cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ፍቅር ካፌ

🌹🌹የፍቅር ታሪኮች🌹🌹 🌹🌹የፍቅር ጥቅሶች🌹🌹 🌹🌹አስተማሪ ፅሁፎች🌹🌹 🌹🌹የፍቅር ግጥሞች🌹🌹 🌹🌹 🌹🌹ፍቅር ካፌ 🌹🌹 https://t.me/joinchat/AAAAAE-PukcYjyqNj6fang join እና sahre በማድረግ ቤተሰብ እንሁን ሀሳብ አስተያየት እና cross ለምትፈልጉ @Fertuyeeee ላይ አናግሩኝ

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
383
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

"ያኔ አገባሻለው" ውበትሽ ሲረግፍ ውብ ፀጉርሽ ሲነጣ ሰውነትሽ ከስቶ መገፋት ሲመጣ አውሬ መስለሻቸው ሲገፉሽ ሲንቁሽ ጓደኛ ሲከዳሽ አናውቅሽም ሲሉሽ ሀዘንሽ አይሎ መኖር ሲያስጠላሽ ስምሽን ሲክዱ ያን ውብ መጠሪያሽ ..... ያነባሽው እንባ በጉንጮችሽ ሲወርድ አጠርግልሻለው ሰዎች በገፉሽ ልክ ሰው ሆኜ መጥቼ ያኔ አገባሻለው....!!! @ሚኪ "2014"
Mostrar todo...
"ናፍቆት" ~ ~ ~ // ~ ~ ~ ~ የናፈቁትን እየዳሩ የወደዱትን እየሞሸሩ (ዐለምን የምን እሹሩሩ) አንዴ ከሆነ ወዲያ ቢባል ሆዴ ባባ (እንደው ምን ሊረባ?) የወደዱት እንዲሳም ሌላን ሲታቀፍ ላያድኑት አበባን ከማርገፍ... እንደው መቀባጠሩ ላይቀየር ነገሩ ( እሱ ነው መለየት ሽሩ ) እኔማ እንሆነው ያልኩሽን ከሌላ ከሆንሽው "ነገ" ያልኩሽን ተስፋ የትም ካደረግሽው ሁሉን በነበር ሲቀር ቅፅበትም ሲያስፈራ ህይወት እንደዚህ ናት ያልዘራሽውን የምታፈራ። ታውቂያለሽ??.... አልዘራሁም አንቺን ማጣት ግን (አጭዳለሁኝ ቅጣት) አልዘራሁ... አልዘራሁ መለየት ግን (አጨድኩኝ መሸኘት) አልዘራሁ መራራቅ (ነገዬ ታየኝ እንደጭራቅ).... እንደልጅነቴ ልክ እንደ'አያ ጅቦ ማጣት ሲያሰፈራራኝ በሰው አፍ ታጅቦ "ይበላሀል!!" ሲሉኝ ጥቅልል ሽፍን ብዬ እንዲያ ነው ምፈራው መለየት አንቺዬ...። እኔማ ያንን አያ ጅቦ ባልፍም ተድበስብሶ መለየት ግን በላኝ ያውም "ከጅብ" ብሶ።..... --------- ---------- ----------- @ሚኪ12 2014.....
Mostrar todo...
"አፋቸው ላይ ስምሽ ሲያምር" ~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ምን ሆኜ ወደድኳት?? ያውም ያልለመድኳት ቀልቡ እንደራቀው ስል እምራቀቀው (እግዜሩ ይወቀው) በዝናባም ሰማይ አንቺን የማስሰው ከዚህ ሁሉ ፍጡር ከሚርመሰመሰው ምንሽን ብቀምሰው? ምንሽን ብለብሰው? (እግዜር ይመልሰው) እርሜን በወደድኩሽ እርሜን ብናፍቅሽ አንቺም ተራምደሽኝ ገስግሰሻልና አርሞኒካ ጥዬ ለመድኩኝ በገና። ቢጤዎቼ መተው "ጨከን ነው" ሲሉኝ እኔም ይኸው ጨከን "ቆምጠጥ" ነው ሲሉኝ እኔም ይኸው ቆምጠጥ ሲሉኝ እየመጡ "ምንድነው መንሰቅሰቅ? ፍቅር ገለመሌ ያውም ለእገሌ አቦ ተዋት" ሲሉኝ "ተውና መንፈቅፈቅ" ሲጠሩ ሲያነሱሽ ባሰብኝ መናፈቅ። የከበበኝ አጀብ እንድተውሽ ብሎ ክፉ ቃል ሲያሰምር እኔ ግን እላለው አፋቸው ላይ ስምሽ ሲያምር። ¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤ ሰኔ 2014
Mostrar todo...
ሚኪ እውነታቸውን ነው?? ======================== የመታሽ ክንፍሽን የቀማሽ ሳቅሽን ማነው?? እኔን እኔን የኔ 'ርግብ አልችልም ሆኖ ነው ከአለም ግብግብ አልችልም ሆኖ እንጂ ባሁኑ ቦታዬ እኔማ እንደድሮ ባቅፍሽ ነው ደስታዬ /ብስምሽ ደስታዬ/ ልጠይቅሽማ ተለያየን ማለት ያስብላል ምን ግዴ? ሰው ትዝታ ሲሆን አቧራ ነው እንዴ?? ተለያየን ማለት ፍቅራችን በነነ ተለያየን ማለት ፍቅራችን ተነነ /..... ማለት ይሆን እንዴ?/ እኔማ ተለይቼሽ እንኳ መውደቅሽ ያመኛል ማዘንሽ ያመኛል ማኩረፍሽ ያመኛል ሰው ግን ይመጣና "አልወጣችልህም ማለት ነው" ይለኛል። ይሄስ.... እውነታቸውን ነው??? 💔 ~~~~~~~~~~~~~ @ሚኪ12 2014 ሰኔ
Mostrar todo...
#ሚኪ "ያለ እሱ አልበላም እሱ ካለ አልበላም!!" ~~~~ ናፍቃኝ ስለነበር ደወልኩላት - ስልኳን አታነሳውም ደገምኩ - አታነሳም ስልኬ ድንገት ጮኸ ሳይቆይ ከፈትኩት - "sorry i can't talk" እውነት አላት ሰዎች ጥንካሬያቸው የሚለካው ባለመውደድ(ማፍ) ነው። ሰዎች ጎበዝ የሚባሉት በንቀታቸው መጠን ነው። ንቀህ እለፈው ያሉን የት ድረስ ተከተሉንና...? ወንድ ልጅ አፉ እጁ ነው..ካለተማታ ምኑን ወንድ ሆነ በሚል ማህበረሰብ ውስጥ ፂም አበቀልኩ - ልጅ እያለን እራሱ ተመተህ እንዳትመጣ!! ተብለን ነበር እኔ ግን ይሄን አምናለው #መጀገን የሚለካው ውለታን በማክበር ልክ ነው። ፍቅር ማለት ምን ማለት ነው?? - አጭር መልስ "ውለታ"። ውለታ ምንድነው - ለምትወደው ሁሉ ነገርህን ማዋል..ራስህም አብረህ መዋል። ይሄ የሌለው ፍቅር ታቦት የሌለው መቅደስ ነው። .... ለሊቴ ተዛባብኝ አውቃለው ሰዎችን መክሬ...ለራሴ ሳልሆን 😏 ጭንቀትን መገላገያ ብዬም ብዙ ሞክሬ ነበር ስብከቶች መዝሙሮች ዘፈኖች ሞቲቬሽን...ሰማሁ የለም እንቅልፌ። የማታ ፍልስፍና 1 ወንዱ በወደደችው ሴት ልክ መኖሩን ያስረግጣል ሴቷ ማንም አያሸንፈውም የተባለውን ወንድ በማሸነፏ የሴቷ የውበቷ መለኪያም ተደርጎ ተነግሯት ይሆናል ግን ይሄ ሁሉ ለምን ሆነ ቢሉ "የበላይነት" ነው። ....."የደወሉላቸው ደንበኛ ስልክ" እኔ እያሰብኩኝ እጄ ሌላ ስራ ሰራ... ደወለላት - ዘግታዋለች ግን ይገርማል ሁሉም ነገር ይቀየራል። ፍልስፍና 2 ሁሉም እንደነበረው አይቀጥልም ብዬሽ አልነበር። ይኸው ... ...ለማውራት ጊዜ ያነሰብሽን ሰው ለመስማት ጊዜ ታጪለታለሽ ... ያለ እሱ አልበላም ያልሽውን ሰው እሱ ካለ አልበላም ማለትሽ አይቀርም.. #2014 @ሚኪ12
Mostrar todo...
"የማታ እንጀራ" የማታ እንጀራ ስጠኝ የጠዋት አታስመርጠኝ ዘግይተህ በሁዋላ አስጊጠኝ ማታ በክብሬ ደብቀኝ ከሰው በር አንተው አርቀኝ ጉልበቴ ፅናቱን ይዞ አቅሜም እንደአቅሙ ተጉዞ ያልጠየቁኝን ሳልመልስ መንገዴን በወግ ልጨርስ... በዐይን እሳት አታስገርፈኝ ማታ አመሻሹን ደግፈኝ በጥላ እንዳልበረግግ በረፋድ እንዳላጣ ጥግ አልጠብቅ እርጥባን ከሰው የማታ ምግቤን አርሰው ሲመሻሽ አታንበርክከኝ ሲደክመኝ ወንዝ አታሻግረኝ ሲጨንቀኝ ከእኔ አትራቀኝ እንደንጋቱ ጠብቀኝ አንገቴ እንዳለ ቀና የወዳጅ ደጃፍ ሳልጠና "ዘራፍ!!" እንዳልኩኝ ያብቃልኝ ሲጨልም መንገድ አቅናልኝ አደራ!! ጌታዬ አደራ!! አትንሳኝ የማታ እንጀራ! #አለምፀሀይ ወዳጆ
Mostrar todo...
#ሚኪ (አሁን ማልቀስ እችላለው??...) "ጎበዝ አይደለህ ?" ትላለች እናቴ "አዎ" እላታለው በኮልታፋ አንደበቴ "ታዲያ ጎበዝ ህፃን ልጅ ያለቅሳል??" ትለኛለች ማልቀሴን እንድተው የመጣውን የእንባዬን ዶፍ ዋጥ አድርጌ "አያለቅስም" እላታለው ... "እኮ ዝም በላ" ታባብለኛለች ብብቷ ስር ከታ እኔም ዝም እላለው በትንሽ ጆሮዬ ድምጿ አስተጋብታ... የሁልጊዜ እንባዬ ገና ሳይመጣብኝ "ጎበዝ ህፃን ልጅ ያለቅሳል?" ስትል አፌ ዝም ብሎ ጭንቅላቴ አያለቅስምን ያሳያታል... በዛ ለምዶ አመል መጥፎ እንባ ሊወርድ ተሰልፎ ይኸው ሊወርድ የነበረው ተመለሰ የልጅነት ያን ምክሯን አስታወሰ... አመታት አለፉ... አሁን ደረስኩልሽ ከፎቶሽ ስር ቆሜ አይንሽን ለማየት አይችልም አቅሜ "እናቴ አሁን አድጌያለው?? ትልቅ ሆኜ አይደለሁ??" ብዙ የዋጥኩት ሀዘን አለኝ አሁን ማልቀስ አችላለሁ?? @ሚኪ12 2014
Mostrar todo...
#ሚኪ "ያልሽውን ሆኛለው" ... ምኞትሽን ሰምቼ ልሁን ያልኩኝ ሰሞን እራሴን አፍርሼ የምትፈልጊውን ሰው ደረስኩ እስከመሆን... ሞክሬ ....የምትፈልጊውን ልሆን እየጣርኩኝ ዳክሬ .... ልክ እንደምኞትሽ ላድር እየሻትኩኝ ለካ... የራሴን ማንነት ንጄው እንደዘበት ተገኘሁ ቀልዬ ከራሴው መ'ሰረት አይገርምሽም....?? ቀለልኩ እንደንፋስ አንቺን ካገኘሁሽ ከዚህ አለም ብጠፋስ.... እያልኩ አስባለው... ደሞ ...ናፍቀሽኛል ደሞስ ሰው አይደለው...?? ብዙ አላዋቂዎች ሰለቸኝ ወሬያቸው "ለሴት ብለህ" ሲሉኝ "ለፍቅር" አልኳቸው ..........እሰይ አሳፈርኳቸው አይ ብታይኝ ኖሮ... ስንቱ ነው ሚተከል ስንቱስ ነው ሚነቀል አንድ አንቺን ፍለጋ ህልምሽን ለማከል... ስንት ለሊት ሁሉ እንቅልፌን እንዳጣሁ አይገባሽም እንጂ... አንቺ አላጠፋሽም እኔው ነኝ ያጠፋው ምን ቀረኝ ብለሽ ነው?? ማነው እሱ እስክባል ተቀየረ እስክባል... እውነቱን ልንገርሽ...? 'ትላንቴን' ....'ዛሬዬን' ...'ነገዬን' ጨክኜ አርጄያለው በይ ውደጅኚ ልይሽ ያልሽውን ሆኛለው.... -------//----------//---------//--------- @ሚኪ12
Mostrar todo...
#ሚኪ እንደ እናቶች ያለ እምነት እንደ እናቶች ያለ ጥበብ #እለምንሀለው ==================== #ፀሀዬ የ'ኔ ፀሀይ.... ክፉዎች ይርገፉ መቼም ላትጠልቂ በርተሽ አስረሻቸው ፀሀዬ ድመቂ ድመቂ... ጽደቂ ፍኪ ተፍነክነኪ ብሪ... ብረሪ ከንፈሽ በአክናፍሽ ዝሪ፣ ፍጠሪ..... ነፍስን እፍ ብለሽ ከራስ በላይ ይሁን ብርሀንሽ ይድመቅ በጥላሽ ምስል ነው ህያውነት 'ሚደምቅ የ'ኔ ቅኔ.... ፀሀዬ ት'ግስቴ.... አበርቺኝ እናቴ.......! ❤❤❤ @ሚኪ2014
Mostrar todo...
#ሚኪ የእናትን መዳፍ እግዜር ከምን ሰራው?? በጠቆረ ቁጥር እጥፍ የሚያበራው ``````` ከአለም ሁካታ አለም እየናጠኝ ምን እሆን ነበረ እጅሽን ባይሰጠኝ ገና ስትነኪኝ እጅሽን በራሴ አርፎ የሚያሸልበው ነውጠኛው መንፈሴ። የኔ እናት `````` እኔ ስለሰልስ መዳፍሽ ሲሻክር ውለታ ልመልስ አልገባም ክርክር አላሰላስልም ጨረቃን`ፀሀይን ቀኔን የምቆጥረው በእናቴ አይን ''''''' የእናትን ተረከዝ ከምን አበጃጀው ከመንገዷ ቀድሞ እግሯ የሚያረጀው... -------------- @ሚኪ 2014....
Mostrar todo...