cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Ethio Facts 🇪🇹 ኢትዮ ፋክት️

ኢትዮጵያ ትቅደም Walk a mile in my shoes, Then you will know how I feel.

Mostrar mĂĄs
Publicaciones publicitarias
435
Suscriptores
+224 horas
+47 dĂ­as
+5530 dĂ­as
Distribuciones de tiempo de publicaciĂłn

Carga de datos en curso...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
AnĂĄlisis de publicaciĂłn
MensajesVistas
Acciones
Ver dinĂĄmicas
01
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለቤተክርስቲያኗ ቅሬታ ምላሽ ሰጥቷል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ(ዶ/ር) ‹‹ ከኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በኩል ዛሬ የቀረበው ቅሬታ እንደደረሳቸው" ተናግረዋል፡፡ ኮሚሽነሩ ለቤተ ክርስቲያኒቱ በሰጡት ምላሽ እንዳሉት ‹‹ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የኃይማኖት ተቋማት በምክክሩ እንዲሳተፉ ይፋዊ ደብዳቤ ልከናል፡፡" ብለዋል። ለአብነትም ‹‹ በአዲስ አበባ በተካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ መርሐ ግብር ከቤተ ክርስቲያኗ የተወከሉ አባቶች በፀሎት ጭምር መድረኩን እንዳስጀመሩት ›› አስታውሰዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ በምክክሩ አንድትሳተፍ ይፋዊ ደብዳቤ መላኩን ያስታወሱት ዮናስ ‹‹ ምናልባት ቴክኒካዊ በሆነ ምክንያት ›› በመሃል የተፈጠረ ችግር ካለ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋር በመነጋገር እንደሚያርሙት አመልክተዋል፡፡ ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ ይህንንም በመገናኛ ዘዴዎች ለህዝብ ይፋ ይገለፃል ብለዋል 👉 በኮሚሽኑ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ከሳምንት በፊት ቅሬታውን ማቅረቡ ይታወሳል።
580Loading...
02
ጥብቅ መመሪያ እንዲተላለፍ ተወስኗል። ቅዱስ ሲኖዶስ በምልዓተ ጉባኤው የብፁዕ አቡነ ልቃስን የአውደምህረት ንግግር ከቤተክርስቲያኒቱ ቀኖና አስተምህሮት ውጭ የሆነ ፣ ቅዱስ ሲኖዶስንም ሆነ ቤተክርስቲያንን የማይወክል ነው ሲል ውሳኔ አሳለፈ። ንግግራቸው ቤተክርስቲያንን ዋጋ እያስከፈላት መሆኑና በቤተክርስቲያንና መንግሥት መካከል የነበረውን ግንኙነት እንዳሻከረው ተመላክቷል። ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የምስራቅ አውስትራሊያ እና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ፅ/ቤት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስ ታህሳስ 19 / 2016 ዓ/ም በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሜሪላንድ ከተማ ሐመረብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ ወቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በዓለ ንግስ ላይ ታቦተ ህጉ በቆመበት እንዲሁም ምእመናን በተሰበሰቡበት ቤተክርስቲያንን የማይመጥንና የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ብሎም የአባትነትን ክብር ዝቅ በሚያደርግ ሁኔታ አንድን ጠቅላይ ሚኒስትር ፦ ° " ግድሉ " ° " ዘርህ ይጥፋ " ° " የአድማ ብተና ይበትንህ " በማለት መናገራቸውን ገልጿል። ይህ ንግግራቸው ፦ ➡️ ቤተክርስቲያኒቱን የማይወክል፣ ➡️ ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ የሆነ፣ ➡️ ቅዱስ ሲኖዶስን የማይወክል፣ ➡️ ለዘመናት ጸንቶ የቆየውን የአባቶች ክብር ዝቅ የሚያደርግ፣ ➡️ የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ዝቅ የሚያደርግ፣ ➡️ ከህገ ኦሪትም ሆነ ከቃለ ወንጌል ያፈነገጠ ንግግር እንደሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ ገልጿል። የብፁዕ አቡነ ሉቃስን ጨምሮ አንዳንድ አባቶች በተለያየ ቦታ የሚያስተለልፏቸው መልዕክቶች ቤተክርስቲያንን ለትችት እየዳረገ እንዲሁም ዋጋ እያስከፈለ ነው ተብሏል። በቀጣይ የመግለጫ አሰጣጥ እና የትምህርተ ወንጌል አሰጣጥ ገዢ ህገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለጥቅምት 2017 ዓ/ም ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርብ ተወስኗል። ከዛሬ ጀምሮ በመላው ዓለም ያሉ አህጉረ ስክበት ስህተት እንዳይፈጸም ቁጥጥርና ክትትል እንዲያደርጉ ያን ሳያደረጉ ቀርተው የተሳሳቱ እና ከቀኖና ቤተክርስቲያን ያፈነገጡ ትምህርቶች አውደምህረት ላይ ቢተላለፉ በኃላፊነት እንደሚያስጠይቅ ጥብቅ መመሪያ እንዲተላለፍ ተወስኗል።
730Loading...
03
ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም የመሸፈን አብዮት ጀምረናል - ም/ጠ/ ሚ ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያን ከተረጂነት የማላቀቅና ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም የመሸፈን አብዮት ጀምረናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መናገራቸውን ፋና ዘግቧል፡፡ አቶ ተመስገን ባደረጉት ንግግር፥ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አስተዳደርን እና ሀገራዊ የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን አዲስ ፖሊሲ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቀዋል፡፡ ከተረጂነት እንውጣ የሚል አብዮት መቀስቀስ የፖሊሲው ዋና ግብ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ አደጋን በራስ የመሸከም አቅም ማዳበር እንደሚያስፈልግ አስረድተው÷ በቅድመ አደጋ፣ በአደጋ እና በድህረ አደጋ የሚሰሩ ስራዎች በታቀደው መሰረት በተናበበ መልኩ መከናወን እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡ እንደሀገር አደጋን በራስ አቅም መቋቋም እንችላለን የሚለውን ትልቅ አብዮት ለማሳካት አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸውንም ነው የተናገሩት። ከተረጅነት ለመላቀቅና እርዳታን በራስ አቅም ለመሸፈን የባህል ለውጥ እንደሚያስፈልግና ልመናን መፀየፍ እንደሚገባም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ ከ 20 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የምግብ ድጋፍ እንደሚሹ በቅርቡ ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም።
670Loading...
04
ተወዳጁ ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ ከ42 ቀናት እስር በኋላ ዛሬ ዳይሬክተሩን ዳግማዊ ፈይሳ ጨምሮ ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ፍርድ ቤት ቀርቧል "በቡድን በመደራጀት ወጣቶችን መልምሎ በማሰማራት፣ ገንዘብ ለሽብር ቡድኑ ሎጂስቲክስ መግዣ ለማዋል... ሕገ-መንግስቱን እና ሕገ-መንግታዊ ስርዓቱን በኃይል በትጥቅ ትግል ለመቀየር ሲንቀሳቀሱ በመገኘታቸው ተጠርጥረው".... የሚሉ መዘርዝሮችን የያዘ የጊዜ ቀጥሮ ማመልከቻ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል። ተዋናይ አማኑኤል እስራኤል አገር "እብደት በሕብረት" የተሰኘ ቴአትሩን ለማሳየት አውሮፕላን ሊሳፈር ሲል ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ/ም ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች ተይዞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ተወስዶ መታሰሩ ይታወሳል። አማኑኤል ከታሰረ ከ42 ቀናት በኋላ በዛሬው ዕለት ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ፖሊስ ፍርድ ቤት አቅርቦት የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለሰኔ 11 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ተዋናይ አማኑኤል በተጨማሪም በቅርቡ በፖሊስ ተይዞ ለእስር የበቃው የ"እብደት በሕብረት" ቴአትር አዘጋጅ አንጋፋው ከያኒ ዳግማዊ ፈይሳን ጨምሮ ሌሎች 20 ሰዎችን በአንድ መዝገብ ለፌደራል መደበኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል። ጠበቆች ተወክለው በመቅረብ የዋስትና መብታቸው ከዚህ ሁሉ የእስር ቀናት በኃላ እንኩዋን ሊፈቀድላቸው የሚገባ መሆኑንና እስሩም አግባብነት የሌለው መሆኑ አንስተው ተከራክረዋል። ሕገ መንግስታዊ እና ስነ ስርአታዊ የሕግ ድንጋጌዎች ተጠቅሶ ሰፊ ክርክር ከተደረገ በኋላ ችሎቱ ሁሉንም ተጠርጣሪዎች ለሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ማረጋገጥ ችያለሁ። Via፣ Yared Shumete      T.me/ethio_mereja
820Loading...
05
#እንድታውቁት🚨 2 የወተት ምርቶች የደህንነትና የጥራት መስፈቶች አሟልተው ባለመገኘታቸው ምክንያት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ማሳሰቢያ ተላለፈ። 1ኛ. #Sultan Instant Full Cream Milk Powder (400g) , (PD 19/02/2024, & Exp 18/02/2026 B.NO.56 2ኛ. #Nura Super Instant Full Cream Milk Powder (400g) PD 01/11/2023 እና Exp 31/10/2025 BT 23246006 LOT No. 230915 291123003127 የወተት ምርቶች የደህንነትና የጥራት መስፈርቶች ያላሟሉ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው የንግድና ቀጠናዊ ትስስስር ሚኒስቴር አሳስቧል። @tikvahethiopia
880Loading...
06
የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ለቆ እንዲወጣ አንፈልግም ሲሉ የሶማሊያ ፌደራል መንግስት አካል የሆኑት “ጁባላንድ” እና “ደቡብ ምዕራብ” ግዛቶች ገለጹ የሶማሊያ ፌደራል መንግስት አካል የሆኑት “ጁባላንድ” አስተዳደር እና “ደቡብ ምዕራብ” በሚል የሚጠራው የሶማሊያ ግዛት አስተዳደር የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ለቆ እንዲወጣ እንደማይፈልጉ አስታወቁ። የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ለቆ መውጣት የተወሳሰበው የሶማሊያ የጸጥታ ሁኔታው ያባብሰዋል፣ አልሸባብ እንዲንሰራራ ያደርገዋል ሲሉ ግዛቶቹ ገልጸዋል። ሁኔታው በሀገሪቱ በሚገኙ ባለድርሻ አካላት ዘንድ ስምምነት ሊፈጠርበት የማይችል ነው ያሉት የጁባላንድ ምክትል ፕሬዝዳንት ሞሃሙድ ሰይድ አደን ውይይት ሊደረግበት ይገባል፤ ማንም በተናጠል ውሳኔ ሊያሳልፍ አይችልም ሲሉ አስታውቀዋል። የደቡብ ምዕራብ ግዛት የጸጥታ ጉዳዮች ሚኒስትር በኤክስ (ትዊተር) ገጹ በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ስራ በተሰማራው የአፍሪካ ጦር ሀይል ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር አስቸጋሪ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ሲል ገልጾ ለአበርክቶው ምስጋና እናቀርባለን፣ የጦሩ ቆይታ ይቀጥላል፣ የድርሻውንም ይወጣል ሲል አወድሷል። የኢትዮጵያ ጦር ለቆ ይውጣ መባሉ አላስፈላጊ እና የተሳሳተ ምክር ሲል ተችቷል።    
890Loading...
07
79 አባላት ያሉት የሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ የቢዝነስ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ ********** በሳውዲ አረቢያ የንግድ ምክር ቤት ፌዴሬሽን የተመራ 79 አባላትን የያዘ የሳውዲ አረቢያ የኢንቨስትመንት እና የንግድ የልዑካን ቡድን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል። ጉብኝቱ የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር ያለመ ሲሆን፤ ልዑኩ በአዲስ አበባ በሚኖረው የሶስት ቀናት ቆይታም ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የማምረቻ ቦታዎችን እንደሚጎበኝ ይጠበቃል። በተጨማሪም የኢትዮ-ሳውዲ አረቢያ የቢዝነስ የምክክር መድረክ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል። በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትና በሳውዲ አረቢያ አቻው መካከል የመግባቢያ ስምምነት ይፈረማል ተብሎም ይጠበቃል።
980Loading...
08
የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል **************** ከግንቦት 28/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። በዚሁ መሰረት ከነገ ግንቦት 28/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በመገባደድ ላይ ባለው ወር ሲሸጥበት በነበረው የሚቀጥል መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
970Loading...
09
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ተግባራዊ ሊደረግ ነው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ተግባራዊ ሊደረግ ነው። የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 ለመተግበር ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል። በዚህ ወቅት አስፈጻሚ አካላት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅን ተግባራዊ ለማድረግ በቀጥታ ወደ ሥራ መግባት እንደሚኖርባቸው የአዲሰ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ተናግረዋል። በውይይቱ ላይ አዋጁ የመኖሪያ ቤት ኪራይ እና አስተዳደር የተረጋጋ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ የአከራይና የተከራዮችን ጥቅምና መብቶችን ሚዛን በጠበቀ መልኩ ለማስፈጸም እንደሚረዳ ተገልጿል። መንግስት የነዋሪውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በርካታ የልማት አመራጮችን ሲፈጽም ቆይቷል ያሉት ሃላፊው፥ የግል ቤቶች ያልተገመተ የዋጋ ጭማሪ ለመቆጣጠር አዋጁ የተከራይና የአከራይ መብቶችን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ እንዲመራ ያስፈልጋል ብለዋል። በመሆኑም አስፈጻሚ አካላት አዋጁን ተግባራዊ ለማድረግ በቀጥታ ወደ ሥራ መግባት ይኖርባቸዋል ነው ያሉት።
960Loading...
10
79 አባላት ያሉት የሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ የቢዝነስ የልዑካን ቡድን ኢትዮጵያን ሊጎበኝ ነው - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳውዲ አረቢያ የንግድ ምክር ቤት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የተመራ 79 አባላትን የያዘ የሳዑዲ አረቢያ የኢንቨስትመንት እና የንግድ ልዑካን ቡድን ኢትዮጵያን ሊጎበኝ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ ገለጹ። ጉብኝቱ የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር ዓላማ ያደረገ መሆኑን አምባሳደር ነብዩ ገልጸዋል።ቡድኑ ዛሬ ማታ አዲስ አበባ እንደሚገባና በሚኖረው የሶስት ቀናት ቆይታም ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የማምረቻ ቦታዎች ይጎበኛል ብለዋል። በሚመለከታቸው የኢትዮጵያ ባለድርሻ መስሪያ ቤቶች በኢትዮጵያ ስላሉት ምቹ የኢንቨስትመንትና ንግድ አማራጮች ለባለሀብቶቹ ገለፃ የሚደረግበት የኢትዮ-ሳውዲ አረቢያ የቢዝነስ የምክክር መድረክ እንደሚካሄድም አስታውቀዋል። የልዑካን ቡድኑ በግብርና፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ በሀይል ማምረት፣ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ እንዲሁም በሌሎች ቁልፍ ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ያሉትን እድሎች ለመገንዘብ እንደሚፈልግም ቃል አቀባዩ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትና በሳውዲ አረቢያ አቻው መካከል የመግባቢያ ስምምነት ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
810Loading...
11
23 ትናንሽ አውሮፕላን ማረፍያዎች ሊገነቡ ነው፡፡ ከፍተኛ የአውሮፕላን ማረፍያ በሌለባቸው ነገር ግን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች አሉባቸው በሚባልባቸው አካባቢዎች ትናንሽ አየር ማረፍያዎች እንደሚገነቡ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አስታውቋል፡፡ የትራንስፖርትና ሎጂስትክስ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በእጅጌ የኢትዮጵያ መንግስት ለአዳዲስ የአውሮፕላን ማረፍያዎች ግንባታ የሚሆን በጀት አለመያዙን ተናግረው አሁን የሚገነቡ ትናንሽ አየር ማረፍያዎች በተለያዩ ወጪዎች የሚሸፈኑ ይሆናል ብለዋል፡፡ በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የሚገነቡት 23 ትናንሽ አውሮፕላን ማረፍያዎች ተለይተው መታወቃቸውን የተናገሩት ሚኒስትሩ የአዋጭነት ጥናት የመሬት ጥናት እና ሌሎችም ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡እነዚህ ግንባታዎች በራሳቸው ወጪ ለማከናወን የክልል መንግስታት ፍላጎት ማሳየታቸው የተነገረ ሲሆን ባለሃብቶችም ጭምር ፍላጎት እንዳላቸው ነው የተነገረው፡፡
870Loading...
12
አዲስ አበባን በመወከል በሀገራዊ ምክክሩ በመሳተፍ ላይ ያሉ ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎቻቸውን ለይተው ማጠናቀቃቸው ተጠቆመ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ እያካሄደ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ የምክክር ምዕራፍ አምስቱም ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎቻቸውን ለይተው ማጠናቀቃቸውን ኮሚሽኑ አስታወቀ። ባለድርሻ አካላቱ ያጠናቀሯቸውን እና ያደራጇቸውን አጀንዳዎች በቃለ-ጉባዔ በማዘጋጀት ለአጠቃላይ መድረኩ የሚያቀርቡላቸውን ተወካይ ግለሰቦችንም መምረጣቸውን ኮሚሽኑ ጠቁሟል። ዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰዓት በተካሄደው መርሐ-ግብር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቡድን ሆነው ተስማምተው ያደራጇቸውን አጀንዳዎች በመረጧቸው ተወካዮች አማካኝነት ለጋራ መድረኩ ማቅረባቸውነ አስታውቋል። ከዚህ በኋላ በሚኖረው መርሐ-ግብር የየባለድርሻ አካላቱ ወኪሎች ከሞደሬተሮች ጋር በመሆን የሁሉንም አጀንዳዎች በጋራ ሆነው አስቸኳይነትን፣ አስፈላጊነትን እና ወካይነትን ከግምት በማስገባት በየፈርጁ ያደራጃሉ ብሏል። በነገው ዕለትም በየፈርጁ የተደራጁት አጀንዳዎች የአዲስ አበባ ከተማ አጀንዳ ሆነው ለምልዓተ ጉባኤው ከቀረቡ በኋላ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተገኙበት የምክክር መድረክ እንደሚካሄድ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። በመወያየት ላይ ያሉት እና ባለድርሻ አካላት ተበለው የተገለጹትም፤ የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች፣ ከሶስቱ የመንግስት አካላት (ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚና ሕግ ተርጓሚ) ተወካዮች፣ የተቋማትና ማህበራት ተወካዮች እንዲሁም የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተወካዮች ናቸው፡፡      T.me/ethio_mereja            ኢትዮ-መረጃ
920Loading...
13
በካፒታል ገብያ ወስጥ ደላላ ለመሆን የ6 ሚሊዮን ብር  ካፒታል ሊኖር እንደሚገባ ተሰምቷል:: በካፐታል ገብያ ወስጥ መንቀሳቀስ ለሚፈልጉ ደላሎች 6ሚሊየን ብር  የተከፈለ  ካፒታል መያዝ እብዳለባቸው  ተገልጧል። ኢትዮጵያ ለካፒታል ገብያ አዲስ ባትሆንም በቅርቡ ካሉ ሁለት አመታት ግን የካፒታል ገብያውን እንደ አዲስ ለማሰጀመር ብዙ ስራዎች መሰራታቸው መረጃዎች ያመላክታሉ ። በዚህ ገበያም ብዙ ተዋናዮች እንዳሉ ይታወቃል ለአብነትም አክሲዮን ሻጭ እና  ገዚ ኦንቨስትመንት ባንክ እና ሌሎችም  ከነዚሀ ተዋናዮች ውስጥ ድግሞ ዋነኛው የሰነደ መዋለ ነዋይ ደላሎች ናቸው፡፡ ለመሆኑ በካፒታል ገብያ ውስጥ ያሉት ደላሎች እነማ ናቸው ስራቸውስ ለመግባት የሚያስፈልጉ መስፈርቶችስ የሚለውን በኢትዮጵያ የካፒታል ገብያ የህግ አማካሪ የሆኑትን አቶ እስጢፋኖስ መልካሙን ጠይቀናል የሰነደ መዋለ ነዋይ ደላሎች በካፒታል ገብያ ውስጥ ያላቸው ሚና? •  የሰነደ መዋለ ነዋይ  ደላሎች በተለምዶ ከሚታወቁት ደላሎች ከስያሜቸው ጀምሮ የተለዩ እንደሆኑ አንስተው  ማህበረሰቡ ከተለመዱትየቤት ወይንም መኪና አሻሻጭ ደላሎች ጋር ማመሳሰል እንደሌለበት ጠቁመዋል፡፡ •   አክሲዮን የሚገዙም ሆነ የሚሸጡ ደርጅቶች ግብይታቸው የሚፈጸምላቸው በሰነደ መዋለ ነዋይ ደላሎች በኩል ነው •  ለገዢም ይሁን ለሻጭ በሰነደ መዋለ ነዋይ ሽያጭ ዙሪያ የማማከር እና ሃሳባቸውን በጥናት የመደገፍ ስራ የሰነደ መዋለ ነዋይ ደላሎች ወደ ካፒታል ገብያው ለመግባት ምን ምን መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው ? አቶ እስጢፋኖስ መልካሙ  በምላሻቸውም፡ •  የተከፈለ 6ሚሊዮን ብር ካፒታል እንደሚያሰፈልጋቸው •  በድርጅት ወይም በኩባንያ መልክም መደራጀት እንዳለባቸው ተጠቁመዋል ለአብነትም አክሲዮንም ሆ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል መሃበር መሆነ አለበት •  የስራ አመራር ቦርድ ሊኖረውም ይገባል ይህ ማለትም ቢያንሥ 3 የዳሬክተሮች ቦረድ ሊኖረው ይገባል •   በግል መይም በሽርክና የሠነደ መዋለ ነዋይ የደላላነትን ፍቃድ መውሰድ አይችልም •  ሌላው ፍቃዱን የሚጠይቀው ኩባንያ ለስራው የሚሆን የፖሊሲ ፍሬም ወርክ ማዘጋጀት አለበት ከሰነደ መዋለ ነዋይ ደላሎች ጋር በተያያዘስ  ከሌሎች በመስኩ ከሚሰሩ ሃገራት ጋር  የተወሰዱ እና የተደረጉ የልምድ ልውውጦች  እንዳሉም ተጠቁሟል።
870Loading...
14
ልዩ መረጃ‼️ እስክንድር ነጋ ከመንግስት ሰዎች የሰላም ድርድር ሂደት መጀመሩ ታውቋል እስክንድር ነጋ የፋኖ ታጣቂዎችን ወክሎ ከመንግስት ድርድር መጀመሩ ተገልጿል። በ3ኛ ወገን አመቻችነት እስክንድር ነጋ ከመንግስት ሰዎች ጋር ቀጥተኛ ያልሆነ የድርድር ሂደት መጀመሩ ተጠቁሟል። መንግስት ከእስክንድር ጋር እያደረገ ያለው ድርድር የሚሳከ ከሆነ ከእስክንድር ቡድን ጋር ከሸዋ የሻለቃ መከታው ቡድን፣ ከወሎ የምሬ ወዳጆ እና የኮ/ል ፈንታሁን ቡድኖች፣ ከጎጃም የማስረሻ ሰጤ እና የማንችሎት ቡድኖች፤ ከጎንደር በሻለቃ ሀብተ ወልድ የሚመራ ቡድን ወደ በድርድርሩ እንዲሳቱፉ ጥረት እየተደረገ ይገኛል። ከሰላም ውጪ ሌላ አማራጭ መንገድ የለም! ሰላም ለኢትዮጵያ
812Loading...
15
Trump could declassify 9/11, Kennedy assassination and Epstein docs if re-elected Donald Trump told Fox News that during his first term he had already declassified “a lot of material” about the Kennedy assassination. The release of the documents would be intended to dispel rumors and restore confidence in the FBI and CIA.
890Loading...
16
NATO chief promotes WW3 – Italian deputy PM ‘This man is dangerous because he talks about the third World War… whoever can, should stop him,’ - Italian Deputy Prime Minister Matteo Salvini.
840Loading...
17
" በሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ " ላይ የመጨረሻ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ረቂቁ ከባለፈው መጠነኛ ማሻሻያዎች ተደርጎበት መቅረቡን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። በመጀመሪያው ረቂቅ አዋጅ ያልነበረና የመንግሥትንና የክልሎችን ግዴታና ኃላፊነት በመዘርዘር የተቀመጠው ክፍል አንዱ ነው። በዚህ ክፍል ላይ መንግሥት በሃይማኖት አስተምህሮና የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንደማይችል ተደንግጓል፡፡ በተጨማሪ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ አገር የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት ተደንግጎ የነበረው የረቂቅ አዋጁ ክፍል ከተሻሻለው ረቂቅ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ ነገር ግን ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ፦ ✔ የሃይማኖት ተቋሙን ኦዲት ሪፖርት ለሰላም ሚኒስቴር እንዲያቀርብ፣ ✔ የበጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ በ3_ወራት የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በገለልተኛ ኦዲተር ማስመርመር እንደሚኖርበት የተቀመጠው የረቂቁ ክፍል በተሻሻለው ላይ ተካቷል፡፡ ሌላኛው ተሻሽሎ የቀረበው የረቂቅ ክፍል አለባበስን እና የተማሪዎች አመጋገብን ጨምሮ በማንኛውም የትምህርት ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚደረግ ሃይማኖታዊ ተግባር የመንግሥትና ሃይማኖት መለያየት መርህንና የሃይማኖት ነፃነትንም በጠበቀ መንገድ መከናወን አለበት የሚለው ነው፡፡ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኩ የመጨረሻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በመንግሥት እና በሃይማኖት መካከል ያለው ልዩነት ምን ድረስ እንደሆነ ሳይታወቅ ቆይቷል ብለዋል። አዋጁን ማዘጋጀትም ያስፈለገው ይህን ጉዳይ በግልጽ ለማስቀመጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ መንግሥት በሃይማኖት ተቋማት ነፃነት ውስጥ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው  ፤ ነገር ግን አብረው በሚሠሩባቸው ጉዳዮች በሕግ የተቀመጠ አሠራር ሊኖር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የተነሱ ሐሳቦችን በግብዓትነት ወስዶ ለሚመለከተው አካል የሚቀርበውን ረቂቅ አዋጅ እንደሚያዘጋጅ ተገልጿል፡፡
970Loading...
18
የህዳሴ ግድብን ግንባታ የሚቃወሙ አካላት በኮንትራክተሮች ላይ ማስፈራሪያ እየላኩ መሆኑ ተሰማ ከዛሬ 13 ዓመታት በፊት የተጀመረውና በመሃል  የግንባታ ሂደቱ ተቋረጦ የነበረዉ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ በተሳተፉት ኮንትራክተሮች ላይ ከፕሮጀክቱ እንዲወጡ የማስፈራራት እና የማባበል ዛቻዎች እየተደረገባቸው መሆኑ ተገልጿል። ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የሚገኙ ተቋሬጭ ኮንትራክተሮች ላይ የሚደረገው ማስፈራሪያ እንደቀጠለ መሆኑን የገለፁት የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ ይህም ቢሆን ግን ግንባታው በታቀደለት ጊዜ ይጠናቀቃል በማለት ተናግረዋል ። የፕሮጀክቱን ሂደት የሚቃወሙ እና አንዳንድ ተቀናቃኞች ሲሏቸዉ የጠሯቸው አካላት ማንነት ከመግለፅ የተቆጠቡት ኢንጅነር ክፍሌ ግንባታው የዛሬ አምስትና ስድስት ዓመት ቆሞ በነበረበት ወቅት ፀጥ ብለዉ እንደነበር አስታዉሰዋል። ግድቡ መሰራት ሲጀምር ዝም ብለዉ ነበር ያሏቸው ተቃዋሚዎች ፕሮጀክቱ የታቀደለትን ግብ ይመታል ሲባል የዲፕሎማሲ ጦርነትን ጨምሮ የማስፈራራት እና የተለያዩ ክሶችን ክፍተዋል ማለታቸዉን ዳጉ ጆርናል ከካፒታል ዘገባ ተመልክቷል። ነገር ግን ይሄ ሁሉ ደረጃ ላይ ታልፎ ነዉ ግንባታው አሁን ለደረሰበት አፈፃፀም መድረስ የቻለው ሲሉም ተደምጠዋል ። ኢንጂነር ክፍሌ እንደተናገሩት እነዚሁ አካላት ኮንትራክተሮችን ያባብላሉ ፣ ፕሮጀክት አታገኙም በሚል የተለያዩ ማስፈራሪያዎች አሁንም ድረስ እያደረጉ ይገኛሉ ። የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ይህን የተናገሩት የታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አሁን የደረሰበትን የግንባታ ሂደት በተመለከተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከህዳሴው ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈትቤትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ለግድብ ግንባታ ድጋፍ የሚያደርጉበትን መተግበሪያ ባስተዋወቁበት መድረክ ላይ ነዉ። የፕሮጀክቱ ግንባታ ከዛሬ 5 ዓመታት በፊት ተቋርጦ በነበረበት ጊዜ ተቃዉሞ ያልነበረበት ቢሆንም ነገር ግን ይህ ግድብ መሰራት መጀመሩ በታወቀበት ወቅት እየደረሱ ይገኛሉ ከተባሉት ተግዳሮቶች ዉስጥ ለግድቡ ብቸኛዉ ሲሚንቶ አቅራቢ በሆነዉ ደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካን ከማቃጠል ጀምሮ ጥሬ እቃዎች እንዳይደርሱት መንገዶችን መዝጋት እና ግብዓቶች ወደ ሳይት እንዳይደርሱ መንገድ ላይ የተልዕኮ ጦርነቶች ይገኙበታል ። ይሁን እንጂ ፕሮጀክቱ ይህ ሁሉ ፈተና እያለበት አጠቃላይ አፈፃፀሙ 96 በመቶ መድረሱንና ቀሪዉ እስከ መጪዉ ጥር ወር ድረስ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል ተብሏል።
840Loading...
19
ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ! በበይነ መረብ (Online) የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና በተመለከተ የተሰጠ ማብራሪያ በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በበይነ መረብ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወረቀት አልባ በማድረግ የዲጂታል ጉዞውን አንድ ምዕራፍ ጀምሯል። ይሄንንም ጉዞ የተሳካ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ ለተፈታኞች በክላስተር የተዘጋጀው ማስፈንጠሪያ (URL) ከፈተናው በፊት ገብተው የሚለማመዱበት ሲሆን የፈተናው እለት ደግሞ መፈተኛ ይሆናል። ስለሆነም ከዚህ በታች በምትፈተኑበት የፈተና ክላስተር ፊትለፊት በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ በመግባት መለማምድ ትችላላችሁ፡፡  እስካሁን username እና password ያለገኘ ተፈታኝ ካለ፣ ከዚህ በፊት ለትምህርት ቢሮዎች ስለተላከ፣ ከየትምህርት ቤቱ አስተባባሪዎች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ክላስተር አንድ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር፡ https://c2.exam.et  ሲዳማ ብሄራዊ ክልል፡ https://c2.exam.et ትግራይ ብሄራዊ ክልል፡ https://c2.exam.et ክላስተር ሁለት ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፡ https://c3.exam.et ጋምቤላ ህዝቦች ክልል፡ https://c3.exam.et አማራ ብሄራዊ ክልል፡ https://c3.exam.et ክላስተር ሶስት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል: https://c4.exam.et ሀረሪ ብሔራዊ ክልል: https://c4.exam.et አፋር ብሔራዊ ክልል: https://c4.exam.et ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል - 1 • አዳማ ከተማ: https://c4.exam.et • አጋሮ ከተማ: https://c4.exam.et • አምቦ ከተማ: https://c4.exam.et • ምሥራቅ አርሲ: https://c4.exam.et • ምዕራብ አርሲ: https://c4.exam.et • አሰላ ከተማ: https://c4.exam.et • ባሌ: https://c4.exam.et • ባቱ ከተማ: https://c4.exam.et • ቤሾፍቱ ከተማ: https://c4.exam.et • ቦረና: https://c4.exam.et • ቡሌ ሆራ ከተማ: https://c4.exam.et • ቡኖ በደሌ: https://c4.exam.et • ዶዶላ ከተማ: https://c4.exam.et • ምሥራቅ ባሌ: https://c4.exam.et • ምሥራቅ ቦረና: https://c4.exam.et • ጉጂ: https://c4.exam.et • ምሥራቅ ሐረርጌ: https://c4.exam.et • ምዕራብ ሐረርጌ: https://c4.exam.et • ሆለታ ከተማ: https://c4.exam.et • ሆሮ ጉዱሩ: https://c4.exam.et • ኢሉባቦር: https://c4.exam.et ክላስተር አራት ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር: https://c5.exam.et ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል - 2 • ጅማ: https://c5.exam.et • ጅማ ከተማ: https://c5.exam.et • ቄለም ወለጋ: https://c5.exam.et • ማያ ከተማ: https://c5.exam.et • መቱ ከተማ: https://c5.exam.et • ሞጆ ከተማ: https://c5.exam.et • ሞያሌ ከተማ: https://c5.exam.et • ነጆ ከተማ: https://c5.exam.et • ነቀምት ከተማ: https://c5.exam.et • ሮቤ ከተማ አስተዳደር: https://c5.exam.et • ሰንዳፋ በኬ: https://c5.exam.et • ሻኪሶ ከተማ: https://c5.exam.et • ሻሸመኔ ከተማ: https://c5.exam.et • ሸገር ከተማ: https://c5.exam.et • ሸኖ ከተማ: https://c5.exam.et • ምስራቅ ሸዋ: https://c5.exam.et • ሰሜን ሸዋ (ኦሮሚያ): https://c5.exam.et • ደቡብ ምዕራብ ሸዋ: https://c5.exam.et • መዕራብ ሸዋ፡ https://c5.exam.et • ምስራቅ ወለጋ፡ https://c5.exam.et • መዕራብ ወለጋ፡ https://c5.exam.et • መዕራብ ጉጂ፡ https://c5.exam.et • ወሊሶ ከተማ፡ https://c5.exam.et ምንጭ፣ ት/ት ሚንስቴር      T.me/ethio_mereja            ኢትዮ-መረጃ
920Loading...
20
⚡️Indian PM Modi set for third term - exit polls The National Democratic Alliance (NDA) are set to hand Narendra Modi a third consecutive term in power, with various exit polls projecting them to win between 353-371 seats in the mammoth Lok Sabha Elections. An estimated 980 million Indians have braved a deadly heatwave - 10 election officials have died due to the heat - to cast their votes across seven stages of an election process that began in mid-April. The opposition INDIA bloc look likely to be restricted to just 133-141 seats.
1150Loading...
21
ስሎቫኒያ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅናን ሰጠች፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ጎሎብ ፍልስጤም ራሷን የቻለች ግዛት ሆና እውቅና ሊሰጣት እንደሚገባ መወሰኑን አስታውቀዋል፡፡ ስሎቫኒያ የስፔን፣ አየርላንድና ኖርዌን ፈለግ መከተሏ፣ ፓርላማው ግን ገና እንዳላጸደቀው ተገልጿል። ጎሎብ በእስራኤልና ሀማስ መካከል ያለው ግጭት ቁሞ ታጋቾች እንድለቀቁም ጠይቀዋል፡፡
960Loading...
22
አቶ የሽዋስ አሰፋ መታሰራቸው ተሰምቷል። በአንድ ወቅት ሰማያዊ ፓርቲን አፍርሰው ወደ ኢዜማ ሲቀላቀሉ "ከትንንሽ ፓርቲ መሪነት ይልቅ የትልቅ ፓርቲ አባል መሆን ይሻላል" በሚል ንግግራቸው ስማቸው ጎልቶ የሚነሳው የሽዋስ አሰፋ ትናንት ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት አንድ ሰዓት ካዛንቺስ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በፖሊስ ተይዘው እንደተወሰዱ ከቤተሰቦቻቸው ተሰምቷል። አሁን ላይ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንዲመገኙ ለማወቅ ተችሏል።
900Loading...
23
“የኢትዮጵያ ወታደሮች በአፍሪካ ህብረት የሚመራው ሃይል አባል አይሆኑም” የሞቃድሾ መንግስት የሞቃዲሾ መንግስት በሶማሊያ የሰፈረው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት በቀጣይ ታህሳስ ወር ሀገሪቱን ለቆ ይወጣል ብሎ እንደሚጠብቅ ተገለጸ ሶማሊያ በሀገሯ በሰላም ማስከበር ተልእኮ ላይ የሚገኙ ሁሉም የኢትዮጵያ ወታደሮች በቀጣይ አመት 2017 ታህሳስ ወር ላይ ጠቅልለው ይወጣሉ ብላ እንደምትጠብቅ ቪኦኤ በዘገባው አስታውቋል። የቪኦኤ ጋዜጠኛ የሆነው ሃሩን ማዕሩፍ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሁሴን ሼክ አሊን ጠቅሶ ትላንት ባሰራጨው ዘገባው የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮ (ATMIS) በቀጣይ አመት ታህሳስ ወር ተልዕኮው ካበቃ በኋላ “የኢትዮጵያ ወታደሮች በአፍሪካ ህብረት የሚመራው ሃይል አባል አይሆኑም” ብሏል። የቪኦኤው ሃሩን የፕሬዚዳንቱን አማካሪ ጠቅሶ እንደዘገበው ከቀጣይ አመት በኋላ በሶማሊያ በሚሰፍረው ጦር ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች እንደማይኖሩ እና ከሌሎቹ የሰላም አስከባሪ ሀይል ካበረከቱ አራቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ቡሩንዲ የተውጣጡ ብቻ እንደሚሆኑ ጠቁሟል። በሶማሊያ ሰላም በማስከበር ላይ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።
890Loading...
24
ጦርነትን ኖረንበታል። የተወሰኑ ችግሮቻችንን ፈትተንበታል። አብዮትን ደጋግመነዋል። የተወሰኑ ችግሮችን ፈትተንበታል። በሁለቱም ያልተፈቱትን ችግሮች ለመፍታት የቀረን መንገድ ምክክር ነው። ምክክርን ግን አልተጠቀምንበትም። ጦርነትና አብዮት የተሟላ መፍትሔ የማያመጡት አሸናፊ እና ተሸናፊ ስለሚያስከትሉ ነው። ቢዘገይም የተሸነፈው ለማሸነፍ ይታገላል። ያሸነፈውም ድሉን ለመጠበቅ ይዋጋል። ምክክር ግን ሁሉንም አሸናፊ ያደርጋል። ከተሸነፍንም ሁላችንም ለሀገራችን ብለን ነው የምንሸነፈው። ይሄ የምክክር ሂደት ሦስት ነገሮች ያስገኝልናል። 1. ሁሉንም ባይሆን እንኳን ዋና ዋና ችግሮችን ይፈታል 2. ከጦርነት ይልቅ ምክክር ባህል እንዲሆን ያደርጋል 3. በተቃራኒ ኃይሎች መካከል መቀራረብና መግባባት ይፈጥራል። ይሄንን መቀራረብ በመጠቀምም ወደፊት በጉዳዮች እየተነጋገርን ለመቀጠል ያስችለናል። በመሆኑም ይኽንን እድል ሳናበላሽ ወደ ተሟላ ድል እንድናሸጋግረው እጠይቃለው።
990Loading...
25
የጋዛን ተኩስ አቁም ሀሳብ እስራኤል መቀበሏን ፕሬዚዳንት ባይደን ገለፁ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ይህን ያስታወቁት በጋዛ ጉዳይ ላይ በያዙት አቋም ምክንያት እየደረሰባቸው ያለው ወቀሳ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ባለበት ወቅት ነው፡፡ ባይደን ዛሬ በነጩ በተመንግሥት በሰጡት መግለጫ እስራኤል በጋዛ ዘላቂ የሆነ የተኩስ አቁም ሊያመጣ በሚችል ሃሳብ ላይ ተስማምታለች ብለዋል፡፡ የሰላም ሀሳቡ በሶስት እርከኖች ተፈጻሚ እንደሚሆን የተናገሩት ፕሬዚዳንት ባይደን፣ የመጀመሪያው እርከን ለስድስት ሳምንታት በሚቆይ ሂደት የሚፈጸም መሆኑን ገልጸዋል። ይህ እርከን የእስራኤል ኃይሎች ሙሉ በሙሉ ህዝብ ከሚበዛባቸው የጋዛ አካባቢዎች ለቀው ሲወጡ ተፈጻሚ ይሆናል ብለዋል። ህጻናት እና ሴቶችን ጨምሮ በሁለቱም ወገኖች በኩል ያሉ በጦርነቱ የታገቱ ወገኖችን ማስለቀቅ እና የሰብአዊ እርዳታ ተደራሽነትን ማፋጠን የስምምነቱ አካል እንደሆነም ገልጸዋል፡፡ "በዚህ የስምምነት ሂደት የሚፈቱ እና ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ የምንፈልጋቸው የአሜሪካ ዜጎች አሉ" ያሉት ባይደን፣ ኳታር ሃሳቡን ለሃማስ ገልጻለች ብለዋል። በሁለተኛው እርከን ሁሉም በህይወት ያሉ ቀሪ ታጋቾች የሚለቀቁ ሲሆን ጎን ለጎን ሁሉም የእስራኤል ወታደሮች ጋዛን ለቀው ይወጣሉ፤ በዚህም ቋሚ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት እንደሚኖር አብራርተዋል።  የመጨረሻው እርከን የጋዛን መልሶ ግንባታ እና ቀሪ በህይወት ያሌሉ የእስራኤል ታጋቾችን የመመለስ ተግባር የሚከናወንበት ነው ተብሏል። እስራኤልም ሆነ ሃማስ በባይደን ሀሳብ ላይ ምንም አለማለታቸውን አልጀዚራን ጠቅሶ ኢቢሲ በገፁ ዘግቧል፡፡
1050Loading...
26
አቡነ ሉቃስ በተከሰሱበት የቅስቀሳ ወንጀል በ6 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ አቡነ ሉቃስ በተከሰሱበት የቅስቀሳ ወንጀል ጥፋተኛ በተባሉበት ድንጋጌ በሥድስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ። የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ሕገ-መንግሥታዊና በሕገ-መንግሥት ሥርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮች የሚመለከተው ችሎት ነው። የፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ በአቡነ ሉቃስ ላይ ከሦስት ወራት በፊት÷ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 247 (ሐ) እና አንቀጽ 258 (ሀ) ሥር እና የወንጀል ሕግ አንቀጽ 251 (ሐ) የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚሉ ሁለት ክሶች ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ ተከሳሹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና የምሥራቅ አውስትራሊያ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ በጠቅላይ ቤተክኅነት የገዳማት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ-ጳጳስ ሆነው በማገልገል ላይ እያሉ ስለ ሰላም እና አንድነት የመስበክ ሐይማኖታዊ ግዴታቸውን በመተው ታኅሣስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በአሜሪካ ቴክሳስ እና አካባቢው በሚገኝ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤተ-ክርስቲያን ታቦት ወጥቶ በቆመበት ዐውደ-ምኅረት ላይ የአመፅ ቅስቀሳ ማድረጋቸውን የክስ ዝርዝሩ ያስረዳል፡፡ የዐቃቤ ሕግን ማስረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የተከሰሱባቸው ክሶች በአንቀጽ 247 (ሐ) ሥር ተጠቃልሎ የጥፋተኝነት ፍርድ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ዐቃቤ ሕግ ካቀረባቸው ሦስት የቅጣት ማክበጃ አስተያየቶች መካከል ፍርድ ቤቱ አንዱን የቅጣት ማክበጃ አስተያየት በመያዝ  እና ተከሳሹም የቀደመ የወንጀል ሪከርድ የሌለባቸው መሆኑን መነሻ በማድረግ አንድ የቅጣት ማቅለያ ተይዞላቸው ዛሬ በዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔ ተሰጥቷል። በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ በእርከን 23 ሥር በሥድስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ በሌሉበት ውሳኔ ሰጥቷል።
1100Loading...
27
የሚኒስትሮች ምክር ቤት 32ኛ መደበኛ ስብሰባ ውሳኔዎች የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 32ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ። 1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበ አዋጅ ላይ ነው። ከህጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ የቆዩ የፖለቲካ ቡድኖች በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ፍላጎት በሚያሳዩበት ጊዜ  እነዚህን አካላት ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ አድርጎ ለመመዝገብ የሚያስችል ስርዓት በነባሩ አዋጅ ላይ አልተካተተም። በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ እና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ፍላጎት በሚያሳዩበት ጊዜ መልሶ መመዝገብ የሚያስችል ስርዓት ለመዘርጋት ረቂቅ የአዋጅ ማሸሻያ ተዘጋጅቶ ቀርቧል። ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል። 2. በመቀጠልም ምክር ቤቱ የተወያየው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የንብረት ማስመለስ አዋጅ ላይ ነው። የወንጀል ፍሬ የሆኑ ንብረቶችንና ገንዘቦችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመያዝ፣ ለማገድ፣ ለመውረስ ወይም ለማስተዳደር የሚያስችል ግልጽና ዝርዝር የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ በመሆኑ፤ በተለያዩ አዋጆች ውስጥ ተበታትነው ያሉትን የንብረት ማስመለስ እና አስተዳደር ድንጋጌዎች በአንድ ወጥ ሕግ ውስጥ በማካተት ለአፈጻጸም ምቹ የሆነ ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ቀርቧል። ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል። 3. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየው በህገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አድርጎ ስለማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በቀረበው አዋጅ ላይ ነው። በወንጀል የተገኘን ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀል የደህንነት ስጋት ከመሆኑ በተጨማሪ የፋይናንስ ስርዓቱ የተረጋጋ፣ ግልጸኝነት ያለው፣ ጤናማና ቀልጣፋ እንዳይሆን የሚያደርግ ነው። ስለሆነም ይህን ወንጀል ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል። ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል። 4. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ሥርዓት ለመደንገግ በቀረበው አዋጅ ላይ ነው። የነዳጅ ውጤቶች ካላቸዉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ አንጻር አቅርቦታቸውን፣ ክምችታቸውን፣ ስርጭታቸውን፣ ዋጋቸውን፣ ጥራታቸዉን እና ደህንነታቸውን መቆጣጠር አስፈላጊ  በመሆኑ፤ እንዲሁም ከአስመጪ ጀምሮ እስከ ተጠቃሚዎች ድረስ ያለው ግብይት ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ፣ ግልጽ፣ ፍትሐዊ እና ተደራሽ የሆነ የአቅርቦት ሰንሰለት እና የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ቀርቧል። ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።
1010Loading...
28
#Ethiopia ማንኛውንም ሰው ከሀገር እንዳይወጣ የማገድ ስልጣንን፤ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበ። የአዋጅ ማሻሻያው ምን ይዟል ? ➡ ማንኛውንም ሰው ከሀገር እንዳይወጣ የማገድ ስልጣንን፤ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ ይሰጣል። ነባሩ ህግ ምን ይላል ? “ ማንኛውም ሰው ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ ሊታገድ የሚችለው በህግ መሰረት በፍርድ ቤት ሲታዘዝ ብቻ ነው ” ይላል። ዛሬ ለፓርላማ የቀረበው የአዋጅ ማሻሻያ በነባሩ ህግ የተቀመጠውን የፍርድ ቤት “ ብቸኛ ስልጣን ” የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ በተጨማሪነት ያጋራ ነው። ➡ አዲሱ ማሻሻያ ፥ " የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ከሚመለከታቸው የደህንነት አገልግሎት እና ህግ አስከባሪ አካላት ከሚያገኘው መረጃ ወይም አገልግሎቱ በራሱ ከሚያገኘው መረጃ በመነሳት፤ በብሔራዊ ጥቅም እና ደህንነት ላይ ሊቀለበስ የማይችል ግልጽና ድርስ የሆነ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል ሁኔታ መኖሩን ሲያምን፤ ማንኛውም ሰው ከሀገር እንዳይወጣ ማገድ ይችላል " ሲል ደንግጓል።  ➡  የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት " ከሀገር እንዳይወጣ ያገደውን ሰው ይዞ የሚያቆይ ከሆነ ፍርድ ቤት መቅረቡን ማረጋገጥ አለበት " ሲል የአዋጅ ማሻሻያው ደንግጓል።  ➡ ዜጎች ከሀገር እንዳይወጡ የማገድ ስልጣን ላይ ማሻሻያ የተደረገው፤ በነባሩ ድንጋጌ ምክንያት እየደረሰ ያለውን " ከፍተኛ ጉዳት " ለመቅረፍ ነው ይላል ማሻሻያው። አሁን በስራ ላይ ባለው አዋጅ መሰረት " ከፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ እስኪገኝ ድረስ በብሔራዊ ጥቅም እና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ ወይም ሊያደርሱ የሚችሉ ሰዎች ከሀገር እየወጡ ከተጠያቂነት እያመለጡ በሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም እና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ነው " መሆኑን የረቂቅ አዋጁ ገልጿል። በሌላ በኩል ፦ ማሻሻያ አዋጁ " አስተዳደራዊ ቅጣት " አንቀጽ ይዟል። " ከጊዜ ወደ ጊዜ በህገ ወጥ መንገድ በሀገራችን ውስጥ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች እየተበራከቱ፤ በህገ ወጥ ድርጊቶች እየተሳተፉ ከፍተኛ ችግር እየፈጠሩ በመሆኑ በአስተዳደራዊ ቅጣት በመቅጣት ከህገ ወጥ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማድረግ አስፈላጊ ነው " ሲል ያስረዳል። በዚህም በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የውጭ ሀገር ዜጎችን " በጥቁር መዝገብ እንዲመዘገቡ እና ከሀገር እንዲወጡ ማድረግ ወደ ህጋዊ ስርዓት እንዲመጡ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና " እንዳለው ተብራርቷል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ አማካኝነት፤ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት አስተዳደራዊ ቅጣት እንዲጥል በአዋጅ ማሻሻያው ስልጣን ተሰጥቶታል። " ይህን አዋጅ አሊያም በዚህ አዋጅ መሰረት የወጣ ደንብ ወይም መመሪያን የጣሰ ማንኛውም ሰው፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድበታል " ይላል ማሻሻያው።
1110Loading...
29
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እያካሄደ ባለው የምክክር ምዕራፍ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት • ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከ2 ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመወከል የሚሳተፉ ተሳታፊዎች በዓድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ ተገኝተው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምክክር ምዕራፍ ጀምረዋል፡፡ • ከግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ግማሽ ቀን በኋላ ተሳታፊዎች በየሕብረተሰብ ክፍሎቻቸው በመሆን ከየማህበረሰብ ክፍሎቻቸው በአደራ ያመጧቸው የአጀንዳ ሀሳቦች ላይ ውይይት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ • ዛሬ ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም በየህብረተሰብ ክፍሎቻቸው ውይይቶችን ሲያደርጉ የነበሩት ተወካዮች የሚስማሙባቸውን የአጀንዳ ሀሳቦች በየማህበረሰብ ክፍሎቻቸው በቃለ-ጉባኤ አስደግፈው ለኮሚሽኑ ያቀርባሉ፡፡ • ተወካዮች በአጀንዳ ሃሳቦቻቸው ላይ ከተወያዩ በኋላ በቀጣይ የምክክር መድረኮች ሀሳቦቻቸውን በውክልና የሚያቀርቡላቸውን 121 ተወካዮችን የሚመርጡ ሲሆን÷ ይህም እስከ ግንቦት 23 ቀን 2016ዓ.ም እንደሚቀጥል ይጠበቃል፡፡
1210Loading...
30
ከካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ የመንግስት አስተዳደሮች፣ ዳኞች እና ደላሎች የሚያገኙትን ያልተገባ ጥቅም ያስቀራል የተባለለት አዋጅ ሊወጣ ነው። በካሳ ክፍያ ሂደት የመንግስት አስተዳደር ዳኞች እና ደላሎች የሚያገኙትን ያልተገባ ጥቅም በማስቀረት ዋናው የመሬት ባለይዞታውን ተጠቃሚ የሚያደርግ አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል። ይህ የተባለው መሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን፣ ካሳ የሚከፈልበትን እና ተነሽዎች መልሰው የሚቋቋበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ ለማሻሻል ውይይት በተደረገበት ወቅት ነው። በውይይቱ የተሳተፉ አካላት እንደተናገሩት ለመሰረተ-ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ መዘግየት ዋናውና ትልቁ ማነቆ የልማት ተነሺዎች የሚጠይቁት የተጋነነ የካሳ ክፍያ መሆኑን ገልጸው፤ ንብረት የሚገምቱ እና ካሳ የሚከፍሉ ተቋማት ወደ አንድ ሊመጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል። በማህበረሰቡም ፕሮጀክቶች ተገንብተው ከሚሰጡት ጥቅም ይልቅ፤ ከካሳ ክፍያ የሚገኘውን ጥቅም አስበልጦ የማየት አስተሳሰብ በመኖሩ፤ ትክክለኛ እና ወቅቱን ያገናዘበ የካሳ ክፍያ ለመፈጸም የአዋጁ መሻሻል አስፈላጊነቱ የላቀ እንደሆነም ባለድርሻ አካላት አንስተዋል። የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በበኩላቸው የአዋጁ መሻሻል በካሳ ክፍያ ሂደቱ በታችኛው እርከን የመንግስት አስተዳደር፣ ዳኞች እና ደላሎች የሚያገኙትን ያልተገባ ጥቅም በማስቀረት ዋና የመሬት ባለይዞታውን ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል። ማሻሻያ አዋጁ መሰረተ ልማቶች ሲገነቡ የንብረት ግመታው እና የካሳ ክፍያው በክልልና  በወረዳ መዋቅሮች የሚፈጸም መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ዜጎች ቅሬታ ሲያነሱም በአቅራቢያቸው የፍትህ አገልገሎት እንዲያገኙ የሚረዳ መሆኑን ተናግረዋል።
1220Loading...
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለቤተክርስቲያኗ ቅሬታ ምላሽ ሰጥቷል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ(ዶ/ር) ‹‹ ከኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በኩል ዛሬ የቀረበው ቅሬታ እንደደረሳቸው" ተናግረዋል፡፡ ኮሚሽነሩ ለቤተ ክርስቲያኒቱ በሰጡት ምላሽ እንዳሉት ‹‹ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የኃይማኖት ተቋማት በምክክሩ እንዲሳተፉ ይፋዊ ደብዳቤ ልከናል፡፡" ብለዋል። ለአብነትም ‹‹ በአዲስ አበባ በተካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ መርሐ ግብር ከቤተ ክርስቲያኗ የተወከሉ አባቶች በፀሎት ጭምር መድረኩን እንዳስጀመሩት ›› አስታውሰዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ በምክክሩ አንድትሳተፍ ይፋዊ ደብዳቤ መላኩን ያስታወሱት ዮናስ ‹‹ ምናልባት ቴክኒካዊ በሆነ ምክንያት ›› በመሃል የተፈጠረ ችግር ካለ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋር በመነጋገር እንደሚያርሙት አመልክተዋል፡፡ ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ ይህንንም በመገናኛ ዘዴዎች ለህዝብ ይፋ ይገለፃል ብለዋል 👉 በኮሚሽኑ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ከሳምንት በፊት ቅሬታውን ማቅረቡ ይታወሳል።
Mostrar todo...
ጥብቅ መመሪያ እንዲተላለፍ ተወስኗል። ቅዱስ ሲኖዶስ በምልዓተ ጉባኤው የብፁዕ አቡነ ልቃስን የአውደምህረት ንግግር ከቤተክርስቲያኒቱ ቀኖና አስተምህሮት ውጭ የሆነ ፣ ቅዱስ ሲኖዶስንም ሆነ ቤተክርስቲያንን የማይወክል ነው ሲል ውሳኔ አሳለፈ። ንግግራቸው ቤተክርስቲያንን ዋጋ እያስከፈላት መሆኑና በቤተክርስቲያንና መንግሥት መካከል የነበረውን ግንኙነት እንዳሻከረው ተመላክቷል። ቅዱስ ሲኖዶስ ፥ ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የምስራቅ አውስትራሊያ እና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ፅ/ቤት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስ ታህሳስ 19 / 2016 ዓ/ም በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሜሪላንድ ከተማ ሐመረብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ ወቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በዓለ ንግስ ላይ ታቦተ ህጉ በቆመበት እንዲሁም ምእመናን በተሰበሰቡበት ቤተክርስቲያንን የማይመጥንና የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ብሎም የአባትነትን ክብር ዝቅ በሚያደርግ ሁኔታ አንድን ጠቅላይ ሚኒስትር ፦ ° " ግድሉ " ° " ዘርህ ይጥፋ " ° " የአድማ ብተና ይበትንህ " በማለት መናገራቸውን ገልጿል። ይህ ንግግራቸው ፦ ➡️ ቤተክርስቲያኒቱን የማይወክል፣ ➡️ ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ የሆነ፣ ➡️ ቅዱስ ሲኖዶስን የማይወክል፣ ➡️ ለዘመናት ጸንቶ የቆየውን የአባቶች ክብር ዝቅ የሚያደርግ፣ ➡️ የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ዝቅ የሚያደርግ፣ ➡️ ከህገ ኦሪትም ሆነ ከቃለ ወንጌል ያፈነገጠ ንግግር እንደሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ ገልጿል። የብፁዕ አቡነ ሉቃስን ጨምሮ አንዳንድ አባቶች በተለያየ ቦታ የሚያስተለልፏቸው መልዕክቶች ቤተክርስቲያንን ለትችት እየዳረገ እንዲሁም ዋጋ እያስከፈለ ነው ተብሏል። በቀጣይ የመግለጫ አሰጣጥ እና የትምህርተ ወንጌል አሰጣጥ ገዢ ህገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለጥቅምት 2017 ዓ/ም ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርብ ተወስኗል። ከዛሬ ጀምሮ በመላው ዓለም ያሉ አህጉረ ስክበት ስህተት እንዳይፈጸም ቁጥጥርና ክትትል እንዲያደርጉ ያን ሳያደረጉ ቀርተው የተሳሳቱ እና ከቀኖና ቤተክርስቲያን ያፈነገጡ ትምህርቶች አውደምህረት ላይ ቢተላለፉ በኃላፊነት እንደሚያስጠይቅ ጥብቅ መመሪያ እንዲተላለፍ ተወስኗል።
Mostrar todo...
👍 2
ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም የመሸፈን አብዮት ጀምረናል - ም/ጠ/ ሚ ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያን ከተረጂነት የማላቀቅና ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም የመሸፈን አብዮት ጀምረናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መናገራቸውን ፋና ዘግቧል፡፡ አቶ ተመስገን ባደረጉት ንግግር፥ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አስተዳደርን እና ሀገራዊ የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን አዲስ ፖሊሲ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቀዋል፡፡ ከተረጂነት እንውጣ የሚል አብዮት መቀስቀስ የፖሊሲው ዋና ግብ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ አደጋን በራስ የመሸከም አቅም ማዳበር እንደሚያስፈልግ አስረድተው÷ በቅድመ አደጋ፣ በአደጋ እና በድህረ አደጋ የሚሰሩ ስራዎች በታቀደው መሰረት በተናበበ መልኩ መከናወን እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡ እንደሀገር አደጋን በራስ አቅም መቋቋም እንችላለን የሚለውን ትልቅ አብዮት ለማሳካት አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸውንም ነው የተናገሩት። ከተረጅነት ለመላቀቅና እርዳታን በራስ አቅም ለመሸፈን የባህል ለውጥ እንደሚያስፈልግና ልመናን መፀየፍ እንደሚገባም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ ከ 20 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የምግብ ድጋፍ እንደሚሹ በቅርቡ ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም።
Mostrar todo...
ተወዳጁ ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ ከ42 ቀናት እስር በኋላ ዛሬ ዳይሬክተሩን ዳግማዊ ፈይሳ ጨምሮ ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ፍርድ ቤት ቀርቧል "በቡድን በመደራጀት ወጣቶችን መልምሎ በማሰማራት፣ ገንዘብ ለሽብር ቡድኑ ሎጂስቲክስ መግዣ ለማዋል... ሕገ-መንግስቱን እና ሕገ-መንግታዊ ስርዓቱን በኃይል በትጥቅ ትግል ለመቀየር ሲንቀሳቀሱ በመገኘታቸው ተጠርጥረው".... የሚሉ መዘርዝሮችን የያዘ የጊዜ ቀጥሮ ማመልከቻ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል። ተዋናይ አማኑኤል እስራኤል አገር "እብደት በሕብረት" የተሰኘ ቴአትሩን ለማሳየት አውሮፕላን ሊሳፈር ሲል ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ/ም ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች ተይዞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ተወስዶ መታሰሩ ይታወሳል። አማኑኤል ከታሰረ ከ42 ቀናት በኋላ በዛሬው ዕለት ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ፖሊስ ፍርድ ቤት አቅርቦት የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለሰኔ 11 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ተዋናይ አማኑኤል በተጨማሪም በቅርቡ በፖሊስ ተይዞ ለእስር የበቃው የ"እብደት በሕብረት" ቴአትር አዘጋጅ አንጋፋው ከያኒ ዳግማዊ ፈይሳን ጨምሮ ሌሎች 20 ሰዎችን በአንድ መዝገብ ለፌደራል መደበኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል። ጠበቆች ተወክለው በመቅረብ የዋስትና መብታቸው ከዚህ ሁሉ የእስር ቀናት በኃላ እንኩዋን ሊፈቀድላቸው የሚገባ መሆኑንና እስሩም አግባብነት የሌለው መሆኑ አንስተው ተከራክረዋል። ሕገ መንግስታዊ እና ስነ ስርአታዊ የሕግ ድንጋጌዎች ተጠቅሶ ሰፊ ክርክር ከተደረገ በኋላ ችሎቱ ሁሉንም ተጠርጣሪዎች ለሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ማረጋገጥ ችያለሁ። Via፣ Yared Shumete      T.me/ethio_mereja
Mostrar todo...
#እንድታውቁት🚨 2 የወተት ምርቶች የደህንነትና የጥራት መስፈቶች አሟልተው ባለመገኘታቸው ምክንያት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ማሳሰቢያ ተላለፈ። 1ኛ. #Sultan Instant Full Cream Milk Powder (400g) , (PD 19/02/2024, & Exp 18/02/2026 B.NO.56 2ኛ. #Nura Super Instant Full Cream Milk Powder (400g) PD 01/11/2023 እና Exp 31/10/2025 BT 23246006 LOT No. 230915 291123003127 የወተት ምርቶች የደህንነትና የጥራት መስፈርቶች ያላሟሉ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው የንግድና ቀጠናዊ ትስስስር ሚኒስቴር አሳስቧል። @tikvahethiopia
Mostrar todo...
የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ለቆ እንዲወጣ አንፈልግም ሲሉ የሶማሊያ ፌደራል መንግስት አካል የሆኑት “ጁባላንድ” እና “ደቡብ ምዕራብ” ግዛቶች ገለጹ የሶማሊያ ፌደራል መንግስት አካል የሆኑት “ጁባላንድ” አስተዳደር እና “ደቡብ ምዕራብ” በሚል የሚጠራው የሶማሊያ ግዛት አስተዳደር የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ለቆ እንዲወጣ እንደማይፈልጉ አስታወቁ። የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ለቆ መውጣት የተወሳሰበው የሶማሊያ የጸጥታ ሁኔታው ያባብሰዋል፣ አልሸባብ እንዲንሰራራ ያደርገዋል ሲሉ ግዛቶቹ ገልጸዋል። ሁኔታው በሀገሪቱ በሚገኙ ባለድርሻ አካላት ዘንድ ስምምነት ሊፈጠርበት የማይችል ነው ያሉት የጁባላንድ ምክትል ፕሬዝዳንት ሞሃሙድ ሰይድ አደን ውይይት ሊደረግበት ይገባል፤ ማንም በተናጠል ውሳኔ ሊያሳልፍ አይችልም ሲሉ አስታውቀዋል። የደቡብ ምዕራብ ግዛት የጸጥታ ጉዳዮች ሚኒስትር በኤክስ (ትዊተር) ገጹ በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ስራ በተሰማራው የአፍሪካ ጦር ሀይል ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር አስቸጋሪ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ሲል ገልጾ ለአበርክቶው ምስጋና እናቀርባለን፣ የጦሩ ቆይታ ይቀጥላል፣ የድርሻውንም ይወጣል ሲል አወድሷል። የኢትዮጵያ ጦር ለቆ ይውጣ መባሉ አላስፈላጊ እና የተሳሳተ ምክር ሲል ተችቷል።    
Mostrar todo...
79 አባላት ያሉት የሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ የቢዝነስ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ ********** በሳውዲ አረቢያ የንግድ ምክር ቤት ፌዴሬሽን የተመራ 79 አባላትን የያዘ የሳውዲ አረቢያ የኢንቨስትመንት እና የንግድ የልዑካን ቡድን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል። ጉብኝቱ የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር ያለመ ሲሆን፤ ልዑኩ በአዲስ አበባ በሚኖረው የሶስት ቀናት ቆይታም ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የማምረቻ ቦታዎችን እንደሚጎበኝ ይጠበቃል። በተጨማሪም የኢትዮ-ሳውዲ አረቢያ የቢዝነስ የምክክር መድረክ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል። በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትና በሳውዲ አረቢያ አቻው መካከል የመግባቢያ ስምምነት ይፈረማል ተብሎም ይጠበቃል።
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram