cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ

ይህ ማኅበረ ቅዱሳን አዲስአበባ ማዕከል የቅ/ማ/ዩ/ግ/ጉባዔ የቴሌግራም ቻናል ነው። #በዚህ_ቻናል 👉ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ወቅታዊ መረጃዎችን ፣መዝሙሮችን ፣ትምህርታዊ ጽሁፎችን እንዲሁም ስለ ግቢጉባዔያችን መረጃዎች እና ማስታወቂያዎች ይደርሳችኋል። ይህንን ሊንክ በመጫን ለወዳጅዎ ያጋሩ!! 👉 @smu_gibi_gubae

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
764
Suscriptores
Sin datos24 horas
+27 días
+730 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ነገ የነበረው የእመቤታችን ዝክር ቦታው በሰንበት ት/ቤት በመያዙ ወደ ቅዳሜ ዞሯል ።
Mostrar todo...
ሰላም : እንዴት ዋላችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች? ነገ ማክሰኞ [ ሰኔ 25] የእመቤታችን ዝክር 📍ቦታ : ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን (አዲሱ ቢጫ ህንጻ 4ኛ ፎቅ) ⏰ሰዓት 6:00 ሁላችንም ጓደኞቻችንን ይዘን እንድንመጣ ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
"...ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ"   መዝ ፻፲፯፥፳፮ ሰላም እህት ወንድሞች እንደምን አላችሁ... የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ እስካሁን የነበረንን የዩኒቨርሲቲና የግቢ ጉባዔ ቆይታ አጠናቀን እነሆ አሁን ፍሬያችንን የምንሰበስብበት ጊዜ ላይ ደርሰናልና እንኳን አደረሰን፣ አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን! ስለሆነም የ2016ዓ.ም ተመራቂዎች የምርቃት ቀን ሰኔ 30 ፣ 2016 ዓ.ም ስለሆነ ሁላችንም አስፈላጊውን ዝግጅት እንድናደርግ እንዲሁም በምረቃው ዕለት" ከጠዋቱ 3:00 ላይ በማ/ስ/ቅ/ ልደታ ለማርያምና ደ/መ /መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ከወላጆቻችን፣ ከንስሐ አባቶቻችን እንዲሁም ከመምህራኖቻችን ጋር በመገኘት የደስታው ተካፋይ እንድንሆን ስንል በልዑል እግዚአብሔር ስም እናሳስባለን። ሰላም እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!
Mostrar todo...
🌹ሕንጸተ ቤታ ለማርያም 🌹 ሰኔ 21 ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል። በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን  በአምላክ እናት ስም የታነጸችው ሰኔ 20 ነው። አናጺውም ደግሞ እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ቦታው #ፊልጵስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ #በእመቤታችን_ስም ነው። ጥንተ ነገሩስ (ታሪኩ) እንደምን ነው ቢሉ:- ... ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ደቀመዛሙርቱን ‹‹ሑሩ ወመሐሩ ኩሎ አሕዛበ፤ አሕዛብን ሁሉ ሒዱና አስተምሩ፡፡›› /ማቴ. 28:19/ ባላቸው ቃል መሠረት ዓለምን በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል:: የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና (ዮሐ. 6:56) አበው ሐዋርያት ቁርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው ያቆርቡ ነበር::  በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን ፣ ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲህ ይከናወን ነበር:: ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኩራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲሔድ ግን ከአሕዛብ ያመኑ ሰዎች ቁጥር እጅጉን በዛ:: በተለይ‎ ቅዱስ ጳውሎስ  ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ:: በዚህ ምክንያት መምሕራን ሕዝቡን ‹‹ካመናችሁ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችሁ?›› ቢሏቸው ‹‹እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት እንደው የለን›› ሲሉ መለሱላቸው:: ... ነገሩ ሲያያዝ ከደጋጉ ሐዋርያት #ጳውሎስና_በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች ‹‹ለምን አናንጽም?›› ብለው ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ ግን ‹‹ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይሆንም›› አለ:: (ለዚህ ነው ዛሬም ሊቀ ጳጳስ ካልፈቀደ ቤተክርስቲያን  የማይታነጸው፡፡) ከዚያ ቅዱሳን ጳውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ሔደው ነገሩን #ለቅዱስ_ጴጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱ ቅዱስ ጴጥሮስም ‹‹የጌታችን ፈቃዱ መሆኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ›› ብሎ አዋጅ ነገረ:: ... በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ:: በሱባዔያቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ፤ እመቤታችን በቀኙ ነበረች፡፡ ሁሉንም ሐዋርያት በሩቅም በቅርብም ያሉትን ደቀ መዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው፡፡ ከዚያም በስተምሥራቅ  ከከተማ ወጣ ወዳለ ሥፍራ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ፡፡ 3ቱንም ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው፡፡ ድንጋዮቹም እንደሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ፡፡ ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሠጣቸው፡፡ እነርሱም እሣት እንዳየው ሰም ከእጃቸው እየለመለሙ (እየተሳቡ) ቁመቱን 24 ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ግርምት የምትሆን 3 ክፍል ያላትን #የመጀመሪያዋን_ቤተክርስቲያን #በ52_ዓ.ም #ሰኔ_20 ቀን አነጹ፡፡ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ፤ ጌታችንም በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም አምሳያ አድርጎ አነጻት፤ ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ለሐዋርያቱ ‹‹እንግዲህ እናንተም እንዲህ አድርጋችሁ ሥሩ፡፡›› ብሏቸው ዐረገ፡፡ ... በማግስቱ ሰኔ 21 ዕለት ደግሞ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላዕክትን፣ ሰማያውያን ቅዱሳንን እና እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን ይዟት ወረደ:: ሐዋርያቱ አብዛኞቹ እዛው ሲጸልዩ አድረው ነበርና ጌታችን ከቅዳሴው በፊት 2 ነገሮችን አሳየ፤ አስቀድሞ ቤተክርስቲያኗን በድንግል እናቱ ስም አክብሮ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን አሳየ:: ... ቀጥሎ ደግሞ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስን ከመካከል አቁሞ ‹‹አርሳይሮስ›› ሲል ሾመው:: ይኼውም የዓለም ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት (ፓትርያርክ) ማለት ነው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ‹‹አክዮስ›› እያሉ 3 ጊዜ አሰምተው ጮሁ:: #አክዮስ ማለት በግዕዙ #ይደልዎ በአማርኛው ደግሞ #ይገባዋል_ያሥምርለት እንደ ማለት ነው:: ... ጌታችን ይህን ከከወነ በኋላ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ:: አማናዊት ማኅደሩን ድንግል ማርያምን መንበር አድርጎ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ተራዳኢ ካህን ቆሞ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሠራኢ ዲያቆን ሆኖ፣ ሐዋርያት ድንግልን ከበው፣ መላእክተ ብርሃን በክብራቸው ቆመው ጌታችን ቀድሶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወዳጆቹ አቀበለ:: ... በዚያች ዕለት በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የማይችል ደስታ ተደረገ:: ከቅዳሴ በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን አዘዛቸው:: ‹‹ከዚህ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም በእናቴ በማርያም ስም አብያተ ክርስቲያናትን አንጹ፤ ይህችን ዕለት የሚያከብራትን አከብረዋለሁ::›› ብሏቸው ከድንግል እናቱ ከመላዕክቱ ጋር ዐረገ:: ... 🌹 ሰኔ ጎልጎታ፦ በሌላ በኩል ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም በዚህ ቀን (ሰኔ 21) ልጇን ወዳጇን ጐልጐታ ላይ ለኃጥአን ምሕረትን ለምናዋለች:: ጌታችንም ‹‹ስምሽን የጠራውን፤ በቃል ኪዳንሽ ያመነውን ሁሉ እምርልሻለሁ፡፡›› ብሏታል መልካም የምስጋና ሌሊት ይሁንላችሁ!!! የድንግል እመቤታችን ልመናዋ ክብሯ፣ ጣዕመ ፍቅሯና በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን::
Mostrar todo...
https://youtu.be/Jx8XoZEvaDw?si=K8JzUWnA7-AHdaRA 👆👆👆 በግቢ ጉባዔያችን በመዝሙር ክፍል ስታገለግል የነበረችው እህታችን ዘማሪ ሊሻን አወቀ #ልዩ_ክብር_አለሽ የሚል አዲስ የምስጋና መዝሙር በዩቲዮብ ቻናሏ ወደ እኛ አድርሳለች። ሁላችንም ይህን ዝማሬ በማዳመጥ እንዲሁም ቻናሏን #ሰብስክራይብ በማድረግ ለቀጣይ ስረዋ እናበረታታት። 👇👇👇 https://youtu.be/Jx8XoZEvaDw?si=K8JzUWnA7-AHdaRA
Mostrar todo...
"ልዩ ክብር አለሽ" አዲስ ዝማሬ || በዘማሪት ሊሻን አወቀ #አዲስ_ዝማሬ #መዝሙረ #mezmur

አመ_፳፩_ለሰኔ_ማርያም_፩_ወረብ_እግዚአብሔር_ውእቱ_ዜማ_.mp39.47 KB
፫_ጽርሐ_ቅድሳቱ_፳፩_ለሰኔ_ማርያም_ዜማ_.mp39.84 KB
፬_ሕንጺሐ_አዳም_፳፩_ለሰኔ_ማርያም_ዜማ_.mp39.04 KB
፭_ሃሌ_ሃሌሉያ_፳፩_ለሰኔ_ማርያም_ዜማ_.mp36.91 KB
፮_ወረብ_ኢይትአጸውዕ_፳፩_ለሰኔ_ማርያም_ዜማ_.mp31.11 MB
፯_ወረብ_በሥላሴሁ_፳፩_ለሰኔ_ማርያም_ዜማ_.mp38.69 KB
፰_ወረብ_ተቀደሲ_፳፩_ለሰኔ_ማርያም_ዜማ_.mp31.17 MB
፱_አመ_ትትሐነጽ_፳፩_ለሰኔ_ማርያም_ዜማ_.mp32.21 MB
ዝማሬ ለሰኔ ማርያም ዜማ .mp32.59 MB
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.