cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ወልድ ዋሕድ ሚዲያ welid wahid media

ይህ የኮተቤ መካነ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤተክርስቲያን ወልድ ዋሕድ ሰንበት ትምህርት ቤት ቻናል ነው 👉👉ለጠቅላላ @weldwahid 👉👉ለአብነት እና ግእዝ ቋንቋ ትምህርት @weldwahidabinet 👉👉 ለቤተ መጻሕፍት አገልግሎት @Abaiyesuslib 👉👉ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @mels_asteyayet

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 054
Suscriptores
+424 horas
+167 días
+8630 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

"ፍጹም ፍቅር በአናንተ ልብ ውስጥ ቢኖር በምድር ላይ ጠላት አይኖርህም።ጠላትህን ለክርስቶስ አሳልፈህ ስጠው።ከጌታ በላይ የሚያክመውና የሚያርመው ባለ ሞያ ወዳጅ አይገኝም።" ✨ቅዱስ ኤፍሬም ዘሶርያ✨
Mostrar todo...
7
🌺🌿🌺 በሕይወት ውስጥ መጀመሪያ ከፊት የሚመጡት ሰዎች "ሔዋንህ" ወይም "አዳምሽ" ላይሆኑ ይችላሉ። ልክ አዳም ከተፈጠረ በኋላ መጀመሪያ በእርሱ ፊት እንስሳትን እንዳገኘ እና ለእነርሱም የሚገባቸውን ስም እየሰጠ እንዳሰናበታቸው፣ አንተም አንዳንዴ በኑሮህ ቀድመህ የምታገኛቸው አካላት "ጎረቤት፣ የሥራ ባልደረባ፣ ጓደኛ" እያልክ ስም የምታወጣላቸው ብቻ ይሆናሉ። ለምን? "እንደ አንተ ያሉ (የሚመቹ) ረዳቶች" አይደሉማ። አዳም ለእንስሳት፣ ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሁሉ ስም ካወጣላቸው በኋላ መጽሐፉ "ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር" ይላል።(ዘፍ 2፥20) 🌺🌿🌺 አዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት ከእንስሳቱ መካከል ፈልጎ በማጣቱ "በቃ የምን መኩራት ነው? ያሉት እነዚህ ስለሆኑ እኔን ባትመስል እንኳ ትንሽ ለእኔ የቀረበችውን ብመርጥ ይሻላል" አላለም።  ከሌሎች ይልቅ በአካላዊ ቁመና ለእርሱ የምትቀርበውን ትልቅ ጦጣ (Chimpanzee) መርጦም ወደ ፈጣሪው በመውሰድ "እባክህ ጌታዬ፣ ለአንተ የሚሳንህ የለምና ትንሽ ጸጉሯን ብትቀንስ፣ ጅሯቷን ብታጠፋ እና ፊቷ አካባቢ ማስተካከያ ብታደርግላት እንደ እኔ ያለ ረዳት ትሆናለች" ብሎ ሲማጸን አናገኝም። ይህን ቢያደርግ ኖሮ አሁን የአዳምን ታሪክ የምናነብ ሰዎች ሁሉ በችኮላው እየተገረምን እንስቅበት ነበር። ምክንያቱም እግዚአብሔር ከጥቂት ቀን በኋላ አጥንቷ ከአጥንቱ፣ ሥጋዋ ከሥጋው የተፈጠረ ሔዋን የተባለች እጅግ ውብ ሚስት እንደሰጠው ስለምናውቅ።  🌺🌿🌺 ከአንተ ጋር በሃይማኖት፣ በአመለካከትና ይህን በመሳሰሉት ነገሮች ጨርሳ ልትገጥም የማትችል የማትመችህን ረዳት "ለአንተ ምን ይሳንሃል? አስተካክልልኝ" እያልክ ለምን ትታገላለህ። በፍጹም ስለማይሆንሽ ሰው ለምን የmodification ጥያቄ ታቀርቢያለሽ? ጥቂት ጊዜ ከታገስህ እግዚአብሔር ለአንተ የምትመችህን (compatible) ረዳት ያመጣልሃል። አሁን ግን ፊት ለፊት ያገኘሃት ጥሩ የሥራ ባልደረባ ወይም ጓደኛ እንጂ የምትመች ረዳትህ አይደለችም። 🌿🌺🌿 በሕይወት ውስጥ ቀድሞ የመጣ ሁሉ ባል ወይም ሚስት አይሆንም። መጽሐፍ ቅዱስም "ቢቻላችሁስ... ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ" ይላል እንጂ "ከሁሉ ጋር ተጋቡ" አላለንም።(ሮሜ 12፥18) 📝️️ ዲ/ን አቤል ካሳሁን 🍁🍁🍁🍁🍁🌷🌷🌷🍁🍁🍁🍁🍁🍁 🌺ሳምንታዊው  🌺 የረቡዕ ጉባኤ🌺     🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺       🌺"ጋብቻ ወይስ ጋር ብቻ ?"🌺           🌺ተከታታይ ትምህርት 🌺                🌺 ሶስተኛ ጉባኤ🌺         ርዕስ፦ የእጮኝነት ጊዜ 🔆🔆🔆🔆ክፍል -2🔆🔆🔆🔆 🕰 12:00-1:40 ⛪️ በምዕራፈ ጻድቃን ሰንበቴ
Mostrar todo...
👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
🌺ሳምንታዊው  🌺  የረቡዕ ጉባኤ🌺     🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺       🌺"ጋብቻ ወይስ ጋር ብቻ ?"🌺           🌺ተከታታይ ትምህርት 🌺                🌺ክፍል ሶስት 🌺 ርዕስ፦ የእጮኝነት ጊዜ ✨✨✨✨ክፍል 2✨✨✨✨ 👉ኦርቶዶክሳዊ የትዳር አጋር አመራረጥ 👉የእጮኝነት ጊዜ ፈተናዎች 👉በእጮኝነት ጊዜ የሚያጋጥሙ ፈተናዎች እንዴት  ይፈታል? 👉አእምሮአዊ ዝግጁነት እንዴት ማዳበር ይቻላል? 👉የአባት/እናቶቻችን የእጮኝነት ልምምድ ከመጽሐፍ ቅዱስ/ቅድሳት መጸሐፍት እና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ይዳሰሱበታል 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁 🗓ነገ ረቡዕ ግንቦት 28/2016            🕰 ከ12:00-1:40     በመምህርና ጋዜጠኛ፦ ግሩም ንጉሤ                ⛪️ በምዕራፈ ጻድቃን ሰንበቴ አዳራሽ 📋ማስታወሻ ደብተር (ወረቀት) እና ብዕር መያዛችሁ አትርሱ። 🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁          🌺@weldwahid🌺
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
''መድኃኔዓለም ሆይ እኛን ስለማዳን መከራን ለመቀበል ዘንበል ላለው ርዕስኽና ስዕርተ ርዕስኽ ሰላም እላለኹ ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ ከሰማየ ሰማያት ወርደኽ ከድንግል ማርያም ተወልደኽ በሥጋ ብእሲ በሕጻን አርአያ በተገለጽክበት ወራት እናታችን ሔዋንን ያሳተ ከይሲ ዲያቢሎስ ፈራ ደነገጠ በኃዘንና በልቅሶም ተዋጠ''             ''መልክአ መድኃኔዓለም''
Mostrar todo...
1
"ማንነትህን ማወቅ" ተወዳጁ ወንድሜ ሆይ! ኃይለኛ ነኝ ብለህ ታስባለህን? ካሰብህ ይህን ኃይልህን ከየት አመጣኸው? አንተ አመድና ትቢያ ጎስቋላና ምስኪን ስለሆንህ ይህ ኃይል የአንተ አይደለም። ይህ ኃይል ከሌላ ሰው ያገኘኸውም አይደለም ከእግዚአብሔር እንጂ። ክብርና ምሥጋና ለእርሱ ይሁንና ኃያል እርሱ ብቻ ነው፡ ኃይልም ሁሉ የሚገኘው ከእርሱ ብቻ ነው። ያንተስ ኃይል ከእግዚአብሔር አይደለምን? ከሆነ ለምን ትታበያለህ? ለምንስ ትኩራራለህ? የእግዚአብሔርንስ ኃይል እርሱን ለማገልገል ካልሆነ ለሌላ ለምን ታውለዋለህ? ስለዚህ ሊከበር የሚፈልግ ቢኖር በእግዚአብሔር ይክበር። እርሱ ከክብር ሁሉ በላይ የሆነና ለምንከብርበት ነገር ሁሉ ምንጩ ነውና። በእግዚአብሔር ኃይለኛ ሆነህ በተፈጥሮህ ደካማ ብትሆን ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር እንዲህ በል። "እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና።" 2ኛ ቆሮ 12:9-10 (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ)
Mostrar todo...
👍 2 2
📕 የወልድ ዋህድ ሰንበት ትምህርት ቤት የአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ቤተመጽሐፍት ለአንባብያን ታላቅ የምሥራች 📘 ከወርኃዊው የመጻሕፍት ዳሰሳ ጋር በአንድ ላይ የሚካሄድ አንባብያንን የሚያነቃቃ  የጥያቄና መልስ ውድድር ሰኔ 9 ይጀምራል::  ስለሚያነብቡአቸው መጻሕፍት ያላቸውን ማስተዋልና መረዳት ለመለካት እጅግ ደማቅ የጥያቄና መልስ ውድድር አዘጋጅቶአል:: 📚  ተወዳዳሪዎች የጥያቄና መልስ ውድድሩ ላይ ለመሳሣተፍ አንባብያን ሁሉ የተጋበዙ ሲሆን ለተወዳዳሪነት የተዘጋጀውን የማጣሪያ ጥያቄ እና መልስ  በወልድ ዋህድ ሚዲያ የቴሌግራም ገጽ የመጽሐፍ ደሰሳ ከመካሄድ በፊት ባሉ ሳምንታት ዘወትር ሐሙስ ምሽት 2:00 የሚለቀቁ ጥያቄዎችን  በመሳተፍ  ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ 4 ተወዳዳሪዎች ሰኔ 9 ለሚደረገው የጥያቄ እና መልስ ተሳተፊ ይሁናል ።   ሽልማቶች 🥇🥈🥉 የጥያቄና መልስ ውድድር ላይ  የሚሣተፉና ከ1-3 የሚወጡ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ዕለት እዚያው ሽልማት ያገኛሉ::   ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ሰኔ 9 የሚካሔደው የመጀመሪያው ዙር  የጥያቄና መልስ ውድድር ላይ ለመካፈል ለምትፈልጉ አንባብያን   ከግንቦት 29 ጀምሮ ዘወትር ሐሙስ  ከምሽቱ 2:00 በወልድ ዋህድ ሚዲያ የሚለቀቀውን ጥያቄ እና መልስ ተሳታፊ መሆን የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።     🌺 @weldwahid🌺
Mostrar todo...
2👍 1
🍁🍁🍁🍂🍂🍂🍁🍁🍁🍂🍂🍂🍁🍁🍁🍂🍂🍂 🍁🍁🍁ኦርቶዶክሳዊ ኑሮ🍁🍁🍁
ሁል ጊዜም በተወሰነ ሰዓት የመንቃት ልምድ ይኑርህ።
ምክንያተኝነትን ከአንተ አስወግድ። ከሰባት ሰዓት በላይ የእንቅልፍ ጊዜ አይኑርህ። ከእንቅልፍህም በነቃህ ጊዜ የተሰቀለውን ጌታችንን በመስቀል ላይ እንዳለ አድርገህ አስብ። ራስህን በብርድልስ ሙቀት አታታል። ከመኝታህ አፈፍ ብለህ ተነሣ። ለጸሎት ስትዘጋጅ ወገብህ የታጠቀ መብራትህ የበራ ይኹን። የጸሎት ልብስህን ልበስ። ይህ ጊዜ የዝግጅት ጊዜ ነው። በሠራዊት ጌታ በልዑል እግዚአብሔር ፊት ልትቆም መኾንህን አስብ። ሁል ጊዜም አእምሮህ የአባትህን የአዳምን የእናትህን የሔዋንን ውድቀት ያስታውስ። አምላክህን የሚያስብ በጎ ሕሊና እንዲኖርህ አባትህ አዳም ተጠልፎ በወደቀበት የሥጋ ሐሳብ፣ የሥጋ ኃጢአት ተጠልፈህ እንዳትወድቅ ፈጣሪህን ለምነው። በፊቱ የምትቆምበትን ጸጋ ብርታት እንዲሰጥህ ለምነው። 🍁🍁🍂 ... በሕመምህ ጊዜ መጀመሪያ በእግዚአብሔር ታመን፥ አዘውትረህ የጌታ ሥቃይ ይታሰብህ። ሥቃይህንና ሕመምህን ያሥታግስልህ ዘንድ የምታውቀውን ጸሎት ያለማቋረጥ ጸልይ። በሕይወት ዘመንህ ሰላማዊና የተረጋጋ ሕይወት እንዲኖርህ ከፈለግህ ሕይወትህን ሊታመን ለሚችለውና አደራውን ለመጠበቅ ለሚቻለው ለእግዚአብሔር አስረክብ። ራስህን ለእግዚአብሔር አሳልፈህ መስጠት ካልቻልክ ፍጹም የኾነ መረጋጋትን አገኛለሁ ብለህ እንዳታስብ። ፍቅር የሚገባውን አምላክህን ውደደውና በፍቅር ኑር። 🍁🍁🍂 ✍ዲ/ን ታደለ ፈንታው 📚መክሊት 2004 ዓ.ም 🍁🍁🍁🍂🍂🍂🍁🍁🍁🍂🍂🍂🍁🍁🍁🍂🍂🍂
Mostrar todo...
👍 2 2
“እንደ እባብ ልባሞች ኹኑ”                            ማቴ.10÷16 እባብ ራሱን (ጭንቅላቱን) ለማዳን ሲል ሌላው ሰውነቱን ለአደጋ እንደሚያጋልጥ ኹሉ አንተም እንዲህ አድርግ፡፡ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል ሀብትህን ወይም ሰውነትህን ወይም የዚህ ዓለም ሕይወትህን ወይም ያለህን ኹሉ እንኳን መስጠት ካለብህ ይህን በማድረግህ በፍጹም አትዘን! አንተ ሃይማኖትህን ይዘህ ወደ ወዲያኛው ዓለም ስትሔድ እግዚአብሔር ደግሞ ኹሉም ነገር እጅግ ውብ አድርጎ ይመልስልሃል፤ ሰውነትህን በታላቅ ክብር ያስነሣልሃል፤ ከሀብት ከንብረት ይልቅም ከመግለጽ ኃይል በላይ የኾኑ በጎ በጎ ነገሮችን ይሰጥሃል፡፡ ኢዮብ ዕራቁቱን ኾኖ በአመድ ላይ ከሞት እልፍ ጊዜ የሚከፋ ሕይወትን እየመራ የተቀመጠ አይደለምን? ነገር ግን ሃይማኖቱን ስላልጣለ አስቀድሞ የነበረው ኹሉ እጅግ በዝቶ ተመልሶለታል፤ ጤናውና ውብ የኾነ ሰውነቱ፣ ልጆችን፣ ሀብቱን፣ ከዚህ ኹሉ የሚበልጥ ደግሞ አክሊለ ትዕግሥትን አግኝቷል፡፡ (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  -  #ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ)
Mostrar todo...
4
Photo unavailableShow in Telegram
"ቤተክርስቲያን ተስፋህ ናት፤ ቤተክርስቲያን መድኃኒትህ ናት፤ ቤተክርስቲያን የመማፀኛ ከተማህ ናት፡፡" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Mostrar todo...
6