የስንኝ ቋጠሮ
Ir al canal en Telegram
የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው። ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!
Mostrar más2 046
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
2 046
2 046
🇪🇹🇪🇹ማንን ልፍታላችሁ?🇪🇹🇪🇹 /ማቴ 27:17/
✅ የጲላጦስ ትልቁ ችግር የውሳኔ ሰው አለመሆኑ ነው። አቋም የሌላቸው ሰዎች ለውሳኔ የእውነትን መለኪያ ሳይሆን የድጋፍ ድምፅ ይፈልጋሉ። እውነትን ከጲላጦስ ሳይሆን ከኢየሱስ አንጻር የተመለከተ ሰው ከመቅበዝበዝ ሕይወት ያለረፈ ነው።
ጲላጦስ የውሳኔ ሰው ባለመሆኑ የማይወዳደሩትን ሊያወዳድር ተነሳ። በመጀመሪያ በርባንና ኢየሱስ አይወዳደሩም። ሲቀጥል የተቀመጠበት ወንበር የፍርድ መስጫ እንጂ የአስመራጭ ኮሚቴ ወንበር አልነበረም። እራሱ መወሰን ሲገባው ማንን ልፈታላችሁ የሚል የምርጫ ጥያቄ ለአይሁድ አቀረበ። አንዳንዴ በእነርሱ ጉዳይ ሌሎች እንዲወስኑላቸው የሚፈልጉ ሰዎች አልገጠሟችሁም??? እነዚህ ሰዎች አቋም የሌላቸው ሰዎች በመሆናቸው የማይወዳደሩትን ነገሮች ሲያወዳድሩ ይውላሉ።
ጲላጦሳዊያን ኢየሱስን ከሰው ጋር፤ ገንዘብን ከሕይወት ጋር፤ እውነትን ከደጋፊ ጋር ያወዳድራሉ። እንደ እነዚህ አይነት ሰዎች ወጣትነታቸው ሲያምታቱበት ለጊዜው ቢሳካላቸውም የዕድሜ ማታ ላይ ግን ብቸኛ ይሆናሉ። አንዱን ስላልመረጡ በመጨረሻም የሚመርጣቸው ያጣሉ። ኢየሱስን ከማንም ሳናወዳድረው እንምረጠው!!! እርሱን የምንመርጠው አማራጭ ስላጣን ሳይሆን ምርጫ ስለሌለን ነው። ከማንም ጋር የማናወዳድረው ጌታ ስሙ ይባረክ።
@bamatub
@bamatub
2 046
👉ሞታችንን ከሞተ ሕይወቱን አንኑር 👈
👉ትንሳዔ የ ክርስትና እምነት መሰረት የተጣለበት፤ የደም ውቅር ትክል ድንጋይ የፀናበት፤ ከ አልፋ እስከ ኦሜጋ ከቅድመ አለም እስከ ዘልአለም፦ ለ ሰው ልጆች ሁሉ እንደ ንጋት ወጋገን ብሩህ ተስፋ የፈነጠቀበት፣ ለ አዲስ ጅማሬ ብሉይ ያረጀበት፣ ድንቅ ክስተት ነው።
👉ትንሳኤ በ አራት ሆሄ የተዋቀረ የ እግዚአብሔር የዘላለም አጀንዳ ነው።
👉በ ትንሳኤ ሃዘን በደስታ ፍዳ በ ፌሽታ ልቅሶ በ እልልታ ሲቀየር በቀራኒዮ ያልተወራረደ እዳ ያልታደሠ ጓዳ የለም።
👉እግዚአብሔር ዘላለምን ፈጥሮ በ ዘላለም ውስጥ ትንሳኤን አቅዶ በ ትንሳዔ ውስጥ ዘላለምን ቋጭቶ ዘላለምን ጀመረው፨
👉ትንሳዔ የ አሁን ሳይሆን የቀድሞ የ ዘንድሮ ሳይሆን የድሮ እንጂ በ ሃሳብ ልእልና የመጣ የሰው ጉዳይ አይደለም፨
👉ይህ ማለት ትንሳዔ ከ ቅድመ አለም በፊት ካለ ከ ዘላለም በሁኋላ ይኖራል ዘላለም በሁኋላ ካለው ማለቴ ነው
👉ከ ምንም በላይ ደግሞ ሞት ራሱ የሞተበት እና ሃጥያት የተቀጣበት ልዩ ጉዳይ ነው። ስለ ትንሳዔ ያልኩትን ከያዛችሁ ያላልኩትን በሉ!! እርሱ ሞታችንን ከሞተ እኛ ህይወቱን እንኑር!!
ሞገስ ሎታ✍
@bamatub
@bamatub
@bamatub
2 046
ማንነትህን አወቅ
👉መቼም ቢሆን መርሳት የሌለብህ ነገር ቢኖር ማንነትህን የሚወስነው መገኛክ አንደሆነ ነዉ
👉መገኛክ መልካም ከሆነ አንተም መልካም ሰው ትሆናለህ
👉ከምታሳየው ተግባር አና ባህርይ በመነሳት ሰው መገናኛህን ሊገምት ይችላል
👉ይህን አውቀህ ውሎህን አስተካክል!! ባህሪህን ከመገኛህ አንፃር ቅረፅ!! በመልካም ስብእና ታነፅ!! ማንነትህን አወቅ!! አታስመስል!!
👉አግዚአብሔር ደግሞ መገናኛችን ነው ካልን ህይወታችን ከ አግዚአብሔር አንፃር መቀረፅ ይኖርበታል!!
👉ምክንያቱም አንበሳ የቱን ያክል ቢራብ ሳር አይበላም!!
👉ትንሽ ደበረኝ ራበኝ ብለህ ሳር አትብላ ልበ ሙሉ ሁን!!
👉ማንነትህን የሚወክል ነገር አይደለምና
🤔ቆይ ለምን ይመስልሃል? ዶክተር አብይ መነሀሪያ አከባቢ ሻይ ቤት ገብቶ ሻይ ማይጠጣው? አዛ ሰው ስለሌለ ነው? አይደለም!! ግን ቦታው አይመጥነውም!
Share it and join it
ሞገስ ሎታ✍
ይቀላቀሉን
@bamatub👈
@bamatub👈
@bamatub👈
2 046
🗝ስኬታማ ለመሆን ተረጋጋ እዚህም እዚያም አትርገጥ፨
🗝ለዓይንህ ያማረህን ሁሉ ለመጨበጥ ጥረት አታድርግ
🗝ለልብህ ትርታ፣ ለነፍስህ እርካታ፣ ለነገ አለኝታ በሚሆንህ ነገር ትኩረትህን ስጥ፨
🗝ከውጭ ይልቅ ውስጥህን አድምጥ
🗝ሁሉን ለመያዝ አትሞክር ሁሉን ለመያዝ ስትሞክር ሁሉን ታጣለህ
?አንዱን ምረጥ ለዛ ነገር ጊዜህን፣ ገንዘብህን ራስህንም ጭምር አሳልፈህ ስጥ፨
🗝ነገር ራስህን ከሰጠህ የሚነፍግህ ዝና የሚያሳጣህ ገንዘብ የሚጎድልህ ክብር አይኖርም፨
🗝በዛ በመረጥከው ነገር ለአለም መድሃኒት ትሆናለህ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሞገስ ሎታ✍
@bamatub
@bamatub
@bamatub
2 046
መኖር እፈራለሁ🔻
ሰው በምድር ላይ ሲኖር እድሜውን ሲጨምር፣
በራሱ አለም ኖሮ ስለ ሁሉ ሲጥር፣
ለነገዬ ብሎ ስንቁንም ሲቋጥር፣
እኔ ግን ፈራሁኝ መኖርን በ ምድር።
አካልን አኑሮ ማለፍ በምድር ላይ፣
እንደ ጅረት ፈሶ መድረሻ በሌለው በገሚስ መንገድ ላይ፣
ትእዛዙን ተላልፎ የመጣውን ከላይ፣
መኖር እፈራለሁ አላማ በሌለው በባዶ ተስፋ ላይ።
ነገ ያልፍልኛል እንደላቀቃለው፣
ሰው የደረሰበት እኔም እደርሳለሁ፣
ኑሮዬን በሙሉ መልካም አደርጋለሁ፣
መኪና ገዛለሁ........................
ቤት እገነባለሁ.............ማለቱ ከሆነ፣
ከሆነ የመኖር መጨረሻ ጥጉ፣
የደስታ ሒወት መጨረሻው ልኩ፣
አሁንም እላለሁ መኖር እፈራለሁ፣
ያለ እርሱ ሒወቴን ማሰብ እጠላለሁ።
ግጥም:- በረከት ሳፍይ
@bamatub
@bamatub
2 046
የስድብ እወጃ🗣🗣
ጭቃን በእጅህ ዝቀህ ያማረረህ ሰው ላይ ብትቀባው፣ ያጨቀየዋል. . . ያቆሽሸዋል።
በዚህ ሂደት ውስጥ ግን ፈፅሞ መዘንጋት የሌለብህ ነገር አለ ፤ ጭቃው ቀድሞ
ያቆሸሸው የአንተን እጅ ነው።
ስድብም እንዲሁ ነው። ስድቡ የታወጀበት ሰው ይሸማቀቅ ይሆናል፣ ስሜቱም ይታወክ ይሆናል። ነገርግን እውነታው ስድቡ ቀድሞ ያቆሸሸው፦ የቀመመውን አእምሮ፣ ያቁላላውን ምላስ እና አፈትልኮ እንዲወጣ የፈቀደለትን ከንፈር ነው።
እና ምን ለማለት ነው ስድብ የሚያረክሰው ተሳዳቢውን እንጂ ተሰዳቢውን አይደለም።
👇👇👇👇
👉 @bamatub👈👈
👉 @bamatub👈👈
👉@bamatub👈👈
👆👆👆👆
2 046
🦅 ንስር አሞራ እና አንተ ፣
አንቺ ፣ እኔ እና እኛ 🦅
💧💧💧
#የሃበሻ ወግ መፅሄት ላይ ታትሞ የወጣ ...
#ከጀመሩት የማያቆሙት ልብ የሚያረካ ፅሁፍ!
√
√
√
👉 ስለ ንስር አሞራ ስነግርህ ከሚገርም መሳጭ ታሪክ ጋር ነው ... እውነት እውነት እልሃለሁ የንስር አሞራ ታሪክ በሁላችንም ህይወት ውስጥ አለና ከራስህ ጋር እያዛመድክ ካነበብከው መጨረሻህን ድል ድል ታሸተዋለህና በፍቅር ተከተለኝ።
#ልጀምርልህ ...
ንስር አሞራ እስከ 70 አመት የሚኖር የእድሜ ባለፀጋ ነው ካልክ ልክ ነህ ... ግና 70 አመት ሙሉ በደስታ ከመኖሩ በፊት በእድሜው አጋማሽ ማለትም በ35 - 40 ባለው እድሜው ላይ ከባድ ነገር ይገጥመዋል ...
√ የመጀመሪያው :- ምግቡን ለማደን የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን ከመሬት ላይ ማንሳት ያቅተዋል ...
√ ሁለተኛው :- አጥንትን ሳይቀር መስበር አቅም ያለው አፉ(መንቁሩ) ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል ...
√ ሶስተኛው:- ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎች ስለሚከብዱት ያ ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ይበር የነበረው ሀይሉ ይክደዋል።
#እነዚህ ሶስት ከባድ ነገሮች ንስር አሞራ በእድሜው አጋማሽ የሚያጋጥሙት ከባድ ችግሮች ናቸው። አሁን ንስር አሞራ ያለው ምርጫ ሁለት ነው።
√ 1ኛ. ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ?
√ 2ኛ. አምስት ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋዕትነትን ከፍሎ ቀሪውን 35 አመት በደስታ ማሳለፍ ?
• የመጀመሪያውን ከመረጠ በእድሜው አጋማሽ ይሞታልና ታሪኩ እዛ ጋር ያበቃል።
• ሁለተኛውን ምርጫ ከመረጠ ግን እነዚህን አምስት መስዋዕትነቶች ማለፍ ይኖርበታል።
√ 1ኛ. ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት የብቻውን ጎጆ ይቀልሳል።
√ 2ኛ. ጎጆ ከቀለሰ በኋላ የመጀመርያ ስራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ ይጥላል።
√ 3ኛ. ይህን ካደረገ በኋላ አዲስ መንቁር ይወጣለታል፡፡ መንቁሩ እስኪያድግ ድረስ ታግሶ በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ መቆየት ግዴታው ይሆናል፡፡
√ 4ኛ. አዲስ መንቁር ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር ነቃቅሎ ይጥለዋል።
√ 5ኛ. አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቁትን እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ ይጥላል። በምትኩ አዲስ ላባ ያበቅላል።
#ይህን 5 ወር በዚህ መልኩ በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ ንስሮች መንደር ብቅ ይላል፡፡
•
•
•
🔥 ወዳጄ ሆይ:- 🔥
√ ችግር ገጠመኝ ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ አትበል ፣
√ ችግሬ ... ችግሬ ... እያልክም ነጠላ ዜማ አትልቀቅ ፣
√ ፊትህንም ችግር ፊት አታስመስል ፣
√ ጥቅም ላይ እያፈጠጠ የሚከተል ሰው በበዛበት አለም ላይ መውደቅህን መጥሪያ ካርድ አታሰራበት ፣
√ መራብ መጠማትህን ፖስት ለማድረግ አትቸኩል ፣
√ መገፋትህን እንደ ትልቅ ነገር ቆጥረህ ኡኡኡ አትበል ፣
√ ስንት ነገር መስራት የምትችልበትን አዕምሮ ለሃሜትና "አሉ ... አለች" መሳሪያ በመጠቀም "የውሸት እየኖርክ - የእውነት አትሙት" ...
በቃ ! ...
√ ልክ እንደ ንስር አሞራ በህይወትህ አጋማሽ ላይ ምርጫ መቶልሃል ...
1ኛ. ችግሩን ታቅፎ መሞት ...
2ኛ. ለችግሩ መስዋትነት ከፍሎ ማለፍ ...
••• ♦ አስተውል ... ♦•••
ሁለተኛውን ከመረጥክ ልክ እንደ ንስሩ አምስት ዋጋዎችን መክፈል አለብህና ዝግጁ ሁን ...
√ 1ኛ. ራስህን ከነገሮች አርቀህ በፅሞና ሃሳብህን መግራት ጀምር ... እዚህ ጋር ከወዳጅም ከጠላትም መራቅ ፍቱን መድሃኒት ነው ... ንስር አሞራው ከፍተኛ ተራራ ላይ የሚወጣው ከሁሉም ንስሮች እርቆ ለህይወቱ ዋጋ ለመክፈል ነው ... ይህን አይነት መላ ምሁራኑ "የስኬት ሱባኤ" ይሉታል።
√ 2ኛ. አንገብጋቢ ችግርህን ለመፍታት ቁርጥ ያለ አቋም ይዘህ እስከ ሞት የሚያደርስ መስዋትነት መክፈል። ንስሩ አፉ ላይ ያለውን ምግብ ማምጫ መንቁሩን እንደሚያስወግደው ሁሉ።
√ 3ኛ. መስዋት የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትዕግስት መጠበቅ ... ይህ ደግሞ ንስሩ መንቁሩ እስኪያድግለት ድረስ ምግብ ሳይበላ እንደሚኖረው ሁሉ አንተም ዋጋ የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትእግስት እና እምነት መጠበቅ።
√ 4ኛ. በትእግስት ጠብቀህ ያሰብከው ነገር ከመጣ በዋላ ህይወትህን ጠፍንገው የያዙህን ነገሮች መፍታት ... ልክ ንስሩ መንቁሩ እንዳደገለት የእግሩን ጥፍሮች በመንቁሩ እየወጋ እንደሚያስወግዳቸው ሁሉ።
√ 5ኛ. ሁሉን ካሳካህ በዋላ ወደ ህልምህ መብረር ... ይህ ማለት ንስሩ የእግሮቹን ጥፍር አስወግዶ እና አሮጌ ክንፎቹን አስወግዶ ከጠበቀ በዋላ አዲስ ክንፍ ፣ አዲስ መንቁር እና አዲስ ጥፍር ካበቀለ በዋላ እንደ አዲስ ጉልበታም ንስር ቀሪ ዘመኑን ይኖራል።
#ሲጠቃለል ...
👉 አንተም ፣ አንቺም ፣ እኔም በዚህ ሁሉ መንገድ አልፈን ከባዱን ጊዜ ካለፍን በዋላ በአዲስ የህይወት መንቁር ፣ የተስፋ ጥፍር እና የስኬት ክንፍ ከፍ ብለን እንበር ዘንድ ..... ኑ ንስር አሞራን እንምሰል።
√ ምንጭ
👇👇
© ከናቲ ቪሎፒያ (ጋዜፀሃዲዛ)
#መረጃው ጠቅሞታል?
#ጠቃሚ መረጃ ከሆነ #ሼር ያድርጉ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 💈💈@bamatub💈💈👈
👉 💈💈@bamatub💈💈👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
2 046
👉አኩኩሉ👈
ሳትባክን ግና በማለዳ
ጀርባህም ሳይጎብጥ አቅምህ ሳይከዳ
ውድ ሃብት የሆነው ጊዜህ ሳይመነምን
የበጋው ወር አልፎ ደመናው ሳይዳምን
ፀሀይ እና ብርሃን ጨረቃ እና ክዋክብት
ፈጥነው ሳይዘጉ የ ፍጥረት መዛግብት
የቀደመው ሲያልፍ አዲሱ ሲመጣ
ውበታት ረግፈው ቢርቱ ሲገረጣ
የወፍጮው ድምፅ ሲላሽ ጀግናው ሲብረከረክ
ቤት የባቂው ሲርድ ህዝብ ሁሉ ሲታከክ
ከሟች ቁጥር ብዛት አልቃሾች ሲዞሩ
በሃዘን ተመቶ ቀየው ከመንደሩ
በእርድና ተከበህ እንዲሁ ስታነጅብ
ክርስቶስን ገፍተህ በሞት ሳትታጀብ
ውሽንፍሩ ሲያልፍ ሳይነካህ እክሉ
ንቃ በል ተነሳ ነግቷል አኩኩሉ!!!!
"በሞገስ ሎታ"
መፅሐፈ መክብብ 12
Join Us
@gitmv
@gitmv
@gitmv
2 046
““ሙሴም ለሕዝቡ፦ አትፍሩ፥ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘላለም አታዩአቸውምና ቁሙ፥ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ።”
— ዘጸአት 14፥13
አትፍሩ፦ ሁሉም ነገር በ እግዚአብሔር ዘንድ ወቅት እና ጊዜ አለው። እግዚአብሔር ከጊዜ ውጭ ቢሆንም በጊዜ ውስጥ የሚሰራ አምላክ ነው።
ለምንድነው ሰዎች የሚፈሩት ብዬ ሳስብ በሁለት ዋና ምክንያቶች እንደሆነ እረዳለሁኝ።
አንደኛው፦ እየሆነ ባለው ጉዳይ ሲሆን ሁለተኛው ሊሆን ስላለው ነገር በማሰብ ነው። በዋናነት ሁለተኛው ብዙ ሰዎችን ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚያናጋ ጉዳይ ነው ነገ ምን ሊሆን ይችላል? ፣እንዴት አልፈዋለው? ፣ ባይሳካስ? ፣ ብሞትስ? በሚሉ እና በመሳሰሉ ጉዳዬች የሚጨነቁ ሰዎች የትዬለሌ ናቸው።
በዚህ ምድር ከ እግዚአብሔር ውጪ ዛሬ ላይ ሆኖ ነገን የቀደመ የለም። እግዚአብሔር ብቻ ነገን እርግጠኛ ነው እርሱ ዘላለምን ኖሮታል። በ እግዚአብሔር የሚተማመን ደግሞ ስለነገ ያቅዳል እንጂ አይጨነቅም። አትፍሩ!! ፍርኃት ዛሬ ላይ ሆናችሁ ከ ነገ እንድትበደሩ ያደርጋል። እጅግ የሚፈሩ ሰዎች በ እግዚአብሔር ተስፋ የማያደርጉ ሲሆኑየፈሩት ያ ነገር ሳያጠፋቸው ፍርሃቱ 90% ቀድሞ ይገላቸዋል። 10% ነው የፈሩት ነገር የመምታት አቅሙ። አሁን የመጣውም የኮሮና ቫይረስ፦ ሳይገድል እኛ በስጋት ከገዳዩ ቀድመን እንዳንሞት እላለሁኝ።
<<በእርግጥ እግዚአብሔር ሳያውቅ የሚሆን ነገር ስለሌለ በ እግዚአብሔር ተስፋ አይቆረጥበትም። አስፈላጊውን ጥንቃቄ እያደረግን እንፀልይ እላለሁኝ። ስላነበባችሁት አመሰግናለሁ!!
።።።ሞገስ ሎታ።።።
@bamatub
@bamatub
@bamatub
@bamatub
2 046
ትንሳዔ የ ክርስትና እምነት መሰረት የተጣለበት፤ የደም ውቅር ትክል ድንጋይ የፀናበት፤ ከ አልፋ እስከ ኦሜጋ ከቅድመ አለም እስከ ዘልአለም፦ ለ ሰው ልጆች ሁሉ እንደ ንጋት ወጋገን ብሩህ ተስፋ የፈነጠቀበት፣ ለ አዲስ ጅማሬ ብሉይ ያረጀበት፣ ድንቅ ክስተት ነው።
ትንሳኤ በ አራት ሆሄ የተዋቀረ የ እግዚአብሔር የዘላለም አጀንዳ ነው።
በ ትንሳኤ ሃዘን በደስታ ፍዳ በ ፌሽታ ልቅሶ በ እልልታ ሲቀየር በቀራኒዮ ያልተወራረደ እዳ ያልታደሠ ጓዳ የለም። እግዚአብሔር ዘላለምን ፈጥሮ በ ዘላለም ውስጥ ትንሳኤን አቅዶ በ ትንሳዔ ውስጥ ዘላለምን ቋጭቶ ዘላለምን ጀመረው፨ ትንሳዔ የ አሁን ሳይሆን የቀድሞ የ ዘንድሮ ሳይሆን የድሮ እንጂ በ ሃሳብ ልእልና የመጣ የሰው ጉዳይ አይደለም፨ ይህ ማለት ትንሳዔ ከ ቅድመ አለም በፊት ካለ ከ ዘላለም በሁኋላ ይኖራል ዘላለም በሁኋላ ካለው ማለቴ ነው
ከ ምንም በላይ ደግሞ ሞት ራሱ የሞተበት እና ሃጥያት የተቀጣበት ልዩ ጉዳይ ነው። ስለ ትንሳዔ ያልኩትን ከያዛችሁ ያላልኩትን በሉ!! እርሱ ሞታችንን ከሞተ እኛ ህይወቱን እንኑር!! መልካም የትንሳዔ በአል
*ሞገስ ሎታ*****
2 046
““ሙሴም ለሕዝቡ፦ አትፍሩ፥ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘላለም አታዩአቸውምና ቁሙ፥ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ።”
— ዘጸአት 14፥13
አትፍሩ፦ ሁሉም ነገር በ እግዚአብሔር ዘንድ ወቅት እና ጊዜ አለው። እግዚአብሔር ከጊዜ ውጭ ቢሆንም በጊዜ ውስጥ የሚሰራ አምላክ ነው።
ለምንድነው ሰዎች የሚፈሩት ብዬ ሳስብ በሁለት ዋና ምክንያቶች እንደሆነ እረዳለሁኝ።
አንደኛው፦ እየሆነ ባለው ጉዳይ ሲሆን ሁለተኛው ሊሆን ስላለው ነገር በማሰብ ነው። በዋናነት ሁለተኛው ብዙ ሰዎችን ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚያናጋ ጉዳይ ነው ነገ ምን ሊሆን ይችላል? ፣እንዴት አልፈዋለው? ፣ ባይሳካስ? ፣ ብሞትስ? በሚሉ እና በመሳሰሉ ጉዳዬች የሚጨነቁ ሰዎች የትዬለሌ ናቸው።
በዚህ ምድር ከ እግዚአብሔር ውጪ ዛሬ ላይ ሆኖ ነገን የቀደመ የለም። እግዚአብሔር ብቻ ነገን እርግጠኛ ነው እርሱ ዘላለምን ኖሮታል። በ እግዚአብሔር የሚተማመን ደግሞ ስለነገ ያቅዳል እንጂ አይጨነቅም። አትፍሩ!! ፍርኃት ዛሬ ላይ ሆናችሁ ከ ነገ እንድትበደሩ ያደርጋል። እጅግ የሚፈሩ ሰዎች በ እግዚአብሔር ተስፋ የማያደርጉ ሲሆኑየፈሩት ያ ነገር ሳያጠፋቸው ፍርሃቱ 90% ቀድሞ ይገላቸዋል። 10% ነው የፈሩት ነገር የመምታት አቅሙ። አሁን የመጣውም የኮሮና ቫይረስ፦ ሳይገድል እኛ በስጋት ከገዳዩ ቀድመን እንዳንሞት እላለሁኝ።
<<በእርግጥ እግዚአብሔር ሳያውቅ የሚሆን ነገር ስለሌለ በ እግዚአብሔር ተስፋ አይቆረጥበትም። አስፈላጊውን ጥንቃቄ እያደረግን እንፀልይ እላለሁኝ። ስላነበባችሁት አመሰግናለሁ!!
።።።ሞገስ ሎታ።።።
2 046
ተወዳዳሪ - N009
💐Philipos Solomon
ልቤ ይፈልግሀል
ፀሀይ ሳትወጣ ማለዳ ሳይመጣ
በሌሊት ተነስቶ የታለህ ይልሀል ፤
ቀኑ መሽቶ ሲሄድ ጨለማው ሲመጣ
እንዳተወኝ ያዘኝ ያንተው ነኝ ይልሀል ፤
ይሄ ምስኪን ልቤ.....
ከሴት ፍቅር ይልቅ ባንተ ፍቅር ፈዙዋል
ካላየህ ካልሰማህ መች በሰላም ያርፋል::
በዚች ክፉ አለም ተንኮል በሞላባት
ሚስም አስመስሎ ነካሽ በበዛባት
እውነተኛ አፍቃሪ ከምድር በጠፋበት ፤ በዚ ክፉ ግዜ
ልቤን አንተን ይልሀል ፡ ከሴት ፍቅር ይልቅ ባንተ ፍቅር ፈዟል፡፡
እግርህ ስር መውደቅ ፡ በፍቅርህ ውስጥ መስመጥ
እንባን እያነቡ ፡ እግሮችህን ማበስ ስራው አድርጎታል
ሚሄድበት የለው ፡ ካንተ ተለይቶ ማን ጋር የሸሸጋል፡፡
አንተ የኔ ፍቅረ የናርዶስ ሽቶ ነህ
የኔ ጽጌረዳ ውበቴ የምልህ
ቃሎቼ ያልገለጡህ ፍቅርህ የማረካኝ
ከናት አባት በላይ የምር የምትወደኝ
አንተ ኮ ፍቅሬ ነህ ክብሬ ሽልማቴ
ማላፍርህ ወዳጅ መመኪያ ጋሻዬ፡፡
አላልቅልህ አለኝ ስላንተ ባወራ
አልገጥምልህ አለኝ ፡ ግጥሙ ቤት አይመታ
አንተን የሚገልፅህ ውብ ቃል ከየት ይምጣ..?
እንዲያው ዝም ከማለት ፡ ይሻለኛል ብዬ.....
እዘባርቃለሁ....
እሞነጭራለው.....
እቺ ትንሽ ልቤ በፍቅርህ ተማረካ
ሳትፈነዳ በፊት ካካሌ አምልጣ
እንደው ከቀለላታ ከረጋች ብዬ ፤ ...እሞነጭራለሁ......
ግጥሙ ቤት ባይመታም ለሚመታው ልቤ ፈውስ አገኛለሁ
በማይገልጡ ቃላት ፡
ማይገለጥ ፍቅር ላስረዳ እጥራለሁ
ብቻ ተረዳልኝ ፡
ከምንም አብልጬ እፈልግሀለሁ፡፡
ከሌሎች አወዳድረው ይምረጡ
QENEA POEM COMPETITION
💐💐💐🔹🔹🔹💐💐💐
@Enzemer_Tube
@Enzemer_Tube
@Enzemer_Tube
