cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ኑ የዲን ዕውቀትን አንድ ላይ እንማር

ሱና የኑህ መርከብ ናት የተሳፈረባት ይድናል ወደ ኋላ የቀረ ይሰምጣል

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
239
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#ከፍተኛ_ጥንቃቄ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት (ጅዳ) ለኢትዮጵያውያን የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል። ከትናንት ምሽት ጀምሮ ለፅህፈት ቤቱ እየደረሱ ባሉት መረጃዎች መሠረት የሳዑዲ የፀጥታ አስጠባቂ አካላት ፦ - በጄዳ ፣ - መዲና ፣ - ጂዛን እና መካ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ዜጎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ። በዚህም ምክንያት ጉዳዩ እስኪጣራ ድረስ ኢትዮጵያውያን ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል። በሳዑዲ አረቢያ በተጠቀሱት ከተሞች የምትገኙ የቲክቫህ አባላት በሙሉ የቆንስላ ጽህፈት ቤቱን የጥንቃቄ መልዕክት በአፅንኦት እንድትወስዱ፣ እራሳችሁን እንድትጠብቁ ፤ ጥንቃቄም እንድታደርጉ አደራ እንላለን። @tekamimrjawoc @tekamimrjawocbot
Mostrar todo...
የአዲስ አበባ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በሌቦች ምክንያት እየተረበሸ ነው፡፡ በውድቅት ሌሊት አድብተውና ተደራጅተው የባቡሩን ማለፊያ የኤሌክትሪክ ገመድ በመስረቅ የተካኑ ሌቦች ከማለዳ እስከ አመሻሽ የሚሰራውን ባቡር እያሰናከሉት መሆኑን ሸገር ስምቻለሁ ብሏል፡፡ በመሬት ውስጥ የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ እንዳይሰረቅ የቀላል ባቡር ትራንስፖርት ሰራተኞች ሳይቀሩ ተራ ገብተው ከፖሊሶች ጋር በትብብር ሲጠብቁ እንደከረሙ ነው ሸገር የዘገበው፡፡በስርቆቱ መበራከት፤ የባቡር ትራንስፖርቱ እየተስተጓጎለ በመሆኑ፤ የባቡር ደንበኞች እየሸሹ ነው ተብሏል፡፡ የሌብነቱን ሁኔታ በመከታተል መፍትሄ እንደሚያበጅለት የፌዴራል ፖሊስ መናገሩ ይታወሳል፡፡በባቡር መንገዱ ላይ ዘለው የሚገቡ መኪኖችና ግጭት ተጨምሮበት የአዲስ አበባን ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ለጠና ችግር እያጋለጡት ነው ተብሏል፡፡ @tekamimrjawoc @tekamimrjawocbot በተጨማሪም በመብራት መቆራረጥና በመለዋወጫ እቃዎች በጊዜ አለመገኘት ምክንያት የባቡር ትራንስፖርት እየተቋረጠ መሆኑን ተሰምቷል፡፡የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት የስራ ሀላፊዎችንና የትራንስፖርት ደህንነት ሀላፊዎችን ስለጉዳዮ ለማነጋገር የተደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡
Mostrar todo...
#ሰበርዜና ‼️ የሰኔ 14ቱ ምርጫ በሶማሌ ክልል አይካሄድም ተባለ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 የሚካሄደው 6ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ በሶማሌ ክልል እንደማይካሄድ አስታወቀ፡፡ የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ምርጫው በክልሉ እንደማይካሄድ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡ ለምርጫው በተያዘለት ጊዜ አለመካሄድ የህትመት ችግር እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች በኩል ከመራጮች ምዝገባ ጋር በተያያዘ የቀረቡ ቅሬታዎችን በምክንያትነት ያስቀመጡት ሰብሳቢዋ የክልሉ የህዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤት እጩዎች ጷግሜ 1 ቀን 2013 ዓ.ም በሚካሄድ ሁለተኛ ዙር ምርጫ እንደሚመረጡ አስታውቀዋል፡፡ ሁለተኛ ዙር ምርጫው የጸጥታና የህትመት ችግር ባጋጠማቸው ሁሉም የሃገሪቱ አካባቢዎች እንደሚካሄድም ነው ሰብሳቢዋ የገለጹት፡፡ ለ6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ከ37.4 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዝግበዋልም ብለዋል፡፡ @tekamimrjawoc @tekamimrjawocbot
Mostrar todo...
Good news የቴሌኮም ፈቃድ ስምምነቱ እየተፈረመ ነው በኬንያው የቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪ ኮም የሚመራው የአራት የቴሌኮም ኩባንያዎች ስብስብ ያሸነፈው የቴሌኮም ፈቃድ ስምምነት ፊርማ ስነ ስርዓት እየተካሄደ መሆኑን የጠ/ሚ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ ፊርማው ከኢትዮ ቴሌኮም በመቀጠል ሁለተኛውን የቴሌኮም አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችል እንደሆነ ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ በቴሌኮም ኦፕሬተርነት ዘርፍ ለመሳተፍ የወጣውን ጨረታ ሳፋሪ ኮምን፣ ቮዳፎንን፣ ቮዳኮምንና ሱሚቶሞን ያካተተው ‘ግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ’ ማሸነፉና 850 ሚሊዬን ዶላር ለመንግስት ገቢ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ ከሰዓት መልስ አዲስ አበባ መግባታቸውም የሚታወስ ነው፡፡ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድፕሬዝዳንት ኡሁሩን “የቴሌኮም ፍቃድ ስምምነትን በምንፈራረምበት በዛሬው ታሪካዊ ዕለት ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደኅና መጡ ለማለት እወዳለሁ” ማለታቸውም አይዘነጋም፡፡ @tekamimrjawoc @tekamimrjawocbot
Mostrar todo...
በአማራ ክልል በደብረ ማርቆስ ከተማ ከ5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው "ደብሊው ኤ" የምግብ ዘይት ኮምፕሌክስ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተመርቋል፡፡ "በደብሊው ኤ" ኢንቨስትመንት ግሩፕ የተቋቋመው የምግብ ዘይት ፋብሪካ ከ1 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በቀን ከ1.3 ሚሊዮን ሊትር በላይ ዘይት ማምረት ይችላልም ተብሏል። @tekamimrjawoc @tekamimrjawocbot
Mostrar todo...
🔔 ሰበር ዜና ‼️ 🔺ከደቂቃዎች በፊት ከመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዞር ሹም በሰጡት መግለጫ መሰረት የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳደር የሆኑትን ዶ/ር ደብረፂዮንን ጨምሮ 6 ከፍተኛ የክልሉ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ውለዋል። 🔺በምስል ተደግፎ የወጣውን መግለጫ OPEN የሚለውን ተጭነው መመልከት ይችላሉ።
Mostrar todo...
open
#NEAEA የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ግንቦት 29 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ በአንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተሰራጨ ያለው መረጃ ትክክለኛ አይደለም ተብሏል። ፈተናው መቼ እንደሚሰጥ ገና #አለመወሰኑን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ @tikvahuniversity አረጋግጧል። የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ረዲ ሽፋ ፈተናው የሚሰጥበት ቀን አሁንም ገና እንዳልተወሰነ ገልፀዋል። ኤጀንሲው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ሲደረስ ይፋዊ የሆነ መግለጫ እንደሚሰጥ ተናግረዋል። Tikvah-University t.me/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h @tekamimrjawoc @tekamimrjawocbot
Mostrar todo...
ETV news የ12ኛ ክፍል ፈተና ግንቦት 29 ይሰጣል። የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና ግንቦት 29 ቀን እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ግንቦት 22 እስከ 24 ቀን 2013 ዓ.ምየዲጂታል መታወቂያ ይሰራጫልም ብሏል። የፈተናው ገለጻ 26 ቀን ተካሂዶ ፈተናው ከግንቦት 29 እስከ ሳኔ 2 ቀን 2013 ዓ.ምድረስ እንደሚሰጥም ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ በቀጥታ (ኦንላይን)ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥም የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ገልጸዋል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር በፈተና አሰጣጡ ላይ ለተፈጠረው መዘግየት በይፋ ይቅርታ መጠየቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል። @tekamimrjawoc @tekamimrjawocbot
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.