cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Trust Agro-consulting and farming P.L.C ትረስት አግሮ-ኮንሰልቲንግ ኤንድ ፋርሚንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

Trust Agro-consulting is a multi-dimensional agricultural consulting firm based in Bishoftu, Ethiopia that operates across the country. Our company was founded by a team of fully qualified and highly exper Farm with confidence +251919076607 +251932314562

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
5 738
Suscriptores
-224 horas
-27 días
-630 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ዋነኛው የእንስሳት መኖ ውድነት መቅረፍያ መንገድ ============================ ድጅታችን #TACF በተናገርነው መሰረት እንደ ቃላችን በዘርፉ የረጅም ዓመታት ልምድ ባለቤት በሆኑ አንጋፋ እና ብርቅዬ ባለሙያዎቻችን እጅግ ግዙፍ በሆኑው ጉመራ የእንስሳት መኖ ማቀናበርያ ፋብሪካ በተግባር ተከናውኗል፡፡ ይህም አሁናዊ የመኖ ውድነትን እያንዳንዱ አርቢ በራሱ በማቀናበር ችግሩን ያቀላል የሚል ተቋማዊ ድጋፋችንን በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡ በቀጣይም በ32ኛ ዙር  የዶሮ እርባታ(የእንቁላል፣የሳሶ እና የ45ቀን ስጋ ዶሮ) ስልጠናዎች ከወዲሁ በ0932042222 ላይ በመደወል  መመዝገብ እንደምትችሉ በታላቅ ደስታ መግለፅ እንውዳለን፡፡ #በመተማመን #ያርቡ
Mostrar todo...
👍 8
Photo unavailableShow in Telegram
31ኛ ዙር  ስልጠና በዘመናዊ የዶሮ እርባታ ============//============= ባንጋፋ ባለሙያዎቻችን ከአነስተኛ ዶሮ እርባታ  እስከ ኢንዱስትሪ ደረጃ በተግባር  ጠቅቀው ይማሩ ♻️ የስልጠ ቀን ከሰኔ 27- ሰኔ 29 ለተከታታይ ሙሉ 3ቀናት ♻️ የስልጠና ቦታ ፡ አ.አ  ጉርድ ሾላ ከሴንቸርይ  ሞል ቀጥሎ ፍሬሽ ኮርነር ያለበት 4 ፎቅ ♻️ የስልጠና ዋጋ፡ 2950 ብር (የምዝገባ፣ የስልጠና፣ የሰርተፍኬት እና ሻይ ቡና ጨምሮ)                                                       ✅ለመመዝገብ  ማስፈንጠሪያውን  ይጫኑ         https://forms.gle/oT4YFduYGv9AXXVN8
Mostrar todo...
👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
29ኛ ዙር የእንስሳት መኖ ዝግጅት እና ማቀናበር  ስልጠና ሊካሄድ እነሆ 1 ቀን ብቻ ቀረው፡፡ ስለዚህም ካላስፈላጊ ወቺ እራሶን አና ድርጅቶን በመታደግ  ይበልጡኑ ትርፎን በ10 ፐርሰንት ክፍ ያርጉ፡፡ ለመመዝገብ ፡0932042222 ላይ አሁኑኑ ይደውሉ፡፡
Mostrar todo...
👍 1👏 1
የገንዘብ ሚኒስቴር የእንስሳት መኖን ጨምሮ በተለያዩ ምርቶች ላይ የ15% ተጨማሪ እሴት ታክስ  ተግባራዊ አድርጓል የሚል ዜና ዛሬ 19/10/2016 ተሰምቱዋል:: በአሁን ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ በአገር አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ የግብርናና በተለይ የእንስሳት እርባታ ልማትችግሮች ጎልተው ይታያሉ፡፡ በባህላዊም ሆነ በዘመናዊ መንገድ ለገበያ የሚቀርብ የእንስሳት ሀብት ልማት ትልቁ ተግዳሮትየእንስሳት መኖ ችግር ነው፡፡  በዘርፉ የተደረጉ በርካታ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በኢትዮጵያየእንስሳት ዘርፍ ምርትና ምርታማነት ዝቅተኛ እንዲሆን ያደረገው ዋና መንስኤ ጥራት የሌለው እና በቂአቅርቦት የሌለው የእንስሳት መኖ ነው፡፡ ልዩ ልዩ ጥናቶች ከለዩዋቸው ዋና ዋና የመኖ አቅርቦት ችግር መንስኤዎች መካከል የሚከተሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ፡- እነዚህም፣ ሀ. በወቅቶች ተለዋዋጭነት ተጽዕኖ ላይ የወደቀ አቅርቦት፣ የመኖ እጥረት እና መኖውን ለማዘጋጀት የሚያስፈልገው ግብዓት ዋጋ መወደድ የእንስሳት መኖ አቅርቦትን በዘላቂነትና ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ እንዳይቀርብ እንቅፋት መፍጠሩ፤ ለ. የእንስሳትን መኖ የሚያቀርቡ እና የእንስሳት እርባታ ንዑስ ዘርፎች ከፍተኛና ተደራራቢ የታክስ ጫና ያለበት መሆኑ፤ ለምሳሌ የእንስሳት መኖውን ለመዘጋጀት ጥቅም ላይ በሚውለው ግብዓት ላይ የ15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚጣልበት ሲሆን፣ በተጨማሪም በእነዚሁ ግብዓቶች አማካይነት ተቀነባብሮ በሚዘጋጀው መኖ ምርቱ ላይ ሌላ የ15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፈላል፡፡ የዶሮ እርባታን በሚመለከት በመንግሥት በቅርቡ የተወሰደው እርምጃ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ በዶሮ ምግብ ግብዓቶች ላይ ተጥሎ የነበረውን ተጨማሪ እሴት ታክስ ሙሉ ለሙሉእንዲቀር ተደርጓል፡፡ ለዶሮ እርባታ የሚያገለግሉ የመኖ ግብዓቶችና ሌሎች መሳሪዎች ከውጭየሚገቡ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሐ. ለገበያ የሚቀርብ የእንስሳት መኖ ጥራትና ደህንነት ማረጋገጥ አስቸጋሪ መሆኑ በተለይም በቅባት እህሎች ተረፈ ምርትም ሆነ በሌሎች የተቀነባበሩ የዶሮ መኖዎች ላይ ሊኖር የሚችለውን ከፍተኛ የአፍላቶክሲን መጠንን መቆጣጠር አዳጋች መሆኑ፤ መ. የእንስሳት መኖ የሚያዘጋጁ ማሽኖች ከአቅማቸው በታች እያመረቱ በመሆኑ ተቀነባብሮ ለሚዘጋጅ የእንስሳት መኖ ያለውን ፍላጎት በሚፈለገው ደረጃ ማሟላት አለመቻሉ፤ ሰ. ተረፈ-ምርቶችን፣ ንጥረ-ነገሮችንና ቫይታሚኖችን እንደገና የማቀነባበር አቅም ዝቅተኛ መሆኑ እና ከውጭ አገር ማስገባቱ ከዋጋና ከውጭ ምንዛሬ ፍላጎት አንጻር አስቸጋሪ መሆኑ፤ ረ. በዘመናዊ መንገድ ለገበያ የሚቀርብ የእንስሳት መኖ ዘርፍን ለማበረታት ጥቅም ላይ የዋለ የቴክኒክ ድጋፎች (ለምሳሌ፡-ጥናቶች፣ የኤክስቴሽን አገልግሎት) አነስተኛ መሆን እንዲያውም በጭራሽ የሌለ መሆኑ፤ ሠ. የግብዓት ዋጋ በመጨመሩና የአገልግሎት አሰጣጡ ምቹ ባለመሆኑ የእንስሳት መኖ የሚያዘጋጁ አምራቾች በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛሉ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የአገራችንን ግብርና እድገት ዓበይት ማነቆዎች መሆናቸው ተደጋግሞ ተገልጿል:: Source  ;Trust agro Consultant
Mostrar todo...
👍 7 2👏 2
Archivo de publicaciones
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.