cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የዑለሞቻችን መንገድ

አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱ ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች እንኩዋን ደህና መጡ የዑለሞቻችን መንገድ ይሄ ቻናል የረሱልን መሀባ ያስተማሩንን ዲኑ ለእኛ እንዲደርስ አስተዋፆ ያደረጉልንን ዑለሞች ማወቂያ ና ስለ እነሱ ያለዉን የተሳሳተ መረጃ ማስወገጃ እንዲሁም መንዙማዎችን ከአካቢሮች የሰማናቸውን ቀሰሶች የምንማማርበት ነው! https://t.me/joinchat/DK2Idf3spn0yN2Vk

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
186
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailable
አሰላማለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ውዶች እነሆ መውሊዱ እየደረሰ ስለሆነ ሁላችንም ከአሁኑ ዝግጅት ማድረግ አለብን ❤️ ኢንሻአላህ እኛም ብዙ ዝግጅት እኛደርግን ነው በቅርቡ ወደ እናተ የምናደርስ ይሆናል በሆኑም አሁን ላይ በፌስቡክ ላይ አዲስ ቻሌንጅ ጀመረናል ሁለችንም መውሊድ ከመድረሱ በፊት ሰው ለመውሊዱ እንዲዘጋጅ መውሊዱን ለመሳታወስ እና ስለመውሊዱ ትምህርት እንዲኛገኙ የምናደርግበት ቻሌንጅ ነው ስለሆነም ሁላችንም ስለ መውሊዱ ይጠቅማል የምትሉትን ፖስት በመፖሰት ቻሌንጁን ይቀላቀሉ እናም ሁላችኝም ፌስፑክ ላይ ከምንፖስተዎ ፖስት ከላይ መፃፊያው ላይ የመሰላልን ምልክት # ነክተን ከዛም በእንግሊዝኛ #mewlidchallenge ብለን በመፃፍ ቻሌጁን እንቀላቀል በተጨማሪም ምንፖስተው ፖስት ከመውሊድጋ የተያያዘ እና ኢስላማዊ መሆን አለበት ያለግባቹን በውስጥ መስመር ጠይቁን ለመጠይቅ 👉 @Specialiol #mewlidchallenge
Mostrar todo...
Live hadra geb geba belu 👆👆👆👆👆
Mostrar todo...
አመት ኡደቱን ገጥሞ አዲሱን ለመቀበል ስናሰፈስፍ የአመቱን ጅማሮው በረሱለሏህ ዐለይሂ ሰላት ወሰላም ሂጅራ እናጅበዋለን። ረሱለሏህ እውነትን ይዘው በይፋ መጣራት ከጀመሩበት ዕለት አንስቶ የተለያየ ስም ወጣላቸው። ደጋሚ፣ ገጣሚ...እብድ ተባሉ። በጣኢፍ ላይ በድንጋይ ተደበደቡ። ላንዷ የደም ጠብታቸው ፊዳ ይሁንና አናትም አባቴ። መለኩ ጂብሪል የተራራ መላዒኮችን ከፈለጉ እንዲያዟቸውና ህዝቦቹን በተራራዎች መሀል ማጥፋት ካሻችሁ ይሀው አላቸው። ራህመት ተደርገው የተላኩት ነብይ ግን ስለራሳቸው ህመምና ስቃይ ሳይሆን ስለ ህዝባቸው መዳን ነበርና ሚያስጨንቃቸው..."ተዋቸው ከልጅ ልጆቻቸው እኔን የሚከተል ይኖራልና" ነበር መልሳቸው። .... ለአስራ ሶስት አመታት ህዝቡን ወደ አሏህን አንድነትና የርሳቸውን መልዕክተኝነት እንዲቀበሉ ጥሪ ሲያደርጉ ቆዩ። አመታቶች በሄዱ ቁጥር ሙሽሪኮች ስቃይና እንግልቱን በደካማ አማኞች ላይ ማበርታቱን ተያያዙት። ረሱለሏህ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በፅናት እየመከሯቸው በጀነት እያበሰሯቸው ሰነባበቱ። ...እያንዳንዱን ተግባርና ንግግር ከአሏህ በሆነ ራዕይ የሚተገብሩት ነብይ ለሂጅራ/ስደት ተነሱ። ለዲን ብሎ የመሰደድን ደረጃ ከፍ ሊያደርጉት ተሰደዱ። እርሳቸው ያደረጉት ማንኛውም ተግባርና ምግባር በእርሳቸው ይልቃልና። .... በሂጅራው አብሯቸው የነበረው አፍቃሪስ...ያ "የሁሉንም ሰው ውለታን መልሰናል፡ የአቡበክር ሲቀር..." ብለው ረሱለሏህ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም የተናገሩለት። ያ የርሱ ኢማንና የኡመቱ በአንድ ሚዛን ቢመዘን የርሱ ሚያጋድለው። ሳያመነታ ቀድሞ ያመናቸው ወዳጅ። በጉዞዋቸው ላይ አብሮነትን የታደለ። አብረው እየሄዱ አቡበክር አንዴ ከረሱለሏህ(ዐሰወ) ፊት ይሆናሉ ከዛም ከኋለቸው፣ ትንሽ ይቆዩና ከበስተቀኛቸው፣ ከዛም በስተግራ በኩል እያሉ የአለሙን ራህመት በአራቱም አቅጣጫ ይዞሯቸው ጀመር። ስለ ድርጊታቸው ሀቢባችን ሢ።ጠይቋቸው...ከፊት ጠላት ሚመጣ ይመስለኝና ከናንተ በፊት ከኔ ጋር እንዲጋፈጥ እልና ከፊት እሆናለሁ ደግሞ ከኋላስ ቢመጣ እልና ወደኋላ እሆናለሁ...በቀኝና በግራ በኩልም ሊመጣ ይችላልና በዚም በዛ ምለው ለዚ ነው ወለላዬ ነቢ! ...ስስቴ ኖት እያሏቸው ነው በተግባር። ደግሞ በዛ ዋሻ /ጋሩ ሰውር/ ስስታቸውን ከታፋቸው አኑረው ጋደም እንዲሉ ካመቻቹላቸው ኋላ በእባብ ስለመነደፋቸው። ከራሳቸው ህመም በላይ የሀቢቤዋ ከተኙበት ያለ ፍላጎታቸው መቀስቀስ ሚታመሙት ሲዲቁ፣ አቃጣይ ህመሙን ውጠው በዝግታ ማንባት የጀመሩበቱ። ላንዷ ጠብታቸው ፊዳ ልሁንላቸውና..። የተፈቃሪያቸው ጉንጭ ላይ በዝግታ በሚፈሳቸው የእንባ ጠብታ ነቅተው በቱፍታቸው አሽረው...በ "ላ ታህዘን" ስጋትና ፍርሀታቸውን ያሶገዱበት ክስተት። .... ደግሞ ወድያ ማዶ የአለሙን ራህመት ለመቀበል ሽር ጉዷን የጀመረችው የስሪብ/ጦይባ። የፋናቸውን እትም ለማኖር ስትቋምጥ። በሀቢቡ ናፍቆት የተጠማች መሬት፡ መዋቧንና ማሸብረቋን በመምጣታቸው ልታውጅ አሰፍስፋ ምትጠብቃቸው። ህዝቦቿም እየመጣላቸው ያለውን ማይጠልቅ ጀምበርን ሊቀበሉ ትዕግስት አጥተው መምጫቸውን በጉጉት የተጠባበቁት፡ በዘምባባ አናት ላይ ተንጠላጥለው እይታቸውን ከመምጫቸው ያንከራተቱ። ነብያችንን ከሩቅ ሲያዩ እንዴት ያለ ስሜት ተስምቷቸው ይሁን። ልባሸውስ ከተጠለጠሉበት ዘንባባ ዘላ መውረድን አልተመችም? በ "ጠለዐል በድሩ አለይና" ታጅበው ዱፉን እየደለቁ አርሂቡልና ሀቢቡና ኑልን ነቢና እያሉ አቀባበል ያደረጉበት። መዲና የተነወረችበት/የተዋበችበት መደማመቋን የጀመረችበት ዕለት። :ሂጅራ...! ሙሀረም 1/1/1444 ~~~~ https://t.me/+Thgs_FEJ8KISTVm9
Mostrar todo...
Photo unavailable
በሂጅራ አቆጣጠር ዛሬ የአመቱ መጨረሻ ነው ከላይ ያለዉን ዱዓ ሶስት ጊዜ እንቅራ
Mostrar todo...
Photo unavailable
دعاء اخير السنة.pdf የአመቱ መጨረሻ የሚደረግ ዱዓ ዛሬ ጁሙዓ የ1143ተኛ ሒጅራ የመጨረሻው ቀን ነው። ጊዜ አመቻችተን ከመግሪብ በፊት እንቅራው። በአመቱ ውስጥ ለሰራናቸው ወንጀሎች በአጠቃላይ ተውበት እናድርግ። የሚመጣውም መልካም እንዲሆንልን ዱዓ እናድርግ ዳሩል ሒጅረተይን የዒልም ማዕከል ሀላፊ https://t.me/DaralHijrataynIslamicSchool
Mostrar todo...
دعاء اخير السنة.pdf3.76 KB
Photo unavailable
{ وَمَا جَعَلْنَا لِبَشَرٍ مِّن قَبْلِكَ الْخُلْدَ أَفَإِن مِّتَّ فَهُمُ الْخَالِدُونَ * كُلُّ نَفْسٍ ذَآئِقَةُ الْمَوْتِ وَنَبْلُوكُم بِالشَّرِّ وَالْخَيْرِ فِتْنَةً وَإِلَيْنَا تُرْجَعُونَ } سورة الأنبياء «(ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለማንም ሰው ዘለዓለም መኖርን አላደረግንም ፡፡ ታዲያ ብትሞት እነሱ ዘውታሪዎች ናቸውን ?! ..ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን፡፡ ወደኛም ትመለሳላችሁ » ፡========================== እዚች ዱንያ ላይ አንዳች ነገር ዘውታሪ እንዲሆንልህ አትጠብቅ .. እራሷ ዱንያም ጊዜያዊ ናት ! አላህ በወደዳቸውና ባከበራቸው ባርያዎቹ በረካ ኻቲማችንን ያሳምርልን ። ሸይኻችን ሰዪዲ አል-ሐቢብ አቡበክር አል-መሽሁር አል-ዐደኒ'ይንም አስደሳች ነገር ሁሉ ዘውታሪ በሆነባት የጀነት ሀገር ድጋሚ አይናቸውን የማየትና እግራቸው ስር የመቀመጥን እድል አላህ በረሕመቱ ይስጠን https://t.me/mededulhabib
Mostrar todo...
Photo unavailable
በደእና ቢስሚሂ ወረፋዕነል ቀለም ተዐለቅና ቢሂ ነፉዙ ለም ነስቀም ሰላም አለይኩሙ ባቡሏሂል አእዘም ተገረምና ለከ ወወጀድነል ከረም አወይ ፍቅር መርዶ አወይ መራቅ እሳት ትልቅ ሠው ወድጄ ልቤን እያመሳት በትዝታው ጥሎኝ አልሆነኝ መነሳት ቀርቦም አላከመኝ የልቤን ትኩሳት ጦይባ የተባለች ሸጋ ልጅ ወድጄ በትርክቷ ክራር ገላዋን ለምጄ ጠብቄያት ቀን ሌቱን እ ርቄ ተደጄ ተድራለች ቢሉኝ ቀረሁኝ ነድጄ ፡ሠላም አለይኩሙ ያ ኢማመል ሓረም ምን ጠቅሞሽ እምባዬ አንቺ ደጓ ጦይባ ተናፍቆትሽ ፍቺኝ አልያም ቀየሽ ልግባ ሠብረሽ በትዝታ አርገሽኝ ማልረባ ብጠጣም አልረካ ብበላም አልሰባ እድሉን ብትሰጪኝ አንቺ ደጓ ጦይባ ልቤ እንዲህ ይልሻል አይኔም እያነባ ዘመን እኔን ገድሎ በኔው ሳያደባ አይኔ አይንሽን ትየው ትዝራ ህይወት ቀርባ ሠላም አለይኩሙ ያ ኢማመል ሃረም ሰላም ይድረሶት ሆዴ💚 _______________ https://t.me/+Thgs_FEJ8KISTVm9
Mostrar todo...
02:04
Video unavailable
:شعراوي❤
Mostrar todo...
11.88 MB
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.