cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Islamic

I'm islam Islam means pease and love For cross፣፣ @guteman1 @ziyadper

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
164
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Watch "as wr wb. የ Dirilis ertugrul የኤርቱጉሩል ትንሳኤ kurulus osman,uyanis buyuk selcuklu in amharic" on YouTube https://youtu.be/B0p-RrJe-A0
Mostrar todo...
as wr wb. የ Dirilis ertugrul የኤርቱጉሩል ትንሳኤ kurulus osman,uyanis buyuk selcuklu in amharic

#Drilis ertugrul#kurulus osman#uyanis buyuk selcuklu#inamharic

📌 ቀዷዬን ሳልጨርስ ረመዷን ገባ⁉️ #በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች❓ ♻️ : ክፍል 245 📌ጥያቄ📌 📌 ያለፈው ረመዷን የተወሰኑ ቀናቶች ቀዷ #ነበረብኝና ያንን ቀዷ ታምሜ ወይም ሳይመቸኝ ቀርቶ ሳይሆን #በስንፍና ሙሉውን ቀዷ ሳላወጣ ቀጣይ ረመዷን መጣብኝ እና አንዳንዶች ሚስኪን #ማብላት አለብሽ አሉኝ ምን ማድረግ ይጠበቅብኛል⁉️ ✅መልስ✅ ✅ በርግጥ የረመዷን ቀዷ የነበረበት ሰው ቀጣዩ ረመዷን ከመግባቱ በፊት ቀዷውን አውጥቶ ማጠናቀቅ #ግዴታ እንደሆነ ኡለሞች በአጠቃላይ ተስማምተውበታል። ለዚህም ማስረጃው አኢሻ ረዲዬሏሁ አንሀ ሶሂህ በሆነ ሀዲስ እንዲህ ማለቷ ነው:— 📔"በእኔ ላይ የረመዷን ቀዷ ፆም ይኖርብኝ ነበር ፣ ለነብዪ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ምቾት ሲባል #ሸዕባን ወር ውስጥ እንጅ ከዛ በፊት ቀዷ ማውጣት አልችልም ነበር።"① እዚህ ሀዲስ ላይ አኢሻ ረዲዬሏሁ አንሀ በዚህ ወር ላይ ቀዷዋን ለማጠናቀቅ #መጓጓቷ ቀጣዩ ረመዷን እስኪገባ ማዘግየት #ክልክል መሆኑን ያመለክታል። ✅ ነገር ግን ቀጣዩ ረመዷን እስኪገባ ድረስ ቀዷውን #ያላጠናቀቀ ሰው ከሁለቱ አንድኛው ሁኔታ ይኖረዋል። እነሱም አንዱ #በሸሪዓዊ ምክንያት ከሆነ ነው ፣ ማለትም በተከታታይ በሽታ ወይም መፆም ፅንስንም ሆነ አካልን ይጎዳል ተብሎ ከተረጋገጠና በሌሎች ከባባድ ምክንያቶች ከሆነ ይህ ሰው ቀዷውን ባለማጠናቀቁ ያሉበትን ቀዷ ማውጣት #ብቻ እንጅ ወንጀልም ሆነ ሚስኪን ማብላት #አይኖርበትም። ✅ ሁለተኛው ደግሞ ሸሪዓዊ #ባልሆነ ምክንያት ማለትም በስንፍና እና በመሳሰሉት ከሆነ ይህ ሰው #ወንጀለኛ በመሆኑ በሱ ላይ #ተውበት ያለበት መሆኑና በሱ ላይ ያሉበት ቀናትን #ቀዷ ማውጣት እንዳለበት ኡለሞች ተስማምተዋል። ሆኖም ከዚህ በተጨማሪ ባሉበት ቀናት ልክ ሚስኪኖችን #ማብላት አለበት ወይስ የለበትም በሚለው ላይ ኢማሙ ሻፊዕይና ሌሎች ከፊል ኡለሞች ከአንዳንድ ሶሀቦች ፈለግ ተገኝቷል በሚል #አለበት ሲሉ ሌሎች ኡለሞች ቡኻሪና አቡ ሀኒፋን ጨምሮ ደግሞ ቀዷና ተውበት እንጅ ሌላ #የለበትም ይላሉ። ✅ ሆኖም ከመረጃ አንፃር በላጩና አመዛኙ አቋም #ሁለተኛው ነው። ምክንያቱም በመጀመሪያ የሶሀባ ንግግር ከአሏህ ንግግር ጋር #ሲገጥም ነው የሚያዘው ፣ ምክንያቱም አሏህ በቁርአኑ በተለያዩ ምክንያቶች የረመዷን ቀዷ ያለበትን ሰው ቀዷ ከማውጣት #ውጭ ሌላን #አላዘዘምና። እንዲህም ይላል: 📖 "...በሽተኛ የሆነም ፣ ወይም መንገድ ላይ ያለ ፣ ከሌሎች (ከረመዷን ውጭ ካሉት ቀናት) መቁጠር (ቆጥሮ #መፆም) ነው ያለበት..." 📚ሱረቱል በቀራህ ፣ 185 ♻️ ምንጭ :— 📚ኢብኑ ኡሰይሚን ፣ ሸርሁል ሙምቲዕ ፣ 6/451 ፣ 📚ኢማሙ ነወዊይ ፣ አልመጅሙዕ ፣ 6/366 ፣ 📚ኢብኑ ቁዳማ ፣ አልሙግኒ ፣ 4/400 ______________ *ያለፈዎትን ፈትዋዎች ለመከታተል 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ✔https://t.me/yeilmkazna
Mostrar todo...
[] የዒልም ካዝና []

★ ★ ★ ★ ★ በውስጥ መስመር ለሚላኩ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥበትና ፈትዋዎቹም በቻናሉ የሚለቀቁበት የቴሌግራም የፈትዋ ቻናል ነው። ያለፈዎትንም ፈትዋዎች ለመመልከትና ለመከታተል ይቀላቀሉ።

🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃 አንድ ሰው አፋልጉኝ ሰዎች እባካችሁ ማንን ነው ካላችሁ ከታች ልንገራችሁ 🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌✒️🖌 #ጀነትን_ፍለጋ #ጉዞ_የጀመረቺ በተውሂድ በሱና ስንቋን ያሳመረቺ 🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃 #ከቢድዓ_ኮተት_ራሷን # ያራቀቺ ህይወቷን በሱና በጣም ያደመቀቺ 🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ለሽርክ ጠበኛ ገዝግዛ የማታረክስ የተውሂድ ዘበኛ ተውሂድ የምታነግስ 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾 የሱና ሰዎችን አጥብቃ የምትወድ የባጢን ሰዎችን ኮንና የምታዋርድ 🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷 #ከወንጀሎች_ሁሉ_ራሷን #ያቀበቺ መጥፎ ከመናገር ሁሌ የተቆጠበቺ 🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃 መልካምን ለመስራት ጊዜ የማትጠብቅ #ዛሬ_ነገ የማትል #ከመጥፎ_ለመራቅ 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ጀግናዋን ካያችሁ ጠቁሙኝ አደራ ወደ ዳሩ-ሰላም ልዝመት ከሷ ጋራ #በተውሂድ #በሱና #ጀነትን ልጋራ 🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾
Mostrar todo...
ለፈገግታ😂 / እንጠያየቅ ማሙሽ እያጠና ነዉ አባቱ ሶፋ ላይ ጋቢ ለብሰዉ ጋደም ብለዋል እናቱ ደግሞ ቡና እያፈሉ ነዉ _ ማሙሽ:- አባዬ የሱዳን ዋና ከተማ ማን ትባላለች??? _ አባት:- አላዉቃትም!!! _ ማሙሽ:- የግብፅ ዋና ከተማ ማን ትባላለች??? _ አባት:- አላዉቃትም!!! _ ማሙሽ:- የኬንያ ዋና ከተማስ??? _ አባት:- አላዉቃትም!!! _ እናት:- አንተ ልጅ ምናለ አባትህን ባትጨቀጭቀዉ _ አባት:- ቆጣ ብለዉ ተይዉ እንጂ ልጅ ካልጠየቀ እንዴት ያዉቃል? እንጠያየቅ😂😂😁 #ሼር / አንድ ግዜ ይቺን '😂' ይጫኑ!! ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ @risaalaatube ለሀሳብና አስተያየት፡ @risaalaacommentbot
Mostrar todo...
ተወዳጁ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በናይልሳት የሚያሳይ ቻናል አለ ፍሪክዌንሲውን እና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የዲሽ ምልክቱን ይጫኑት👇👇👇
Mostrar todo...
🏆 join 🏆
Frequency
⭐የወጣቱ እና ኡስታዝ ቃለ ምልልስ ✔ወጣት፦ ኡስታዝ ሰላት መቼ ነው መጀመር ያለብኝ ✔ኡስታዝ፦ ከመሞትህ አንድ ቀን በፊት ✔ወጣቱ፦ የምሞትበትን ቀን አላውቀውማ ✔ኡስታዝ፦ እንግዲያውስ ሁሌም እየሰገድክ ጠብቀው መልካም ምሽት ➢@risaalaatube @risaalaatube
Mostrar todo...
በአርቱግሩል ፊልም ምክንያት እስልምናን የተቀበለችው #ኸድጃ ለ Anadolu Agency እንደት እንደሰለመች በሚከተለው መልኩ ገልፃለች " በጣም በደበረኝና በተበሳጨሁበት ቀን NETFLIX ላይ የአርቱግሩልን ፊልም ማየት ጀመርኩ ። ታሪኩ እኔ ከዚያ በፊት ምንም የማላውቀው ታሪክ ነው ። ስለ ፈጣሪ ፣ ኢስላም ፣ ስለ ሰላም ፣ ስለፍትህና ከተበደሉ ከተጨቆኑ ወገኖች መቆምን ፊልሙ በሚናገር ጊዜ ትኩረቴን ሙሉ ሳበኝ ።" ትላለች ኸዲጃ ወዲያው የፊልሙ አፍቃሪ ሆነች ። ግና ደግሞ አንድ የፊልሙ ካራክተር የሷን ልብ ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጠረው - #የኢብን_አረቢ ! አንዱሉሲያዊው የኢስላም ፈርጥና የአርቱግሩል ጉዞ ቀያሽ የኢብን አረቢ ንግግር ኢስላማዊ ጥበብ ቀልቧን ገዛው ። " የእርሱ ንግግሮች ያስለቅሱኛል በእንባ እንድሞላ ያደርጉኛል ። እርሱ የእኔ በጣም ተወዳጁ ገፀባህሪ ነው ። ፊልሙ ሙሉ በሙሉ ማረከኝ ። ሁሉንም ክፍል አራት ጊዜ ደጋግሜ አይቸዋለሁ ። ብዙ ጊዜ ፊልሙን እያየሁ በመሃል አቆመውና የገፀባህሪዎቹን ማንነት በኢንተርኔት እፈልጋለሁ ፤ ከዚያ በሗላ ስለ ኢስላምና ስለ ኦቶማን ኢምፓየር ማንበብ መረጃዎችን በጥልቀት መፈለግ ጀመርኩ። " ብላለች ኸድጃ ለአናዶሉ። ኸድጃ የ ባፕቲስት ክርስቲያን ነበረች ። " በገፀባህሪያቱ ውስጥ ያሉት የሞራል እሴቶች ውስጤን ዘልቀው ገቡ ። ይህ ፊልም ማየት መጀመሬ ለኔ ታላቅ ምልክት ነበር ። ስለ እምነቴ ብዙ ጥያቄዎች ነበሩኝ ይህ ፊልም ግን ሁሉንም ጥያቄዎቼን ግልፅ አደረገልኝ " በማለት ግልፃለች ሰለምቴዋ ኸድጃ ። ኸድጃ ከዚያ በሗላ ስለ እስልምና በስፋት ማንበብና መማር ጀመረች ። ቅዱሱን የአላህ ቃል ቁርአንን በእንግሊዝኛው ትርጉሙ ማንበብ ያዘች ። ከዚያም በእስልምና ተማረከች እስልምናንም ለመቀበል ወሰነች። ኸድጃ ይህን ከወሰነች በሗላ አካባቢዋ ወደሚገኝ መስጅድ አቀናች ። እዚያ ጥሩ የሙስሊም ጀመአዎችን አገኘች ። ሶላት እንደት መስገድ እንዳለባት ተማረች ከዚያም " ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት ጌታ የለም ሙሃመድም የአላህ ባሪያውና መልእክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለሁ " በማለት ሸሃዳን ያዘች። ኸድጃ ሰለመች!! ኸድጃ የ 6 ልጆች እናት ናት ። አሁን ኸድጃ ሂጃቧን ለብሳ በኢስላማዊ ስርአት ነው የምትኖረው ። ሁሉም ልጆቿ ለምን እንደዚህ አደረግሽ ብለው አልጠየቋትም ። የመጨረሻው ልጇ እርሷን ተከትሎ እስልምናን ተቀብሏል። ነገር ግን ከጓደኞቿ የገጠማት ከዚህ የተለየ ነው ። " ጓደኞቼ አእምሮየ በሌላ አስተሳሰብ እንደተበረዘ ነው የሚያምኑት ። ወደ እስልምና ከተመለስኩ በሗላ ሊያዩኝ አይፈልጉም። እኔ አልከራከራቸውም ። ስለነርሱ እምነት እኔ ምንም አልላቸውም እነርሱም ስለኔ እምነት ምንም ሊሉኝ አይገባም " ትላለች ኸድጃ ! ኸድጃ አሁን ይህ እጅግ ዝነኛ ፊልም የተቀረፀባትንና እውነተኛዎቹ የታሪኩ ተዋኒያን ያለፉባትንና የተቀበሩባትን ቱርክን ለመጎብኘት አጥብቃ ትፈልጋለች ። " ሁልጊዜም ቱርክን ለመጎብኘት አስባለሁ ። የኮሮና ወረርሽኝ የሚያበቃ ከሆነ በመጪው ሰኔ ወደ ቱርክ እጓዛለሁ ። ይህን ጉዞየን ሳስብ እንባ ይቀድመኛል " ትላለች የነ አርቱግሩል ታሪክ ልቧን የተቆጣጠረው ኸድጃ ። ኸድጃ ወደ ቱርክ ስትሄድ መጀመሪያ መጎብኘት የምትፈልገው የአርቱግሩልን መቃብር ነው ። ያን የኡስማኒያ ( ኦቶማን) ልእለሀያሉ ሱልጧኔት መሰረት የጣለውን አርቱግሩልን ! ኸድጃ እንደዚህ ትላለች " አላህን ሁልጊዜም አመሰግነዋለሁ ! በዚህች የዱኒያ ህይወት ውስጥ ሌላ ቀንን ጨምሮልኝ ይህን እድል ስለሰጠኝ አብዝቼ አመሰግነዋለሁ ። ብዙዎች ይህች ህይወት አጭር እንደሆነች አያውቁም ! እኔ ለሰዎች የማስተላልፈው መልእክት ቢኖር እውነተኛ ላልሆነ ነገር ህይወታቸውን እንዳያባክኑ ነው ! ህይወት ማለት የምትለብሰው ልብስ አይደለም ! የምታሽከረክረው መኪናም አይደለም ! ዙሪያችሁን ተመልከቱ ! ህይወታችሁን በጥንቃቄ እዩ! " አያችሁ አይደል የሚዲያን ተፅኖ?? አያችሁ አይደል እስልምናችሁን በሚገባ ለሌሎች ባንፀባረቃችሁት ጊዜ ውበቱን? አያችሁት አይደል ትውልድ እንደ እንደሚቀረፅ ? አስተሳሰብ እንደት እንደሚገነባ?!! አያችሁት አይደል በስንፍናችን ባለመስራታችን ብዙዎችን የብርሃንን መንገድ እንዳያዩ እንዳደረግን!!! #Seid_Mohammed_Alhabeshiy #hidayah
Mostrar todo...
ከታሪክ አምድ❤️ / ለምን ትለፋለህ? በኢራቅ ሀገር ውስጥ አላህን አብዝቶ በመገዛቱ ይታወቃል ። በእስልምና አስተምህሮት የታነፀ ፣ ኢማን ወደ ልቡ የገባ ድሀ ወጣት ነበር ። የእርሱ አይነት ባህሪና ጥንካሬን ሁሉም ይመኛል ። አንድ ቀን ከጓደኛው አቡ ሱለይማን ዳረኒ ጋር ወደ መካ ጉዞን ሊያደርጉ ወስነው የሚያደርሳቸውን ቅፍለት መምጣት ይጠባበቁ ይዘዋል ። ቃፊላው ደረሰና ጉዟቸውን ወደ መካ ጀመሩ ። በጉዟቸው መሀል ላይ የኢራቁ ወጣት የሚያሳየው ዒባዳ አስደንቋቸዋል ። እነርሱ ሲበሉ እርሱ ይፆማል ። ሲተኙ ለሊቱን ወደ ጌታው በመዞር በቂያመ-ለይል ያነጋል ። ሁኔታው ቢያስገርማቸውም ቀርቦ ምክንያቱን ለመጠየቅ ግን ማንም አልደፈረም ። መካ ደርሰው ጉዳያቸውን ፈፅመው በመመለስ ላይ ሳሉ ጓደኛው አቡ ሱለይማን ከጓደኞቹ እሱን ነጠል አድርጎ "ወንድሜ ሆይ! ለዚህ ሁሉ ዒባዳ ያነሳሳህን ነገር ንገረኝ? ለማወቅ ጓጉቻለሁ" በማለት ጠየቀው። እሱም እንዲህ ሲል መለሰ፦ "አንድ ቀን ተኝቼ በህልሜ ከወርቅና ብር የተገነቡ በሉልና አልማዝ ያሸበረቀ ህንፃዎችን ተመለከትኩ ። ከበሩ ደጃፍ ላይ ዓይኗን የነፃ ፀጉሯን የለቀቀች ውብ እንስት ቆማ አየሁ። የለበሰችው ቀሚስ ከሀር የተሠራና አዝራሩንም በወርቅ የተለበጠና ያማረ ልብስ ነበር። እሷን በተመስጦ በመመልከት ላይ ሳለሁ ደስ በሚል ቀልብን በሚማርክ አንደበቷ "እኔን ለማግኘት ከፈለግክ በዒባዳህ ላይ ፅና ። በአላህ እምላለሁ እኔ አንተን ለማግኘት በዱዓ እየለፍሁና እየታገልኩ እገኛለሁ ። የእኔ መህር የለይል ሰላትና ፆም ነው።" አለችኝ አስከተለና ወንድሜ ሆይ ! በዚህ በምታየው ዒባዳ እሷን ለማግኘት በመጣጣር ላይ ነኝ በማለት መለሠልኝ። አቡ ሱለይማን ይህንን ታሪክ ሰምቶ ካበቃ በኋላ "ይህ ሁሉ ትግል ሁረል ዐይንን ለማግኘት ከሆነ ከሁረል አይን በላይ የሆነውን ጀነት ለማግኘት ምን ያህል ይለፋ ይሆን? በማለት ተናገረ። #ሼር ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ @risaalaatube ለሀሳብና አስተያየት፡ @risaalaacommentbot
Mostrar todo...
▫️የመላዕካዎችን ዱአ ለሚፈልግ ሰው ቀላል መንገድ ▪️ስምንት ሁኔታዎች ላይ መላይካዎች ላንተ ዱአ ያደርጉልሀል እናም እንዳትዘናጋ; 🔺 መስጊድ ቁጭ ብለህ ሰላት በምትጠባበቅበት ወቅት፣ 🔺 የታመመን ስትጠይቅ፣ 🔺 በሰላት ላይ የመጀመሪያው ሰፍ ስትቆም፣ 🔺ሙስሊም ወንድምህን ስትዘይር፣ 🔺 በሩቅ ለወንድምህ ዱአ ስታደርግ፣ 🔺ሰዎችን መልካም ነገር ስታስተምር፣ 🔺 በውዱእ ላይ ሆነክ ስትተኛ፣ 🔺 ሱህር ስትበላ፤ -------------------------------------- 🔗 @risaalaatube -------------------------------------- 💬 @risaalaacommentbot --------------------------------------
Mostrar todo...
▫️የቁርኣን ሚስጥር ሰፊዉ የእርሻ መሬት በማሳ ተሸፋኗል። ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ይታያል ። ከዚህ ጫካ የሚሰማው የወፎች ዝማሬ አስደሳች ነው። ከእርሻ መሬቱ አጠገብ የሚያልፈዉ ወንዝ ዉሃ ድምፅም ለጆሮ በጣም ደስ ይላል። የእርሻ መሬቱ ባለቤት አንድ ሙስሊም ሽማግሌ ናቸዉ። አኚህ ሰዉ ከመሬታቸዉ አቅራቢያ በሠሩት ቤት ከልጃቸዉ ልጅ ጋር ይኖራሉ። ሰዉየዉ ታድያ ሁል ጊዜ ጠዋት ጠዋት ቁርኣን የማንበብ ልምድ ነበራቸዉ። ሕፃኑ የልጃቸዉ ልጅም በሁሉም ነገር አያቱን መምሰል ስለሚፈልግ እርሳቸዉን አስመስሎ ቁርአን ይቀራ ነበር። ከእለታት አንድ ቀን ሕፃኑ ልጅ "አያቴ ልክ አንተ እንደምትቀራዉ አድርጌ ቁርኣን እቀራለሁ፤ ምን ማለት እንደሆነ ግን አይገባኝም። ትንሽ ትንሽ የምረዳዉን ሀሳብ እንኳ ልክ ቁርኣን እንደዘጋሁት እረሰዋለሁ። ግን ቁርኣን ማንበብ ምን ጥቅም አለዉ?" ሲል አያቱን ይጠይቃል። አያትየዉ በቅርጫት የያዙትን ከሰል ምድጃዉ ዉስጥ እየጨመሩ ነበር ጥያቄዉን ያዳመጡት። ወደ ልጅ በመቅረብም የያዙትን የከሰል ቅርጫት እየሰጡት አጠገባቸዉ ካለዉ ወንዝ ዉሃ ይዞ እንዲመጣ ይነግሩታል። ልጅም በተባሐዉ መሠረት ወደ ወንዙ ይሄዳል። ነገር ግን ቤት እስከሚደርስ የቅርጫቱ ዉሃ ፈሶ አለቀ። አያትየዉም እየሳቁ "ዉሃዉ ፈሶ እንዳያልቅ ፈጥነህ መምጣት አለብህ " በማለት በድጋሚ ወደ ወንዙ ይልኩታል። በዚህ ጊዜ ልጅ በቅርጫቱ የቀዳዉን ዉሃ ይዞ በጣም እየሮጠ ቤት ይደርሳል ። ነገር ግን አሁንም ቅርጫቱ ዉስጥ ምንም ዉሃ አልነበረም ። ቤት እስኪደርስ በቀዳዳዎቹ በኩል ፈሶ አልቋል ። ትንፋሹ እየተቆራረጠ በቅርጫት ውሃ ቀድቶ ማምጣት የማይቻል መሆኑን ለአያቱ ለማስረዳት ሞከረ። ከቅርጫት ይልቅ ባልዲ እንደሚሻል ነገራቸው። አያቱ ግን "እኔ የምፈልገው ዉሃ በቅርጫት ነዉ። አንተ ዉሃዉን ለማምጣት ብዙ ጥረት ባለማድረግህ ነዉ ያልተሳካልህ" በማለት ሐሳቡን ተቃወሙ። እንደገና ሄዶ እንዲሞክር ወደ ወንዙ በመላክም ከቤት ወጥተው ይከታተሉት ጀመር። በዚህ ጊዜ ልጁ ዉሃ በቅርጫት መያዝ እንደማይችል በጣም እርግጠኛ ሆነ ። ነገር ግን ነገሩ የማይሆን መሆኑን ለአያቱ ለማሳየት ሲል በድጋሚ ዉሃዉን በመቅዳት እጅግ በጣም ፈጥኖ ወደ ቤት ደረሰ። ቅርጫቱ ግን አሁንም ባዶ ነበር። ትንፋሹ እየተቆራረጠ "አየህ አይደል አያቴ ምንም ጥቅም የለውም" በማለት ተናገረ። አያትየውም "ምንም ጥቅም የለውም ብለህ ነው የምታስበው ? እስኪ ቅርጫቱን ተመልከት" አሉት ። ልጁም ቅርጫቱን ሲመለከተው የተለየ ሆኖ አገኘዉ።በፊት በከሰል ዱቄት ቆሽሾ ያስጠላ ነበር። አሁን ግን ዉስጡም ሆነ ዉጪዉ በጣም ንጹሕ ሆኗል። አያትየዉ ንግግራቸዉን በመቀጠል "አየው ልጄ! ዘወትር ቁርኣን የምትቀራ ከሆነ የዚህን ዓይነት ለዉጥ ታያለህ። ሁሉንም የቁርኣን ቃላት መረዳት ሊያስቸግርህ ይችላል። ማስታወስም ያቅትህ ይሆናል። ነገር ግን ቁርኣን ስትቀራ ትለወጣለህ። በዉስጥህ ሆነ በውጫዊ ማንነትህ ላይ አዲስና መልካም ሰዉ እየሆንክ ትሄዳለህ። ይህን ነዉ አላህ በሕይወታችን ዉሰጥ የሚሰራዉ" አሉት። -------------------------------------- 🔗 @risaalaatube -------------------------------------- 💬 @ziyadper --------------------------------------
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.