cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

BOOKS COLLECTION(ቤተ-መጽሀፍት)

👉 በቻናላችን የሚያገኟቸው ነገሮች፦ 📒 የመፅሐፍ ጥቆማ 📗 ልብ አንጠልጣይ ትረካዎች 📘 እንዲሁም አዝናኝ እና ቁም ነገሮችን ከዚህ ቻናል ያገኛሉ! ➠ መጽሀፍት ብቻ ከፈለጉ: @book1912

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
3 908
Suscriptores
+224 horas
-57 días
-3030 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

https://t.me/tapswap_mirror_2_bot?start=r_601655565 🎁 +2.5k Shares as a first-time gift የ Notcoin እድል ላመለጣቹ በTapSwap ተጠቀሙ!!
Mostrar todo...
ተነስቷል !!❤️ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም በዓል!!
Mostrar todo...
4
Photo unavailableShow in Telegram
📜የሰው ልጅ ሕልውና ምድር ላይ ሀ ብሎ ሲጀምር ጊዜ አሀዱ ብሎ መቁጠር እንደጀመረ ይገመታል። ምክንያቱም ሰው ከመፈጠሩ በፊትና ከሞተ በኋላ ስላለው አያውቅም፣ስለዚህ ህልውና ሲጀምር ጊዜ ጀመረ ፣ጊዜ ማለት በእጅ ውስጥ ያለ ነው። ትናንት አልፏል። ነገም ደግሞ አያስተማምንም። ስለዚህ ጊዜ ዛሬ ነው። በተለይ ደግሞ አሁን ። 📜ልማድ ብቻ ይዘን የትም ልንደርስ አንችልም፣ ባዶ ኩራት ይዘን እንቀራለን፣ ህልውናን መገመት ያለብን በስራ እንጂ በእድሜ: በሀሳብ እንጂ በትንፋሽ፡ በስሜት እንጅ በከንቱ የሚባክኑ ደቂቃዎች አይደለም ፣ ጊዜን የምናሰላው በልብ ትርታ መሆን አለበት።በስራ የማይገልጡትን ነገር በአፍ ብቻ መናገር ምላስን ማባለግ ነው።የባለገች ምላስ ህሊና ላይ ታምፃለች። እምነትና ድርጊት ከተለያዩ ምሰሶው በምስጥ እንደተበላ ቤት መዛግ ከዚያም መፍረስ ይመጣል ወና ቤት መሆን ነው። 📜ከተማራችሁት ወጣቶች የሚጠበቀው'ኮ ያገሪቷን ችግር በጥሞና አስተውላችሁ ዘላቂ መፍትሄ መሻት ነው፣ ለግልቢያውማ ማሀይምስ ብልጭ ካለበት ይጋልብ የለም እንዴ! ወደፊት ልንራመድ የምንችለው በወሬ በፍልስፍና በስራ በማይገለጥ የመፅሀፍ እውቀት አይደለም። ስርየታችን ስራ ነው፣ ስልጣን ይዞ በመኮፈስ ስልጣንን እንደ እውቀት በመቁጠር፣ ስልጣንን እንደ ሃላፊነት ሳይሆን እንደ መብት በማየት አይደለም በስራ እንደገና መወለድ ያስፈልጋል። 📜የኔ ጥሪ ስራ ነው። መናገር አላውቅም። ያ የጥሪ ሰዓት ሲደርስ በቆራጥነት መነሳቱ ሀጢያት አይደለም። ከማፍረስ መገንባት ፤ ከብዙ ምልልስ ትንሽ ስራን ፤ ከበቀል ይቅርታን ፤ከጥላቻ ፍቅርን ፤ ከማይምነት እውቀትን እመርጣለው። ✍ በዓሉ ግርማ @bete1912 @bete1912
Mostrar todo...
👍 8 2
💔 ወርቃማው ጥገና! 💔በጃፓን ሃገር ውስጥ ለብዙ መቶ አመታት የከረመ ልምምድ አለ፡፡ ጃፓኖች አንድ ከሸክላ የተሰራ እቃ ሲሰበርባቸው እንደገና የመጠገኑን ስራ “ኪንሱጊ” (Kintsugi) ብለው ይጠሩታል፡፡ 💔ይህ ቃል የሁለት የጃፓንኛ ቃላት ጥምረት ነው፡ “ኪን” (Kin) ማለት ወርቃማ ማለት ሲሆን፣ “ሱጊ”(Tsugi) ማለት ደግሞ ጥገና ማለት ነው፡፡ የእነዚህ ሁለት ቃላት ጥምረት የሚሰጣቸው ይህ “ኪንሱጊ” (Kintsugi) የተሰኘ አንድ ቃል ትርጉም አንድ ነገር ከተሰበረ በኋላ እንደገና በወርቅ መጠገንን የሚያመለክት ነው - ወርቃማ ጥገና! 💔ከዚህ ልምምዳቸው የተነሳ አንድ የተሰበረ የሸክላ እቃ እንደገና ሲጠገን ይህ የጥገና ሂደቱ በእቃው ታሪክ ውስጥ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ እቃው በመሰበሩ የተነሳ እንደገና ሲጠገን በሶስት መልኩ የላቀ ሆኖ ይወጣል፡- 1) ጥንካሬው ይጨምራል 2) ዋጋው ይጨምራል፣ 3) ውበቱ ይጨምራል፡፡ 💔በሕይወታችሁ ልባችሁን ሰብሮና ስሜታችሁን አቁስሎ የነበረ ያለፈ ልምምድ ካለ፣ አሁንም ተመሳሳይ ልምምድ ውስጥ በማለፍ ላይ ካላችሁና ወደፊትም በሚሰብር ልምምድ ውስጥ ስታልፉ ይህንን የጃፓኖችን የጥገና ሂደት አትዘንጉ፡፡ በሁኔታው ተስፋ በመቁረጥና ተሰብራችሁ ለመቅረት ራሳችሁን ካልጣላችሁ በስተቀር እንደገና ትጠገናላችሁ፡፡ ከተጠገናችሁ በኋላ ግን ከበፊቱ ይልቅ ጠንካራ ሰዎች፣ ዋጋችሁ የከበረና ከበፊቱ ይልቅ እጅግ ውብ ሆናችሁ ነው የምትወጡት፡፡ ❤️ሆኖም፣ ጥገና ጊዜን እንደሚፈልግ አትዘንጉ፡፡ ጥገና ያለፈውን ረስቶ ፈጣሪን በመታመን ወደፊት የመገስገስን ቆራጥነትም እንደሚፈልግ አትርሱ፡፡   Beauty can be found in imperfection.              ✍ ዶ/ር እዮብ ማሞ @bete1912 @bete1912        
Mostrar todo...
4
🪽በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን የተሳፈረ ሰውዬ የበረራ አስተናጋጇ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት የአውሮፕላኑ መጸዳጃ ቤት ውስጥ መጠቀም ይጀምራል። ታዲያ በመሐል አንዲት ቀይ ማብሪያና ማጥፊያ የምትመስል ነገር ያይና ነካ ያደርጋታል። በዚህ ቅፅበት አውሮፕላኑ በሐይል መንገጫገጭና ወደ ጎን ማጋደል ይጀመራል። ሰውዬውም ደንግጦ ወይኔ ሳላውቅ የማይነካ ነገር ነክቼ ሕዝብ ጨረስኩኝ ብሎ በነካት ቀይ ነገር ይጸጸታል። ከጥቂት ቆይታ በኃላ ግን መንገጫገጩ ይቆምና ጨርሶ ከመጸዳጃ ቤት ይወጣል። ሁሉም ሰው "አንተ የማትረባ! ጨርሰኸን ነበር እኮ!" ብሎ ይጮህብኛል ብሎ ቢጠብቅም ዞር ብሎ ያየው ሰው እንኳን አልነበረም።   🪽መቀመጫው ላይ እንደደረሰም አጠገቡ የተቀመጠውን ሰው ቀስ እና ስቅቅ ብሎ "ይቅርታ የማይነካ ነገር ነክቼ ጨርሻቹ ነበር አይደል?" ይለዋል።  ሰውዬውም "አረ በፍጹም እንደዛ እንዳታስብ! ይህን ያሕል ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮች እኮ መፀዳጃ ቤት ውስጥ አይደረጉም ...ካፒቴኑ ያለበት ክፍል ውስጥ ነው ያሉት። በአጋጣሚ ትንሽ የአየሩ ሁኔታ አስቸጋሪ ስለሆነ ነው አውሮፕላንኑ የተንገጫገጨው" ይለዋል።  🪽ብዙ ጊዜ ሰዎች እንደዚህ ያስባሉ። የሆነች ነገር ነክተው ሕይወትህን የሚያንገጫግጩ እና መጨረሻህን የሚወስኑ ይመስላቸዋል። የረሱት ነገር ቢኖር ይህን ያክል ጥንቃቄ የሚፈልገው ነገር እነሱ አጠገብ ሳይሆን የሕይወትህ ካፒቴን ጋር እንዳለ ነው። እንደዛማ ባይሆን ኖሮ ቀይዋን ነገር እየጠቀጠቁ ሕይወታችንን መንገጫገጭ ብቻ ያደርጉት ነበር። ምስጋና ለካፒቴኑ ይሁንና እንደዚሕ አይነት ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮችን በሱ እጅ ብቻ እንዲገኙ አድርጓቸዋል። 🪽ዋና ነገሬ ያለው እኔና ፈጣሪ ጋር ነው በማለት በእረፍት እንኑር፣ ሰማያዊ ጥበብ በጆሮ አይሰማም። እምነት በዓይን አይታይም። ሁሉንም ክብርና ምስጋና የፈጠረን ይውሰድ። 📖አርምሞ @bete1912 @bete1912
Mostrar todo...
9👍 3
🫧አንዳንድ ወቅት አለ ስሜት የሚነዳ ፤ የሂወት ድግግሞሽ እንደጦስ ዶሮ የሚያዳክር፤  እጅ እና እግር እንደተጠፈረ  አቅም አልባነት የሚበላ ፤ አካባቢ ላይ ምን እንደተካሄደ የማይገባህ ። 🫧አንዳንድ ወቅት አለ ማጤን ማመዛዘን ያንተ የማይሆንበት ፤ የመረጥከው ምርጫ የሚያድሞከሙክኽ።  መባተልን የምትመስልበት፤   የመጣህበት መንገድ አሳስቶህ የማትመለስበት ። 🫧አንዳንድ ወቅት አለ ምርጫ የሚያባትልህ ፤   የመፍዘዝ ስሜት የሚሰማህ ፤   ሰው ሁሉ  የጠላኽ የሚመስልህ ፤  ኃላ  የመቅረት ስሜት የሚንጥህ ። 🫧አንዳንድ ወቅት አለ  ማድረግ እንደሌለብህ እያወክ  የምታከናወነው ፤ የስሜትህ ባርያ የምትሆንበት ፤ መገኘት እንደሌለብህ እያወክህ የምትገኝበት  ። 🫧እንዳንድ እለት አለ ብልጥ ነኝ ባዮች የሚበልጡ ፤ አራዳ ነኝ ባዮች የሚያሞኝህ፤ በዝባዦች የሚበዘብዙህ፤ ባለጡንቻዎች አቅማቸውን የሚለኩብህ እንዲም ሁሉ ሆኖ ሳለ 🫧በግዜ እናምናለን ። ግዜ ሃያል ነው ። ሁሉም ይስተካከላል፣ መስመር መስመር ይይዛል  ።አይነጋም ያልነው ጨለማ ስንቴ ነግቷል።                 ✍አድሃኖም ምትኩ መልካም ሰንበት❤️ @bete1912 @bete1912      
Mostrar todo...
5
💡ከዜሮ መጀመር ትችላለህ 📍ያለንን ነገር ሁሉ ብናጣ ፡ የተመካንባቸው ሰዎች ቢርቁን ፡ በሽታ ቢያሰቃየን ፡ የባንክ አካወንታችን ባዶ ቢሆን ፡ ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች ቢከሰቱብን ፡ ሁሌ ከዜሮ መጀመር ይቻላል። እድሜያችን ቢገፋ እንኳን በልጅነታችን የተመኘነውን ማንነት በየትኛውም ጊዜ መገንባት እንችላለን ። ከኛ የሚጠበቀው ለመለወጥ ያለን ቁርጠኝነታችን ፡ ፅናታችን ፡ እምነታችንና ትዕግስታችን ነው። ማትኮር ያለብን ችግሩ ላይ ሳይሆን ወይም ስለችግሩ ማልጎምጎም ሳይሆን ችግሩን ለመፍታት የሚረዱንን መሰረታዊ ጽንስ ሀሳቦች ቁርጠኝነት ፡ ጽናትና ፡ ትዕግስት ላይ ነው። 💡 የሕይዎትህ መለወጫ መሪ ያለው በራስህ እጅ ላይ ነው። ሌሎችንና ሌላ ጊዜን አትጠብቅ። ጊዜው አልፏል ብለህም አትቁም ፡ ያንተ ጊዜ አሁን ነው። ጉዳይህ ያለቀና ያበቃለት ቢመስልም አንተ ከጠነከርክ እንዲሁም ከልብህ ፡ እኔ አሁንም ተስፋ አለኝ ብለህ ከባዶ የመነሳቱ ድፍረቱ ካለህ ያኔ አንተ አንፀባራቂ ብርሀንን ታያለህ። ራስህንም ድሮ ከነበርክበት ባዶነት አውጥተህ እንደገና ሕይዎትን የመኖር ፅንሱን ውስጥህ ትፀንሳለህ። ያኔ አንተ ተቆርጠህ ከተጣልክበት ትቢያ እንደገና አገግመህና ፡ አቆጥቁጠህ ትታያለህ። ልምላሜህም ከበፊቱ የበለጠ ይሆናል። ቅርንጫፎችህ ፡ ተቆረጡ እንጂ ዋናውን የሕይዎት ምስጢር የያዘችው አንተን ከአፈሩና ፡ ከውሃው የምታገናኝህ ስራህ አልተቋረጠችምና እንደገና ትለመልማለህ። እንደገና እራስህን በእድገት ምናብ ከዋጀኽው በድጋሚ ታብባለህ። 📍በድጋሚ ቀንበጥ ፡ ቀንበጥ የሆኑ የሚያስጎመጁ ፡ አረንጓዴ ቅጠሎችንና ፡ ቅርንጫፎችን ፡ ታቆጠቁጣለህ። ግመል በበረሓ ስትጓዝ በረሓው ላይ ውሃ እንደሌሌ ታውቃለች። ግን ወደ በረሓው እንድትገባና ፡ እንድትጓዝ ስናደርጋት ፡ ወደ ኋላ አታፈገፍግም ወይም አትፈራም። ምክንያቱም ፡ የሻኛው ጮማ ውስጥ በቂ የሆነ ምግብና ፡ ውሃ እንዳለ እርግጠኛ ስለሆነች እሷ የምትዘጋጀው ከበረሓው ፡ ከመግባቷ በፊት ውስጧ ምግብ በማጠራቀም ነው። አንተም እንደ ግመሏ ውስጥህ ላይ አትኩር። ሌሎችን የበረሓው ግለት ፡ የበረሓው ንዳድ ፡ የበረሓው አሸዋና ፡ የበረሓው መጨረሻ መራቅ ተስፋ ቢስ ሲያደርጋቸው ፡ አንተ ግን ለድል አነሳሳቸው ፡ ውስጣቸው ያለውን የአሸናፊነት  ጮማ ፡ የተስፋ ጮማ ፡ የፍቅር ጮማ ሻኛ እንዳለ ንገራቸው። አንተ ከፊት ሆነህ ባለህ የዕውቀት ፡ የፅናት ፡ የትዕግስት ፡ ብረሀንህ ጉዟቸውን አቅልጥላቸው። 💡አንተ ራስህን ከምንምና ፡ ከባዶ አንስቶ ለትልቅ ደረጃ ፡ የሚያበቃ አቅም በውስጥህ አለ። አንድ ልታውቀው የሚገባህ ትልቅ ቁምነገር ፡ ዜሮ ፡ የቁጥሮች መጨረሻ ሳይሆን ፡ የቁጥሮች መጀመሪያ መሆኑን ነው። ያለህ ነገር ሁሉ ዜሮ የሆነ ከመሰለህ ፡ እንግዲያው አንተ ደስ ሊልህ ይገባል። ምክንያቱም ፡ በህይዎትህ ያለህ ደስታ ሁሉ ፡ ያለህ ሀብት ሁሉ ፡ ያለህ ዝና ሁሉ ፡ ያለብህ ገንዘብ ሁሉ ፡ ያለህ ተቀባይነት ሁሉ ፡ እንደገና ከዜሮ ፡ መጨረሻ ፡ ወደሌለው ቁጥር "ሀ" ብሎ ሊንደረደር ነውና !!!         📓የኔ ስጦታ ✍ብሩክ የሺጥላ @bete1912 @bete1912
Mostrar todo...
7👍 1
🐶 ቅብጥብጡ ውሻ 🐶የት እንዳነበብኳት ባላስታውስም ከረጅም ጊዜ በፊት ያነበብኳት አንዲት አጭር ታሪክ ትዝ አለችኝ፡፡ አስተምራኝ አልፋለች፣ ዛሬም ባሰብኳት ቁጥር ታስተምረኛለች፡፡ የአንድ ሰውና የውሻው አጭር ታሪክ ነው፡፡ 🐶በገጠራማው አካባቢ የሚኖር አንድ ሰው ከቤቱ ወጥቶ ወደ 30 ደቂቃ የሚፈጅ የእግር ጉዞ ካደረገ በኋላ መድረስ ወደሚገባው የወዳጁ ቤት ደረሰ፡፡ ከእሱ ጋር እሱ በሄደበት ሁሉ የሚከተለው በጣም የሚወደው ውሻው እንደተለመደው ተከትሎት መጥቷል፡፡ ሰውየው ወዳጁ ቤት ሲደርስ ከወዳጁ ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ወዳጁ፣ “ያ ሁልጊዜ በሄድክበት ሁሉ የሚከተልህ ውሻህስ የት አለ?” ብሎ ገና ከመጠየቁ ውሻው እያለከለከና በውኃ ጥም ለሃጩን እያዝረከረከ ከባለቤቱ ጀርባ ከተፍ አለ፡፡ የዚህ ሰው ወዳጅ የሰውየውን አለመድከም ከውሻው ማለክለክ ጋር አነጻጸረና፣ “ውሻህን ምን አድርገኸው ነው እንደዚህ የደከመው፡፡ አንተ ምንም የድካ ስሜት አይታይብህም፣ እሱ ግን በጣም ደክሟል” አለው፣ ልክ በውሻው ላይ እንደጨከነበትና ችላ እንዳለው አይነት ስሜት በሚሰጥ ሁኔታ፡፡ 🐶የውሻውም ባለቤት ይህ የለመደውና በሄደበት ሁሉ ሰዎች የሚጠይቁት ጥያቄ በመሆኑ ብዙም ሳይገረም በውስጡ አቀባብሎ ያለውን መልስ መለሰለት፣ “የሚገርምህ ነገር ሁለታችን ከቤት ተነስተን እኩል መንገድ ነው የመጣነው፡፡ በእኔና በእሱ መካከል ያለው ልዩነት እኔ ቀጥ ብዬና ተረጋግቼ ነው የመጣሁት፣ እሱ ግን እንዴ ወደ ግራ፣ አንዴ ደግሞ ወደ ቀኝ ሲባዝን፤ አንዴ አንድን ነገር ሲያባርር፣ እንዴ ደግሞ ቆም ብሎ መሬቱን እያሸተተ አንድን ነገር አገኛለሁ ብሎ ሲቆፍ፣ እኔ ስርቅበት ደግሞ ለመድረስ ሲሮጥ . . . ሁል ጊዜ እሱን የሚያደክመው ይህ ቅብጥብጥ ባህሪው ነው”፡፡ 🐶ለካ ያለመጠን የሚያደክመን መንገዳችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ የሚያዝለን ስራችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ በቀኑ መጨረሻ ላይ ዝልፍልፍ የሚያደርገን የቀኑ ዋና ዓላማችን አይደለም፣ ለካ በኑሮ ድክም ያልነው በተለመደው የኑሮ ሂደት አይደለም፡፡ እኛን የሚያደክመንና ዝለት ውስጥ የሚከተን በመንገዳችን ላይ በማያገባን ነገር እየገባን ወዲህና ወዲያ የምንለው ነገር ነው፡፡ ይህ እውነት የገባኝ ቀን . . . 🐶ስለማያገባኝ ሰው ማውራት አቆምኩኝ፣ በማያገባኝ ስፍራ መገኘት ተውኩኝ፣ ምንም ለውጥ በማያመጣ ነገር ላይ መከራከርን ጣልኩት፣ ምንም ተጽእኖ ከማላመጣለት ሰው ጋር መነታረክን ተወት አደረኩኝ፣ ድምዳሜ ላይ ስደርስ ምንም ፋይዳ የማያመጣልኝን ጉዳይ ማሰላሰል እርግፍ አደረኩኝ . . . በአጭሩ የማደርገው ነገር ሁሉ ከዋናው የህይወቴ ዓላማና እሴት ጋር የመጣጣሙን ጉዳይ ማሰብ መኖር ጀመርኩኝ፡፡ ይህንን ያደረኩኝ ጊዜ ብዙ ሸክም ከላዬ ላይ የተነሳ ያህል እርምጃዬ ቀለለኝ፣ ምክንያት-የለሹ የድካም ስሜት ተወኝ፣ የጀመርኩትን ግቤን ጥጉ የማድረስ ጉልበት አገኘሁኝ! ለካ እኔንም ልክ እንደ ቅብጥብጡ ውሻ ያደከመኝ ቀጥታው ሳይሆን ግራ-ቀኙ እና መለስ-ቀለሱ ነው!     ✍ ዶ/ር እዮብ ማሞ @bete1912 @bete1912
Mostrar todo...
👍 4 1
📚የአማርኛ እና የእንግሊዝኛ መፅሀፍትን ለማግኘት: @book1912 🔎ፈልጋችሁ ያጣቹት መጽሀፍ ካለ ደሞ:@yabuka1912
Mostrar todo...
#ዝምታ🤫 የስኬትህ ሀይል የተረዱ በዝምታ ውስጥ ሆነው አንገታቸውን አቀርቅረው ለህልማቸው እውን መሆን ይፈጋሉ ። የዝምታን ሀይል ያልተረዱ ደግሞ ሕልማቸውን ላገኙት ሰው ይናገራሉ ። በአከባቢህ ሁለት አይነት ሰዎች አሉ ለአንተ ከፍታ መሰላል የሚሆኑ በተቃራኒው ደግሞ መሰላልህን የሚነቀንቁ። የዝምታ ሀይል እጅጉን ግዙፍ ነው ። ፀሀይ ምታበራው በዝምታ ውስጥ ነው ፤ የመሬት ዙረት ሚከናወነው በከባድ ድምፅ ታጅቦ አደለም ፤ ሰውነታችን ውስጥ የሚካሄደው የ ሕዋሳት ዝውውር በዝምታ ውስጥ ። በዝምታ ውስጥ ትላልቅ ተዐምራት ይፈጠራል ። ወዳጄ !! ከነዚህ ተፈጥሯዊ ነገሮች ማነስ የለብህም በዝምታ ስራ ስኬትህ እንደ ፀሀይ ማብራቱ እርግጥ ይሆናል!። @bete1912 @bete1912
Mostrar todo...