cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የደሱ ግጥሞች

☞ የስብህና ልቀት ለማምጣት ከመፃህፍት ጋር እናዉጋ ☞ በዚህ ቻናል ተወዳጅ የሆኑ ግጥሞችንና አስተማሪ ታሪኮችን ይቀርቡበታል ለሃሳብ አስተያዬታች @Almnu6 @Almnu6 መነጋገር ይቻላል ገጣሚ ማለት በአጭረር አነጋገር እረጅም ሃሳብን መግለፅ ነዉ፡፡

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 430
Suscriptores
-324 horas
-67 días
-3530 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ካልጠበቁት ሰው እንደሚሰነዘር ጥቃት አሳማሚ ህመም የትም የለም !! በሂወቴ ከምጠላው ማንነቴ ስሜት እና እውነቴን ተከትዬ ቀድሜ ማጥቃት አለመቻሌ ነው !! እስከመቼ የምችለው ቀድሞኝ እያጠቃኝ ይጥለኛል ?? እስከመቼ ነገሮች ከብዙ አቅጣጫ ለማየት ስወናወን ከአንድ አቅጣጫ የሚያይ ይረታኛል ?? ጨካኝን አረመኔ ሳንሆን ፣ ጥቅመኛን ስግብግብነት ሳይጠናወተን ፤ ደደበን ሳንደነቁር እንዴት ማሸነፍ ይቻለናል ?? እስከመቼ መቀደሜ እልህ እና ድብርት ወልዶ መጥመልመሌ ፍቅር ይመስለኛል ?? በጠላትነት የምንቆጥረው ፣ የማንወደው፣ የማይወደን ፣ ከዚ ቀደም የበደለን ፤ ከዚ ቀደም የበደልነው ። ሊበድለን ምቹ ግዜ የሚያመቻች ነው ብለን በዓይነ ቁራኛ የምናየው ቢበድለን ... ህመሙ አጥንታችንን ዘልቆ አይፍቀንም ! አምነን ጥርጣሬያችንን አውልቀን ጥለን ፤ ፍላጎታችን ሰውተን ፣ ቢገፉን የሚገሉን ገደል አፋፍ ላይ ጀርባችን ሰጥተን የመቆም ያህል እምነት የሰጠናቸው ሰዎች ሆን ብለው ሲጨክኑብን የሚያመን ህመም ሰቅጣጭ ነው !! ጠላቴን እኔው እታገለዋለሁ ወዳጄን ብቻ አራራልኝ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Mostrar todo...
"ቀን ሲጨልምብን መኖር ስልችት ሲል ምናለ አንዳንዴኳ'ን ሞት በ'ጃችን ስንመርጥ ፈጣሪ ይቅር ቢል
Mostrar todo...
😭
«እኔ ኢትዮጵያውያንን አላምንም ከራሴ ጀምሮ። በጭንብል ተሸፍነን የምንኖር ህዝቦች ነን። ለሰው የምናሳየው ገፅታና እውነተኛው ባህሪያችን የተለያዩ ናቸው። እንደ ተረታችን ፣ ስነ ፅሁፋችንና ንግግራችን ባህርያችንም ሰምና ወርቅ ነው ... በዚህ ላይ ደግሞ ክፉውና በጎውን ነገር አንዱን ከሌላው ለይተን የምናይበት መለኪያ የለንም ፤ የማንኛውም ነገር መሠረታዊ መለኪያችን የግል ጥቅማችን ነው። ለዚህም ነው ተንኮል የሚበዛው፤ መተማመን የሌለው፤ የወዳጅነት ወይም የጓደኝነት ትርጉሙ የማይታወቀው ፤ ሀሜት አሉባልታና እርስ በዕርስ መበላላት የሚበዛው። ኢትዮጵያዊያን ስንባል የምናውቀው መርህ አንድ ብቻ ነው ፤ የግል ጥቅም! ከራስ በላይ ነፋስ ፤ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል... ሰውን ማመን ቀብሮ ፥ ይሉታል ከነተረቱ። የሚያሳዝን ነው... ለግል ጥቅማችን የሚበጅ ከሆነ እንዋሻለን። ስንዋሽ ህሊናችንን ቅንጣት ታህል አይቆረቁረንም። እንዴት አድርጎ ለግል ጥቅም የተገዛ ህሊና ሊቆረቁረው ይችላል? ለተንኮል አንመለስም የምንሸርበው ተንኮል ጓደኛን፤ ወዳጅን ፤ የስጋ ዘመድን አይለይም ቅናት ባህላችን ነው። ምግባር የሚባለውን ነገር በአፍ ካልሆነ በቀር በተግባር አናውቀውም። በአጠቃላይ ክፉውንና በጎውን ለይቶ የሚያይ ህሊና የለንም፤ ያስተማረንም የለም። የተማርነው ነገር ቢኖር በአደባባይ ሰው መስሎ መታየትን ነው፤ ሰው መሳይ በሸንጎ ይሉ የለም? በአደባባይ ሁሉም ጨዋ፣ ልበ ሙሉ፣ ጀግና፣ አትንኩኝ ባይ፣ ኩሩና ቅን፣ በጎ አሳቢና ታማኝ፣ አስተዋይና ትሁት ነው። በአደባባይ የምናጠልቀው ጭንብል ይህ ነው። በግል ኑሮአችን ግን ከስብቅ ፣ ከምቀኝነት ፣ ከተንኮል፣ ከቅናት ፣ ለውሸት፣ ከአሉባልታና ከሀሜት፣ ለግል ጥቅም ለመልከስከስና ለመልፈስፈስ ከፍርሃትና ከአድር ባይነት ርቀን አንገኝም። መለያ ባህርያችን ግብዝነት ነው። የግብዝነት ጭንብል አጥልቀን ነው የምንኖረው። ያለ ጭንብል እናስቀይማለን... ወይም እናምራለን፤ አይታወቅም። ያለ ጭንብል ታይተን አናውቅማ!» በዓሉ ግርማ የቀይ ኮከብ ጥሪ 1972 ዓም ገፅ 234 በፅሑፉ ሃሳብ ትስማማላችሁ?
Mostrar todo...
🌹
👍
🙈
😂
ምሽት በረንዳ ላይ (በእውቀቱ ስዩም) አገር ምድሩ መሽቶ ሌቱ ምጣድ ሆኖ ፥ በኮከብ ተሟሽቶ የጎዳናው መብራት ፥ጨለማው ላይ ሲገን ከመስኮት አምልጦ ፥የወጣ ወጋንን ሳር ቅጠሉን ሲያሳይ አጥብቄ ስፈልግ ፥የእለት ያይኔን ሲሳይ የሌት አይኔን ሲሳይ በኩርማን ገላዋ፤ እራፊ ደርባ የራሷ ሻጭ ሆና ፤ለሸመታ ቀርባ በሌት ይፋ ሆና፥ በቀን ልትደበቅ ያልቀጠረችውን ፥የምትጠባበቅ አንዲት ሴት እያየሁ አሰላስላለሁ ፤ “ አብረዋት ያደጉ፤ ብጤዎቿ ሁሉ በድሜና በውበት እሷን የሚያክሉ ተድረው እንደ ሴት፥ ተከብረው እንደ ሰው የባሎቻቸውን ደረት ተንተርሰው ፍቅር ሲያጣጥሙ ወይ በንቅልፍ ሲሰጥሙ ይች ወገን አልባ የሌሊት አበባ በቀትር ተኝታ ለውድቅት የነቃች የቱን ፍሬ በልታ ለዚህ ፍዳ በቃች ?” እያልሁ አስባለሁ፥ ደሞ ከደጃፌ ትንሽ ማዶ ርቆ የመሸበት ለማኝ ፤ መንገዱ ዳር ወድቆ በግልጥ ይታየኛል “ ረፍትን ላክልኝ ፥ወይ እንጎቻህን ጣል በራብ እና በንቅልፍ ሰው እንዴት ይቀጣል" የሚል ይመስለኛል ፤ በረንዳ ላይ ቆሜ፥ በሌሊት ስምሪት ከመስኮት በወጣ፥ የብርሀን ቅሪት አይቼ ማልዘልቀው ያገሬ ጎዳና የት ላይ ነው የሚያልቀው መከራና ውበት የሚያፈራርቀው::
Mostrar todo...
👌 አይኑ ተመልክቶ ልቦናው ያልቃኘ የያዘውን ትቶ ሌላ ያልተመኘ አካላዊ ወረት ያረገጠው ደጁን አለወይ ከሰዎች ያልካደ ወዳጁን ውድ ፍቅረኛውን ልቡ እንዳፈቀረ በስዋ ተወስኖ ዘላለም የኖረ እስከ መጨረሻው መንፈሱ ሳይላላ ከሚወደው በቀር ያልተመኘ ሌላ ማናት ወይስ ማነው ይህንን የሰራ በቃሉ የሚገኝ ባአስቀመጡት ስፍራ ከሴትም ከወንድም ያልተለዋወጠ ማን ይሆን ወዳጁን በሌላ ያልሸጠ ተፃፈ💪💪💪💪💪ኩረጃጃ
Mostrar todo...
👍 1
በዘመን ጠባሳ የደከመ ተስፋ፣ ከሚጨበጥ ጥሪት ላያገኝ ሲለፋ፣ ከመቅፅበት ቢቆቆ ለፀሎት ከአምላኩ፣ እንዴት ሰው ያገኛል ንግስቱን በልኩ። ተፃፈ✍ደሱ(ማነሽ ባለ ግጥሟ)
Mostrar todo...
🌹
👍
🙈
😂
😍 ስወድሽ 🌹 ፡ የውልሽ ውዴ ሆይ ከዚ ሁሉ ፍጡር፣ እኔና አንቺ ብቻ በምድር ላይ ብንቀር፣ በራሳችን አለም በራሳችን ቅጥር፣ ብዬ ተመኘሁኝ በዝቶ የኔ ፍቅር፣ ፡ ከምድር ጥግ ጫፍ ከሰማይ አፍላጋት፣ ለማንም ያልታየ ደግሞም ለነብያት፣ እኔ ልብ ውስጥ አለ እጅግ እልፍ ናፍቆት፣ ፡ ቴዎድሮስ ገብርዬን ሚያምነውን ያህል፣ እኔ አምንሻለው ለስትንፋሴ ጣዖት የሆንሻት ይመስል፣ ፡ ቃሎቼ ቢያወሩሽ አንቺ ማለት ለኔ፣ የናርዶስ ሽቱ ነሽ የመስዋዕት ከርቤ፣ ፡ እኔ አንቺን ስወድሽ እልፍ ነው መዘዙ፣ አመዳም ተራሮች አብረቅርቀው ወዙ፣ ፣ እኔ ነኝ የማውቀው ይብስ አንዳንዴማ፣ ናፍቆትሽ ሲያዞረኝ እንደ ክፉ ገልማ፣ እንኳን ሌላ ቀርቶ ራሴንም አልሰማ፣ ፡ ብቻ የምነግርሽ እኔ አንቺን ስወድሽ፣ አለም ትቀናለች ምን ብዬ ልንገርሽ፣ ፡ የፏፏቴ ድምፀት ይሁን ላንቺ ሆታ፣ ከአንደበት አልባው ከአለት እልልታ፣ ከተመረጡቱ ከፃድቃን ተርታ፣ ነፍሴ ታጥንልሽ ለፍቅርሽ ተገዝታ፣ ፡ ፀሃይ ነሽ ለኔ አለም ሁልጊዜም አንዳንዴ፣ ቃል አይገልፀው ፍቅሬን እልፍ ነው መውደዴ፣ ፡ ማህሌቱን ሲደግም ከአትሮኖስ ቆሞ፣ ስምሽን ቢያነሳው ቅር አይለኝ ደግሞ፣ ፡ እንደ በተስኪያን ደጅ ግንባርሽን ስሜ፣ እንደ ቀሲስ መስቀል አንቺን ተሳልሜ፣ ብኖር እመኛለሁ ✍✍ሸጋ ነገር ናት ሼርርር
Mostrar todo...
*የማጋራት ጣዕም* (በረከት በላይነህ) ብልህ! ስንጥቅ ምጣድ ጣደ ፣ ሽንቁር ድስቱን ጣደ ፤ ቅጠሉን ፣ እንጨቱን ፣ ኩበት ...ምናምኑን በእርጥቡ ማገደ ። . እንክርዳዱን ፈጨ ፣ ያለእርሾ አቦካ ፤ የነቀዘ ጓያ በሽሮ ስም ከካ ። . ዲቃላውን ድንች ፣ ከደረቀው ሽንኩርት ፣ ከወየበው ጎመን ፣ ከሸክላው በርበሬ - ያለጨው ቀየጠው ፤ ከዚያ ! "እንብላ !" ይለናል 'በሰው' ሊያጣፍጠው
Mostrar todo...
ደክሟችሁ ያውቃል ተስፋ አጥታችሁ ታቃላችሁ ተዘበራርቃችሁ ብቻ ተውት
Mostrar todo...
😭
ሰው ክቡር እያለ ሹም እንዲህ ሳይበዛ፣ ያኔ ንጉስ ነበርኩ እኔም እንደ ዋዛ!!
Mostrar todo...
🌹
👍
🙈
😂
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.