cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Amhara Bureau of Agriculture

BOA

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 527
Suscriptores
+224 horas
+57 días
+3230 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለውን የክላስተር እርሻ ገቢራዊ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን እናሳድግ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ የአማራ ክልልን ግብርና በሜካናይዜሽን፣ በምርጥ ዘርና ማዳበሪያ አቅርቦት፣ በምርምር የወጡ አዳዲስ ዝርያዎችን በማስተዋወቅ፣ ለባለሙያዎችና ለአርሶ አደሮች ስልጠናዎችን በመስጠት የግብርና ዘርፉን ለማሻገር ስር ነቀል እርምጃዎች ተወስደዋል። ሌላው የትኩረት ማዕከል ደግሞ የክላስተር እርሻን በማስፋፋት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረትም ተጠቃሽ ነው። የግብርና ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ከሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ከዶ/ር ማንደፍሮ አስላከ ጋር በክላስተር እርሻ ምንነትና አስፈላጊነት ዙሪያ ቆይታ አድርገናል። ክላስተር በአንድ የተወሰነ አካባቢ ያሉ አርሶአደሮች አጎራባች መሬቶችን አንድ ላይ በማሰባሰብ፣ ምርታማነታቸውን ለማሳደግ አብረው የሚሰሩበት፣ ሀብትና እውቀት የሚጋሩበት፣ ልምድ የሚለዋወጡበት አሰራር የሚፈጥር ነው። ለዘርፉ ሁለንተናዊ እድገት የግብርና ባለሙያዎች የሚሰጧቸው አገልግሎቶች፣ ድጋፎች እና ክትትሎች የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ፣ በምርምር ተቋማት የሚገኙ የምርምር ውጤቶችም ፈጥነው ወደ ስራ እንዲገቡ የተሻለ እድል ሊፈጥር የሚችል እንደሆነም ይታመናል ሲሉ ዶ/ር ማንደፍሮ አስላከ አብራርተዋል። በአማራ ክልል በ2016/17 የመኸር ምርት ዘመን 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በክላስተር እርሻ የኮሞዲቲ ሰብሎችን ለማልማት የታቀደ ሲሆን ወደ 100 ሚሊዮን የሚጠጋ ኩንታል ምርት በክላስተር ከሚለማው ማሳ ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል ። ዶ/ር ማንደፍሮ አስላከ እንደገለፁት በምርት ዘመኑ በመደበኛ ከሚሸፈነው ከአምስት ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ውስጥ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በክላስተር እርሻ ይሸፈናል ብለዋል። በክልሉ በተመረጡ አስር ሰብሎች ላይ የክላስተር እርሻ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ስንዴ ፣ጤፍ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣አኩሪ አተር፣ ሰሊጥ፣ ሩዝ እና ሌሎችም በክላስተር ከሚመረቱ መካከል ዋነኞቹ መሆናቸውን ተናግረዋል። የክላስተር እርሻ ዘዴ ዋና ጥቅም መሬት በማሰባሰብ ወጪን በመቀነስ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆን መቻል ነው። በዚህ ዘዴ የአርሶ አደሩን ምርታማነት ማሳደግ ብቻ ሳይሆን አመጋገብ ላይም ለውጥ እንዲያመጣ ማስቻል ነው። የክላስተር እርሻ በዋናነት አርሶ አደሮች ከተበጣጠሰ የማሳ አጠቃቀም በመውጣት በአንድ ላይ እንዲያመርቱ ለመደራጀት እና አስፈላጊው የግብርና ቴክኖሎጂን ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ ያግዛል። የግብርና ባለሙያዎችም በተናጠል ከሚከናወን የግብርና ስራ ይልቅ በክላስተር የሚለማ እርሻ ላይ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ የተሻለ አቅም ይፈጠርላቸዋል በማለት አስረድተዋል። በየደረጃው የሚገኙ የግብርና ባለሙያዎችም አርሶ አደሩ የክላስተር እርሻ ዘዴን እንዲያዘወትር ግንዛቤ በመፍጠር፣ የክህሎት ስልጠና በመስጠትና ለአርሶአደሩ የገበያ ትስስር በመፍጠር የማይተካ ሚና እየተወጡ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል። አርሶ አደሩ በክላስተር እርሻ ተጠቃሚ እንዲሆን ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ ያሉ የግብርና ባለሙያዎች ልዩ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ አርሶ አደሩን በሙያ የመደገፍ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የክላስተር አሰራር ዘዴ በአንድ የተወሰነ አካባቢ ያሉ አርሶአደሮች አብረው የሚሰሩበት፣ አጎራባች መሬቶችን አንድ ላይ በማሰባሰብ፣ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ ሀብትና እውቀት የሚጋሩበት እንዲሁም ልምድ የሚለዋወጡበት ጭምር በመሆኑ በስፋት ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ያሉት ዳይሬክተሩ የክላስተር እርሻ ዋና አላማም የክልሉን አርሶአደሮች ምርታማነትና ትርፋማነት ማሻሻል ስለመሆኑ አንስተዋል። በአማራ ክልል የክላስተር እርሻ ከሚታረሰው መሬት 48 በመቶ እንዲሁም ከታቀደው ምርት 60 በመቶ ይሸፍናል ያሉት ዶ/ር ማንደፍሮ አስላከ 39 ሽህ 834 የክላስተር አደረጃጀት ለመፍጠር ታቅዶ እስካሁን ባለው መረጃ 31 ሽህ 228 ወይም የእቅዱን 78% የክላስተር አደረጃጀት መፍጠሩን ገልፀዋል። አዘጋጅ:- አንተነህ ሰውአገኝ ካሜራ:- ጌታቸው ታፈረ ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የግብርና ቤተሰብ ይሁኑ👇 ድረገጽ http://www.amhboard.gov.et/ ቴሌግራም  https://t.me/AmharaBureauofAgriculter ፊስቡክ  https://www.facebook.com/profile.php?id=100064357704820 ዩቱዩብ  https://www.youtube.com/@amharaagriculturebureau6055
Mostrar todo...
Amhara Bureau of Agriculture

BOA

Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
የስንዴ ሰብል የአመራረት ፓኬጅ ክፍል ሁለት ሰብል ጥበቃና እንክብካቤ 👉 በሰብል ጥበቃና እንክብካቤ ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት ወቅታዊ የተባይ አሰሳ ማካሄድና የተቀናጀ የተባይ መከላከል ዘዴን ተግባራዊ ማድረግ 👉ተገቢ የመርጫ መሳሪያና የመርጫ ጫፍ መጠቀም 👉 ዲፍሌክተር ኖዝል (የመርጫ ጫፍ) እና የመርጫ መሳሪያ ግፊት መቆጣጠሪያ ዝቅተኛ ግፊት ሀይል ላይ በማድረግ ለፀረ- አረም ኬሚካል መጠቀም፡፡ 👉 ኮን ኖዝል (የመርጫ ጫፍ) እና የመርጫ መሳሪያ ግፊት መቆጣጠሪያ ከፍተኛ ግፊት ሀይል ላይ በማድረግ ለፀረ ነፍሳት እና በሽታ ኬሚካል መጠቀም፡፡ አረም መከላከል በባህላዊ መከላከል 👉 የሰብል ፈረቃ መጠቀም፣ከአረም የጸዳ ማሳ ማዘጋጀት፣ንጹህ ዘር መጠቀም፣ 👉በእጅ ማረም፡ - • 1ኛ አረም ሰብሉ ከበቀለ ከ18-20 ቀን፣ • 2ኛ አረም ሰብሉ ከበቀለ ከ35-40 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ማካሄድ • 3ኛ አረም እንደአስፈላጊነቱ ታይቶ የሚታረም ይሆናል፡፡ በኬሚካል መከላከል 👉የስንዴ ሰብልን በተቻለ መጠን በእጅ ማረም ጥሩ ቢሆንም የጉልበት ዕጥረት በሚኖርበትና የአረሙ ክስተት ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ የተመረጡና የተመዘገቡ ኬሚካሎችን በአምራቹ የአጠቃቀም መመሪያ መሠረት መጠቀም፣ ነፍሳት ተባይ ቁጥጥር ክሽክሽ 👉 ይህ ተባይ ከሰብሉ ቡቃያ እስከ ዕድገት ደረጃ በሰብሉ ላይ በመከሰትና የተክሉን ፈሳሽ በመምጠጥ ጉዳት የሚያደርስ ተባይ ነው። በባህላዊ መከላከል 👉 የእርሻ ቦታ ንጽህናን መጠበቅ፣ሰብልን እያፈራረቁ መዝራት፤ለተባዩ እንደ አማራጭ ምግብነት የሚያገለግሉ ተክሎችን ቀድሞ ማስወገድ፣ 👉 በነጭ ሽንኩርት መከላከል:- 100 ግራም የተወቀጠ ነጭ ሽንኩርት፣ ግማሽ ሊትር ውሃ፣ 10ግራም ዱቄት ሳሙናና፣ 2 ማንኪያ የሚኒራል ዘይት ማዘጋጀት፡፡ በደቃቁ የተወቀጠውን ነጭ ሸንኩርት ከዘይቱ ጋር ለ24 ሰዓት መዘፍዘፍ፤ ሳሙናውን ከውሃ ጋር መበጥበጥና ከዘይቱና ሽንኩርቱ ድብልቅ ጋር መቀላቀል፡፡ በዚህ መሠረት የተዘጋጀውን ቅልቅል በጨርቅ አጥልሎ አንድ እጅ ከ20 እጅ ውሃ ጋር በጥብጦ በመርጫ መሳሪያ መርጨት፤ 👉በትንባሆ መከላከል፡- 1 ኪ/ግ የተወቀጠ የትንባሆ ቅጠልና ግንዱ ከ15 ሊትር ውሃ ጋር ለ1 ቀን መዘፍዘፍና አንድ እፍኝ ቁርጥራጭ ሳሙና መጨመር፣ ከዚያም ከአንድ ቀን በኋላ በጨርቅ ማጥለልና ወዲያውኑ መርጨት ወይም 250 ግራም የተወቀጠ ትምባሆ ቅጠል፣ 30 ግራም የዱቄት ሳሙና እና 4 ሊትር ውሃ ቀላቅሎ ለ30 ደቂቃ መቀቀል፡፡ ይህን ቅልቅል አንድ እጅ ከ4 እጅ ውሃ ጋር በጥብጦ በጨርቅ ማጥለልና በመርጫ መሳሪያ መርጨት፤ 👉በእንስሳት ሽንት መከላከል:- የእንስሳቱን ሽንት በተለያዩ እቃዎች በማጠራቀም ከ7-15 ቀን ድረስ እንዲብላላ ማድረግና የተብላላውን የከብት ሽንት ከውሃ ጋር እኩል በእኩል በሆነ መጠን በጥብጦ በመርጫ መሳሪያ መርጨት።በተለይ ለፀሐይ ቢጋለጥ የመብላላት ሂደቱን ያፋጥነዋል፡፡ በኬሚካል መከላከል 👉 ነፍሳት ተባዩ በየዓመቱ አይቀሬ በሆነባቸው አካባቢዎች 👉ማርሻል 25% ኢሲ፣ ሮገር ወይም ኢትዮላታዮን 40% ኢ.ሲ 1-2 ሊትር፣ዲያዚኖን 60% ኢሲ 0.5 ሊትር፣ ማላታዮን 50% ኢሲ 2 ሊትር፣ ካርቦሳልፋን 50% ኢሲ 1 ሊትር በሄ/ር ሂሳብ በ200 ሊትር ውሃ በርዞ መርጨት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ሌሎች የተመዘገቡ ኬሚካሎችን በአምራቹ የአጠቃቀም መመሪያ መጠቀም ይቻላል፡፡ የገብስ ዝንብ (Shoot fly)፣ ደገዛና ፌንጣ በጤፍ ስብል ላይ የተጠቀሰውን መከላከያ ዘዴ መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ መሰክን መከላከል (Chuffer grub) በባህላዊ መከላከል (Cultural practice) 👉 ማሳን በበጋ ወራት ጠለቅ አድረጎ ማረስ፣ እርሻው በመንደር (ጓሮ) አካባቢ ከሆነ በእርሻ ጊዜ ዶሮዎችን በማሰማራት ከአፈሩ በላይ የሚወጡትን ቅንቡርሶች እየለቀሙ እንዲበሏቸው ማድረግ ያስችላል፡፡ በኬሚካል መከላከል 👉ክሩዘር 350% ኤፍ.ኤስ (Flowable solution) ከ100-200 ግራም በ1ሊትር ውሃ በጥብጦ 1ኩ/ል ዘር አሽቶ መዝራት፣ 👉 የመሰክ ተባይ በየዓመቱ በሚከሰትባቸው አካባቢዎች የተባዩ ክሰተት አይቀሬ መሆኑ ከተረጋገጠ ከዘር በፊት አፈሩን (እርሻዉን) በፀረ-ተባይ ኬሚካል መርጨትና በተገቢዉ ሁኔታ በእርሻ ከአፈሩ ጋር እንዲቀላቀል (እንዲገናኝ) ማድረግ፡፡ ለዚህም ዱርስባን 48% ኢሲ 2.5 ሊትር/ሄር፣ ማላታይን 50% 50% ኢሲ 2 ሊትር/ሄር፣ ካርባሪል 85% ደብልዉ ፒ 1.5 ኪ.ግ/ሄር በ1000 ሊትር ዉሃ በጥብጦ መርጭት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ሌሎች የተመዘገቡ ኬሚካሎችን በአምራቹ የአጠቃቀም መመሪያ መጠቀም ይቻላል፡፡ ምስጥን (Termite) መከላከል በባህላዊ መከላከል (Cultural practice) 👉የሰብል ቅሪቶችን ከማሳው ላይ ቶሎ ማንሳት፣ ሰብሉ እንደታጨደ ማሳውን ወዲያውኑ ማረስ፣ ኩይሳውን ቆፍሮ ንግስቷን አውጥቶ መግደል፣ የተብላላ የከብት ሽንት በኩይሳው ዉስጥ መጨመር፣ 👉 መርዛማ ፀረ-ተባይ እጽዋትን መጠቀም • የአሳ ባቄላ (Fish bean) ቴፍሮዚያ (Tephrosia vogelli) የተባለውን እጽዋት ቅጠሉን ጨቅጭቆ በውሃ በመበጥበጥ በኩይሳው ውስጥ መልቀቅ፤ • ቅጠሉን አድርቆና ፈጭቶ /ወቅጦ/ በዛፎችና በሌሎች ምስጥ አዘውትሮ በሚታይባቸው አካባቢዎችና በሰብል ክምር ስር መነስነስ፤ • ከሰብሉ ስር ቅጠሉን መጎዝጎዝ (Mulching)፣ በኬሚካል መከላከል 👉 ኩይሳው ባለበት ቦታ በመቆፈር ለአንድ ኩይሳ ዱርስባን 48% ኢ.ሲ ወይም ዲያዚኖን 60% ኢ.ሲ ከ20-30ሚ.ሊትር ከ15-20 ሊትር ውሃ እየበረዙ መጨመር፣ 👉 ሌሎች በአገራችን የተመዘገቡ ፀረ-ነፍሳት ኬሚካሎችን በአምራቹ የአጠቃቀም መመሪያ መሰረት መጠቀም ይቻላል፡፡ ነቀዝን መከላከል 👉 በየአካባቢው ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉትን ባህላዊ መከላከያ ዘዴዎች ጥራቱን የማያበላሹትን መርጦ መጠቀም የሚቻል ሲሆን ለምሳሌ አዞ ሀረግ ቅጠሉና ግንዱን ቆራርጦ በእህል ማካማቻው አፍና በተከማቸው እህል መሀል ማስቀመጥ፣ የመረዝ ቅጠል አድርቆ በመፍጨት ዱቄቱን እህሉ ጋር አደባልቆ ማስቀመጥ፡፡ 👉 ፀረ-ተባይ ኬሚካል መጠቀም ካስፈለገ ግን አክትሊክ 2% ዱቄት በተባዩ ለተወረረ 50 ግራም ላልተወረረ ደግሞ 25 ግራም ለ1 ኩ/ል ሂሳብ በማስላት በጥንቃቄ ከእህሉ ጋር በአካፋ አደባልቆ ማከማቸት ያስፈልጋል፡፡ የስንዴ በሽታ ቁጥጥር 👉ቢጫ ዋግን (yellow rust)፣ የግንድ ዋግን (Stem rust) እና የቡናማ ዋግን (brown rust) መከላከል በባህላዊ መከላከል 👉ከላይ የተጠቀሱትን በሽታዎች በአንጻራዊነት የሚቋቋሙ ዝርያዎችን (ቀቀባ፣ ደንፌ/ደንደአ፣ ሚሊኒየም፣ ታይ፣ አባይ፣ እመጓ፣ አዴት-1) መጠቀም፣ በኬሚካል መከላከል 👉ቲልት 250 ኢ.ሲ (ኘሮፒኮናዞል) 0.5 -1 ሊትር፣ ጀባ 25 ኢ.ሲ፣ ናቹራ 250 ኢ.ደብሊው፣ ናቲቮ ኤስ.ሲ 300፣ ፕሮግረስ 250 ኢ.ሲ፣ Rex® Duo፣ በተጨማሪም ሌሎች የተመዘገቡ ኬሚካሎችን በአምራቹ የአጠቃቀም መመሪያ መጠቀም ይቻላል፡፡ ] ሴኘቶሪያ በሽታ በባህላዊ መከላከል 👉 የሰብል ፈረቃን መጠቀም፣ 👉 ሰብል ከተሰበሰበ በኋላ የሰብሉን ቅሬት ሰብስቦ ማቃጠል፤ 👉ቅሬቱ ተሰብስቦ ከተቃጠለ በኋላ 2 ጊዜ ደጋግሞ በማረስ የቀረውን ቅሬት ሰብል ወደ አፈር ውስጥ አንዲቀበር ማድረግ፤ 👉 በማሳው ላይ እና በማሳው ዙሪያ የሚበቅሉ ወፍዘራሽ (Volunteer) የስንዴ ተክሎችና የበሽታው መቆያ አስተናጋጅ ተክሎችን ማሰወገድ። በኬሚካል መከላከል 👉ቲልት 250 ኢ.ሲ(ኘ
Mostrar todo...
photo_2024-06-13_05-52-41 (2).jpg0.91 KB
448465245_872930168195565_7700397692961127841_n.jpg1.05 KB
147A8468.JPG11.85 MB
147A8503.JPG11.15 MB
147A8505.JPG12.79 MB
417447072_872929508195631_7050377832734655805_n.jpg0.75 KB
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በወቅታዊ የክረምት የግብርና ስራዎችን ገመገመ ሰኔ 07/2016 ዓ.ም የግብርና ቢሮ በምዕራብ አማራ የሚገኙ የግብርና መምሪያ ሀላፊወችና የSMS የቴክኒክ ቡድን የ2016/17 በክረምት የሠብል ልማት ስራዎች ላይ ተወያየ፡፡ በመድረኩም የተገኙት የግብርና ቢሮ አመራሮች፣የምዕራብ አማራ ግብርና መምሪያ ኃላፊዎች፣ዳይሬክቶሬቶች እና ስምሪት የተሰጣቸው የSMS የቴክኒክ ቡድን ባለሙያዎች የተሳተፉበት ነው፡፡ በመድረኩም ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አጀበ ስንሻው ሲሆኑ በንግግራቸውም የSMS የቴክኒክ ቡድን አላማው በዚህ ወቅት በችግር ውስጥም ሁነን ድጋፍና ክትትል በማድረግ ክፍተቶችን ለመሙላት ከዚያም ያለፉ ለቀጣይ ለምናከናውናቸው የሠብል ልማት ስራችን በግብዓትነት እንዲያገለግሉን የታሰበ ነው ብለዋል፡፡ አክለውም በተለየ ትኩረት የምናደርግባቸው የክረምት የሠብል ልማት ስራችን የእርሻ ድግግሞሽ፣የዘር አቅርቦትና ስርጭት፣የአረንጓዴ አሻራ፣አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ስራና የክላስተር ስራችን በልዩ ትኩረት መስራት አለብን ሲሉ አቶ አጀበ ስንሻው ተናግረዋል፡፡ የግብዓት አቅርቦታችን ስራ በተገቢው ካልሰራን የሠብል ልማት ስራችን ሙሉ አይሆንም በተለይም ምርጥ ዘር በተገቢው ጊዜ የደረሰ መሆኑን ማረጋገጥ እና በሚፈጠር የዘር ስርጭና አቅርቦት ክፍተት ተፅዕኖው ከፍ ያለ ነው፡፡ ጨምረውም የክላስተር ስራችን በተጠናከረ መልኩ መስራት አለብን ጥቅሙም ላቅ ያለ ነው፣ለክትትልና ቁጥጥር፣ለገበያ ትስስርና መሰል ጥቅሞች አሉት አሁንም የዘር ብዜት ስራችን መሰረታዊ ለውጥ በሚያመጣ መልኩ ነው መስራት ያለብን ብለዋል። የክልሉን የመልማት ፍላጎት መሠረት ያደረገ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፣ችግር አለ በማለት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አይቻልም ከነችግሩም ቢሆን መሥራት አለብን ሲሉ ተናግረዋል ፡፡ የአረንጓዴ አሻራ ስራችን በተጨባጭ 1.7 ቢሊዮን ችግኝ መትከል መቻላችን በዚህ መድረክ ማየት አለብን፣የችግኝ የማጓጓዝ ስራ እና የጉድጓድ ቁፋሮ የት ደረጃ እንዳሉ ማወቅ አለብን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የሌማት ትሩፋት ስራችን በአገር ደረጃ ልዩ ትኩረት የተሠጠው መሆኑን በመግለጽ በትኩረት መሰራት አለበት፣ጥቅሙም ቢሆን ከሠብል ልማት ቀጥሎ ተስፋ የተጣለበት መሆኑን በመረዳት የእንስሳት ሃብት ልማታችን ለኢኮኖሚው ያለውን ድርሻ መረዳት አለብን ሲሉ አቶ አጀበ ስንሻው በመክፈቻ ንግግራቸው በአንክሮ ገልፀዋል፡፡ በዚሁ መድረክ የግብርና መምሪያ ሀላፊወችና የSMS የቴክኒክ ቡድን በዞንና ወረዳ የተመለከታቸውን በተሠጣቸው ቸክ ሊስት መሰረት ዝርዝር ሠነድ ያቀረቡ ሲሆን በጥንካሬና በድክመት በመለየት አቅርበዋል፡፡ በቀረበው መድረክም የማሳ መረጣ፣የአረንጓዴ አሻራ፣የእንስሳት ሃብት ልማት፣የዘር ብዜትና የግብዓት አቅርቦትን በተመለከተ በዝርዝር ቀርቧል፡፡ በመጨረሻም አቶ አጀበ ስንሻው የስራ ስምሪት የሰጡ ሲሆን በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ሁነን የተሰሩ ሰራዎች አበረታች መሆናቸው በመገልፅ እንደ ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት ሰራችን ኮሚዲቲ ሰብሎችን ላይ፣አረንጓዴ አሻራ ስራችን፣ክላስተር ተኮር እና የዘር ብዜት ስራችን በጋራ ተረባርበን በመተግበር የማንወጣው ተራራ የለም ሲሉ አቶ አጀበ ሰንሻው ገልፀዋል ። ዘጋቢ:- አሻግረው ፈረደ ካሜራ ማን:-ጌታቸው ታፈረ ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የግብርና ቤተሰብ ይሁኑ👇 ድረገጽ http://www.amhboard.gov.et/ ቴሌግራም https://t.me/AmharaBureauofAgriculter ፊስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100064357704820 ዩቱዩብ https://www.youtube.com/@amharaagriculturebureau6055
Mostrar todo...
Amhara Bureau of Agriculture

BOA

********* የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ከዞኖች የሜኔጅመንት አባላት ጋር በወቅታዊ ሥራዎች ላይ ግምገማዊ ወይይት በማድረግ ላይ ነው የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ከምዕራብ አማራ የዞን ግብርና መምሪያዎች ጋር በመሆን የ2016/17 የክልሉ ወቅታዊ የግብርና ልማት ሥራዎች ያለበትን ሁኔታ በጋራ እየተገመገመ ሲሆን በግምገማዊ ወይይት መድረኩ ላይ አቶ አጀበ ሰጋሻው የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ፕሮግራሙን አስጀምረውታል። ተሳታፊዎችም የሁሉም የምዕራብ አማራ ቀጠና ዞን ግብርና መምሪያ የማኔጅመንት አባላት፣ የቢሮው ማኔጅመንት ፣ በመስክ ሥራ ስምረት ወስደው የነበሩ SMS - subject Matter Specialist አባላት እና ሌሎች ባለሙያዎች የተገኙበት ወሳኝ መድረክ ሲሆን የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ፣ የባህር ዳር ከተማ አሰተዳደር ግብርና መምሪያና የSMS ቡድን አባላት መልካም የግብርና ልማት ተሞክሮዎች፣ ስኬቶችንና ያገጠሙ ችግሮችን እያቀረቡ ናቸው። *በግምገማ መድረኩ ትኩረት የተደረገባቸው ወቅታዊ የግብርና ልማት ሥዎችም ➔የግብዓት አቅርቦትና ስርጭት ➔የምርጥ ዘር አቅርቦትና ስርጭት ➔ የ2016/17 የመኽር ምርት ዘመን ሰብል ልማት ሥራ ➔የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ➔የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ደን ልማት ሥራ በተመለከተ ለማዘጋጀት የታቀደ ችግኝ፣ቦታ ልየታና ሌሎች ቅድመ ዝግጅቶች ➔ መደበኛ ኮምፖስት ➔ ቨርሚል ኮፖስት ➔ባዮ ሳላሪ ዝግጅትና በሌሎች ነጥቦች ላይ ወይይት እየተደረገ ነው፡ ፡ ግምገማዊ ውይይቱ አሁንም እንደቀጠለ ነው። ዝርዝር ዘገባው ይቀጥላል... *አዘጋጅ- አምሳሉ ጎባው *ፎቶ - ጌታቸው ታፈረ ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የግብርና ቤተሰብ ይሁኑ👇 ድረገጽ http://www.amhboard.gov.et/ ቴሌግራም https://t.me/AmharaBureauofAgriculter ፊስቡክ https://www.facebook.com/profi *****
Mostrar todo...
Amhara Bureau of Agriculture

BOA

photo_2024-06-13_05-52-41.jpg0.88 KB
photo_2024-06-13_05-52-41 (2).jpg1.22 KB
photo_2024-06-13_05-52-41 (3).jpg0.68 KB
photo_2024-06-13_05-52-42 (2).jpg1.34 KB
photo_2024-06-13_05-52-42.jpg1.42 KB