cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ኦርቶዶክስ ማህየዊ

☘ኦርቶዶክሳው ትምህርቶች @mahyewi7

Mostrar más
Japón9 018El idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
586
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

+++ መልአኩ ነው +++ ሰዓቱ ሌሊት ነው ፤ እንደ አጋጣሚ ሆኖ በዚያ ሌሊት መላው የቤተሰባችን አባል አምሽቶ እየተጫወተ ነው፡፡ ከዚህ የቤተሰብ ስብስብ መካከል ሳይገኝ የቀረው አንድ በወኅኒ ቤት የታሰረ ልጅ ብቻ ነበር፡፡ድንገት የጊቢው በር በተደጋጋሚ ተንኳኳ፡፡ በሁላችን አእምሮ በሌሊት የሚያንኳኳው ማን ነው ? የሚል ጥያቄ ተፈጠረ፡፡ ሠራተኛችንሮጣ ሔዳ በሩን ሳትከፍተው ተመልሳ እየሮጠች መጣች፡፡ በደስታ ሰክራ ‹‹የታሰረው ልጃችን በር ላይ ቆሟል!›› ብላ ተናገረች፡፡‹በድምፁ አወቅኩት!› እያለች ዘለለች፡፡ ከሁኔታዋ የተነሣ ‹አብደሻል እንዴ!?› አላት ቤተሰቡ ሁሉ፡፡ እስዋ ግን በእርግጠኝነትተናገረች! በቀን የታሰረው ልጅ በሌሊት ተፈቶ መምጣቱ ፈጽሞ ሊታመንን የማይችል ነገር ነው፡፡ ቤተሰቡ ሁሉ የታሰረው ልጅ መጣ ብሎአላመነም፡፡ ሁሉም ማን ሊሆን ይችላል ብሎ ሲገምት የጠረጠረው አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ ‹‹ምናልባት ደጅ የቆመው የታሰረው ልጃችን ሳይሆን እሱን ለመጠበቅ ከእግዚአብሔርየተሠጠው ጠባቂ መልአኩ ይሆናል›› አሉ ሁሉም፡፡ የበሩ መንኳኳት አሁንም ስላልቆመ ቤተሰቡ ግር ብሎ ወጣና ተቻኩሎ በሩን ከፈተ፡፡በደጅ የቆመው ግን እንደተባለው የታሰረው ልጅ ራሱ ነበር፡፡ ሁሉም ተደሰተ!!! ይህገጠመኝ ባለንበት ዘመን የተፈጸመ ነው ተብሎ ቢነገር መቼም ብዙ የሚያምን ሰው አይኖርም፡፡ በሌሊት በር ሲንኳኳ በብዙዎቻችን አእምሮውስጥ መጀመሪያ የሚመጣው ጥርጣሬ ‹ሌባ ሊገባ ይሆን?› የሚል ስለሚሆን ዱላ ፍለጋ እናማትራለን፡፡ ወይ ደግሞ ሌሊቱ ወደ መንጋቱየተቃረበ ከሆነ ‹‹የምን መርዶ ሊያረዱኝ ይሆን? የቱ ዘመዴ ሞቶ ይሆን?› የሚል ጭንቀት ይፈጠራል፡፡ ‹የሚያንኳኳው የእግዚአብሔርመልአክ ይሆናል› ብሎ የሚጠረጥር ሰው ግን በዚህ ዘመን ለማግኘት ያስቸግራል፡፡ እንዲህ ብሎ ግምቱን የሚናገር ሰው ከቤተሰባችንመካከል ቢገኝ እንኳን እንደ ዕብድ ልንቆጥረው እንችላለን፡፡ ታዲያ ይህን ገጠመኝ ከየት አመጣኸው ትሉኝ ከሆነ መልሱ ከመጽሐፍ ቅዱስየሚል ነው፡፡ በሐዋርያትዘመን ሔሮድስ የተባለው ንጉሥ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስን ወኅኒ ቤት ውስጥ ወርውሮት ነበር፡፡ የቀሩት ደቀመዛሙርትና ክርስቲያኖችበዚያ ሰሞን ሲጸልዩ ከርመዋል፡፡ በአንድ ሌሊት በማርቆስ እናት ቤት ውስጥ ተሰብስበው አምሽተው ነበር፡፡ ድንገት የቤቱ በር ሲንኳኳሮዴ የምትባል የቤት ሠራተኛ ደጁን ልትከፍት ወጣች፡፡ ማነው ብላ ስትሰማ የቆመው እስረኛው ቅዱስ ጴጥሮስ መሆኑን በድምፁ አወቀች፡፡ደስታ ግራ ሲያጋባት በሩን መክፈትን ረስታ ወደ ውስጥ ሮጠችና ጴጥሮስ መምጣቱን ተናገረች፡፡ እነርሱ ግን አላመኑአትም፡፡ ጤንነቷንተጠራጥረው ‹አብደሻል› አሏት፡፡ እርግጠኛ ሆና ተናገረች፡፡ እነርሱ ግን መልሰው ‹‹የቆመው ጴጥሮስ ሳይሆን (ጠባቂ) መልአኩ ነው፡፡››አሉ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች እንዲህ በር ሲንኳኳ ‹መልአክ ነው› ብለው የሚገምቱ መንፈሳዊያን ነበሩ፡፡ (ሐዋ. 12፡12-15) ቅዱሳንመላእክት እኛ የሰው ልጆች ከመፈጠራችን ቀድመው የተፈጠሩ ታላቅ ወንድሞቻችን ናቸው፡፡ እንዲያውም ምድርና የሰው ልጅ ሲፈጠር ደስእያላቸው ‹‹እልል›› ይሉ ነበር፡፡ (ኢዮ. 38፡6) ቅዱሳን መላእክትን እግዚአብሔር ለእንዳንዳችን ጠባቂዎች አድርጎ ሠጥቶናል፡፡ከክርስቶስ እግር ሥር ቁጭ ብለው የተማሩት ቅዱሳን ሐዋርያት ስለ መላእክት ጠባቂነት ጋር ይህን ያህል እምነት ከነበራቸው እኛምየመላእክቱን ጠባቂነት ማመን ለዚህ ዘመን ክርስቲያኖችም ምን ያህል ይገባን ይሆን? ቅዱሳን መላእክት በክርስትና ሕይወት ለሚኖርሰው ሁሉ የመላእክት ረዳትነት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ለሁሉ ብርታት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን በሥጋው ወራት በተያዘባትምሽት ሲጸልይ ‹‹ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታው መልአክ ታየው›› ተብሎ ተጽፏል፡፡ (ሉቃ. 22፡43) ይህም ቀርበው አገለገሉት‹ለከ ኃይል› እያሉ አመሰገኑት ማለት ሲሆን ለእኛም የመላእክት ርዳታ አያስፈልገኝም እንዳንል የሚያስተምረን ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት እኛን መርዳት ሳይሆን እርስ በእርሳቸውም ይረዳዳሉ፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነን ቅዱስ ገብርኤል ስለ ቅዱስ ሚካኤል የሰጠው ምስክርነት ነው፡፡ ነቢዩ ዳንኤል ወደ እግዚአብሔር ሦስት ሱባኤ ሙሉ እየጾመ ሲጸልይ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጸለትና እንዲህ ሲል ተናገረው፡፡‹ዳንኤል ሆይ ወደ አንተ ልመጣ ተልኬ ሳለሁ የፋርስ መንግሥት አለቃ (የፋርስ ነገሥታት ላይ አድሮ ክፉ የሚያሠራቸው ዲያቢሎስ)ሃያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ› በዚህ ንግግሩ እንደምናየው በምን ምክንያት ወደ እርሱ ከመምጣት እንደዘገየ አስረዳው፡፡ በመቀጠልም መልአኩ ገብርኤል እንዴት ዲያቢሎስን መዋጋቱን ትቶ እንደመጣ ለዳንኤል ሲያብራራለት ‹‹ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ ፤ እኔምከፋርስ ነገሥታት አለቃ (ከዲያቢሎስ ጋር) በዚያ ተውሁት›› ብሏል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል እርሱን ሊረዳው የሚቻለው ኃያል መልአክ ማንብቻ እንደሆነ ሲገልጽም ‹‹ከአለቃችሁ (ከእስራኤል ጠባቂያችሁ ማለቱ ነው) ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም፡፡›› በማለትደምድሟል፡፡ (ዳን.10፡13፣21) የአንዱ መልአክ ረዳትነት ለሌላው መልአክ እንዲህ የሚስፈልግ ከሆነ እኛ ደካሞቹ ምን ያህል የመላእክትረዳትነት ያስፈልገን ይሆን? በየጊዜው በየሰዓቱ ጠባቂ መላእክትን ይዘዝልን!! አሜን ፫። ወስብሐት ለእግዚአብሔር @Eftah_bemaleda
Mostrar todo...
ይሄ በ2012 ዓም በመርካቶ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል በዕንባ ያስተላለፉት መልዕክት ነው። በተለይ ኦርቶዶክሳውያን እንጠንቀቅ። ቅዱስነታቸው አክቲቪስት አይደሉም። የሁላችን አባት ናቸው። ረመጥ በሆነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እያንዳንዱ እርምጃ፣ ንግግር ተመንዝሮ በሚያስፈርጅበት ሃገር የተሾሙ፣ የተቀቡም አባት ናቸው። በተለይ አሁን ደግሞ የባሰ አርታኢሌ ላይ መጣዳቸውን እያሰብን እንጠንቀቅ። ከማይመስሉን ጋር ሆነን አብረን አፋችንን አናላቅ። ምክሬ ነው። … በዚህ ዕድሜ ላይ ያለ ሰው ዕንባ እንኳን አልነበረውም። ቅዱስነታቸው ግን ዕምባ አውጥተውም አልቅሰዋል። ከትግራይ ውጪ ላሉትማ፣ ቢቸግራቸው ተደራጅታችሁ ራሳችሁን ጠብቁ ጭምር ብለዋል። እስቲ እንዲህ ያለ ሌላ አባት ጠቁሙኝ።
Mostrar todo...
4.44 MB
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤ በሰላም አደረሰን! በፍቅር ተስቦ የወረደው ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የፍቅሩን ፍፃሜ በመስቀል ላይ ገልፆልን ሀያል ጌታ በመሆኑ ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል እኛም ልክ እንደ ሐዋርያቱ በተዘጋ ቤት ሆነን ትንሳኤውን ሰምተናል ረድኤት በረከቱ በእያለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን! @Eftah_bemaleda
Mostrar todo...
• “ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን” •  “በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን” •  “ዐሠሮ ለሰይጣን” •  “አግአዞ ለአዳም” •  “ሰላም” •  “እም ይእዜሰ” •  “ኮነ” •  “ፍሥሐ ወሰላም” … እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሰን  !!
Mostrar todo...
ክርሰቶሰ ተንሥኦ እሙታን! በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን! አሰሮ ለሰይጣን ! አግዐዞ ለአዳም ! ሰላም ! እምይዕዜሰ! ኮነ ! ፍሥሐ ወሳላም ! "'ተሻግረናል"' ☦️
Mostrar todo...
🎉ተነስቷል ሞት ሊይዘው አልቻለምና የተገነዘበትን ልብስ ትቶ ልብሰ መንግስቱን ለብሶ ተነሳ... በተወለደ ጊዜ የእናቱን መሀተመ ድንግልና እንዳለወጠ ሁሉ በትንሳኤውም መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል በመላእክት ታጅቦ በክብር ተነሳ። እንኳን አደረሳችሁ መልካም በዓለ ፋሲካ ይሁንልን!! @Eftah_bemaleda
Mostrar todo...
#ቀዳም_ሥዑር (የተሻረች ቅዳሜ) የዐቢይ ጾም የመጨረሻዋ ቅዳሜ ብዙ ስያሜዎች አሏት፦ #ቀዳም_ሥዑር፡- በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡ #ለምለም_ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡ (የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡) #ቅዱስ_ቅዳሜ፡- ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡ (ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት ሚያዝያ 2004 ዓም) @Eftah_bemaleda
Mostrar todo...
የማይታመም የርሱን ሕማሙን እንናገራለን፣የማይሞት የርሱን ሞቱን እንናገራለን፣የፍቁር የጌታ ሕማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል ሕሊናም ይመታል!" 👉እጅን ወደኋላመታሰር፡- ሰው እጁን ወደ ኋላ ቢታሰር ልቀቁኝ፣ ምን አደረኩ፣ አለቃችሁም እያለ ይዝታል፣ ለመፈታትም ይታገላል። ክርስቶስ ግን ይህን አላደረገም በቅዳሴ ሠለስቱ ምዕት ”እንደ ሌባ የኋሊት አሰሩት፣ እንደ የዋህ በግ በፍቅር ተከተላቸው፣ ሊፈርዱበት በአደባባይ ተቀመጡ። ”ሲል እንደተጻፈ ሁሉን በሥልጣኑ ማድረግ የሚችል ጌታ ዝም ብሎ በፍቅር ተጎተተላቸው። 👉በገመድ መጎ’ተት፡- መጎ’ተት ድካምን ያበረታል፣ ሰውነትን እየከረከረ ከባድ ስቃይን ያደርሳል፣ ያቈስላል፣ አካልን ይልጣል፣ እንኳን ለሰው ልጅ ለእንስሳት እንኳን ምን ያህል ከባድ ነው?ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ይህን ስለ ፍቅር ታገሠ። 👉ምድር ላይ መውደቅ፡- ከምድር ላይ መውደቅ ለእሾህ እና ለጠጠር ያጋልጣል። በሰዎች ዘንድም መሳለቂያ ያደርጋል። ምንም ባልቀመሰ፣ ውሃን እንኳን ባልቀመሰ ሆድ ሲሆን ደግሞ ስቃይ ይበረታል።ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ይህን ስለ ፍቅር ታገሠ። 👉ልብስን መገፈፍ፡-ሰው እርቃኑን በልብሱ ይሸፍናል፣ ማዕረጉንም በልብሱ ይገልፃል። ለከዋክብት የብርሃን ልብስ ያለበሳቸው እርሱ ግን በዕለተ ዓርብ እርቃኑን በቀራንዮ አደባባይ አቆሙት።ይህንንም ስለ ፍቅር ታገሠ። 👉ምራቅ ሲተፉበት መታገስ፡- ምራቅ መትፋት ሰውን ያስቀይማል፣ ጥላቻንና ንቀትን ያሳያል። የዕወሩን ዓይን ያበራ እርሱ በፊቱ ላይ ተተፋበት። ቅዱስ ኤፍሬም “ለእኛ ፊት ክብርን የሰጠ እንዳንተ ያለማን አለ? የዕውሩን አይን ስታበራ እንኳን አርአያችንን አክብረህ ወደ መሬት ተፋህ እንጂ በፊቱ ላይ አልተፋህበትም” ሲል ገለጸ።እነርሱ ግን ይህን ድንቅ የሚያደርግ ጌታ ተፉበት እርሱም ስለፍቅር ታገሣቸው። 👉በጥፊ መመታት፡-በጥፊ መመታት ንዴትን እልህን፣ብሶትን ቀስቅሶ ለድብድብ ይጋብዛል፣ ትዕግሥትን ይፈታተናል።እርሱ ግን ስለወደዳቸው ፈንታ በጥፊ ሲመቱት ምንም አልመለሰም። 👉ጀርባን መገረፍ፡-በጅራፍ መገረፍ ይለበልባል፣ሰውነትን ያቆስላል።ጅራፉ ጫፍ ላይ ስለት ሲኖረው ደግሞ ስቃዩን ማሰብ ይከብዳል።ስጋውአልቆ አጥንቱ እስኪታይ ቢገርፉትም እርሱግን ይህንንም ስለፍቅር ታገሠ። 👉ራስን በዱላመመታት 👉የእሾህ አክሊል መድፋት፡-አንዲት እሾህ ስትወጋን እንኳን ሰውነታችን ላይ ታላቅ ህመም ይፈጥርብናል፡እሾሆችን ሰብስቦ አክሊል ሠርቶ በራሱ ሲያደርጉበት ስቃዩ እንዴት የከፋ ይሆን?ለሱራፌል የብርሃን ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የእሾህ አክሊል አቀዳጁት።ይህንንም ስለፍቅር ታገሠ። 👉መስቀል መሸከም 👉በችንካር መቸንከር 👉በመስቀል ላይመሰቀል 👉መራራ ሐሞትንመጠጣት፡-ሐሞት መራራ ጣዕም ያለው ሲሆን ተጠማሁ ባላቸው ጊዜ መራራ ሐሞትን ሰጡት።                @Mahyewi7 ╰══•:|★✧💚💛❤✧★|:  ══╯
Mostrar todo...
Unexpected error, try again later.
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.