cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵 🇪🇹ኢትዮጵያ አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ ቤተሰብ ይሁኑ Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵 @Daily_News_Ethiopian አስተያየትና መልክት ካሎት @Natty19 ምርትና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን @Natty19

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
8 385
Suscriptores
-724 horas
-337 días
-15230 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ከ2 ዓመት በላይ በእስር ላይ የነበሩት አቶ ታዲዎስ ታንቱ ትናንት መፈታታቸው ታውቋል።
Mostrar todo...
👍 4
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ግንቦት ፳፩ ቀን ፳፱፲ወ፮ ዓ/ም ባደረገው የጠዋቱ የግንቦት ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት ሰየመ። በዚሁም መሰረት በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት የተሰየሙት ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሕገ ቤተ ክርስቲያን በሚያዘው መሰረት ከቋሚ ሲኖዶስ ለምልአተ ጉባኤ እንዲቀርቡ የተመሩ እና ተጨማሪ የሚባሉ አጀንዳዎችን በመቅረጽ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የማስጸደቅ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴነት የተመረጡት አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚከተሉት ናቸው። 1.ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ 2.ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ 3.ብፁዕ አቡነ ማርቆስ 4. ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ 5. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል 6. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ 7. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ኢኦቴቤ ሕዝብ ግንኙነት
Mostrar todo...
👍 10🙏 2
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! - ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሰሜን ጎጃምና የባሕር ዳር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ - ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት! እግዚአብሔር አምላካችን በቤተ ክርስቲያን ላይ በየጊዜው የሚደርሰውን ፈተና በማስቻል ለዚህ ሲኖዶሳዊ ምልአተ ጉባኤ እንኳን በሰላም አደረሰን! ‹‹አስተብቊዓክሙ አኃዊነ በስሙ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትበሉ ኵልክሙ አሐደ ቃለ ወአሐደ ነገረ ወትኩኑ ፍጹማነ ወኢትትፋለጡ ወሀልዉ በአሐዱ ምክር ወበአሐዱ ልብ፤ ወንድሞች ሆይ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ፣ በአንድ ልብና በአንድ ሐሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ›› (፩ቆሮ ፩፥፲)፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን መልእክት ለቆሮንቶስ ሰዎች ለመጻፍ ሲያስብ አንድ ዓቢይ ምክንያት እንዳለው ከመልእክቱ ይዘት መረዳት ይቻላል፤ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች አንድነትንና ሰላምን ፍቅርንና መተባበርን ከምትሰብከው ወንጌለ መንግሥተ እግዚአብሔር ወጥተው ብዙ ርቀት ሂደዋል፤ አንድነቱ፣ ኅብረቱ መረዳዳቱ መተጋገዙና መተባበሩ ከመካከላቸው ጠፍቶአል፤ ሌላው ቀርቶ ቅዱስ ቊርባንን ለመቀበል በሚሰበሰቡበት ጊዜ እንኳ የሀብታምና የድሀ የሚል ክፍፍል ተፈጥሮ ቤተ ክርስቲያኗን አደጋ ላይ ጥሎአል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን እና ይህንን የመሳሰለ ፈተና በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ሥር እየሰደደ መምጣቱን በእጅጉ አሳስቦታል፤ ይህ የሰላምና የአንድነት ጠንቅ የሆነው የመለያየት አዝማሚያ በጣም ሰፍቶ ቤተ ክርስቲያንን ከማፍረሱ በፊት በትምህርት በምክርና በተግሣጽ ማረም እንዳለበት ቅዱስ ጳውሎስ ተገንዝቦአል፤ እሱ ራሱም በአካል በመካከላቸው ተገኝቶ ሊያስተካክላቸው ፈቃደኛ ነበረ፤ ነገር ግን እሱ በዚህ ጊዜ በሮም ውስጥ እስር ቤት ላይ ስለነበረ አልቻለም፤ የነበረው አማራጭ በጽሑፍ ማስተማርና መምከር ነውና፤ ይህንን መልእክት ጽፎላቸዋል፡፡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት! ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዘላቂው የቤተ ክርስቲያን ፈተና ሲነግረን ‹‹ወበዓለምሰ ሀለወክሙ ትርከቡ ሕማመ፤ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ›› እንዳለው ቤተ ክርስቲያን ከፈተና ተለይታ አታውቅም፤ ፈተናውም ከተወሰነ አቅጣጫ ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ከብዙ አቅጣጫ ይከባታል፤ የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻም አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ፣ የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው፤ ባዕዳውያን አይሁድ ጌታን ይዘው የገደሉ የውስጥ ሰው የሆነው ይሁዳ በሰጣቸው ምልክት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች፤ እንደተነገረው የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት ሆነውባታል፤ ከጥንት ጀምሮ የነበረ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ፣ የጸሊአ ሢመትና የጸሊአ ንዋይ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩም ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል፣ ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጐደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ተሰሚነትና ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው፡፡ እነዚህና እነዚህ የመሳሰሉ ክሥተቶች በውስጣችን ሥር በሰደዱ ቁጥር ጉዳትን እያስከተሉ ነው፤ ሰዎች ከኦርቶዶክሳዊ ቀኖና እና ሥርዓት ባፈነገጠ መልኩ ራስን በራስ የመሾም አባዜ እየተለማመዱ ነው፤ እሽቅድምድሙም በዚህ ዙሪያ አይሎአል፤ በአጠቃላይ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችን የፈተነ መለያየት በቤተ ክርስቲያናችንም ብቅ ጥልቅ እያለ እየፈተነን ነው፤ የፈተናው መንሥኤ ውጫዊ ሳንካ ባይጠፋበትም የውስጣችን ሰዎች ለሱ ምቹ ሆነው መገኘታቸው አልቀረም፤ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ፈተና የማይናቅ ጉዳት እየደረሰባት ነው፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ሰላምዋና አንድነቷ ጥያቄ ላይ ወድቆአል፡፡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት! በሀብተ መንፈስ ቅዱስ ወልደን፣ በሀብተ ክህነት ሹመን፣ በመዐርገ ምንኩስና አልቀን በቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት ያስቀመጥናቸው ሰዎች በውኑ ‹‹እርስ በርስዋ የምትለያይ ቤት… የሚለውን አምላካዊ አስተምህሮ እንዴት ዘነጉት? ወይስ ድሮውንም ሳያውቁት ነው ኃላፊነቱ የተሰጣቸው? ወይስ ደግሞ ሆን ብለው ቃሉን ቸል ብለውታል? ሁሉም ውሉደ ክህነት ለዚህ መልስ መስጠት ይጠበቅበታል፤ በመልካም አስተዳደርና በቂም በቀል እያሳበቡ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ብሎም ለማፍረስ መሮጥ በማናቸውም መመዘኛ ሚዛን አይደፋም፤ ውሃም አያነሣም፡፡ ችግር ሲኖር በመወያየት በጥበብና በሕግ ማረም እንጂ የጋራ ችግርን ለተወሰነ አካል በመለጠፍና እሱን ብቻ ተጠያቂ በማድረግ ንጹህ መሆን አይቻልም፤ ሁሉም ጓዳው ቢፈተሽ ከዚህ የተለየ ነገር አይገኝም፤ አንድነትንና ሰላምን ግቡ ያደረገ ግምገማን መገምገም፣ መወያየትና መመካከር፣ ሕግንና ሥርዓትን ማእከል አድርጎ መሥራት ተመራጭ መፍትሔ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ባለፉት ዓመታት አስከፊ በደል ተፈጽሞአል አሁንም አልቆመም፤ ይሁን እንጂ በደል ዛሬ ብቻ የተጀመረ አድርገን አናስብ፤ ይብዛም ይነስ በደል ፊትም ነበረ፤ ዛሬም አለ፤ ነገም የተለየ ነገር ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በደልን በካሣና በዕርቅ በይቅርታና በምሕረት መዝጋት፣ ተመሳሳይ በደል እንዳይፈጸም አስተማማኝ የሆነ ተቅዋማዊ ሥርዓትን ማበጀት መልካም ፈሊጥ ይሆናል፤ በደልንና ጥፋትን ምክንያት አድርገን እስከ ዘለቄታው መለያየትን መምረጥ ግን ራስን በራስ መጉዳት ይሆናል፤ ስለዚህ ይህ ቅዱስ ጉባኤ በዚህ ዙሪያ በስፋትና በጥልቀት በመወያየት ሁሉንም ሊያስማማ በሚችል መልኩ ወደ ሰላምና ዕርቅ ሊያደርስ የሚችል ስራ መስራት ይኖርበታል፡፡ ብፀዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖስ አባላት! የማኅበረ ሰባችን ችግር በቤተ ክርስቲያን ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ በሀገር ደረጃ እየቀጠለ ያለው አለመግባባትም ለጠቅላላ ማኅበረ ሰባችን ፈተና ከሆነ ውሎ አድሮአል፤ የቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ምንጭ ከሆኑትም አንዱና ዕድል ሰጩ ይህ ሀገራዊ አለመግባባት ነው፤ በዚህ አለመግባባት ምክንያት ገዳማውያን መነኮሳት፤ መምህራን ካህናት ምእመናን አብያተ ክርስቲያናት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ በሰላም ወጥቶ መግባትም አጠራጣሪ ሆኖአል፤ ይህንን ችግር ለመፍታት የሚደረግ ጥረትም ጎልቶ አይታይም፡፡ በመሆኑም ይህ ክሥተት እውን ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ችግር በራሳችን መፍታት የማንችል ሰዎች ነን ወይ? ለኛስ ከኛ የበለጠ ማን ይመጣልናል? የሚለውን ጥያቄ ልናነሣ ግድ ነው፤ ስለዚህ ለሀገር ህልውናና ድኅነት የሚበጅ ነገር እንዲመጣ ቤተ ክርስቲያን ባላት ሃይማኖታዊና ሰብአዊ ኃላፊነት ጠንክራ መስራት ይጠበቅባታል፤ ከዚህ በተረፈ ይህ ዓቢይ ጉባኤ ወሳኝና ወቅታዊ እንዲሁም ሐዋርያዊና ቀኖናዊ በሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር የሚበጁ ነገሮችን በማየት ጠቃሚ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፍ በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
Mostrar todo...
👍 2 1
በመጨረሻም ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በእግዚአብሔር ፈቃድ የተጀመረ መሆኑን በመንፈስ ቅዱስ ስም እናበስራለን ፡፡ መልካም ጉባኤ ያደርግልን! እግዚአብሔር አምላካችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን፡፡ አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ግንቦት ፳፩ ቀን !፻0፮ ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
Mostrar todo...
🙏 5
Photo unavailableShow in Telegram
#Amhara ኢሰመኮ፦ - ከየካቲት 15 እስከ 28 ቀን 2016 ዓ/ም በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ደጋ ዳሞት ወረዳ (ዝቋላ ወገም፣ ፈረስ ቤት01፣ ገሳግስና ጉድባ ሰቀላ ቀበሌዎች) እና ሰከላ (አጉት፣ ጉንድልና አምቢሲ ቀበሌዎች እና ግሼ ዓባይ ከተማ) በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በታጣቂዎች መካከል የተካሄዱ የትጥቅ ግጭቶችን ተከትሎ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት፣ አካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ደርሷል። - የካቲት 20/2016 በሰሜን ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ ብራቃት ቀበሌ በሚገኘው የጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የአብነት ተማሪዎች የዕለቱን ትምህርትና ጉባኤ ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ አጠናቀው ወደ ማደሪያ ጎጇቸው ከገቡ በኋላ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አባላት ከሌሊቱ 6፡30 ሰዓት ገደማ ላይ ወደ ቦታው ደርሰው ተማሪዎችን “ #ውጡ ” እያሉ ተኩስ በመክፈት ቀድመው በወጡ #በ11_ተማሪዎች ላይ ግድያ እንደፈጸሙ፤ ሌሎች 8 ተማሪዎችንም ደግሞ በቁጥጥር ሥር አውለው ካሳደሩ በኋላ በማግስቱ ምንም ጥፋት የለባችሁም ብለው እንደለቀቋቸው ኢሰመኮ ለመረዳት ችሏል። በወቅቱ በአቅራቢያው የሚንቀሳቀስ የታጠቀ ኃይል እንዳልነበር ምስክሮች አስረድተዋል። - መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ/ም በኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን የተነሱ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር #በኤፍራታና_ግድም እና #ቀወት ወረዳዎች በሚገኙ የተወሰኑ ቀበሌዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት በሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን፣ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ ንብረት መውደሙን፣ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን እና የቀንድ ከብቶችና ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች መዘረፋቸውን ኢሰመኮ ተረድቷል። - መጋቢት 6 ቀን 2016 በአማራ ክልል፣ በባሕር ዳር ከተማ ዘንዘልማ አካባቢ አቶ ብርሃኑ ሽባባው አካል ፣ አቶ በላይ አካል እና አቶ ተሾመ ይበልጣል የተባሉ ነዋሪዎች አንዱ በሚሠራበት ሱቅ እና ሁለቱ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ " ኑ ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ " በሚል በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ መጋቢት 7 ቀን 2016 በባሕር ዳር ቀበሌ 14 በተለምዶ ጉዶ ባሕር አካባቢ #የፊጥኝ_እንደታሰሩ በጥይት ተገድለው ተገኝተዋል። - በባሕር ዳር ዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ ጋጃ መስክ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ መጋቢት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት በተፈጸመ ጥቃት ሶላት ስግደት አከናውነው ወደ ቤታቸው እየተመለሱ የነበሩ የእስልምና ተከታይ 5 ሰዎች (4ቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ) ተገድለዋል። - ሚያዝያ 7/2016 ከጧቱ 3፡00 ሰዓት ላይ በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ አጎና ቀበሌ ላይ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከእስቴ ወረዳ ወደ ላይ ጋይንት ወረዳ በመጓዝ ላይ እያሉ በአካባቢው ላይ በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች (#ፋኖ ) ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ታጣቂዎቹ አካባቢውን ጥለው እንደሸሹ #የመንግሥት_የጸጥታ_ኃይሎች ወደ ቦታው በመግባት 7 (1 ሴትና 6 ወንዶች) ሲቪል ሰዎች ላይ ከሕግ ውጪ ግድያ ፈጽመዋል። ከ15 በላይ የሚሆኑ የቆርቆሮ ክዳን ያላቸው መኖሪያ ቤቶች እና 3 የገለባ ቤቶችና ንብረት መቃጠላቸውን እንዲሁም ከ100 በላይ የሚሆኑ የቀበሌው ነዋሪዎች ወደ ሌላ አካባቢ የተፈናቀሉ መሆኑን የቀበሌው ነዋሪዎች እና ተጎጂዎች ገልጸዋል። - ግንቦት 4/2016 ዓ/ም ከቀኑ ከ7፡00 ሰዓት አካባቢ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ተሬ ቀበሌ ውስጥ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በጉሎ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ግቢ ውስጥ 2 ሲቪል ሰዎች ሲገደሉ አንድ ሴት መምህርትን ጨምሮ ሌሎች 9 ሲቪል ሰዎች የቆሰሉ መሆኑን ኢሰመኮ ተረድቷል። #Amhara #EHRC
Mostrar todo...
👍 7 1
ታጣቂ ኃይሎችን አግኝቶ ለማናገር ሙከራ መጀመሩን ምክክር ኮሚሽኑ ገለጸ ዋናው ሀገራዊ ምክክር የሚጀመርበት ቀን አለመቆረጡን ኮሚሽኑ ገልጿል። ለዘመናት የተሻገሩ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ የህዝብ ጥያቄዎችን በምክክር እፈታለሁ ያለችው ኢትዮጵያ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አቋቋማ እየንቀሳቀሰች ነው፡፡ ምክክሩ በህዝቦች እና በፖለቲካ ተዋናያን መካከከል ለንትርክ እና ልዩነት መሰረት የሆኑ አብይት አጀንዳዎች ላይ ተመካክሮ መፍትሄን ለማስቀመጥ አለማውን አድርጓል፡፡ ከተቋቋመ ሁለት አመታትን የተሻገረው ኮሚሽኑ በመጣባቸው መንገዶች ነገሮች አልጋ በአልጋ አልነበሩም፡፡ ኮሚሽኑ የአካታችነት እና የገለልተኝነት ጥያቄዎች ይቀርቡበታል። በግጭቱ ውስጥ ያሉ የታጠቁ ኃይሎች መሳተፋቸው አለመረጋገጡ እና በሀገሪቱ በተለያዩ ማዕዘናት ያሉ ግጭቶች በምክክሩ ውጤታማነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራሉ የሚሉ ስጋቶችን በቡዙዎች ዘንድ ተፈጥረዋል። ይህ ቢሆንም ኮሚሽኑ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተንቀሳቅሶ የተሳታፊ ልየታ አጀንዳ የመሳባሰብ እና የስልጠና ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ሲገልጽ ቆይቷል፡፡ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ የሀገሪቷ ወቅታዊ የሰላም ሁኔታ ምክክሩ በታሰበው ፍጥነት እንዳይጓዝ ቢያደርጉም ግጭት በሌለባቸው ክልሎች የተሳታፊዎች ልየታ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል። ነገርግን አቶ ጥበቡ እንዳሉት ኮሚሽኑ ግጭት ባለባቸው የኦሮሚያ ዞኖች እና የአማራ ክልል እንዲሁም በትግራይ ክልል ቀሪ ስራዎች አሉት። ከሁለት አመታት ጦርነት መልስ በሚገኝው የትግራይ ክልል ነባራዊ ሁኔታዎች በሚፈቅዱበት ጊዜ ወደ ተሳታፊ ልየታ እና ወደ ሌሎች ተግባራት ለመግባት ዝግጅቶች ተጠናቀዋል ብለዋል አቶ ጥበቡ። ቃል አየባዩ አሁን ባለው ሁኔታ በትግራይ እና አማራ ክልሎች የተሳታፊ ልየታዎች ገና አልተጀመረም ብለዋል። ታጣቂዎችን በሀገራዊ ምክክሩ የማሳተፍ ጉዳይ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የፍትሀዊ ተጠቃሚነት ጥያቄዎችን የሚያነሱ ታጣቂዎች ካልተሳተፉ ምክክሩ ውጤታማ አይሆንም የሚልም ስጋት ይደመጣል። ከየትኞቹ ታጣቂዎች ጋር ተነጋገራችሁ ምላሻቸውስ ምን ነበር? በሚል የጠየቅናቸው ቃል አቀባዩ ለሂደቱ ውጤታማነት በሚል ይፋ ከማድረግ ተቆጥበዋል፡፡ ጥሪ መደረጉን እና በምክክሩ ተሳታፊ እንዲሆኑም ሙከራዎች እንደቀጠሉ ናቸው የሚሉት አቶ ጥበቡ ወደፊት ውጤቱን አብረን እናያለን ብለዋል፡፡ ከነገ ግንቦት 21-27 በአዲስ አበባ የሚከናወነው የምክከር ምእራፍ ሶስት ዋና ዋነ ተግበራት የሚያከናወኑበት ነው። ከነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከከል ደግሞ እድሮች ፣ የመምህራን ማህበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የንግድ ማህበረሰብ ፣ የሀይማኖት ተቋማት፣ ተፈናቃዮች እና ሌሎችም እንደየፈርጃቸው ሀሳብ እንዲያዋጡ ለማድረግ ተሞክሯል ብለዋል ቃል አቀባዩ፡፡ ተሳታፊዎች በምክክርና በዉይይት የአጀንዳ ሀሳብ ይሰጣሉ፣ አጀንዳወችን የጋራ ማድረግ እና ማደራጀት እንዲሁም ለዋናዉ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮቻቸዉን መለየት እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡ በአዲስ አበባ በሚያደርገው የምክክር ምእራፍ  መድረክ ከ 2500 በላይ ተወካዮች እንደሚሳተፉበት የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም ኮሚሽኑ ተመሳሳይ መርሃ ግብሮችን በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እንደሚያከናዉን ነው የተነገረው፡፡ ዋናው ሀገራዊ ምክክር መቼ እንደሚጀመር የተጠየቁት አቶ ጥበቡ ሂደት በመሆኑ የተቆረጠለት ቀን የለም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። በሂደቱ ምክክር እንዲካሄድባቸው የሚቀረጹ አጀንዳዎች እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ማተኮር እንዳለባቸው፣ የአለመግባባት መንስዔዎችን በትክክል በሚዲስስ አጀንዳ የሚያተኩሩ እና ጥልቀትና አግባብነት ያላቸው መሆን እንዳለባቸው መርሆዎች ተቀምጠውለታል፡፡ ለተወሰነው ሰው አጀንዳ የሆኑ ጉዳዮች ለሌላው አጀንዳ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ አልፎ አልፎም ጉዳዮችን አይነኬ ለማድረግ የሚሞክሩ አመለካከቶችም አሉ፡፡ ኮሚሽኑ ነገ በመዲናዋ በሚጀምረው በቀጣይም በክልሎች በሚያከናውናቸው መድረኮች አጀንዳዎች ከተሰበሰቡ በኋላ ከላይ በተቀመጡት መስፈርቶች መሰረት ለምክክር እንደሚቀርቡ ይጠበቃል። አሜሪካን ጨምሮ በርካታ ሀገራት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የትጥቅ ግጭት እና ሌሎች ልዩነቶች በምክክር እና በንግግር እንዲፈቱ ጥሪ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።
Mostrar todo...
👍 4
በዚህ ሰአት ከቅድስተ ማሪያም ገዳም በቀጥታ የርክበ ካህናት ጉባኤ የመክፈቻ የፀሎት ፕሮግራም እየተደረገ ይገኛል https://www.youtube.com/live/d3WjSPUwJGU?si=EqUqJ0qmOWGoEbB0
Mostrar todo...
👍 1
በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ማን ዩናይትድ ከ አርሰናል የሚያረጉትን ጨዋታ በመጠባበቅ ላይ ናቸው።
Mostrar todo...
👍 3 3😱 1
👍 3
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.