cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

K.k.s.c Wereda 10 Selam ber gudgnt

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
821
Suscriptores
Sin datos24 horas
+17 días
+730 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

በወረዳችን የፈተና ጣቢያ የተደለደላችሁ ት/ቤቶች በተመደባችሁበት ት/ቤት በወረደው ፕሮግራም መሰረት ተከታተሉ።
Mostrar todo...
ማስታወቂያ ቀን 26/09/2016 ዓ.ም የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የ2016 ዓ/ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ያካሄዳል።በመሆኑም አሰፈታኝ የትምህርት ቤቶች ከላይ የተያያዘውን መፈተኛ ጣቢያ ለተፈታኞች እንድታሳውቁ እና ሰኔ 03/2016 ዓ.ም ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች በመፈተኛ ጣቢያቸው በመገኘት ኦሬንቴሽን እንድወስዱ መልዕክቱ በትምህርት ቤቱ አማካኝነት እንዲተላለፍላቸው በጥብቅ እናሳስባለን። #ማሳሰቢያ:-1)አድሚሽን ካርድ ያልሰጣችሁ ትምህርት ቤቶች በአስቸኳይ እንድትሰጡ። 2)ተማሪዎች ለኦሬንቴሽን ወደመፈተኛ ጣቢያ ሲመጡ የትምህርት ቤታቸውን መታወቂያ እና አድሚሽን ካርድ መያዝ ይጠበቅባቸዋል። #የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት
Mostrar todo...
የ6ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና መልስ
Mostrar todo...
6.rar0.69 KB
8.rar0.54 KB
Repost from N/a
Photo unavailableShow in Telegram
Repost from N/a
አስቸኳይ ማስታወቂያ ቀን 19/9/2016 ዓ.ም ለሁሉም የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ነገ ግንቦት 20/2016 ዓ.ም ትምህርት የማይኖር መሆኑን እናሳስባለን።
     ኮ/ ቀ/ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት
Mostrar todo...
ሥነ-ምግባር ማለት የሁለት ቃላት ጥምር ሲሆን ትርጉሙም “ስነ” የሚለው ቃል “ሠነየ” ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆን 1) ያማረ፣ 2) መልካም የሆነ፣ 3) ደስ የሚያሰኝ፣ 4) የበለጠ፣ የተሻለ ማለት ነው፡፡ “ምግባር” የሚለው ደግሞ “ገብረ” ካለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም 1) ሥራ፣ 2) ፈጠራ፣ 3) ድርጊት፣ 4) ክንውን ማለት ነው፡፡ በአጠቃላይ ሥነ ምግባር ስንል መልካም፣ የተገባ፣ የተፈቀደ፣ የተወደደ፣ ያማረ ሥራ ወይም ድርጊት ማለት ነው፡፡ የስነ-ምግባር መሰረቶች 1) ቤተሰብ፡ 2) ከባባዊ ሁኔታዎች 3) አቻዎች 4) ልማድ፡- 5) ግብረገብ /እሴቶች፡- የሥንምግባር ፋይዳዎች /ጠቀመታዎች 1) 1.አዎንታዊ የድርጅት ባህል ይገነባል 2) የተገልጋይን አመኔታና ዘላቂነትን ያረጋግጣል 3) ሰራተኞች ቁርጠኛ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ 4) የህግ ጥሰቶችንና ቅጣቶችን ይቀንሳል፣ 5) የተገልጋይ እርካታን ይጨምራል 6) ከባለድርሻ አካላት ጋር መልካም ግንኙነት ለመፍጠር ያስችላል 7) አፈጻጸምን ለማሳደግ ያግዛል፣ የስነ-ምግባር መገለጫዎች ስነ-ምግባር 1) ታማኝነት 2) አክባሪነት 3) ኃላፊነት 4) ፍትሃዊነት በጣም አስፈላጊ የሙያ ባህሪያት መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚባሉት፡- 1) ብቃት/ Competence 2) እውቀት/ Knowledge 3) ህሊና/Conscientiousness 4) ታማኝነት/ Integrity 5) አክብሮት/Respect 6) ስሜታዊ ብልህነት/ Emotional Intelligence 7) ተገቢነት/ Appropriateness/ እና 8) በራስ መተማመን/ Confidence ናቸው፡፡ ሙያዊነትን/ባለሙያነትን ማዳበር የምንችልባቸው መንገዶች  ውጤታማ መሆን 1) የባለሙያ ምስል መፍጠር 2) የላቀ አገልግሎት መስጠት 3) ችግር ፈቺ መሆን 4) ታጋሽ መሆን 5) ውጤታማ ግንኙነት ማድረግ 6) ግንኙነቶችን መገንባት ቁልፍ የሙያ ስነ-ምግባር የሚባሉት 1) ለህብረተሰቡ ደህንነት፣ ጤንነት እና በጎ አድራጎት መትጋት 2) በሙያው (ባለው አቅም) ማገልገል 3) ማንኛውንም ነገር ትክክለኛውን እና እውነት ተከትሎ የስራ ስነ-ምግባር 1) በሥራ ቦታ በጊዜ መገኘት 2) ከሥራ አለመቅረት 3) የሥራ ስነ-ስርዓት 4) የሥራ መሳሪያዎችን በጥንቃቄ መያዝ 5) ከሥራ ባልደረቦች ጋር ተባብሮ/ተመካክሮ መሥራት/ 6) እምነት የሚጣልብን መሆን 7) ትሁት መሆን 8) የሥራ ተነሳሽነት 9) ሥራ ወዳድነት 10) አርዓያ መሆን 11) የተገልጋይ አመኔታ እና ዘላቂነት ማረጋገጥ 12) የህግ ጥሰቶች እና ቅጣቶች መቀነስ 13) የተገልጋይ እርካታ መጨመር 14) ከባለ ድርሻ አካላት ጋር መልካም ግንኙነት መፍጠር 15) ወጭን መቆጣጠር 16) አፈጻጸምን ማሳደግ በሥራ ላይ የሚታዩ የስነ-ምግባር ጉድለቶች 1) የጥቅም ግጭት 2) አድሎ 3) የሀብት ብክነት 4) ማጭበርበር 5) መረጃን ማዛባት 6) መረጃን በትክክል አለመያዝ 7) በጥቅማ ጥቅም መደለል 8) ጉቦ/ማቀበል/መደለል/ 9) አደራ መብላት 1) ሀሜት/የአሉባልታ ወሬ/ 2) ውሳኔዎችን ከራስ ጥቅም አንጻር ብቻ መወሰን 3) አለመግባባት/አለመናበብ 4) ዝቅተኛ የደንበኛ አገልግሎት 5) ውሸት 6) ያለሙያ ሥራ መስራት 7) ስንፍና 8) ተስፋ ቢስነት ለስነ-ምግባር ጉድለት እንደ ምክንያት የሚቀርቡ ሰበቦች 1) ሁሉም ሰው እንደዚያ ነው/እኔ ከሰው በምን እለያለሁ 2) የእኔ ስራ አይደለም 3) ማንም ሰው ሊያውቅብኝ አይችልም 4) የሚከፈለኝ በቂ አይደለም 5) ይህ የእኔ ኃላፊነት አይደለም 6) በመመሪያዎች እና ደንቦች ማመካኘት የስራ ስነ-ምግባርን ለማጠናከር የሚረዱ መንገዶች 1) ሁሉንም ሰራተኛ በእኩል ማየት 2) እውቅና መስጠት 3) ተገቢውን እርምጃ መውሰድ 4) መግባባት 5) ግልጸኝነት 6) ስልጠናዎችን ማዘጋጀት 7) የትግበራ እቅድ ማውጣት 8) ገምቢ ግብረ መልስ መስጠት የሙያዊ ስነምግባር ሞዴሎች 1) ራስን የማስተዳደር ሞዴል 2) የሶሻሊስት ሞዴል 3) የተግባርና ኃላፊነት ሞዴል የመንግስት ሰራተኞች ሊከተሏቸው የሚገቡ የሥነ ምግባር መርሆዎች 1) ቅንነት/የተሟላ ስብዕና/Integrity 2) ታማኝነት (loyality) 3) ግልጽነት (Transparency 4) ምስጢር መጠበቅ (Confidentiality 5) ሐቀኝነት (Honesty) 6) የሕዝብ ጥቅም ማስቀደም (Serving the Public Interest) 7) ህጋዊ በሆነ ሥልጣን መገልገል (Exercising Legitimate Authority) 8) አድልዎ አለመፈፀም (Impartiality) 9) አድልዎ አለመፈፀም (Impartiality) 1) ህግን ማክበር (Respecting the Law) 2) ለሕዝብ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት (Responsiveness) 3) አርአያ መሆን (Exercising Leadership)
Mostrar todo...
ለአገልግሎት ተጠቃሚዎች በግልና በመንግስት ትምህርት ተቋማት እና ምዘና ጣቢያዎች ተገልጋዮች ማንኛውም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለው ብልሹ እና ሌብነት ማለት ፡- 1) በCOC /ሙያ ብቃት ምዘና በተመለከተ 2) በእውቅና ፈቃድ እና እድሳት/አዲስ እውቅና፤እድሳት/ በተመለከተ/ 3) በኢንስፔክሽን ደረጃ ፍረጃ በተመለከተ የትምህርትስልጠናጥራትቁጥጥርባለሥልጣን ኮልፌ ቅ/ጽ/ቤት የሥነ-ምግባርና ፀረሙስና ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁ.22 በአካል በመምጣት ወይንም 1) በነፃ ስልከ ቁ.9302 2) በጥቆማ ሳጥን በ3ኛ ፎቅ በቢሮ ስልክ 01113836135 የሥራ ክፍሉን ጠቅሶ ማስገባት ይችላሉ፡፡
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች!✅ ======================== ⭐️ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው:: ⭐️ከፈተና በፊት ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምንችለበት መንገድ:- ------------------------------------------------ ✅ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት። ✅ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ ✅ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ።  ✅ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን። ✅ ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል። ✅ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።  ቻናሉን ለወዳጅዎ 🌟Share ያድርጉ ቻናላችን ይህ ነው
Mostrar todo...