ሁለ ገብ😘😘😘
Ir al canal en Telegram
እዚህ Channel ላይ ማንኝውንም ነገር ማግኘት ይችላሉ ብቻ የምትቁዋቸውን ሁሉ ወደዚህ channel ይጋብዙ group መቀላቀል አይርሱ !!
Mostrar más463
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
+3030 días
Archivo de publicaciones
463
[እኔ ጠላሻለሁ]
እኔ ጠላሻለሁ፣
እንደ ጫማ ሽታ
ልክ እንደ በሽታ
ጌታ በባሪያው ላይ እንደ ሚበረታ፤
እኔ ጠላሻለሁ፣
እንደ ረጅም መንገድ
ላብታም እንደ መስገድ
ከጠጡ በኋላ እንደ መንገዳገድ፤
እኔ ጠላሻለሁ፣
ገንዘብ እንደ ማጣት
ዳገት እንደ መውጣት
ከያዘ እንደ ማይለቅ እንደ ጨካኝ ቅጣት፤
እኔ ጠላሻለሁ፣
ልክ እንደ መልከስከስ
እምነት እንደ ማርከስ
ማስቲካ እያኘኩ ምላስ እንደ መንከስ፤
እኔ ጠላሻለሁ...(ወዘተ)...
አሁን ግን ፈራሁኝ ጀመርኩኝ መብሰልሰል
ጠላሁሽ ያበዛው ወድጄሽ ነው መሰል!😁😁
#keld21
@keld21
@keld21
463
.....ተስፋ...
በቃላት ስብስብ_በፊደላት ዜማ
ተቀብሮ በልቤ_በሰው ላይቀማ
ከኔ ጋር እያለ_ሃሳቡን ሳልሰማ
የተለየ እለት ድንገት_የወረሰኝ የቀኑ ጨለማ
መልካም የመሰለኝ_ያኔ ያስከተልኩት
ከተስፋዬ ርቄ_ግዜን የገደልኩት
መስሎ ይታየኝ ነበር_ እኔ የቀደምኩት
ለካሱ ቀድሞኛል_ወደሁአላ ትቶኝ
መንገድን ሊያስተምር_ተስፋን አሳጥቶኝ::
463
✅️አንድ አንድ ቀን ይደብራል ። ገገማ ገገማ ሰዎች ፊትህ ግንጭር ይላሉ ፤ ትሁቱ ሳይቀር ይጠግብብሃል ፤ ወዳጆችህን አጠገብህ ታጣችዋለህ ፤ አጠገብህ ያሉት አይረዱህም ። አውጥተህ አውርደህ ያቀድከው ይከሽፋል፤
⭐የምቶደው ማክያቶ ጠዓም አልባ ይሆናል። ገርል ፍሬንድህ ከመሬት ተነስታ ታኮርፍሃለች ፤ ካላገኘሁህ የምትለው ልጅ ስልኳ አይነሳም ወይ አይመቸኝም ትልሃለች።
የቸኮለ ይገፋሃል፤ ወያላው መልሴን ስትለው ይጮህብሃል፤ የሚካለብ ባለ መኪና ክላስኩን ይነፋብሃል። ATM እምቢ ይልሃል እበደረዋለሁ ያልከው ልጅ ቀድሞ ብድር ይጠይቅሃል ፤ ስልክህ ባትሪ ይጨርሳል።
ከሩቅ ጠርቶ ሰላም የሚልህ ጀለስ በቅንድቡ ሰላም ይልሃል። ፀሃይም ንፋስም አንተን በተለየ የሚያጠቁህ ይመስልሃል ። ድምፅ ይደብርሃል ፤ ሁሉም በጠላትነት የፈረጀህ አይነት ስሜት ይጠናወትሃል ፤ ዜናው ይቸክሃል ፤
ቢያንስ ከዚህ ዉስጥ አብዛኞቻቺን 3ወይ 4 ነገሮችን አጋጥመውን ይሆናል 😒
ይሄኔ
⭐ቀስ ብለህ ጎንበስ ብለህ ድምፅህን አጥፍተህ እቤት ገብተህ ተኛ የፈለገ ቢሆን ነገ እንደዚህ አይጨክንም።
ሁሉም በእንቅልፍ ያልፋል 😊
@keld21
@keld21
463
@keld21
@keld21
ና ቦታ ቀይረን!
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ያኔ ከጅምሩ ሄዋን ስትሳሳት
አንተ ብትሆንም በግፍ ያሳመንካት
ከተንኮልህ ክብደት ከጭካኔህ ብዛት
ብለን ብንጠራህም የጨለማው አባት
ከራስህ ተምረን የክፋትን መንገድ እንዲህ እንደዋዛ
ካንተ ክፉ ስራ የኛ ምቀኝነት እጅግ ስለበዛ
ናቦታ ቀይረን አንተ እዚ ሁንና እኛ እንሁን እዛ!
እኛው እርስ በራስ ከሆንን እንቅፋት
ቆመን ካቀጣጠልን የጥላቻን እሳት
ሌላው ካላመመው የሌላኛው ጉዳት
መጠንቀቅ ካቃተን ፈጣሪን ከመክዳት
ሲዖል የኛ ትሁን ምድርን ውሰዳት!
የምድርን በረከት መካፈል ከፈራን
አዳምነት ጠፍቶ በዘር ከተስማማን
ተፈጥሮን ክደናት ካመለክን ገንዘብ
ሀሜትን ከመዝራት ካቃተን መሰብሰብ
እኛነት ኮስምኖ እኔነት ከረታን
የክህደት ቀንበር መሸከም ካዋጣን
መዋረድን መርጠን ፈልገን ከመጣን
ሰውነትን ረግጠን ምንሆነው ካሳጣን
ና ቦታ ቀይረን አንተ ሰው ሁንና እኛ እንሁን ሰይጣን!
ተፃፈ በዳኒኤል ከተማ
@keld21
@keld21
463
Repost from Ethio crypto
በጀርመን ሐገር የሒትለር ልጅ አብሮ ከሚማርበት ክፍል አንድ መምህር "ተማሪዎች በክንፋቸው ከሚበሩት እንሰሳት መኻል አንድ ጥቀሱ?" ብሎ ይጠይቃል።
በዚህ ቅፅበት የሒትለር ልጅ እጁን አውጥቶ "ዝሆን!" በማለት መለሰ።
አስተማሪውም "አጨብጭቡለት! ሞቅ አድርጋችሁ አጨብጭቡለት…የኔ አንበሳ!" ይላል። ክፍሉም በጭብጨባ ብዛት ቀውጢ ሲሆን ይሄን የሰማ ርዕሰ-መምህር ይመጣና "ምንድነው?" ሲል ቢጠይቅ አስተማሪው ጉዳዩን ሹክ ይለዋል።
ከዚያም ርዕሰ-መምህሩ "ደግማችሁ አጨብጭቡለት እንዲህ አይነት እሳት የሆነ ተማሪ ከየት ይገኛል!" እያለ ጠጋ ብሎ ለመምህሩ በጆሮው "ወንድሜ እኛ ከምንበር ዝሆኑ ቢበር ይሻላል!" አለው።
•••
"ሉባር" ከበረደድ ገዳሙ (115)
