cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Abu mahir lbnu kedir

የዚህ ቻናል አላማው ኢስላማወዊ ትምህርቶችን በቁርኣንና በሀዲስ ማስረጃ ተደግፎ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ስለዚህ ሙስሊም ወንድሞችና እህቶቻቹን አድ በማድረግ ተባበሩን ጀዛኩም አሏሁ ኸይር

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 514
Suscriptores
Sin datos24 horas
-77 días
+630 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ بسم الله الرحمن الرحيم ጥቂት ዳሰሳ ስለ ኹለፋኡ ራሺዲን መስጅድና መድረሳ ቁጥር -1 በቅድሚያ ለአለማቱ ጌታ ምሰጋና የተገባው ነው፡፡ ኹለፋኡ ራሺዲን መስጅድና መድረሳ በ2007 ዓ/ል በወረሃ ነሐሴ የመስጅዱ ቦታ ለመግዛት የዛሬ አያድርገውና ሁሉም ሰላም በነበረበት ወቅት /አሁንም ሁሉንም ወደ ሰላም ወደ ትክክለኛው መንሀጅ ይመልሰውና/ በቆዳና ሌጦ /በሙሳ ራማሽ መስጅድ/ ውይይት ተደረገ፡፡ በዚህ ውይይት ላይ በከተማው ውስጥ የሚኖሩ ሰለፊዮች በጋራ በመሆን ሹራው ተካሄድ ፡፡ በዚህ ሹራ ላይ ለቦታው ግዢ የሚሆን መዋጮ ይሰብሰብ ተብሎ 11000 (አስራ አንድ ሺህ ብር/ ተሰበሰበ፡፡ በዚህም በመነሳሳት የጀማው ፍላጎት በማየት አይደለም የመስጅዱ ቦታ ብቻ መግዛት መስጅድ መስሪያም ያዋጣል በማለት ቦታው በቀብድ ብቻ በመክፈል 500 ካሬ ሜትር ቦታ ተገዛ፡፡ በተገዛውም ቦታ 72 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ቆርቆሮ በቆርቆሮ ተሰራ፡፡ እንዲህ እንዲህ እየሆነ መስጅዱ ለከተማው ሁለተኛ የሱና መስጅድ በ2008 ዓ/ል ተሰርቶ ለምዕመናኑ ለስግደት፣ ለቂራትና በተለያዩ ኡስታዞች እና መሻኺዎች ዳዕዋ ለማድረግ በቃ፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ የመስጅዱ ቦታ መስፋፋት አለበት ብሎ የመስጅዱና የመድረሳው ኮሚቴ በ2012 ማስፋፊያ የሚሆን ቦታ ለመግዛት ውይይት ከሀገር ውጭም በሀገር ውስጥም ካሉ የሱና ወንድምና እህቶች ጋር መመካከር ጀመረ፡፡ ምክክሩም ፍሬ አፍርቶ በ2013 ዓ/ል ከመስጅዱ በቂብላ በኩል 265 ካሬ ሜትር ከነበረው ቦታ ላይ ባለው አቅም ግዢ መፈጸም ቻለ፡፡ አሁንም ይህ ቦታ ለግንባታ በቂ አይሆንም በማለት ተጨማሪ ግዢ ለመፈጸም አቅም ባይኖርም በብድር ለመግዛት ተነሳሳ ፡፡ በዚህ በተነሳሳ ሰዓት ሀገራዊ የመንሀጅ ይባስ ብሎ በከተማችን የመንሀጅ ችግር በሰፊው በሱና ወንድምና እህቶች ላይ ክፍተት መፈጠር ጀመረ፡፡ ያኔ የመስጅዱና የመድረሳው ኮሚቴ ባለበት ቆም በማለት ቅድሚያ የመንሀጅ ጉዳይ ይብሳል በማለት እይታችንንና ትኩረታችንን ሙሉ በሙሉ በሆነ ሁኔታ ወደዛው መንሀጃዊ ጉዳይ ሆነ፡፡ በዚህም ጊዜ ሀገራችን ባሉ ዱዓቶችና መሻኺዎች ዳዕዋ በመጋበዝ ለአብነትም በመጀመሪያ ዑስታዝ ሸምሱ ጉልታ(አቡ ሀመውያ) ዳዕዋ አደረገ በመቀጠል በኡስታዝ ሙሀመድ አልወልቂጤ በከተማዋ በነበረው ነባራዊ ሁኔታ ፕሮግራም እንዲሰጥ ተደረገ ፣ በተጨማሪም በዑስታዝ ሻኪር ሱልጣን እና በሼህ አብዱልሀሚድ አለተሚ ዳዕዋ እና ኮርስ እንዲሰጡ ተደረገ ፣ በመቀጠልም ዑስታዝ ባህሩ ተካ ፣ ሼህ መህቡብ ከሳንኩራ ፣ ሼህ ሀሰን ገላው እና ሼህ ዩሱፍ አህመድ ከባህርዳር የዳዕዋ ፕሮግራም ተይዞላቸው ዳዕዋ አደረጉ። በተጨማሪም ከመንገድም ሲያልፋ በማረፈም ጭምር ምክር በመለገስ ዶክትር ሼህ ሁሴን አስልጢይ ፣ ሼህ ጧሀ ኸድር ፣ ሼህ አብድልከሪም ከጅማ እና ሌሎች ኡስታዞች በተገኘው አጋጣሚ ዳዕዋ ተደርጓል፡፡ በከተማዋ እና በአከባቢው በመንሀጅ ጉዳይ ሲባባሱ ተባረሩ የተባሉት ደረሶችን አቅፎ በመያዝ መስጂድ የለንም ብለው እንዳይቦዝኑ እና ኡስታዞቹ የዳዕዋ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ተደረገ ። በዚህ በተጨማሪ በከተማው ውስጥ ክፍተቶቹ ሲባባሱ የጁማዕ ሶላት በዚሁ መስጅድ 1444ኛው ዓመተ ሂጅራ ረመዷን ወር ላይ ተጀመረ፡፡ ከዚህ በኋላ ከተማው ውስጥ የጁማዕ ኹጥባ ለማቅረብ የማይቀርቡ የነበሩ ዑስታዞችን ማለትም ዑስታዝ ኑራዲስ እና ዶክተር ሸምሱን በመጋበዝ ኹጥባ ከመስጅዱ ካለው ኢማም/ዑስታዝ/ ጋር በመቀያየር ማድረግ ጀመሩ፡፡ ይህ በንዲህ እያለ በ2016 ጉንችሬ በነበረው ሀገራዊ ሙሀደራ ላይ የነበሩ መሻኺዎችና ዱዓቶች ወደ ከተማችን በመጋበዝ ዳዕዋ አደረጉ፡፡ በዚህም ቀን ታዳሚው ያለን ቦታ ተብቀቅቶና ተጠጋግቶ የሙሃደራውን ፕሮግራም ታዶሞ ቢሄድም የነበረው መጨናነቅ በመገንዘብ ከዚህ በፌት የነበረው የቦታ ማሰፋፊያ ፕሮግራም ዳግም እንቅስቃሴ ማድረግ ተጀመረ ፡፡ በዚህም እንቅስቃሴ ከዚህ ቀደሙም ከሀገር ውጭ ባሉ እህቶቻችን በማነሳሳት ሌሎችም ወንድሞቻችንን በመጨመር በሀገር ውስጥም በጁማዕ ሶላትና በኢድ ሶላት እና በሌሎች እንቅስቃሴ በማድረግ ተጨማሪ 250 ካሬ ሜትር መግዛት ተቻለ፡፡ በመጨረሻም እነዚህ የተገዙ ቦታዎች ላይ በቂ ባይሆንም ሁሌም ቦታ ብቻ መግዛት ሳይሆን በጊዜ ሂደት እንደአስፈላጊነቱ ማሳፋፊያ ይደረጋል ብሎ በማሰብ አሁን ግን ግንባታ መጀመር ያስፈልጋል በማለት የመስጅዱና የመድረሳው ኮሜቴ በጥልቀት ተወያይቶ የዲዛይን ስራ ማሰራት ጀመረ…………… ስለሆነም ለዚህ ግንባታ ከሀገር ውጭም ውስጥም ያላችሁ በተለይም የከተማው ተወላጅና ነዋሪ የሱና ወንደምና እህቶቻችን የሆናችሁ ከጎናችን በመሆን ይህንን መስጅድና መድረሳ ግንባታው በተለመደው ትብብር እና ድጋፍ ዕውን እናድረግ ይላል የኹለፋኡ ራሺዲን መስጅድና መድረሳ ኮሚቴ። https://t.me/butajira_akababi (https://maps.app.goo.gl/Xy9umwAkJsLpkiYF7) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ /የከተማና የኢንዱስትሪ ማዕከል/ ሰኔ 18 ፣ 2016 ዙልሂጃ 25፣ 1445
Mostrar todo...
የቡታጅራና አካባቢው የሠለፊዮች ጀመዓ (የኹለፋኡ ራሺዲን መስጅድና መድረሳ ጀማዕ) ገተማ

(የኹለፋኡ ራሺዲን መስጅድና መድረሳ ጀማዕ) ኹለፋኡራሺዲን መስጅድ እና መድረሳ አካውንት 1000436020507 ንግድ ባንክ 0023244120101 ዘምዘም ባንክ (ሱና የሚጠፋው በጃሂል ድፍረትና በዓሊም ዝምታ ነው።)

https://maps.app.goo.gl/Xy9umwAkJsLpkiYF7

ሸይኽ ሙቅቢል ረሂሙሁሏህ ጫት ዘካ አለዉ እንዴ ተብለው ተጠየቁ❓አው አለዉ አሉ ምንድነው ዘካው ተባሉ ነቅሎ መጣል ነው አሉ 👌 https://t.me/Abumahiraselefiy https://t.me/Abumahiraselefiy
Mostrar todo...
Abu mahir lbnu kedir

የዚህ ቻናል አላማው ኢስላማወዊ ትምህርቶችን በቁርኣንና በሀዲስ ማስረጃ ተደግፎ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ስለዚህ ሙስሊም ወንድሞችና እህቶቻቹን አድ በማድረግ ተባበሩን ጀዛኩም አሏሁ ኸይር

Photo unavailableShow in Telegram
📢 ምዝገባ ጀምረናል 👉 እነሆ ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል ክረምቱን ልዩ በሆነ መልኩ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 9:20 ሰኣት (ቀን ሙሉ) ከሐምሌ 1 እስከ ነሃሴ 30 ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቆ ምዝገባ መጀመሩን በታላቅ ደስታ ይገልፃል!! የሚሰጡ የሸሪዓ ትምህርቶች 🔹ቁርኣን ከቃዒደቱ ኑራኒያ ጀምሮ 🔹ዐቂዳ (እምነት ነክ ስለ ተውሂድ…) 🔹ፊቅህ (ስለ ጡሃራ፣ ሶላት…) 🔹ሲራ   (የነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እና የሶሃቦችን ታሪክ…) 🔹ነቢያዊ ሐዲሶች… 🔹አደብ (ኢስላማዊ ስርኣት…) ✅ በፍጥነት በማስመዝገብ ልጆች በጊዜያቸው እንዲጠቀሙ ያድርጉ!! 🕰 የምዝገባ ቀን:- ከሰኔ 17 እስከ ሰኔ 28 ሰኣት:- በሁሉም ቀናት ከቀኑ 10:00 እስከ 12:00 ✅ ልብ ይበሉ! ሸሪዓን በጠበቀ መልኩ ሴቶችን በሴት ወንዶችን በወንድ ኡስታዞች እናስተምራለን 🏢 ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል አድራሻ:- አለምባንክ ከኦርዶፎ ህንፃ ፊትለፊት ወደ ቤተል በሚወስደው ኮብልስቶን መንገድ ከድልዲዩ በስተቀኝ እንገኛለን 📞Tel:+251920908031 የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://t.me/DarASSunnah1444 https://t.me/DarASSunnah1444
Mostrar todo...
ከአሉ ተባለ ወሬ ተከልክለናልና እንጠንቀቅ!! ——— አሎባልታ ወሬ ብዙዎችን በተለያየ መንገድ አክስሯል!! አሉ ተባለ ወሬ በማህበረሰቡ ላይ ጉዳቱና መዘዙ የከፋ ስለሆነ ሸሪዓችን አጥብቆ ከልክሏል። ከወርራድ አስሰቀፊይ ተይዞ እንዲህ አለ:- ሙዓዊየህ ወደ ሙጊረህ ቢን ሹዕበህ እንዲህ በማለት ፃፈ፣ ከአላህ መልክተኛ ﷺ ከሰማሀው ምክር የሆነ ነገር ወደኔ ፃፍልኝ አለው፣ ሹዕበህ ኢብኑ ሙጊረህም እኔ ከመልክተኛው ﷺ የሚከተለውን ሲሉ ሰምቻለሁ በማለት ፃፈለት:- “አላህ ሶስት ነገሮችን ጠልቶላችኋል፣ አሉ ተባለን፣ ገንዘብን ማባከንና ጥያቄ ማብዛትን።” [ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት ሶሂህ ሀዲስ ነው።] በዚህ አሉ ተባለ ወሬ ስንቱ ሱሰኛ ሆነ?! ስንቱ ከቂርኣት (ከደርስ) ርቆ በዚህ ተጠመደ?! ያውም የበለጠ ከማበላሸት ውጭ ሊያስተካክለው በማይችለው ነገር ላይ ገብቶ ስንቱ ተጠመደ?! ስንቱ ነው በእንዲህ ያሉ ወሬዎች ተጠምዶ እውቀት ፈላጊ ምስኪኖችን ከደርስ ያቋረጠው?! ስንቱ ነው በዚህ መልኩ ለቢድዐህ ባለቤቶችና ለአስመሳዮች በር የከፈተው?! ስንቱ ነው በዚህ ተግባር ተዘፍቆ ከድሮ ጀምሮ ወደ ቡድንተኝነት (ተሀዙብ) ያመራው?! እንንቃ!! ጎበዝ ጊዜያችን አናባክን!! ወዳጅነትን አሻክረው በጀመዓ ላይ ክፍተት እንዲፈጠር ሰበብ ከሚሆኑ ተግባሮች እንራቅ!! አሉ ተባለ ወሬን አጥብቀን ተጠይፈን እንራቅ!! ታላቁ ፈቂህ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- “በአሉ ተባለ ወሬ፣ ጥያቄን በማብዛትና ጊዜን በማባከን መወጠር (ቢዚ busy) መሆን በሰዎች መካከል ከተንሰራፋ በእውነቱ በሽታ ነው!! አላህን ጤነኛነትን እንጠይቀዋለ!!። ይህ ተግባር እንደ ትልቅ አንገብጋቢ ጉዳይ ይሆንበታል፣ በል እንዲያውም አንዳንዴ (በዚህ ተግባር ያልገጠመውን) ጥላትነት ለማይገባው ሁሉ ጥላትነትን ይጠቀማል፣ አለያም ደግሞ (በዚህ ተግባር ስለ ገጠመው ብቻ) ወዳጅነት የማይገባውን ወዳጅ ሊያደርግ ይችላል። ወደዚህ ደረጃ የሚደርሰው፣ ለዚህ እውቀትን ከመፈለግ አርቆ ውጥረት ውስጥ ለከተተው (ለአሉ ባልታ ወሬ) ከሰጠው ትኩረት የተነሳ ነው። እንደ ማስረጃ የሚያቀርበው ደግሞ ሀቅን መርዳት ነው የሚል ነው። እውነታው ግን እንደዛ አይደለም!። ይልቅ እውነታው ነፍስንም ሆነ ሰዎችን በማይመለከታቸው ነገር ውጥረት ውስጥ መክተት ነው!!። የሆነ ወሬ ሳትፈልገው መምጣቱ ግን ውጥረት ውስጥ ሊከትህ አይችልም፣ እንደ ወሬ ማንኛውም ሰው ዘንድ ሳይፈልገውና ለወሬው ቦታ ሰጥቶ ሳይዘጋጅለት ሊመጣው ይችላል ነገር ግን ቦታ አይሰጠውም፣ በሱ ውጥረት ውስጥ አይገባም!!። ትልቅ ትኩረት የሚሰጠውም ጉዳዩ አይሆንም!! ምክንያቱም እውቀት ከመፈለግ ያዘናገዋል፣ ነገሮችንም ያበላሽበታል፣ በማህበረሰቡም ውስጥ የቡድንተኝነትን በር ይከፍታል፣ በዚህ ሰበብም ኡመቱ ለመከፋፈል ይበቃል።” [መጅሙዕ አል-ፈታዋ 26/127] ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) በድጋሚ ተፍሲሩ ጁዝእ ዐማ ገፅ 197 ላይ እንዲህ አሉ:- “በእኛ ላይ ግዴታ የሚሆነው ፊትናዎችን ግልፅ የወጡትንም ይሁን በድብቅ የሚሰራጩትን መጠንቀቅ ነው!!፣ ሰዎችንም ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ ከሚያነሳሱ ነገሮች ሁሉ መራቅ ይጠበቅብናል፣ ሁሌም መረጋጋትን መያዝ ይጠበቅብናል፣ ከአሉ ተባለ ወሬ እና ጥያቄን ከማብዛት መራቅ ግዴታ ይሆንብናል፣ ይህ ነቢዩ ﷺ ከከለከሉት ተግባርም ነው። ስንት (በአሉ ተባለ ወሬ የምትሰራጭ) አንዲት ቃል የሰላ ሰይፍ የማይሰራውን ሰርታለች?!፣ በእኛ ላይ ግዴታ የሚሆነው የሚግባባና የሚዋደድ ማህበረሰብ እንዲሆን ከፊትና እና ፊትናን ከሚቀሰቅስ ነገር መራቅ ነው!!።” ✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
Mostrar todo...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

Photo unavailableShow in Telegram
ضريح الشرك❌ دمر الله تلك المباني🤲🏻 " يابني لاتشرك بالله إن الشرك لظلم عظيم " أثنى الله على ثمانية عشر نبيا، ثم قال: "ولَوْ أشرَكوا لحَبِطَ عنهُمْ مَا كَانُوا يعْمَلُونَ". وأثنى على سيد الأولين والآخرين، ثم قال: "ولقد أوحِيَ إلَيكَ وإلَى الذينَ مِنْ قَبلِكَ لئِنْ أشرَكتَ ليحبَطَنَّ عمَلُكَ، وَلَتَكُونَنَّ مِنَ الخَاسِرِينَ". لا محاباة في الدين، ولا عاطفة في العقيدة والتوحيد، فإن الله حذر صفوة الخلق من الشرك، وأمرهم بعبادة الله وحده لا شريك له، وإلا حبط كل عملهم وإن أقاموا الصلاة وآتوا الزكاة وقطّعوا الدهر ذكرا وعبادة. ألا أيها الداعي مع الله آخرا ألم تدرِ أن الشركَ شرّ الكبائرِ وقد يغفر الله الكبائر كلها ولكنه للشرك ليس بغافر #التوحيد_حق_الله_على_العبيد #التوحيد_أولا ☝🏻✔ توحيد لا شرك #الدعوة_السلفية ✅📚 السنه اتباع لا ابتداع وخرافه ونعوذ بالله من أن نشرك به شيئا 🤲🏻
Mostrar todo...
↪️ ለሁጃጆች ↪️ በሚና መስጂድ በሁጃጆች ማረፊያ በተዘጋጀው ድንኳን ለሁጃጆች  የተሰጠ አጠቃላይ ኢስላማዊ ወስያ(ምክር)  ↩️ نصائح إسلامية عامة للحجاج في الخيمة المقامة للحجاج في مسجد منى. ➴➴➴➴➴ ==================== ያዳምጡ። ➴➴➴➴➴ ==================== 🎙 በተከበሩ ሸይኽ ሱለይማን አል'ሩሃይሊ ሀፊዘሁሏህ 🎙 لفضيلة الشيخ سليمان الرحيلي -حفظه الله- 🗓 ዙል ሂጃ ‐  ከ10 እስከ 13- 1445هي 🕌 በሳዑዲ አረቢያ ከተማ በሚና መስጂድ በሀየጃጂች ማረፊያ ድንኳን 🕌 بمدينة مينة[إلسعدية]؛ في مسجد مينة ➴➴➴➴➴ ==================== #size መጠን 5.35MB #length 09:50min 🕌ለሀጃጆች ዙል ሂጃ ከ10 እስከ 13 የተሰጠ አጠቃላይ ምክር 🌎ሚና፣ ሳዑዲ አረቢያ የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصير
Mostrar todo...
_شيخ_سليمان_الرحيلي_١٤٤٥_في_منى_10.mp39.06 MB
ዳዕዋ ዳዕዋ ዳዕዋ 📢 ‼️ አስላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ ውድና የተከበራችሁ የሱና እአህቶችና ወንድሞች በያላችሁበት ቦታ ሁናችሁ ያአላህ እዝነቱና በረከቱ አይለየን አይለያችሁ በሱናም ላይ አላህ ያፅናን ያፅናችሁ እንኳን ለ (1445) ኢደል አድሃ በአል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ እነሆ አስደሳች ዜና ይዘን ዘልቀናል የፊታችን እሁድ ማለትም ሰኔ ቀን /16/2016/ታላቅ የዳዕዋ ዝግጅት ስላለን በተባለው ቦታ በጧት በመገኝት የዳዕዋው ተቋዳሽ ትሆኑ ዘንድ ታድማችኋል 🔄ብርቅየ ተጋባዥ እንግዶቻችነን ስናሳውቃችሁ በታላቅ ደስታ ነው ↘️1 ሸይኽ ሙሐመድ ሃያት ከሃራ ↘️2 ሸይኽ ሁሴን ከረም     ከሃራ ↘️3 ሸይኽ ሙሃመድ ሲራጅ ከሃሮ ↘️4 ሸይኽ ሁሴን አባስ  ከጉራ    ወርቄ ↘️5 ኡስታዝ ኑራድስ           ከሃራ ↘️6 ኡስታዝ ኑረድን            ከመርሳ ↘️7 ኡስታዝ አብዱረህማን  ከመርሳ የሚጠቀሱትና የሚዳሰሱት እርዕሶች በሰአቱ በቦታው ላይ የሚነገሩ ሲሆን ጥሪውን አስታውሱ እንዳትረሱ 👁‍🗨የዳዕዋው ባታ አጆሜዳ ሲሆን ከጃራ ከፍ ያለች ከድሌሮቃ ዝቅ ብላ የምትገኝ የገጠር አድስ ከተማ ናት  ወረዳ ሃብሩ ቀበሌ ( 024) በድጋሜ አጆ ሜዳ 🕑 የሚጀመርበት ሰአት ከጧቱ ሁለት 2:00 ሰአት ጀምሮ እስከ 10:00 ሰአት ድረስ የዘልቃል የኦናይን ስርጭትም ስለሚኖረን ሳትርቁ ጠብቁን 🕌 መስጅደ ፉርቃን አጆ ሜዳ ሰኔ/ቀን/16/2016/1445/ዓ/ሂ https://t.me/hussenhas
Mostrar todo...
አቡ አዒሻ العلم نور

የዚህ ቻናል ዋና አላማ ሱናን ማንገስ ሽርክን ማርከስ ነው!! የሱና መሻይኮችና የሱና ዳዒዎች የሚላክበት የዳዕዋ የደርስ ሴንተር ቻናል ነው ሐሳብ አስተያትን ያለምንም ጥበት እንቀበላለን ቅድሚያ ለተውሂድ በተግባር

↪️ የአረፋ ኹጥባ/የዒደል አዷሃ(ምክር) ↩️ خطبة العرفة؛ ➴➴➴➴➴ ==================== ✅ ርዕስ፦ ➴➷➘ "« መሰረታዊ፣አሳሳቢና ወቅታዊ አጠቃላይ ኢስላዊ ምክር በሚል  የተመጠነ ወሳኝ ምክርና ማብራሪያ» በሚል አንገብጋቢ እና ወቅታዊ ርዕስ '✅العنوان:-« الحصول على أفضل النتائج هو أفضل ما لديك"" هذا هو أفضل ما في الأمر» ከተዳሰሱ ነጥቦች በከፊል:- 👉ከሸርክና ጀሙሽሪክ መራቅ እንዳለብን፣ ማጭበርበር፣መዋሸትና የሰወችን ሀቅ መጠበቅ፣የ ወላጆችን ሀቅ መጠበቅ እንዳለብን። 👉የዲን ምሰሶ በሆነውን በተዉሑድ መጠንከር አለብን። 👉ኡዱህያችንን በትክክል ማስተናገድ እንዳለብን። 👉በተውሒድ አንድ መሆን ይገባናል። በተውሑድ ፍፁም ታዛዥ መሆን አለብን ልክ እንደ ነብያቲች፣ሰሀቦች። 👉፣የኡዱህያ መስፈርት እና በኡዱህያ ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራርሪያ ተብራርቶበታል። ያዳምጡ። 👉የአጂነብይ ወንድና ሴት መቀላቀል/ኢኅቲላጥ/ን አሏህን በመፍራት መራቅ እንዳለብን ተብራርቷል። ➴➴➴➴➴ ==================== 🎙 በሸይኽ ሐሰን ገላው ሐሰን ሀፊዘሁሏህ 🎙 لفضيلة الشيخ حسن بن غلاو حسن -حفظه الله- 🗓 ሰኔ‐ 07‐ 10 - 2016 E.C 🕌 ባህር ዳር ከተማ 🕌 بمدينة بحردار [إثيوبيا]؛ في مسجد البخاري ➴➴➴➴➴ ==================== #size መጠን 5.35MB #length 07:25 min 🕌ለባህር ዳር ሰከፍዪች የተደረገ 🌎ባህር ዳር፣ ኢትዮጲያ የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصير
Mostrar todo...
Muhadera mp33.85 MB
Photo unavailableShow in Telegram
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.