cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ሐሽማል ቤተ-መዘክር

👉Only for readers 👋መግቢያ👋 መግቢያ ለመግባቢያ ገታ አርገነዋል የቃላትን ግልቢያ እናም በዚህ ሀሳብ ከተስማማህበት ያንኳኳኸዉን በር የገለፅከዉን ገፅ ፈቅደናል ግባበት ምንጭ - ካልታወቀ ገጣሚ Join the group @amharicbooksforeadersgroup አድሚኑን በ ቀጥታ ለማናገር ይህንን ቦት ተጠቀሙ @Digitallibraryofhashmal_bot

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
3 847
Suscriptores
+2124 horas
+867 días
+35930 días
Distribuciones de tiempo de publicación

Carga de datos en curso...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Análisis de publicación
MensajesVistas
Acciones
Ver dinámicas
01
Media files
2780Loading...
02
Media files
5992Loading...
03
...ተመልሳ እንደማትመጣ ልቡ ያቃዋል…ብቻ ልፋ ቢለው እንደሆነም ይረዳዋል…ቀኑን ሙሉ ሲያማትር ቢውልም አንዳች አዲስ ነገር እንደማይፈጠር ከእሱ በላይ ማንም ሊያውቅ አይችልም…ማንም! …ግን እራሱን መሟገት አይፈልግም…ባትመጣም ትመጣለች ማለትን ይመርጣል…እራሱንም መሸወድ፣ ከራሱ ጋር ፀብ እንደሆነ ቅንጣት ታህል አይጠፋውም…ግን "አትመጣም" ከሚለው የእውነት ጩኽት ይልቅ "ትመጣለች" የሚለው ሹክሹክታ ለእሱ ሰላም አለው። …ከሰላም በላይ ደሞ ምን አለ?   ✍🏽 ፊሊሞን የማርያም ልጅ
7375Loading...
04
Media files
9070Loading...
05
Media files
9675Loading...
06
Media files
9231Loading...
07
📙 ይድረስ ለውዷ ፊያሜታ ጊላይ... እንደምን አለሽልኝ..? እኔ በልጅነቴ ፍቅር እስከ መቃብር ነው ሲሉ ሰምቼ ዙቤይዳን እስከማገኝ ድረስ ኦሮማይን የሙጥኝ ብየ ነበር የቆየሁት። ሳድግ የፍርድ ቀን ዘመቻ ላይ ሆኜ በትኩሳት እየተንቀጠቀጥኩኝ... መልህቅ እንደሌለው መርከብ እየተናወጥኩኝ... ሌቱም አይነጋልኝ ስል ተገኘሁ። ሌላ ጊዜ ደግሞ ከአመጓ እስከ ዝጎራ እያካለልኩ መርበብትና ሰበዝን ይዤ በጠበኛ እውነቶች ስም አንፈርስም አንታደስም የሚል መፈክር ማሰማት ጀመርኩኝ። አይይይ... ይሄ ነገሬ እንኳን ለኔም አልገባኝም... ብቻ ሌላ ሰው ላይ ስፎክር እንደ ኢያሪኮ ግንብ በቅፅበት ለመፍረስ እንዳይሆንብኝ ሁሉቱ ጊዮርጊሶች ይጠብቁኝ። 📙 ይገርምሻል አንዳንድ ቀንና ህይወት ርዕስ የለውም ይባላል። ብዙ ሰው የሚስማማበት ሃሳብ ግን ያፍቃሪ ሰው ትንፋሽ ልክ እንደ መንደሪን ጣፋጭ መድሃኒት መሆኑን ነው። ከዕለታት ግማሽ ቀን ቤተልሄምን ተይው ፖለቲካን ዝም ብለሽ ሳሚኝ እያልኳት ሀገር ያጣ ሞት ድንገት በጠቢባን መንገድ በኩል ሲመጣብኝ ምንሽሮን ዋስ ጠርቼ አመለጥኩት። በሰሞነ ህማማት ደግሞ ገላና ገላዬ ሲታመሙብኝ ትዝታሽን ለኔ ትዝታየን ለአንቺ እያሰብኩኝ አሳለፍኩ። 📙 አንቺዬ ደግሞ ያልተነገረ ተረክና ያልተፃፈ ኑረት ታሪክ አይሆንምና አንድ ቀን ሜሎሪናን ህልምሽን አጫውችኝ ብያት ስታወጋኝ የአማኑኤል ሆስፒታል ታሪኮችን አስታወሰችኝ። እግረ መንገድ ይሁን እንጅ ዶክተር አሸብር የታካሚውንና የልብ ጠጋኙን ማስታወሻ እያገላበጠ ፊት ለፊቱ አሳንቲ የሰማይ ላይ ስዕል መስላ እንደተሰየመች በምናቤ ውል አለችብኝ። በመጨረሻም ከዚህ በላይ የነገርኩሽን ታሪክ ጨምሮ የአና ማስታወሻ፣ ዮቶርና ፖፒዮ የተሰኙትን ዜማዎች ከወንድም ሐሽማል ጋር ጋብዠሻለሁ። . . ያንቺው ጠኃ ባላደራ ...! የመፅሃፍት ስምና ገፀባህርያትን በመጠቀም የተፃፈ ታሪካዊ ደብዳቤ:: ✍️ መሳይ አርቀው ፊያሜታ ተናፍቀሻል🥰 ስንቶችን አንብበዋል?😊 ⛵️⛵️⛵️ "ማንበብ ፋሽን ነው።" Join us @noahbookdelivery
9267Loading...
08
Media files
7600Loading...
09
Media files
8580Loading...
10
Media files
510Loading...
11
ከርግቦች ትራስ ስር (አሌክስ አብርሃም) የላባን መከዳ አምነህ አትመቻች ቂም በቀል ነው ከታች! የመስዋዕት አንገት አግኝቶ እስኪመዘዝ አንዳች የሚወገር አንዳች የሚወገዝ "ከርግቦች" ትራስ ስር የዛገ ሰይፍ አለ በፍቅር እየማለ! ማነህ ባለሳምንት ማነህ ባለዝክር ተሰልፏል ከሳሽ ተሰብቋል ምስክር ብቻ እጣ ይውጣብህ ልክም ሁን ስህተት አንተን ሞረድ አርጎ የተረሳው ሁሉ ይነቃል ከዝገት!
1 0932Loading...
12
📕📚📓 #ባሎች_ሆይ_ተመከሩ 📕📚📓 🙏 ሚስትህን በምስጋና፣ በአክብሮትና በብዙ ፍቅር እንጂ ተራ በሆነ መንገድ ፈጽሞ አታናግራት 🙏 👉ሚስትህን በምስጋና፣ በአክብሮትና በብዙ ፍቅር እንጂ ተራ በሆነ መንገድ ፈጽሞ አታናግራት 👉ከራስህ ሕይወት ይልቅ እንደምትወዳት ንገራት፤ ምክንያቱም ይህ የአሁኑ ሕይወት ከንቱ ነውና፤ በሚመጣውም ዓለም በፍጹም ፍቅር አንድ እንድትኾኑ ይሁን 👉እሷን እንዲህ በላት፦ “በምድር ያለን ጊዜ አጭርና የሚያልፍ ነው፤ ነገር ግን በዚህች አጭር ጊዜ አምላክን የምናስደስት ከሆነ ይህን ሕይወት ለሚመጣው መንግሥት መለወጥ እንችላለን። ያን ጊዜ ከክርስቶስ ጋርም ሆነ እርስ በርሳችን ፍጹም አንድ እንሆናለን፣ እናም ደስታችን ወሰን አይኖረውም። ፍቅርሽንም ከኹሉም ነገር በላይ ከፍ አድርጌ እመለከታለሁ፣ አንዳችን ከአንዳችን ጋር ከመቃቃር በላይ፣ ምንም አይነት መከራ አያሰቃየንም። እርስ በእርሳችን ማር ከሆን የአለም መከራ አይመረንም፣ ኹሉንም መታገስ እንችላለን” 👉ከእርሷ ጋር አብሮ መዋልን የምትወድ መኾኑን አሳያት፣ በየገበያው ከመዞርም ከርሷ ጋር ቤት ውስጥ መሆንን እንደምትመርጥ አሳያት 👉በጓደኞችህና በልጆችህ ፊት አወድሳት 👉ስለ መልካም ተግባሯ አመስግናት፣ የሞኝነት ነገር ካደረገች በትዕግስት ምከራት። 👉በቤት ውስጥ አብራችሁ ጸልዩ፣ ወደ ቤተክርስቲያን አብራችሁ ሂዱ፣ ወደ ቤት ስትመለሱ አንደኛችሁ ሌላኛችሁን የንባብና የጸሎት ጥያቄዎችን ጠይቁ። ትዳራችሁ እንደዚህ ከሆነ ፍፁምናችሁ ከቅዱሳን መነኮሳት ጋር የሚወዳደር ይሆናል። 👉 የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አዲሱ #የነፍስ_ምግብ መጽሐፍ
1 29210Loading...
13
https://t.me/addexdrop_bot?start=9614879bbc05eb6b9c3b80474f09cf35
9531Loading...
14
Earn +50 Addex coins for inviting each person! Your invitation link: https://t.me/addexdrop_bot?start=9614879bbc05eb6b9c3b80474f09cf35 Total invited: 0 partners Earned: 0 Addex coins
10Loading...
15
https://t.me/getcapybot/now?startapp=MzE0NTU2NDMxfGViODA3OWY1LTdlY2QtNGZjNy1hMjg3LWU4OGZjZTFhZjRiNg==
1 0861Loading...
16
Media files
9400Loading...
17
ዛሬ ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቀን ነው! ስለ ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቀን አንዳንድ ነገሮች! የዓለም መጽሐፍ ቀን በየዓመቱ ሚያዝያ 15 ይከበራል። የመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅፅ የተገኘው በቻይናውያን በ3ኛው ክፍለዘመን ነበር። በ15ኛው ክፍለዘመን አጋማሽ የህትመት ማሽኖችን መፍጠር በመቻሉ የመጻህፍት አብዮት አሁን ወዳንበት ደረጃ ተሸጋገረ። ሚያዝያ 15 ለዓለምአቀፍ የመጽሐፍ ቀንነት የተመረጠበት ምክንያት የዊልያም ሼክስፒር እና ስፔናዊው የታሪክ ጸሐፊ ኢንካ ጋርሲላሶ ዴ ላ ቬጋ የሞቱበት ቀን በመሆኑ እንደመታሰቢያ እንዲሆን ነው። በእዚህ ቀን በዓለምአቀፍ ደረጃ በተለይ ወላጆች ለልጆቻቸው መጻሕፍትን በስጦታ መልክ በመስጠት ያከብሩታል። የቀኑም ትልቁ ዓላማ የንባብ በዓል ማዳበረ ነው። ✍ ኖህ book delivery
1 0181Loading...
18
የክብር ሽልማት የግለታሪክ ምርጥ አምስት እጩዎች በዚህ ሊንክ ገብተው ይምረጡ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://kibershilemat.com
1 0150Loading...
19
የክብር ሽልማት የአመቱ ምርጥ አምስት በግጥም ሙድብል ተለይተዋል በዚህ ሊንክ ገብተው ይምረጡ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://kibershilemat.com
7950Loading...
20
የክብር ሽልማት የአመቱ ምርጥ አምስት በአጫጭር ልብወለድ ምርጥ አምስት እጩዎች በዚህ ሊንክ ገብተው ይምረጡ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://kibershilemat.com
7230Loading...
21
የመጀመሪያ ቀጠሮ            የመጀመሪያ ግብዣ የባጥ የቆጡን ሲያወሩ ቆዩና "ምን አይነት ሰው ነሽ?" አላት አፉ ጋር የደረሰውን ጉርሻ እየጎረሰ "ምን አይነት ሰው ነኝ መሰለህ" የጠቀለለችውን ጉርሻ ቁጭ አድርጋ ቀጠለች "በጣም ስለወደፊታቸው የሚጨነቁ አስር እና ሀያ አመት የሚያቅዱ አይነት ነበርኩ። ከዛ ድንገት የሆነ ቅፅበት ላይ ታክሲ ላይ ያየሁት ጥቅስ አባነነኝ "ዛሬ ቢሆንስ የምትሞተው" ይላል ከዛ ያስጨንቁኝ የነበሩ ነገሮች በሙሉ ዋጋ አጡብኝ በቃ የእለቱ እለት ማታ እንደሚሞት ሰው መኖር ጀመርኩ ራሴን የምከለክለው ነገር አልነበረም ሁሉንም አድርጌዋለሁ አሁን ምንም የቀረኝ የምለው ነገር የለም በቃ ለሁሉም ነገር ስሜት አጥቻለሁ ነው የምልህ። ነገሮች ቀስ ብለው እንዳይሆኑ አጣደፍኳቸው እና የሚያስደስቱኝ እና የሚያሳዝኑኝ ነገሮች ተመናመኑ አንዳንዴ ከልክ በላይ ነገሮችን መገፋፋት ዋጋቸውን ያሳጣዋል።" አለችው እና መብላቷን ቀጠለች። መልዕክቷ ግልፅ ነበረ <ላንተ የሚሆን የማቀርበው ትኩረት እና ጉጉት አይኖርም> ማለቷ ነው። እነሆ የመጀመሪያም      የመጨረሻም ቀጠሯችን ሆነ ማለት ነው። ✍ Thoughts
7895Loading...
22
በቀደም አመሻሻይ ላይ ፒያሳ ነበርኩ ። ከእጮኛዬ ጋ ከተለያየን ጀምሮ ሄጄ አላውቅም ። የተራመድንባቸው ጎዳናዎች በፍርስራሽ አፈር ተሸፍነዋል ፣ ሲኖትራኮች ይንጎራደዳሉ ፣ ሻይ የጠጣንባቸው ካፌ ፣ ያደርንበት ሆቴል ፣ የተላፋንባቸው ቤቶች ፣ ቆመን ፎቶ የተነሳንባቸው ፣ የሳቅንባቸው ቦታዎች እንደ'ኛ ታሪክ አንዱም የለም እንደ'ኛ ፍቅር ቋሚ መስሎኝ ነበር ። ፒያሳ ረጅም ጊዜ ያልሄድኩት ትውስታዬን ፣ ትዝታዬን እንዳይቀሰቅስ ነበር ። ረዳቶች ፒያሳ... ፒያሳ ....ፒያሳ ሲሉ ልቤ ድንግጥ ይል ነበር ። ሰፈር ፣ ቦታ እንደዚህ ከፍቅር ፣ ከትውስታ ፣ ከትዝታ ጋ የተዋሃደ መሆኑን አላውቅም ነበር ። በቀደም ለመጀመርያ ጊዜ ፒያሳ ስሄድ ..... ፍርስርስ ብሏል እንደ'ኛ እምነት..... እንደ'ኛ ፍቅር ...... እንደ'ኛ እውነት .... እንደ'ኛ ቃል ..... መጥፎ ትውስታዬ የሚቀሰቅስብኝ ቦታ መፍረሱን ሳይ መጀመርያ ምቾት ሰጠኝ ። ትንሽ ሲቆይ ቅር አለኝ። የሆነ ፍቅሬም ፣ ትውስታዬም የመቀማት አይነት ። ለፒያሳ አስመስዬ ለትዝታዬ ፣ ለትውስታዬ ብዙ ላሳለፍኩበት ስፍራ አለቀስኩ ። አንድ አንድ ሰዎች ያረጀ ቤት ፣ የንግድ ሱቆች ፣ ሰፈር የፈረሰ ይመስላቸዋል ....ትዝታ ፣ ታሪክ ነው የፈረሰው። ማነው የኛ ፍቅር ላይ በግዴለሽነት የተረማመደው ማነው ትዝታችንን ካለውቀት የደረመሰው ?? ከዚ ሁሉ በኃላ ፒያሳ ...ፒያሳ ሲባል እንደነግጥ ይሆን ? ©Adhanom Mitiku
8884Loading...
23
ባዶ እጆች ነን። ባዶ እጅ ይሰጣል፣ ባዶ እጅ ይቀበላል። "ስለ እናት down syndrome እና otisem የተጠቁ ህፃናትን እና ወላጅ ያጡ ህፃናትን ማሳደጊያ"  አዲስ አበባ ፤ ሣር ቤት በተለምዶ ቫቲካን ኤንባሲ አካባቢ  ለሚገኘው የተራድኦ ድርጅት ->የልብስ(የተለበሰ፣ ቤት የተቀምጠ የማያገለግሉ ጫማና ልብሶችን እና ሌሎችም... ) ➙የንፅህና መጠበቂያዎችን (ሳሙና፣ ዳይፐር፣ ሶፍት፣ ሞዴስ እና ሌሎችም....) ->ምግብወጪ መሸፈን የምትፈልጉ ->የመማሪያ ግብአቶች(ደብተር፣ እስኪርብቶ፣ ቦርሳ እና ሌሎችም...) -> መፅሀፍቶች (አዲስና አሮጌ፣ አጋዥና መማሪያ፣ የስነልቦና እና ስነጽሑፍ አዘል ተነበው ከቤታችሁ የተቀመጡ መፅሀፍት እና ሌሎችም...) ማገዝ ከፈለጋችሁ 👇 ➙ በአዲስአበባ ኤዞፕ ቤተ መጽሐፍት። አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት የሚገኘው መደብር እየሄዳቹህ ከእነሱ ዘንድ #ለባዶ_እጆች በማለት ማስቀመጥ ትችላላችሁ። ወይም በስልክ ቁጥር-> #0911723656 መሳይ ብትሉ ታገኙታላቹህ። ➙ወይም እነሆ መጻሕፍት ➍ኪሎ ምኒሊክ ት/ቤት ፊት ለፊት ሮሚና ዝቅ ብሎ #ለባዶ_እጆች በማለት ወይም በስ.ቁ-> #0912735000 ➙እንደዚሁም በአብርሆት እና ጃፋር መጽሐፍ መደብር በሚቀርባችሁ አከባቢ ጎራ እያላችሁ #ለባዶ_እጆች በማለት ያላችሁን የቁሳቁስ እገዛ ማድረግ ትችላላችሁ። እኛም አሰባስበን ከልዩ እና ከሚያምር ዝግጅት ጋር ለ "ስለ እናት " የበጎ አድራጎት ድርጅት ከባዶ እጆች፤  ለተዘረጉልን ባዶ እጆች ልንሰጥ ተዘጋጅተናል እና ባዶውን እጃችንን ሙሉሉን። ለበለጠ መረጃ እና በቅርበት ለማውራት ይደውሉ⬇ 0906945795 0964668988 0946408853 እናመሰግናለን 🙏
8720Loading...
24
ከ በእምነት ላይብረሪ
8696Loading...
25
“ቆልፎ ያስቀረኝ ጽሑፍ!” ሳይጀመር የተደመደመ ሕይወት ከሶስት አመት በፊት አንድ የአርባ አመት እድሜ ላይ የነበረ ሰው ሳማክረው፣ የሚሰራውን የስራ አይነት ከገለጠልኝ በኋላ እንዲህ ሲል አጫወተኝ፡- “የምሰራውን ስራ አልወደውም፣ ምክንያቱም በእጄ ላይ ብዙ ሞያዎች እያሉኝ ስራዬ ግን ምንም ሞያ የማይጠይቅና ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ የማያልፍ ክፍያ የሚከፍል ነው፡፡ በዚህ ስራ ከተሰማራሁ አስራ ሁለት አመቴ ነው፡፡ አሁን ግን እጅግ መረረኝ”፡፡ ይህንን ንግግሩን ካደመጥኩ በኋላ በመጀመሪያ የጠየኩት ጥያቄ፣ “ለምን በዚህ ስራ ይህንን ያህል አመት ለመቆየት ፈለክ?” የሚል ነበር፡፡ “በፍላጎት ነው ብለህ ነው?!” አለኝ፣ አንገቱን በማቀርቀር፡፡ “ታዲያ በምንድን ነው?” አልኩት፣ ከተል አድርጌ፡፡ እርሱም በግልጽነት ለምን በዚያ ስራ እንደከረመ በግልጽ ነገረኝ፡፡ “ገና በሃያዎቹ መጨረሻ እድሜዬ ላይ አንድ ቀን በመንገድ ቆሜ ያንኑ ስራዬን እንዴት መቀየር እንዳለብኝ በማሰላሰል ላይ ሳለሁ ነፋስ ያባረረው አንድ የመጽሔት ቁራጭ ፊቴ ደረሰ፡፡ ማንበብ ስለምወድ አነሳሁትና ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ሳይቀደድ የተረፈው ክፍል ርእስ እንዲህ የሚል ነበር፣ የሚሆነው ይሆናል፣ የማይሆነው ደግሞ አይሆንም፡፡ ቀልቤን ሳበኝና ማንበብ ቀጠልኩ፡፡ በወቅቱ የሚበላኝን የሕይወቴን ሁኔታ እንዳከከልኝ ተሰማኝ”፡፡ ትንሽ በዝምታ ከተዋጠ በኋላ መናገሩን ቀጠለ፡፡ “ጽሁፉን ሙሉውን ሳነበው የሚናገረው የአንድ ሰው ፍጻሜ ገና ሳይወለድ የተወሰነና የተደመደመ እንደሆነ፣ ሁሉም ሰው ሕይወት የሚያቀብለውን የቅድመ-ውሳኔ ገጠመኝ ከመቀበልና ከመኖርና ውጪ ምንም ማድረግ እንደማይችል ነው፡፡ በጣም ደነገጥኩኝ፡፡ ጽሑፉ ባለሁበት ኖሬ፣ በዚሁ ሁኔታ ከማለፍ ውጪ ምንም ብታገል የተመደበልኝን መለወጥ እንደማልችል በደንብ አድርጎ አሳመነኝ፡፡ አለቀ! ከእለት ጉርስ ለማያሻግር ስራ ሰክኜ ለአመታት የመቆየቴ ሁኔታ የተቀበልኩት የመጣው ያንን ጽሑፍ ካነበብኩኝ በኋላ ነው፡፡” “ለምን የጽሑፉን ሃሳብ ዝም ብለህ አምነህ ተቀበልከው” አልኩት፡፡ ሲመልስልኝም፣ “እኔ ቤተሰቦቼ ማን እንደሆኑ የማላውቅ፣ እድሜዬን ሁሉ ብቻዬን ታግዬ የኖርኩ ሰው ነኝ፡፡ ራሴንና ኑሮዬን ለመለወጥ የሞከርኩ፣ ነገር ግን ሁሉም ነገር አልለወጥ ብሎ ያስቸገረኝ ሰው እንደሆንኩ ቀድሞውኑ አስብ ስለነበረ ጽሑፉ ያንኑ ዝንባሌዬን አጠናከረውና አመንኩት፡፡” ከዚህ ንግግራችን በኋላ ከእሱ ጋር ብዙ የምክክር ጊዜ አሳልፈናል፡፡ አሁን አመለካከቱን፣ ራሱንና ስራውን ለውጦ እንዲያውም ሌሎችን መካሪና ደጋፊ ሆኗል፡፡ በቅርቡ ሳገኘው ያየሁበት ለውጥ አስገራሚ ነው፡፡ ይህንን ታሪኩንም በጽሑፌ እንዳካፍልም ፈቀደልኝ፡፡ የሚኖሩት ኑሮ አንዴ የተወሰነና ሊለወጥ የማይችል እንደሆነ የሚያስቡ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ ፈረንጆቹ ይህንን አመለካከት fatalistic attitude ይሉታል፡፡ ያለቀለትና ቅድመ-ድምዳሜ ተወስኖለት የተጀመረ ሕይወት እንዳለን ማመንን የሚጠቁም ሃሳብ ነው፡፡ ይህ አይነቱ አመለካከት ያላቸው ሰዎች በሕይወታቸው ያለውን ምንም ነገር ለመቀየር አቅሙ እንደሌላቸው ነው የሚያስቡት፡፡ የወቅቱ ኑሯቸው ሁኔታ ለእነሱ የተመደበና ምንም ቢታገሉ ሊለወጥ እንደማይችል ያስባሉ፡፡ ስለዚህም የነበረውንና ያለውን በመቀበል ያዘግማሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች በዙሪያቸው ብዙ ሰዎች በማለም፣ በመስራትና በማመን ሕወታቸውን ሲለውጡ እያዩ እንኳን ንቅንቅ አይሉም፡፡ ምክንያቱም እነዚያኞቹ በሕይወታቸው የሚያዩት ለውጥም ሳይቀር ቀድሞውኑ ለእነሱ የተወሰነላቸው እንደሆነ ስለሚስቡ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ራስን ለማሻሻል ምንም አይነት መነሳሳት ስማይኖራቸው የመጣላቸውን እየተቀበሉና ያንኑ እየኖሩ ዘመናቸውን ይጨርሳሉ፡፡ ሕይወት ግን እንደዚያ አይደለችም፡፡ ሕይወት የምርጫ መስክ ነች፡፡ ሕይወት የዘራነውን የምናበቅልባት መሬት ነች፡፡ ሕይወት ፈቃዳችንን፣ ጉልበታችንንና ሌሎችንም እሴቶቻችንን አስተባብረን ከአንድ ደረጃ ወደሌላኛው ደረጃ እንደመሰላል የምንወጣት የምታጓጓ መስክ ናት እንጂ ታሪካቸው ተጽፎና አልቆ ያከተመለትና ፍጻሜ የተበየነባቸው ሰዎች መተራመሻ አይደለችም . . . ✍️ ዶክተር አዮብ ማሞ
9928Loading...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
👍 5 2
...ተመልሳ እንደማትመጣ ልቡ ያቃዋል…ብቻ ልፋ ቢለው እንደሆነም ይረዳዋል…ቀኑን ሙሉ ሲያማትር ቢውልም አንዳች አዲስ ነገር እንደማይፈጠር ከእሱ በላይ ማንም ሊያውቅ አይችልም…ማንም! …ግን እራሱን መሟገት አይፈልግም…ባትመጣም ትመጣለች ማለትን ይመርጣል…እራሱንም መሸወድ፣ ከራሱ ጋር ፀብ እንደሆነ ቅንጣት ታህል አይጠፋውም…ግን "አትመጣም" ከሚለው የእውነት ጩኽት ይልቅ "ትመጣለች" የሚለው ሹክሹክታ ለእሱ ሰላም አለው። …ከሰላም በላይ ደሞ ምን አለ?   ✍🏽 ፊሊሞን የማርያም ልጅ
Mostrar todo...
👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
👍 8
Photo unavailableShow in Telegram
📙 ይድረስ ለውዷ ፊያሜታ ጊላይ... እንደምን አለሽልኝ..? እኔ በልጅነቴ ፍቅር እስከ መቃብር ነው ሲሉ ሰምቼ ዙቤይዳን እስከማገኝ ድረስ ኦሮማይን የሙጥኝ ብየ ነበር የቆየሁት። ሳድግ የፍርድ ቀን ዘመቻ ላይ ሆኜ በትኩሳት እየተንቀጠቀጥኩኝ... መልህቅ እንደሌለው መርከብ እየተናወጥኩኝ... ሌቱም አይነጋልኝ ስል ተገኘሁ። ሌላ ጊዜ ደግሞ ከአመጓ እስከ ዝጎራ እያካለልኩ መርበብትና ሰበዝን ይዤ በጠበኛ እውነቶች ስም አንፈርስም አንታደስም የሚል መፈክር ማሰማት ጀመርኩኝ። አይይይ... ይሄ ነገሬ እንኳን ለኔም አልገባኝም... ብቻ ሌላ ሰው ላይ ስፎክር እንደ ኢያሪኮ ግንብ በቅፅበት ለመፍረስ እንዳይሆንብኝ ሁሉቱ ጊዮርጊሶች ይጠብቁኝ። 📙 ይገርምሻል አንዳንድ ቀንና ህይወት ርዕስ የለውም ይባላል። ብዙ ሰው የሚስማማበት ሃሳብ ግን ያፍቃሪ ሰው ትንፋሽ ልክ እንደ መንደሪን ጣፋጭ መድሃኒት መሆኑን ነው። ከዕለታት ግማሽ ቀን ቤተልሄምን ተይው ፖለቲካን ዝም ብለሽ ሳሚኝ እያልኳት ሀገር ያጣ ሞት ድንገት በጠቢባን መንገድ በኩል ሲመጣብኝ ምንሽሮን ዋስ ጠርቼ አመለጥኩት። በሰሞነ ህማማት ደግሞ ገላና ገላዬ ሲታመሙብኝ ትዝታሽን ለኔ ትዝታየን ለአንቺ እያሰብኩኝ አሳለፍኩ። 📙 አንቺዬ ደግሞ ያልተነገረ ተረክና ያልተፃፈ ኑረት ታሪክ አይሆንምና አንድ ቀን ሜሎሪናን ህልምሽን አጫውችኝ ብያት ስታወጋኝ የአማኑኤል ሆስፒታል ታሪኮችን አስታወሰችኝ። እግረ መንገድ ይሁን እንጅ ዶክተር አሸብር የታካሚውንና የልብ ጠጋኙን ማስታወሻ እያገላበጠ ፊት ለፊቱ አሳንቲ የሰማይ ላይ ስዕል መስላ እንደተሰየመች በምናቤ ውል አለችብኝ። በመጨረሻም ከዚህ በላይ የነገርኩሽን ታሪክ ጨምሮ የአና ማስታወሻ፣ ዮቶርና ፖፒዮ የተሰኙትን ዜማዎች ከወንድም ሐሽማል ጋር ጋብዠሻለሁ። . . ያንቺው ጠኃ ባላደራ ...! የመፅሃፍት ስምና ገፀባህርያትን በመጠቀም የተፃፈ ታሪካዊ ደብዳቤ:: ✍️ መሳይ አርቀው ፊያሜታ ተናፍቀሻል🥰 ስንቶችን አንብበዋል?😊 ⛵️⛵️⛵️ "ማንበብ ፋሽን ነው።" Join us @noahbookdelivery
Mostrar todo...
7👍 2👎 1🔥 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
👍 6👏 4
Photo unavailableShow in Telegram
👍 1