cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ABRHOT

በዚህ ቻናል ሀሳብ ያላችለሁ @ownkin

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
185
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

✍️ ሄዶን እውነት እውነት አለ ምናቤን ያነጠው እውነት ስሜት አለ ነበሬን የሸጠው እኔ ውስጥ እኔ አለ ነገ የማለውጠው @merekkk
Mostrar todo...
በዝምታ መሀል እንዳለው ሹክሹክታ በለቅሶ መሀል ላይ እንደ ጮኸ እልልታ በድቅድቅ ጨለማ እንዳለችው ጨረር በተንጣለለው ሀይቅ እንደገባች ጠጠር በሞት ከተማ ውሰጥ እንዳለችው ህይወት ሀሰትን እንደ እውነት በቆጠረች ምድር ያለች ቅንጣት ውሸት . . . . . .እውነት
Mostrar todo...
✍ህያው ..ህይወትን ለምን ሸሸኍት?.. ፍቅር በህግ ሲደቆስ: ብርሀን በጭለማ ሲለኮስ: ፈገግ ያሉት እየከሰሙ: ጆሮዎች ዋይታ ሲሰሙ: የተስፋ መጥኔ ሲላላ: ጸንተው በቆሙት አናት ላይ የመውደቅ ጥላ ሲያጠላ: የድክመት ብርታት ሲጎላ ሀይለኛ ሀይሉ ሲከዳው: ታዲያ የኔ ጥርስ ምን ተዳው.. ከዓለም እውነት ተጣልቶ በጉያው ነገን አግቶ ዛሬን እያታለለ: አለ ፈገግ እንዳለ.. @merekkk መ ረ ቅ
Mostrar todo...
✍🏼ህያው በቃ አልናፍቅሽም? . . አየሁ.. የ'ናቴን ሙዳይ ከፈትኩት አየሁ.. እንደ ባለጌ ጎረምሳ ያባቴን ኮት ኪስ ደፈርኩት አዘንኩ.. ውስጡ አልነበረም ያሰብኩት። . . በቃ አልናፍቅሽም?.. @merekkk
Mostrar todo...
✍️ሄዶን የለምም አንልም ኖሮም አላየንም አለንም አንልም ባዶም አይደለንም። @merekkk
Mostrar todo...
ሳያዩ የሚያምኑ ብፁሀን ለመባል የሚንደረደሩ፣ አሉ በሀገሩ አሉ በመንደሩ። ፍርድን ይሽታሉ፣ ከለኮሱት እሳት ያመልጡ ይመስሉ፣ ወይ ወረድ ወይ ፍረድ እግዜርን ይላሉ ቢወርድ እና ቢፈርድ ከፈራጁ ጀርባ በፍርድ ሰገነት ፍርዱን ለመታዘብ ይቆሙ ይመስሉ። ጦርነት አውጆ በንፁሀን ደም ላይ የተረማመደ፣ ና ውረድ ይለዋል የሚወርድ መስሎት እርሱ እንደወረደ።
Mostrar todo...
ስርየት የማይሞት ሲያጣጥር ሺ ጉድጓድ ሲያስቆፍር ሲደግስ ሲጣራ ሲያስለቅስ ሲያቅራራ ለደሃ በጀና ሙታን ይነሳሉ ያንዱ ስቃይ ላንዱ ስርየት ነው እያሉ ✍melat eshetu
Mostrar todo...
ቢሆን” እንዳመተ ፍዳ ልክ እንደ በፊቱ ሐጢያት ስናበዛ ቢገለጥ ቅጣቱ በለምጥ ቢመታን ቢቀር ምህረቱ በጥቁሮች መዲና በዚች ኩሩ አገር በጣም ብዙ አበሻ ፈረንጅ ይሆን ነበር ምንጭ: ዮርዳኖስ አስራት
Mostrar todo...
ቂምና ምስጋና ሆድ የለህምና እንደኔ በሆድህ ቂም መያዝ ባታውቅም ለሆዳም ሆዴ ስል በሆዴ ቂም ይዤ በፊትህ ባልፀድቅም በሰው ፊት ፃድቅ ነኝ ተመስገን እያልኩኝ በሰማይ በምድር የእለት እንጀራዬን እየከለከልከኝ አመት ፆሜን ሳድር ተመስገን ! ተመስገን ነው !😄😄 ✍ melat eshetu
Mostrar todo...
( የጨረፍታ ብርድ ) የቆላ ሰዎች ወደ ደጋ፤ የደጋ ሰዎች ወደ ቆላ እየተፈራረቁ ፣ እየተሰደዱ፣ እየተተረማመሱ መኖር ለአያሌ ዘመናት የነበረ ደግሞም የሚቀጥል ነው ። በተለምዶ ቢሆን በዛን ዘመን የአንድ ሰው ፊት አይቶ እገሌ መልኩ ቁጭ ደገኛ አይደል የሚመስለው ይሄኛው ደግሞ ቁርጥ ቆለኛ አይደል የሚመስለው እየተባባሉ መገመት ያረጀ ያፈጀበት ልማዳችን ነው ። ወሎ በሚባለው በያኔ ክፍለ ሀገር ከቆላ አካባቢ ሁለት ሰዎች እልም ያለ ጠብ ውስጥ ይገባሉ ። የአካባቢ መንደርተኞች ሽማግሌዎችን አሰናድተው ሽምግልና ያስቀምጧቸዋል ፤ ጠበኞችም ባንገታችን ካራ ይግባ ሲሉ ለያዥ ለገናዥ ያስቸግራሉ ። ንትርኩ በዚህ የሚቋጭ አይደለም እና ወደ ደሴ ተጉዘው ችግራቸው በፍርድ እዲከድኑት የአካባቢ ሽማግሌዎች ይበይናሉ ። መንደሬው ወደ ደሴ የሚሄዱበት ቀነ ቀጠሮ ቆርጦ እነዛን ጠበኞችን እስከ ገጠሩ መውጫ አፋፍ ድረስ ተሰናበታቸው ። ጠበኞችም እየተፍገመገሙ የቆሪጥ እየተገለማመጡ አንደኛው ለአንድኛው የአይኑን ሽፍሽት ሳያርገበግቡ ስንቃቸውን ለብቻቸው እንደተመገቡ የዕኩለ ቀን ጉዞአቸውን አገባደዱ ። ጀንበር በምታዘቀዝቅበት ሰአት ከደሴ አቅራቢያ ጊንባ እየተባለ በሚነገርለት ስፍራ ደረሱ ። ምሽቱን መጓዝ ስላልቻሉ በከፊል ጫካ ከሆነ ስፍራ አድረው በነጋታው ፍርዳቸውን ለመቀበል ተስማምተው እዛው ጫካው ውስጥ ተኙ ። በጫካው ውስጥ ካለው የአራዊት ድምፅ እና የአዋፋት ጫጫታ ይልቅ የጊንባ ብርድ አጉል ረበሻቸው ። ብርዱ አይጣል ነው ፤, አያስቆም አያስቀምጥም ። ከዛም ጠበኞች የነበሩት ሰዎች ተቃቅፈው ተቀመጡ ። ኋላም እርስ በእርሳቸው እርቅ አውረደው እንዲህ ተባባሉ " የጨረፍታ ብርድ አለውድ ያስተቃቅፋል "። ለፍርድ ደሴ መሄዳቸው ትተው በመጡበት ተመለሱ ። አሁን ድረስ በአካባቢው ይሔ ወሬ ይወራል ። ይቺ አጭር ታሪክ ጠብ በደላላ ለሆነ ከምንም ነገር ይልቅ ጠብ ለሚቀድው የጨረፍታ ብርድ ፍቱን መድሃኒት ናት ። ✍ ፊሊሞን ነጋ @ownkin @djmdx
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.