cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ኪነ - ቃል..♨

በዚህ ቻናል ◈ሰፊ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ እይታዎች ◈ህይወትን የሚያድሱ የስነ-ልቦና ምክሮች ◈የአንጋፋ እና ጀማሪ ገጣሚያን ግጥሞች ◈ግሩም የፍቅር ታሪኮችና ወጎች ◈በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ በኢትዮጵያውያን አና በውጭ ሀገር ደራስያን የተጻፉ አማርኛ መፅሃፍት በጥቂቱ የሚቀርቡበትና ውብ የጥበብ ስራዎች በድምፅ ሚተረኩበት ግሩምና ድንቅ ቻናል ነው። ግጥም ለመላክ ➫ @Melikitegna_bot

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
888
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-3630 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ንብ እና ሥነ-ምኅዳር ═══•🐝•═══ ንቦች ‹የመላው ዓለም ዜጎች› ናቸው። በስድስቱም የፕላኔታችን አኅጉሮችና በመላው የምድራችን አገሮች ውስጥ ይገኛሉ። ምግባቸው ፖለን እና ኔክታር ሲሆን የንግሥቲቱ ምግብ ደግሞ ሮያል ጄሊ ነው። ንቦች እንደ ማር፣ ፕሮፖሊስ፣ ሰም፣ ሮያል ጄሊ የመሳሰሉትን እፁብ ድንቅ ምርቶችን ሠርቶ ከማቅረብ ባለፈ ለአካባቢያችን ሥነ-ምኅዳር እና ለሥነ-ሕይወታዊ ሂደት ከፍተኛ ጠቀሜታ አላቸው። በእንግሊዘኛው አጠራር ‹Environmental Friendly› በሚል ስያሜ የሚገለፁ ሲሆን ከሥነ-ምኅዳር ጋር ተስማሚ የሆነ ተፈጥሮ እንዳላቸው ተመስክሮላቸዋል። በርካታ ማለፍያ የሆኑ አካባቢያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ሲሆን፤ አንዳችም ዓይነት ጉዳት በአካባቢ ላይ አያደርሱም። ከአንድ አበባ ወደ ሌላው አበባ ፖለን የተባለውን የአበባ ዘር (ፅጌ ዘር) በማሰራጨት አበቦችን በማራከብ የማራባት ተግባርን ይፈፅማሉ። በዓለም ላይ ካሉት ባለ አበባ እፅዋቶች ውስጥ 80 ፐርሰንት የሚራቡት በንቦች አማካኝነት ነው። በዚህ መልኩ ከሚራቡት ንብ ዘራሽ እፅዋት ውስጥ ለምሳሌ ያህል፦ ሱፍ፣ ኑግ፣ ብርቱካን፣ በሶብላ፣ ለውዝ፣ ፓፓያ፣ አተር፣ ኮክ፣ ወይን፣ ዱባ፣ ጥጥ፣ ማንጎ፣ ዘይቱን፣ ጤና-አዳም፣ ጦስኝ፣ ጥቁር አዝሙድ፣ በርበሬ፣ ባቄላ፣ ሽምብራ፣ ጎመን ዘር፣ ተልባ እና አቮካዶ ይገኙበታል። ━━━━━━━━ 📗 ማርና ሞሪንጋ ✍ ዶክተር ኬ.ኬ. 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks
Mostrar todo...
ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

የስነ-ፅሁፍ ቻናላችንን 👉

https://t.me/Ethiobooks

ተቀላቀሉ። ለማንኛውም አስተያየት እና ማስታወቂያ 👉 @firaolbm @tekletsadikK እናመሰግናለን። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Photo unavailableShow in Telegram
(''ዛሬ በልግ ነው ዘወትር አለቅሳለሁ ዛሬ በልግ ነው ፀደዩ ምንኛ ይርቃል።'') 📖ትኩሳት📖 በጋሽ ስብሀት ገ/እግዚአብሔር share 🖇 @ethio_fiction
Mostrar todo...
"ደራሲ ደራሲ ከመሆኑ በፊት አንባቢ ነው ። ደራሲ ደራሲ ከሆነም በኋላ አንባቢ ነው ።የህይወት ቅጠሎችንም ያነባል ፤ እድሜ ልኩንም ያነባል ።" ደበበ ሰይፋ። #share and join for more👍 SHARE🌼 =ኪ==ነ==ቃ==ል= Share & join @write_event @write_event @write_event
Mostrar todo...
ምክር ከሃኪሞች ሠፈር! አርበኛው አያቴ ሆስፒታል ሄዶ ሲመለስ ብስጭትጭት አለ። "ምነው ምን ነካህ?" "ጠቅል የድሃ ልጅ አስተምሮ ተጫወተብን" "እንዴት?" "ሃኪም አትብሉ ይላል?የታመመ ጥሩ ጥሩውን ካልበላ ይሆናል?የደሃ ልጅ ስለሆነ እሱ ያላገኘውን ሰው ሲበላ አይኑ ደም ይለብሳል።ታድያስ?ጮማ እትብሉ፣ቅቤ አትብሉ፣ጠጅ አትጠጡ እናስ?እለዋለሁ አትክልት ብሉ ባዶ ሽሮ ምናምኒት የሌለው " "ምን አልከው?" "ሽሮውን አንተው እንዳደክበት እዛው ሙትበት፤እኔ የሰጠኝን በረከት ትቼ ያልሰጠኝን ስበላ አልገኝም።ድሃ የድሃ ልጅ አልኩታ" አለማየሁ ገላጋይ -ውልብታ **** ሰውየው በእድሜ የገፉ ባለጠጋ ናቸው። ሃኪም ጋር ሄደው "አባት በሽታዎችዎ እነ ደምግፊት፣ስኳር እና ዩሪክ አሲድ የመሳሰሉት እርስዎ የሚያዘወትሯቸውን ምግቦች ይከለክላሉ። ጥሬ ስጋ፣ቅባት የበዛባቸው..." "ጮማስ?" "እሱንም" "ጠጅስ" "አይፈቀድም ወይ ይቀንሱት" "እና ሞትን ሞተህ ጠብቀው ነው የምትለኝ" በሃይሉ ገ/መድህን ከሸገር ኢንተርቪው *** እኚህኛው ደግሞ ኑሮ የደቆሳቸው እናት ናቸው። "እማማ በሽታ ሳይሆን ያለብዎ ችግር እራስዎን ያለመጠበቅ ነው።በምግብ ይጠገኑ ለምሳሌ ጥዋት ሲነሱ እንቁላል፣በምሳ ሰዓትም እማይከብድ መረቅ ነገር ከተገኘም ጭማቂ ወይም..." "ጨረስክ?" "አዎ ጨርሻለሁ ብቻ ለስለስ ያለ ነገር..." "ጨረስክ ወይ? "ጨርሻለሁ" "አንት ቅንዳሻም!እራስህ የማትበላውን ለኔ ታዛለህ!" ተስፋዬ ካሳ #share and join for more👍 SHARE🌼 =ኪ==ነ==ቃ==ል= Share & join @write_event @write_event @write_event
Mostrar todo...
ሀይማኖት በኢ–አማኙ እይታ ! ከቴዎድሮስ ተ/አረጋይ የፌስቡክ ገጽ የተገኘ ቴዎድሮስ :– የእግዚአብሔርን መኖር ፋይዳ እናጥብበውና ሀይማኖት ሌላ ቢቀር በስነምግባር ት/ቤትነቱ እንኳ አስፈላጊ አይሆንም ? ዜና :– አይሆንም ። ግብረገብን ሀይማኖት አይደለም የፈጠረው ፤ ከሰብዕና ላይ ነጥቆ የወሰደው ነው ። ቡድሂስቶች ጋ ሂድ ። ከእኛ የበለጡ ደጎች ናቸው ። ክርስትና ወይም እስልምና አይደለም ደግ ያደረጋቸው ። ክርስትናን ወይም መጽሐፍ ቅዱስን አያውቁም ። ማንኛውም ሀይማኖተኛ ጥቅሙን አስቦ ነው እግዚአብሔርን ያመነው ፤ ዘለዓለማው ሕይወትን ለማግኘት ። እኔ ደግ ስሆን ግን ምንም አስቤ አይደለም ። ደግ መሆን ስላለብኝ ፤ ሌላው ሰው ደግ ቢሆንልኝ ስለምፈልግ ነው ። አንተ ላይ ክፉ የማላደርገው እኔ ላይ ክፉ እንዲደረግ ስለማልፈልግ ነው ። ይህ ደግሞ የሀይማኖት ህግ አይደለም ። በሀይማኖት ስም አይደለም እንዴ ሞትና እልቂት የደረሰው ? አሜሪካ ውስጥ አንድ የካቶሊክ ቄስ አንድን ውርጃ የሚሰራ ዶክተር ቤቱ በር ላይ ገደለው ። ከዚያ ሄዶ እጁን ለፖሊስ ሲሰጥ " የእግዚአብሔርን ስራ ሰራሁ " ነው ያለው ። ይህን የሰማ ስቲቨን ዊልበርግ የተባለ የፊዚክስ ሊቅ ምን አለ መሰለህ ? ቃል በቃል እንጥቀሰውና " With out religion you will find good people doing good things , bad people doing bad things . But good people to do bad things you need religion " ( " ያለ ሀይማኖት ጥሩ ሰዎች ጥሩ ፣ መጥፎ ሰዎች መጥፎ ሲሰሩ ታገኛለህ ። ነገር ግን ጥሩ ሰዎች እርኩስ ነገር እንዲሰሩ ከፈለግህ ሀይማኖት ያስፈልግሀል " ማለት ነው ።) ( ከ" ፍልስምና " 3 መጽሐፍ የተወሰደ) አንድ አባት ገዳም ውስጥ በጽድቅ እየኖሩ ሳለ አንድ ሐሳብ ወደ አዕምሯቸው ይመጣል። "ይህን ሁሉ ዓመት በጽድቅ ኖሬ ሳበቃ ከሞት በኋላ ሕይወት ባይኖርስ? ፈጣሪ ባይኖርስ? መና መቅረቴም አይደል?" ብለው አሰቡ። ከጥቂት ቀናት በኋላ ሞቱና ሰማይ ቤት ሄዱ። መልኣክት በሥራ ተወጥረው ሳለ ነው የደረሱት። መልኣክቱ ይራወጣሉ። ምን እየሠሩ እንደሆነ አልገባቸውም። አንድ መልኣክ ይመጣና "እዚህ ምን እየሠራህ ነው? ምን ታደርጋለህ?" ብሎ ጠየቃቸው። "በቅርቡ ሞቼ ለፍርድ መጥቼ ነው!" ብለው መለሱለት። መልኣኩ በአንክሮ ካስተዋላቸው በኋላ "ማን ነው የምትባለው? ከየትስ ነው የመጣኸው" ሲላቸው፥ "ሰው ነኝ! መሬት ከምትባል ፕላኔት ነው የመጣሁት" ብለው መለሱለት። መልኣኩ እጅግ ተገርሞ "መሬት የሚባል ፕላኔት እና ሰው የሚባል ፍጡር አላውቅም!" አላቸው። መልኣኩ ትንሽ አሰበና ከሱ ከፍ ላለው መልኣክ ነገሩን አሳወቀ። መልኣክቱ ግራ ሲገባቸው የባሕር መዝገቡን አገላብጠው ቢመለከቱት መሬትና ሰው የሚባል ነገር ጨርሶውኑ አጡ። ግራ ሲገባቸው ሽማግሌውን ይዘው እግዚአብሔር ጋር ወሰዱት። እግዚአብሔርን እጅግ በሥራ ተወጥሮ ያገኙታል። እግዜሩም እጅግ ተቆጥቶ "ምንድነው በተዋረድ ወስኑ አላልኳችሁም?! ለምን ሥራ ታስፈቱኛላችሁ?" አላቸው። መልአኩም "መሬት ከሚባል ፕላኔት ሰው የሚባል ፍጡር እግዚአብሔር ፈጥሮኛል ብሎ መጥቶ ነው" አለው። እግዜሩ ቢያስብ ቢያስብ ሰውን ስለመፍጠሩ ሊያስታውስ አልቻለም። "ለመሆኑ ባሕር መዝገቡ ላይ ሰፍሮ ይሆን?" ብሎ ጠየቃቸው። "የባሕር መዝገቡ ላይ መሬት የሚባል ፕላኔትም ሆነ ሰው የሚባል ፍጡር ጨርሶውኑ የለም" አሉት። እግዜሩም "በቃ ምናልባት ከመጀመሪያዎቹ ሥራዎቼ አንዱ ሊሆኑ ስለሚችሉ Others የሚባል Folder ክፈቱና እዚያ ላይ መዝግቧቸው" አለ። #ዓለማየሁ ገላጋይ ከፈረንሳይ ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ ያገኘውን ተረክ በሸገር ኤፍኤም ከመዓዛ ብሩ ጋር ባደረገው ቆይታ ከተናገረው የተወሰደ፨
Mostrar todo...
የባህር ፈርጥ ነሽ፣ ሽሽግ ድብቅ እንቁ የንጋት ድርሳኔ፣ ያገር በቃይ ስንቁ ሁለመናሽ ሙሉ፣ የሴት እፁብ ድንቁ ብርሃኔ ነሽና ለኔስ ማታ ማታ አትጥፊ ከጎኔ ነይ የኔ ዘንካታ የቀኑማ ቀን ነው ያልፋል በጨዋታ የከንፈሯ ድባብ፣ ጥዑም ቃል ማስፈሪያ አጀብ የንብ ንግስት፣ የማር መናኸሪያ ውበት አርከፍክፎ፣ ተፈጥሮ የመጠናት የቁም ነገር መዝገብ፣ የዕምነት ማህተብ ናት የዕምነት ማህተብ ናት [2x] ማርና ወተቴ ነሽ፣ ደጋፌና ክብሬ ለቤቴ እስኪ ስሚኝ ልንገርሽ ላዚም ስላንቺ ካንጀቴ አንቺ ነሽ ሕይወቴ፣ የፍቅር እመቤቴ የባህር ፈርጥ ነሽ፣ ሽሽግ ድብቅ እንቁ የንጋት ድርሳኔ፣ ያገር በቃይ ስንቁ ሁለመናሽ ሙሉ፣ የሴት እፁብ ድንቁ የጥርሷ ብርሃን፣ ሕይወት የሚዘራ ተፈጥሮዋ አበባ፣ እንቡጥ ያላፈራ እንደ ዕውነት እንደ ውኃ፣ እያደር የጠራ ለምልክት ላይነት፣ ለይታ የተሰራ ለይታ የተሰራ…ላይነት የተራ ባዘንም በደስታዬ፣ ምሶሶ ዋልታዬ ለቤቴ ውዳሴ ገዴ ክብሬ፣ ዐብይ ጉዳዬ ሕይወቴ አንቺን ያበቀለ ቀዬው እንዴት ዋለ ማርና ወተቴ ነሽ፣ ደጋፌና ክብሬ ለቤቴ እስኪ ስሚኝ ልንገርሽ ላዚም ስላንቺ ካንጀቴ አንቺ ነሽ ሕይወቴ፣ የፍቅር እመቤቴ አንቺን ያበቀለ ቀዬው እንዴት ዋለ [2x] #ቴዎድሮስ_ታደሰ_ሁለመናሽ_ሙሉ 🥰
Mostrar todo...
''እናትዬ'' ''ወዬ አባትዬ'' ''አንድ ነገር ልጠይቅሽ ነበር። መጀመሪያ ግን እንደማትናደጅብኝ ቃል ግብልኝ'' ''የሚያናድድ ነው ምጠይቀኝ?'' (ከደረቱ ላይ ቀና ብላ እያዬችው ጠየቀች) ''እ አ..ይ...አዎ! ማለቴ ይሄ ጥያቄ አንቺን ያናድድሻል ብዬ ነው ማሬ'' (ጭንቅ ብሎታል ምን ብሎ እንደምጀምርላት ግራ ገብቶታል። በጭራሽ የማትወደው ጥያቄ እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። ግን ደሞ መልስ ካላገኘለት በጭራሽ እንቅልፍ አይወስደውም። መወሰን አቃተው።) (ንግግሩ አሳቃት እና ሳቅ ብላ።) ''ደሞ ምን ማለት ነው ይሄ!? አይ! አዎ! አንዱን ምረጥ አባትዬ። እሺ በቃ ጠይቀኝ ፈቅጀልሃለው። መቼም አንዴ አንተን ጥሎብኛል አቃጥላት ብሎ ሃሃ. . . ጠይቀኝና ካናደደኝ ልናደዳ እንግዲህ።'' (አለችው እየቀለደችበትና እየሳቀች አይን አይኑን በፈገግታ እያየች) ''ግን ይሄን ጠየኩሽ ማለት እኔ አላምንሽም ማለት አይደለም እሺ?'' (አላት በልምምጥ። የነገሩ አካሄድ የገባት እሷ ደረቱ ላይ ተደግፋ ከተቀመጠችበት ቀና ብላ ተቀመጠች። ልታስጨርሰው ስለፈለገች ዝም ብላ መስማቱን ቀጠለች። ፈራት። አንዴ ጀምሮታል ያለው አማራጭ መቀጠል ብቻ ነው። ባለፈው እንደዚህ ባለ ተመሳሳይ ጉዳይ የመለያየት ጫፍ ላይ ደርሰው እንደተመለሱ ያውቃል። በጭራሽ ሊያጣት አይፈልግም። በጣም ይወዳታል። እንደዚህ ያለ ነገር ውስጥም የሚገባው እሷን ላለማጣት ካለው ፍራቻ የተነሳ ነው።) ''ይሄውልሽ ምን መሰለሽ ከያሬድ ጋ ያላቹህ ቀረበታ ብዙም ምቾት አይሰጠኝም። ባለፈው ብሮሽ ሄጄ ሳለሁ ፡ ምን አይነት አስተያየት ስያይሽ እንደ ነበር ማስተዋል ችያለሁ። ደሞ አስር ጊዜ ነው ወደ ብሮው የምጠራሽ። በዚህ ላይ ደሞ ቁልምጫው. . .'' (እያለ ሊቀጥል ሲል አቋረጠችው። በወሬው ላለመበሳጨት ጥረት እያረገች) ''እንደ አባትዬ እንዴት እንደዚህ ታስባለህ? እሱ እኮ አለቃዬ ነው። በማንኛውም ሰዓት ለስራ ወደ ብሮው ሊጠራኝ ይችላል። ሰውዬው ለራሱ ባለትዳር ነው። በጣም የምወዳት ሚስት አለችው። እና ደሞ እኔን ብቻ አይደለም በቁልምጫ የሚጠራኝ። ይመስለኛል እንደልምድ ሆኖበታል። ሙሉ እስታፍ ውስጥ ያሉ ሰራተኞችን እንደዛ ነው የምጠራው። ሰውየው እንዴትም ሊያዬኝ አይችልም ይሄ በአእምሮህ እየፈጠርክ የምታስበው ነገር ነው። ዋ! እንዳትጀምረኝ ደሞ'' (ነገሩን ቀለል ለማድረግ እየሞከረች ሳቅ ብላ) ''ምን ማለት ነው በአእምሮህ እየፈጠርክ ነው ምታስበው ማለት!? ያላየሁትን ነገር እንዴት ፈጥሬ ላስብና ላወራ እችላለሁ? አንቺ ራሱ ሆን ብለሽ እንዳልገባሽ ለመምሰል ካልጣርሽ በስተቀር ፡ ማየት ለሚፈልግ ሰው ፡ ግልፅ የሆነ የሽፍደት አስተያየት ነው የሚያይሽ።'' (ሳያውቀው በጣም ስሜታዊ ሆኖ ስለነበር ፡ በኃይሌ ቃል የነበር የሚያወራት። ቃላት መምረጡን እረሳ። እሷም ፊቷ እየተቀየረ ነው። ብስጭቷ ሳትፈልገው እየገነፈለ ይመጣል። እንደምንም ልትቆጣጠረው እየሞከረች።) ''ሽፍደት? ምን ማለት ይሆን ደሞ ይሄ? ደሞ መስሎህ ነው እንጂ : እኔ ሆን ብዬ እንዳልገባኝ እያስመሰልኩ አይደለም። ይልቅስ ምንም ያላሰበውን ሰውዬ እየፈረድክበት እንደሆነ ሊገባህ የሚገባው አንተ ነህ። አዬህ አይደል ለዚህ ነው አታምነኝም የሚልህ።'' ''እና ይሄ አንቺን ካለማመን ጋር ምን ያገናኘዋል? የሃለቃሽ አስተያየት ደስ አላለኝም ማለት። አንቺን አላምንሽም ማለት አይደለም።'' ''ነው እንጂ። በደንብ ነው። ብታምነኝማ ኖሮ መቼ ሁልጊዜ እንዲህ ያለ አተካራ ውስጥ እንገባ ነበር። ብታምነኝማ ሺህ ጊዜ የሃለቃዬ አስተያዬት ደስ ባይልህ : በእኔ ከተማመንክ ምንም ባላስፈራህ ነበር። ለምን እንደዚህ ታረገኛለህ ግን? እንደ ማፈቅርህ ታውቃለህ። አማራጭ አጥቼ አንተን እንዳልመረጥኩህም ጠንቅቀህ ታውቃለህ። ልምረጥ ቢል ብዙ ሰዎች በዙሪያዬ እንደነበሩ ታውቃለህ አይደል?'' (አሁን አኮረፈች) ''አዎ አውቃለሁ የኔ እናት እሺ በቃ ትቸዋለሁ። አሁን አታኩርፊ'' (እጇን ይዞ በእጆቹ እያሻሼ አባበላት) ''እና እንዲህ ያለ ሁኔታ ውስጥ እንድሆን ለምን ታደርጋለህ!? አላሳዝንህም? አንተ እኔን እንድታምነኝ ፡ ያላረኩት ምን አለ? እስኪ ንገረኝ ምንድነው ያላረኩት!? በእናትህ ዳጊ እንደዚህ አታድርገኝ በእናትህ ልለምንህ'' (አሁንም እንዳኮረፈች ሳግ በሚተናነቀው ድምፅ።) ''እናትዬ እውነተን ነው ሚልሽ። በፍቅራችን እምልልሻለሁ ፡ ከራሴ በላይ ነው የማምንሽ።'' ''እና ካመንከኝ ለምን ትጠራጠራለህ? እኔን ብታምነኝ ይሄ ሁሉ ነገር ባልተፈጠረ ነበር። ባንተ ምክንያት ብቻ በጣም የተሻሉ ስራዎቼን ትቻለሁ። በጣም መልካም የሆኑ የሴትም ሆነ የወንድም ጓደኞቼን ርቂያለሁ። አንተ ስለማትፈልግ ብቻ ማድረግ እየፈለኩ ማላደርጋቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ህልሜን : የምወደውን ስራ : ቤተሰቤን ሳይቀር ላንተ ሲል ትቻለሁ። ታውቃለህ!? የሚኖረው ህይወት መኖር የምፈልገውንና እኖራለሁ ብዬ ስመኝ የኖርኩትን ህይወት አይደለም። መኖር ያለብኝን ህይወት ሁሉ ፍቅራችን ይበልጣል ብዬ ተውኩ። ሳገባህ ከተሻለህ ብዬ አገባሁሁ። ግን አንተ ጭራሽ ባሰብህ። ስራ ቦታዬ ድረስ እየድክ ሰላም ትነሳኛለህ። ለራስህም ሰላም ታጣለህ። በቅናት ምክንያት እኔን ከነ መፈጠሬ እረስተህ ገና ለገና አስተያየቱ አላማረኝም ብለህ ከመንገደኛ ጋር ሁሉ ሳይቀር ፀብ ውስጥ ትገባለህ። ከሰው ጋር ተቀምጠን ስንጫወት ነገሩን በሌላ ተርጉመህ ጥል ውስጥ ስለምትገባ : ካሁን አሁን እንድህ ይፈጠራል እያልኩ ነፍሴን አስጨንቃታለሁ። ሰውነቴ በሰቀቀን ያልቃል። ትላንት በመጣሁበት መንገድ ታክሲ ሳይቀናኝ ቀርቶ መንገድ ቀይሬ በቀናኝ በኩል ቢመጣ : ደሞ በዛ በኩል ምን ተገኘ ትለኛለህ። ከማን ጋር ነው የመጣሽው? ታክሲ ውስጥ አብሮሽ የተቀመጠው ወንድ ነው አይደል? ሆንብለሽ ነው ከወንድ ጋ የተቀመጥሽው ትለኛለህ። አሁንስ እኔ ድክም ስልችት ነው ያለኝ።'' ''በነገሩ ስትንገሸገሽ አይቶ ደነገጠ። ግን አሁንም ብሆን የመቀጠል እንጂ ነገሩን የማብረድ አላማ ያለው አይመስልም።'' ''እናትዬ አሁን ምትይኝን ነገር ሁሉ የማደርገው እኮ ለፍቅራችን ብዬ ነው።'' ''ለፍቅራችን ብዬ!? ምን ማለት ነው ለፍቅራችን ብዬ? እኮ እንዴት ሆኖ ነው እንደዚህ ያለ አቅል የሚያስት ቅናት ለፍቅራችን የሚጠቅም የመሰለህ? ይሄውል ብገባህ ቅናትህ ቀን በቀን ፍቅራችንን እየገደለው ነው'' ''ይሄ በጭራሽ ቅናት አይደለም።'' ''እሺ ባክህ እና ምንድነው!? ባልዋልኩበት : ባልነበርኩበት እያነበርከኝ : ባልተኛሁበት እያስተኛኸኝ : ባልሄድኩበት : ባልተቀመጥኩበት እያስቀመጥከኝ : ያልተፈጠረ ነገር ፈጥረህ እያወራህ : ጭራሽ እያበድክ እስክመስለኝ ድረስ : ሁሉንም ሰው በጥርጣሬ ዓይን እያየህ። እና ይሄ ቅናት ካልተባለ ምን አይነት ስም ልትሰጠው ነው? ይሄ ለኔ ከቅናትም በላይ ነው። ይሄ በሽታ ነው። የለየለት እብደትም ጭምር ነው የሚመስለኝ'' (ብላ ከአጠገቡ ተነስታ ሌላ ቦታ ቁጭ አለች) ''ኧረ ባክሽ እና አብደሀል እያልሽኝ ነው? እብድም መሰልኩሽ!? ታዲያ ለምን ፀበል አትወስጅኝም እ? እንደሱ አይሻልሽም?'' (አላት በንዴት ጦፎ ነገሮች ወደጭቅጭቅ መቀየራቸውም ንግግሯም ከጎኑ ተነስታ ቦታ ቀይራ መቀመጧም አበሳጨው።)
Mostrar todo...
''ተው ግን ዳጊ ተው ትዕግስተን እየጨረስኩ እንደሆነ ለምን አይታይህም ግን።'' (አሁን እንባዋ መውረድ ጀመረ። እንዲህ ስትለው ይፈራል። ነፍሱ ትሸበራለች። ደንግጦ ከተቀመጠበት ተነስቶ የተቀመጠችበት ሄዶ አቅፎ ሊያባብላት ስሞክር : እንዳያቅፋት ተከላከለች። ታግሎ አቀፋት። ትወደዋለች መጨከን አትችልም ተሸነፈችለት።) (ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ እየገነፈለ ያስቸገረውን ንዴቱን ለመቆጣጠር ብሞክርም አልቻለምና ይሄው እንደለመደው አስለቀሳት። ሳያስበው በልምምጥ የጀመረው ወሬ ቅርፁን እየቀየረ እየቀየረ ሄዶ ምልልሳቸው ወደ ጭቅጭቅ ተቀየረ። የእሱም ልምምጥ በቁጣ ተተካ። ላይ ላዩን እንደዚህ እየተቆጣ ቢያወራም ፡ ውስጡን ግን አንዳች የፍርሀት ስሜት ሰቅዞ ይዞታል። ቢትሄድብኝስ : እንደ ባለፈው : በቃ የኔና ያንተ ነገር አብቅቷል ቢትለኝስ!? የሚል ሃሳብ አእምሮው ላይ ስመጣ ፈራ። አጥብቆ አቀፋት። ልቡ ይታወክ ጀመር። ጨነቀው። ምድር ላይ የሚያስፈራህ ነገር ምንድነው? ተብሎ ቢጠየቅ ሁለት ጊዜ ሳያስብ ማርቲን ማጣት ነው ብሎ ይመልሳል። ግን ደሞ ሁልጊዜ ነገሮችን የሚያበላሸው ራሱ ነው። በዚህ ምክንያት አንድ ቀን ጥላው እንደምትሄድ ያውቃል። የሆነ ቀን በዚሁ ጉዳይ ተጣልተው ብዙ ብዙ ተጨቃጭቀው : እቤት ተቀምጣ ምርር ብላ ስታለቅስ : እሱ ጭንቅላቱን ይዞ ሶፋው ላይ አጎንብሶ እንደ ተቀመጠ ጓደኛው ድንገት ይመጣል። ምን ሆናችሁ ነው ብለው ፡ ትንሽ ተጋጭተን ነው አለው። ታዲያ የዛን እለት ጓደኛው ሚስቱን አባብሎ ልሸመግላቸው ተቀመጠ። እናም ጓደኛው ነገር ለማለዘብ ብሎ : ለሚስቱ ለሰነዘረላት ጥያቄ እንዲህ ብላ መመለሷ አስደነገጠው። ይሄውልህ አሴ የጎደኛው ስም አሰግድ ነው። ባሏ ስጠራው በሰማችው እሷም አሴ እያለች ነው ምጠራው። ''በህይወቴ ውስጥ ከምንም በላይ ለፍቅራችን ግዴታዬን ተወጥቻለሁ . . . . . ካልሆነ መሄድ እችላለሁ።'' ነበር ያለችው። ታዲያ ይሄን ስትል ቀዝቃዛ ውሃ የተቸለሰበት ይመስል ከተቀመጠበት ብትት ብሎ ብድግ አለ። እሱ በተራው ማልቀስ ጀመረ። የዛን እለት አሳር ፍዳውን በልቶ ጓደኛው አስታርቋቸው ሄደ። ታዲያ ሁልጊዜም ቢሆን እንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ስገቡ ያንቀን የተናገረችው ነገር በጆሮው እያስተጋባ ያርደዋል። ቢሆንም ግን ክፉ አመል የሆነበት እና መቼ እንደተፀናወተው የማያውቀው አደገኛ ቅናት አለበት ለመዳን ቢታገልም መፈወስ ያልቻለበት ደዌ። ልክ እንደ {ታምራት ደስታ ሙዚቃ ወድጄ አይደለም ምቀናው ጥሎብኝ ነው የኔ ፍቅር} እንደሚለው። እሱ ራሱ ጭንቅ ስለው ከፍቶ የሚሰማው ይሄን ሙዚቃ ነው። በነገሩ ተበሳጭታ አላናግርህ ስትለውና ስታኮርፍ ይሄን ሙዚቃ በምትወድለት ድምፁ ሲያንጎራጉርላት አንጀቷ አይችልም። አቅፋ ትስመውና ማውራት ይጀምራሉ። ግን አሁን አሁን ይሄን ፍቅር ልታድን እንደማትችል እየገባት መጥቷል። ልጅ በጣም ብትወድም በዚሁ ፍራቻዋ ምክንያት ነው የመውለድ ፍላጎቷን ያዘገየችው። እዚህ ትዳር ውስጥ ልጅ ማምጣት የልጁን ህይወት ማበላሸት ነው ብላ ነው ምታስበው። ምክንያቱም ይሄ ትዳር በፍቺ እንደሚጠናቀቅ ልቧ ያውቀዋል። እናም ከምታፈቅረው ሰው ልጅ መውለድ ፡ ብትፈታው እንኳን ለትዳሯ እና ለፍቅሯ ለከፈለችው መስዋዕትነት ሁሉ መታሰቢያ ነው ብላ ብታስብም ፡ ልጇን ያለአባት ማሳደግ ግን ልክ አይደለም ብላ ታምናለች። ባሏ ሁልጊዜ የእንውለድ ጥያቄ ያነሳል። ግን ለእሱም ቢሆን ቅናት የለብኝም እያለ ብከራከራትም መቅናትህን አቁመህ እኔን በሙሉ ልብህ አምነህ እንደሰው ማህበራዊ ህይወት ኖሮን ጤናማ ህይወት መኖር ስንጀምር ያኔ እወልዳለሁ ትለዋለች። ደሞ ሁልጊዜም ቢሆን ስላም ሆነው ስለችግሮቻቸው ሲያወሩ : ቅናት እንዳለብህ ማመን ካልቻልክ መዳንም አትችልም ትለዋለች። ካልታረምክ አልወልድልህም ማለቷ ለሱም ባህሪውን ለማስተካከል ጉልበት ይሆነዋል ብላ ታስባለች። የባሏን አስቸጋሪ አመል ለማረቅ ብዙ ነገር ታደርጋለች። ይሄን ትዳር ከተወች ምድር ላይ ብቻዋን እንደምትቀር ታውቃች። እሱ እንዳይቀና ለማድረግ ከህይወቷ ያላስወጣችው ሰው የለም ከወንድ ጓደኞቿ ጋር ብጠረጥራትና ብቀና ከሴት ጓደኞቿ ጋር ደሞ ከማን ጋር ልታገናኝሽ ነው እያለ ቁም ስቅሏን ያሳያታል። ከዚህ ሁሉ ብቀርስ ብላ ሁሉንም እርግፍ አድርጋ ተወችለት። አሁን ግን ትዳርዋን ፡ ፍቅሯን ለማዳን መሞከር እና ማድረግ ያለባትን ሁሉ አድርጋ ጨርሳለች። እሱን ካጣች እንደምትጎዳ እንደምትሰበር ታውቃለች። ከሁሉ በላይ ግን እሱ እሷን ስያጣት የሚሆነውን ነገር ማሰብ ይከብዳታል። በጭራሽ ተጎድቶ ልታየው አትችልም። የሱን ጉዳት የማየት አቅም የላትም። ከራሷ በላይ የሱ ህመም ያማታል። በትዳሯ በኩል ያልተሰማ ብዙ ፀሎት : ያልሰመረ ብዙ ስዕለት አላት። አንዳንዴ አምላኳን እንዲህ ብላ ትጠይቀዋለች። የማያልቅ ፍቅር ሰጥተሄን ስታበቃ : ቅናት ይሉት ስሌት ፍቅራችንን ገዝግዞ ስቆርጠው እያየህ እንዴት ዝም ብለህ ታያለህ!? እንዴት አንድ የማርያም ምህረት ለፍቅራችን አጣህ!?) ሰብለ ወንጌል #share and join for more👍 SHARE🌼 =ኪ==ነ==ቃ==ል= Share & join @write_event @write_event @write_event
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ኬቨን ሃርት የተባለው ኮሜዲያን። እዚህ የስኬት ጫፍ ላይ ከመድረሱ በፊት ብዙ መከራ ያሳለፈና አትችልም ተብሎ የተገፋ ሰው ሲሆን፣ ከሲንግል እናቱ ቤት ሥራ ፍለጋ ሲወጣ እናቱ የሰጡት ስጦታ መጽሐፍ ቅዱስ ነበር። ኬቨን አንድ ቀን የሚመገበው አጥቶ በጣም ቸግሮት ለእናቱ ይደውላል፣ ማሚ ስራ ማግኘት አልቻልኩም እባክሽ እርጂኝ አላቸው? እናቱም የሰጠሁህን መጽሐፍ ቅዱስ አንበብክ ወይ ? እርሱም ራበኝ እያልኩሽ የምን መጻሕፍ ነው የምትይው አላቸው። ልጄ አሉት የሰጠሁህን መጻሕፍ ቅዱስን አንብበህ ቢሆን ኖሮ እኮ አይርብህም ነበር አሉት። ኬቨን እናቱ አንብብ ያሉትን መጻሕፍ ቅዱስ ሳያነብ እናቱ በማኅፀን በር ካንሰር ያርፋሉ፣ እርሱም በዓለም ምርጡ ኮሜዲያን ውዱ አከተርም ከሆነ በኃላ፣ አንድ ቀን የልጅነት ፎቶግራፎቹን ለፊልም ፈልጎ ሲበረብር ያንን እናቱ የሰጡትን መጻሕፍ ቅዱስንም ገለጠው፣ ውስጡ እናቱ ለስራ መፈለጊያና መጠነኛ ቤት መከራያ እንዲሆነው የተውለትን 1ሺ ዶላር አገኘ። ገንዘቡ ለአሁኑ ኬቨን ምንም ብትሆንም እናቱ ግን ንብረታቸውን ሸጠው ነበር ለልጃቸው የሰጡት። መጻሕፍት ውስጥ ብዙ መልሶች አሉና መጻሕፍትን እናንብብ። ቀና ብሎ በዕውቀት ለማውራት ብዙ አጎንብሶ ማንበብን ይጠይቃል። ፍፁም አብርሃም✍️✍️ #share and join for more👍 SHARE🌼 =ኪ==ነ==ቃ==ል= Share & join @write_event @write_event @write_event
Mostrar todo...
🔅ለሰው ምን ያህል መሬት ይበቃዋል? (በሌቭ ቶልስቶይ) ከረዥም ዘመን በፊት በአንድ ትንሽ የደቡብ ኤዥያ አገር የሚኖሩ ብልህ ንጉሥ ነበሩ። ግዛታቸውን ለመገንጠል የተነሳ አንድ የውስጥ ወንበዴ ቡድን አስቸግሯቸው ስለነበር በጦርነት ሊያጠፏቸው ወሰኑ፤ ለጦር አዛዡም ይህን ጦርነት በድል ፈፅሞ ከተመለሰ ከፍተኛ የሆነ ሀብትና መሬት እንደሚሰጡት ቃል ገቡለት። በዚህም የተነሳ የንጉሡ ጦር በከፍተኛ ቆራጥነት ተዋግቶ የወንበዴው ጦር ተደመሰሰ። የሞተው ሞቶ የቀረው ቆስሎም ተማረከ፤ ንጉሡ ቃል እንደገቡት ለጦር አዛዡ ብዙ ሀብት ከመደቡለት በኋላ "በእግሩ ቀኑን ሙሉ ፀሀይ እስክትጠልቅ የሄደበትን የግዛቴን መሬት ለክታችሁ ስጡት።" ብለው ሸለሙት። የጦር አዛዡም ተደሰተ፤ ብዙ ለም የሆነ መሬት መያዝ ይፈልግ ስለነበር በተዘጋጀበት ቀን በጣም በማለዳ ተነስቶ ስንቅ አዘጋጅቶ መጓዝ ጀመረ። በመጀመሪያ ጉልበቱ የቻለውን ያህል በለሙ መሬት ላይ ሮጠ። መሬት ለኪዎችም በፈረስ ይከተሉት ነበር፤ ከዚያም በፍጥነት ቀኑ ሳይመሽ ይራመድ ጀመር። ብዙ ከሄደ በኋላ ወደ ከሰአት ምሳውን ሳይቀር እየሄደ በላ። ሆኖም ከበላ በኋላ ጥቂት መሬት ሄዶ ስለደከመው እየተራመደ ውሃ ጠጣ። ዘጠኝ ሰአት ያለእረፍት ተጉዞ በመጨረሻ እገሩ በጣም ዛለ፤ ቢሆንም አንድም እርምጃ ቢሆን ለም መሬት ነውና መራመዱን ቀጠለ። ሲል ሲል እግሩ መራመድ አቅቶት ዝሎ ወደቀ። አሁን ለኪዎቹ ምልክት ሊያደርጉ ሲሉ "ቆዩ ... ቆዩ" ብሎ መዳኽ ጀመረ። ከዚያም ጥቂት ሄዶ በልቡም መሳብ ጀመረ፤ በመጨረሻ ፀሃይ ገና ሳትጠልቅ የቻለውን ተንጠራርቶ ሲሳብ ልቡ ቀጥ አለችና ትንፋሹ ቆሞ ሞተ። የንጉሡ ቦታ ለኪዎችም ደነገጡ። የጦር አዛዡን ከሞተበት ሳያነሱ በፈረስ መልእክተኛ ወደ ንጉሡ ቤተ መንግሥት ላኩ፤ መልክተኞቹም የአዛዡን ሲጓዝ ውሎ ልቡ ደክሞ መሞቱን ነግረው "ምን ያህል መሬት እንስጠው?" ብለው ጠየቁ። ንጉሡም እጅግ አዝነው "ለሰው ምን ያህል መሬት ይበቃዋል?" ብለው ተከዙ፤ "እንግዲህ ይህ ሰው የወደቀበትን ቦታ ብቻ ከእግሩ ጫፍ እስከ ራሱ ጫፍ ብቻ ለክታችሁ ስጡት። ሬሳውንም እዚያው ቦታ ቆፍራችሁ በክብር ቅበሩትና የጀግና ሃውልት አቁሙለት።" አሏቸው፤ በተባለው መሰረት የጦር አዛዡ በመጨረሻ በሞተባት ቦታ በክብር ተቀበረ። በመቃብሩም ሀውልት ላይ "ለሰው የሚበቃው መሬት ይህ ነው።" ተብሎ ተፃፈ።    #share and join for more👍 SHARE🌼 =ኪ==ነ==ቃ==ል= Share & join @write_event @write_event @write_event
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.