cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

MUAZ MEDIA

"አላማዬ ወጣቱን የጥሩ ስነ-ምግባር ባለቤት ማድረግ ነው"። Tiktok 👇 https://www.tiktok.com/@lij_muaz?_t=8Z1Zk6YYK1e&_r=1 Facebook👇 Instagram 👇 እኔን ቀጥታ ማግኘት ለምትፈልጉ @LijMuaz_bot

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 243
Suscriptores
+624 horas
+237 días
+9330 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

🌙 | መቼ ነበር የሞቱት 🥀✍️ ✅:ረሱል  صلى الله عليه وسلم በ 11ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:አቡ በክር በ13ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኡመር ኢብኑል ኸጣብ በ23 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኡስማን ኢብኑ አፋን በ35 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:አልይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ በ40 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢባኑ አባስ በ68 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢብኑ ኡመር በ 73ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ሰኢድ ኢብኑል ሙሰየብ በ94 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ሀሰኑል በስሪ በ110ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት ✅:አቡ ሀኒፋ በ 150 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢማሙ ማሊክ 179 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢማሙ ሻፊኢይ 204 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢማሙ አህመድ 241ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢማሙል ቡኻሪ 256ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢማሙ ሙስሊም 261ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢብኑ ማጀሕ 273 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:አቡ ዳዉድ 275ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ቲርሚዚይ 279 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ነሳኢይ 303 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢብኑ ጀሪር 310ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢብኑ ኹዘይማ 311 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢብኑ ሂባን 354ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ዳረቁጥኒይ 385ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:አል_ሃኪም 405ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢብኑ ሀዝም 456ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:በይሐቂይ 458 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢብን አብድል በር 468ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኸጢብ አልበግዳኢይ 463ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢብኑል አረቢይ 543 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢብኑል ጀውዚይ 597 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ቁርጡቢይ 671ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ነወዊይ 676 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢብኑ ተይሚያ 728 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ዘሐቢይ 748 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢብኑል ቀይም 751ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢብኑ ከሲር 774 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢብኑ ሀጀር 852 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ሲዩጢይ 911 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:አሚር አሰንኣኒይ 1182ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ሙሀመድ ቢን አብድል ወሓብ 1206 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢማሙ ሸውካኒይ 1250ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢማሙል አሉሲይ 1342ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢብኑ ሲእዲይ 1376 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢማሙ ሺንቂጢይ 1393ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢብኑ ባዝ 1419 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢማሙል አልባኒይ 1420ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ✅:ኢብኑ ኡሰይሚን 1421ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት ✅:ኢማሙል ዋዲኢይ 1422 ኛው አመተ ሒጅራ ነበር የሞቱት። ይጠቅማችሁ አል አንብቡት @muaz_media
Mostrar todo...
👍 12👌 6
01:29
Video unavailableShow in Telegram
ሰበሀል... ኸይር ያጀመኣ?? ☑️ የጧት ዚክር እንዳንረሳ!! ▪️اللهم بِكَ أصْبَحْنَا، وَ بِكَ أمْسَيْنَا، وَ بِكَ نَحْيَا، وَ بِكَ نَمُوتُ، وَ إلَيْكَ النُّشُورُ.   አላህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል፡፡ በአንተ ለምሽት እንበቃለን፡፡ በአንተ ህያው ሆነና፡፡ በአንተም እንሞታለን፡፡ መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡ (ቲርሚዝይ) == @muaz_media
Mostrar todo...
16.71 MB
👍 15
በቀጣይ ... ምን ይለቀቅላችሁ??? 1⃣ የነብያት........ታሪክ 👍 2⃣ የሰሀቦች ......ታሪክ 🍓 @muaz_media
Mostrar todo...
👍 9
❒ሐበሻው ቢላል ኢብኑ ረበሕ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ❒ ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ ክፍል 4⃣ ❒❒📖📖❒❒ ረሱል ﷺ ወደ ካዕባ በተጠጉበት ወቅት ተመለከቷቸው። በድል ደስታ በተሞሉ ዐይኖቻቸው ገረፍ ካደረጓቸው በኋላ፦ "ስትነጋገሩ የነበራችሁትን ነገር አውቄዋለሁ" በማለት እያንዳንዳቸው የሚሰነዘሩትን ትችት ነገሯቸው። ሀሪስና ዐትታብ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ፦ "አንተ የአላህ መልእክተኛ ነህ" በማለት መስለማቸውን አሳወቁ። "አንድም ሰው ያልሰማን በመሆኑ ሶስተኛ ወገን ያልነውን ነገረህ ለማለት አንደፍርም።" አሉ። ስለ ቢላል ረዲየሏሁ ዐንሁ ያላቸውን አመለካከትም ቀየሩ። ረሱል ﷺ መካ እንደገቡ የተናገሩትን አዋጅም ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸ ው አመኑ። ታላቁ ነብይ ﷺ መካ በገቡበት ወቅት ይህን ታሪካዊ ንግግር አድርገዋል፦ "ሕዝበ ቁረይሽ ሆይ! አላህ ከናንተ የጃሂልያን ደካማ አመለካከት እና በአባት በቅድመ አያት መኩራራትን አስወግዷል። ሰወች ሁሉ የመነጩት ከአደም ነው....... አደም ደግሞ የተነሳው ከአፈር ነው። •••✿❒🌹❒✿••• ቢላል (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ከረሱል ﷺ ጎን ሳይነጠል ኑሮውን መግፋት ቀጠለ። እርሳቸው በተገኙበት ዘመቻ ሁሉ ዘምቷል ለሶላት "አዛን" ያደርጋል። ከጨለማ ወደ ብርሀን፥ ከባርነት ወደ ነፃነህ ያወጣውን ታላቅ ዲን አርማ ያስተጋባል። ቢላል ረ.ዐ ከነብዩ ሙሀመድ ﷺ ጋር ያለው ቀረቤታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ መልእክተኛው ﷺ "የጀነት ሰው" እያሉ ያሞካሹት ነበር። እርሱ ግን ትናንት ባርያ የነበረ ሀበሻ መሆኑን ብቻ ነበር የሚያወሳው። ከዕለታት አንድ ቀን ለራሱና ለ ወንድሙ ሚስት ለማጨት ወደ አባቶቻቸው ሄደ። እንዲህም አላቸው "እኔ ቢላል እባላለሁ ይህ ደግሞ ወንድሜ ነው። ሀበሻዊ ባሪያወች ነን...በተሳሳተ እምነት ላይም ነበርን፣ አላህ መራን... ነፃ አወጣን። ልጆቻችሁን ከዳራችሁልን አልሀምዱሊላህ እንላለን፣ ከከለከላችሁን ደግሞ አሏሁ አክበር እንላለን። •••✿❒🌹❒✿••• ረሱል ﷺ ወደ አኼራ ከተሻገሩ በኋላ የሙስሊሞች የበላይ ኸሊፍ ሁነው የተሾሙት አቡበክር አስ-ሲዲቅ ረዲየሏሁ ዐንሁ ነበሩ። ቢላል ረዲየሏሁ ዐንሁ ወደ ኸሊፋው በመሄድ እንዲህ አላቸው፦ አንተ የረሱል ﷺ ምትክ ኸሊፋ ሆይ እኔ የአላህ መልእክተኛ ﷺ ለአንድ አማኝ ብልጫ ያለው ስራ በአላህ መንገድ "ጅሀድ" ማድረግ ነው፥ ሲሉ ሰምቻለሁ። አቡበክርም (ረዲየላሁ ዐንሁ) "ቢላል ለመሆኑ የፈለግከው ነገር ምንድን ነው? አሉት። ቢላልም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) "እስክሞት ድረስ በ'ፊ ሰቢሊላህ' ላይ ለመሳተፍ እሻለሁ" አለ። አቡበክርም (ረዲከሏሁ ዐንሁ) ማን አዛን ያደርግልናል? አሉ። ቢላልም እኔ ከረሱል ﷺ በኋላ ለማንም አዛን አላደርግም አለ ዓይኖቹ እያነቡ። አቡ በክርም ረ.ዐ ቢላል ሆይ! እባክህ ከኛ ጋር ቀርተህ አዛን አድራጊያችን ሁን ? አሉት። ቢላል ረዲየሏሁ ዐንሁ ግን ቁርጥ ያለ አቋሙን አሳወቀ። "ከባርነት ያወጣኸኝ ለአንተ አገልጋይ እንድሆን ከሆነ ያሻህን መፈፀም ትችላለህ። ነፃ ያወጣኸኝ ለአላህ ከሆነ ለርሱ ተወኝ።" አቡበክርም ረዲየሏሁ ዐንሁ ቢላል ሆይ እኔ ነፃ ያወጣውህ ለአላህ ስል ነው አሉ። •••✿❒🌹❒✿••• ከዚህ በኋላ ስላለው የቢላል ረዲየሏሁ ዐንሁ ታሪክ መፅሀፍት የተለያየ አቋም ይዘዋል። ከፊሎቹ የአቡበክርን ረ.ዐ ተማፅኖ በመቀበል እሳቸው እስካሉ ድረስ በመዲና ቆይቶ ከዚያም ወደ ሻም ሂዷል ሲሉ። ከፊሎቹ ከመጀመሪያው ወደ ሻም በመሄድ ባሰበው መስክ በየጊዜው በጅሀድ በመገኘት ህይወቱን አሳልፏል ይላሉ። ያም ሆነ ይህ ግን ቢላል የመጨረሻ ህይወቱን እንደጅማሬው ሁሉ በ ጂሀድ ለማሳለፍ ችሏል። አዛን ዳግም ለመድረግ ግን አቅም አልነበረውም። "አሽሃዱ አንነ ሙሀመደን ረሱሉሏህ" የሚለውን ሐረግ ጮሆ ለማሰማት ሳግ ይይዘዋል...ዕንባ ያሸንፈዋል። የረሱል ﷺ ትዝታ በአዕምሮው ይቀረፃል ትንፋሽ ያጥረዋል። የመጨረሻ አዛን ያደረገው ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየሏሁ ዐንሁ ለጉብኝት ሻም በገቡበት ወቅት ነበር። የሻም ሰወች ቢላል አንድ ወቅት ሶላት እንኳን አዛን ያሰማቸው ዘንድ ዑመር ረ.ዐ ግፊት እንዲያደርጉ ጠየቁ። ቢላል ረዲየሏሁ ዐንሁ ተስማማ። አዛን አሰማ። እርሱና በረሱል ﷺ ዘመን የነበሩ ሶሐባወች በእንባ ተራጩ። በተለይ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁ እንባቸውን ለረጅም ጊዜ መግታት አልቻሉም። •••✿❒🌹❒✿••• ቢላል ረዲየሏሁ ዐንሁ በጅሀድ ፊ ሰቢሊላህ ላይ እያለ ከዚህ አለም በሞት ተለየ በሻም። •••✿❒ተፈፀመ❒✿••• @muaz_media
Mostrar todo...
👍 21
00:32
Video unavailableShow in Telegram
2.80 MB
👍 22💯 4
Photo unavailableShow in Telegram
🔔አዲስ ቪድዮ🔔 ሙስሊሞችን ያስቆጣው የኢማሙ ድርጊት https://youtu.be/OKqlSVl7EEY?si=qLH0Zh_4CbA1i_Qg @Muaz_Media // Like, Share,
Mostrar todo...
👍 19
✅ዛሬ አልያም ነገ ላንመለስ የምንጓዝ ከንቱ አላሚ ለከንቱ አለም የምንፈዝ የዘነጋን የነገውን የምናልም የዱንያውን ኪስ ላይኖረው ከፈናችን ይዘን ላንሄድ ይህ ሀብታችን ለምን ይሆን ዲንን ሽጠን ማደራችን ለዚች አለም ለጠፊ አገር መልፍታችን እያወቅነው እንደምኔድ ሁሉን ጥለን ምንድን ይሆን ያዘናጋን ? ምንስ ይሆን ያታለለን ? @muaz_media
Mostrar todo...
👍 29
ሐበሻው ቢላል ኢብኑ ረበሕ (ረድየላሁ አንሁ) ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ ክፍል 3⃣ ❒❒📖📖❒❒ ሙስሊሞች "አሏሁአክበር ....አሐድ ....አሐድ... " ሲሉ ይሰማል ኡመያ ይህን ቃል በሚገባ ያስታውሰዋል. ትናንት የቢላል ረድየላሁ አንሁ የጣር ድምፅ ነበር። አሁን ደግሞ የአዲሱ ትውልድ መፈክር ሁኗል። ልቡ ተሸበረ ሰይፍ ለሰይፍ ተፋተገ። አንገት ተቀላ። ከዚህም ከዚይም የጣር ድምፅ ይሰማል። ጦርነቱ ሊገባደድ ነው። የሙስሊሞች የኃይል ሚዛን ደፍቷል። ቁጥራቸው አነስተኛ ቢሆንም በአላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ እርዳታ ግዙፉን የቁረይሽ ጦር ድል በመንሳት ላይ ናቸው። ብልጣ ብልጡ ኡመያ ኢብን ኸለፍ ነፍሱን ለማትረፍ በመፈለጉ ዐብዱረህማን ኢብን ዐውፍ ረድየላሁ አንሁ በመባል ከሚታወቀው እውቅ ሶሐባ ዘንድ በመጠጋት እጁን ለመስጠትና ምርኮኛው ለመሆን እንደሚፈልግ ገለፀለት። ዐብዱረህማንም ረድየላሁ አንሁ ጥያቄውን በመቀበል ምርኮኞች ወደ ተሰበሰቡበት ቦታ እየወሰደው ሳላ ቢላል ረድየላሁ አንሁ ጋር ፊት ለፊት ተገናኙ። •••✿❒🌹❒✿••• በከፍተኛ ድምፅ፦ "የክህደት መሪ የሆነው ኡመያ ኢብን ኸለፍ እርሱ ነፃ ከወጣ እኔ ነፃ ልሁን!" በማለት ቁጭቱን አሰማ። ሰይፉን ወደሱ በማቅናትም አንገቱን በጥሶ ሊጥለው ሲዘጋጅ ዐብዱረህማን ኢብን ዐውፍረድየላሁ አንሁ ፦ ቢላል ሆይ ይህ ሰው ምርኮኛየ ነው። አለው። ቢላልም ረድየላሁ አንሁ ጦርነቱ አላቆመም ! ፍልሚያው ተጧጡፏል፤ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለን ምርኮኛየ ነው ትላለህ? አለው። በመቀጠልም፦ "ከጥቂት ደቂቃወች በፊት ሰይፉ በሙስሊሞች ደም የተዘፈቀውን ግለሰብ ምርኮኛዬ ነው ብለህ ልታድነው ትከጅላለህ አለው። ቢላል ረድየላሁ አንሁ ወንድሙን ዐብዱረህማንን ረድየላሁ አንሁ ብቻውን ማሳመን እንደተሳነው በመገንዘቡ ፦ እናንተ የአላህ ዲን አጋዦች ያ (አንሷረሏህ) የክህደት መሪ የሆነው ኡመያ ኢብን ኸለፍ እዚህ ይገልኛ.... ዛሬ ነፃ ከወጣ እኔ ነፃ እንድወጣ አልሻም...." በማለት አስተጋባ። ሙስሊሞች ኡመያንና አብሮት ከጦርነቱ የተሰለፈውን ልጁን ከበቧቸው። ዐብዱረህማን ረድየላሁ አንሁ ቦታ ለቀቀ። •••✿❒🌹❒✿••• ቢላል ረድየላሁ አንሁ ኡመያን በተጠማ ሰይፉ ከተፈው። "አሐድ...አሐድ..."የሚል መፈክሩንም አሰማ። በእርግጥ ቢላል አላህን የሚፈራና ሩህሩህ ሰው ነው። በኢስላም ላይ ከፍተኛ በደል የፈፀመውን እና እርሱንም ኢ-ሰብአዊ ድርጊት የፈፀመ በትን ኡመያ ኢብን ኸለፍን ግን ሊያዝንለት ይገባ ነበር ለማለት አንደፍርም ። ወቅቱ በኢስላምና በኩፍር (በክህደት) መካከል ወሳኝ ግብግብ የተፈጠረበት በመሆኑ በክህደት አራማጆች ላይ አይቀጡ ቅጣት ማድረስ አስፈላጊ ነበር። ቢላልም ረድየላሁ አንሁ እዚህ አኳያ ነበር ኡመያ በወቅቱ ነፃ መውጣት የማይገባው መሆኑን የወሰነው። - ቀናት ቀናትን ወልደው አመታት አለፉ። ነብዩ ሙሐመድ ﷺ ወደ መካ በድል ተመለሱ። "አሏሁ አክበር!" እያሉ ድምፃቸውን በማሰማት አስር ሺህ ሙስሊሞች መካን አጥለቀለቋት ወደ ካዕባም አመሩ ....... •••✿❒🌹❒✿••• "ቀናት ቀናትን ወልደው አመታት አለፉ። ነብዩ ሙሐመድ ﷺ ወደ መካ በድል ተመለሱ። "አሏሁ አክበር!" እያሉ ድምፃቸውን በማሰማት አስር ሺህ ሙስሊሞች መካን አጥለቀለቋት ወደ ካዕባም አመሩ። ይህን ቦታ ሙሽሪኮች ለማምታታት የጣዖት እምነትን ሲያንፀባርቁ ነበር። የጣዖታት ምስልም መናኸሪያ አድርገውት ቆይተዋል። .. እውነት.....ፈካ....ሐሰት ተነነ። በዚያች እለት ላት....ዑዝዛ...ሁበል.... የተባሉ ጣዖታት ቦታ አጡ። ሰወች ለድንጋይና ለታቦት መገዛታቸው አከተመ ሰዎች ከንግዲህ አንድና ሸሪክ የሌለውን አላህም ብቻ እንጅ ሌላ ኃይልን እንደ ማይገዙ እውን ሆነ። ነብዩ ሙሀመድ ﷺ መካ ሲገቡ እንደማንኛውም መሪ ሆታና እልልታ አልነበረም። ይልቁንም አንገታቸውን ደፍተው በከፍተኛ አደብ ነበር። •••✿❒🌹❒✿••• ከጎናቸው ቢላል (ረዲየሏሁ ዐንሁ) አለ። ከካዕባ ጣራ ላይ በመውጣትም በከፍተኛ ድምፅ "አዛን" ጥሪ እንዲያሰማ አዘዙት። በታላቅ ቦታና አጋጣሚ ሀበሻው ቢላል (ረዲየሏሁ ዐንሁ) "አዛን" አሰማ። በሺህ የሚቆጠሩ ሙስሊሞችም እርሱን በመከተል የአላህን መልእክት ደጋህመው አሰሙ። -በከፍተኛ የአላህ ፍርሀትና ደበብታ ። አጋሪወች የሚሰሙትን እና የሚያዩትን ማመን አልቻሉም። "እውን ሙሀመድ ድሀ ተከታዬቹ ትናንት ከሀገር እንዳልተባረሩ ዛሬ ሀገሪቱን ተቆጣጠሩ...?" - "ሙሀመድ አስር ሺህ አማኞችን ይዞ መምጣቱ እውን ነውን....?" - "ካገር ያባረርነው፥ የተጋደልነው፥ ተወዳጅ ቤተሰቦቹንና ወገኖቹን የ ገደልንበት ሙሀመድ እውን በድል መጣ" -"የፈፀምነውን ግፍ በመርሳት ሙሀመድ ሂዱ ነፃ ናችሁ! ብሎ ማሰናበቱ እውን ነውን...?" •••✿❒🌹❒✿••• ከላይ 👆 ﷺ ያላልንበት ምክንያት የሙሽሪኮች ንግግር ስለሆነ እና ይህን ንግግር ስለማይጠቀሙ ታሪክ ላለማዛባት ነው። ሶስት ሰወች ግን በካዕባ አካባቢ ተቀምጠዋል። የቁረይሽ መኳንንት ናቸው። ቢላል (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ጣዖታቸውን በእግሩ እየሰባበረ አዛን ሲያደርግ ሰምተዋል። አቡ ሱፍያን ኢብኑ ሀርብ፡ ዐትታብ ኢብኑ ኡሰይድ እና ሀሪስ ኢብኑ ሂሻም። ዐትታብ ዐይኑን በቢላል ላይ ጣል በማድረግ፦ "ኡሰይድን አላህ መልካም ውሎለታል። ይህን የሚጠላውን ነገር ሳይሰማ (ሞተ)" አለ። ሀሪስ ደግሞ "በአላህ ስም እምላለሁ ሙሀመድ ለዚህ ደረጃ የተገባ ነው የሚል እምነት ቢኖረኝ እከተለው ነበር" ሲል፥ በጥቂቱ ቀድሟቸው ኢስላምን የተቀበለው አቡ ሱፍያን ግን "እኔ አንድም ነገር ለመናገር አልሻም፤ ብናገር እንኳ ይህ ጠጠር ሳይቀር የተናገርኩትን ለሙሀመድ ﷺ ያደርሳል" በማለት ስጋቱን ገለፀ። ረሱል ﷺ ወደ ካዕባ በተጠጉበት ወቅት ተመለከቷቸው። በድል ደስታ በተሞሉ ዐይኖቻቸው ገረፍ ካደረጓቸው በኋላ...... የመጨረሻውክፍል ክፍል 4⃣ ይ ቀ ጥ ላ ል ኢሻአላህ................... •••✿❒🌹❒✿••• @muaz_media
Mostrar todo...
👍 23
ቁርዓን🌺 ውብ የሆነ ቲላዋ ማራኪ በሆነ ድምፅ ሱረቱል ካፍ✅ 🌺🌺🌺🌺🌺 👇👇👇👇👇 ቃሪእ አብደላ አልጆሀኒ                       ⇩   ╭┅━━•🍃⚘🍃•━━━┅ ⚘  ⚘ #መልካም #ጁምኣ @muaz_media
Mostrar todo...
2_5384501560128570525.mp319.41 MB
👍 20
👉 ከጁመዓ ቀን ሱናዎች ➊ ﺍﻟﻐﺴﻞ ➋ ﺍﻟﻄﻴﺐ ➌ ﺍﻟﺴﻮﺍﻙ ➍ ﻟﺒﺲ ﺍﻟﺠﻤﻴﻞ ➎ ﻗﺮﺍﺀﺓ ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻜﻬﻒ ➏ ﺍﻟﺘﺒﻜﻴﺮ ﻟﺼﻼﺓ ﺍﻟﺠﻤﻌﺔ ➐ ﺍﻹﻛﺜﺎﺭ ﻣﻦ ﺍﻟﺪﻋﺎﺀ ﻭﺍﻟﺼﻼﺓ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻨﺒﻲ ገላን መታጠብ ሽቶ መቀባት ለወንዶች ሲዋክ መጠቀም ጥሩ ልብስ መልበስ ሱረቱ ከህፍን መቅራት በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት ማብዛት (( ﻗَﺎﻝَ ﺭَﺳُﻮﻝَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﷺ ﻣﻦ ﻗﺮﺃ ﺳﻮﺭﺓَ ﺍﻟﻜﻬﻒِ ﻓﻲ ﻳﻮﻡِ ﺍﻟﺠﻤﻌﺔِ ، ﺃﺿﺎﺀ ﻟﻪ ﻣﻦ ﺍﻟﻨﻮﺭِ ﻣﺎ ﺑﻴﻦ ﺍﻟﺠﻤُﻌﺘَﻴﻦ )) የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ((የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃንን ያበራለታል)) ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺠﺎﻣﻊ - ﺭﻗﻢ : ‏( 647 👉በጥቅል ጁሙኣ ቀንን በኢባዳ ልንለያት ይገባል قال الإمام ابن القيم رحمه الله وهو يتحدّث عن خصائص يوم الجمعة: ኢብኑ ልቀይ አላህ ይዘንለት ስለ የውመል ጁሙኣ የጁሙኣን ቀን በተመለከተ ኢንዲህ ይላል። " إنه اليوم الذي يُستحب أنْ يُتفرغ فيه للعبادة، የጁሙኣ ቀን ማለት ኢባዳ ለማስራት ሲባል የተላያዪ ሚያዘናጉ ነገሮችን ትቶ ዝጎጁ የከሚኮንበት ቀን ነው። وله على سائر الأيام مَزِيَّةٌ بأنواع من العبادات، واجبة ومستحبة، ለጁመኣ ቀን ከተለያዩ ቀናቶች የሚለይበት የኢባዳ አይነታዎች ከወጅብም እና ከሱና አሉ። * فالله سبحانه جعل لأهل كلِّ ملة يومًا يتفرغون فيه للعبادة، ويتخلون فيه عن أشغال الدنيا، فيوم الجمعة يوم عبادة، ለሁሉም ህዝብ (ኡማ) ለኢባዳ ዙጎጁ የሙሆኑበት ከዱንያ ሹጉል የሚያገሉበትን ቀን አድርጎዋል ። የጁመኣ ቀን የኢባዳ ቀን ነው ። * وهو في الأيام كشهرِ رمضانَ في الشهور، وساعة الإجابة فيه كليلة القدر في رمضان؛ የጁመኣ ቀን ከቀናቶች መካካል ሲነፃፀር ረማዷን በወራቶች መካከል እንዳለው ደረጃ ነው ። በጁማኣ ቀን ያለችዋ ዱኣ ኢስቲጃባ የሚሆንባት ሳኣት በረማዷን ላይ እንዳለችዋ ለይለቱል ቀድር ነች ። ° ولهذا من صح له يوم جمعته وسلم، سلمت له سائرُ جمعته، ومن صح له رمضان وسلم، سلمت له سائر سنته، ومن صحت له حجته وسلمت له، صح له سائر عمره ለዚህም ሲባል ጁምኣው ሰላም የሆነለት እና የተስተካከለለት ከጁሙኣው የተቀራው ጌዜ ሰላም ይሆንለታል ይስተካከልለታል ረማዷኑ የተስተካከለለት እና ሰላም የሆነለት አመቱ ይስተካከልለታል ሰላምም ይሆንለታል ሀጁ የተስተካከለለት እና ሰላም የሆነለት ኢድሜው ሰላም ይሆንለታል ይስተካከልለታል ። 《فيوم الجمعة ميزان الأسبوع، ورمضان ميزان العام، والحج ميزان العمر》. የጁሙኣ ቀን የሳምንቱ ሚዛን ነው ረመዳን የአመቱ ሚዛን ነው ሀጅ የኢድሜው ሚዛን ነው ። 📚ምንጭ ዛድ አልመኣድ 📚من كتاب زاد المعاد ➬➬➬➬➬ @muaz_media
Mostrar todo...
👍 17