cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ዮሐንስ ጌታቸው

ርቱዕ ሐልዮ ጥያቄና አስተያየት ካልዎት ይስጡ! @tmhrte_tsdk_bot

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 897
Suscriptores
+224 horas
+47 días
+530 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
#በኩረ_መዘምራን_ኪነ_ጥበብ_ወ/ቂርቆስ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ብዙ አበርክቶዎችን ያደረጉ፤ በመዝሙራቸው ብዙዎችን ያጽናኑ፣ የብዙዎችንም ልቡና ወደ ንስሐ የመሩ፤ ከ50 ዓመታት በላይ ቤተ ክርስቲያንን ያገለገሉ። በዝማሬያቸው መሐል የሚመክሩ፣ የሚያጽናኑ አባታችን ቀድሞ ያማቸው በነበረው የጀርባ ሕማም ታመዋልና ለሕክምና ይኾናቸው ዘንድ እባክዎትን የበኩልዎትን ያድርርጉ ዘንድ ግዴታ እንዳለብዎት በመረዳት ከታች በተቀመጠው የእርሳቸው አካውንት ያስገቡ። በእርግጥ እርሳቸውን ተለምነን አልነበረም ማሳከም የነበረብን፡ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ኹሉ አሟልተን ልንንከባከባቸው ይገባ ነበር። ግን ያው ብዙዎቻችን እውነተኛ አገልጋዮችን በአግባቡ ባለመከታተላችን በብዙ ችግር ውስጥ ኾነው ያገለግላሉ። አርአያ የሚኾኑንን ባናሳዝናቸውና በረከት ብናገኝባቸው መልካም ነው። እንግዲህ የባንክ አካውንታቸው ይኸው እንረባረብ! CBE 1000481007287 KINETIBEB W/KIRKOS W/MESKEL CMC Michael Branch
Mostrar todo...
MK TV || የወጣቶች ገጽ || የዓይን ፍቅር እንደቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እንዴት ይታያል? https://youtube.com/watch?v=aChY_ZFvMPs&si=mexiKLxmL-lB6Q0i
Mostrar todo...

የደማስቆው ጴጥሮስ ፦ "ሕይወት ከጭንቀት ነጻ የኾነ ተስፋ ነው፤ ሀብት ከስሜቶች የተሰወረ ነገር ግን በመረዳት እና በነገሮች እውነተኛ ተፈጥሮ የተረጋገጠ ነው።" ይላል። St. Peter of Damaskos (Twenty-Four Discourses no. 6, The Philokalia Vol. 3 pg 224)። ይህ ሊቅ ሕይወት ከክፉ ጭንቀት የራቀ ወይም ነጻ የኾነና በተስፋ የተመላ መኾኑን ይገልጻል። ያልተገባ ጭንቀት ተስፋን የሚያጨልምና ሰዎችን በስጋትና ፍርሓት ዱላ የሚቀጠቅጥ መኾኑን ልብ ማለት ይገባል። አረጋዊው ፓይሲየስ እንዲህ ይላል፦ "በመንፈሳዊ አኗኗራችን የግድ ልንጠነቀቅ ይገባናል። መንፈሳዊ ሰዎች በከንቱ ውዳሴ ሲጠቁ፥ በጣም ትንሽዬ እርካታ ይሰማቸዋል፤ ነፍሳቸው ደግሞ በባዶነት ስሜት ይቀራል። ... የከንቱነት ስሜት ሲጨምር ውስጣዊ የኾነ የባዶነት ስሜት የባሰ ያሠቃያቸዋል። ጭንቀትና ተስፋ መቍረጥ ሲኖር አጋንንት በመንፈሳዊ ሕይወትህ ላይ ሥራ ላይ ናቸው ማለት ነው። ስለ ምንም ነገር ልትጨነቅ አይገባም። ጭንቀት የዲያብሎስ ሥራ ነውና። ጭንቀትን ባየህ ጊዜ ሰይጣን ጣልቃ እንደ ገባ እርግጠኛ ኹን።" https://www.orthodoxroad.com/anxiety-and-burning-out-in-the-christian-struggle/። ክፉ ጭንቀት ኹል ጊዜም ቢኾን ሰይጣናዊና ጎጂ እንደ ኾነ ከዚህ ልብ ልንል ይገባናል። ተስፋ ወደ መቍረጥና እምነት ወደ ማጣት፥ ራስንም ወደ መጥላት የሚወስደን ጭንቀት ከሰይጣን እንደ ኾነ ኹል ጊዜም ቢኾን ልናውቅና ልንጠነቀቅ ይገባል። https://t.me/phronema
Mostrar todo...
ዮሐንስ ጌታቸው

ርቱዕ ሐልዮ ጥያቄና አስተያየት ካልዎት ይስጡ! @tmhrte_tsdk_bot

+++++++++++#ጭንቀት#++++++++++ ጌታችን በወንጌል ጭንቀትን አስመልክቶ ሲናገር ስለ ልብስ፣ ስለ ምግብ ብለን ልንጨነቅ እንደማይገባን ያስጠነቅቀናል። የሕይወት ዓላማችን ስለዚህ ስለሚቀረው ልብስ ማማር ወይም ጌጠኛ መኾን አለመኾንን እያሰቡ መጨነቅ አይደለም። ልብስ ቀሪ ነገር ነውና። ከድኅነታችን በላይ ስለ ልብስ ውበት የምንጨነቅ እጅግ ብዙ ነን። ይህ ታዲያ ጉዳት አይደለምን? ያማረ ልብስ መርጠን ውጫዊ ውበታችንን ለማሳመር እንጥራለን፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ እንድንወደድ የሚያደርገውን መልካም ሥራ ቸል እንላለን። መጨነቅ ለሚገባን ሳንጨነቅ በስንፍና ኾነን ለማያስጨንቀው በእጅጉ ስንጨነቅ እንገኛለን። ጌታችን ለዚህ ነው "ስለዚህም እላችኋለሁ ለነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ለሥጋችሁም በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል አትበልጥምን? ሥጋስ ከልብስ አይበልጥምን? የማይዘሩና የማያጭዱ በጎተራም የማይሰበስቡ የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ፤ ሰማያዊ አባታችሁ ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ ትበልጡ የለምን? ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው? ስለ ልብስ ለምን ትጨነቃላችሁ? የምደረበዳ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ እዩ፤ ... እንግዲህ ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ። ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይሹታልና፤ ለእናንተ ግን ሰማያዊ አባታችሁ ይህን ሁሉ እንድትሹ ያውቃል። እናንተስ አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።" ይላል። ማቴ 6፡25-34። እንግዲህ ይህ አምላካዊ ቃል የሰዎች የመጀመሪያ ምርጫና ትኩረት ምን መኾን እንዳለበት በራሱ በአምላካችን የተገለጸ ነው። ልብሶቻችን ሥርዓት የለሽ የኾኑት የሕይወት ዓላማችን ምድራዊ ተድላ ላይ እንዲመሠረት ስላደረግነው ነው። ሁለቱ ነገሮች በሕይወታችን ተገለባብጠዋል። በጣም የሚያሳፈልገንን ትተነው ብዙም የማይጠቅመንን አጥብቀን ይዘነዋል። ከእግዚአብሔር ሐሳቤ ይልቅ የራሳችንን ስሜት ቀዳሚ ቦታ ላይ አስቀምጠናል። ስለ አለባበሳችን ደጋግመን ከማሰባችን የተነሳ ወደ መጨነቅ ደርሰናል። ልክ አንዲት እናት ምጥ ይዟት እንደ ምትጨነቅ እኛም የኃጢአት ምጥ ይዞን በእጅጉ እንጨነቃለን። አትጨነቁ ያለንን አምላክ ለመስማት ፈቃደኛ መኾን እስኪያቅተን ድረስ ስለ ልብስ በማሰብ በጭንቀት ተወጥረናል። ስለዚህ ልብስ ከመልበሳችን በፊት ይህን ረጋ ብለን እናስብ! ፈጣሪያችን እያዘነብን እንደ ኾነ እናስተውል። ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ከላይ ያለውን ጥቅስ መሠረት አድርጎ በፍጹም ስለ ልብስ ብለን መጨነቅ እንደሌለብን ይመክረናል። "... በዚህም ልንጨነቅ እንደማይገባን ብቻ ሳይኾን ሰዎች በሚለብሷቸው ውድ አልባሳትም ጭምር ልንማረክ (ልንቀና) እንደማይገባን አስተማረን። ለምን ቢሉ እንደዚህ ያለው ውበት እንደ ሣር ነውና፤ እንደዚህ ያለው መልክ እንደ ቡቃያ ነውና። እንዲያውም ሣር እንደዚህ ካሉት አልባሳት ይልቅ እጅግ ውድ ነው። ታዲያ በውድነት ደረጃ ሣር እንኳን ሳይቀር በሚበልጣቸው ነገሮች ራስህን የምታስታብየው ለምንድን ነው? ... ለምሳሌ "የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ" ካለ በኋላ "አይደክሙም" ብሎ ጨምሮ ተናግሯልና። ይህም የሚለን እነዚህን ትእዛዛት የሚሰጠን በፍላጎት ከድካም አርነት ሊያወጣን ሽቶ ነው። በርግጥ ድካሙ ያለው አለመጨነቁ ላይ ሳይኾን ስለ እነዚህ ነገሮች መጨነቅ ላይ ነውና። "አይዘሩም" ብሎ መናገሩም መዝራት መከልከሉን አይደለም፤ እጅግ መጨነቅን ነው እንጂ። ልክ እንደዚሁ "አይደክሙም አይፈትሉምም" ሲልም ሥራን ሳይኾን በዚህ ዓለም አሳብ እጅግ መጨነቅን ሲከለክል ነው።" ይላል። (ገብረ እግዚአብሔር ኪደ (ተርጓሚ)፣ የማቴዎስ ወንጌል ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንደተረጎመው ድርሳን 1-24፣ 1ኛ ዕትም የካቲት 2011 ዓ.ም፣ ገጽ 424-425)። እንግዲህ ልብስ ለመልበስ ስንዘጋጅ ስለ ውበቱ በማሰብ እስከ መጨነቅ ድረስ መጓዝ ምን ያህል ጉዳት እንደ ኾነ ልብ እንበል። በተለይ ደግሞ የልብስን ኃላፊነት ረስቶ ራስን ማራኪ አድርጎ ለማቅረብ የሚደረግ መጨነቅ በእጅጉ የተነቀፈ ነው። አኹን የምንለብሰው ልብስ የሚያረጅ፣ የሚቀደድ፣ የሚያልቅ፣ የሚጣል ልብስ ነው። ልብሱን ተጠቅመን ስናበቃ እንጥለዋል፥ ኾኖም በኋላ ለምንጥለው ልብስ ልቡናችንን እናስገዛለን፥ ይህ ሁሉ አእምሮ ካለው ሰው የሚጠበቅ አልነበረም። ሐሳባችን በሙሉ ምድራዊ መኾኑን በዚህ እንወቅ። ሊቁ በተጨማሪ "በመጨነቃችን ራሳችንን ከመጉዳት የዘለለ ሌላ የምናተርፈው ወይም የምናገኘው ነገር የለምና። እግዚአብሔር ብንጨነቅም ባንጨነቅም የሚያስፈልገንን ነገር ይሰጠናልና። በተለይ ደግሞ የማንጨነቅ ስንኾን የሚያስፈልገንን ነገር እንደሚያስፈልገን ዐውቆ ይሰጠናል። እንደዚህ ከኾነ ታዲያ እንዲያውም "አትጨነቅ" የሚለውን ትእዛዝ በመተላለፍ ተጨማሪ ቅጣት በራስ ላይ ከማምጣት በቀር ተጨንቀህ የምታተርፈው ምንድን ነው? አንድ ሰው ወደ ባለጠጋ ሰው ቤት ለግብዣ እየሄደ "ምን እበላለሁ?" ብሎ አይጨነቅም፤ ወደ ምንጭ ውኃ እየሄደ "ምን እጠጣለሁ?" ብሎ አይብከነከንም። እንግዲያውስ እኛም ከየትኛውም ዓይነት ምድራዊ ምንጭ በላይ የተትረፈረፈ ውኃ ወይም ቁጥር የሌለው የተሰናዳ ማዕድ አለንና እርሱን እያየን ነዳያን ወይም በአእምሮ ሕፃናት አንኹን። ይኸውም መግቦተ እግዚአብሔርን ማለቴ ነው።" ይላል። (እንደ ላይኛው ገጽ 429)። ዮሐንስ ዘሰዋስው ፦ " በእውነት ጌታን የሚወድ፣ የሚመጣ መንግሥቱን ለማግኘት ብሎ እውነተኛ ጥረት ያደረገ፣ በእውነት ስለ ኃጢአቶቹ ያዘነ፣ በእውነት ስለ ዘለዓለማዊ ሥቃይና ፍርድ የሚያስብ፣ በእውነት ጊዜ ሞቱን እያሰበ በፍርሓት የሚኖር ሰው፣ ስለ ገንዘብ ፍቅር ወይም ስለ ንብረቶች፣ ወይም ስለ ቤቶች፣ ወይም ስለ ዓለማዊ ክብር፣ ወይም ስለ ወዳጆቹ፣ ወይም ስለ ወንድሞቹ ወይም በምድር ስላሉት ማናቸውም ነገሮች ኹሉ የሚጨነቅ ወይም የሚያስብ አይደለም። ነገር ግን ምድራዊ የሚኾኑ ማዕሠሮችን ኹሉ በማራገፍ፣ የገዛ ጭንቀቶቹንም ኹሉ በመግፈፍ ... ያለ ማመንታት ኾኖ ክርስቶስን ይከተላል።" ይላል። (ሳሙኤል ፈቃዱ (ሐተታ እና ትርጒም)፣ ምዕራግ እና ድርሳን፣ 2011 ዓ.ም፣ ገጽ 100-101)። ሕሊናችንን ኹል ጊዜ ከፍ ወዳለው ሰማያዊ ነገር ልናበርረው ይገባናል። በዚህ ዓለም እስካለን ድረስ ለሥጋዊ ሕይወታችን የሚያስፈልጉን ብዙ ነገሮች መኖራቸው የታወቀ ቢኾንም፥ በአግባቡ በምንሠራው ሥራ እግዚአብሔር በፈቀደው መንገድ ተጉዘን ማግኘት ይገባናል እንጂ በብልጣብልጥነት መንገድ በመጓዝና የተፈጠርነው ለቍሳዊ ነገር እንደ ኾነ እስኪያስመስልብን ድረስ ትክዝ ብለን በመጨነቅ አይደለም። ያልተገደቡ ፍላጎቶች እንዲኖሩን አድርገን ራሳችንን ስላላመድን፥ እኒያን ያስፈልጉናል የምንላቸውን ነገሮች የምናጣቸው መስሎ ሲሰማን ገና በሩቁ እጅግ በጣም እንጨነቃል። ይህ በስግብግብነታችን ምክንያት የሚመጣብን ጭንቀት ኋላ እያገረሸ ይሄድና ፍላጎቶቻችንን ማሟላት ሲያቅተን ራስን ወደ ማጥፋት ችኲል ውሳኔ ውስጥ እንገባለን።
Mostrar todo...
Anxiety and Burning Out in the Christian Struggle - Orthodox Road

When asked about lay people coming home from a hard day of work and feeling too tired to complete a service commonly done after the evening meal, St. Paisios replied: When they come home at night from work and feel tired, they should never pressure themselves and become anxious.  Instead, they should always say to … Continue reading Anxiety and Burning Out in the Christian Struggle

የደማስቆው ጴጥሮስ ፦ "ሕይወት ከጭንቀት ነጻ የኾነ ተስፋ ነው፤ ሀብት ከስሜቶች የተሰወረ ነገር ግን በመረዳት እና በነገሮች እውነተኛ ተፈጥሮ የተረጋገጠ ነው።" ይላል። St. Peter of Damaskos (Twenty-Four Discourses no. 6, The Philokalia Vol. 3 pg 224)። ይህ ሊቅ ሕይወት ከክፉ ጭንቀት የራቀ ወይም ነጻ የኾነና በተስፋ የተመላ መኾኑን ይገልጻል። ያልተገባ ጭንቀት ተስፋን የሚያጨልምና ሰዎችን በስጋትና ፍርሓት ዱላ የሚቀጠቅጥ መኾኑን ልብ ማለት ይገባል። አረጋዊው ፓይሲየስ እንዲህ ይላል፦ "በመንፈሳዊ አኗኗራችን የግድ ልንጠነቀቅ ይገባናል። መንፈሳዊ ሰዎች በከንቱ ውዳሴ ሲጠቁ፥ በጣም ትንሽዬ እርካታ ይሰማቸዋል፤ ነፍሳቸው ደግሞ በባዶነት ስሜት ይቀራል። ... የከንቱነት ስሜት ሲጨምር ውስጣዊ የኾነ የባዶነት ስሜት የባሰ ያሠቃያቸዋል። ጭንቀትና ተስፋ መቍረጥ ሲኖር አጋንንት በመንፈሳዊ ሕይወትህ ላይ ሥራ ላይ ናቸው ማለት ነው። ስለ ምንም ነገር ልትጨነቅ አይገባም። ጭንቀት የዲያብሎስ ሥራ ነውና። ጭንቀትን ባየህ ጊዜ ሰይጣን ጣልቃ እንደ ገባ እርግጠኛ ኹን።" https://www.orthodoxroad.com/anxiety-and-burning-out-in-the-christian-struggle/። ክፉ ጭንቀት ኹል ጊዜም ቢኾን ሰይጣናዊና ጎጂ እንደ ኾነ ከዚህ ልብ ልንል ይገባናል። ተስፋ ወደ መቍረጥና እምነት ወደ ማጣት፥ ራስንም ወደ መጥላት የሚወስደን ጭንቀት ከሰይጣን እንደ ኾነ ኹል ጊዜም ቢኾን ልናውቅና ልንጠነቀቅ ይገባል።
Mostrar todo...

+++++++++++#ጭንቀት#++++++++++ ጌታችን በወንጌል ጭንቀትን አስመልክቶ ሲናገር ስለ ልብስ፣ ስለ ምግብ ብለን ልንጨነቅ እንደማይገባን ያስጠነቅቀናል። የሕይወት ዓላማችን ስለዚህ ስለሚቀረው ልብስ ማማር ወይም ጌጠኛ መኾን አለመኾንን እያሰቡ መጨነቅ አይደለም። ልብስ ቀሪ ነገር ነውና። ከድኅነታችን በላይ ስለ ልብስ ውበት የምንጨነቅ እጅግ ብዙ ነን። ይህ ታዲያ ጉዳት አይደለምን? ያማረ ልብስ መርጠን ውጫዊ ውበታችንን ለማሳመር እንጥራለን፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ እንድንወደድ የሚያደርገውን መልካም ሥራ ቸል እንላለን። መጨነቅ ለሚገባን ሳንጨነቅ በስንፍና ኾነን ለማያስጨንቀው በእጅጉ ስንጨነቅ እንገኛለን። ጌታችን ለዚህ ነው "ስለዚህም እላችኋለሁ ለነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ለሥጋችሁም በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል አትበልጥምን? ሥጋስ ከልብስ አይበልጥምን? የማይዘሩና የማያጭዱ በጎተራም የማይሰበስቡ የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ፤ ሰማያዊ አባታችሁ ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ ትበልጡ የለምን? ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው? ስለ ልብስ ለምን ትጨነቃላችሁ? የምደረበዳ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ እዩ፤ ... እንግዲህ ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ። ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይሹታልና፤ ለእናንተ ግን ሰማያዊ አባታችሁ ይህን ሁሉ እንድትሹ ያውቃል። እናንተስ አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።" ይላል። ማቴ 6፡25-34። እንግዲህ ይህ አምላካዊ ቃል የሰዎች የመጀመሪያ ምርጫና ትኩረት ምን መኾን እንዳለበት በራሱ በአምላካችን የተገለጸ ነው። ልብሶቻችን ሥርዓት የለሽ የኾኑት የሕይወት ዓላማችን ምድራዊ ተድላ ላይ እንዲመሠረት ስላደረግነው ነው። ሁለቱ ነገሮች በሕይወታችን ተገለባብጠዋል። በጣም የሚያሳፈልገንን ትተነው ብዙም የማይጠቅመንን አጥብቀን ይዘነዋል። ከእግዚአብሔር ሐሳቤ ይልቅ የራሳችንን ስሜት ቀዳሚ ቦታ ላይ አስቀምጠናል። ስለ አለባበሳችን ደጋግመን ከማሰባችን የተነሳ ወደ መጨነቅ ደርሰናል። ልክ አንዲት እናት ምጥ ይዟት እንደ ምትጨነቅ እኛም የኃጢአት ምጥ ይዞን በእጅጉ እንጨነቃለን። አትጨነቁ ያለንን አምላክ ለመስማት ፈቃደኛ መኾን እስኪያቅተን ድረስ ስለ ልብስ በማሰብ በጭንቀት ተወጥረናል። ስለዚህ ልብስ ከመልበሳችን በፊት ይህን ረጋ ብለን እናስብ! ፈጣሪያችን እያዘነብን እንደ ኾነ እናስተውል። ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ከላይ ያለውን ጥቅስ መሠረት አድርጎ በፍጹም ስለ ልብስ ብለን መጨነቅ እንደሌለብን ይመክረናል። "... በዚህም ልንጨነቅ እንደማይገባን ብቻ ሳይኾን ሰዎች በሚለብሷቸው ውድ አልባሳትም ጭምር ልንማረክ (ልንቀና) እንደማይገባን አስተማረን። ለምን ቢሉ እንደዚህ ያለው ውበት እንደ ሣር ነውና፤ እንደዚህ ያለው መልክ እንደ ቡቃያ ነውና። እንዲያውም ሣር እንደዚህ ካሉት አልባሳት ይልቅ እጅግ ውድ ነው። ታዲያ በውድነት ደረጃ ሣር እንኳን ሳይቀር በሚበልጣቸው ነገሮች ራስህን የምታስታብየው ለምንድን ነው? ... ለምሳሌ "የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ" ካለ በኋላ "አይደክሙም" ብሎ ጨምሮ ተናግሯልና። ይህም የሚለን እነዚህን ትእዛዛት የሚሰጠን በፍላጎት ከድካም አርነት ሊያወጣን ሽቶ ነው። በርግጥ ድካሙ ያለው አለመጨነቁ ላይ ሳይኾን ስለ እነዚህ ነገሮች መጨነቅ ላይ ነውና። "አይዘሩም" ብሎ መናገሩም መዝራት መከልከሉን አይደለም፤ እጅግ መጨነቅን ነው እንጂ። ልክ እንደዚሁ "አይደክሙም አይፈትሉምም" ሲልም ሥራን ሳይኾን በዚህ ዓለም አሳብ እጅግ መጨነቅን ሲከለክል ነው።" ይላል። (ገብረ እግዚአብሔር ኪደ (ተርጓሚ)፣ የማቴዎስ ወንጌል ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንደተረጎመው ድርሳን 1-24፣ 1ኛ ዕትም የካቲት 2011 ዓ.ም፣ ገጽ 424-425)። እንግዲህ ልብስ ለመልበስ ስንዘጋጅ ስለ ውበቱ በማሰብ እስከ መጨነቅ ድረስ መጓዝ ምን ያህል ጉዳት እንደ ኾነ ልብ እንበል። በተለይ ደግሞ የልብስን ኃላፊነት ረስቶ ራስን ማራኪ አድርጎ ለማቅረብ የሚደረግ መጨነቅ በእጅጉ የተነቀፈ ነው። አኹን የምንለብሰው ልብስ የሚያረጅ፣ የሚቀደድ፣ የሚያልቅ፣ የሚጣል ልብስ ነው። ልብሱን ተጠቅመን ስናበቃ እንጥለዋል፥ ኾኖም በኋላ ለምንጥለው ልብስ ልቡናችንን እናስገዛለን፥ ይህ ሁሉ አእምሮ ካለው ሰው የሚጠበቅ አልነበረም። ሐሳባችን በሙሉ ምድራዊ መኾኑን በዚህ እንወቅ። ሊቁ በተጨማሪ "በመጨነቃችን ራሳችንን ከመጉዳት የዘለለ ሌላ የምናተርፈው ወይም የምናገኘው ነገር የለምና። እግዚአብሔር ብንጨነቅም ባንጨነቅም የሚያስፈልገንን ነገር ይሰጠናልና። በተለይ ደግሞ የማንጨነቅ ስንኾን የሚያስፈልገንን ነገር እንደሚያስፈልገን ዐውቆ ይሰጠናል። እንደዚህ ከኾነ ታዲያ እንዲያውም "አትጨነቅ" የሚለውን ትእዛዝ በመተላለፍ ተጨማሪ ቅጣት በራስ ላይ ከማምጣት በቀር ተጨንቀህ የምታተርፈው ምንድን ነው? አንድ ሰው ወደ ባለጠጋ ሰው ቤት ለግብዣ እየሄደ "ምን እበላለሁ?" ብሎ አይጨነቅም፤ ወደ ምንጭ ውኃ እየሄደ "ምን እጠጣለሁ?" ብሎ አይብከነከንም። እንግዲያውስ እኛም ከየትኛውም ዓይነት ምድራዊ ምንጭ በላይ የተትረፈረፈ ውኃ ወይም ቁጥር የሌለው የተሰናዳ ማዕድ አለንና እርሱን እያየን ነዳያን ወይም በአእምሮ ሕፃናት አንኹን። ይኸውም መግቦተ እግዚአብሔርን ማለቴ ነው።" ይላል። (እንደ ላይኛው ገጽ 429)። ዮሐንስ ዘሰዋስው ፦ " በእውነት ጌታን የሚወድ፣ የሚመጣ መንግሥቱን ለማግኘት ብሎ እውነተኛ ጥረት ያደረገ፣ በእውነት ስለ ኃጢአቶቹ ያዘነ፣ በእውነት ስለ ዘለዓለማዊ ሥቃይና ፍርድ የሚያስብ፣ በእውነት ጊዜ ሞቱን እያሰበ በፍርሓት የሚኖር ሰው፣ ስለ ገንዘብ ፍቅር ወይም ስለ ንብረቶች፣ ወይም ስለ ቤቶች፣ ወይም ስለ ዓለማዊ ክብር፣ ወይም ስለ ወዳጆቹ፣ ወይም ስለ ወንድሞቹ ወይም በምድር ስላሉት ማናቸውም ነገሮች ኹሉ የሚጨነቅ ወይም የሚያስብ አይደለም። ነገር ግን ምድራዊ የሚኾኑ ማዕሠሮችን ኹሉ በማራገፍ፣ የገዛ ጭንቀቶቹንም ኹሉ በመግፈፍ ... ያለ ማመንታት ኾኖ ክርስቶስን ይከተላል።" ይላል። (ሳሙኤል ፈቃዱ (ሐተታ እና ትርጒም)፣ ምዕራግ እና ድርሳን፣ 2011 ዓ.ም፣ ገጽ 100-101)። ሕሊናችንን ኹል ጊዜ ከፍ ወዳለው ሰማያዊ ነገር ልናበርረው ይገባናል። በዚህ ዓለም እስካለን ድረስ ለሥጋዊ ሕይወታችን የሚያስፈልጉን ብዙ ነገሮች መኖራቸው የታወቀ ቢኾንም፥ በአግባቡ በምንሠራው ሥራ እግዚአብሔር በፈቀደው መንገድ ተጉዘን ማግኘት ይገባናል እንጂ በብልጣብልጥነት መንገድ በመጓዝና የተፈጠርነው ለቍሳዊ ነገር እንደ ኾነ እስኪያስመስልብን ድረስ ትክዝ ብለን በመጨነቅ አይደለም። ያልተገደቡ ፍላጎቶች እንዲኖሩን አድርገን ራሳችንን ስላላመድን፥ እኒያን ያስፈልጉናል የምንላቸውን ነገሮች የምናጣቸው መስሎ ሲሰማን ገና በሩቁ እጅግ በጣም እንጨነቃል። ይህ በስግብግብነታችን ምክንያት የሚመጣብን ጭንቀት ኋላ እያገረሸ ይሄድና ፍላጎቶቻችንን ማሟላት ሲያቅተን ራስን ወደ ማጥፋት ችኲል ውሳኔ ውስጥ እንገባለን።
Mostrar todo...
+++++#ክርስቶስ_ተንሥአ_እሙታን#+++++ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፦ ክርስቶስ ከሙታን ተነሣ፥ የትንሣኤ ባለ ቤት ነውና አንድም ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ ብሏልና አንድም በአዳም የቀደመ ኃጢአት ምክንያት ይዛ ታስቀር ወይም ታበሰብስ የነበረችውን መቃብር እርሱ ገብቶ ለወጣትና የትንሣኤ ቦታ አድርጓታልና፤ ሞቶ መቅረት በእርሱ ሞት ተሽሮ ትንሣኤ በእርሱ ታወጀ ለማለት በክርስቶስ ትንሣኤ በኩል ለኹላችንም ትንሣኤ የተሰጠን መኾኑን ነገረን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አለ፦ ሞት የተሻረችው ትንሣኤ የተሰጠችው ሥልጣኑ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ በኾነለት በሥግው ቃል በኢየሱስ ክርስቶስ ነውና፤ አንድም በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን በአምላክነት ክብሩና ሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መበስበስን አስቀርቶ ተነሥቷልና። አሠሮ ለሰይጣን፦ ሰይጣንን አሠረው አለ፥ ሰይጣን ግዙፍ ኾኖ በገመድ የሚታሠር ኾኖ ሳይኾን የቀደመ ኃይሉን አድክሞበት ተነሣ አንድም የሠይጣን የቀደመ ሥልጣኑ ተወሰደበት (ጻድቃንን እንኳ ሳይቀር ወደ ሲኦል ያስገባ ነበርና) አንድም በአዳም ላይ ገዢ ኾኖ "አዳም ገብሩ ለዲያብሎስ ሔዋን አመቱ ለዲያብሎ" የሚል ደብዳቤ አጽፎ አዳምና ሔዋንን ባሪያው አድርጎ የሚገዛበት ኃይሉ ተወስዶበታልና አንድም ሰይጣን ታሠረ አለ እንደ ቀደመው በሙሉ ነጻነትና ሥልጣን እንዳያስት በቅዱስ መስቀሉ ተቀጥቅጦ ደክሞልና አንድም ምእመናን የመስቀሉን ምልክት ቢያሳዩት በርሮ ይጠፋልና። አግአዞ ለአዳም፦ አዳምን ነጻ አወጣው አለ ለምን ቢሉ በዲያብሎስ ባርነት ነበርና ከዚያ መውጣቱን ሲያይ አንድም የሞት ተገዢ ኾኖ ነበርና ከዚያ መውጣቱን ሲያይ አንድም ከባሕርይ መጎስቆል ከጸጋ መገፈፍ ከርግማን ኹሉ ክርስቶስ ኢየሱስ ነጻ አውጥቶታልና አንድም ከሲኦል ወጥቶ ወደ ቀደመ ስፍራው ወደ ገነት ተመልሷልና። ሰላም፣ እም ይእዜሰ፣ ኮነ፣ ፍስሐ ወሰላም፦ ከእንግዲህ ወዲህ ሰላም ፍጹም ደስታና ሰላም ኾነ፦ ይኸውም በክርስቶስ የተገኘች አዲስ ሕይወት ናት። እርሱ "የሰላም አለቃ" ተብሏልና በእርሱ የሚያምኑ ከእርሱ የምትገኘውን የእውነት ሰላም ደስታ ይወስዷታልና። ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰዎች ዘንድ የጠፋችውን ደስታና ሰላም መልሶ ሰጥቷቸዋልና አንድም በኢያንዳንዱ አማኝ ሰውነት ውስጥ የክርስቶስ ሰላምና ደስታ ከእንግዲህ ትገለጣለችና አንድም ጥላቻ ርቃ የክርስቶስ ፍቅር በክርስቲያኖች ዘንድ ትታያለችና አንድም ራሱ ክርስቶስ ራሱን ሰላምና ደስታ አድርጎ ለክርስቲያኖች ሰጥቷልና በእርሱ የሚኖሩ ይኾናሉ ሲል አንድም ቅ.ዮሐንስ አፈ ወርቅ ኢየሱስ ክርስቶስን ኹሉን የሚጠቀልል ፍቅር ይሏልና ያን ሲያስታውስ፥ ይህ እንዴት ነው ቢሉ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያስፈልገንን መልካም ነገር ኹሉ መኾኑን የሚገልጥ ነው። እውነተኛ ብርሃን፣ እውነተኛ ሕይወት፣ እውነተኛ ምግብና መጠጥ፣ እውነተኛ ሰላምና ደስታ፣ እውነተኛ ዕረፍትና እርካታ እርሱ ነውና። https://t.me/phronema
Mostrar todo...
ዮሐንስ ጌታቸው

ርቱዕ ሐልዮ ጥያቄና አስተያየት ካልዎት ይስጡ! @tmhrte_tsdk_bot

Repost from National Lottery et
Photo unavailableShow in Telegram
✔️እንኳንንንን ደስስስስ አላችሁ👇👇👇 ብሄራዊ ሎተሪ ለባለ ዕድለኞች አስደሳች ዜና ይዞ መጥቷል የኢትዮጲያ ብሄራዊ ሎተሪ የማህበረሰቡን የቤት እጦት እና ፍላጎት በመገንዘብ ከEthio Telecom ጋር በመተባበር፣ #100_ሚሊዮን_ብር በመመደብ #ሚያዚያ 27/2016 በፋሲካ እለት የሚጠናቀቅ ልዪ የሆነ "ቤተሰባችንን ይቀላቀሉ " ፕሮግራም አዘጋጅቷል። የኢትዮ ቴሌኮምና ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር በወሰነው መሰረት  ድርጅታችን በቴሌቪዢንና በሬድዮ ለማስታወቂያ ይመድበው የነበረውን በጣም ከፍተኛ ገንዘብ በመቀነስ የቴሌግራም ቻናል በመክፈት ራሱን እያስተዋወቀ ይገኛል!! ቴሌግራም ገፃችንን ብዙ ተከታይ እንዲያገኝ (ሼር) ላደረጉ ተከታዮቻችን 1ኛ እጣ ባለ 3 መኝታ ለ 25 ዕድለኞች 2ኛ እጣ ባለ 2 መኝታ ለ 25 ዕድለኞች 3ኛ እጣ ባለ 1 መኝታ ለ 50 ዕድለኞች እና ቀጥሎ ላሉ 200 እድለኞች የ1 አመት ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎት ሽልማት ይኖረዋል፡፡ አሁንስ ምን ይጠብቃሉ ሊንኩን ተጭነው ከገቡ በኃላ፣ ይህን ፅሁፍ ለ40 እና ከዛ በላይ ለሆኑ ወዳጅ ጓደኛችዎና ግሩፓች ላይ ሼር ፎርዋርድ ሲያደርጉ፣ የመሸለም እድሎ የሰፋ ነው። ይህን የማይገኝ አጋጣሚ በከንቱ እንዳያሳልፉ አሁኑኑ ሼር ፎርዋርድ ያድርጉ ፡፡ ከ40 በላይ ሼር ማረጋችሁ የመሸለም እድላችሁን ያሰፋዋል ልብ ይበሉ ❗️ ሼር አድርገው ሲጨርሱ ከታች ባለው ቦት ላይ 👇👇            @Prize_12_Bot          @Prize_12_Bot     Start በማለት የሽልማቱን ቀን ይጠባበቁ በኮምፒውተር እጣ አወጣጥ መሠረት #ሚያዝያ 27/2016 በትንሣኤው እለት ተሸላሚ ባለ ዕድለኛዎችን በ ቴሌግራም ቻናላችን የምንገልፅ ይሆናል መልካም እድል ከ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር @NATIONAL_LOTTERYET @NATIONAL_LOTTERYET ♻️ ሼር ሲያረጉ እኛ ደሞ እንሸልሞታለን!!
Mostrar todo...
❌👉[የሰሞኑ መነጋገሪያ ርዕስ]በመምህር ዮሃንስ ጌታቸው ነገረ ክርስቶስ💥 https://youtube.com/watch?v=F7UnnzvPwHo&si=qsH49Mf6_gKLIgPW
Mostrar todo...