cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ቢኒ የመጻሕፍት ግብዣ

👉 ሰሞነኛ ትኩስ መፅሐፍት ከነድስቱ እንገጮታለን። 👉 ዘርፈ ብዙ የሆነውን የኪነት ወሬ እስከነቃጭሉ ዱብ እናረጋለን። 👉 ነባርና አዳዲስ መፅሐፍትን መጠነኛ ዳሰሳ አድርገን እንጠቁሞታለን። ✴ ወሬ ጥሩ ስለሆነ በዚህ ቦይ ላኩልኝማ @a3b2ysm

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
2 102
Suscriptores
Sin datos24 horas
-67 días
-3030 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
አሁን ያሉት የ60ዎቹ ትውልድ ጽሑፍ ከዘመን ጓዶቻቸው ጋር የነበረውን መጠባጠብ ከመዘገብ ፈቅ ብለው በተማሩበት መስክ ያከማቹትን ዕውቀት በቋንቋችን በመጻፍ ሳይንስን ማኸዘብ ለምን ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ አልሆነም? ለዚህኛው ትውልድ ከያ ትውልድ ፍጭት ይልቅ ያ ትውልድ ከነበረው ዕውቀት ቆርሶ ቢሰጠው አይሻልምን?
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በወመዘክር አዳራሽ፥ የደጋ ሰው አልበም ላይ የውይይት ሐሳብ ይቀርባል። መነሻ ጽሑፍ አቅራቢ፦ ቢኒያም አቡራ እና ትሬዛ ዮሴፍ አዘጋጅ፦ ዐውደ ፋጎስ የውይይት ክበብ ቀን፦ እሑድ / ሰኔ 16 ሰዓት፦ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ቦታ፦ በወመዘክር አዳራሽ (ብሔራዊ አከባቢ ከሚገኘው ከድሮ ኢቲቪ ሕንጻ ጀርባ) መግቢያ፦ በነጻ
Mostrar todo...
አምላክ ለእኛ ብሎ ቢያፈሰው ደሙን ለምን ከለከለች ፀሐይ ብርሃኗን? ረቡኒ፣ በጎልጎታ ሲሰቀል ፀሐይ አሻፈረኝ ብላ ብርሃኗን ከልክላለች። ፀሐይ እምቢኝ እንዳለች ከአራቱ ወንጌላት ሦስቱ ዘግበውታል። በዚህ ቀን ሊፈጠር የሚችል የፀሐይ ግርዶሽ እንደሌለ ሳይንቲስቶች አረጋግጠዋል። ለደቂቃዎች እንጂ ለሰዓታት የሚቆይ የጨረቃ ግርዶሽም እንደሌለ እሙን ነው። ፀሐይ ብርሃኗን የነፈገችው በደመና ጉያ ተሸሽጋ አይደለም። ታዲያ ለሦስት ሰዓታት የቆየው የፀሐይ ዝምታ ለምንድነው? ደሙን ያፈሰሰው ለእኛ ሆኖ ሳለ ፀሐይ ምን ይሁን ብላ ነው የሸሸችው? ይኼ ምርምር የሚጠይቅ ሚስጥር ነው። ጨለማ የእግዚአብሔር ሕልውና ያለመኖር ውክል ነው። ክርስቶስ የሰው ልጆችን ኃጢዓት በሙሉ የመሸከሙ የማረጋገጫ ሰነድም ጭምር ነው። በዚህም የክርስቶስን የሰቆቃውን ክብደት እናያለን። የእግዚአብሔር አብ አጠቃላይ ፍርድም ይንፀባረቃል። የፀሐይ ግብዓቱ ከፈርዖን አገዛዝ ነፃ ለመውጣት የተደረገውን ተዓምር ያስታውሰናል። እስራኤላዊያን ከግብፅ ባርነት ከመላቀቃቸው በፊት ሦስት ቀን በግብፅ ጨለማ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱሳችን ያወሳል። እስራኤላውያን ከሦስቱ የጨለማ ቀናት በኋላ ከግብፅ ባርነት ነፃ እንደሆኑ ሁሉ፣ በዕለተ ስቅለት ከረበበው ጽልመት ማግስት የሰው ዘር በሙሉ ከኃጢአት ባርነት ነፃ ወጥቷል። በሥራ ከሚመጣ የጽድቅ ባርነት በፀጋ ወደ ሚገባበት የጽድቅ ነፃነት መልሶናል። በግብፅ ምድር የጨለመችው ፀሐይ ሙሴ እጁን አንስቶባት ሲሆን በዕለተ ስቅለት የጠለቀችው ፀሐይ ግን በገዛ ፍቃዷ ይመስላል። የከበረው ስጋ የከበረው ደም በመስቀል ላይ ዋለ ኢየሩሳሌም የሰው ልጅ ራሱን ወደ መንፈሳዊ ረቂቅነት መቀየር ስለማይችል፥ ፈጣሪ ራሱን ወደ ተጨባጭ አካል መቀየር ነበረበት። "የከበረው ስጋ የከበረው ደም" በማለት መለኮት  ራሱን ወደ ተጨባጭ አካልነት መቀየሩን ጥቁምታ ንሰጠናል። ወልድ መለኮታዊ ክብሩን ትቶ ስጋ መልበሱ ለፍጥረቱ ያለውን ጥልቅ ፍቅር ያመለክታል። ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት ሲል መስቀል ላይ የዋለበትን የፍቅር ውሃ ልክ የሚተካከል አይገኝም። እዩት ኢየሱስን መስቀሉ ማማሩ ለተመራመረው ብዙ ነው ሚስጥሩ መስቀልና የመስቀል ውበት እርስ በራስ የሚቃረኑ ሐረጎች ናቸው። መስቀል በሰቀቀን የታጨቀ የሰቆቃ ጥቅል እንጅ አንዳች የውበት ዘለላን ያነገበ ነዶ አይደለም። መቸም መስቀል ስንል እንጨቱን አለመሆኑን ልብ ይሏል። በተለየ ሁኔታ የኢየሱስ መስቀልን እንዲያምር የሚያደርግ የስዕል ባለሙያ እንጅ የመጽሐፍ ቅዱስ ተረክ የለም። እንደውም እንደውም የመሲሕው መስቀል በየትኛውም ሰፊ ትከሻ የሚሸከሙት ሆኖ አናገኘውም። መስቀሉ ከገዛ ወገኖቹ  ዘንድ ቅቡልነት ከማጣት የሚጀምር እንጅ ሰያፉን እንጨት ተሸክሞ ተራራ ከመውጣት ብቻ አይደለም። ሌላው ሌላው ይቅርና ሐዋርያቱ እንኳን ብቻውን ትተውታል። ቁንጫ እንኳን ከፍራሹ ጋር አብሮ ይቃጠላል። ፎካሪው ጴጥሮስ እንኳን ከመስቀሉ ግዝፈት የተነሳ በአንድ የክህደት መለዮ ሦስቴ ቃለ-አባይ ሆኗል። ታዲያ ምኑ ጋር ነው የኢየሱስ መስቀል ማማሩ? የመስቀሉን ውበት ሚስጥር እሱው ይግለጥልን! ቢመቱት ቢሰቅሉት ቢያላግጡበትም ምንም አላገኙም ከሱ ዘንድ ስህተት ፈጣሪ መሆኑን ሚስጥሩ ገብቷት ጌታ ላይ ዝም አለች ግዑዟ መሬት ትዕቢተኛ በቆሎ ከጤፍ ማኅፀን ዱቄት የሚወጣ አይመስላትም። ግዑዟ መሬት የገባትን እውነት፣ ሕያው ነኝ ባዮቹ የሰው ልጆች ሊያስተውሉ ዘንድ አልተቻላቸውም። ልሳነ-ሰቡ፣ ፈጣሪው ላይ እያላገጠ ሲያዋርደው፣ ምድር ግን በልሳነ-ተፈጥሯዊ አርምሞ፣ ፈጣሪዋን አከበረችው። የአለማችን አብዛኛው ጦርነቶች የተካሄዱት በተራራዎችና በኮረብቶች ላይ ነው። ጦርነቱን ያሸነፈው ሀገር በኮረብታው አናት ላይ ትልቅ እንጨት በመትከል ባንድራውን ያውለበልባል። ኢየሱስ በቀራኒዮ ኮረብታ የተውለበለበ የእግዚአብሔር መንግሥት ሰንደቅአላማ ነው። በመጨረሻም ይኼ ታላቅ ንጉስ ሲገለጥ በሰማይ የናቁት የወጉት ይሉለታል ዋይ ዋይ ምድርና ሰማይ ከፊቱ ሲሸሹ ወዴት ልግባ ይላል ትልቁ ትንሹ መልካም በዓል 🙏 ከቢኒያም አቡራ
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
የሚሳም ተራራን ካነበብኩ በኋላ የተሰማኝን እንዲህ ባለ ዳሰሳ አቅርቤያለሁ።  ሊንኩን በመጠቀም ዳሰሳውን ማግኘት ይችላሉ። https://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=32452:%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%88%B3%E1%88%9D-%E1%89%81%E1%88%B5%E1%88%8D&Itemid=211
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
"አዝማሪው ልቤን የት አገኛለሁ?" እያላችሁ፥ ልቤን ውልቅ ስታደርጉ የነበራችሁ እስኪ እንያችሁ። ሁለተኛ ዕትም በገበያ ላይ ውሏል🙏 ዋና አከፋፋይ - ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ህንፃ ጎን በ ሀሁ የመፃህፍት መደብር ያገኙታል፡፡
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ዓለማየሁ ገላጋይ፣ በወሪሳ አውድማ ላይ በምጸታዊ መንሽ ማኅበራዊ አዝዕርትን ንፋስ ላይ አበጥሯል። በታለ ማሰሮ ጦማራዊ ልቦለድን ንጧል። በኢህአዴግን እከስሳለሁ ሙቀጫ የጋዜጠኝነትን ዘነዘና ይዞ ምኩራብ ወጥቷል። በቅበላ ብራና የድህረ ዘመናዊ ልቦለድን ከትቧል። በመልክአ ስብሃት ሰፌድ ላይ ሰበዝም፣ አለላም፣ አክርማም ሆነ ስንደዶ ለመሆን የሚመች፥ የደቦ ከያኔ መሆኑን ተመልክተናል። በየፍልስፍና አጽናፍ ተርጓሚነቱን፣ በስብሃት ገ/እግዚአብሔር ሕይወትና ክሕሎት - ኀያሲነቱን አስመስክሯል። በየተጠላው እንዳልተጠላው አይነኬ ዕሳቤዎችን በመጠይቅ ወንፊት አንገዋሏል። በአጥቢያ የንስር ዓይናማነቱን፣ በመለያየት ሞት ነው ሊቀ-መጣጥፍነቱን፣ በፍቅር ስም ላይ ደግሞ experimental novelist-ነቱን ተመልክተናል። በኩርቢት መም ላይ የስሜት ጂምናስቲክ አሠርቶናል። በ18ኛው ደሞ 24 እንዳልሞላው ሊያስታውቀን ተከስቷል። እኔ በበኩሌ በጋሽ ወንድዬ ዓሊ ብሂል "የሥነ-ጽሑፍ ወዛደር" ብዬዋለሁ። what a ትጋት?!?! ቢኒያም አቡራ
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
#ካነበብኳቸው የ"ያ-ትወልድ" መጻሕፍት የኔ ምርጦች፦ ❤ማማ በሰማይ - ሕይወት ተፈራ 💙በአጭር የተቀጨ ረዥም ጉዞ - አንዳርጋቸው አሰግድ 💚እኛና አብዮቱ - ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ 💛የሻምላው ትውልድ - ፋሲካ ሲደልል 🧡የጭድ እሳት - ፕሮፌሰር ጴጥሮስ ቶጃ 💜የሱፍ አበባ - ሀብታሙ አለባቸው ❤ያልታሰበው - ኮ/ል ብርሃኑ ባየህ 💚በሀገር ፍቅር ጉዞ - አብዩ ብርሌ 💜ዳኛው ማነው - ታደለች ኃ/ሚካኤል #የእናንተስ?
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
#የደራሲዎች ማስተርፒስ (በኔ የንባብ ደረጃና አቅም) ❤ ፍቅረማርቆስ ደስታ - ከቡስካ በስተጀርባ ❤ ሀብታሙ አለባቸው - ታላቁ ተቃርኖ ❤ ወንድዬ ዓሊ - ወፌ ቆመች ❤ አዳም ረታ - የስንብት ቀለማት ❤ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር - ሌቱም አይነጋልኝ ❤ በዓሉ ግርማ - ኦሮማይ ❤ ሀዲስ ዓለማየሁ - ፍቅር እስከ መቃብር ❤ ዳኛቸው ወርቁ - አደፍርስ ❤ አቤ ጉበኛ - አልወለድም ❤ እንዳለጌታ ከበደ (ዶ/ር) - በዓሉ ግርማ ሕይወቱና ሥራዎቹ ❤ ጸጋዬ ገብረመድህን (ሎሬት) - እሳት ወይ አበባ ❤ ዘነበ ወላ - ማስታወሻ / ልጅነት ❤ በዕውቀቱ ስዩም - ከአሜን ባሻገር ❤ ብርሃኑ ዘርይሁን - የታንጉት ሚስጥር ❤ ኃይለመለኮት መዋእል - ጉንጉን የእናንተስ????
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ዛሬ ነው! ... 11:31 ይጀምራል። ወመዘክር እንገናኝ! ... መግቢያ በነጻ አድራሻ፦ ብሔራዊ አከባቢ ከሚገኘው ከድሮ የ etv ሕንጻ ጀርባ ወይም ከፌና ፊትለፊት (ወመዘክር-የኢትዮጵያ ቤተመጻሕፍትና ቤተመዛግብት)
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
የፊታችን አርብ 11:30 በወመዘክር አዳራሽ "የዓድዋ ስንኞች እና ንቡር ጠቃሽነታቸው" በተሰኘ ርዕስ የጂጂ፣ የቴዲ አፍሮ እና የዳኘ ዋለ አድዋን መሠረት ባደረጉ ሙዚቃዎች ላይ የውይይት ሐሳብ ይቀርባል። የውይይት ጽሑፍ አቅራቢ - ቢኒያም አቡራ
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.