cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ፍቅር እና ቀልድ

🙌 አላማችን እናንተን ፈታ ማረግ ነው 🙌 ቀልዶች: ሽንት አስጨራሽ fun GIF:ትረካዎች: መጣጥፎች ሌሎችንም የሚያገኙበት ምርጥ ቻናል🤗 ᎪᏞᏞ ᏆN ᎾNᎬ FᎾᎡ ᎪNY ᏢᎡᎾᎷᎾᎢᏆᎾN 👉 @ahmibb . . . . . . .

Mostrar más
Advertising posts
80 623Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

😎😎 🎃At Share To Ur Friends
Mostrar todo...
😂😂😳 🎃At Share To Ur Friends
Mostrar todo...
🤤🤤🤤😂 🎃At Share To Ur Friends
Mostrar todo...
😂😂😂👏👏👏 🎃At Share To Ur Friends
Mostrar todo...
❤️❤️አለመታደል ነው❤️❤️ 🌼🌼🌼ክፍል 4🌼🌼🌼 እኔም አልገባኝም። …… ስምሪት ለምን እናቴን አስታወሰችኝ? …… ‘ስምረት ሞተች‘ የሚለው የአርሴማ ጥሪ የፈጠረብኝ ድንጋጤ እንዴት ብሽቅ ለሆነው የአሁኑ ስሜቴ ጎታች ምክኒያት ሆነ? በውል ያለየሁት ለስምሪት የተሰማኝ ስሜት በምን ስሌት ወደልጅነት ትዝታዬ አሸመጠጠኝ? አላውቅም…… ምናልባት እስከማስታውሰው ለሰው ግድ የሰጠኝ በዚህ ክስተት ስለሆነ? ምናልባት ሰው መሆን ለሰው ማሰብን ያካትት ይሆን? ምናልባት ሰው ሆኜ ይሆን? ምናልባት ሰው በሆንኩ ቅፅበት እንደሰው ግድ ሳይሰጡኝ ያለፍኳቸውን ክስተቶች ማሰላሰል መጀመሬ ይሆን? አላውቅም…… ብቻ ‘ምንም ሽራፊ ስሜት አይሰጠኝም‘ ያልኳቸው ስንጣቂ የኑሮ ሰበዞቼን ሳይቀር ሳልፈልግ እያሰብኳቸው ነው። …………… “እያስጨነቅኩህ ነው?” አለችኝ ስምሪት ደጋግማ የማልወዳትን እናቴን እና የተለየ ስሜት የፈጠረችብኝን ሴት ምን እንዳመሳሰላቸው ስትጠይቀኝ ቆይታ “እናቴን እንደማልወዳት እርግጠኛ እየሆንኩ አይደለም።” መለስኩላት… … ፀጥ አለችኝ። ……… አይኖቿን አጥብባ ስታየኝ ቆየችና። …… “ለምን አታረጋግጥም?” አለችኝ “ምኑን?” “ለእናትህ የሚሰማህን ስሜት?” “እንዴት? በምን?” “ፈልጋቸዋ!! ፈልገህ አግኛቸው።” “የት ብዬ? ትሙት? ትኑር? እንኳን ማወቅ ይከብዳል። 11 ዓመት ብዙ ነው።” ይሄን ለሷ ስመልስላት ራሴን ሰማሁት…… ጥያቄዬ ልፈልጋት? ወይስ አልፈልጋት? የሚለውን እርከን አልፏል። …… ‘አልፈልጋትም‘ የሚለውን ጭራሽ አለማሰቤ አስገረመኝ። እሷም ይህ የገባት መሰለኝ… … ፈጠን ብላ “ራስህን ዝግጁ ካደረግክ ፍንጭ የምናጣ አይመስለኝም።” አለችኝ ዝግጁነቴን ለማረጋገጥ ነው መሰል ከአፌ የሚወጣውን ቃል አፏን ከፍታ እየጠበቀች። ፀጥ አልኩ። ፀጥ አለችኝ። …… እያየኋት እንደሆነ ሲገባት ታቀረቅራለች……… እያየችኝ እንደሆነ ሳውቅ አይኖቼን በሌላ አቅጣጫ አርቄ እልካቸዋለሁ። “ስምሪት?” “አቤት?” “እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ?” ራሷን በመነቅነቅ እንድቀጥል ተስማማችልኝ። “ለምንድነው ከሌላ ሰው በተለየ የምትቀርቢኝ? የምትሰሚኝ? የምታወሪኝ?” የጠበቀችው ሌላ ጥያቄ እንደሆነ ሁሉ ፊቷ ረገበ……… “ከአይምሮ ይልቅ ልብ ይማርከኛል።” መልሷ እርግጠኛነት ነበረው “ማለት?” “ከእውቀት ይልቅ ለቅንነት ዋጋ እሰጣለሁ ማለት ነዋ!! ቅንነት የሌለበት እውቀት በዜሮ ይባዛብኛል። ቅንነት የሞላበት አለማወቅ እንኳን ይገዛኛል። ልብህ ቅን ነው።” ብላኝ ከኔ መልስ እንደማትጠብቅ ተደላደለች… … እሷ በገለፀችኝ ልክ ልበ—ቅን መሆኔን እጠራጠራለሁ። …… ቅንነት ይመነዘራል። እኔ ስለራሴ እስከማውቀው ከራሴ ውጪ ለማንም ግድ ኖሮኝ ለሰዎች ቀና ለማድረግም ሆነ ቀና ለማሰብ ተጨንቄ አላውቅም። …… ማንም ጉዳዬ አይደለም። የማንም ጉዳዩ እሆናለሁ ብዬም አስቤ አላውቅም። ……… እሷ እንደዚህ ናት። ስለእኔ ስታወራ ባለቤቱ እርግጠኛ ከሆንኩት በላይ እርግጠኛ ናት… … ምናልባት እኔ ራሴን ከማዳምጠው በላይ እሷ ስለምታዳምጠኝ ይሆን? ሁሌም የምትጠቁመኝ ኪሩቤል መድረስ የሚችልበትን ጫፍ እንጂ ሰወች ወይ እሷ ‘መዳረሻ‘ ብለው የሰቀሉትን ጫፍ አይደለም። …… “ስምሪት?” ባልጠራትም እየሰማችኝ እንደሆነ አውቃለሁ። ከእስከዛሬው ሁሉ በተለየ እንድትሰማኝ ፈለግኩ። “አቤት?” “ከዛን ቀን በኋላ አንቺን እንደአለቃዬ ወይም እንደጓደኛዬ ማሰብ እየቻልኩ አይደለም።” አልኳት። ከአፌ እስኪወጣ እየጠበቀችው ያለ ንግግር እንደሆነ ሁሉ መገረምም መደንገጥም ሳይታይባት ” አንድ እርምጃ ጠልቀህ ያወቅከኝ ስለመሰለህ ነው?” መልስ የምትፈልግም አትመስልም “ማለት?” አልኳት ያለችው ሳይገባኝ ቀርቶ ሳይሆን የማስረዳት አቅም ከድቶኝ “ኪሩ ልብሳቸውን ስትገፍ ያወቅካቸው እንደሚመስሉህ ሴቶች እርቃኔን ስላየኸኝ ገበናዬን የገለብክ አይምሰልህ።” የምታወራበት ቅላፄ የማላውቀውና ምሬት የተቀላቀለበት ነው። ምን እንደምላት እና ለሷና ለማውቃቸው ሴቶች የሚሰማኝን የአንድ ጤፍ ፍሬና የተራራ ያህል የገዘፈ የስሜት ልዩነት ማስረዳት ባለመቻሌ ተናደድኩ። “እንደዛ አይደለም የተሰማኝ። ውስጤ የቀረውን የገላሽን ምስል ሳስበው አብሬሽ መተኛት አይደለም የሚሰማኝ። ተሰምቶኝ በማያውቅ መልኩ ከወለሉ ላይ አንስቼሽ አልጋ ላይ ያደረስኩሽ ቅፅበት የእድሜ ዘመኔን ያህል ረዥም እንዲሆን ነው የሚሰማኝ። ክንዴ ላይ እንዳቀፍኩሽ የተከደኑ አይኖችሽን በስስት እያየሁ ዘመናቴ ቢያልቁ ነው የተሰማኝ። …… ” ይግባት አይግባት እንጃ… … ከዚህ በላይ ማስረዳት ግን አቃተኝ። …… ደቂቃዎችን ትንፋሽ ያጠረኝ እስኪመስለኝ ፀጥ አለች። ሲገባኝ ሁሉም ሰው የሆነች “የለውጥ ኩርባ” አለችው። አስተሳሰቡ ወይ ስሜቱ ወይ ድርጊቱ… … የሚቀየርባት። ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚታጠፍበት……ወይም ከወደቀበት መቀመቅ የሚስፈነጠርበት……… ወይም ለዛለው ጉልበቱ አቅም የሚያገኝበት… … ያቺ የለውጥ ኩርባ አንድ የሆነች ኢምንት ክስተት ልትሆን ትችላለች…… ወይም ዓረፍተ ነገር… … ወይም… … …የኔ የለውጥ ኩርባ ያቺ ቀን ነበረች። …… “ልክ አይሆንም። እኔና አንተ ከዚህ ቀደም ከነበረን የዘለለ ግንኙነት ሊኖረን አይችልም አለችኝ..✍ ይቀጥላል...✍ For any comment👉 @ahmibb Join 👉 @fkrenakald @fkrenakald
Mostrar todo...
👍 64
❤️❤️አለመታደል ነው❤️❤️ 🌼🌼🌼ክፍል 3🌼🌼🌼 እናቴ ሸርሙጣ ነበረች። …… ሀገር ያወቃት ሸርሙጣ። …… ከማን እንደወለደችኝ አታውቅም። …… ባሏ ነው የሷ ዲቃላ መሆኔን የሚነግረኝ…… እሷም ግን ‘ሂድ ከዚህ ጥፋ! ዲቃላ‘ ትለኛለች ስትሰድበኝ… … የሌላ ሰው ነውር እንደሆንኩ ሁላ አትገባኝም። … አንዳንዴ አቅፋኝ ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች። …… ወዲያው መልሳ ለአይኗ እቀፋታለሁ። …‘ዞር በልልኝ‘ ትለኛለች። ቆንጆ ናት።…… ህልም የመሰለች ቆንጆ… ባሏ ጥንቅቅ ያለ ሱሰኛ ነው። …… ብዙ ያልጠየቅኳቸ … ያልተመለሱልኝ ጥያቄዎች አሉ። … ማወቅም አለማወቅም የሚሰጠኝ ሽራፊ ስሜት የለም። …… እናቴ እንዴት አንድ ዘመድ እንኳን አይኖራትም? የምንኖርበትን ቪላ አወረሱኝ የምትላቸው ቤተቦቿ እንዴት አንዲት የዘር ትራፊ አይኖራቸውም? ለምን በየቀኑ ከተለያየ ወንድ ጋር ትሆናለች? ባሏ ከመስከር ውጪ የሚያደርገው የመልስ ምት እንዴት አይኖርም? …… አላውቅም…… እነሱ ለኔ ግድ እንደሌላቸው ሁሉ እኔም ጉድጓድ ቢገቡ ግድ አልነበረኝም…… በየማታው እሱ ሰክሮ ይገባል… … እሷ ተኳኩላ ትወጣለች። …… ልጥገብ ወይ ልራብ፣ ልደሰት ወይ ልዘን፣ ልክሳ ወይ ልወፍር፣ ልማር ወይ ሜዳ ልዋል፣ ልታመም ወይ ጤነኛ ልሁን…… ግዳቸው አይደለሁም። …… ምናቸውም አልነበርኩም።………… አብሬያቸው ሆኜ የረሱኝ።… … “እናትህ ሸርሙጣ ናት! ወንድ አትጠግብም።…… ለገንዘብ ብላ አይደለም የምትሸረሙጠው…… ሽርሙጥና ሱስ ሆኖባት ነው። …… ” ይለኛል ይዞ ከመጣው ቢራ እየቀዳልኝ… … ጠዋት ግን ገንዘብ ስትሰጠው አየዋለሁ። …… ከርሱ ጋር በየቀኑ እየሰከርኩ ማደር ልምዴ ሆነ። …… ይቀዳልኛል… … እጠጣለሁ…… አጣጩ እንጂ የማድግ ልጁ አይደለሁምና በየቀኑ የሚግተኝ አልኮል ምን እንደሚጎትትብኝ ግድ የለውም። ለወጉ በአመቱ መጀመሪያ እንድታስመዘግበኝ ተለማምጫት ት/ ቤት እገባለሁ። … አመቱን ሙሉ እመላለሳለሁ… ስንተኛ ክፍል እንደሆንኩ አያውቁም። …… እድሜዬንም ይዘነጉታል። … የትምህርት ቤት ስሜን ሁሉ የማስታውሳቸው እኔ ነኝ።…… የአባቴ ስም የባሏ ስም ነው። “የማንም ዲቃላ አባት አይደለሁም። አባትህን ሄደህ ፈልግ።” ይለኛል ከሷ ጋር ሲጣላ……… እኔ ለነሱ ‘የለሁም‘። አስረኛ ክፍል ስደርስ እሱ በጉበት ካንሰር ሞተ። …… እናቴ ድንገት ተቀየረች። “ርቄ ልሄድ ነው።” አለችኝ አንድ ቀን በጠዋት የት? ወዴት? ለምን? አላልኳትም። …… ትምህርት ቤት ደርሼ ስመለስ የለችም። …… አልጋዋ ላይ የተወሰነ ገንዘብ እና ደብዳቤ አስቀምጣልኛለች። የፃፈችልኝ… እንዳልፈልጋት…… ትምህርቴን እንድማር…… ጎበዝ ልጅ እንድሆን……ሱስ እንዳቆም…… እና እናት ስላልሆነችልኝ ይቅር እንድላት…… አልከፋኝም። እንደውም ደስ አለኝ። ክልስ ነኝ። …… አባቴ ምናዊ እንደሆነ አላውቅም። …… እንዴትስ ላውቅ እችል ነበር? “ይሄኔ እኮ የዘጋ ሀብታም ፈረንጅ ይሆናል አባትህ።” ይሉኛል አብሮአደጎቼ በቀልድ… … የሚጎፈንነኝ ቀልድ መሆኑ አይገባቸውም። የሚያውቁኝ ሰወች ስለእናቴ ሲያጉረመርሙ እሰማለሁ… … ያስጠላኛል። ያስጠሉኛል። …… ስለቤተሰብ ትስስር ተያያዥ ነገር መስማትም ማየትም አልፈልግም። …… እውነት ግን አባቴ ክዶኝ ነው? ወይስ ጭራሽ መፈጠሬን አያውቅ ይሆን? አላውቅም።…… የራሱ ጉዳይ!! …… ቤተሰብ ብቻ ሳይሆን ጓደኛም የሌለኝ ሆንኩ። …… ከሱሴ ተጋባሁ። …… ከሱሶቼ ጋር በፍቅር ተቆራኘን። ከእንጀራ አባቴ ሱስ… … ከእናቴ ሽፍደት… … ከራሴ ቅጥ ያጣ ግድ የለሽነት… … አወጣጥቼ የአሁኑ ኪሩቤል ተሰራ።…… “ኪሩ?…… ኪሩ?” ትከሻዬን እየወዘወዘች ጠራችኝ ። ስምሪት ናት።…… ቡና ልንጠጣ ተቀምጠናል። “ፊትህ እኮ ደም መስሏል። ምን እያሰብክ ነው?” አለችኝ መልሳ ከዛ ቀን በኋላ ደህና መሆኗን ልጠይቃት አስባለሁ…… ልክ ሳያት እተወዋለሁ። …… ልትጠይቀኝ የምትፈልገው ያላት ይመስለኛል። …… አትጠይቀኝም።… … እንደበፊቱ መጫወት አቃተን። …… “ለሴት ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የተለየ ስሜት ሳይሰማኝ አልቀረም።” አልኳት “ተመስገን ነው። …… እንዴት የተለየች ብትሆን ነው?” አለችኝ ምንም ጉጉት ሳያድርባት… … “በማላውቀው ምክኒያት እናቴን መሰለችኝ።” “እናትህን እኮ አትወዳቸውም።” አለችኝ ሰውነቷ እየፈሰሰ እስኪመስለኝ ተኮማትራ “አዎን አልወዳትም። …… ” የሚሰማኝን መግለፅ ከበደኝ። ‘ግፈኛዋ እናቴን መሰልሽኝ። …… ግን በተለየ ወደድኩሽ።‘ ነው የምላት?… … እንኳን ለርሷ ለራሴ የተደበላለቀ ነገር አለው። …… ለርሷ ላስረዳት ቀርቶ ለራሴም አልገባኝም...✍ ይቀጥላል...✍ for any comment 👉 @ahmibb join 👉 @fkrenakald @fkrenakald
Mostrar todo...
👍 144