es
Feedback
ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁

ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁

Ir al canal en Telegram

👉plexiglass 👉engraving 👉orginal cosmotics 👉 natural face products like Kesil 👉Gift packages 📞0942410512 metis_bag 🏠🏠 Megenagna 3M Mall 1st floor

Mostrar mĂĄs
1 896
Suscriptores
Sin datos24 horas
-47 dĂ­as
-2830 dĂ­as
Archivo de publicaciones
ጥያቄ እና መልሳችን ሊጀምር ነው የዛሬው ርዕሳችን #ስለ_እርግዝና ይሆናል ስለ እርግዝና ያላቹን ማንኛውም ጥያቄ ማቅረብ ትችላላቹ። @DrJanogp

10 ቶሎ ለማርገዝ የሚረዱሽ ምግቦች https://youtu.be/Gfj1bVjSsmg

ዛሬ አንድ ርዕስ መርጠን የእናንተን ጥያቄ ለመቀበል ወስነናል። በምን ጉዳይ ይሁን?

የኩላሊት ሕመም ይሰማዎታል? ጥርጣሬ አልዎት? እንግዲያውስ፡ ይምጡ እና ነጸ የኩላሊት ምርመራ ያድርጉ! ቀን፡ መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ሰዓት ፡ 3፡30-9፡30
የኩላሊት ሕመም ይሰማዎታል? ጥርጣሬ አልዎት? እንግዲያውስ፡ ይምጡ እና ነጸ የኩላሊት ምርመራ ያድርጉ! ቀን፡ መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ሰዓት ፡ 3፡30-9፡30

የተለያዩ የቀዶ ህክምና እየተሰጠ ነው #ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ በቅዱስ ጳሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በሴት ዶክተሮችና የህክምና ባለሙያዎች ብቻ የተመራ የተለያዩ የቀዶ ህክምና እየተሰጠ
+2
የተለያዩ የቀዶ ህክምና እየተሰጠ ነው #ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ በቅዱስ ጳሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በሴት ዶክተሮችና የህክምና ባለሙያዎች ብቻ የተመራ የተለያዩ የቀዶ ህክምና እየተሰጠ ይገኛል። አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓለም ለ111ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ46ኛ ጊዜ “እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ ነው፡፡ (ኢዜአ) @DrJano @DrJano

ጓደኞቻችሁ ወደዚህ ቻናል ቤተሰብ እንዲሆኑ t.me//DrJano ለጓደኞቻችሁና በየ ግሩፑ ሸር አድርጓቸው። @DrJano @DrJano

✍️ #ህጻን #ልጅዎ #ላይ #እነዚህን #ያስተውሉ ? 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #የልጅዎ የሰውነት ሙቀት መጠን 38 ዲግሬሲንቲ ግሬት ወይም ከዚያ በላይ ከሆነና ባንድ ጊዜ ከ2 ሰአት በላይ ካለቀሰ ፣ ምግብ የማይወስድ ከሆነ፣ተቅማጥ ካለ ፣ ያለማቋረጠጥ ማስመለስ ፣እንቅልፍ ሲያበዙ ወይም ባልተለ መደ መልኩ ንቁ ከሆኑ ባፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መውሰድ። ⏩ #አንድ ህፃን ለጥቂት ሰኮንዶች ያህል ቸጭንቅላቱ ከተናጋ ማዳን የማይቻል የአንጎል ጉዳት ይድረስበታል። ⏩ #ጨቅላ ህፃናትን በሚያለቅሱበት ወቅት ለማባበል ካለማወቅ አልያም ከጭንቀት የተነሳ በሃይል ሲወዘወዝ የልጁ አንጎል በራስ ቅሉ ውስጥ ከኋላ ውድፊት ይወዛወዛል በዚህ ምክንያት እብጠት እና መድማትን ያስከትላል። ⏩ #የልጆ አይነ ምድር ውሃማ፣አረንጓዴ፣ጠረን ያለው ከሆን ወደ ጤና ተቋም መውሰድ። ⏩ #ልጆች ሲርባቸው፣ሲረጥቡ፣ ሆዳቸው ሲነፋ ፣በጣም ሲሞቃቸው ወይም በጣም ሲበርዳቸው ሊያለቅሱ ይችላሉ። ⏩ #ማርን ከ 12 ወራት በታች ላሉ ልጆች አይስጡ። ⏩ #ጨቅላ ልጆች በሚጠቡ ሰአት ከወተቱ ጋር አብሮ የሚገባ አየር (ጋዝ) ካለ እንቅልፍ እምቢ ሊላቸው ይችላል። ስለዚህ ልጆን ማስገሳት ጠቃሚ ነው። ⏩ #የልጆ እትብት ደርቆ ለመውደቅ ከ12-14 ቀን ሊያስፈልገው ይችላል፤ ከዚህ ካለፈ ባለሙያ ማማከሮን አይዘንጉ፡፡ ⏩ #በመኝታ ጊዜ ልጆን አጥብቀው በማቀፍ የሚወዱት መዝሙር ደጋግመው ይዘምሩለት፤ተመሳሳይ መዝሙር መዘመር ልጅዎ እንዲሰክን እና ደህንነት እንዲሰማው ያደርጋል። ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥ ✅ ለተጨማሪ የጤና መረጃዎች ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 https://t.me/+6X9O71L_Vu1iY2Y0

✍ #የማንኮራፋት #ምክንያቶቹ #ምን #ይሆኑ? 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #ማንኮራፋት አንድ ሰዉ በሚተኛበት ወቅት የጎረነነ ድምፅ የአየር መተላለፊያ ቧንቧ በከፊል መዘጋት በሚኖርበት ወቅት የሚከሰት ነዉ፡፡ ማንኮራፋት በትናጋዎ ዉስጥ ባሉ የላሉ ክፍሎች ዉስጥ የሚተነፍሱት አየር በሚያልፍበት ወቅት እንዲርገበገቡ ስለሚያደርግ ማንኮራፋት እንዲከሰት ያደርጋሉ፡፡ 👉 #መንስኤዎቹ 📌 #የአፍና #ሳይነስ #አፈጣጠር፡- ዝቅ ያለና የወፈረ ትናጋ የአየር መተላለፊያን ያጠባል፡፡ በጣም ወፍራም የሆኑ ሰዎች በአየር መተላለፊያ ቱቦዎች(ጉሮሮ ጀርባ) ትርፍ አካል/ tissues ስላለቸዉ የአየር መተላለፊያ ቱቦዉ እንዲጠብ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም እንጥልዎ ረጅም ከሆነች የአየር መተላለፍን ሊዘጋ ስለሚችል መርገብገቡ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ 📌 #አልኮሆል/#መጠጥ #መጠጣት፡- ከእንቅልፍ በፊት አልኮሆል አብዝተዉ የሚወስዱ ከሆነ ማንኮራፋት እንዲከሰት ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ መጠጥ የጉሮሮ ጡንቻዎች እንዲላሉ ስለሚያደርግ ሰዉነታችን በተፈጥሮ የአየር ቧንቧ እንዳይዘጋ የሚከላከልበትን መንገድ እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ 📌 #የአፍንጫ #ችግሮች፡- ለረጅም ጊዜ የአፍንጫ መጠቅጠቅ ችግር ከነበረ ወይም የአፍንጫ ዉስጥ ችግሮች ካሉ ማንኮራፋት እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ 📌 #በተደጋጋሚ #የአተነፋፈስ #መቆራረጥ #መኖር/ Sleep apnea:- ይህ ዋና መገለጫዉ ካንኮራፉ በኃላ ለተወሰኑ ሰከንዶች መተንፈስ ማቆም ሲኖር ነዉ፡፡ ከዚያን ድንገት አየር አጥሮት ከእንቅልፈዎ በድንገት ይነቃሉ፡፡ 👉 #አጋላጭ #ሁኔታዎች 🔺 ወንድ መሆን 🔺 ክብደት መጨር/ወፍራም መሆን 🔺 ጠባብ የአየር በተላለፊያ ያላቸዉ 🔺 መጠጥ የሚጠጡ 🔺 የአፍንጫ ላይ ችግሮች ካሉ 🔺 በቤተሰብ ዉስጥ መሰል ችግር ካለ የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡ 👉 #ምልክቶች 🔺 በእንቅልፍ ሰዓት የሚረብሽ ድምፅ መኖር 🔺 ቀን ቀን እንቅልፍ መብዛት 🔺 ትኩረት ማጣት 🔺 የጉሮሮ ህመም 🔺 ያልተረጋጋ እንቅልፍ መኖር 🔺 የአየር ማጠር ወይም ትንታ መኖር 🔺 የደም ግፊትና 🔺 ማታ ማታ የደረት ህመም መከሰት ናቸዉ፡፡ 👉 #ዉስብስብ #ችግሮቹ 🔺 ቀን እንቅልፍ እንቅልፍ ማለት 🔺 ቁጡነት/ብስጩነት መጨመር 🔺 ትኩረት ማጣት 🔺 የደም ግፊት፣የልብና ስትሮክ ችግሮች መጨመር 🔺 እንደ ሃይለኝነት፣የመማር ችግርና የመሳሰሉት የባህሪ ለዉጦች መጨመር (በተለይ በህፃናት ላይ) 🔺 የትደር/ፍቅር አጋርዎን እንቅልፍ መረበሽ 👉 #መከላከያዎቹ 🔺 ዉፍረት ካለዎ ክብደትዎን መቀነስ 🔺 በጎንዎ መተኛት ፡- ተንጋሎ መተኛት ምላስ ወደኃላ ሄዶ የአየር ቧንቧ ይበልጥ እንዲጠብ ስለሚያደርግ በጎን በኩል መተኛት ይመከራ፡፡ 🔺 ሲተኙ የመኝታዎን ራስጌ ከፍ ማድረግ 🔺 በቂ እንቅልፍ ለመተኛት መሞከር 🔺 ናዛል ስትሪፕ መጠቀም 🔺 የአፍንጫ መዘጋትን/መታፈንን መታከም 🔺 አለርጂዎች ካሉ እነሱን መታከም 🔺 ወደ መኝታ በሚሄዱበት ጊዜ የአልኮሆል መጠጦችን ያስወግዱ 🔺 ሲጋራ ማጨስ ማቆም 🔺 በሃኪም ያልታዘዙ የእንቅልፍ መድሃኒቶችን አለመዉሰድ ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥ ✅ ለተጨማሪ የጤና መረጃዎች ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 https://t.me/+6X9O71L_Vu1iY2Y0

✍ #ብጉር 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #ብጉር በቆዳ ላይ የሚገኙ የፀጉር ቀዳዳዎች በቅባት እና በሞቱ የቆዳ ሴሎች ሲሞሉ ወይም ሲደፈኑ የሚከሰት የቆዳ ችግር ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ብጉር ነጭ ወይም ጥቁር ጫፍ አንዳንዴም ቀያይ ነጠብጣቦች በቆዳ ላይ ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ነጠባጣቦቹ መጠናቸው ሊለያይ ይችላል፤ ህመም ሊኖራቸውም ላይኖራቸውም ይችላል፡፡ ብዙውን ጊዜ ብጉር በፊት ላይ የሚወጣ ቢሆንም በአንገት፣ ደረት፣ ትከሻ እና ጀርባም ላይ ሊወጣ ይችላል፡፡ ⏩ #ብጉር በማንኛውም ሰው ላይ ሊያጋጥም የሚችል ነው፡፡በአብዛኛውን ግን ብጉር በጉርምስና ወይም በወጣትነት እድሜ ውስጥ ያሉት ላይ ይበረታል፡፡ በሂህ ጊዜ የመጣ ከሆነ እድሜ በጨመረ ቁጥር እየቀነሰ ሲመጣ ጥቂቶች ላይ ግን አብሮአቸው ይኖራል፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ግን አንዳንድ ጊዜ ብጉር በሆርሞን ችግር ምክንያት ህፃናት ላይ ሊታይ ይችላል፤ በእርግዝናም ወቅት የመከሰት እድል አለው፡፡ ⏩ #ምልክቶቹ 🔺 ነጭ/ ጥቁር ጫፍ ያላቸው ነጠብጣቦች 🔺 ትናንሽ ቀያይ ህመም ያላቸው ነጠብጣቦች 🔺 ቀያይ ጫፍ ላይ ትንሽ መግል ያላቸው ነጠብጣቦች 🔺 ተለቅ ያሉ ጠጣር ህመም ያላቸው እብጠቶች 🔺 ህመም ያላቸው መግል የያዙ ከቆዳ ስር ያሉ እባጮች ⏩ #ብጉር #መንስኤው 🔺 ቅባትማ የቆዳ አይነት መኖር 🔺 የፀጉር ቀዳዳዎች በቅባት እና በሞቱ ሴሎች መዘጋት 🔺 ባክቴሪያዎች 🔺 የአንዳንድ ሆርሞኖች ስራ መጨመር (ለምሳሌ Androgen) ⏩ #ብጉር ቅባት አመንጪ እጢዎች (Sebaceous gland) በሚበዙበት የቆዳ ክፍል አካባቢ ነው የሚወጣው፡፡ እነዚህም ፊት፣ ግንባር፣ ደረት፣ የላይኛው የጀርባ ክፍል እና ትከሻን ያጠቃልላል፡፡ ⏩ #የፀጉር ቀዳዳዎች ከቅባት አመንጪ እጢዎች ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ የእነዚህ ቀዳዳዎች ግርግዳ ሲያብጡ ነጣ ያለ አናት ይኖራቸዋል፤ ወይም ደግሞ አናታቸው ክፍት ከሆነ ሲጠቁር ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ቀዳዳዎቹ በባክቴሪያ እና ቅባት ይሞላሉ፡፡ ⏩ #ቀያይ ከፍ ከፍ ያሉ ውስጣቸው ነጭ የሆኑ ነጠብጣቦች የሚፈጠሩት ደግሞ የፀጉር ቀዳዳዎች በቅባት ከመዘጋታቸው በላይ በባክቴሪያ ሲጠቁ ነው፡፡ ⏩ #ብጉርን #ምን #ሊያባብሰው #ይችላል? 🔺 የሆርሞን መለዋወጥ ወይም መዛባት 🔺 አንዳንድ መድሐኒቶች 🔺 አመጋገብ (የተጠበሱ ምግቦች፣ በካርቦሀይድሬት የበለፀጉ ምግቦች) 🔺 ጭንቀት ወይም ውጥረት 🔺 ሸካራ ሳሙና መጠቀም እና በጣም የሞቀ ውሃ መጠቀም 🔺 የፀጉርና ቆዳ መጠበቂያ ውጤቶች በተለይ በውስጣቸው የሚያሳክክ ንጥረ ነገር የያዙ ከሆነ ⏩ #ተጋላጭነት #የሚጨምሩ #ሁኔታዎች 🔺 የጉርምስና የእድሜ ክልል 🔺 የሆርሞን መዛባት 🔺 የዘር ተጋላጭነት 🔺 ቅባትማ ነገሮችን በቆዳ ላይ መጠቀም 🔺 ቆዳን የሚፈገፍጉ (የሚፈትጉ) ነገሮች 🔺 ጭንቀት ⏩ #ብጉርን #መከላከል #ይቻላል? 🔺 ብጉርን በዘላቂነት መከላከል ባይቻልም እንዳይባባስ የሚወሰድ እርምጃዎችና ጥንቃቄዎች ግን አሉ። ከነዚህም መካከል፦ 🔺 በዝግታ ወይም በጣም ሳያሹ መታጠብ ለቆዳዎ ጤንነት አስፈላጊ ነው። በጣም ማሸት፣ መጥረግ፣ መፈተግ ወይም መፈግፈግ ተገቢ አይደለም። 🔺 በጣም እንዳያልብዎ መጠንቀቅ። ላብ እንዲያልበን የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎች ካደረግን በኋላ ወዲያው መታጠብ። 🔺 ፀጉርዎ ቅባት ካለው ወይም ከበዛበት መታጠብ 🔺 ጭንቀትን አለማብዛት 🔺 አንዳንድ የፀጉር መንከባከቢያ ምርቶችን መጠቀም ማቆም፤ እንደ ጄል፣ ክሬምና የመሳሰሉት 🔺 ፊትዎን ቶሎ ቶሎ ከመንካት መቆጠብ 🔺 ለስላሳ የኮተን ልብሶችን መጠቀም፤ በተለይ ከቆዳ ጋር ንክኪ ያላቸው ከሆነ 🔺 ከቅባት እና ኬሚካል ጋር ያለዎትን ግንኙነት መቀነስ ለምሳሌ እንደ ፔትሮሊየም ያሉትን 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ‼️ ሌሎች እንዲጠቀሙበት በቅንነት ሼር ያድርጉ!! @DrJano @DrJano @DrJano @DrJano

ሰላም ውድ ዶ/ር ጃኖ ቤተሰቦች በቅርቡ ላይቨ በቴሌግራም ጥያቄ ና መልስ ለማዘጋጀት አስበናል ለዚህም እንዲረዳ ግሩፖችንን እና ቻናሉን እንድትቀላቀሉ በአክብሮት እጠይቃለሁ!! ግሩፕ : @DrJanogp ቻናል : @Drjano ግሩፓችን ላይ ሰው አድ በማድረግ ተባበሩን

✍️ #በጨጓራ #ውስጥ #ከመጠን #በላይ #የአሲድ #መመንጨት 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #አነሳሽ#ምክንያቶች 🔺 ብዙ ምግብ መመገብ ወይም ከተመገቡ በኃላ ወዲያውኑ ጋደም ማለት 🔺 ከልክ ያለፈ የሰውነት ክብደት 🔺 ከባድ ምግብ ተመግበው በጀርባ መተኛት ወይም ወዲያውኑ አጎንብሰው ስራዎችን መስራት 🔺 በመኝታ ጊዜ ምግብ መመገብ 🔺 ውጥረት ወይም ጭንቀት 🔺 አሲድ ያላቸው እንደ ብርቱካን እና ሎሚ ፍራፍሬዎችን መመገብ፣ከዚህ በተጨማሪ ቲማቲም፣ቸኮሌት፣ነጭ እና ቀይ ሽንኩርት ወይም ቅመም ወይም ቅባት ያላቸውን ምግቦች መመገብ 🔺 የአልኮል፣የለስላሳ እና ካፌንነት ያለባቸው ቡናና ሻይ ምግብዎችን መመገብ መጠጦችን እና ምግቦችን መውሰድ 🔺 ሲጋራ ማጨስ 🔺 ነፍሰጡር መሆን 🔺 አንዳንድ መድኃኒቶች እንደ አስፕሪን፣አይቢፕሮፍን፣አንዳንድ የጡንቻ ማፍታቻ ወይም የደም ግፊት ሕክምና መድኃኒቶችን መውሰድ 🔺 ቅመማ ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ ⏩ #ምልክቶች 🔺 የማቃጠል ህመም ስሜት ከጨጓራ ተነስቶ እስከ ደረት አልፎም ጉሮሮ ጋር የሚደርስ ቃር 🔺 መራራ አሲድ ወደ ጉሮሮ ወይም አፍ መድረስ 🔺 ሆድ መነፋት 🔺 ደም ወይም ጥቁር ነገር የቀላቀለ አይነምድር 🔺 ደም የተቀላቀለ ትውከት 🔺 ማግሳት 🔺 ምግብ ያለመፈጨት ችግር 🔺 ስቅታ እና ማቅለሽለሽ 🔺 ያለምንም ምክንያት ክብደት መቀነስ 🔺 ደረቅ ወይም ፉጨት ያለው ሳል ወይም ዘላቂ የጉሮሮ ቁስል 🔺 የጆሮ ሕመም ⏩ #መፍትሔው 🔺 ቅመም የገባበትና ማጣፈጫ ያለበትን ወይም የተጠበሰ ምግብ ማስወገድ 🔺 አልኮል መጠጦችን እና ካፌንነት ያላቸውን መጠጦችን ማስወገድ 🔺 ወተት ይጠጡ 🔺 ሙዝ፣ ማንጎ፣ ሀብሀብ፣ ፓፓዬ እና ቴምር ያዘውትሩ 🔺 ምግብዎን ቶሎ ቶሎ አይመገቡ (በደንብ አኝከው ይዋጡ) 🔺 በቀን ከ2.5 ሊትር በላይ ውሃ ይጠጡ 🔺 ጣፋጭ ፣ቆምጣጣ ምግብዎችን አይመገቡ 🔺 በእግር መሄድ ያዘውትሩ 🔺 በተቻለ መጠን ደስተኛ ይሁኑ (ጭንቀት ያስወግዱ) 🔺 በህክምና ባለሞያ የታዘዘ የፀረ-አሲድ መድሃኒት መውሰድ ✅ ለተጨማሪ የጤና መረጃዎች ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇 https://t.me/+6X9O71L_Vu1iY2Y0

✍ #የማህጸን #ቱቦ #መዘጋት 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን 👉👉 #የማህፀን ቱቦ መዘጋት የተለመደ የመካንነት መንስኤ ነው።የማህጸን ቱቦ ስፐርም ህዋስ እና እንቁላል የሚገናኙበት እና የሚዳብርበት የማህጸን ክፍል ነው። የተዘጋ የማህጸን ቱቦ ስፐርም ህዋስ እና እንቁላል እንዳይገናኝ ሊያደርጋቸው ይችላል። 👉👉 #ሁለቱም ቱቦዎች ሙሉ በሙሉ ከተዘጉ, ያለ ህክምና እርዳታ እርግዝና የማይቻል ይሆናል:: የማህፀን ቱቦ በከፊል ከተዘጋ ወይም አንዱ ቱቦ ብቻ ከተዘጋ እርግዝና ሊፈጠር ይችላል። ይሁን እንጂ ከማህጸን ውጭ እርግዝና አደጋ ይጨምራል፡፡ 👉👉 #የማህጸን #ቱቦ #መዘጋት #ሊያስከትሉ #የሚችሉ #መንስኤዎች 📌 የዳሌ አካባቢ እና የማህጸን ኢንፌክሽን 📌 የአባላዘር በሽታ 📌 የፈነዳ ትርፍ አንጀት 📌 የማህጸን ህዋስ የማህጸን ቱቦ ላይ ሲያድግ 📌 የማህጸን የዉስጠኛዉ ክፍል መጣበቅ 📌 የሆድ ቀዶ ህክምና ከነበረ 📌 ከማህጸን ዉጭ እርግዝና ከነበረ 📌 ተደጋጋሚ ዉርጃ ከነበረ 👉👉 #የማህጸን #ቱቦ #መዘጋት #ሲኖር #የሚታዩ #ምልክቶች 📌 የዳሌ አካባቢ እና የታችኛዉ የሆድ ህመም 📌 በግንኙነት ወቅት ህመም 📌 ሽታ ያለዉ የማህጸን ፈሳሽ 📌 ከፍተኛ ትኩሳት 📌 ማጥዎልወል እና ማስመለስ 📌 የወር አበባ መዛባት 📌 መዉለድ አለመቻል 👉👉 #ለማህጸን #ቱቦ #መዘጋት #የሚደረግ #ህክምና 📌 የማህጸን ቱቦ ላይ ያለዉ ጠባሳ ትንሽ ከሆነ የማህጸን ቱቦ ተከፍቶ ጠባሳዉ በቀዶ ህክምና እንዲወገድ ይደረጋል፡፡ 📌 የማህጸን ቱቦ ላይ ያለዉ ጠባሳ ከተባባሰ በመጠን ትልቅ ከሆነ ሙሉ በሙሉ ተቆርጦ እንዲወጣ ይደረጋል፡፡