cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

oline ንግድ እና ዜና chanall

🇪እዚህ🇹 oline ንግድ ዜና chanal ላይ #የሚሸጥ_እቃዎች #የግዢ_ማስታወቅያ #የጨረታ_ማስታወቅያ #የንግድ_ማስታወቅያ #ትኩስ ዜናዎች 🍻🏍🚘🚲🏡👖👟ማንኛውንም የግዢ አልያም የሽያጭ ማስታወቂያ አድሚን ለምትፈልጉ በቅናሽ ዋጋ ለ 2ሳምንት፦50 ለ1 ወር፦100 ለ2ወር፦150 https://t.me/seya222 coll-0964138647

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
168
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Nike airforce Nist Made veitnam 1800 birr ይደውሉልን 0964138647 @seya222 @seya222
Mostrar todo...
* ደብረ ማርቆስ " ከዛሬ ጀምሮ በደብረ ማርቆስ የተጣለው የሰዓት ዕላፊ ገደብ እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት እንዲሆን ተወስኗል " - የደ/ማርቆስ የፀጥታ ግብር-ሃይል በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳር ከዚህ ቀደም የተላለፉት ሌሎች ውሳኔዎች እንደተጠበቁ ሆነው የሰዓት ዕላፊ ገደቡ ማሻሻያ እንደተደረገበት የደ/ማርቆስ የፀጥታ ግብር-ሃይል አስታውቋል። በዚህ መሰረት ከንጋቱ 12 ሰዓት በፊት መንቀሳቀስ እንደማይቻል የተከለከለው የሰአት እላፊ ገደብ ወደ ንጋቱ 11 ሰዓት ዝቅ እንዲል ተደርጓል። ከምሽት 3 ሰዓት የነበረው የሰዓት ዕላፊ ገደብ ደግሞ ወደ ምሽቱ 4 ሰዓት ተሻሽሏል። የከተማዋ ማህበረሰብ ለራሱ ሰላም ሲል የተጣለውን የሰዓት ገደብ አክብሮ መንቀሳቀስ እንደሚገባው ተገልጿል።
Mostrar todo...
መተከል ዞን ግድያው ቀጥሏል። ትላንት በዚሁ መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ 5 የጸጥታ ኃይሎች እና 1 የቻይና ዜጋ በታጣቂዎች ተገድለዋል። ይህንንም ግድያ የክልሉ የሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል። ትላንት አመሻሽ ላይ በታጣቂዎች በተፈጸመው ጥቃት ፤ በመንገድ ስራ ላይ የተሰማሩ አንድ ቻይናዊ እና ኢትዮጵያዊ መገደላቸውን ቢሮው ገልጿል። በትላንቱ ጥቃቱ የተገደሉት የጸጥታ ኃይሎች፤ አንድ የመከላከያ ሰራዊት አባል እና አራት የፌደራል ፖሊሶች ናቸው። ከእነርሱ በተጨማሪ ሁለት የጸጥታ ኃይሎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በጥቃቱ ህይወታቸውን ያጡት ቻይናዊ እና ኢትዮጵያዊ የመንገድ ሰራተኞች ፤ ከግልገል በለስ ወደ ጉባ በሚወስደው የ70 ኪሎ ሜትር መንገድ ስራ ላይ የተሰማሩ እንደነበር የክልሉ ሰላም ግንባትና ፀጥታ ቢሮ አሳውቋል። የግልገል በለስ – ጉባ መንገድ ከአዲስ አበባ በደብረ ማርቆስ፣ አንጅባራ እና ቻግኒ አድርጎ ወደ ህዳሴው ግድብ የሚወስድ ዋነኛ መንገድ ነው።
Mostrar todo...
#ETHIOPIA😷 በኮቪድ-19 ሳቢያ በአንድ ቀን የ27 ዜጎች ህይወት አለፈ። በየዕለቱ በሽታው የሚገድላቸው ሰዎች ቁጥር እይሻቀበ ነው። ዛሬ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 27 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,728 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,352 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል። የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 756 ሰዎች በፅኑ ታመዋል [ከትላንትናው በ30 ሰዎች ጨምሯል] የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከቀን ወደ ቀን እየከፋ በመሆኑ መላው የቲክቫህ አባላት ጥንቃቄያችሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ እንድታጠነክሩ አደራ እንላለን።
Mostrar todo...
* ባህር ዳር "የሰዓት ገደቡ ተነስቷል" - የባህርዳር ከተማ ፀጥታ ም/ቤት በአማራ ክልል መዲና ባህርዳር ከተማ እስከ ምሽቱ አራት (4) ሰዓት ተጥሎ የነበረው የሰዓት ገደብ ከዛሬ ጀምሮ መነሳቱን የባህርዳር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት አስታውቋል። በሌላ በኩል በየከተማው መግቢያና መውጫ ከፖሊስ፣ ከአድማ ብተና ውጭ ማንም መኪና አስቆሞ መፈተሽ የተከለከለ መሆኑን ጥብቅ ማሳሰቢያ ተላልፏል። የባህር ዳር ነዋሪዎች ለፖሊስና ለፀጥታ አካላት መረጃ እና ጥቆማ ለመስጠት በ 0582264666 መደወል ይችላሉ ተብሏል።
Mostrar todo...
"...ከበዓሉ ጋር ተያይዞ ርችት መተኮስ በፍፁም የተከለከለ ነው" - የአዲስ አበባ ፖሊስ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከበዓሉ ጋር ተያይዞ ርችት መተኮስ በፍፁም የተከለከለ መሆኑን በዛሬው ዕለት አሳውቋል። ክልከላው የተላለፈው የተለያዩ አጋጣሚዎችን በመጠቀም የከተማውን ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ሃይሎችን ለመቆጣጠር እና ምቹ ሁኔታ ማሳጣት እንዲቻል ነው ሲል ፖሊስ ገልጿል። ህብረተሰቡ ከበዓሉ ጋር ተያይዞ ርችት መተኮስ በፍፁም የተከለከለ መሆኑን ተገንዝቦ ለጋራ ደህንነት አስፈላጊውን ትብብር ሊያደርግ እንደሚገባ ፖሊስ አሳስቧል።
Mostrar todo...
#UPDATE ስቴም ፓወር ከቪዛ እና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ በመጀመሪያው ዙር 114 ሰልጣኞች እድሉን ያገኙ ሲሆን በሁለተኛው ዙር ከ190 በላይ ሰልጣኞች ስልጠናውን ወስደዋል። ስልጠናውን ከወሰዱ ሰልጣኞች መካከል የራሳቸውን የፈጠራ ሀሳብ ይዘው ለመጡ የመነሻ የገንዘብ ተሰጥቷቸው በቡድን እንዲሁም በግል ሆነው ሥራቸውን ጀምረዋል። ሥራቸውን ከጀመሩ በኋላም የቴክኒካል ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል። ስቴም ፓወር ፣ ከቪዛ እና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርነት እየተካሄደ ያለው ይህ ፕሮጀክት ከሰብ ሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት ቪዛ ካከናወናቸው ፕሮጀክቶች ምርጡ በመሆን ተመርጧል። በሥራ ፈጠራ ክህሎት እና በመሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ያተኮረው ይኸው ስልጠና ሦስተኛ ዙር ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን በምዝገባ ላይ ይገኛል። በሥልጠናው መሳተፍ የምትፈልጉ በተለይ የፈጠራ ሀሳብ ያላችሁ በነጻ መመዝገብ ትችላላችሁ።
Mostrar todo...
እናት ፓርቲ ለአፋር እና ሱማሌ ክልል ርዕስ መስተዳደሮች ደብዳቤ ላከ። ፓርቲው በላከው ደብዳቤው በአዳይቱ እና ገዳማይቱ አካባቢ ባለው ችግር ምክንያት የሚጠፋው የንፁሃን ህይወት እንደሚያሳስበው ገልጾ ክልሎቹ ያለውን ችግር በውይይቱ ይፈቱት ዘንድ ጠይቋል። እናት ፓርቲ ፥ "ኢትዮጵያ በክፉ ሀሳብ በተጠነሰሰ ጦርነት እየተለበለበች ባለችበት በዚህ ወቅት በአዳይቱና ገዳማይቱ አካባቢ፣ በሁለቱ ክልሎች መካከል እሰጥ አገባው ተባብሶ ጦርነት ወደሚመስል ኩነት መቀየሩ እና በዚሁ ሳቢያ ከዕለት ወደዕለት ንጹሓን መሞታቸው እጅጉን ያሳስበናል" ብሏል። በሌላ በኩል እናት ፓርቲ በሰሜን ጎንደር ዞን፣ ዳባት ወረዳ፣ ጭና ቀበሌ በንጸሓን ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ በጽኑ አወግዛለሁ ብሏል። እንዲህ ያሉ ተመሳሳይ ተግባሮች " ሕወሓት " በተቆጣጠራቸው የሰሜን ወሎ አካባቢዎች ዳግም ላለመፈጸማቸው ዋስትና የለምና መንግስት አስፈላጊውን ርብርብ ሁሉ አድርጎ እንዲታደጋቸው ሲልም ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.