cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ከዚህም ከዚያም

ሰላም ውድ አባላቶቻችን እንዲሁም እንግዶች ይህ ቻናል ለእናንተ ይጠቅማችኋል ብለን የምናስባቸውን - ታሪኮች - አጫጭር ፅሁፎች - ግጥሞች እንዲሁም ሌሎች ጠቃሚ እና አስተማሪ መረጃዎችን የምናደርስበት ነው።

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
206
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Repost from N/a
#መልካምነት_እና_መልካም_አስተሳሰብ_ለጥሩ_እና_መልካም_ህይወት_እና_ውጤት #ህይወታችን በመልካም እና በጥሩ ነገር እንዲሞላ: - ምንጊዜም ነገሮችን በመልካም ጎናቸው እንረዳ - መልካም እናስብ - መልካም ነገር እንናገር - መልካም ነገር እናድርግ #መልካምነት_ለጥሩ_እና_መልካም_ህይወት_እና_ውጤት Telegram: @NUHAMEN_INSPIRATION Tiktok: tiktok.com/@nuhamen_inspire ለሀሳብ ፣ አስተያየት እና ጥያቄ ፡ @NUHAMEN_inspirebot
Mostrar todo...
#የእንቅልፍ_እጦት_እክል/INSOMNIA ይህ ማለት ለመተኛት መቸገር፡በቂ ለሆነ ጊዜ በእንቅልፍ አለመቆየት ወይም ተኝተን ስንነሳ ምንም አይነት እረፍት የማይሰጥ ከሆነ የዚህ እክል ምልክት ነው ማለት እንችላለን።በአጠቃላይ የዚህ ችግር ተጠቂ የኖኑ ግለሰቦች ጥቂት ሰአታት የሚተኙ ወይም የተመቻቸ ቦታ ኖሮ መተኛት ሚቸገሩ ናቸው።ይህም እንቅልፍ ማጣት በቀን ተቀን እለታዊ ክንዉናችን ላይ ተጽኖ ይፈጥራል።ይህ ችግር በተወሰነ የሰአት ገደብ ከፍለን ከዚ በታች የሚተኙ ይህ እክል አለባቸው ለማለት እንቸገራለን ምክንያቱም የተለያዩ ግለሰቦች የተለያየ የእንቅልፍ ጊዜ ስለሚኖራቸው ነው።አብኛዉን ጊዜ ይህ ችግር ብቻዉን የሚመጣ ሳይሆን ከተለያዩ የጤና ችግር እና እለት ተእለት ከሚገጥሙን ስንክሳር ጋር የሚያያዝ ነው #ለምሳሌ ህመም፡ጭንቀት እና የተላያዩ የጤና ሁከቶች ጋር ይዛመዳል እነዚህ ተዛማጅ ባሉበት ወቅት ይህን እክል ለማስወገድ እና ለማከም ቀለል ይላል ምክንያቱም እነዙህ ምክንያቶች ከታወቁ እነሱን ማከም ያንን እክል ለማስወገድ ይረዳል።በአጋጣሚ ግን ምንም አይነት ተጓዳኝ ችግር ሳይኖር የእንቅልፍ ማጣት ችግር እራሱ ዋነኛ ችግር ሆኖ ሊመጣ ይችላል በዚህ ወቅት እራሱን እንቅልፍ ማጣትን ማከም ይኖርብናል ማለት ነው።በህክምና የተለያዩ ይህን ችግር ለመቅረፍ የሚረዱ መንገዶች ሲኖሩ ለዛሬ ከነዚህ መካከል በቀላሉ ቤት ወስጥ መተግበር የምንችላቸዉን መንገድ እናያለን እሱም ፦ጤናማ የእንቅልፍ መርህ ፡ የሰዉነታችን ጡንቻዎች የማዝናናት/ሪፍሬሽ ማድረግ ፡ እራስን መቆጣጠር ነው በህክምናው ወደ ተወሳሰቡ የህክምና መንገድ ከመሄዳችን በፊት ይህን ህክምና ማድረግ ይመከራል 1 ጤናማ የእንቅልፍ መርሆች መከተል 👇👇👇 #እረፈት እስኪሰማን ብቻ መተኛት ከዛም ከአልጋል ላይ መነሳት #ቋሚ የሆነ የእንቅልፍ ጊዜ ማበጀት ለምሳሌ ሁሌ 3 ሰአት ወደ መኝታ ማምራት #እንቅልፍ ሳይመጣ ወደ አልጋ በማምራት ለመተኛት መሞከርን ማወገድ #ከምሳ በኋላ የሚወሰዱ አነቃቂ መጠጦችን ማስወገድ ለምሳሌ ቡና #የመተኛ ጊዜያችን ሲደርስ ምንም አይነት አልኮል አለመዉሰድ #አለማጨስ በተለያ ማታ ላይ #ለመተኛት በምንሰናዳበት ወቅት የተለያዩ ሀሳቦች ሚያስጨንቁን እና ሚረብሹን ከሆነ የምናስበዉን ነገር በወረቀት ላይ መጻፍ እና ሲነጋ ለዛ ነገር መፍትሄ መፈለግ #መተኛት ሲያቅተን የተለያዩ መጻፍት ወይም አልጋ ላይ ሆኖ ቲቪ መመልከትን ማስወገድ #አልጋ ላይ ሆኖ ምግብ መመገብን ማስወገድ #አልጋ ላይ ሆኖ ስልክ ማናገርን ማስወገድ #በቀን ላይ ለአጭር ጊዜ የሚወሰዱትን ናፕ ማስቀረት #እንቅልፍ አልወስደን በሚል ወቅት በተደጋጋሚ ሰአታችንን በማየት መጨነቃችን ማስወገድ ይኖርብናል #እየራበን ወደ መኝታ አለማምራት #የመተኛ ክፍላችንን በተቻለ መጠን አመቺ እና ለእንቅልፍ እንዲጋብዝ አድርጎ ማዘጋጀት ለምሳሌ መብራት ፡ጫጫታን ማወገድ #ቋሚ የሆነ የስፖርት እንቅስቃሴ ማድረገ 2 የሰዉነታችን ጡንቻዎች የማዝናናት/ሪፍሬሽ ማድረግ 👇👇👇 ይህን ለመከወን በመጀመርያ የፊታችን ላይ ያሉትን ጡንቻ ለቀቅ ለማድረግ እና ለማዝናናት ለ5-6 ሰኮንድ ለሚያህል ጊዜ ጥርስትን ነክሶ/ጡንቻን በመወጠር/ መቆየት በመቀጠልም ለ20-30 ሰኮንድ ለቀቅ ማድረግ።ይህን መጀመርያ ከፊታችን ጡንቻዎች ጀምረን እስከ እግራችን ድረስ ይህንን መንገድ መከወን። ይህን በተደጋጋሚ መሞከር ይህም መንገድ ዉስጣዊ ስሜታችን ረጋ ሲለሚያደርገው ቶሎ እንቅልፍ እንዲወስደን ይረደናል። 3 እራስን መቆጣጠር፦ይህ ሀሳብ እንደ አንድ የህክምና መፍትሄ የመጣው በእንቅልፍ እጦት የተጠቁ ሰዎች ነቅተው ስራቸዉን እንዲከዉኑ ወይም በንቃት ያለዉን ነገር እንዲከታተሉ አልጋቸው ላይ መሆንን ይመርጣሉ።ከዚህም ጥናት በመነሳት ሀኪሞች መፍትሄ ለእንቅልፍ ማጣት ይህን አመላክተዋል፦አንድ ሰው ወደ አልጋው አምርቶ ከ20 ደቂቃ/ሰአት ማየት አይመከርም/ በላይ እንቅልፍ ካልወሰደው ከመተኛ ክፍሉ ወጥቶ ወደ ሌላ ክፍል በማምራት ሌላ ነገር መከወን ለምሳሌ ማንበብ ነገር ግን ስናነብ እንቅልፍ ከመጣ ተመልሶ ለመተኛት መሞከር አሁንም ወደ አልጋ አምርተን ያለ ምንም እንቅልፍ 20 ደቂቃ ካለፈ ያሁኑንን መንገድ በመደጋገም መሞከር ይሞከራል ይህ መንገድ ስኬታም መፍትሄ የሚሆነው አራት ዋና ህጎችን ስናከብር/ስነተገብር ነው 👇👇👇 #ህግ1 እንቅልፍህ ሲመጣ ብቻ ወደ አልጋህ ሂድ #ህግ2 አልጋህን ለመተኛት ብቻ ተጠቀመው ማለትም አልጋ ላይ ሆነህ ማንበብ ወይም መብላት አስወግድ #ህግ3 አልጋህ ላይ ሆነህ አይወስደኝም ብለህ አትጨናነቅ ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ተነስና ሌላ ክፍል አምራና ሌላ ነገር ስራ እንቅልፍህ ከመጣ ተመለስ እና ተኛ ካልሆነ ይህን መንገድ ደጋግመው #ህግ4 ሁል ጊዜ ማታ በደንብ ተኛህ አልተኛህ ቋሚ የሆነ የመነሻ ጊዜ አበጅ በተጨማሪ በቀን የሚደረግ እንቅልፍን አስወግድ #በነዚህ_በቤት_ዉስጥ_በሚከወኑ_መንገዶች_ምንም_አይነት_ለዉጥ_ካላመጣ_ወደ_ጤና_ተቋም_በማምራት_በመድሀኒት_ማስወገድ_ይቻላል @kezihm_keziam12
Mostrar todo...
. 🌀what if we see life just a bit differently? "Its not what you do its how you do it, Its not what you see its how you look at it Its not how your life is its how you live it" 💢ካህሊል ጂብራል የምንኖርበትን አለም በደንብ የሚገልጽ ድንቅ አባባል አለው። " ደስታ እና ሀዘን አይነጣጠሉም፤ በአንድ አንገት ላይ የበቀሉ ሁለት እራሶች ናቸው" ብሏል። 💢ምንም አወንታዊ ብንሆን፤ ምንም የእምነት ሰው ብንሆን ምንም የተማርን እና የተመራመርን ብንሆንም፤ ከህይወት መፈራረቅ አናመልጥም። ከሀዘን እና ከደስታ፤ ከስኬትና ከውድቀት ቅብብሎሽ አንድንም። ይህ እውን ከሆነ የምንለውጠው በዙሪያችን ያለውን ሳይሆን፤ በውስጣችን ያለውን ነው። 🌀ችግር አታሳየኝ እንደማለት ችግርን የማልፍበት ጽናቱን ስጠኝ ብንል፣ አልውደቅ ሳይሆን ስወድቅ የምነሳበት ጉልበት ይኑረኝ ብንል፣ በሩ አይዘጋብኝ ሳይሆን እሲከከፈትልኝ ድረስ የማንኳኳበትን ትዕግስት ስጠኝ ብንል፣ ፈተና አይግጠመኝ ሳይሆን ፈተናውን የማልፍበትን ጥበብ ይግለጽልኝ ማለት ብንጀምር የውጭውን አለም መቆጣጠር ቢያቅጠን ወሳኝ የሆነው የራሳችን አለም ላይ ሰላም እናሰፍናለን። ሰው በአስተሳሰቡ ይኖራል፤ የህይወት እይታውም ሆነ እጣፋታው የሚወሰነው በአስተሳሰቡ ነው። መልካም ኑሮ በመልካም አስተሳሰብ ይገነባል። 💢 የትኛውም የህይወት ጎዳና ላይ ብንቆምም፤ ወደፈልግንበት መዳረሻ የመሄጃው እድል ዛሬም አለን። ቀዳሚው ተግባር ግን አስተሳሰባችን ላይ መስራት ነው። ✍ሚስጥረ አደራው @kezihm_keziam12
Mostrar todo...
❄️አትቁም_ወደ_ነገ_ሂድ… "… እንደኔ ግን መሄድ ከመቆም ይሻላል። ... መቆም ቢያንስ ለጠላቶችህ የታወቀ አድራሻ ይሰጣል። መሄድ ግን ቢያገኙህ እንኳን ለፍተው እንዲያገኙህ ያደርጋል። መቆም በቆምክበት ቦታ ብቻ ያለውን እድል እንድትጠቀም ያደርግሃል ፤ መሄድ ግን የማታውቀውንም ዕድል እንድትሞክር ይረዳሃል። ስትቆም መጀመሪያ ታረጃለህ ፣ ቆይቶም ትበሰብሳለህ። ስትሄድ ግን መጀመሪያ ትደክማለህ ፣ ቀጥሎ ግን ትጠነክራለህ። ባለቀ ትናንት አትታሰር ፣ በተበላ ዛሬ አትወሰን ፤ ይልቅ ወደ ማይታወቀው ነገ ሂድ። ነገ ወዳ አንተ ሳይመጣብህ አንተ ወደ ነገ ሂድ። አንድ ቦታ ላይ የግድ እንድንቆም ቢፈለግ ኖሮ እግር ሳይሆን እንደ ዛፍ ሥር ይሰጠን ነበር። የመሄዳችን ዋናው ምክንያቱ የምንቆይበት ምክንያት አለመኖሩ ነው።" ⚜ምንጭ:-✍ "የአዲስ አበባ ውሾች" በዳንኤል ክብረት ☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️ @kezihm_keziam12
Mostrar todo...
​የትኩረት ያለህ! በሕይወታችን ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች አንዱ እና ዋነኛው ችሎታ ለአስፈላጊ ነገሮች ትኩረት መስጠት ነው፡፡ በየትኛውም እድሜ ብንሆን፤ ተማሪም ሆንን ሠራተኛ፤ በአጠቃላይ በምናደርጋቸው ነገሮች ላይ አተኩረን ውጤት ማስመዝገብን እና በአግባቡ ሥራዎቻችንን ማጠናቀቅ እንፈልጋለን፡፡ ትኩረታችንን ከተሰረቅን ከፍተኛ የሆነ የጊዜ እና የአቅም መባከን ያጋጥመናል፡፡ አስፈላጊ በሆኑ ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ ካልቻሉ፤ ከታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች መከተሉ ይጠቅማል፡፡ አንደኛ፡ አካባቢያችሁን አጢኑ ለትኩረታችን መሰብሰብም ሆነ መበተን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከሚያበረክቱ ነገሮች አንዱ አካባቢያችን ነው፡፡ በብዛት የምንሠራበት አካባቢ ምን አይነት ነው የሚለውን ማሰብ ይኖርብናል፡፡ ጽዱ ወይስ ቆሻሻ? ሁሉም በአግባቡ የተቀመጠበት ወይስ ብትንትን ያለ? ጸጥታ የሰፈነበት ወይስ በቀላሉ ልንረበሽ የምንችልበት? -- እነዚህን እና መሠል ጥያቄዎችን ለራሳችን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ በአጠቃላይ ከትኩረት ጋር በተያያዘ አካባቢያችንን ለሁለት መክፈል እንችላለን - ድምጽን እና እይታን በተመለከተ፡፡ ከድምጽ አንጻር ያለንበት ቦታ ወሳኝነት አለው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ጫጫታ ያለበት ቦታ ሆነው፣ ወይንም ደግሞ ለስለስ ያለ ሙዚቃ እየሠሙ መሥራት ይችላሉ፡፡ ይህ ግን ለአብዛኛው ሰው ላይሠራ ይችላል፡፡ ብዙ ሰዎች ሥራቸውን በትኩረት ለማከናወን ጸጥታ ይፈልጋሉ፡፡ በዚህም ምክንያት እኛ ከየትኞቹ ሰዎች እንደምንመደብ አውቀን ሁኔታችንን ማስተካከል ወሳኝ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ እይታን በተመለከተ ነው፡፡ አንዳንዶች የሚሠሩበት አካባቢ ያሉ ነገሮች ዝብርቅርቅ ሲሉ ደስ እንደሚላቸው ቢናገሩም - ከቅልጥፍና አንጻር ከተመለከትነው ብዙም የሚያዋጣ አይደለም፡፡ የምንሠራበት አካባቢ ላይ ያሉ ነገሮች ቦታ ቦታቸውን የያዙ ከሆኑ፤ ለቅልጥፍና አመቺ ከመሆኑ በተጨማሪ፤ ትኩረታችን እንዲሰበሰብ ይረዳል፡፡ ሁለተኛ፡ ቴክኖሎጂን በቦታው! ቴክኖሎጂ ብዙ ትሩፋቶችን ወደ ሕይወታችን ይዞ መጥቷል፤ ይህ ግልጽ ነው፡፡ ሆኖም ግን በዚያው ልክ ደግሞ የሰዎች የትኩረት አቅም ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እያሳደረ ይገኛል፡፡ ትኩረትን ከሚሰርቁ ነገሮች አንዱና ዋነኛው ቀበኛችን የሞባይል ስልክ ነው፡፡ የሞባይል ስልካችን "መልእክት አለህ!" እያለ አጭር ድምጽ ያሰማል፣ የሚደወሉ ጥሪዎችን ያስተጋባል፣ ከማኅበራዊ ሚዲያ በኩል አዲስ ነገር እንደ ደረሰን ድምጽ ያሰማናል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ትኩረት ከሚፈልግ ሥራ ለአፍታም ቢሆን ትኩረታችንን ወደ ስልካችን እናዞራለን፡፡ ሆኖም ግን ተመልሰን ወደምንሠራው ሥራ ትኩረታችንን ለመመለስ ሃያ ሦስት ደቂቃ ይፈጅብናል፡፡ ይህ ማለት ለሁለት ሰዓት ያህል አንድ ሥራ ላይ ለማተኮር ተቀምጠን፤ ሁለት ጊዜ ስልካችን ትኩረታችንን ቢወስድብን፤ በአጠቃላይ አርባ ስድስት ደቂቃ የሚሆን ጥራት ያለው የሥራ ጊዜ አባክነናል ማለት ነው፡፡ እንግዲህ… ስልካችን (ወይም ሌሎች የምንጠቀማቸው ቴክኖሎጂዎች) በቀን ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ትኩረታችንን ሰርቀውን ይሆን? ምን ያህል ደቂቃዎችንስ አባክነን ይሆን? ለዚህ ትልቁ መፍትሔ የሚሆነው ትኩረት አድርገን ለመስራት ስንፈልግ ስልካችንን ወይም ሌሎች ትኩረት ሳቢ የሆኑ ነገሮችን እንዳይረብሹን ማድረግ ነው፡፡ ከቻልን ሥራችንን እስከምንጨርስ ድረስ ስልካችንን ፍላይት ሞድ (Flight/Airplane Mode) ላይ ማድረግ፤ ካልቻልን ደግሞ ቢያንስ ሳይለንት በማድረግ ስልካችንን የማንነካካበት ቦታ ማስቀመጥ የተሻለ ነው፡፡ ይህንን በማድረጋችን ብቻ እጅግ ብዙ ሰዓት ከብክነት ማዳን እንችላለን፡፡ ሦስተኛ፡ አእምሯችንን እንወቀው አእምሯችን የሚያስብበት እና ነገሮችን የሚያከናውንበት የራሱ መንገድ አለው፡፡ ይህንን መንገድ ጠንቅቆ ማወቅ ትኩረታችንን የምንጨምርባቸውን መንገዶችም ይጠቁመናል፡፡ ከእነዚህ መካከል አንደኛው በአንድ ጊዜ ረጅም ሰዓት ለሥራ ከመቀመጥ ይልቅ፤ በከፍተኛ ትኩረት የምንሠራባቸውን ጊዜያት መመደብ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል - አራት ሰዓት ሙሉ በአንድ ቦታ ተቀምጦ ሥራ ከመሥራት ይልቅ፤ ሠላሳ ደቂቃ ሠርተን ከሦስት እስከ አምስት ደቂቃ እረፍት መውሰድ - እና በዚህ ሁኔታ አራቱን ሰዓት መሥራቱ የተሻለ ነው፡፡ በተጨማሪም ደግሞ ለረጅም ሰዓት የምንሠራ ከሆነ ተነስቶ መንጠራራት፣ ትንሽ ዞር ዞር ማለትም ይመከራል፡፡ ይህ አእምሯችን እንዲነቃቃ ያግዘዋል፡፡ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ለአእምሯችን አስፈላጊውን እረፍት እየሰጠን ብንሠራ በከፍተኛ ትኩረት ሥራዎቻችንን ማጠናቀቅ ያስችለናል፡፡ አራተኛ፡ በቂ እንቅልፍ እናግኝ አእምሯችን ታታሪ ሠራተኛ ነው፡፡ እኛ ተኝተንም ቢሆን ይሠራል፡፡ ሆኖም ግን አእምሯችን ተኝተን የሚሠራው እና ነቅተን የሚሠራው በእኩል መጠን አይደለም፡፡ እኛ ስንተኛ አእምሯችን የጽዳት ሥራን ይሠራል፡፡ ይህም ማለት ቀን ያየናቸውን እና የሰማናቸውን ነገሮች በአጠቃላይ የማጣራት (አስፈላጊውን ለረጅም ጊዜ እንድናስታውስ፣ አላስፋላጊውን ደግሞ እንድንረሳ) ሥራ ይሠራል፡፡ ለቀጣይ ቀን ሥራ ተዘጋጅቶ የሚቀመጠውም ስንተኛ ነው፡፡ ሆኖም ግን በቂ እንቅልፍ ካላገኘን፤ አእምሯችን በአስፈላጊ ነገሮች ላይ ትኩረት ለማድረግ እጅግ በጣም ይቸገራል፡፡ ልብ ካላችሁ ሹፍርና እና ማሽን ላይ የሚሠሩ ሰዎች በቂ እንቅልፍ እንዲያገኙ ይመከራሉ፡፡ የዚህም ምክንያት ከእንቅልፍ እጦት የሚመጣው የትኩረት ማነስ አደጋ ስለሚያስከትል ነው፡፡ በመሆኑም ስለ ትኩረታችን ስናስብ ለአእምሯችን በቂ እንቅልፍ የመስጠቱ ነገር ላይም ብናስብ መልካም ነው፡፡ ማጣቀሻ - Forbes ድረገጽ፥ Lifehack ድረገጽ፥ daveasprey ጦማር @kezihm_keziam12
Mostrar todo...
ስሜቴ በፎቶ ብገልፀውስ http://t.me/Bereket_meskele
Mostrar todo...
B.M📷ⓅⒾⓒⓉⓊⓇ🎥

እኛ እንደናንተን ለማስደሰት ነው የምንጥረው የስሜት መገለጫዎች አንዱ ፎቶ ነው #ስሜቴን_በፎቶ_ብገልፀውስ በሚል ሀሳብ ነው ይሄ channel የተከፈተው ለProfile picture የሚሆኑ #ስሜትን_የሚገልፁ #የደስታ_መግለጫ #ሀዘን // // #ምቾት // // #ፈተና // // #ስኬት // // አሉን ፎቶዎች Comment @Beriiii116

😄ስለ🤣ደ😂ስ😅ታ😆
😃😄😁😆😅😂🤣
☹️ሰለ😣ማ😖ዘ😫ን😩
☹️😣😖😫😩😣😖
❣ስ💘ለ💕ፍ💓ቅ💖ር💘
💔❣💕💞💓💗💖💘💝
🛩ስለ✈️ስ🛫ኬ🛬ት🚀
🚁🛩✈️🛫🛬🚀🛰
አለ ብዙ የተለያዩ pp አሉ
👈👈👈👈👈👈
sticker.webp0.32 KB
ፍቅር በፍልስፍና እይታ ፧ ንፅረተ-ፍቅር 📖📜📜📖 አብዛኞቻችን "ፍቅር" ሲባል ከሰማን እዝነልቦናችን ላይ የሚመጣብን በወንድና በሴት መካከል ያለው የመቀራረብ ስሜት ነው ። በእርግጥም እንዲህ ያለው ፍቅር ተጨባጭና ለተመልካች ግንዛቤ የማያዳግት ነው ። ተጨባጭነቱንና ግልፅነቱን ያገኘው በቴአትሮች ፣ በሆሊውድ ፊልሞች ወይም በፍቅር ልቦለዶች ብርታት ነው ማለት አይቻልም ። በነባሩ ባህል ውስጥ ስንመለከት የኖርነው እንዲህ ያለው የወንድና የሴት ፍቅር ወደ አንድ አካልና አንድ አምሳልነት ሲያመራ ነው ። 📖📜📖 ፍቅር አይነቱ ብዙ ነው ። በፆታዊ ፍቅር ብቻ አይገደብም ። የመጽሐፍ ቅዱሱ ንጉስ ዳዊት ቤርሳቤህን በማፍቀር ብቻ እሷን አግኝቶ አልተገታም ። በህይወቱ ውስጥ ሌላም አይነት ፍቅር እንዳለ አሳይቷል ። ለምሳሌ ለዮናታን ከፍተኛ ፍቅር ነበረው ከዚህም ባሻገር ልጁ አቢሴሎም ሲሞትም "አቢሴሎም ልጄ ልጄ" ሲል በተሰበረ ልብ ፍቅሩን ገልጿል ። ስለዚህ የጓደኝነትና የስጋ ዝምድና ፍቅር እንዳለ በዚህ እንረዳለን ። በፕሌቶና በሶቅራጥስ እንዲሁም በኢየሱስና በደቀመዛሙርቱ መካከል የነበረው ደግሞ እውቀትን ወይም ሃይማኖትን ተንተርሶ የሚመጣውን ፍቅር ይገልፅልናል ። በዚህ አይገታም የሰው ልጅ አገሩን፣ ወገኑን ፣ አቋሙን ፣ ቤተሰቡን ፣ አምላኩን በማፍቀር የተለያየ ፍቅር መኖሩን አሳይቷል ። 📖📜📖 የተለያዩ ግንኙነቶችን እራሳቸውን አስችለን የምንወክልበት መጠርያ ስለምናጣላቸው በጋራ ስያሜ የምንደፈጥጥበት ግዜ ብዙ ነው ። ፍቅርም አይነቱ ብዙ ቢሆንም አንዱን ካንዱ የሚለይ ስም ግን ሲውጣለት አይታይም ። ይሄንን ክፍተት ተመልክተው ለፍቅር አይነቶች ሶስት መጠርያ ያዘጋጁ ግሪኮች ናቸው ። "ፊልያ" (Philia)፣ "ኢሮስ" (Eros)፣ እና "አጋፔ" (Agape)ይሏቸዋል ። ምናልባት በጥሬው ብንተረጉማቸው "የወዳጅነት" ፣ "የምኞት" እና "የልግስና" የፍቅር አይነቶች ልንላቸው እንችላለን ። ፊልያ በንጉስ ዳዊትና በዮናታን መካከል የነበረውን የጓደኝነት ፍቅር ይወክላል ። ኢሮስ ደግሞ አፍቃሪው ተፈቃሪውን በማግኘት እርካታን የሚቃብዝበት አይነቱ ነው ። በወንድና በሴት መካከል የሚከሰተውን ማለታችን ነው ። አጋፔ ደግሞ መንፈሳዊ ፍቅር ሆኖ በሰውና በፈጣሪው ወይም በሰዎች መካከል ይከሰታል ። በቅዱሳት መጻህፍት አማካኝነት አምላክ ለሰው ልጆች ያሳየው ፍቅር በአጋፔ ውስጥ የሚጠቃለል ነው ። በአፀፋው ሰዎች ስለፈጣሪያቸው የሚቀበሉት መከራና ሞት የዚሁ የፍቅር አይነት ውጤት ነው ። 📖📜📖 ምኞት ያለበት ኢሮስን ጨምሮ ሶስቱም አይነት ፍቅሮች የተሸጋጋሪነት ጠባይ አላቸው ። ስለዚህ ፍቅር ሁልግዜም ከአንዱ ወደ ሌላው የሚያነጣጥር ጥልቅ ስሜት ነው ለማለት ተገደናል ። ነገር ግን እራስ አፍቃሪነትስ?የት ይመደባል?"ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ" የሚለው የአምላክ ትእዛዝ ለእራስ አፍቃሪነት እውቅና አይሰጥም?የስነ-ምግባር ሰዎች እና የስነ-ልቦና ምሁራን እራስን ማዕከል ያደረገ ፍቅርን ጤናማ ያልሆነ ስሜትና ያለመብሰል ምልክት አድርገው በመፈረጅ ያጥላሉታል ። የሃይማኖት ጉባኤዎችም ለራሳችን እራሳችን የምናሳየውን ፍቅር ያወግዙታል ፧ ምንጭ 👉 " የፍልስፍና አፅናፍ " ደራሲ 👉 ዶክተር ሞርቲመር ጄሮም ትርጉም 👉 ደራሲ ዓለማየሁ ገላጋይ ፧ ፨ በነገራችን ላይ ባሁን ሰአት ግሪኮች ከላይ ከጠቀስናቸው ሶስቱ የፍቅር አይነቶች በተጨማሪ አራተኛ ስተሪጅ(Sturige)ወይም "ቤተሰባዊ ፍቅር" የሚሉት አይነት ፍቅር እንዳለም ያምናሉ አንዳንድ መጽሀፍትም በዛ መነሻነት ፍቅርን በአራት ከፍለው ይገልጹታል ። @kezihm_keziam12
Mostrar todo...
ሰላም ውድ የ #ከዚህም_ከዚያም ቻናል ቤተሰቦች በያላቸሁበት ሰላም ሁኑልን! ሰሞኑን በቻናላችን ላይ የምንለቅቃቸውን መረጃዎች ለእናንተ ባለማድረሳችን ይቅርታ እየጠየቅን ይህም የተፈጠረው በሁኔታዎች አለመመቻቸት መሆኑን ልንገልፅ እንወዳለን። እናንተም ውድ አባላቶቻችን ከጎናችን ሆናችሁ ስለረዳችሁን አናመሰግናለን🙏🙏 እኛም ከአሁን በሁዋላ ጠቃሚ ፅሁፎችን ለእናንተ ማድረስ እንቀጥላለን።
Mostrar todo...
# ትምህርት_ለእውቀት_ወይስ ....? • ትምህርት ለእውቀት ሳይሆን ትምህርት ለሥራ የሚል ነገር የፈጠሩት ጥቅመኛ ሰዎች ይመስሉኛል። የሰውን ልጅ እንደመሳሪያ የሚያዩና የተሻለ መሳሪያ እንዲሆን የሚፈልጉ ናቸው ትምህርትን ለሥራ ያሉት። በዚህ የተነሳ ትምህርት አንዱ የጭቆና መሳርያ ሆኗል። ሰዎች በትምህርት ሽፋን የበሰበሰ አስተሳሰባቸውን ፣ ምክንያት የለሽ እምነታቸውንና ጠባቸውንም ጭምር ይጭኑብሃል። ትምህርት ዋና ግቡ መሆኑ የነበረበት እውቀት፣ ነጻነት፣ ምርምርና ራስህን ለማወቅ ነው። እንደዚያ ሲሆን ነው ጥሩ የሚሆነው። በጥንት ዘመን ትምህርት የተጀመረው፣ ለማወቅ ለመመራመር፣ ለመደነቅ ብቻ ነበር። አንድ ሰው በራሱ መንገድ ተመራምሮ የደረሰበትን የእውቀት ደረጃ ለሌሎች በነፃነት ያካፍላል፤ ያስተምራል። ሆኖም በመጀመርያ ሶፊስቶች የሚባሉ መጡና ጥበብን፣ እውቀትን፣ ትምህርትን ገበያ ለማዋል ሙከራ አደረጉ። እነ ሶቅራጥስ መጥተው ወደ ቀደመው ክብሩ መለሱት። በዚህ መንገድ ብዙ ዘመንም ተኖረ። በመጨረሻ ዘመነ ካፒታሊዝም መጣ! የሰውን ክብር በሚያወጣው ዋጋ ብቻ የሚመዝን፣ ሌላው የባርነት ዘመን መልኩን ቀይሮ መጣ። በባርነት ዘመን የሰው ልጅ ተገዶ በኃይል እየተያዘ ነበር የሚሸጠው። በአሁን በካፒታሊዝሙ ዘመን ግን የሰው ልጅ በራስ ተነሳሽነት ፣ ከአስፈሪው የኑሮ መከራ ለማምለጥ በፈቃደኝነት፣ ራሱን ለገበያ ያወጣል። ደሞዝ በሚል ስምም ይሸጣል። እንዲህ አይነቱ መሄጃ ያጣ ሰው የኮርፖሬት ድርጅቶች በርካሽ ዋጋ ይገዙታል። እድሜውን፣ ችሎታውን፣ ጉልበቱን መዝነው አውርደው አውጥተው ይገዙታል። ስሙን ግን ቅጥር ነው የሚሉት፣ ግዢ አይሉም። በእግር ኳስ፣ በእስፖርቱ አካባቢ ነው በእውነተኛ ስሙ ሲጠራ አልፎ አልፎ የምንመለከተው። በዘመነ ካፒታሊዝም ሁሉም ነገር ወደ ገበያ ነው። ሽንትና ሰገራም ወደ ኃይል ማመንጫነት ወደ ማዳበሪያነት ተቀይረው ገበያ ውለዋል። ሁሉም ነገር ወደ ገበያ በሚለው ሰው በላ የካፒታሊዝም ሕግ ጥበብም ትንህርትም እንዲሁ የገበያ ሸቀጦች ሆኑ። • # ምንጭ:- "የፍልስፍና መንገድ" በመጽሐፈ ኦዜል @kezihm_keziam12
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.