም በምንም የሚታወቅ አይደለም።ይህ ማለት ውስጣዊ ማንነታችን የማይገለጥ በውጫዊ ማንነታችን ተሽፍኖ ይቀራል ማለት ግን አይደለም።የሚታይበት የሚገለጥበት ጊዜ አለ። ሐና በውጪአዊ አካሏ በካህኑ በዔሊ ፊት የወይን ጠጅ ያሰከራት እንደምናምንቴ የተቆጠረች ነበረች በዉስጣዊ ማንነቷ ግን ከእግዚአብሔር ጋር የምትነጋገር እግዚአብሔር ልመናዋን የሰማላት የተባረከች ሴት ነች።1ኛ ሳሙ(1÷13) ነብዩ ቅዱስ ዳዊት በውጪአዊ አካሉ በእናትና በአባቱ በወንድሞቹም ፊት የተናቀና ታናሽ ሰው ነበረ በውስጣዊ አካሉ ግን በእግዚአብሔር የተመረጠ የተከበረ ኃያልና ቅዱስ ሰው ነበረ።1ኛ ሳሙ(16÷12) ኤልያብ በውጫዊ አካሉ በአባቱና በወንድሞቹ እንዲሁም በሳሙኤልም ፊት ያማረና የተወደደ የተመረጠም ነበረ ነገር ግን በውስጣዊ አካሉ በእግዚአብሔር ያልተመረጠ ያልተፈለገ የተናቀ ሰው ነበረ።1ኛ ሳሙ(16÷7) በርጠሚወስ በውጫዊ አካሉ ማየት የተሳነው በጎዳና ላይ ቁጭ ብሎ የሚለምን በሰው የተናቀ ኢየሱስ ሆይ ማረኝ ብሎ እንዳይጮህ የተከለከለ ሰው ነው በውስጣዊ ማንነቱ ግን የዳዊት ልጅ ኢየሱስን አምኖ በእምነት የጠራ በእምነቱም እንደዳነ በአዳኙ በኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰከረለት ነው።ሉቃ(18÷42) ባለሽቶዋ ማርያም በውጫዊው አካሏ በስምኦንና በይሁዳ ፊት እጅግ የተናቀችና የተጠላች ወደ ቤት እንኳን እንዳትገባ በር የተዘጋባት የማትረባ ሴት ነበረች በዉስጣአዊ አካሏ ግን በኢየሱስ ክርስቶስ የተወደደች ይቅርታን ፈልጋ ይቅርታን ያገኘች ኢየሱስ ክርስቶስን ያመነችም የወደደችም ነበረች እርሱም የወደዳትና ያደረገችለትንም መታሰቢያ አድርጎላታል።ማር(14÷9) ሰው ሆነን በሰው ዘንድ በውጫዊው አካላችን ልንጠላ ወይም ልንወደድ እንችላለን።ነገር ግን የእኛ የእውነተኛ መገለጫችን ውስጣዊ ማንነታችን ስለሆነ ውስጣዊ ማንነታችንን መስራት ይኖርብናል።ውጪአዊው ግንባታ የትም አያደርስም።በአፍ እየመረቅን ልባዊ ተራጋሚ መሆን የሚያዋጣ አይደለም። ውጫዊ ማንነት ጳጳስ ውስጣዊ ማንነት ??? >>. >> መነኩሴ >> >> ??? >>. >>ካህን >>። >> ??? >> >> ዲያቆን >> >> ??? >> >> መምህር >> >> ??? >> >>ዘማሪ >> >> ??? >> >> ክርስቲያን >> >> ??? " እንዲሁ እናንተ ደግሞ በውጭ ለሰው እንደ ጻድቃን ትታያላችሁ፥ በውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ዓመፀኝነት ሞልቶባችኋል።ማቴ( 23:28) ከመባል እንዲያወጣን ውስጣችችን ሰርተን በውስጥ የምንከብርበትና የምንንነግስበት ያድርገን።አሜን!
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.