cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Holy Spirit

Holy sprit channel is created for every one in our world to preach word of God @Theholysprit

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
1 765
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

🌻🌻የ መስቀል በዓል 🌻🌻 "፤ የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና። " (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1: 18) 👉ስለዚ የመስቀሉ ቃል የማንደራደርበት የመዳን እና ያለመዳን ጉዳያችን ነው 👉ግን የመዳናችን ዋስትና መስቀሉ(እንጨቱ) ወይስ ቃሉ 👉ከ ቀደምት ኢትዮጵያዊ አባቶቻችን ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው መስቀሉን(እንጨቱን) የማምለክ የመሳም እና እንደ ትልቅ የ እምነት መሰረት ማየት 👉እኔ ግን ዛሬ ስለ መስቀሉ ሳይሆን ስለ መስቀሉ ቃል ልንገራቹ 👉ያ የመስቀሉ ቃል በ ዩሀንስ ወንጌል ላይ "፤ በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። " (የዮሐንስ ወንጌል 1: 1) 👉ስለዚህ ያ ቃል እየሱስ ነው የመስቀሉ እየሱስ ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚያብሔር ኃይል ነው። 👉ስለዚ እኔ መስቀል(እንጨት) በመያዝ የማከብረው በዓል የለኝም ቃሉን(እየሱስን) በመየዝ እንጂ። 🙏ወንድሞቼ እህቶቼ እኔ መስቀሉን ሳይሆን መስቀሉ ላይ የተሰራልኝን ስራ እያየው እያሰብኩ ቀኑን አሳልፋለው። ቃሉ እንደሚለን እንመላለስ ከ ወንድማቹ ቢኒያም share this message for holy day gift
Mostrar todo...
Join our channel @Theholysprit @Theholysprit
Mostrar todo...
ፅሁፉን ከወደዳችሁት like በማድረግና ለሌሎች ሰዎች share በማድረግ ትውልድ እናድን @Theholysprit @Theholysprit
Mostrar todo...
❤ 12
✝ 8
👍 14
<<ለቸርነቷ ልማድ ወሰን የለውም>> መጽሐፍ ቅዱስ በቸርነቱ ወደር የሌለው እግዚአብሔር መሆኑን ‹‹ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል÷ በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ››፣ ‹‹የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ነው። ቃል ኪዳኑንና ምስክሩን ለሚጠብቁ›› ‹‹በአንተ ለሚያምኑ በሰው ልጆች ፊት ያዘጋጀሃት ለሚፈሩህም የሰወርሃት÷ ቸርነትህ እንደ ምን በዛች!›› በማለት ያስነብባል (መዝሙር 23፡6፤ 25፡10፤ 31፡19)፡፡ ቸር የሚለው ቃል ትርጉም ‹‹የሚሰጥ፣ ለጋስ፣ አባ መስጠት፣ እጀ ሰፊ›› የመኒል በመሆኑ ከሰዉ ልጆች መካከል በልዩ ልዩ ቸርነት ውስጥ ሊገለጡ የሚችሉ ሰዎች ሞለተዋል፡፡ ነገር ግን ደካማ የሰው ልጅ በመሆናቸው ቸርነታቸው ፍጹም አይደለም፡፡ በአንዱ ቸር ቢሆኑ በሌላው ንፉግ (ስስታም) ሆነው ይታያሉና፡፡ ለቸርነቱ ወሰን የሌለው እግዚእሔር አምላክ ብቻ ነው፡፡ የገድለ አርሴማ ጸሐፊ ግን ይህን የእግዚአብሔርን ባሕርይ ለፍጡር ለመስጠት እጁ የታዘዘለት ሰው ነው፡፡ ሐሳንም ‹‹ቅዱሳን ሰማዐት በምድር እንደሚወርድ እንደ ዝናብ ነጠብጣብ ስለሆነው ስለ ሥቃይዋና ግፍዋ ብዛት ይደሰቱባታል፡፡ ለግፍዋ መጠን ቊጥር የለውም፡፡ ለቸርነቷ ልማድም ወሰን የለውም፡፡ የእግዚአብሔር ነገሩንማ ጥበቡ ዕፁብ ድንቅ ነውና›› በማለት አስፍሮታል፡፡ ጸሐፊው በዚህ ስፍራ ወደ ምድር በሚወርድ የዝናብ ነጠብጣብ የመሰለው ስቃይዋና የደረሰባት ግፍ ብሎ ያስቀመጠው ምን እንሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ መጽሐፉን ባነበብኩበት ወቅት በዚህ መጠን የሚገለጸ ሥቃይና ግፍ ቀርቶ ሰማዕትነትን ከመቀበሏ ውጪ የደረሰባት ነገር አላየሁም፡፡ ከዚህ ይልቅ ግን ምንም እንኳ ሥቃይና ግፍ ደረሰባት ቢባልም ሥቃይና ግፍ ስታደርስ የምትታየው እርሷ ናት፡፡ ለዚህም በገድሉ ላይ፤ ቡርክት አርሴማም መለሰችለት በጌታዬ ላይ የስድብ ቃል ከምሰማ፤ ልገድልህ በወደድሁ ነበር፡፡ ወይም ሞት በተሻለኝ ነበር፡፡ ድርጣድስም ልጇን ስታበረታታ በሰማ ጊዜ የእናትዋን የዐጋታንና የቀወድስት አርሴማን ጥርሶች ይሰበሩ ዘንድ አዘ፡፡ እግዚእሔር ግን በንጉሥ ድርጣድስ ላይ ኀይልንና ብርታትን ሰጣት፡፡ እርሱ በፀብ ኀይለኛና የታወቀ፣ ፈጽሞም የበረታ ሲሆን፣ ወደ ኋላው ጣለችውና በምድርም ጎተተችው፡፡ ያን ጊዜም ንጉሥ ድርጣድስ በወታደሮቹ ት በብፅዕት ቅድስት አርሴማ ስለተሸነፈ አፈረ፡፡ ቡርክት አርሴማም መለሰለችለት፡፡ እንዲህም አለች፤ ፊቷን በጥፊ ወደ መታት ወደዚህ ንጀለኛ ላይ፣ በእጇ ጣት በትእምርተ መስቀል እያማተበች፣ ፊቷን በጥፊ የመታት፣ ያ ወንጀለኛ ሕያው እንደሆነ ወደ ሲኦል ይወርድ ዘንድ፣ ምድርም አፏን ትከፍትና እንደ ዳታንና አንደ አቤሮን ትውጠው ዘንድ ወደ ፈጣሪዋ ለመነች፡፡ እንደ ብፅዕት አርሴማ ቃልም ሆነ፡፡ በሰጠመበትም ላይ ዘጋችው፡፡ ቅድስት አርሴማ ያደረገችውን ይህን ተኣምር ያዩ ከወታደሮች ብዙዎቹ ሸሹ፡፡ ንጉሡም ይሸሽ ዘንድ ከዙፋኑ ተነሣ፡፡ ያን ጊዜም ቡርክት አርሴማ ፈገግ አለች፡፡ ቅዱሳን ሰማዕትም ስለ እርስዋ ተደሰቱ፡፡ መላእክት በላይዋ ሲከቡአት አይተዋልና፡፡ ተብሎ ተጻፈውን መመልከት ይቻላል፡፡ በእነዚህ ምንባባት ውስጥ ‹‹ልገድልህ በወደድሁ›› በማለት እሷ እየተሰቃየች ሳይሆን ዛቻ እያቀረበች መሆኑን፣ ንጉሡን መሬት ላይ ጥላ እንጎተተችው እና የንጉሡን ወታደር ‹‹ሕያው እንደሆነ ወደ ሲኦል ይወርድ ዘንድ›› ቃል በማውጣት ‹‹ሕያው እንደ ሆነ›› ምድር እንድትውጠው በማድረግ ደስ እንደተሰኘች (‹‹ያን ጊዜም ቡርክት አርሴማ ፈገግ አለች›› ተብሎ ተጽፋልና) የተመለከተ ልባም አንባቢ እንደ ዝናብ ነጠብጣብ የሆነው መከራዋ የቱ ነው ደግሞ እንዲህ ብዙ የሆነ ሥቃይና ግፍ ሲያደርጉባት ወሰን የለውም የተባለው ቸርነቷ ምንድን ነው ብሎ ይጠይቃል @Theholysprit
Mostrar todo...
አንድ ወዳጄ ገድለ አርሴማን እያነበብኩ አየኝና ‹‹እኔ የምልህ አርሴማ ከመቼ ጀምሮ የመጣች ቅድስት ነች?›› ሲል ጠየቀኝ፡፡ ከዚህ በኋላ በተለያየ አጋጣሚ ያገኘኋቸውን የቤተ ክርስቲያን አባቶችና ወጣት አገልጋዮችን የወዳጄን ጥያቄ ጠይቄ ነበር፡፡ በሚገርም ሁኔታ የሁሉም መልስ ተመሳሳይ ነበር፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ግን የአንድ አባት መልስ ሐሳቤን ይገልጥልኛልና የእሳቸውን ንግግር ቃል በቃል ለማስቀመጥ ልሞክር ‹‹አይ አንተ! ከመቼ ጀምሮ እንደገባችና ማን እንዳመጣት እንኳ የማትታወቅን ሴት ቅድስት ትላለህ እንዴ?›› ነገሩ እንዲህ ሆኖ ሳለ አሁን አሁን አርሴማ ከቅዱሳን ወይም ከሰማዕታት አንዷ ብቻ ሳትሆን ልቃ እና ገና የምትታይ ሆናለች፡፡ ይህንንም ብዙዎች አብያተ ክርስቲያናትና አድባራት በደባልነትም ቢሆን ታቦተ አርሴማን በማስገባት ላይ መሆናቸውን ማስተዋል ይቻላል፡፡ ከዚህም ሁሉ በላይ ለአርሴማ ተብሎ የተመረጠው ቀን ስድስት መሆኑ ከሠላሳው ቀናት አንዴ (በወር ውስጥ አንዴ) ብቻ ስሙ ይጠራ የነበረውን ኢየሱስን ሙሉ በመሉ ለመሸፈን የተሠራው ሥራ ውጤታማ መሆኑን ያሳያል፡፡ ይህም ደግሞ ኢየሱስ የሚለውን ስም የማይወደው ጠላት ስሙን ከቤተ ክርስቲያን ለማስወጣት እየሠራ ያለው ሥራ አንዱ አካል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ዛሬ በቅዱሳን ስም በማደብዘዝ ላይ ሲሆን ነገ ደግሞ…፡፡ ለስመ ኢየሱስ ፍቅር ያላቸው የቤተ ክርስቲያን አባቶች እና አገልጋዮች ‹‹እነርሱም ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ ተቈጠሩ ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ›› የሚለውን ቃል በማስታወስ ስለ ስሙ ሊናቁ እንጂ ስሙ ሲናቅና በሌላ አካል ሲሸፈን ዝም ብለው ሊመለከቱ እንደማይገባ ሊያስተውሉ ይገባል (የሐዋርያት ሥራ 5፥41)፡፡ ከእርሱ ውጪ ማንም የለንም፤ ከእርሱም ሌላ በሕይወታችን ላይ ልናነግሠውም ሆነ ስፍራ ልንሰጠው የምንችለው አካል የለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ከእርሱ ሌላ ማንም በሕይወታችን ላይ ቦታ እንዲኖው አይፈቅድም፡፡ ስለዚህም ወቅትና አጋጣሚ እየጠበቁ የሚመጡ ‹‹ቅዱሳን›› የእርሱን ቦታ እንዲይዙና ስፍራውን እንዲቆጣጠሩት መፍቀድ አይኖርብንም! አለበለዚያ ግን ከፈቃደ እግዚአብሔር ውጪ እየኖርን ነው ማለት ነው! @Theholysprit
Mostrar todo...
በወቅቱ ልትሰሙት የሚገባ መልክት ለክርስቲያኖች በሙሉ ለዘመድ ወዳጆቻችሁ አስተላልፉ @Theholysprit @Theholysprit
Mostrar todo...
6.50 KB
መንፈስ ቅዱስ ሆይ ካንተ ውጪ ሌላ መሻት የለንም ፡፡እኔ ምፈልገው አንተን ነው፡፡ join us @Theholysprit @Theholysprit @Theholysprit we always talk about holy spirit 🇪🇹✝🇪🇹✝🇪🇹✝🇪🇹✝🇪🇹✝🇪🇹✝✝✝✝
Mostrar todo...
Holy spirit pls come and change this atmosphere we need u more than any thing
Mostrar todo...
🌻🌻የ መስቀል በዓል 🌻🌻 "፤ የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና። " (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1: 18) 👉ስለዚ የመስቀሉ ቃል የማንደራደርበት የመዳን እና ያለመዳን ጉዳያችን ነው 👉ግን የመዳናችን ዋስትና መስቀሉ(እንጨቱ) ወይስ ቃሉ 👉ከ ቀደምት ኢትዮጵያዊ አባቶቻችን ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው መስቀሉን(እንጨቱን) የማምለክ የመሳም እና እንደ ትልቅ የ እምነት መሰረት ማየት 👉እኔ ግን ዛሬ ስለ መስቀሉ ሳይሆን ስለ መስቀሉ ቃል ልንገራቹ 👉ያ የመስቀሉ ቃል በ ዩሀንስ ወንጌል ላይ "፤ በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። " (የዮሐንስ ወንጌል 1: 1) 👉ስለዚህ ያ ቃል እየሱስ ነው የመስቀሉ እየሱስ ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚያብሔር ኃይል ነው። 👉ስለዚ እኔ መስቀል(እንጨት) በመያዝ የማከብረው በዓል የለኝም ቃሉን(እየሱስን) በመየዝ እንጂ። 🙏ወንድሞቼ እህቶቼ እኔ መስቀሉን ሳይሆን መስቀሉ ላይ የተሰራልኝን ስራ እያየው እያሰብኩ ቀኑን አሳልፋለው። ቃሉ እንደሚለን እንመላለስ ከ ወንድማቹ ቢኒያም share this message for holy day gift
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.