cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

🌴🌴የጀነት ጨፌ🌴🌴

በአላህ ፍቃድ በዚ ቻናል 🔶አስተማሪ ቂሷዎች 🔶ሀዲሶች 🔶ፈገግታ 🔶አነቃቂ ምክሮች 🔶አለማቀፍ Islamic መረጃ 🔶ሀላል መዝናኛ 🔶Islamic ስነፅሁፎች 🔶 እና ሌሎችም.... @yejenetchefa_bot

Mostrar mĂĄs
El paĂ­s no estĂĄ especificadoEl idioma no estĂĄ especificadoLa categorĂ­a no estĂĄ especificada
Publicaciones publicitarias
457
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 dĂ­as
Sin datos30 dĂ­as

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ሸይኽ ሐሰን ታጁ ኢብን ሸይኽ ለጋስ ሐፊዘሁላህ ------------------------------------------------------------ ከዛሬ 106 ዓመታት በፊት ጎንደር ውስጥ ታዋቂ የሆነ ቄስ በእባብ ተነድፎ ወደ ሸይኽ ለጋስ ዘንድ መጣ፡፡ ቀዬውም በእኒሁ ታላቅ ሸይኽ ስም "የሸይኽ ለጋስ መንደር" በመባል ይታወቅ ነበር። የሸይኽ ሐሰን ታጁ አያት ዘንድ ማለት ነው። በዚህ አጋጣሚ እስከዛሬ ድረስ በፕሮግራም መድረክ ላይ እንኳን ከቴሌቭዥን መስኮት ውጭ አይቻቸው ከማላውቃቸው የሀገራችን ብርቅዬ ዐሊሞች ውቅጥ አንዱ ሸይኽ ሐሰን ታጁ ነው። . የጎንደር ቀሳውቅስት እስልምናን እንደሚጸየፉ ሸይኹ ያውቃሉ፡፡ በተለይም ሙሐመድ የሚለውን ስም መስማት አይፈልጉም፡፡ ሸይኹ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ቀሳውስቱ ነቢዩን እንዲጠሩ ማድረግ ፈለጉ፡፡ ውሃ በስኒ አቀረቡና፡-“ባልንጀራችሁ እንዲፈወስ ከፈለጋችሁት እዛዜን በጥሞና አድምጡ፡፡ ሳታዛንፉም ፈጽሙ፡፡ የዚህ ሰዉ ፈዉስ ከነብዩ ሙሐመድ ስም ጋር የተቆራኘ ነዉ፡፡ ስለሆነም የርሳቸዉን ስም በጋራ አንድ ሺህ ጊዜ ጠርታችሁ በስኒ ከተቀመጠዉ ዉሀ ዉስጥ ትፉበት፡፡ እርሱን ሲጠጣ ይድናል፡፡” አሏቸው፡፡ ይህ ትእዛዝ ለቀሳውስቱ ከባድ ነበር፡፡ መስማት የማይሹትን ስም ሊያወሱ፣ ከማውሳት አልፈው ሊያወድሱት? በሽተኛው ይንገበገባል፡፡ አፋጣኝ መፍትሔ ያስፈልገዋል፡፡ የታዘዙትን ካልፈጸሙ ሰዋቸዉ መሞቱ ነው፡፡ . እየመረራቸውም ቢሆን ሐላፊነቱን ተቀበሉ፡፡ መቁጠሪያቸውን ያዙና በጥንቃቄ የነቢዩን ስም መጥራት ጀመሩ፡፡ አንድ ሺህ ጊዜ ከጠሯቸው በኋላ ከስኒው ላይ ምራቃቸውን ተፉበት፡፡ ሸህ ለጋስም ከመድሐኒት ጋር በመቀላቀል ለበሽተኛው ሰጡት፡፡ በአላህም ፈቃድ ተፈወሰ፡፡ . ለቀሳውስቱም፡-“የተፈወሰው በነቢዩ ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በርሳቸዉ አምላክ በረከት ነው” ሲሉ አስተማሯቸው፡፡ ሸይኽ ለጋስ እንደ ቀድሞ ታላላቅ ከዋክብት ዑለሞቻችን በርካታ ገድሎችን ሰርተዋል። . . ከሸይኽ ሐሰን ታጁ ሐፊዘሁላህ መጽሓፍ የተወሳ @jenutelfirdews
Mostrar todo...
የቱርኮች ውህደት የኢራን የህልውና ስጋት ?? የቱርክ ፕሬዝዳንት የኤርዶጋን ንግግር እና መዘዙ ! #Ethiopian | ~ ባለፈው ኢራን ስለምን ከአዘርባጃን ይልቅ ለአርሜኒያ ወገነች በሚል ያሰፈርኩትን ፅሁፍ አስታወሳችሁት ? አዎ የኢራን ስጋት የቱርኮች ውህደት ነው ያን ውህደት ለማምከንና ለማጨናገፍ ስትልም ከአርሜኒያ ጎን በመሆን ኣዘርባጃን እንዳትረጋጋ ስታደርግ ቆይታለች ብያችሁ ነበር ። እነሆ አሁን ያ የኢራን ስጋት ስጋ ለብሶ ደልቦና ፋፍቶ ከፊት ለፊቷ ተደቀነ! ያ ለዘመናት ታንቆ የነበረ በኢራን የሚገኙ ቱርኮች የውህደት ፍም አሁን በኤርዶጋን አማካኝነት ተለኩሶ ሁለቱን ሀገራት ወደቃላት ጦርነት አስገብቷቸዋል። ኢራን በሀገሯ የሚገኘውን የቱርክ አምባሳደር ጠርታ ማብራሪያ ጠይቃለች ። ኤርዶጋንንም ተችታለች ። ቱርክም በአፀፋው በሀገሯ የሚገኘውን የኢራን አምባሳደር ጠርታለች። አሁን ሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል ። ለመሆኑ የቱርክ እና ኢራን የእሰጣገባ ቅፅበታዊ ምክንያት (Immediate cause ) ምንድን ነው? ሁላችንም እንደምናውቀው ከቀናት በፊት የአዘርባጃን የድል ቀን ሲከበር ፕሬዜዳንት ረጀብ ጦይብ ኤርዶጋን በክብረ በአሉ ላይ ተገኝተው ከፍተኛ ወኔ ቀስቃሽ ንግግር ማድረጋቸው ይታወቃል። ያ የአዘርባጃን ድል የመላው ቱርካዊያን ድል መሆኑንም አስምረው ቀጣዩ ስራ ቱርካዊያን ህዝቦችን ማዋሀድ ላይ እንደሚተኮር መግለፃቸውና በዚያም ስራ ላይ ፍንጭ የሚሰጥ ነገር መናገራቸው ይታወቃል። ቱርካዊያን ሲባሉ እንግድህ እጅግ ሰፊ መልክአምድርን የሚያካልሉ ፤ ከሜድትራኒያን ባህር እስከ ማእከላዊ ቻይና ድረስ የተዘረጉ ሰፊ ህዝቦች ናቸው። ቱርክሜኒስታን ፣ ቱርክ ፣ ኡዝቤክስታን ፣ ካዛኽስታን ፣ ኪርጊስታን ፣ አዘርባጃን ፣ ታጂኪስታን የመሳሰሉት ሀገራቶች ቱርካዊያን መሆናቸውን የምናውቀው ሀቅ ነው ። ይሁን እንጅ ቱርካዊያን እነዚህ ብቻ አይደሉም። ከኢራን አጠቃላይ ህዝብ 40 % የሚሆነው ቱርካዊ ነው ። በሶሪያ ከአረቦች ቀጥሎ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ቱርኮች ናቸው። እናም የቱርኮች አንድነት ሲታሰብ ካለነዚህ ህዝቦች አይታሰብም። የችግሩ ጥልቀት እዚህ ጋር ነው ! ኤርዶጋን በአዘርባጃን የድል ቀን ላይ ይህችን ግጥም አነበቡ " የ አራስ ወንዝን ለሁለት ከፈሉት እንዳንገናኝም በድንጋይ በአለት ጥቅጥቅ አርገው ሞሉት አልፈልግም ነበር ከናንተ መነጠል ከናንተ መለየት አስገደዱኝ እንጅ ነጣጠሉኝ እንጅ ተጠቅመው በገጉልበት " ትላለች የግጥሟ ስንኝ ። ይህ በኢራን ከፍተኛ ድንጋጤን እና ቁጣን ነው ያስከተለው ። የ አራስ ወንዝ በኢራን የሚገኙ ቱርኮችን እና በአዘርባጃን የሚገኙ ቱርኮችን የሚያገናኝ ወንዝ ነው ። እናም ኢራን ያንን ወንዝ ቆርጣ ነው ወደ ቱርኮችን ወደ ኢራን የቀላቀለቻቸው ። ይህ በኢራን የሚገኙ አዘርባጃን ቱርኮች የውህደት ጥያቄ ውስጥ ውስጡን ሲብላላ ቆይቶ ነው ዛሬ በኤርዶጋን አማካኝነት ወደ አደባባይ የወጣው ። እና ኢራንን ከዚህ በላይ ምን የሚያስደነግጣት ይኖራል? የኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሀመድ ጃቫድ ዛሪፍ እንደዚህ ተናደው የሚያውቁ አይመስልም። ለመደመሪያ ጊዜ በፐርሺያ ቋንቋ በፃፉት የትዊተር መልእክታቸው ኤርዶጋንን በቃላት ወርፈዋል ። ጃቫድ ዛሪፍ " ይህ ለእርሱ የሰጡት እና አርሱም በተሳሳተ መንገድ ያነበበው ግጥም የአራስ ወንዝን ከኢራን በሀይል ስለመገንጠል እንደሚያወራ አልነገሩትም " በማለት ኤርዶጋንን ዘልፈዋል። የኢራን ሌሎች ባለስልጣናትም በከፍተኛ ቁጣ ኤርዶጋንን አውግዘዋል። " ሰለምንወዳቸው አዘርባጃናዊያን ዜጎቻችን ማንም ሊያወራ አይቻለውም " በማለትም የኤርዶጋንን ንግግር አጣጥለዋል ይህንን ተከትሎ ቱርክም አፀፋውን መልሳለች። የቱርኩ ወጭ ጉዳይ ሚኒስት ሜቭሉት ካቩሶግሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ " ቱርክን እና መሪዋን እንድትዘልፉ አንፈቅድላችሁም " ብለዋል። የቱርክ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ፈህረዲን አልቱን በበኩላቸው " ጎረቤታችሁ የሆነችው አዘርባጃን የድል ቀኗን እያከበረች ባለችበት እናንተ እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት ደስታዋን ልትጋሯት ሲገባ ቃላት እየለቃቀማችሁ ሌላ የጠላትነት አጀንዳ ውስጥ መግባታችሁ ምክንያታችሁ ምን ይሆን " በማለት የኢራን ባለስልጣናትን አውግዘዋል። የኤርዶጋንን ግጥም ተከትሎ በርካታ ኢራናዊያን ባለስልጣናቱን ጨምሮ ኤርዶጋንን በማህበራዊ ሚዲያዎች ኤርዶጋንን ሲያወግዙ ውለዋል። በርካቶች ኤርዶጋን የኦቶማንን የመስፋፋት አላማ አንግቦ የኢራንን ግዛት ቆርሶ ለመውሰድ ተዘጋጅቷል ስለዚህ አስፈላጊውን ዝግጅት ኢራን ልታደርግ ይገባል እያሉ ነው። ቱርክ በበኩሏ ኢራን ከዚህ አደገኛ አካሔዷ እንድትቆጠብ ከማሳሰብማ አልፋ ለባለስልጣናቶቿ መረን የለሽ ንግግር ማብራሪያ እንድትሰጥ ጠይቃለች። ሁለቱም ሀገራት አምባሳደሮቻቸውን ጠርተዋል። እናም ያ ቀጠና በዳግም ትኩሳት ተወጥሯል። እንዳልኳችሁ በአዘርባጃን ከሚኖሩት ቱርካዊያን በላይ በኢራን የሚኖሩት ቱርካዊያን ቁጥራቸው ይልቃል። በአዘርባጃን ከሚገኘው የአዘርባጃን ግዛት በኢራን የሚገኘው የአዘርባጃን ግዛት በሁለት እጥፍ ይገዝፋል። የአብዛኛው የኢራን ከተሞች ነዋሪ ቱርካዊ ነው ። በዚህ የአዘርባጃን ድል ቀን ግጥም እነ ተብሪዝ ፣ የሳባላን ተራራ ተዘክረዋል። ሁለቱም አሁን በኢራን ይገኛሉ። ኢራን ይህ አንድነቴን አደጋ ውስጥ የሚከተ በህልውናየ ላይ የተጋረጠ አደጋ ነው በማለት እያስጠነቀቀች ነው። የአዘርባጃን ቱርኮች በኢራን ውስጥ በከፍተኛ ጭቆና ይኖራሉ። በቋንቋቸው መማር ፣ የመገናኛ ብዙሀን ማሰራጨት ባህል ወጋቸውን ማስፋፋት አይችሉም። ቱርካዊነታቸውን እንዲያንፀባርቁም አይፈቅድላቸውም ። ባለፈው አዘርባጃን ከአርሜኒያ ጋር በነበራት ጦርነት ለአዘርባጃን ያላቸውን አጋርነት በማሳየታቸው ብዙዎቹ ታስረዋል ። ይህም የበለጠ ተገፊነትን ጨምሯል። ኢራን ለሁለት መቶ አመታት በሰልጁቅ ቱርኮች ስር ትተዳደር ነበር። እነ ሬይ ፣ ኢስፋሃን ፣ ሀማዳን ፣ ነይሳቡር የሙሳሰሉ የአሁን የኢራን ከተሞች የቱርኮች መናገሻ ከተሞች ነበሩ። የቱርኮች መንግስት ተዳክሞ አካባቢውን የኢራኑ ሳሳኒድና ሩሲያ ሲቆጣጠሩት ነው ከፊል አዘርባጃኖች ወደ ሩሲያ ከፊሎቹ ደግሞ ወደ ኢራን በሀይል የተጠቃለሉት ። የሩሲያዎቹ ነፃ ሲወጡ የኢራኖቹ አዘርባጃን ቱርካዊያን ግን እስካሁን ነፃ አልወጡም ። እናም አሁን የነፃነት ትግሉ ላይ ኤርዶጋን ክብሪት የጫረበት ይመስላል። @jenutelfirdews
Mostrar todo...
#ሱብሀነላህ😍 “መልካም አድርግ” - መልካምነት ዞሮ ወደ አንተ ይመጣል! የሥጋ ፋብሪካ ሠራተኛ ናት፡፡ እንደወትሮው ሁሉ የእለት ተግባሯን ስታከናውን ቆይታ፥ መሽቶ ወደ ቤቷ ከመሄዷ በፊት አንድ አደጋ ገጠማት፡፡ ሥጋ የሚቀመጥበትን በረዶ ቤት አየት አድርጋው ለመመለስ ወደ ውስጥ እንደዘለቀች፥ ሳታስበው የማቀዝቀዣው ክፍል በድንገት ተዘጋ። በሩን ደጋግማ ደበደበች፡፡ እንጥሏ እስኪሰነጠቅ ጮኸች። ዳሩ ግን የሚከፍትላት ሰው አልነበረም፡፡ ሁሉም ሠራተኛ ወደየቤቱ ሄዷል፡፡ ደቂቃዎች ከነፉ፤ ሰዓታት ተቆጠሩ፡፡ ሞት አድፍጦ ነፍሷን ሊነጥቃት አፍንጫዋ ሥር እንደደረስ ተረዳች፡፡ ቢሆንም ጨርሶ እስትንፋሷ አልተቆረጠም፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለች በድንገት ያልጠበቀችው አጋጣሚ ተፈጠረ፡፡ ከፋብሪካው ዘበኞች መካከል አንድ አዛውንት ወዳለችበት ክፍል መጡና ከውጭ በኩል በሩን ከፍተውት ገቡ፡፡ ተዝለፍልፋ መውደቋን እንዳዩ ተሯሩጠው አነሷት፡፡ ከሞትም ታደጓት፡፡ ይሄን የአደጋ ዜና የሰሙ ሰዎች ሽማግሌውን ጠየቋቸው፡፡ ‹‹ስትጮኽ ካልሰሟት እንዴት ብለው ወደዚያ ክፍል ሄዱ?›› አሏቸው፡፡ አዛውንቱ ሲመልሱ፤ ‹‹እኔ በዚህ ፋብሪካ መሥራት ከጀመርኩ ሠላሳ ዓመት ያልፈኛል፡፡ ሁሌም ሠራተኞች ወጥተው ሲሄዱ እከታተላለሁ፡፡ ከሠራተኞች ሁሉ በተለየ ደግሞ ይቺ ሴት ሰላምተኛዬ ናት፡፡ ጠዋት ማታ ሰላም ሳትለኝ አትገባም-አትወጣም፡፡ በእለቱ ከሚወጡት ሠራተኞች መካከል ፈልጌ ሳጣት፣ ቅር ቅር እያለኝ ያስለመደችኝን ሰላምታ ፍለጋ ወደ መሥሪያ ክፍሏ አመራሁ፡፡ እናም በዚያ መልኩ ደረስኩላት!!›› አሉ። . በወጉ ካሰብነው እንኳን 'ሰላም' ይቅርና 'ሰላምታም' ትልቅ ዋጋ አለው፡፡ በሰላምታ ውስጥ ፍቅር፣ በሰላምታ ውስጥ መተሳሰብ፣ በሰላምታ ውስጥ መልካምነት አለ። አነሰም በዛ ለሰው ልጆች ፍቅር ማሳየትና መልካም መሆን፣ መቼ እንደሚከፍለን አናውቅም። አልፎ አልፎ የሠራናቸው መልካም ነገሮች ቀጥታውን መንገድ ትተው በእጅ አዙር ሊመጡም ይችላሉ፡፡ ቁም ነገሩ እሱ ብቻ አይደለም፤ ዋናው ጉዳይ መልካም ነገር ማድረግ ከሕሊና እርካታ እስከ ከፍ ያለ ሽልማት ያስገኝልናል። መቸም የሞትን ጽዋ ከማለፍ የበለጠ ትልቅ ሽልማት የለም። በተቃራኒው ግፍም ስንሠራ አንድ ቀን ሒሳብ ሊያወራርድ ይመጣልናል፡፡ የሰማይ ቤቱን ጽድቅና ኩነኔ ብንተወው እንኳን፥ በምድር ላይ ሳለን በልጆቻችን ጭምር ሒሳብ ማወራረዳችን አይቀርም፡፡ አይ ከተባለም፣ ሽልማትና ቅጣትን ታሳቢ ማድረግ አይገባም ከተባለም፥ ገጣሚው እንዳለው፡- "ጽድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም፤ ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም!" ብሎ ማሰብ ብልህነት ነው። መልካም ጊዜ!! (መሳፍንት ተፈራ) ▬▬▬▬▬▬▬ @jenutelfirdews
Mostrar todo...
ህይወት አጭር ናት። ዝቅ ሊያደርጉህ የሚተጉትን ሰዎች አሉባልታ የምትሰማበት ጊዜ የለህም። መልካም እንደሆንከው መልካምነትህን ቀጥልበት። ስላንተ ምንም ይበሉ ራስህን እንዳትጠራጠር። @jenutelfirdews
Mostrar todo...
#ኑ አብረን እንስራ !!! @halalbusines1 @halalbusines1 ጊዜው 👥#የሶሻል ??#ሚዲያ ነው ፣ ይህንን የሶሻል ሚዲያ አብዮት በብልሀት እንጠቀምበት ፣ ልክ እንደ ??#ቢዝነስ 🧳#ማን ። የሶሻል ሚዲያ ፈጣሪዎች ሶሻል ሚዲያን የፈጠሩት ለምን ይመስሎታል❓ እስቲ ይገምቱ ። @halalbusines1 @halalbusines1 እንደማንኛውም ሰው ካሰቡት 💃#ለመዝናኛ ሊሉን ይችሉ ይሆናል ፣ ይህ ግን 👺#ፈፅሞ ልክ አይደለም ። ሶሻል ሚዲያ የተፈጠረው ፈጣሪዎቹ 🤑#ሊነግዱበት ብቻ ነው ። ለማረጋገጥ የፈጣሪዎቹን ሀብት ማየት በቂ ነው ። 🆘 ይህን እውነታ ግን አይነግሩንም ። 🆘 እኛም እንደ ፈጣሪዎቹ 🤔#ብልህ እንሁን ። ❗️ይህ እድል እንዳያመልጦ ብዙዎችን የሚቻሳትፍ በጊዜና በቦታ ያልተወሰነ ስራዎትን እየሰሩ ገቢዎትን ያሳድጉ🚀 በሕብረት፣በታማኝነትና በአንድነት እጅለእጅ ተያይዘን ወደ ከፍታ እንጓዝ!!! ፋይናንሺያል ኔትወርኪንግ ቢዝነስ ግሩፕ 🔰FULL INFORMATION🔰 👇 https://t.me/Eth_fnb_bot?start=r07325283120 @halalbusines1 || @halalbusines1 @FNB_00 @FNB_00 Contact
Mostrar todo...
🔰FNB INFO🔰

welcome to Financial Networking Business Group

https://t.me/comparison2012 ለአቶ ሳዳት ከማል እና ለአቶ ኢብኑ ምነወር እዲሁም ለተከታዩቻቸዉ የተላለፈ መልእክት ከሙስሊሞች ጉዳይ
Mostrar todo...
1.27 MB
@Share251 ን ይቀላቀሉ!
Mostrar todo...
❤️ 3,230
​​​​​​​​​​​​​​​​ ልትነግራቸው ነው " ብላ አፈጠጠችበት ይሄን ስሰማ በዛ በጨቅላ አቅሜ መሸከም ከምችለው በላይ ነበር ሰሚራ ብረቱን ለምን እንደያዘችው ያኔ ነበር የገባኝ መቋቋም አቃተኝ የሰማሁትን ማመን አልቻልኩም አንድ ሰው ከሞተ ድጋሚ ከሰዎች ጋር መገናኘት እንደማይችል ነበር እናቴ የነገረችኝ ታድያ እናቴንም ድጋሚ ላገኛት አልችልም ማለት ነው .......ስለ ሞት እንኳ በቅጡ አላውቅም ነበር አይሆንም አባቴ እንዲህ አያደርግም አባቴ እናቴን በጣም ነወ የሚወዳት እያለኩ ከ እራሴ ጋር አወራለሁ፡፡ አባቴም መናገር ጀመረ ይበልጥ ተጠግቼ ማዳመጥ ጀመርኩ እሱ ይሄን እንደማያደርግ እንዲያረጋግጥልኝ በማሰብ ግን..... እናቴን ገደሏት ሀሊማ አሳዛኝ እና አስተማሪ ታሪክ
Mostrar todo...
ሀሊማ
እንዳያመልጦ
ኤርዶጋን በዛሬው እለትም በኢስታምቡል "ሸህሪባን ሀቱን" መስጂድን መርቀው ከፍተዋል። በየሳምንቱ አዲስ መስጂድ! አልተቻሉም ረኢስ ኤርዶጋን!!
Mostrar todo...
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ!!! ውድ የኢልም ቤት ተከታታዬች በዚህ ግሩፕ ሲደረግ የነበረው ትምህርት በቻናላችንን ሁኗል። በግሩፑ የቀረበት ምክንያትም አንዳንድ ሰዎች ከዚህ ግሩፕ ሰው እያወጡ አዛ እያረጉ ስለሆነ ወደ ቻናል ለመቀየር ተገደናል። ይህ ግሩፕ እሚቆይ እስከ እሁድ ብቻ ነው ስለዚህ ተልተሎ ብላችሁ ወደ ቻናሉ ተቀላቀሉ። ቻናላችንን👇👇👇
Mostrar todo...
ለመቀላቀል
JION US
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sĂłlo permite el anĂĄlisis de 5 canales. Para obtener mĂĄs, elige otro plan.