cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ዳዕዋ ሠለፍያ በኢቅራ

ማስረጃ በዞረበት እንዞራለን ! ለአንድም አካል ወገንተኛ ፤ጠርዘኛ አንሆንም ፈፅሞ!!! Comment and Suggestion 👇👇👇👇👇 ይህ የቴሌግራም" ቻናል"የሚ•ቴ•ዩ የሚዛን ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎችን ያማከለ ሲሆን በውስጡም ኢስላማዊ ትምህርቶች፣ ሙሀደራዎች፣ፈትዋዎች፣መጣጥፎችና መሰል ጥቅም አዘል ፓምፕሌቶች ይለቀቁበታል። ኢንሻኣላህ በመልቀቁላይ ابو القاسم

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
176
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

♦️زكاة الفطر صاع من قوت البلد ♦️ዘካተል ፊጥር በሀገር ከተለመዱ ለቀለብ የሚውሉ የምግብ አይነቶች አንድ ሷዕ ይወጣል። 📌الحمد لله والصلاة والسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه ومن اهتدى بهداه، أما بعد: 📌ከብዙ ወንድምና እህቶች ዘካተል ፊጥርን በተመለከተ ጥያቄዎች ይሰነዘራሉ። ከነዚህም ጥያቄዎች መካከል 1:–ሩዝን ማውጣት ይቻላል? 2:–በሚበላ ፋንታ ገንዘብን ብናወጣስ? የሚሉ ጥያቄዎች ይገኙበታል። 🔺በመጀመሪያ ልንገነዘበው የሚገባ ነገር ዘካተል ፊጥርን ማውጣት ግዴታ መሆኑን ነው። ከነቢዩ صلى الله عليه وسلم እና ከባልደረቦቻቸው ፀድቁዋል። ከተምር፣ ከገብስና መሰል ከሆኑ የሚበሉ ነገራቶች አንድ ሷዕ ያወጡ እንደነበር። ማሳሰቢያ:– "ሷዕ" ማለት አራት እፍኝ ማለት ነው። በዚህ ዙሪያ ከመጡ ሃዲሶች የኢብኑ ኡመርን ሃዲስ ዋቢ አድርገን እንመልከት 🔺عن ابن عمر رضي الله عنهما قال: "فرض رسولُ الله ﷺ زكاة الفطر, صاعًا من تمرٍ, أو صاعًا من شعيرٍ، على العبد والحرِّ, والذكر والأنثى, والصَّغير والكبير, من المسلمين, وأمر بها أن تُؤدَّى قبل خروج الناس إلى الصلاة". متَّفقٌ عليه.  ♦️ዘካተል ፊጥርን ወይም ዘካን ማዘግየት ብይኑ ምንድን ነው ⁉️ 🔺ዘካን ከጊዜው ማዘግየት አይፈቀድም። ዘካም ሆነ ዘካተል ፊጥር ግዜው ሲደርስ ተገቢ ለሆነው አካል ማደረስ ግዴታ ነው። 🔺ዘካተል ፊጥር የሚሰጥበት ግዜ ከኢድ ሶላት በፊት የኢድ ነጋት ላይ ወይም የኢድ ለሊት ላይ ይህ ማለት የኢድ ዋዜማ ላይ ማለት ነው። በተለምዶ ገበረላ እይተባለ በሚጠራው ለሊት ማለት ነው። ♦️ዘካተል ፊጥርን ለሌላ ሀገር ማወጣት ያለው ብይን ምንድን ነው❓ 🔺በላጭና ተመራጭ የሚሆነው አንድ ሰው በሚኖርበት ሃገር ላይ ላሉ ተገቢ ለሆኑ አካላቶች ማውጣቱ ነው። ነገር ግን ለሌላ ሃገር እንዲሰጥ የሚያደርጉት ነገራቶች ካሉ ችግር እንደሌለው ኡለማዎች ያስቀምጣሉ። ♦️ዘካተል ፊጥር ምን ያክል ነው የሚወጣው❓ 🔺ዘካተል ፊጥር የሚወጣው አንድ ሷዕ (አራት እፍኝ) ነው፣ ከሁሉም ቀለቦች። ♦️ዘካተል ፊጥርን ከሚበላ ይልቅ በብር ማውጣት ያለው በይን ምንድን ነው❓ 🔺ዘካተል ፊጥርን በገንዘብ ማውጣት ተገቢ አይደለም። አብዛኛው ኡለማዎችም በዚህ አቋም ላይ ናቸው። ዘካተል ፊጥር በገንዘብ ማውጣት ተገቢ አይደለም። ምክኒያቱም ነቢዩ صلى الله عليه وسلم እና ባልደረቦቻቸው በገንዘብ ሳይሆን ከሚበላ ነገር ነበር ሲያወጡ የነበረው። ስለዚህ እነሱ በተጓዙበት ልንጓዝ ይገባል። ♦️ዘካተል ፊጥርን ከሩዝ ማውጣት ያለው ብይን ምንድነው❓ 🔺ሸይክ ኢብን ባዝ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ :– "ሩዝም ሆነ ሌሎች የሃገሪቱ ቀለብ ከሆኑ ነገራቶች ማውጣት ይቻላል። እንዳውም ከሩዝ ማውጣት በጣም የተሻል ነው። ምክኒያቱም ዛሬ ላይ ሰዎች ከሚጠቀሙት ቀለብ መልካም የሚባለው ስለሆነ።" ምንጭ: — مجموع الفتاوى ومقالات ابن باز بتاريخ 1408/9/23 هجري ♦️ማሳሰቢያ: — ➡️አንድ ሰው ዘካተል ፊጥርን ረስቶ መሰጠት ባለበት ግዜ ካልሰጠ ከኢድ ሶላት ሲመለስ ቢሰጥ ይበቃለታል ይላሉ ሽይኽ ኢብን ባዝና ሌሎችም። ➡️ዘካተል ፊጥር መሰጠት ያለበት መጠን አንድ ሷዕ መሆኑ ግልፅ ነው። ባይሆን ግና በኪ•ግ መስጠት ለሚፈልግ በዑለማዎች የተቀመጠው የተለያየ ነው። ከ2 ኪሎ ግራም ትንሽ አለፍ ብሎ ጀምሮ እስከ 3 ኪሎ የተሰጡ ሃሳቦችን ልናገኝ እንችላለን። ይህ የሆነው በጊዜው ኪሎ ግራም ስላልነበረ ሁለተኛ ደግሞ ሰ ዕ የስፍር እንጂ የክብደት መለኪያ ስላልሆነ ነው። ስለዚህ የእህል አይነት ሲለያይ በስፍር ተመሳሳይ ቢሆኑ እንኳ በሚዛን ክብደታቸው ሊለያይ ይችላል። አንድ ጣሳ ተምር እና አንድ ጣሳ ዱቄት እኩል ኪሎ ክብደት እንደማይኖረው ማለት ነው። እዚህ ጋር ልብ ሊባል የሚገባው 3 ኪሎ ተደርጎ ቢሰጥ በላጭ መሆኑ ነው። ➡️ዛካተል ፊጥርን ከ አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀደሞ መስጠት እንደሚቻል ኡለሞች ይገልፃሉ ። ወደ ቻናሉ ጆይን ለማለት ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️ https://telegram.me/abutoiba ወንድማዊ ምክራችሁን በዚህ ለግሱኝ። ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️ @AbuAyub_bot
Mostrar todo...
አቡ አዩብ ሙሃመድ ሰይድ ሙሃመድ

قال الإمام مالك ((لايصلح آخر هذه الأمة إلا بماصلح أولها))

4_6025836827070433836.mp38.89 KB
👆🏻👆🏻👆🏻 🔊 #ሙዚቃ (ዘፈን) ማድመጥ እወዳለሁ በተለይም የሱዳንን እና ሌሎቹን መስማት በኢስላም እንዴት ይታያል ? ለምንስ ተከለከለ? 🎙 በሸይኽ ሙሐመድ ወሌ ረሂመሁላህ 👉🏼 ዩቱዩብ ላይ ለማድመጥ https://youtu.be/s2x4dlFpua0 ሱንና ቲዩብን ይቀላቀሉ 👇👇👇 ዩቲዩብ ፌስቡክ ቴሌግራም
Mostrar todo...
ሙዚቃ ማዳመጥ.mp32.17 MB
ርዓን ያቃራቸው ነበር፡፡ ረሱል በሞቱበት አመት ግን ሁለት ጊዜ ቁርዓን አቃርቷቸዋል፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ሙስሊም በረመዷን ፕሮግራም አውጥቶ የተወሰኑ ጁዝኦችን በቀንም ይሁን በሌሊት ሊቀራ ይገባዋል፡፡ 4ኛ. ዘካህ መስጠት:– ከኢስላም ማእዘናቶች መካከል አንዱ ዘካ ነው፡፡ ሙስሊሞች የአላህን ረህመት ለማግኘት እና አጅራቸው እንዲነባበር ዘካቸውን በረመዷን ቢያወጡ ተመራጭነት አለው፡፡ ረሱል ﷺ በረመዳን መልካም ተግባርን እና ሶደቃን ያበዙ ነበር፡፡ አብደላህ ብን አባስ رضي الله عنه የሚከተለውን ተናግረዋል፡- "كان رسول الله ﷺ أجود الناس ، وكان أجود ما يكون في رمضان حين يلقاه جبريل ، وكان يلقاه في كل ليلة من رمضان فيدارسه القرآن فلرسول الله ﷺ أجود بالخير من الريح المرسلة" البخاري: ٨ “የአላህ መልክተኛ ከሰዎች በጣም ለጋስ ነበሩ ፡፡ በረመዷን ከጅብሪል ጋር ሲገናኙ ደግሞ ልግስናቸው ይጨምራል፡፡ በየረመዷን ሌሊት ከረሱል ጋር ይማማራሉ፡፡ ልግስናቸው ከብርቱ ነፋስ የፈጠነ ነበር፡፡” (ቡኻሪ: 6) ይህ ሙስሊሞች በተለየ ሁኔታ ሲቸገሩ የሚደገውን ሶደቃ ሳይጨምር በረመዷን ተፈጻሚ የሚሆነውን ሶደቃ የሚያስገኘውን ጥቅም ብቻ ይገልጻል፡፡ 5ኛ. ሶደቃ:– ሶደቃ ከአላህ ዘንድ ኢባዳችን ተቀባይነት እንዲኖረውና ምንዳችን እንዲነባበር ያደርጋል፡፡ በተጨማሪ ጥላ በሌለበት የቂያማ ቀን በአላህ ጥላ እንድንጠለል ምክንያት ይሆናል፡፡ ስለዚህ ከረመዷን ውጭ መሶደቅ አጅር የሚያስገኝ ቢሆንም በረመዷን የምንሶድቀው ሶደቃ አጅሩ ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ሶደቃዎችን ከሰዎች እይታ ውጭ ማድረግ መልካም ተግባር ከመሆኑ ባሻገር የሰለፎችም ተግባር በመሆኑ በየቤቱ የሚገኙትን መሳኪኖች ኢኽላስ በተሞላበት ሁኔታ መጎብኘት አስፈላጊ ነው፡፡ @IbnuAhmedMuhammed
Mostrar todo...
በረመዷን ወር ሙስሊሙ ሊሰራቸው የሚገቡ መልካም ተግባራት 1ኛ. ዱዓና አላህን መዝከር:– አንድ የአላህ አገልጋይ (ባሪያ) ወደአላህ ከሚቃረብባቸው ታላላቅ ተግባራቶች መካከል አንዱ ዚክር (አላህን ማስተወስ) ነው፡፡ ለዚክር ሲባል ነው አምልኮቶችና መልካም ስራዎች የተደነገጉት ፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡- ﴿فَاعْبُدْنِي وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي﴾ طه: ١٤ “ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡” (ጦሃ፡ 14) ሙስሊሞች ነፍሳቸውን ከሚጠምዱበትና በላጭ ከሆኑ የኢባዳ ተግባራቶች መካከል አንዱ ዚክር እንደሆነ ኡለማዎች ይናገራሉ፡፡ የዚክርን ደረጃ የሚናገሩ በርካታ መረጃዎች በቁርዓንም በሀዲስም መጠዋል፡፡ ከነዚህ መካከል የሚከተለው ይገኝበታል፡- ﴿وَالذَّاكِرِينَ اللَّهَ كَثِيراً وَالذَّاكِرَاتِ أَعَدَّ اللَّهُ لَهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْراً عَظِيماً﴾ الأحزاب: ٣٥ “አላህን በብዙ አውሽዎች ወንዶችና አውሽዎች ሴቶችም አላህ ለእነርሱ ምህረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡” (አል`አህዛብ፡ 35) የዚክርን ደረጃ በተመለከተ ነብዩ - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡- "ألا أنبئكم بخير أعمالكم ، وأزكى عند مليككم ، وأرفعها في درجاتكم ، وخير لكم من إنفاق الذهب والورق ، وخير لكم من أن تلقو ا عدوكم فتضربوا أعناقهم ويضربوا أعناقكم ؟ قالوا بلى . قال : ذكر الله" الترمذي: ٣٣٧٧، ابن ماجه: ٣٧٩٠ احمد: ٢١٧٠٢ “ከጌታችሁ ዘንድ አትራፊ ፤ ደረጃችሁን ከፍ አድራጊ፤ ወርቅና ብር ከመለገስ በላጭ የሆነ ፤ ከጠላት ጋር ተገናኝታችሁ እነርሱም የእናንተን እናንተም የእነርሱን አንገት ከምትመቱበት የበለጠውን መልካም ስራ ልንገራችሁን?” በማለት ጠየቁ፡፡ ሶሃቦችም “አዎ” በማለት መልስ ሰጡ፡፡ “አላህን መዝከር ነው፡፡” በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡ (ቲርሚዚ: 3377, ኢብኑ ማጀህ: 3790, አህመድ: 21702) ከዚክሮች ሁሉ በላጭ ረሱል ﷺ በቦታ በወቅት ገድብ ያደረጉላቸው ዚክሮች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- ከእንቅልፍ ስንተኛና ስንነቃ፣ መስጊድ ስንገባና ስንወጣ፣ በመኪና ተሳፍረን ስንጓዝ የሚባሉ ዚክሮች በስድ ከምንዘክራቸው ዚክሮች በደረጃ ይበልጣሉ፡፡ ዚክሮች ከሚያስገኙት ጥቅም መካከል የአላህን ውዴታ ማስገኘት፣ ወደአላህ ማቃረብ፣ ሰይጣንን ማባረር፣ ሀሳብና ጭንቀትን ማስወገድና ሐጢያትን ማሰረዝ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ዚክር ከኢባዳው ሁሉ በጣም ቀላሉና ገሩ እንደሆነ ኡለሞች ይናገራሉ፡፡ ዚክር ጀነት ለመግባት ትልቁ ሰበብ ነው፡፡ ኢብነል አረቢ رحمه الله ዚክርን አስመልክቶ የሚከተለውን ተናግረዋል፡- “ዚክር ለስራችን ትክክለኛነት መስፈርት ሲሆን አላህን ያልዘከረ ስራው ጎደሎ ይሆንበታል፡፡ በነዚህ ምክንያቶች ዚክር ከስራዎች ሁሉ በላጭ ነው፡፡” ጾመኛ በሚያፈጥር ጊዜ የሚያደርገው ዱዓ ተመላሽ እንዳማይሆን ረሱል ﷺ በሚከተለው ሐዲሳቸው ተናግረዋል፡- "إن للصائم عند فطره دعوة ما ترد" ابن ماجه: ١٧٥٣ “ጾመኛ በሚያፈጥር ጊዜ የማይመለስ ዱዓ አለው፡፡” (ኢብኑ ማጀህ: 1753) የኢፍጧር ጊዜ ከሚደረጉ ዱዓዎች መካከል የሚከተለው ይገኝበታል፡- "ذهب الظمأ وابتلت العروق وثبت الأجر إنشاء الله" ابو داود: ٢٣٥٧ “ጥማቱ ተወገደ የደም ስሮች ረሰረሱ አጅርም ኢንሻአላህ ተረጋገጠ፡፡” (አቡ ዳውድ ዘግበውታል) 2ኛ. ሶላት:– በረመዷን ወር ወደአላህ ከምንቃረብበት መልካም ተግባራት መካከል ከኢስላም ማእዘናቶች መካከል ሁለተኛ የሆነው ሶላት ነው፡፡ ነብዩ - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - የሚከተለውን ተናግረዋል፡- "رأس الأمر الإسلام ، وعموده الصلاة" الترمذي: ٢٦١٦، احمد: ٢٢٠١٦ “የነገሩ ሁሉ ቅንጭላት ኢስላም ሲሆን ምሰሶው ደግሞ ሶላት ነው፡፡” (ቲርሚዚይ: 2616, አህመድ: 22016) ከነብያችን የመጡ ሀዲሶች ሁሉ በፈርድ ሶላት ትሩፋት ላይ ብቻ የተወሰኑ አይደለም፡፡ በትርፍ ሶላቶችም የምናገኛቸውን ጥቅሞች የሚናገሩ ሐዲሶች በርካታ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ከፈርድ ሶላት በኋላ የሚሰገዱ አስራሁለት ረዋቲብ ሱና ሶላቶችን ጠብቆ የሰገደ የሚያገኘው አጅርና ደረጃ በሚከተለው ሀዲስ ተነግሯል፡- "ما من عبد يصلي لله كل يوم ثنتي عشرة ركعة تطوعا غير فريضة إلا بنى الله له بيتا في الجنة " مسلم: ٧٢٨ “አንድ ሰው ከፈርድ ሶላቶች ውጭ በየቀኑ አስራሁለት ረከዓዎችን አይሰግድም አላህ በጀነት ቤትን የሚገነባለት ቢሆን እንጂ፡፡” (ሙስሊም: 728) ከፈጅር በፊት ሁለት ረከዓዎችን በመስገድ የሚገኘው ደረጃ ደግሞ በሚከተለው ሐዲስ ተነግሯል፡- "ركعتا الفجر خير من الدنيا وما فيها" مسلم “የፈጅርን ሁለት ረከዓ የሰገደ በዱንያና በውስጧ ካሉት ሁሉ በላጭ ነው፡፡” ሙስሊም: 725 በረመዷን ወንጀልን ከሚያስምሩ ተግባራት መካከል የተራዊህ ሶላት ወይም ቂያመ ለይል ይገኙበታል፡፡ ረሱል ﷺ የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡- "من قام رمضان إيمانا وحتسابا غفر له ما تقدم من ذنبه" البخاري: ٣٧، مسلم: ٧٥٩ “አምኖና ከአላህ ዘንድ የሚገኘውን አጅር ሂሳብ አድርጎ ረመዷንን የቆመ ያለፈው ወንጀል ይሰረዝለታል፡፡” (ቡኻሪ: 37, ሙስሊም፡ 759) የተራዊህ ሶላት በጀመዓ የሚፈጸም ጠንከር ያለ ሱና ነው፡፡ ነብዩ ﷺ አስራ አንድ (11) ረከዓዎች ይሰግዱ ነበር፡፡ ስድ በሆነ ሁኔታ መስገድ እንደሚቻል የሚጠቅስ ትክክለኛ ሐዲስ በመኖሩ አንድ ሰው ከአስራ አንድ ረከዓዎች በላይ ቢሰግድ ችግር የለውም፡፡ የሚፈለገውን አጅር (ምንዳ) ከአላህ ዘንድ ለማግኘት ሶላታችንን በተረጋጋ እና አላህን በመፍራት መፈጸም አለብን፡፡ አንድ ሰው የፈጅርን ሶላት ሰግዶ ጸሐይ እስከምትወጣ ድረስ ዚክር ዘክሮ ከዚያም ሁለት ረከዓን የሰገደ የሚከተለውን አጅር ያገኛል፡- "من صلى الفجر في جماعة ، ثم قعد يذكر الله حتى تطلع الشمس ، ثم صلى ركعتين ، كانت له كأجر حجة وعمرة تامة ، تامة ، تامة " الترمذي: ٥٨٦ “የፈጅርን ሶላት በጀማዓ ሰግዶ ጸሐይ እስክትወጣ ድረስ አላህን በመዝከር ሁለት ረከዓ የሰገደ የተሟላ የተሟላ የተሟላ የሀጅና የኡምራ አጅር አለው፡፡” (ቲርሚዚይ: 586) 3ኛ. ቁርዓን መቅራት:– አንድን የቁርዓን ሐርፍ የቀራ በአስር እጥፍ እንደሚባዛለት በሚከተለው የነብዩ ሐዲስ ተነግሯል- "من قرأ حرفا من كتاب الله فله به حسنة والحسنة بعشر أمثالها لا أقول الم حرف ولكن الف حرف ولام حرف وميم حرف" الترمذي: ٢٩١٠، الدارمي: ٣٣٥١ “ከአላህ ኪታብ አንድ ሀርፍ የቀራ አንድ ሀሰና (መልካም አጅር) አለው አንዱ ሀሰና በአስር አምሳያ ይባዛል፡፡ አሊፍ ላም ሚም የሚለው እንደ አንድ ሀርፍ ነው ብየ አልልም፡፡ ግን አሊፍ ሀርፍ ነው ላም ሀርፍ ነው ሚም ሀርፍ ነው፡፡” (ቲርሚዚይ: 2910, ዳሪሚይ፡ 3351) በዚህ ስሌት ቁርዓን የቀራ ሰው በርካታ ሀሰናቶችን ያገኛል፡፡ ይህን ምንዳ ታሳቢ በማድረግ ነው ረሱል ﷺ ዘወትር ቁርኣን መቅረትን የሚያበዙት፡፡ ጅብሪል عليه السلام በየአመቱ ረመዷን ላይ እየመጣ ቁ
Mostrar todo...
ፆመኛ የሆነ ሰው ሊተገብራቸው የሚገቡ ተመራጭ ተግባራት ማንኛውም ፆመኛ የረመዳንን ወር እያንዳንዱን ቀን እንዲሁም ሰዓት አላህን በመገዛትም ሆነ ሌሎችን በመጥቀም እንዴት መጠቀም እንደሚችል ለማስረዳት የተዘጋጀ ማሳያ ነው፡፡ ዓብደላህ ቢን መስዑድ (አላህ ስራውን ይውደድለትና) እንዲህ ይል ነበር ‹‹ዕለቱን ሣልጠቀምበት ዕድሜዬ እየቀነሰ ሥራዬ ሳይጨምር ፀሀይ ከምትጠልቅበት ቀን የበለጠ የሚቆጨኝ ምንም ነገር የለም›› ኢማሙ አነኸሚም የረመዳንን አንድ ቀን ትሩፋት ሲገልፁ እንዲህ በማለት ነበር የሚገልፁት ‹‹ረመዳንን አንድ ቀን መፆም ሌላ ጊዜ ሺ ቀን ከመፆም ይበልጣል፤ በእለቱም (ሱብሀነላህ) አላህ ጥራት ይገባው ማለትም በሌላ ቀን ሺህ ጊዜ ከማለት ይበልጣል፤ በእለቱም አንድ ረከዓ መስገድ ከሌላ በሺህ ይበልጣል፡፡›› ውድ ወንድም እና እህቶች በተቻለ መጠን ማንም ወደ አላህ ራህመት (እዝነት) ሳይቀድመን ከሁሉም ይበልጥ ቀዳሚ ልንሆን ይገባል፡፡ አላህ ለመልካሙ ሁሉ ያድለንና፡፡ ከሱቢህ በፊት ተመራጩ ተግባር ሁለት ረከዓ ቢሆንም እንኳ ተሐጁድ (የለሊት ሰላት) መስገድ አላህ እንዲህ ይላል ‹‹እርሱ የመጨረሻይቱን ዓለም (ቅጣት) የሚፈራ፣የጌታውንም ችሮታ የሚከጅል ሲሆን በሌሊት ሰዓቶች ሰጋጅና ቋሚ ሆኖ ለጌታው የሚገዛ ሰው (እንደ ተስፋ ቢሱ ከሓዲ ነውን በለው)›› አዝ-ዙመር-9 መልዕክተኛውም (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን)እንዲህ ይላሉ ‹‹ በሌሊት ተነስቶ ቤተሰቦቹንም ቀስቅሶ በጋራ ሁለት ረከዓ ከሰገዱ አላን ብዙ ካወደሱ (አወዳሽ) ይመዘገባሉ›› (አቡ ዳውድ፣ነሳዒና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል) ሰልት ብኑ አሽየም የተባለ ሰው ሌሊቱን ሙሉ ይሰግድ ነበር በሰሀር(ከሱቢህ በፊት ባለው ሰዓት) እንዲህም ይል ነበር ‹‹አምላኬ! እንደ እኔ ያለ ጀነትን ሊፈልግ አይገባም ነገር ግን በእዝነትህ ከእሳት ጠብቀኝ›› አሏህን የማምለክ ፈቅድ (ኒያ) ኖሮት በተጨማሪም ሱናን ተግባራዊ ከማድረግም አንፃር በማሰብ ሱሁርን (ፆም ማሰሪያ) መብላት፡፡ ይህም መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አንዲህ ስላሉ ነው ‹‹ ስሁር ተመገቡ (ብሉ) ስሁር መብላት በረካ አለውና›› (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል) ሱቢህ አዛን እስከሚል ኢስቲግፋር ከአላህ መጠየቅ አላህ ስለ መልካም አማኞች ባህሪ ሲገልፅ እንዲህ ይላልና ‹‹ በሌሊት መጨረሻዎችም እነሱ ምህረትን ይለምናሉ›› አዝ-ዛሪያት 18 ፈጅር ከደረሰ በኃላ ተመራጩ ተግባር ለአዛኑ ተገቢውን መልስ ከሰጠ በኋላ የሱቢህ ሱናን ሁለት ረከዓ መስገድ፡፡ ይህንን በማስመልከት ነብያችን እንዲህ ብለዋል፡፡ ‹‹የሱቢህ (ሱና) ሁለቱ ረከዓዎች ከዱንያና በውስጧ ካሉት ይበልጣሉ›› (ሙስሊም ዘግበውታል) ሱቢሂን ለመስገድ በጊዜ መስጅድ መገኘት፣ ነብያችን (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) እንዲህ ብለዋልና ‹‹ የዒሻእ ሰላትና የሱቢህ ሰላትን (በጀመዓ መስገድ) ያለውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳኹም (በጉልበታቸው እየተጓዙ) ቢሆን ይመጡ ነበር›› (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል) ኢቃም ስኪል ድረስ ዱዓእ በማድረግ፣ ወይም ቁርዓንን በመቅራን ጊዜውን መጠቀም፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ‹‹ከአዛንና ኢቃም መካከል ዱዓእ አይመለስም (ተቀባይነት ያገኛል)›› ብለዋልና (አህመድ፣ቲርሚዚና አቡዳውድ ዘግበውታል) ከሰላቱ በኋላ አላህን ለማወደስ (ዚክር ለማድረግ) መቀመጥ ለምሳሌ፡-የጧት ውዳሴን ፀሀይ እስኪወጣ ድረስ ነብያችን (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ሱቢህን ከሰገዱ በኋላ እግራቸውን አጣጥፈው ፀሀይ በደንብ እስክትወጣ ድረስ ይቀመጡ ነበር፡፡(ሙስሊም ዘግቦታል) ይህንን ጊዜ በዚክር (አላህን በማወደስ) ማሳለፍ የተወደደ መሆኑን በርካት የዲን ሊቃውንቶች ገልፀዋል፡፡ ይህ ተግባር የቀደምት አበው (ሰለፎች) ልምድም ነበር፡፡ ሁለት ረከዓ የተሟላ ሀጅንና ዑምራን ምንዳ በማሰብ መስገድ፡፡ ይህንንም በተመለከተ ተወዳጁ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል ‹‹ሱቢህን በጀመዓ የሰገደ ከዚያም ፀሀይ እስክትወጣ ድረስ ተቀምጦ አላህን ያወደሰ ቀጥሎም ሁለት ረከዓ የሰገደ ልክ የተሟላ የሀጅ የዑምራ ምንዳ ይቆጠርለታል›› ቀኑን ሙሉ መልካም ለመስራት ማቀድና መወሰን ከዚህ በኋላ ተመራጩ ተግባር 1.ጊዜ ካለ ትንሽ እረፍት መውሰድ ምንዳውን ግምት ውስጥ በማስገባት ሙዓዝ (አላህ ስራውን ይውደድለትና) ‹‹ (ለሰላት) መቆሜን እንደማስበው ሁሉ መኝታዬንም አስባለሁ (ምን አገኝበታለሁ ብዬ አስባለሁ)›› ይል ነበር፡፡ 2.ወደ ስራ ወይንም ወደ ትምህርት መሄድ 3.ቀኑን ሙሉ አላህን እያወደሱ ማሳለፍ (በስራ ቦታም ይሁን በሌላ ስፍራ) 4.የእለቱን ሰደቃ (ልገሳ) መፈፀም የመላኢኮችን ዱዓእ ግምት ውስጥ በማስገባት ‹‹ አላህ ሆይ! ለጋሽን ምትክ ስጠው የሚለውን ዱዓእ ዙሁር ሲደርስ ተመራጩ ተግባር አዛን በሰማ ጊዜ መልስ መስጠትና ዙህርን በጊዜውና በጀመዓ መስገድ በጊዜ በመምጣትን ቅዱመ ዝግጅት በማድረግ ኢብኑ መስዑድ (አላህ ስራውን ይውደድለትና) እንዲህ ይል ነበር ‹‹ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የቅናቻን ፈለግ አስተምረውናል፣ ከቅናቻ ፈለጎችም መካከል አዛን በተባለበት መስጅድ ውስጥ መስገድ ነው፡፡ (ሙስሊም ዘግበውታል) ከዐሱር በኋላ ተመራጩ ተግባር ዐስርን መስገድ ከዚያ በፊት አራት ረከዓ ሱና መስገድ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ‹‹ከዐስር በፊት አራት ረከዓ የሰገደ ሰው አላህ አዘነለት›› ብለዋልና (አቡዳውድና ቲርሚዚ) መስጂድ ውስጥ ጥሩና ጠቃሚ ምክር የሚሰጥ ከሆነ ምክሩን ማድመጥ የተለያዩ መልካም ተግባራት 1.አላህን ለማወደስ (ዚክር) ለማድረግ ወይም እለታዊ የቁርዓን ድርሻን ለመቅራት መስጂድ መቀመጥ 2.ባለበት አካባቢ በመስጅድም ይሁን በቤት ውስጥ ማፍጠሪያ ማዘጋጀት ወ.ዘ.ተ በርካታ መልካም ስራን መፈፀም ከመግሪብ በፊት ያለ ተመራጭ ተግባራት መግሪብ ከመድረሱ በፊት በዱዓእ መወጠር ምክንያቱም የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ስላሉ ‹‹ሶስት አይነት ሰዎች ዱዓቸው ተመላሽ አይሆንም (ተቀባይነት ያገኛል)›› ከተጠቀሱትም መሀል አንዱ ‹‹ፆመኛ የሆነ ሰው እስኪያፈጥር›› (ቲርሚዚ ዘግበውታል) ማፍጠሪያ ሲደርስ በቴምር እሸት ወይም በቴምር ነጠላ በሆነ ቁጥር ማለትም (1፣3፣5…) አድርጎ ማፍጠር አፍጥረው ሲጨርሱ የሚባለውን ዚክርና ዱዓእ አለመዘንጋት ትርጉሙ  ‹‹ ጥሙ ጠፋ፣ ደም ስሮችም ራሱ፣ በአላህ ፍቃድም ምንዳው ፀና›› (አቡዳውድ ዘግበውታል) ወቅቱ ከገባ በኋላ ተመራጩ ተግባር የመግሪብ ሰላት በመስጅድ በጀመዓ ለመስገድ በጊዜ በመገኘትና ከአዛንና ኢቃም መሃል ዱዓ ማድረግ ሱና መስገድ ከቤተሰብ ጋር ተሰብስቦ በአንድ ማእድ ላይ በመሆን ማፍጠር፡፡ አላህ በሰላምና በጤና ዕለቱን ለማጠናቀቅ የበቃንን ጌታ በማመስገንና ቤተሰብን ከማስደሰትም ጋር፡፡ ኢሻ እና ተራዊህን በጀመዓ ለመስገድ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን ማድረግ እንደምሳሌም፡- ውዱዕ ማድረግ ሽቶ መቀባት (ለወንዶች ጥሩና የፀዳ ልብስ መልበስና ወ.ዘ.ተ ያለውን ምንዳ ግምት ውስጥ በማስገባት ወደ መስጅድ መጓዝ ከኢሻዕ በኋላ ተመራጩ ተግባር ተራዊህን ከኢማሙ ጋር አሟልቶ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ መስገድ።የረመዷን ትሩፋት ጾም ከኢስላም ማዕዘናቶች መካከል አንዱ ሲሆን የሚያስገኛቸው ፋይዳዎችና በረከቶች በርካታ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ፋይዳዎች መካከል የአላህ መልክተኛ ﷺ በሐዲሳቸው የተናገሩት አንዱ ነው፡፡ "من صام رمضان إيمانا واحتسابا غفر له ما تقدم من ذ
Mostrar todo...
نبه" البخاري: ٣٨، مسلم: ٧٥٩ “ከአላህ ዘንድ የሚገኘውን አጅር ታሳቢ አድርጎ እና አምኖ የረመዷንን ጾም የጾመ ከዚህ በፊት ያለፈው ወንጀሉ ይሰረዝለታል፡፡” (ቡኻሪ: 38, ሙስሊም: 759) ጾም በመጾም የሚገኘው ምንዳ ወይም አጅር እንደ ሰዎች ኒያ ወይም ኢኽላስ ሊለያይ ይችላል፡፡ በጾሙ መካከል ተፈጻሚ የሚሆኑ መልካም ተግባራቶች አንዱን ከፍ አንዱን ዝቅ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ የጾምን አዳብና ስርዓት የሚጠብቅ እና የማይጠብቅ ከአላህ ዘንድ እኩል ደረጃ አይኖረውም፡፡ የረመዷንን ወር ከሌሎች ወሮች ለየት የሚያደርገው የሚሰሩ መልካም ተግባራት ሁሉ ምንዳቸው እጥፍ ድርብ መሆኑ ነው፡፡ በዚህም ረመዷን አላህ ከሰጠን ትልቁ ጸጋ መካከል አንዱ መሆኑን ልንገነዘብ እንችላለን፡፡ ለዚህ ነው ነብያችን ﷺ ይህ ወር ከመግባቱ በፊት በከፍተኛ ጉጉት የሚጠብቁት፡፡ ኢብን አልቀይም رحمه الله የረሱልን ﷺ የኢባዳ ባህሪ ሲገልጹ “የረመዷንን ሌሊቶችንም ይሁን ቀናቶች ከሌሎች ወራቶች በተለየ ሁኔታ በኢባዳ ያሳልፉ ነበር” ይላሉ፡፡ ነብያችን ﷺ የረመዷንን መግባት ሲያበስሩ እንዲህ ይላሉ፡- "إذا كانت أول ليلة من رمضان صفدت الشياطين ومردة الجن وغلقت أبواب النار فلم يفتح منها باب وفتحت أبواب الجنة فلم يغلق منها باب ونادى مناد ياباغي الخير أقبل وياباغي الشر أقصر ولله عتقاء من النار وذلك في كل ليلة" الترمذي: ٦٨٢، ابن ماجه: ١٦٤٢ “የረመዷን የመጀመሪያው ሌሊት ሰይጣናትና አመጸኛ ጅኖች ይታሰራሉ የእሳት በሮች እንዳይከፈቱ ተደርጎ ይዘጋሉ፡፡ የጀነት በሮች እንዳይዘጉ ተደርጎ ይከፈታሉ፡፡ “መልካም ፈላጊ ሆይ ወደመልካሙ ፊትህን አዙር ሸር ፈላጊ ሆይ ከሸርህ ተቆጠብ” በማለት ተጣሪ ይጣራል፡፡ ለአላህ በየሌሊቱ ሁሉ ከእሳት ነጻ ወጭዎች አሉት፡፡” (ቲርሚዚይ: 692, ኢብኑ ማጀህ: 1642) ይ ቀ ጥ ላ ል ... @IbnuAhmedMuhammed
Mostrar todo...
ሁሴን ሞባይል
Mostrar todo...
ሁሴን ሞባይል.mp32.00 MB
📚ኢኣነቱል ኢኽዋን ➖➖➖➖➖ 📌العلم قبل القول والعمل እውቀት ከንግግርም ከተግባርም ይቀድማል ◾️ይህንን ኪታብ በውዱ ኡስታዛችን ኡስታዝ አብዱረህማን ሰኢድ (አቡ ሒዛም) አላህ ይጠብቀው የተዘጋጀና ባማረ እንዲሁም አጠር መጠን ባለ ሁኔታ ስለረመዷን የሚተነትን ኪታብ ነው። ◾️የዚህ ኪታብ አዘጋጁ ኡስታዛችን ኡስታዝ አብዱረህማን ሰዒድ (አቡ ሒዛም) ነው። ኢንሻ አላህ ⏱ ጁመአ 17/7/2013 ደርስ ስለሚጀመር 🔺በአካል መገኘት ለማትችሉ ኦድዮ በተከታታይ የምንለቅላችሁ ይሆናል። ♦️ለእህቶቻችንም በቂ ቦታ የተዘጋጀ ስላለ መሳተፍ ትችላላችሁ NB :- የሚቀራው መስጅደል ኸይር ሲሆን ቦታውን ለማታውቁት ወንድሞች እና እህቶች 📣📣📣አከባቢው አዲስ ለሆነባቹህ ወንድሞችና እህቶች ቢያሳ እንደ ደረሳችሁ ቀጥታ ወደ ኤለመንታሪ በሚያስኬደው ምንገድ በመጓዝ አፕዳ ቢሮ አለፍ ብሎ በቀኝ በኩል ያለው መስጂድ ነው ወደቻናላችን ለመቀላቀል ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️ https://t.me/durusuabihizam https://t.me/abumahi13/230 https://telegram.me/abutoiba ወንድማዊ ምክራችሁንና አስተያየታችሁን በዚህ አደርሱን ⬇️⬇️⬇️⬇️ @Abumahi_bot @AbuAyub_bot
Mostrar todo...
دروس وفوائد أبي حزام عبدالرحمن بن سعيد

Durusu@abu-hizam

Mostrar todo...
قَنَاةُ أَبِي رَيِّسٍ لِنَشْرِ السُّنَّةِ

አዲስ ሙሐደራ 🌐የተውሒድ አንገብጋቢነትና የሽርክ አስከፊነት 🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር (ሀፊዞሁሏህ) 🕌 በኮንበልቻ አንሷር መስጅድ t.me/abu_reyyis_arreyyis/2227 t.me/abu_reyyis_arreyyis/2227

Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.