cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

🧖SafetyNet(የደህንነት መረብ)

Stay Away From Evil Thought & Yearn Now Eternal Things @safetynetchannel

Mostrar mĂĄs
Publicaciones publicitarias
207
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 dĂ­as
-730 dĂ­as

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ሰላማችሁ ይብዛ ውድ የቻናላችን ተከታታዮች እንደምን ከረማችሁ?ከረዥም ጊዜ በኋላ የደህንነት መረብ ቻናላችን ዘመኑን በዋጁ እና መንፈሳዊ ህይወትን በሚያንጹ ጠቃሚ ትምህርቶች እና መርሃ ግብሮች ተመልሶ መጥቷል።እግዚአብሄር ቢፈቅድና ብንኖር ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ ከበፊት ያቆምነውን ትምህርቶች እንቀጥላለን።ጌታ በነገር ሁሉ እንዲረዳን ጸልዩልን።ተባረኩ🙏
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
የክርስትንና መንገድ እንደ "አስቸጋሪ፣ የማይቻልና ጠባብ" አድርገን እንደናስብ የሚያደርገን፣ ለሥጋችን የሚመቸውን ሰፊውን መንገድ ስለምንመረጥ ነው። ከክርስቶስ ፍቅር ይልቅ በሰፊው በር በኩል የምናገኘው የኀጢአት ደስታ ስለሚበልጥብን ነው። ሾለ በደላችንና ስለኀጢአታችን በመስቅል ሞት ሕይወቱን ሾለ ለእኛ አሳልፎ የሰጠው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "አስጨናቂ ገዢ" አይደለም። በመስቀሉ ላይ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ፍቅር የተረዳ ሰው ጠባቡን መንገድ እንደ ዕዳ አያየውም። ይልቁንም ለዓለምና ለሥጋው ፈቃድ በየጊዜው ይሞቷል። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚለው፣ “ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ፤ ከእንግዲህ እኔ አልኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በውስጤ ይኖራል። አሁንም በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና ሾለ እኔ ራሱን አሳልፎ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለኝ እምነት ነው።” ( ገላትያ 2 : 20) ክርስቶስን መሲሕ ብቻ ሳይሆን ጌታ አድርጐ በልቡ ላይ አንግሧል።  ከኀጢአት ከሚገኘው ደስታ ይልቅ በማይወዳድር መልኩ በክርስቶስ ፍቅርና ክብር ደስ ይለዋል። የዓለም ሳይሆን የክርስቶስ ፍቅር እስረኛ በመሆኑ በጠባቡ በር ይገባል። ጠባቡ በር የፍቅርና የክብር በር ነው። በአንድ ጊዜ የጌታም የዓለምና የሥጋ መሆን አይቻልም። የት ይሆን ያለነው? አቤቱ፤ የመስቀልህ ፍቅር ያድሰን። አሜን! ግርማ በቀለ (ዶ/ር) @nazrawi_tube
Mostrar todo...
👑የንጉስ ገበታ👑 ዕብራውያን 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ሊቀ ካህናት ሁሉ ስለ ኃጢአት መባንና መስዋዕትን ሊያቀርብ ከሰው ተመርጦ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ ስለ ሰው ይሾማልና፤ ² እርሱ ራሱም ደግሞ ድካምን ስለሚለብስ፥ ላልተማሩትና ለሚስቱት ሊራራላቸው ይችላል፤ 🛐SAFETYNET CHANNEL🛐
Mostrar todo...
🔥ህያው-ዘር🔥 የሰው ልጅ ዘርቶ በማያጭድበት ሰርቶ በማይበላበት በዚያ በደጉ ጊዜ በሰናዩ ዘመን ጥሮ ግሮ ባላመጣው እንዲሁ በአምላክ ችሮታ  በይሁንታ ቃሉ በተፈጠሩ የምድር ፍሬ እና ቡቃያ ታጅሎ ይኖር ነበር ።በዚው የህይወት ስርአት ቢዘልቅ ምን ነበረበት 🌘ግና የሰው ልጅ ከአምላክ ትእዛዝ በተቃርኖ በመሄዱ ዛሬ እንደ መርህ አለፍ ሲልም እንደ መፈክር የምንለፍፈውን ዘርቶ ማጨድ ሰርቶ መብላት የሚባል አዲስ ርእዮትን ለፍጥረተ-አለም አስተዋወቀ። እንግዲህ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ነው ዘርም መዘራት ስራም መሰራት የተጀመረው። ይህ የመዝራት እና የማጨድ መርህ ለረዥም ዘመናት ከሰዎች የህይወት ስርአት ጋር የተጋመደ እና የተዛመደ ዘመን ዘለቅ እና እድሜ ጠገብ መርህ ነው።በእጅጉ የሚገርመው ደግሞ ይሄን ስነ- ፍጥረትን የሚዘውረውን መርህ ከሃሊ ኩሉ የሆነው ምጡቁ አምላክ አለሙን ለማዳን መጠቀሙ ነው።የእግዚአብሄር ሕያው ዘር ወደ ሰው ሙት ዘር ይገባ ዘንድ የሰማይ ዘር ወደ ምድር መዘራት አለበት።ምክንያቱም ዘር ካልተዘራ አይበቅልም።አፈር ካልለበሰ ካልሞተ ፍሬን አይሰጥም።ለዛም ነው ከአብ የወጣው የሰማዩ ዘር ስጋን ለብሶ ወደምድር በመሞት ሊዘራ የመጣው።የዘር ህይወቱ ያለው ሞቱ ውስጥ ነውና የሰማዩ ዘር የሃጢአት ጽልመት ባጨለመው የሰው ልጅ ልብ ላይ በመዘራት የህያውነትን ፍኖት በመሞት ጀመረው። ፍጹም ባእድ የሆነ ያልተለመደ የህይወት ብርሃን ሙቱ ዘር ላይ በራ።የዘር ተፈጥሮ ሞቶ መነሳት ከስሞ መፍካት በመሆኑ የሰማዩ ዘር ሞቶ አልቀረም ሞቶ ተነሳ አጥፊው ዘር ደግሞ በተራው ከሰመ ህልሙ ጨለመ።የሰው ሙት ዘር  በህይወት ዘር ተወረሰ።ትንሳኤ ሆነ።የሰማዩ ዘር ላይሞት ተነሳ።እንግዲህ ይሄ ነው ቁምነገሩ ህይወት ያለው ሞት ውስጥ ነው።ትንሳኤ ያለው ስቅለቱ ውስጥ ነው።እናም ከማይጠፋ ዘር እንደተወለደ አማኝ እኛም ዘሩን እንዝራ የትንሳኤው ህይወት ይብዛ ይባዛም።እጅ ላይ ያለ ዘር አያፈራም።እኛ የተካፈልነውን የህይወት ዘር ሃጢአት ባጨለመው ልቦች ላይ ያለስስት እንዝራው። “....... ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።”   — ኢሳይያስ 53፥10 ✍ምናሴ ይርጉ #safetynetchannel
Mostrar todo...
Repost from HUFELLOW
Photo unavailableShow in Telegram
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ብዙ የእግዚአብሔር ባህሪያት ቢኖሩም በዋናነት ተገልፆ የምናገኘው ግን ቅድስናው ነው። ለምሳሌ  በኢሳይያስ 6፥3 “ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች” እያሉ መላዕክቱ ሲያመሰግኑት እናገኛቸዋለን። በሌሎች ቦታዎችም ላይ በብዛት ተጠቅሶ የምናገኘው እውነት መሆኑ አሻሚ አይደለም። ይሁንና ታዲያ ይህ በእንዲህ እንዳለ አያበቃም። ሾለ ቅድስናው የምናወራለት አምላክ እኛም ከቅድስናው መንፈስ እንደመካፈላችን በፊቱ ቅዱሳን እንድንሆን ይሻል። ይህ ደግሞ አንዱ እግዚአብሔርን መምሰል የምንችልበት ባህርይ ነው። በመቀደስ እርሱን እንምሰል !!! #share_to_other Join us on @HUfellow #share_to_others #Horeb_Ds
Mostrar todo...
👑የንጉስ ገበታ👑 📖2ኛ ቆሮ 1📖 ²¹ በክርስቶስም ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው፥ ²² ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው። 🛐SAFETYNET CHANNEL🛐 💁‍♂https://t.me/safetynet7 #join and #share
Mostrar todo...
🧖SafetyNet(የደህንነት መረብ)

Stay Away From Evil Thought & Yearn Now Eternal Things @safetynetchannel

ሰላም ውድ የቻናላችን ተከታታዮች እንደምን ውላችኋል?በእናንተው ድምጽ መሰረት የsafetynet ቻናል ትምህርታችንን እንድንቀጥል የሚያስችለንን አዎንታዊ ምላሽ ስላገኘን ትምህርታችንን እና ሌሎችም ጠቃሚ መርሃግብሮችን አዘጋጅተን በቅርብ ቀን እንመለሳለን።
Mostrar todo...
የsafetynet ቻናል ትምህርቶች እንዲቀጥሉ ይፈልጋሉ?Anonymous voting
  • አዎን እፈልጋለሁ
  • አይ አልፈልግም
0 votes
👑የንጉስ ገበታ👑 📖ቆላስይስ 3📖 ¹ እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ፤ ² በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ³ ሞታችኋልና፥ ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና፤ ⁴ ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ። ⁵ እንግዲህ በምድር ያሉቱን ብልቶቻችሁን ግደሉ፥ እነዚህም ዝሙትና ርኵሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣኦትንም ማምለክ የሆነ መጎምጀት ነው፤ 🛐SAFETYNET CHANNEL🛐
Mostrar todo...