cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ጥበብ

ሐሳብ ጥበብ ነው። ከጥበብ ማዕድ እንቆርሳለን። ያጋሩ። ሐሳብ፣ አስተያየት ለመስጠትና ለማስታወቂያ @KYEAB29 ላይ ያነጋግሩ። ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን!

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 515
Suscriptores
Sin datos24 horas
-67 días
-3630 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
#የዓለም_የመጻሕፍት_ቀን እንኳን አደረሰን! እንኳን አደረሳችኹ! ክብር ለዓለም ደራሲዎች! የንባብ አክፍሎታችኹን ለማድረስ በሚከተሉት ገጾች ተቀላቀሉን። @Light_Book_Delivery @Light_Book_Delivery @Light_Book_Delivery_1 @Light_Book_Delivery_1 @Light_Equb @Light_Equb @Love_Of_Sophia @Love_Of_Sophia
Mostrar todo...
#ከሞተች_ቆይቷል ከሞተች ቀይቷል ብዙ ዘመን ኾኗል ብዙ ነበር ጊዜው ግን ፎቶግራፏ አለ ደብዳቤዋም አለ በጠጕሯ ጉንጉን የጠቀለለችው ምን ቀን ቀጠሮ ነው ቀን የቀን ጎደሎ የቀን ጥቁር መጥፎ አበባ ሔድኩ ይዤ እዛ አበባ አልጠፋም በመቃብሯ ውስጥ አበባ ተኝቷል፡፡ ስሜቴ ፈነዳ ገላዬን በተነው ነፍሴን ነቀነቃት ገላዬን በተነው፡፡ ነፍሴን ነቀነቃት እንባዬ ወረደ ጉንጬን አረጠበው ለተረሳ ነገር እንዴት ያለቅሳል ሰው! ለተረሳ ነገር ምን ጊዜው ቢረዝም የዚኽ ዓለም ጣጣ እያንከራተተኝ የዚኽ ዓለም ስቃይ እየቦረቦረኝ ሲጨንቀኝ ሰውነት ፍቅሬ ይኹን ያንቺ የኔ መቃብር ቤት ሕይወት ነዶ ጠፍቶ ሞት ፍሙን ሲያዳፍን ያን ጨለማ ጓዳ ሔጄ ልተኛበት። ይመስላል ዘላለም ሰው ሰውን ሲወዱት ዐይኑን ዐይኑን ሲያዩት ይመስላል ዘላለም አድማስ አልፎ አድማስ ምጥቀት አልፎ ምጥቀት ጠፈር አልፎ ጠፈር ይመስላል ዘላለም ሰው ባ'ካል የሚኖር ድሮ ዐውቀዋለው ተረድቼዋለኹ ፀሐይ ጥቁር ስትኾን ቀን ቀንን ሲያጠላው ሌት ሌትን ሲሸፍን እረስቸው እንደኹ፡፡ እንዴት አንቺን ልርሳ ነፍሴ አብሯት የሚኖር የፍቅርሽ ጠባሳ፡፡ ˝ፍቅርሽና ፍቅሬ የተወሳሰበው አልበጠስ አለኝ ብስበው ባስበው˝ ማን ነበር ማ ነበር ማ ነበር እንደዚኽ ብሎ የገጠመው? ይመስላል ዘላለም አንቺ የኔ እመቤት ብያት የነበረ አንተ የኔ ጌታ አንተ የኔ ጌታ ብላኝ የነበረ አንቺ የኔ እመቤት ይመስላል ዘላለም፡፡ እንባዬ ወረደ ልቤን አቃጠለው ልቤ ተነደለ የሰቀቀን እሳት አካሌን ሲያነደው ደሜ ገነፈለ የደም ጥቁር እንባ ቆዳ የሚያሳስር መንፈስ የሚያባባ አለቀሰቅሳትም ቡዳ እሷን አይበላም ቢስ እሷን አያይም አልቀሰቅሳትም በነብሴ ተጉዤ እጠይቃታለኹ ዐውቃለው ዐውቃለኹ በመቃብሯ ውስጥ ጢስ እንጨት ይጨሳል ከርቤ ብርጉድ እጣን መቃብሯ ሽቱ ጣፋጭ መኣዛ አለው አጥንቷ ታቦቱ መቅደስ ቤተልሔም ቅኔ ማኅሌቷ እጣኑ ይጨሳል ይታጠናል ቤቷ ፍቅሬ ሙሽራዬ እመቤቴ ፍቅሬ ያለም አለኝታዬ አቴቴዋ ይታጠናል ልዩ መዓዛ አላት በመቃብሯ ውስጥ ጢስ እንጨት ይጨሳል በመቃብሯ ውስጥ አበባ ተኝቷል፡፡ ፍቅሬ ፍቅሬ ፍቅሬ፤ ፍቅሬ ፍቅሬ ፍቅሬ እመቤቴ ፍቅሬ እመቤቴ ፍቅሬ፤ እመቤቴ ፍቅሬ እመቤቴ ፍቅሬ ፍቅሬ አለኝታዬ ፍቅሬ አለኝታዬ፤ ፍቅሬ አለኝታዬ ፍቅሬ አለኝታዬ እንባዬ ወረደ………………….. እንግዲኽ ይበቃል ይቅር ይቅር ይብቃ በድካም መድከም ባ'ሳብ ሐሳብ አለ ባ'ዘን…………..ሐዘን……….ሐዘን። ለተናፈቅሽው ❤ © ገብረ ክርስቶስ ደስታ! @Love_Of_Sophia @Love_Of_Sophia
Mostrar todo...
2
ከሞተች ቆይቷል [ ገብረክርስቶስ ደስታ ] ከሞተች ቀይቷል ብዙ ዘመን ሆኗል ብዙ ነበር ጊዜው ግን ፎቶግራፏ አለ ደብዳቤዋም አለ በጠጉሯ ጉንጉን የጠቀለለችው ምን ቀን ቀጠሮ ነው ቀን የቀን ጎደሎ የቀን ጥቁር መጥፎ አበባ ሄድኩ ይዤ እዛ አበባ አልጠፋም በመቃብሯ ውስጥ አበባ ተኝቷል፡፡ ስሜቴ ፈነዳ ገላዬን በተነው ነፍሴን ነቀነቃት ገላዬን በተነው፡፡ ነፍሴን ነቀነቃት እንባዬ ወረደ ጉንጬን አረጠበው ለተረሳ ነገር እንዴት ያለቅሳል ሰው! ለተረሳ ነገር ምን ጊዜው ቢረዝም የዚህ ዓለም ጣጣ እያንከራተተኝ የዚህ ዓለም ስቃይ እየቦረቦረኝ ሲጨንቀኝ ሰውነት ፍቅሬ ይሁን ያንቺ የኔ መቃብር ቤት ህይወት ነዶ ጠፍቶ ሞት ፍሙን ሲያዳፍን ያን ጨለማ ጓዳ ሄጄ ልተኛበት። ይመስላል ዘላለም ሰው ሰውን ሲወዱት አይኑን አይኑን ሲያዩት ይመስላል ዘላለም አድማስ አልፎ አድማስ ምጥቀት አልፎ ምጥቀት ጠፈር አልፎ ጠፈር ይመስላል ዘላለም ሰው ባካል የሚኖር ድሮ አውቀዋለው ተረድቼዋለው ፀሀይ ጥቁር ስትሆን ቀን ቀንን ሲያጠላው ሌት ሌትን ሲሸፍን እረስቸው እንደሁ፡፡ እንዴት አንቺን ልርሳ ነፍሴ አብሯት የሚኖር የፍቅርሽ ጠባሳ፡፡ ˝ፍቅርሽና ፍቅሬ የተወሳሰበው አልበጠስ አለኝ ብስበው ባስበው˝ ማን ነበር ማ ነበር ማ ነበር እንደዚህ ብሎ የገጠመው? ይመስላል ዘላለም አንቺ የኔ እመቤት ብያት የነበረ አንተ የኔ ጌታ አንተ የኔ ጌታ ብላኝ የነበረ አንቺ የኔ እመቤት ይመስላል ዘላለም፡፡ እንባዬ ወረደ ልቤን አቃጠለው ልቤ ተነደለ የሰቀቀን እሳት አካሌን ሲያነደው ደሜ ገነፈለ የደም ጥቁር እንባ ቆዳ የሚያሳስር መንፈስ የሚያባባ አለቀሰቅሳትም ቡዳ እሷን አይበላም ቢስ አሷን አያይም አልቀሰቅሳትም በነብሴ ተጉዤ እጠይቃታለው አውቃለው አውቃለው በመቃብሯ ውስጥ ጢስ እንጨት ይጨሳል ከርቤ ብርጉድ እጣን መቃብሯ ሽቱ ጣፋጭ መኣዛ አለው አጥንቷ ታቦቱ መቅደስ ቤተልሄም ቅኔ ማህሌቷ እጣኑ ይጨሳል ይታጠናል ቤቷ ፍቅሬ ሙሽራዬ እመቤቴ ፍቅሬ ያለም አለኝታዬ አቴቴዋ ይታጠናል ልዩ መዓዛ አላት በመቃብሯ ውስጥ ጢስ እንጨት ይጨሳል በመቃብሯ ውስጥ አበባ ተኝቷል፡፡ ፍቅሬ ፍቅሬ ፍቅሬ፤ ፍቅሬ ፍቅሬ ፍቅሬ እመቤቴ ፍቅሬ እመቤቴ ፍቅሬ፤ እመቤቴ ፍቅሬ እመቤቴ ፍቅሬ ፍቅሬ አለኝታዬ ፍቅሬ አለኝታዬ፤ ፍቅሬ አለኝታዬፍቅሬ አለኝታዬ እንባዬ ወረደ………………….. እንግዲኽ ይበቃል ይቅር ይቅር ይብቃ በድካም መድከም ባሳብ ሐሳብ አለ ባዘን………….. ሃዘን……….ሃዘን
Mostrar todo...
Repost from አገረ ሻባካ
የሴትነት ከፍታ እናት ናት። ብልኽ ናት። አይመስልኽም እንጂ ከእሷ በላይ የሚረዳኽ የለም፤ ሳትናገር ነው የምታውቅኽ። እንጠባይኽ ብላ ያየችውን እንዳላየች ስለምታልፍና ነጻነትኽን ከማንም በላይ ስለምትጠብቅ እንጂ ስለአንተ ከራስኽ በላይ ታውቃለች። እስከመጨረሻው አብራኽ የምትጓዘው እናትኽ ናት። ካላመንኸኝ በዕለተ ዐርብ እስከመስቀል አብሮት ማን እንደነበር እስከሞት የደረሰውን ጌታ ጠይቀው። ሴት ልጅ የምትከብረው በመውለድ እንደኾነ ቅዱሱ መጽሐፍም ይነግርኻል። ስትወልድ የሰውነት ኹሉ ልክ ትኾናለች። ከፈጣሪኽ በታች አምላክኽ ትኾናለች። እናትኽ... ስትጨልም አብራኽ ትጨልማለች፣ ስትሰንፍ ፍጹም ልታበረታኽ አብራኽ ትሰንፋለች፣ ብርታቷን ልታጋባብኽ በወረት ሳይኾን በፍጹም ፍቅር የምትጥር ናት። እሷ ጋር የአንተ በሽታ በሽታዋ ነው። ስለአንተ ደኅንነት እንጂ ለበሽታኽ ግድ አይሰጣትም። እሷ ጋር የአንተ ዝቅተኛነት ሳይኾን መኖርኽ ብቻ ዋጋ አለው። እሷ ጋር ከአንተ ሐዘን በላይ የሚያሳዝናት የለም። እሷ ጋር ደሀ ብትኾንም ሀብትዋ እንደኾንኽ ትቆጥራለች። እሷ ጋር መለዋወጥ፣ በአንተ ተስፋ መቁረጥ የለም። ሰዎች መልክኽን፣ ዕውቀትኽን፣ ሞራልኽን፣ ሕመምኽን፣ ችግርኽን፣ ስንፍናኽን ተመልክተው ሊሸሹኽ፤ አይረባም ብለው ከሕይወታቸው ሊያስወጡኽና ተስፋ ሊቆርጡብኽ ይችላሉ። እናትኽ ግን ስትወልድኽ እንደተደሰተችው ኹሉ እስከሕቅታዋ ድረስ ያው በአንተ ደስተኛ ናት። ስለምታደርግላት አይደለም...በቃ ስላለኻት ስለተወለድኽላት ብቻ ደስተኛ ናት። ከእሷ ውጪ የአምላክኽ ምድራዊ አምሳል ማን ሊኾን ይችላል? ማንም የማይተካት የፈጣሪኽ ጸጋ ናት። @Love_Of_Sophia @Love_Of_Sophia
Mostrar todo...
3👍 2
Repost from አገረ ሻባካ
Photo unavailableShow in Telegram
የሩቅ - ቅርብ ድንገት ይመጣሉ፤ ብድግ ብለው ይሔዳሉ። ሳታስበው ያገኙኻል፤ ማሰብ ስትጀምር የሉም። ስትተኛ ሥርኽ ነበሩ፤ ስትነቃ ታጣቸዋለኽ። ድክመትኽን ዕያዩ ቀርበውኽ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ትሰለቻቸዋለኽ፤ በአንተ ላይ ተስፋቸው ይሟጠጥና ከአንተ መሸሽ ይመርጣሉ። ደካማነትኽ ከፍቅራቸው በልጦ ብተውኽ ምን አጣለኹ ይሉኻል። ያገኙኽ ትናንት ነው፤ የተዉኽ ደግሞ ዛሬ። በአንድ ቀን ውስጥ (በጥቂት ጊዜያት ግፋ ቢል በትንሽ ዓመታት) ከአንተ ለመራቅ ኹለቴ አያስቡም። ፍጹምነትኽን ስለሚሹ ጥቁር ነጥብ ካዩብኽ እስከዛሬ በምድር ከታዩት አስከፊው ሰው አንተ ትኾናለኽ። ስሕተት ከተገኘብኽ በቃ አታስፈልግም። በሩቁ - ይቀርቡኻል። የሩቅ - ቅርብኽ ናቸው። ርቀውኽ ይመለከቱኻል። ከአንተ ጋር ያላቸው ቅርበት ገደብ በተበጀለት አጥር የተቀጠረ ነው። እነኚኽ ብዙኃኑ ናቸው። . . . . . (ክፍል ፩) ✍ ፒያንኪያ @KYEAB29 @Love_Of_Sophia @Love_Of_Sophia
Mostrar todo...
👍 2
Repost from አገረ ሻባካ
Photo unavailableShow in Telegram
አንዲት እድሜ ለስንት ትኾናለች??? በጨዋታችን መኻል "ባል ፈልግልኝ" አለችኝ ምን ዓይነት? አልኋት። "ጥሩ ጠባይ ካለው ይበቃኛል"። የምሯን እንደኾነ ኹሉ ነገሯ ይናገራል። ጉጉቷ አንጀቴን በላው።     ፍቅረኛ ኖሮሽ ያውቃል? አልኋት። ጥያቄውን ለማሰላሰል ስታገል በደረቁ ወጣብኝ።       "ነበረኝ" "ዛሬ ነገ እያለ ሕልሙ ላይ ተመስጦ ድክመቴን እያጎላ እያሳጣ ከዛሬ ነገ እንጋባለን እያለ ቀኔን ዕድሜዬን በልቶ ተልካሻ ምክንያቶችን ጠቃቅሶ ተለየኝ። አኹን ሌላ ከእኔ በአሥር ዓመት የምታንስ ጉብል አግብቶ ወልዶ ይኖራል"     ምናለ.... ካልወደድኻት፣ ካላገባኻት ብትተዋት፤ ቀኗን ባታኝከው! ውበቷ ሳይደበዝዝ፣ የከጀለችውን አማርጣ በጊዜዋ ታግባ።     *  ጊዜ ለሴት ልጅ ከወንድ ልጅ የበለጠ ትርጉም አለው። ✍ አድኃኖም ምትኩ 📖 አዎ!...እሱ ጋር ያመኛል! (የተቀነጨበ) @Love_Of_Sophia @Love_Of_Sophia
Mostrar todo...
4
Repost from አገረ ሻባካ
Photo unavailableShow in Telegram
ምን ኾኜ ነው? ተስፋ ነበረኝ የምፈልገው ልደርስበት የምመኘው ሥፍራም ነበረኝ ። ምን ኾኜ ነው? ትንሽ ነገር ያስደስተኝ ነበር። እናቴ ከወትሮ ለየት ያለ ወጥ ከሠራች ዓለም ሙሉ ይመስለኝ ነበር። ደስተኛ ነበርኹ። አኹን ዳስ ተጥሎ ቢደገስልኝ ግድ አይሰጠኝም። ጥቂት ይበቃኝ ነበር እኮ። በሹክሹክታ የነገሩኝ ጎልቶ ይሰማኝ ነበር። አኹን እየጮኹብኝም አልሰማ። ትንሽ እኮ ይበቃኝ ነበር... ምን ኾኜ ነው? በፊት ስሔድበት የሚያስደስተኝ ስፍራ ነበር። አኹን ቦታ ለመቀየር ብቻ ነው የምንቀሳቀሰው። በፊት አንድ ማንኪያ ቡና እርካታን ያጎናጽፈኝ ነበር...አኹን የጀበናውን ያኽል ቡና ብይዝም የጠጣው አይመስለኝም። በቡና አልነቃ። በአነቃቂዎች አልነቃ። ዐውቄ ነው መሠል ተኝቻለኹ። ምን ኾኜ ነው? ማን ነው ተስፋ የነፈገኝ ? በማን ነው የደከምኹት ? መቼ ኑሬ ነው ያረጀኹት? ድሮ መቼ ነው? ድሮ የዛሬ ዓመት? ድሮ ትላንትና? የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ©ሶፊ
Mostrar todo...
👏 5
Photo unavailableShow in Telegram
ለማን ትነሣላችኹ? @Love_Of_Sophia @Love_Of_Sophia @Love_Of_Sophia
Mostrar todo...
👍 2
Repost from አገረ ሻባካ
Photo unavailableShow in Telegram
መንገደኛ ነኝ፤ ቀንና ጨለማ በመንገዴ ላይ ይመላለሳሉ። እየሔድኹ ይነጋል፤ ስጓዝ ይመሻል፤ ቆሜ አላውቅም፤ ድካሚ የሚሰማኝ ስለምጓዝ አይደለም፤ ጉዞዬ ተቀምጦ ስለኾነ እንጂ። መንገደኛ ተጓዥ ነኝ፤ ፀሐዬ ተገፍትራ ጨረቃ ልትወጣ እያኮበኮበች ቢኾንም ለጨረቃም ቦታ ተነፍጋ ደመና አደምምኗል። ምሽት ከደመና ጋር ምንኛ ያስፈራል? የእኔ ፀሐይ ጉዞዬ ሳያልቅ የምትወጣው መቼ ነው? ☀️☀️☀️🌤🌤🌤🌤⛅️⛅️⛅️ ✍ ፒያንኪያ @Love_Of_Sophia @Love_Of_Sophia
Mostrar todo...
👍 1
Repost from ☀LIGHT BOOKS☀
ልዩ የንባብ ድግስ ''የመጻሕፍትን ዜማ ዐይኖቻችን ያዜማሉ'' __ የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን በ፳፻፲፭ ዓ.ም የመሠረትነው የበይነ መረብ (Online) የመጽሐፍ ዕቁብና የንባብ ቤተሰባችን እነኾ የአንድ ዓመት ሕጻን ሊኾነው እያኮበኮበ ነውና እርስዎም የዚኽ የቴሌግራም ማዕቀፍ ቤተሰባችን አባል ስለኾኑ በዛሬው ዕለት በዕለተ ቅዳሜ ከምሽቱ 1:00 ባዘጋጀነው ልዩ የንባብ እና የጭውውት ድግስ ላይ ከወዳጅ ጓደኛዎ ጋር እንዲገኙልን የምድር ውድ ገጸበረከቶች በኾኑት በመጻሕፍት ስም በማክበር ጠርተንዎታል። በድግሳችን ላይ.... ➡ መጻሕፍት ይነበባሉ፤ በስጦታ ይሰጣሉ። ➡ ጨዋታዎችና ሽልማቶችም ተዘጋጅተዋል። ጠሪ አክባሪ ነውና እንድትገኙልን ጋብዘናል። የ2015 ዓ.ም የመጽሐፍ ዕቁብ ቤተሰብ አድራሻ 📍 ➡ ወደ ቴሌግራም  @Light_Equb ገባ ሲሉ ያገኙናል። ሰዓት ⏰ ➡ ዛሬ ምሽት 1:00 ጀምሮ
Mostrar todo...
👍 2