cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

🤗🤩ልዩ ልዩ friends forever

👌ጥቅሶች 👌🤔🤔🤔 😁 🅥🅘🅓🅔🅞 🌌𝕚𝕤𝕝𝕒𝕞𝕚𝕔 𝕨𝕒𝕝𝕝𝕡𝕒𝕡𝕖𝕣 👍Islamic neshida 👆motivation pictures ☺☺☺ 👉የተለያዩ ምክሮች

Mostrar mĂĄs
El paĂ­s no estĂĄ especificadoEl idioma no estĂĄ especificadoLa categorĂ­a no estĂĄ especificada
Publicaciones publicitarias
136
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 dĂ­as
Sin datos30 dĂ­as

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

💠✅ #ይነበብ ✅💠 🚹 አንድ በጣም ተናዳጅ ወጣት ነበር አንድ ጊዜ ይህን ባህሪው ያስተዋለ አባት አንድ ትምህርት ሊሰጠው ፈለገ ከዚያም ጠራውና በርካታ ሚስማር አሸከመውና በቀኑ ውስጥ በተናደድክ ቁጥር ሂድና አጥራችን ላይ ያለው እንጨት ላይ ምታው አለው። ሚስማሩን ተቀበለና የመጀመሪያ ቀን 37 ሚስማር አጥራቸው ላይ መታ። አባት የሚሰጡትን ትምህርት ሳይታክቱ እየተከታተሉ አጥራቸው ላይ የሚመታው ሚስማር በከፍተኛ ሁኔታ ቀነሰ። ከዚያም ልጁ ብዙም ሳይቆይ ንዴቱን መቆጣጠር ጀመረ እንደውም አንድም ሚስማር ሳይመታ መዋል ጀመረ። ይህን ባህሪ ለውጥ ለአባቱ እስኪነግር ድረስ በጣም ቸኩሏል አባትም በጣም ተደስቶ በል አሁን የመታከውን እያንዳንዱን ሚስማር ንቀለው አለው። ከዛም ከሳምንታት በኋላ ነቅሎ ጨረሰ እና ለአባቱ ነገረው። አባቱ የልጁን እጅ በፍቅር ይዞ ወደ አጥሩ አመሩ። "ጥሩ ስራ ሰርተሀል ልጄ ነገር ግን እነዚህን ቀዳዳዎች ተመለከትካቸው አንተም በንዴት ውስጥ ሆነክ አንድን ቃል ስትወረውር እንዲህ የማይመለስ ጠባሳ ጥሎ ያልፋል ምንም ይቅርታ ብትደጋግም ጠባሳውን አታጠፋውም"። ስለዚህ የምትናገረውን ቃላት ከመናገርህ በፊት አመዛዝነክ ተመልከት ሰውን የሚጎዳ ከሆነ አትጠቀመው የሚጠቅም ከሆነ ግን ተናገረው። "አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሼር ለወዳጅዎ ያካፍሉ" https://t.me/mfkfriends https://t.me/mfkfriends
Mostrar todo...
🤗🤩ልዩ ልዩ friends forever

👌ጥቅሶች 👌🤔🤔🤔 😁 🅥🅘🅓🅔🅞 🌌𝕚𝕤𝕝𝕒𝕞𝕚𝕔 𝕨𝕒𝕝𝕝𝕡𝕒𝕡𝕖𝕣 👍Islamic neshida 👆motivation pictures ☺☺☺ 👉የተለያዩ ምክሮች

አሰላሙአለይኩም ወራህወቱላሂወበረካቱህ የ ኢንተራንስ(EUEE )ማለፍያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ እንዲሁም ከፍተኛ ውጤት ያመጣችሁ በዛሬው እለት(እሁድ 1-9-2013) በደሴ ከተማ በደዌ ሜዳ መስጅድ ከ አሱር ብኋላ የዳእዋና የ ኢፍጣር ኘሮግራም ስላለ በአላህ ስም እድትገኙ እንጠይቃለን። @mfkfriends @mfkfriends
Mostrar todo...
#ለፆመኛ_የተወደዱና_የተጠሉ_ነገሮች ፆመኛ የሚከተሉትን ቢፈፅም ይወደዳል፦ ❶.ሱሁር (ከጐህ በፊት መመገብ)፡- ነቢያችን (ﷺ) እንዲህ ብለዋል “ሱህር (ከሱብህ በፊት) ተመገቡ በሱሁር ረድኤት አለ፡፡” 📚አል ቡኻሪ (❶❾❷❸) ሙስሊም (❶⓿❾❺) ጥቂት መጉረስ ወይም አንድ ጉንጭ እንኳ መጐንጨት ሱሁር ያስብለዋል፡፡ ወቅቱ ከእኩለ ሌሊት ጐህ እስኪቀድ ድረስ ነው:: ❷.ሱህርን ማዘግየት፡- ዘይድ ኢብን ሳቢት “ከነቢያችን (ﷺ) ጋር ሱህር ከተመገብን በኋላ ሱብህ ሰገድን” ብለው ሲናገሩ “በመካከላቸው የነበረው ወቅት ምን ያህል ነበር”? ብለው ጠየቋቸው:: እሳቸውም “ሀምሳ የቁርአን አንቀፆች የሚያስነበብ ወቅት ነበር”አሉ:: 📚አል ቡኻሪ (❺❼❺) ሙስሊም (❶⓿❾❼) ❸.ቶሎ ማፍጠር (ፆም መፍታት)፦ ፀሐይ መጥለቁ ሲረጋገጥ በፍጥነት ማፍጠር የተወደደ ተግባር ነው:: ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል “ሰዎች ፍጡር ላይ እስከቸኮሉ ድረስ ከመልካም አይወገዱም፡፡” 📚አል ቡኻሪ (❶❾❺❼) ሙስሊም (❶⓿❾❼) ❹.በተምር እሸት ማፍጠር፡- አነስ ባስተላለፉት ሀዲስ “ነቢዩ(ﷺ) ካገኙ በተምር እሸት ካላገኙ በተምር ተምርም ካላገኙ ውሃ በመጎንጨት ያፈጥሩ ነበር”:: 📚 አቡዳውድ (❷❸❺❻) ቲርሚዚ (❻❾❻) ❺.በፍጡር ወቅት ዱዓ (ፀሎት) ማድረግ፡- ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል “የሶስት ሰዎች ዱዓ ተመላሽ አይሆንም ፆምኛ ፆሙን እስኪፈት፣ ፍትሃዊ መሪና ተበዳይ” 📚 ቲርሚዚይ (❷❺❷❻) በይሀቂይ (❸❶❸❹❺) ❻.አቅም እስከፈቀደው ድረስ በብዛት መመፅወት ቁርአን ማንበብ፣ ፆመኛን ማስፈጠርና ሌሎችንም መልካም ተግባሮችን መፈፀም፡፡ኢብኑ ዓባስ እንዳስተላለፉት “ነቢዩ(ﷺ) መልካምን በመቸር አቻ አልነበራቸዉም በተለይ በረመዳን ከጅብሪል ጋር ሲገናኙ ቸርነታቸው እጅግ ይጨምራል:: ጅብሪል በየረመዳኑ እየመጣ ቁርአንን ይማማሩ ነበር፡፡ የአላህ መልዕክተኛ ከጅብሪል ጋር ሲገናኙ ከተላከ ንፋስ የፈጠኑ ቸር ይሆናሉ፡፡” 📚 አል ቡኻሪ (❻) ሙስሊም (❷❸⓿❽) ❼.የሌሊት ሰላት ማብዛት፡- በተለይም የመጨረሻዎቹን የረመዳን አስር ቀናት የሌሊት ሰላት ማብዛት የተወደደ ነው፡፡አኢሻ ረዐ እንዳሉት “የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) የረመዳን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ጅማሬ ላይ ሽርጣቸውን ጠበቅ አድርገው ሌሊቱን ያለእንቅልፍ ያሳልፋሉ:: ቤተሰቦቻቸውንም ያነቃሉ” አል ቡኻሪ (❷⓿❷❹) ሙስሊም (❶❶❼❹) በሚከተለውም ሀዲስ በጥቅሉ እንዲህ ብለዋል “የረመዳንን ሌሊት በእምነትና ምንዳን በማሰብ የሰደገ ቀደም ሲል የፈፀማቸው ኃጢአቶች ይታበሳሉ፡፡” ሙስሊም (❼❺❾) ❽.ዑምራን መፈፀም፡- ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል “በረመዳን ዑምራን መፈፀም ከእኔ ጋር ሐጅ እንደማድረግ ነው፡፡” አል ቡኻሪ (❶❽❻❸) ሙስሊም (❶❷❺❻) ❾.ሰው ሲሰድበው ፆመኛ ነኝ ማለት፡- ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል “አንድ ሰው ከሰደበው ወይም ከመታው እኔ ፆመኛ ነኝ ይበል፡፡” አል ቡኻሪ (❶❾⓿❹) ሙስሊም (❶❶❺❶) አንደኛ፡ ለፆመኛ የተወደዱ ነገሮች ሁለተኛ፡ በፆም እለት የሚጠሉ ነገሮች የሚከተሉት ነገሮች ለፆምኞች የተጠሉ በመሆናቸው የፆም ምንዳ እንዳይቀንስ ሲባል ጥንቃቄ ሊደረግባቸው ያስፈልጋል፡፡ ❶.በደምብ መጉመጥመጥና በአፍንጫ መሳብ፡- ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል “(ውዱእ ስታደርግ) ፆመኛ ካልሆንክ በአፍንጫህ በደምብ ሳብ” 📚ቲርሚዚይ (❼❽❽) ነሳኢይ (❶/❻❻) ኢብን ማጃህ (❹⓿❼) ❷.መሳሳም፡- ባለትዳሮች ከሁለት አንዳቸው ወይም ሁለቱም ስሜታቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው ግንኙነት ወደ መፈፀም ወይም የፍትወት ጠብታ ለማፍሰስ የሚዳርጋቸው ከሆነ መሳሳም አይፈቀድም፡፡ ነገር ግን የተጠቀሰው ስጋት ከሌለ ችግር የለውም ምክንያቱም ነብዩ (ﷺ) ፆመኛ ሆነው ባለቤታቸውን ይስሙ ነበር፡፡ አዒሻ “ከማናችሁም ይበልጥ ስሜታቸውን መግዛት ይችሉ ነበር፡፡” ብለዋል 📚 አል ቡኻሪ (❶❾❷❼) ሙስሊም (❶❶⓿❻) ❸.አስፈላጊ ሳይሆን ምግብን መቅመስ፡- ምግብ የሚሰራ ሰው ጣእሙን ለማወቅ ወደ ሆዱ እንዳይገባ ጥንቃቄ አድርጎ ሊቀምስ ይችላል፡፡ መቅመስ ሳይስፈልገው ያለምክንያት መቅመል ግን ይጠላል:: ምንጭ፦አል ፊቅሕ ሙየሰር #ቁርአን_ና_ሃዲሰ ✍🏻✍🏻 Sheref Mohamed ★彡 ላልደረሰው ለማዳረስ ሼር ማድረግ አይርሱ‼ 彡★ ------------*********------------- የውዱ ነብያችንን ﷺ(ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሀድስና የተለያዩ ትምህርቶችን ለመከታተል ወደ ግሩፑ ይቀላቀሉ ✶⊶⊷⊶⊷❍ 😍👇👇👇❍⊶⊷⊶⊷✶ የቁርአን ና ሃዲስ ተአምራት። ኢስላማዊ ጉሩፕ @mfkfriends።።...... .👍👍👍👍👍join @mfkfriends........... 👍👍👍👍join
Mostrar todo...
📌ረመዷን መች ነው⁉️ #በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች❓ ♻️ : ክፍል 162 📌ጥያቄ📌 📌 ብዙ ጊዜ በየማህበራዊ ሚዲያው የሚተላለፍ አንድ ሀዲስ አለ ፣ እሱም ረመዷን መች እንደሆነ #ለመጀመሪያ ጊዜ ለወንድሙ የተናገረ #እሳት ከሱ ሀራም ትሆንበታለች ይላልና ይህ ሀዲስ ትክክለኛነቱ እንዴት ነው⁉️ ✅መልስ✅ ✅ ይህ ሀዲስ #በየትኛውን የሀዲስ ኪታብ ላይ በጭራሽ ሊገኝ #ይቅርና በተቀጠፋ ሀዲሶች መዝገብ ውስጥ እንኳን #የማይገኝ በነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ላይ #የተቀጠፈ ሀዲስ ነው።ይህን ሀዲስ በየትኛውም መልኩ #ማሰራጨትም ሆነ #ማስተላለፍ የተከለከለ ነው። ♻️ ምንጭ: ኢማሙ ሲዩጢይ ፣ ተድሪቡ ራዊ ____________ *ያለፈዎትን ፈትዋዎች ለመከታተል 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ✔https://t.me/yeilmkazna
Mostrar todo...
[] የዒልም ካዝና []

★ ★ ★ ★ ★ በውስጥ መስመር ለሚላኩ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥበትና ፈትዋዎቹም በቻናሉ የሚለቀቁበት የቴሌግራም የፈትዋ ቻናል ነው። ያለፈዎትንም ፈትዋዎች ለመመልከትና ለመከታተል ይቀላቀሉ።

🥀 አስር (10) የሱብሂ ሰላት ጥቅሞች 🕋════❀🕌❀════🕋 🍃 በእስልምና ህግጋት ውስጥ በዋነኝነት የሚጠቀሰው ሰላት ነው። ሰላት አንድ ባሪያ ወደ ጌታው የሚቃረብበት መንገድ ነው። በ24 ሰዓት ክፍለ ጊዜ 5 (አምስት) የተለያዩ ወቅቶችን ወደጌታው የሚሰግድበት ሶስቱ በጨለማው ጊዜ የሚሰገዱ ሲሆን የተቀሩት ሁለት ሰላቶች በቀኑ ክፍለ ጊዜ ይሰገዳሉ። የቀኑ የመጀመሪያው ሰላት በቀኑ የንጋት ክፍለጊዜ ላይ የሚገኘው የሱብሂ ሰላት ሲሆን ስለሱብሂ ሰላት ጠቀሜታዎች እንዳስስ። የሱብሂ ሰላት ሌላኛው መጠሪያው ፈጅር በመባል ይታወቃል። በርካታ ኡለሞች ከሀዲስና ከቁርአን በመነሳት አስር ጠቀሜታዎችን ያስቀምጣሉ። የሱብሂ ሰላትን በጀመአ መስገድ ለአንድ ሰው በህይወቱ ላይ የሚፈጥረውን ጠቀሜታ እንመልከታለን። ▪️1. ቀኑን በሙሉ በአላህ ጥበቃ ስር ይውላል •┈┈┈┈•❒✹❒•┈┈┈┈• ጁንዱብ ቢን አብደላህ ቢን ሱፍያን በጅሊ አላህ መልካም ስራዎቻቸውን ይውደድላቸው አሉ ነብያችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም አሉ “ሱብሂን ሰላት በጀምአ የሰገደ በአላህ ጥበቃ ስር ይውላል …….” “የሱብሂን ሰላት በጀመአ መስገድ በቀኑ ክፍለጊዜ በአላህ ጥበቃ ስር ይውላል ፣የሰው ልጆች ከሰዎች ጠባቂ ተላቀው በጌታቸው እንዲብቃቁና እንዲጠበቁ የሚደርግ ሰላት ነው፣……..” [📚ሙስሊም ወአህመድ] ▪️2. አጅሩ(ምንዳው) ለሊቱን እንደቆመ ይቆጠርለታል •┈┈┈┈•❒✹❒•┈┈┈┈• አቢሁረይራ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ“የኢሻን ሰላት በጀመአ የሰገደ ግማሹን ለሊት እንደቆመ ሲሆን ሱብሂን በጀመአ የሰገደ ሙሉውን ለሊት እንደቆመ ይቆጠራል።” [📚ሙስሊም] ▪️3. ከሙናፊቅነት ነጃ ይባላል •┈┈┈┈•❒✹❒•┈┈┈┈• አቢሁረይራ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ“በመናፍቃን ላይ ከባድ ሰላቶች የሱብሂና የኢሻ ሰላቶች ናቸው የእነዚህን ሰላቶች ጥቅም ቢያውቁ ኖሮ በዳዴም ቢሆን ወደሰላቱ ይመጡ ነበር።” [📚አህመድ፣ቡኻሪ እና ሙስሊም] ▪️4. ሙሉ የሆነን ኑር (ብርሃንን) ይለብሳል፤ በቂያም ቀን (በትንሳኤ ቀን) •┈┈┈┈•❒✹❒•┈┈┈┈• ከቡረይዳ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ተይዞ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም “በጨለማ መስጂዶችን የሚጓዙ በየውመል ቂያማ (በትንሳኤ ቀን ) በሙሉ ኑር (ብርሃን) ይሆናሉ።” [📚አቡ ዳውድ እና ቲርሚዚ] ▪️5. መልአክቶች ይመሰክሩለታል፤ ያወድሱታልም •┈┈┈┈•❒✹❒•┈┈┈┈• አቢሁረይራ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ “በሰው ልጆች ላይ የተመደቡት መልአክቶች ይቀያየራሉ። በቀኑና በምሽቱ ክፍለ ጊዜ የሚቀያየሩበት ሰአት የሱብሂ ወቅት ላይ እና የአስር ወቅት ላይ ሲሆን ከዛም የ24 ሰአት ውሎአቸውን አላህ እያወቀ ለመልእክተኞቹ ይጠይቃቸዋል። ባሮቼን እንዴት ትታችኃቸው መጣችሁ ብሎ ሲጠይቃቸው፤ እነሱም እንዲህ ይመልሳሉ። እየሰገዱ ትተናቸው መጣን። ስንመጣም እየሰገዱ አገኘናቸው።” [📚ቡኻሪ ወሙስሊም] ▪️6. አጅራቸውን ልክ ሀጅ እና ኡምራ አድርገው እንደመጡ ማስመዝገብ ይችላሉ •┈┈┈┈•❒✹❒•┈┈┈┈• አነስ ቢን ማሊክ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ባስተላለፉት ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ“የሱብሂን ሰላት በጀመአ የሰገደ ከዛም ፀሀይ እስክትወጣ በዚክር ቁርአን በመቅራት እና መሰል ኢባዳዎች ሲሰራ ቆይቶ ሁለት ረካአን የሰገደ ከሀጅ እና ከኡምራ ጋር የሚስተካከል አጅርን አገኘ ሙሉ መሉ አጅርን ሸመተ” [📚 ቲርሚዚ] ▪️7. ዱንያ ላይ አከፋፍሎ የማይጨርሰውን ምርኮ ያገኛል •┈┈┈┈•❒✹❒•┈┈┈┈• ኡመር አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና በስተላለፉት ሀዲስ ላይ “ከነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ይዞ በዘገበው ስለምርኮ እና ውርስ እያወሩ በነሩበት አጋጣሚ ብዙዎቹ በዚህ ምርኮ ላይ ፈጥነው ውሳኔን የሚወስኑ ፈጣኖች ሲሆኑ አንድ ምንም የለሌለው ሰው እንዲህ አላቸው ምን አይነት ነገር ላይ እንፍጠን ውሳኔያችንስ ምን ላይ ይሁን ስለበላጩ ምርኮ ከዚህ በሚበልጠው ሲላቸው ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ “ልምከራችሁን? (ልጠቁማችሁን) ከህዝቦች በላይ ስለተደረጉት በምርኮ ላይ ፈጥነው ከሚሽቀዳደሙት?ህዝቦች ናቸው የሰላተ ሱብሂን ሰላት በጀምአ የተካፈሉት ናቸው ከዚያም ፀሀይ እስኪወጣ አላህን የሚዘክሩ የሆኑት እነዚህ ናቸው ወደእውነተኛው ምርኮ በፍጥነት የሚሽቀዳደሙት።” [📚ቲርሚዚ] ▪️8. ከሱብሂ ሰላት በፊት የሚገኘውን ትልቅ እድል ይገጥማቸዋል •┈┈┈┈•❒✹❒•┈┈┈┈• አኢሻ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ባስተላለፈችው ሀዲስ ላይ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ“ከሱብሂ በፊት የምትሰገደው ሁለት ረከአ ሰላት ዱንያና ዱንያ ከያዘቻቸው ነገሮች በሙሉ ትበልጥለታለች” [📚ሙስሊም] ▪️9. ከእሳት ነፃ ይባላል በጀነትም ይበሰራል •┈┈┈┈•❒✹❒•┈┈┈┈• ኡማራህ ቢን ሩወይባ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ “ፀሀይ ከመግባቷ በፊት እና ፀሀይ ከመግባቷ በፊት ሰላትን የሰገደ ሰው እሳት አያገኘውም” ይህም ማለት “የሱብሂ እና የአስር ሰላቶች ናቸው።” [📚ሙስሊም] ▪️10. በቂያማ ቀን (በትንሳኤ ቀን)ጌታውን ለማየት ይታደላል •┈┈┈┈•❒✹❒•┈┈┈┈• ጀሪር ቢን አብድላህ በጀሊይ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ይላል “ከነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ተቀምጠን የለይለተ በድርን (ከረመዳን ለሊት) ጨረቃ በተመለክትን ጊዜ እንዲህ አሉ “ልክ ይችን ጨረቃ እንደምታዩት ጌታችሁን ማይት ትሻላችሁ እንግዲያውስ ፀሃይ ከመውጣቷ በፊት እና ከመግባቷ በፊት ያሉትን ሰላቶች እራሳችሁን አሸንፉ” [📚ቡኻሪ እና ሙስሊም] ሙእሚን አላህን እውነት ብሎ ላመነ አንዱም ሀዲስ በቂ ነበር። የሰው ልጆች ግን ዝንጉና ረሺ በመሆናቸው በርካታ አስታዋሽ ሀዲሶች ሊቀርብ ችሏልና የሱብሂን ሰላት በጀምአ ለመስገድ ከምንግዜው በላይ መጠናከር ይኖርብናል። መቼስ በቂያማ ቀን የአላህ ፊት ማየት የማይሻ የለም እና ይህን ለማግኘት በእነዚህ ሰላቶች መበራታት አለብን እስቲ ይህን የቁርአን አንቀፅ አንብበው፦ وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ نَّاضِرَةٌ ﴿٢٢﴾ إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٌ ﴿٢٣﴾ “ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው። ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው።” ይህን ከባድ ቀን እንደዋዛ ልታሳልፈው ነው ወንድሜ? ይህን ታላቅ ብስራት እንደቀልድ ልታባክነው አሰብክን? የተጫነብንን አብዋራ አራግፈን ከቸልተኝነት እና ከአላዋቂነት ለመንቃት ይህች ቁርአን። ይህች አለም ደሞ ጠፊ መሆኗን ባወቅን ጊዜ ምነኛ በባነንን ነበር! ነፍስህ በዚያ በውድቅት ለሊት ተኛ ብላ በትወሰውስህ ሙአዚኑ እንዲህ ሲል ንቃ! “አሰላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም” “ሰላት ከእንቅልፍ ትበልጣለች” ብሎ ሲጠራክ ጌታክን ለማየት እንደምትቻኮል አትጠራጠር! ያን ጊዜ የሰላተ ሱብሂን ጥፍጥና ታገኝና ዱንያ አሉ በሚባሉ ማናቸውም ነገሮች የማትተካውን ደስታ እና ከአላህ ጋር ከባድ ፍቅርን ትላበሳለክ። ═════❀🍓❀═════ 💎https://t.me/Tibyaan54
Mostrar todo...
💎ቲብያን 💎 የተለያዩ ዳዕዋዎች የሚተላለፉበት ቻናል!

🍂የቲብያን ቻናል ዋና አላማው አላህ ኢኽላሱን ይስጠንና በተቻለን አቅም ጠቃሚ ናቸው የምንላቸው ወቅታዊ ሙሃደራዎችን እንዲሁም ጠቃሚ ማስታወሻዎች አጫጭር ፁሁፎችና ፎቶዎችንምን ! ላልደረሳቸው ማድረስ ነው። «السلفية منهجي»

https://t.me/joinchat/AAAAAEPOgchGXF37Mja27A

✔️✔️ #ቀልድ መሳይ ቁም ነገር ላካፍላችሁ። አንድ ሙስሊም ያልሆነ ሰው ወደ አንድ ሸህ...መጣና የምከተሉትን ጥያቄዎች ጠየቃቸው። #በኢስላም ሴት ልጅን መጨበጥ የተከለከለው ለምንድን ነው?? 🏿 #ሸህ፦.አንተ የንጉስ ኤልሳቤጥን እጅ መጨበጥ ትችላለህ? ሙስሊም ያልሆነ ፦በርግጥ አልችልም አንዳንድ ሰዎች አሉ የምጨብጧቸው። 🏿 #ሸህ፦ ሴቶቻችን ንግስቶች ናቸው ። ንግስት ደግሞ የእንግዳ ( የተከለከለ) ሰውን እጅ አትጨብጥም ። ሙስሊም ያልሆነ፣፦ የሙስሊም ሴቶች ለምንድን ነው የምሸፋፈኑት? 🏿 #ሸህ.፦ ፈገግ ብለው ሁለት ከረሜላዎችን አወጡና አንዱን ሽፋኑን ገልጠው ሌላውን ሸፍነው አቧራ ላይ ጣሏቸው ። ከዚያም የትኛውን ትመርጣለህ? አሉት #እሱም ፦ የተሸፈነውን አለ። 🏿 #ሸህ.፦ እኛ ሴቶቻችንን እንደዚህ ነው የምናየውና የምንከባከበው። ሴት ልጅ እንደ ጨራቃ መሆን የለባትም ሁሉም እንደ ልቡ የሚያያት እና የሚመኛት፤ እንደ ጸሃይ መሆን አለባት አይቶ እይታውን የሚቀንስ። ሙስሊም ያልሆነ ፦ ፈጣሪ አለ ካላችሁ አሳዩኝ .. 🏿 #ሸህ፦.እስቲ ወደ ላይ ቀና በልና ጸሃይን እያት . #ካፊሩ፦አልችልም ጨረሯ ከባድ ነው ። 🏿 #ሸህ ፦ የሱን ፍጥረት ማየት ካልቻልክ እንዴት ፈጣሪን ማየት ትችላለህ አሉት? በመጨረሻም ወደ ቤቱ ወሰዳቸውና የወይን ፍሬ ሰጠቸው ። 🏿 እሳቸውም ተመገቡ ( በሉ) እንደገና ወይን ጠጅ አመጣና ሰጣቸው ። 🏿 #እሳቸውም #አልጠጣም አሉት። እሱ ፦ወይን ፍሬ ከበሉ ለምን ወይን ጠጅ አይጠጡም ሲል ጠየቃቸው ? 🏿 #ሸህ..፦ ሴት ልጅ አለህ አሉት ? #እሱም፦ አዎ አለ። 🏿 #ሸህ፦ ልጅህን ታገባታለህ አሉት? እሱም፦ በፍጹም አለ። 🏿 #ሸህ፦ ሱብሃን አሏህ ..እናቷን አግብተሃታል ልጅህን ግን አታገባትም የተወለደችው ግን ከርሷ ነው በማለት የኢማን ጥልቀታቸውን አሳዩት፡፡ #share
Mostrar todo...
@mfkfriends.. 👍👍👍 @mfkfriends🤗🤗🤗
Mostrar todo...
@mfkfriends. 👍👍👍👍🥰🥰 @mfkfriends👍👍👍👍
Mostrar todo...