cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ግቢ ጉባኤ (OFFICIAL)

🖋️✍️ ይህ ቻናል በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ግቢ ጉባኤ የተከፈተና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ትውፊትና አስተምህሮ የጠበቁ ትምህርቶች፣ ወቅታዊ መረጃዎች፣ ኪነጥበባዊ ፅሁፎች፣ ዝማሬዎች የሚለቀቁበት ነው። ጽሑፎቹን ለጓደኞችዎ share በማድረግ የበኩልዎን ድርሻ ይወጡ! ያሎትን ጥያቄ ሀሳብ አስተያየት በ @referal_gibi_gubae ያድርሱን። 🙏

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
896
Suscriptores
Sin datos24 horas
+97 días
+3230 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
#ከእግዚአብሔር_ቤት_መረቅናችሁ።                        መዝ 118:26 🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓      ውድ የግቢ ጉባኤያችን ቤተሰቦች የሆናችሁ እጩ የ [PHARMACY] እና [Ansthesia] ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ! ▬▬▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬ በግቢ ጉባኤ ሆነን የእግዚአብሔርን ቃል ተመግበን የመንፈስ መጠጥ ጠጥተን በፍቅር ተረዳድተን በአገልግሎት ተግተን በጸሎት ፀንተን በቃሉ ተሰብስበን ኖረን ይኸው ዛሬ ላይ ደርሰናል እናንተም(ተመራቂዎች) ልባችሁ ውስጥ የፃፋችሁትን ፍቅር ይዘናል ያለፈ ሳይሆን ህያው ትዝታንም በልባችን አትመናል! በአንዲት ቤ/ክ ውስጥ ብንሆንም በመንፈስ ባንራራቅም በአካል ግን ልንለያይ ነውና ዳግም እግዚአብሔር ፈቅዶ እስክንገናኝ "ሰላም ሁኑ" እንባባል! የሚኖሩን መርሃግብሮች 🔘መዝሙር 🔘ትምህርት ና 🔘የምስጋና መርሐግብር 🗓 ቅዳሜ ሰኔ 22 2016ዓ/ም 📍ደብረ ኢየሱስ ቤ/ክ አዳራሽ ⏰11:30 @referal_gibi      @referal_gibi @referal_gibi       @referal_gibi
Mostrar todo...
4
Photo unavailableShow in Telegram
🙏እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
#አመቤቴ_ሆይ ከልጅሽ ሌላ ባለመድኃኒት አልሻም፣ ከጸሎትሽም ረዳትነት በቀር ደግሞ ኃጠአቴን የሚያስተሠራይልኝ አልፈልግም። ንጽሕት ሆይ ከርኩሰቴም ከዕዳ በደሌም ሁሉ ንጽሕ አድርጊኝ፨ ከሥጋና ከነፍስም ቁስሌም ፈውሽን። ለደዌ መድኃኒት ይሹለታል ለቁስልም አቃቂር መልካሙን ቅመም ይፈልጉለታል የኃጠአት ቁስል ግን ያለ ልጅሽ ፈቃድ አይጠገንም። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
✨የእመቤታችን ዝክር ኑ አብረን እንዘክር ሳምንታዊው_የአንድነት_ጸሎታችን_ እንደተጠበቀ ነው 🗓 ቀን : ዘወትር አርብ ⏰ ሰዓት ፡ ከ11:40 📍 ቦታ: ደ/ኢየሱስ ወቅ/አርሴማ ቤተክርስቲያን ሪ/ግ/ግ/ጉ/ አዳራሽ
Mostrar todo...
👍 2
ሰኔ 21 ለሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። 👉 ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል። የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው። ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ። ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የነሶሎሞን ቤተ መቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር። ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን ታላቁ ነብይ ኤልሳዕ አረፈ። ይህ ነብይ በ 12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነብዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርቢኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል። የእምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነብይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት ላይ በስፋት ተጽፏል ሰኔ 20 ቀን እረፍቱ ነው ቤተክርስቲያን የዛሬውን ቀን እመቤታችንን እና ነብዩን አስባ ትውላለች። ከበዓሉ ያሳትፈን የእመቤታችን ምልጃና ረዳትነት አይለየን!
Mostrar todo...
🙏 2👍 1
ምን ? የፈጣሪ ያለህ ! እስካሁን ሰምታችሁት የማታውቁትን ልብ የሚያሞቅ መረጃ ልነግራችሁ ነውና እንኳን ደስ ያላችሁ ! ደግሜ እላለሁ እንኳን ደስ አላችሁ ! ለበርካታ ዓመታት በሞቀ ጎጆዋ እቅፍ ድግፍ አድርጋ ከጸላኤ ሰናይ ወጥመድ ሰውራ ብዙ ልጆቿን ለፍሬ ያበቃች እመ ኵሉ አርድእት የምንላት ስሟን ጠርተን የማንጠግባት እንኳን በጉያሽ ኖርኩ የምንላት ሞገሳችን እናታችን ግቢ ጉባኤ በYouTube መጣች ! የእናታችን ናፍቆት ያንገበገበን የፍቅሯን እሸት ባለንበት ልንቀምስ ነውና ተደሰቱ ! " የሕይወቴ መስታወት " " የተማሪዎች ገዳም " እያሉ የፍቅሯን ጥግ የሚገልጹበት ቋንቋ ቢያጡ የሚቀኙላት በአንች መኖር መልካም ነው የሚሏት ግቢ ጉባኤ ከመላው ጓዳዋ ረኀበ ነፍሳችንን ልታጠፋልን እነሆ ወደ እኛ መጣች ! የ YouTube ገጹን ቢያንስ 20 ሰው ( ተማሪ ያልሆነ ) subscribe እናስደርግ ! # Like , # Share አድርጉ ሳትባሉ ስለምታደርጉ አሁን አንጽፍም ! ይኸው እናታችሁ ቤት ግቡ 👇👇👇 https://www.youtube.com/@06refferal https://www.youtube.com/@06refferal ይኸን መልእክት Share አለማድረግ ንፉግነት ነው ✊
Mostrar todo...
5👏 1
ምን ? የፈጣሪ ያለህ ! እስካሁን ሰምታችሁት የማታውቁትን ልብ የሚያሞቅ መረጃ ልነግራችሁ ነውና እንኳን ደስ ያላችሁ ! ደግሜ እላለሁ እንኳን ደስ አላችሁ ! ለበርካታ ዓመታት በሞቀ ጎጆዋ እቅፍ ድግፍ አድርጋ ከጸላኤ ሰናይ ወጥመድ ሰውራ ብዙ ልጆቿን ለፍሬ ያበቃች እመ ኵሉ አርድእት የምንላት ስሟን ጠርተን የማንጠግባት እንኳን በጉያሽ ኖርኩ የምንላት ሞገሳችን እናታችን ግቢ ጉባኤ በYouTube መጣች ! የእናታችን ናፍቆት ያንገበገበን የፍቅሯን እሸት ባለንበት ልንቀምስ ነውና ተደሰቱ ! " የሕይወቴ መስታወት " " የተማሪዎች ገዳም " እያሉ የፍቅሯን ጥግ የሚገልጹበት ቋንቋ ቢያጡ የሚቀኙላት በአንች መኖር መልካም ነው የሚሏት ግቢ ጉባኤ ከመላው ጓዳዋ ረኀበ ነፍሳችንን ልታጠፋልን እነሆ ወደ እኛ መጣች ! የ YouTube ገጹን ቢያንስ 20 ሰው ( ተማሪ ያልሆነ ) subscribe እናስደርግ ! # Like , # Share አድርጉ ሳትባሉ ስለምታደርጉ አሁን አንጽፍም ! ይኸው እናታችሁ ቤት ግቡ 👇👇👇 https://www.youtube.com/@06refferal https://www.youtube.com/@06refferal ይኸን መልእክት Share አለማድረግ ንፉግነት ነው ✊
Mostrar todo...
4
🔔በሰመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ  አሐዱ አምላክ አሜን! ለ 2016 የ pharmacy እና anesthesia ተመራቂ ተማሪዎች ስልጠና ተዘጋጀ! አምላክ ሰማይ ወምድር ልዑል አግዚአብሔር ፈቃዱ ቢሆን በዚ ዓመት ለሚመረቁ ተማሪዎች በተዘጋጀው በዚህ ህይወት ከምረቃ በኋላ ስልጠና:- 📌  ቤተ ክርስቲያን ከምሩቃን ምን ትጠብቃለች 📌ወጣትነትና ፆታዊ ጉዳዮች 📌ኦርቶዶክሳዊነትና ዘመናችን 📌ኦርቶዶክሳዊ የ ህይወት መርህ እና አላማ   ያለው ሰው ጉዞ የተካተቱ ሲሆን 📆ቀን 20 ና 21/10/2016 ሐሙስ ና አርብ ⏰ሰዓት :ጠዋት 2:30 -5:00 እንዲሁም ከሰዓት 8:00 -10:00 🪧ቦታ : ቤተ - አብረሃም https://t.me/referal_gibi https://t.me/referal_gibi
Mostrar todo...
👍 7
🟢🟡🔴 የመንፈስቅዱስ መውረድና ልሳን ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚች ምድር ላይ በሚያስተምርበት ጊዜ ለመረጣቸው ደቀመዛሙርቱ ብዙ ነገሮችን አስተምሯቸው ብዙ ምሥጢሮችንም ገልጦላቸዋል። እነሱም የእርሱን አምላክነት፣ የእርሱን የእግዚአብሔር ልጅነት ፣ የእርሱን ፈዋሽነት፣ የእርሱን አዳኝነት አምነው ለአመታት ከእርሱ ጋር ኖረዋል እርሱ ለሰው ልጆች ድኅነት ሲል በመስቀል ተሰቅሎ ሞቶ ተቀብሮና  ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ ግን ደቀመዛሙርቱ በእምነታቸው ያላደጉ ስለነበሩ ሰውን ማጥመዳቸውንና ስለመምህራቸው መመስከርን ትተው ወደ ቀደመ ሥራቸው ተመልሰው ነበር። 🟢ሐዋርያት 1÷5-8 ላይ እንደ ተገለፀው ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ በተለያዩ ቦታዎችና ሁኔታዎች ለአርባ ቀናት እየታያቸውና ስለመንግስተሰማያት እያስተማራቸው ቆይቷል በዚህም ቆይታው  “ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኃላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ።” 🟡እንዲሁም ለእስራኤል መንግስትን ስለሚመልስበት ወራት በጠየቁት ጊዜ " አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።"  🔴ከሞቱም አስቀድሞ ደግሞ በዮሐ 16 ላይ "የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም። ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።" ብሎ ቃል ገብቶላቸው ነበርና 🟢ባረገ በአስረኛው በተነሳ ደግሞ በሃምሳኛው ቀን
"ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው። እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው። በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።"(ሐዋ 2፥1—4)
በዛች ዕለት ሐዋርያት የመንፈስቅዱስ መውረድን ተከትሎ ብዙ ፀጋዎችን አግኝተዋል 💨መነፈስ ቅዱስ አፅናኝ ነውና አፅናንቷቸዋል 🔥መንፈስቅዱስ የሚያፀና ነውና ጎዶሎ እምነታቸውን ሙሉ አድርጎ በተቀበሉት መንገድ አፅንቷቸዋል 💨መንፈስ ቅዱስ የሚያስጨክን ነውና በአለምና በሥጋቸው ጨክነው ስለክርስቶስ እንዲመሰክሩ አድርጓቸዋል 🔥መንፈስቅዱስ እውቀትን የሚገልጥ ነውና የሚናገሩትንና የሚፅፉት ሁሉ ገልጦላቸዋል። ከላይ ያየናቸውንና የበለጠውን ሁሉ ፀጋ ተቀብለው ሳሉ  በዕለቱ ግን መንፈስቅዱስ ለመቀበላቸው ትልቁ ምልክት በልሳን መናገራቸው ነበር። ይህንንም ተከትሎ በዘመናችን የሚገኙ የእምነት ተቋማት መናፍቃን አንዳንዶች መንፈስቅዱስ በሚለው ሰበብ እርኩሳን መናፍስት አጋንንትን እየጠሩ ሌሎችም ደግሞ ከህዝቡ ተቀባይነትን ለማግኘትና ህዝቡን ለማጭበርበር በመለማመድ በማነኛውም ቋንቋ ትርጉም የሌላቸውና በሥርዓት ያልተሰደሩ ድምፆችን እንደ እብድ በመንቀጥቀጥ በመንዘፍዘፍና አእምሯቸውን በመለወጥ ሲያነበንቡ ይታያሉ፤ ይህም ተግባር ፈፅሞ የተሳሳተና መፅሐፍቅዱስንና በውስጡም የሚገኙ ኀይለ ቃላት ካለመረዳት የተነሳ የተፈጠረ መወናበድ ነው። ለዚህም ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል።  🟡 የመጀመርያው ማስረጃችን የቃሉ ትርጉም ነው። ልሳን የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም  ቋንቋ ወይም አንደበት ማለት ነው እንጂ በሥርዓት ያልተሰደሩ ድምፆች ስብስብ ማለት አይደለም። 🪽ሌላውና ዋነኛው ማስረጃችን ሐዋርያት በበዓለ ሃምሳ ወይም በበዓለ ጰራቅሊጦስ የተናገሩት ልሳን ምን አይነት ነው የሚለው ነው። ለዚህም በ ሐዋ ሥራ 1: 5-11 ድረስ ባለው ኀይለቃል ውስጥ ብዙ ነገሮችን ማለት ይቻላል በጥቂቱ ግን የሚከተሉትን እንመልከት
❤️እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ።(ሐዋ 2፥6)
❤ እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን?(ሐዋ 2፥8)
❤ በወቅቱ የነበሩት ሰዎች ቋንቋዎች አንድ በአንድ መጠቀሳቸው።(ሐዋ 2፥9—11)
በዚህም መሠረት በበዓለ ሃምሳ ሐዋርያት የተናገሩት ልሳን የተለያዩ ሰዎች የሚግባቡበት ቋንቋ እንደሆነ እርግጥ ነው። 🔴
ሐዋ 10 " ከጴጥሮስም ጋር የመጡት ሁሉ ከተገረዙት ወገን የሆኑ ምዕመናን በአሕዛብ ላይ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ስለ ፈሰሰ ተገረሙ፤ በልሳኖች ሲናገሩ እግዚአብሔርንም ሲያከብሩ ሰምተዋቸዋልና። በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ፦ እነዚህ እንደ እኛ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ እንዳይጠመቁ ውኃን ይከለክላቸው ዘንድ የሚችል ማን ነው? አለ።"
ይህ ደግሞ አህዛብ በነበሩትና በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ከተጠመቁ በኋላ መንፈስቅዱስ ስለወረደላቸውና በልሳን ስለተናገሩት ቆርኔሌዎስና ቤተሰቦች የሚናገር ክፍል ሲሆን የእነርሱም እንደ ሐዋርያቱ እንደነበረ በቅዱስ ጴጥሮስ " እነዚህ እንደ እኛ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ..." በሚለው ቃል ማረጋገጥ ይቻላል። #⃣በዚህ እንዳልተሳካላቸው የተረዱት መንፈስ ጠሪዎቹና አጭበርባሪዎቹ የሚያነበንቡት ትርጉም አልባ ድምፅ ከዕለተ ጰራቅሊጦሱ የተለየ የመላዕክት ቋንቋ እንደሆነ በድፍረት ሲናገሩ እንሰማቸዋለን ። ለዚህ ስህተታቸው ደግሞ  “በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ...” የሚለውን የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ያነሳሉ። 👉በመጀመርያ ሐዋርያቱ ያልተገለጠላቸውና ከነሱም በኋላ የተነሱ ታላላቅ አባቶች ያልተናገሩት የመላእክት ቋንቋ  መቶ አመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ለተነሱና ሥራቸው ሁሉ ምድራዊ ለሆነ ሰዎች እንዴት ይገለጣል አንዴትስ ሆኖ ይታደላል??? 👉 ሁለተኛውና ዋነኛው መላዕክት በሰው እንዲህ ነው ተብሎ የሚነገር ቋንቋ የላቸውም። ታድያ ቅዱስ ጳውሎስ ለምን በመላእክት ልሳን አለ ቢሉ እግዚአብሔርን በሚጠሩበት እግዚአብሔርን በሚያመሰግኑበት ያማረ የተዋበ ልሳን ማለቱ ነው እንጂ  እያሉ ሊቃውንቱ ያሰረዳሉ። ለዚህ ደሞ ማስረጃችን መላእክት በሚገለጡበት ሁሉ የሚናገሩት በሰው ቋንቋ ነው ። ለምሳሌ : *ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንንና ዘካርያስን ሲያበስር የተናገረው በራሳቸው ቋንቋ ነው እንጂ በሌላ አይደለም በጣም የሚገርመው መላእክት ብቻ ሳይሆኑ እግዚአብሔርም ለነ ሙሴ ለነ አብርሐም ለነ ኖህ በሚገለጥበት ጊዜ የሚያናግራቸው በራሳቸው ቋንቋ ነበር ይልቁንም በ ሐዋ ሥራ  26 ላይ “ሁላችንም በምድር ላይ በወደቅን ጊዜ፦ ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል የሚል ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲናገረኝ ሰማሁ።” ብሎ ቅዱስ ጳውሎስ ሲናገር ኢየሱስ ክርስቶስ  የተናገረው በዕብራይስጥ ቋንቋ እንደ ነበር ግልፅ ተደርጎ ተቀምጧል። ምናልባት በ1ኛ ቆሮንቶስ 14 ላይ የተገለፀው እንደኛ ያለውን ልሳን ነው እንዳይሉ ከሚከተለው ኀይለ ቃል  3 ነገሮችን እንመልከት። ይቀጥለል... https://t.me/referal_gibi https://t.me/referal_gibi
Mostrar todo...
#አዲስ_መረጃ #የካፌ_ሰዓት እንደሚታወቀው የግቢያችን ካፌ ምግብ ማውጣት እንደማይቻል ከቀናት በፊት አሳውቋል ነገር ግን እኛ ኦርቶዶክሳውያን የሰኔ ፆምን ከሰኔ 17 እስከ ሐምሌ 5 ቀን ድረስ እንፆማለን እናም በመደበኛ የምሳ ሰዓት(6:00) ላይ ካፌ ገብተን መመገብ ስለማንችል ምሳችንን 9:00 እራታችንን ደግሞ ከ12:30 -1:00 እንድንመገብ ስለተፈቀደ በተባለው ሰዓት ሁላችንም እየመጣን እንድንስተናገድ ይሁን! ፆሙንም የነፍስ ዋጋ የምናገኝበት ያድርግልን! 📌ምሳ 9:00-9:30 📌ራት 12:30-1:00
Mostrar todo...
🙏 5👍 4👏 2
"አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው" መዝ 46 ፥1
ሐዋርያት የሰበሰቧት ቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች፣ በመንፈስ ቅዱስ አንድ የሆነን ወንድሞቼ፣ እህቶቼ ነገ መውጫ ፈተና ተፈታኞች ግቢ ጉባኤያችን መልካም ፈተና እንዲሆን ትመኝላችኅለች ውድ ቤተሰቦቻችን ጥበብ እና ዕውቀትን ለቅዱሳን የገለጸ አምላከ ቅዱሳን ለእናንተም ገልጾላችሁ መልካም ውጤት እንድታገኙ እግዚአብሔር አምላክ ይፍቀድላችሁ። ሁሌም በጨነቀን ጊዜ ከጎናችን የማትጠፋ እናታችሁ እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረድኤቷ ከጎናችሁ አትለይ በውጤታችሁ ታስደስታችሁ Pharmacy፣ medicine እና anesthesia ተፈታኞች በሙሉ መልካም ዕድል ይግጠማችሁ ✨እግዚአብሔር አምላክ ከሁላችን ጋር ይሁን።
Mostrar todo...
13👍 1
" ዘወጠነ : ወዘተግሀ : ወዘደክመ : ወዘጸና : ይፌጽም " የጀመረ : የተጋ : የደከመ እና የጸና ይጨርሳል ።
ገና በልጅነት አፍ ባልፈታ አንደበት ረጅሙን የትምህርት ፍኖት ' ሀ ፣ሁ ....ሆ ' ብላችሁ ጀመራችሁ ። ከፊደላት እስከ ውስብስብ የዓለም ጥበብ መማርን በትጋት ቀጠላችሁ ። በዚህ ሁሉ ውጣውረድ ነገን እያሰባችሁ በድካማችሁ ጸናችሁ ። አሁን ተራው አነሆ የመጨረስ ነው ! ነቢየ እግዚአብሔር ክቡደ መዝራዕት ሙሴ ሕዝበ እስራኤልን ከዘመናት ባርነት ነጻ ሊያወጣ ከምድረ ግብፅ ወደ ተስፋዋ ምድር ከንዓን ሲጓዙ ባሕረ ኤርትራ ላይ ደረሱ ፤ በዚህን ጊዜ እስራኤላውያን የባሕር ሲሳይ ሊያደርገን ነው ያመጣን ብለው ከግብፅ ነጻ ያወጣቸውን እግዚአብሔር ጠረጠሩትና አንጎራጎሩ ፤ የባሕሩ ጌታ በኃይሉ አሻገራቸው ። የጠቢብ ዓይኖቹ በራሱ ላይ ናቸው እንዲል ወደ እኛ እናምጣውና ከብዙ ፈተናዎች እግዚአብሔር ጠብቆ አሳልፏችኋል ፤እስኪ አስቡት ከዚህ ለመድረስ ስንት ፈተናዎችን ተፈተናችሁ? ቁጥሩን እንኳ የምታውቁት አይመስለኝም ።እነዚህን ፈተናዎች ያለፋችሁት በራሳችሁ ኃይል ነውን? አይደለም በመድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ቸርነት እንጅ ። ስለዚህ እነዚህን ሁሉ ፈተናዎች ያሳለፋችሁ እግዚአብሔር የቀረችውን አንድ ፈተናም ሊያሳልፋችሁ የታመነ ነው ። እንደ እስራኤላውያን ከሀሊነቱን አትጠራጠሩት ። ይህን የፈተና ባሕር በጸናች ክንዱ ከፍሎ ያሻግራችኋል ። " እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?” ሮሜ 8፥31 ስለዚህ የጀመረ : የተጋ : የደከመ እና የጸና ይጨርሳል ። የመውጫ ፈተና | EXIT EXAM | የምትፈተኑ የግቢ ጉባኤኣችን # Doctors , # Pharmacists & # Anesthetists በፍጻሜአችሁ እግዚአብሔር ይረዳችሁ ዘንድ ልመናችን ነው ። ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ የምንላት መዝገበ በረከት ቅድስት ድንግል ማርያም በውጤት በረከት ትጎብኛችሁ ። 14 | 10 | 2016
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.